19/10/2023
ነጋዴውን ከገበያተኛው የሚያገናኝ ኢትዮጋይድ የተሰኘ የሞባይል መተግበርያ ይፋ ተደረገ።
በፍለጋ አይድከሙ በማለት የተለያዩ ድርጅቶችን(መደብሮችን)፤ ሆቴሎችን እና የተለያየ የሙያ ዘርፍ ነጋዴዎችን በቀላሉ ለማግኘት የሚችል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ።
የተለያዩ የንግድ ድርጅት ባለቤቶች ኢትዮጋይድ የተሰኘ መተግበርያውን በመጠቀም (Yellow Page) እንዲመዘገብ በማድረግ ለተጠቃሚዎች አድራሻቸውን ፣ የስልክ ቁጥራቸውን፣ የቅርንጫፋቸውን ብዛት እና መሰል መረጃዎችን በቀላሉ እንዲገኙ የሚያደርግ አፕሊኬሽን መሆኑ ተገልጿል ።
ኢትዮጋይድ(Ethioguide) የተሰኘው መተግበሪያ በቴክኖሎጂ በመታገዝ እጅግ ዘመናዊ እና ጊዜውን የዋጀ አገልግሎት እንዲሆን ከፍ ተደርጎ የተሠራ የሞባይል መተግበሪያ መሆኑ የአይቲ ባለሙያ የሆኑት አቶ ኃይለየሱስ ዘሪሁን ገልጸዋል መተግበርያው በአሜሪካን ኮሎራዶ ከተማ እየሰራ ያለ መሆኑን ጠቅሰው ወደ ኢትዮጵያም በማምጣት የንግድ ድርጅቶች ከደንበኞቻቸው ጋር በቀላሉ እንዲተዋወቁ ብሎም ተጠቃሚዎች በአቅራቢያቸው ያሉትን ጠቃሚ መደብሮች በስልካቸው ላይ በማሳየት እና ከመደብሮቹ ጋር እንዲገናኙ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ ነው ሲሉ አስረድተዋል።
መተግበርያውንም በመጠቀም የትኛውም ግለሰብ በቀላሉ የሚፈልገውን የንግድ ድርጅት ስም ወይንም ስልክ በማስገባት መረጃ ማግኘት እንዲችል የሚያደርግ መድረክ(Platform) መሆኑን የገለጹት የድርጅቱ የሚፈለገው የንግድ ድርጅት(መደብር) የት እንደሚገኝ ፤ ምን አገልግሎት እንደሚሰጥ ፣ ደብሩን ማነጋገር ቢፈለግ በቀላሉ መደወል፤ ቦታውን በመጠቆም ወይም መልዕክት መላክ እንዲቻል ተደርጎ የተሠራ መተግበሪያ ነው።
መተግበሪያው ለተጠቃሚዎች ቀላል ፣ ግልጽ እና ተደርጎ የተሠራ ስለሆነ ተጠቃሚዎች ብዙ ሳይደክሙ በቀላሉ የሚፈልጉትን የንግድ መደብሮችን ፣አሁነኛ እና የተጣሩ መረጃዎች ለተጠቃሚዎች ቀላል በሆነ መልኩ ይዞ መቅረቡንም መስራቾቹ አስታውቀዋል።