30/01/2022
ልብ ይነካል 👉🏾እናቱ የተገደለበት ልጅ የገዳዩን እንባ አበሰው ❤️....*****.....
👉🏾በዕለተ ቅዳሜ ጥቅምት20 የሰፈሩ አድባር በሁሉ የሚወደዱ እናታችን የሺ ውድነህ ኮልፌ07 ከሚገኘው ቤታቸው ሁሌም እንደሚያደርጉት አማኑኤል ቤተክርስቲያን ለመሳለምና ለቅሶ ቀብር ለመሄድ በጠዋት ይወጣሉ!
👉🏾እማማ ኖክ ኮልፌ18 ጋር ደርሰው የእግረኛ መንገዱን እየተሻገሩ አንድ ከባድ መኪና ድንገት ይገጫቸዋል😭
👉🏾ያለአባት 8 ልጆቻቸወን ታግለው ያሳደጉት እናት የሺ ወንዱ ልጃቸው ቴዲ ሆስፒታል እየሮጠ ቢደርስም ህይወታቸው አልተረፈላቸውም😭 ሞቱባቸው😭
👉🏾ለቅሶ ደርሼ በዛው ፀሎት አድርሼ እመለሳለው ያሉት ደጓ እናት እግዚአብሔር ቀናቸው ነው ብሎ ጠርቶ ወሰዳቸው!እሁድ ጥቅምት 21 ልጆቻቸው አምርረው እያለቀሱ ከወዳጅ ዘመድ ጋር ቀበሯቸው😭
👉🏾ይህ ደግ ቤተሰብ የሚወዷት እናታቸው ሀዘን ገና ከልባቸው ሳይወጣ ገጭቶ ከገደላቸው ሹፌር ጋር ለእርቅ ተቀምጠው ይቅር ተባብለው ሁሉም ነገር በሽምግልና አልቋል🙏 ቤታቸው የነበረው ድባብ ሁሉንም አስለቅሷል😭::
👉🏾ምንም ወገንና ዘመድ የሌለው የገጫቸው ሹፌር ሽማግሌ አጥቶ ሲንከራተት እናት የሞተባቸው ልበወርቆች አይዞህ ብለው ደግፈውት በጎደለው ሽማግሌእንዲሆኑ አባት አመቻችተውለት በእርቁ ሰዓት እንባውን መቆጣጠር አቅቶት ሙሉ ሰአቱን ስቅስቅ ብሎ ሲያለቅስ ውሏል😭::
👉🏾ካሳ ተብሎ የተሰጠውንም ሙሉ 80, 000ብር ላዘኑት እንባ ማበሻ ይሁንልን ለአረጋውያኑ አስቤዛ ተገዝቶ ይሰጥልንብለው ልጆቻቸው ለባይሽኮልፌ በጎአድራጎት አስረክበዋል🙏💖 እንዲህ አይነት ደግነት እንዴትስ
ይገኛል???
👉🏾ከሁሉ የሚገርመው መጨረሻ ላይ ሊለያዩ ሲሉ ገጭቶ የገደላቸው ሹፌር ራሱን መቋቋም አልቻለም! ይቅር ያሉት የእናት የሺ ልጆች ደግነት የበለጠ እንድፀፀት አደረገኝ ብሎ ስቅስቅ ብሎ እንደገና አለቀሰ😭 "በቃ እግዚአብሔር የጠራት በዚህ ነው አታልቅስ" እያሉ አባባዮቹ ደግሞ ከ3ወራት በፊት እናታቸውን ያጡት ልጆቿ እነቴዲ ነበሩ🙏::
…..*****…..
እናታችን ፅጌማርያም ነፍስ ይማር
ልበወርቆች ቀሪ ዘመናቹ በደስታ ይለቅ🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም::"
…..*****…..
መረጃ ምንጭ:
…..*****…..