DireTube

DireTube DireTube.com is the #1 Ethiopian Video Sharing Site. DireTube is an Ethiopian media and entertainment website founded on October 26, 2008.

ኢንተር ሌግዢሪ ሆቴል ተቀጣበአዲስአበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ካሳንቺስ አካባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ወደ ኮሪደር ልማት አስፓልት የለቀቀው ኢንተር ሌግዢሪ የተባ...
24/01/2025

ኢንተር ሌግዢሪ ሆቴል ተቀጣ

በአዲስአበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ካሳንቺስ አካባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ወደ ኮሪደር ልማት አስፓልት የለቀቀው ኢንተር ሌግዢሪ የተባለ ኢንተርናሽናል ሆቴል 300 ሺህ ብር መቀጣቱን እና ቦታውን እንዲያጸዳ መደረጉን የአዲስ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ በከተማዋ ውስጥ የተለያዩ ስራ ላይ የተሠማሩ የንግድ ድርጅቶች እና ግንባታ ገንቢዎች በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅ እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

በተጨማሪም በከተማዋ ደንብ በሚተላለፉ የግልና የመንግስት ድርጅቶች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡(AMN)

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ባሉ ትምህርት ቤቶች ዙሪያ አዋኪ ናቸው የተባሉ፤ እንደ መጠጥ ቤቶች፣ ቁማር ቤቶች እና ሌሎች ከ1,900 በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተ...
24/01/2025

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ባሉ ትምህርት ቤቶች ዙሪያ አዋኪ ናቸው የተባሉ፤ እንደ መጠጥ ቤቶች፣ ቁማር ቤቶች እና ሌሎች ከ1,900 በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወስዷል ተባለ፡፡

እነዚህ ከ1,900 በላዩ የንግድ ተቋማት በ ትምህርት ቤቶች ዙሪያ በ500 ሜትር ራዲየስ ላይ የሚገኙ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ከትምህርት ቤቶቹ ከ200 - 500 ሜትር ራዲየስ ላይ ያሉ 936 የንግድ ተቋማት መታሸጋቸውን ሰምተናል፡፡

ይህንን የሰማነው ከከተማዋ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ነው።

በትምህርት ቤቶች ዙሪያ የነበሩ እና አገልግሎት መስጠት ያቆሙት እነዚህ የንግድ ተቋማት ተለዋጭ ቦታ ተሰጥቷቸው እንዲሰሩ እየተደረገ ነው የተባለ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ በዚያው ቦታ ላይ ዘርፍ ቀይረው እንዲሰሩ መደረጉ ተነግሯል።

በተጨማሪም ሸቀጦች ላይ ያለ አግባብ ዋጋ በጨመሩ፣ በህገወጥ መንገድ ምርት ያከማቹ ነጋዴዎችም ተገኝተው ቅጣት ተጥሎባቸዋል ያለው ቢሮው በዚህም በበጀት ዓመቱ 2,000 የሚደርሱትን ቀጥቻለሁ ብሏል።

(ሸገር ሬድዮ)

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሩብ ዓመት ሪፖርት ምን ይላል?***"....መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ በደቡብ ጎንደር ዞን፣ ሊቦ ከምከም ወረዳ፣ አግድ ቀ...
24/01/2025

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሩብ ዓመት ሪፖርት ምን ይላል?
***
"....መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ በደቡብ ጎንደር ዞን፣ ሊቦ ከምከም ወረዳ፣ አግድ ቀበሌ፣ ውሻ ጥርስ በተባለ ጎጥ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በአካባቢው በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) መካከል የነበረውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ፤ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አካባቢውን ከተቆጣጠሩ በኋላ ቤት ለቤት በመግባት “የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ” እንዲሁም “ፋኖን ትደግፋላችሁ” በሚል በ8 ሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል። ከእነዚህም መካከል 1 የዘጠኝ ወር ነፍሰ ጡር እናትን ጨምሮ 3 ሴቶች እና 1 ሕፃን ይገኙበታል። በተጨማሪም 2 ሲቪል ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት እንዳደረሱ እና ሌሎች 6 ሲቪል ሰዎችን ይዘው እንደወሰዱና ይህ ሪፖርት እስከ ተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሰዎቹ የት እንዳሉ እንደማይታወቅ የመረጃ ምንጮች አስረድተዋል።..."
(ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይከተሉ)

***
https://ehrc.org/%E1%89%A0%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%89%A0%E1%8C%8D%E1%8C%AD%E1%89%B5-%E1%8B%90%E1%8B%8D%E1%8B%B5-%E1%8B%8D%E1%88%B5%E1%8C%A5-%E1%8B%AB%E1%88%89-%E1%8A%A0%E1%8A%AB%E1%89%A3-2/?fbclid=IwY2xjawIAYZVleHRuA2FlbQIxMQABHZECO1PttdXgpcsRGSlTJxBLb3NkR7tnarH1gxEgEbtDthsioxsy-d2O7A_aem_aihpmcJXjX5Oj8Fg6F4fjA

ከኤጀንሲው ሰራተኞች ጋር በጋራ በሚሰሩ ህገወጥ ደላሎች ምክንያት አገልግሎት ፈላጊው  ህዝብ አሁንም እየተንገላታ ነው ተባለ፡፡በርካታ የህዝብ ቅሬታ ከሚቀርብባቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች አን...
24/01/2025

ከኤጀንሲው ሰራተኞች ጋር በጋራ በሚሰሩ ህገወጥ ደላሎች ምክንያት አገልግሎት ፈላጊው ህዝብ አሁንም እየተንገላታ ነው ተባለ፡፡

በርካታ የህዝብ ቅሬታ ከሚቀርብባቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች አንዱ በሆነው፤ በኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ኤጀንሲ በህገወጥ ደላላ ብር ተበላን የሚሉ ዜጎች አቤቱታን እያቀረቡ ይገኛል ፡፡

የአስቸኳይ ፓስፖርት ላልተወሠነ ጊዜ አገልግሎት መስጠት አቁሞ የነበረ መሆኑን ተከትሎ ህገወጥ ደላሎች ከውስጥ ሠው እንዳላቸው በማሳመን እና ተጨማሪ ክፍያን ጭምር በማስከፈል የአገልግሎት ፈላጊውን ህብረተሠብ ብር በመብላት ላይ እንደሚገኙ ዜጎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

እነዚህ ደላሎች ህገወጥ ስራቸውን በመስሪያ ቤቱ አካባቢ ሆነው መስራታቸው ህዝብን የበለጠ እንዲታለል አድርጎታል ይላሉ ቅሬታ አቅራቢዎች፡፡

የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ማስተዋል ገዳ፤ ህብረተሠቡ በዋነኝነት እየታለለ ያለው ፖስፖርቱን ለማግኘት ካለው ፍላጎት አንፃር የሚባለውን በማመኑ ነው ይላሉ፡፡

ህገወጥ ስራ ከሚሰሩ ደላሎች ጋር በጋራ የሚሠሩ ሰራተኞች እንዳሉ ደርሰንበት ለህግ ተላልፈው እንዲሰጡ አድርገናልም ብለዋል።

እነዚህ ህገወጥ ደላሎች በአብዛኛው ኢንተርኔት ቤት ያላቸው ናቸው የሚሉት ዳይሬክተሯ፤ እነሱን የማገድ ስልጣኑ የለንም ብለዋል።

ከመስሪያ ቤታችን ጋር የሚሠሩትን እና ህገወጥ ሰራተኞችን በህብረተሰብ ጥቆማ እንዲሁም በምርመራ በህግ አግባብ እንዲቀጡ መስሪያ ቤቱ ሀላፊነቱን እየተወጣ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

(ኢትዮ ኤፍ ኤም)

ጉምሩክ ኮሚሽን የ "ኤሌክትሮኒክ ካርጎ ትራኪንግ" ሥርዓትን ሊተገብር ነው የኢትዮጵያ ኤሌክትሮኒክ ካርጎ ትራኪንግ ስርዓት እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን ስራ ላይ ለማዋል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መ...
24/01/2025

ጉምሩክ ኮሚሽን የ "ኤሌክትሮኒክ ካርጎ ትራኪንግ" ሥርዓትን ሊተገብር ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሮኒክ ካርጎ ትራኪንግ ስርዓት እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን ስራ ላይ ለማዋል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸው ተገለጸ

የጉምሩክ ኮሚሽን የሚሰጣቸውን አገልግሎት ለማሻሻል እና የህግ ተገዥነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የቴክሎጂ ውጤቶች ተግባራዊ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡

ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ ኤሌክትሮኒክ ካርጎ ትራኪንግ ስርዓት፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን መሰረት ያደረገ የድንበር ቁጥጥር እንዲሁም ሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች ልማት ያለበት ደረጃ እና ወደ ሙሉ ትግበራ ስለሚገባበት ሁኔታ ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፕሮጀክቶቹ ስራ አስኪያጅ ሽብሩ ተመስገን (ዶ/ር) እና ሌሎች የኮሚሽኑ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ የኮሚሽኑን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን እና የህግ ተገዥነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስትትዩት እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት ኤሌክትሮኒክ ካርጎ ትራኪንግ ስርዓት እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሙሉ ትግበራ ለማሸጋገር እየተሰራ መሆኑንም ኮሚሽነሩ አስረድተዋል፡፡

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢንስቲትዩቱ የኮሚሽኑን አገልግሎት የሚያሳልጡ ዘርፈ ብዙ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እያለማ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሮኒክ ካርጎ ትራኪንግ ስርዓት እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሙሉ ትግበራ ለማሸጋገርም ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በውይይቱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሮኒክ ካርጎ ትራኪንግ ስርዓት እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች ያሉበት ደረጃ በዝርዝር የተገመገመ ሲሆን ቀሪ ስራዎች በአጭር ጊዜ ተጠናቀው ወደ ሙሉ ትግበራ እንዲገቡ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

(ጉምሩክ ኮሚሽን)

 #ይህ ድንግልና ለእርሷ ብቻ የተሰጠ ነው  “እግዚአብሔር አንድ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወድዶአልና። ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታች...
24/01/2025

#ይህ ድንግልና ለእርሷ ብቻ የተሰጠ ነው

“እግዚአብሔር አንድ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወድዶአልና። ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም፤” ይላል። ዮሐ፡3፥17፣ 1ኛ፡ዮሐ፡4፥10። ይህን መውደድ ይህን ፍቅር የገለጸው ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና በመወለድ ነው። የእመቤታችን ድንግልና በሦስት ወገን በሥጋዋ፥ በነፍሷና በልቡናዋ ነው። ይህ ድንግልና፡- የዘለዓለም ድንግልና ነው። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ “ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፣ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፣ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች፤” ብሎአል። ኢሳ፡7፥14።

ነቢዩ ቅዱስ ሕዝቅኤልም “ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በስተውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ፤ ተዘግቶም ነበር። እግዚአብሔርም ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፣ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል፤” ብሎአል። ሕዝ፡44፥1። የተዘጋ የመቅደስ በር የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። “ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፤” የሚለው ኃይለ ቃል በድንግልና ጸንታ እስከ ዘለዓለሙ እንደምትኖር ይነግረናል። “ሰው አይገባበትም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል” ሲልም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ፀንሳ፥ በድንግልና የወለደችው ኢየሱስ ክርስቶስ የባህርይ አምላክ በመሆኑ፥ ከርሷ በተዋህዶ ሰው የሆነ የባህርይ አምላክ እንጂ ዕሩቅ ብእሲ አይወለድምና በድንግልና እንደጸናች ትኖራለች።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመጽነሷ በፊት፣ በጸነሰችም ጊዜ፣ ከጸነሰችም በኋላ ድንግልናዋ የጸና ነው፤ ከመውለዷ በፊት፣ በወለደችም ጊዜ፣ ከወለደችም በኋላ ኅትምት በድንግልና ናት። የውዳሴ ማርያም አንድምታ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ያላትን አብራርቶ ይነግረናል፡፡ እመቤታችን መልአኩ ሲያበስራት “ወንድ ሳላውቅ ይህ ነገር እንደምን ይሆንልኛል?” የሚል ጥያቄ አንስታ ነበር፡፡ ይህን ያለችው ክብር ይግባትና የወንድ ሀሳብ በአእምሮዋ ፈጽሞ ተመላልሶ ስለማያውቅ ነው፡፡ ሌሎች ሴቶች ስለወንድ ከመናገርና በሕጋዊ ሩካቤ ከመገናኘት ቢታቀቡ ከማሰብ ግን አይነጹም፡፡ እምቤታችን ግን ከመናገር ከማድረግ ከማሰብ ንጽህት ናት፡፡

በሥላሴ አኗኗር ወልድ ለአብ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ልጅ እንደሆነ ሁሉ ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያምም ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ልጇ ነው። በጳጳስ ወንበር ቄስ፣ በንጉሥ ዙፋን ራስ ደፍሮ እንደማይቀመጥ ሁሉ በአምላክ ዙፋን በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን ማን ያድራል? ለዚህም ነው እግዚአብሔር ለነቢዩ ለሕዝቅኤል አስቀድሞ የነገረው። ጠቢቡ ሰሎሞንም “እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፣ የተዘጋ ምንጭ፣ የታተመ ፈሳሽ ናት፤” ብሎአል። መኃ 4፥12። እንደተቆለፈች አምላክ ብቻ አድሮባት የወጣባት ገነት፣ እንደተዘጋች የዘለዓለምን ሕይወት ክርስቶስን ያመነጨች፣ እንደታተመች የሕይወትን ውኃ ክርስቶስን በአራቱም ማዕዝን አፍስሳ የተጠሙ ነፍሳትን ያረካች፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብቻ ናት።

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

2ኛው ዙር አለም አቀፍ የቁርአንና አዛን ውድድር ሽልማት የፊታችን ጥር 25 ይካሄዳል2ኛው ዙር አለም አቀፍ የቁርአንና አዛን ውድድር ሽልማት 2025 የፊታችን ጥር 25 በአዲስ አበባ ስታዲየም...
24/01/2025

2ኛው ዙር አለም አቀፍ የቁርአንና አዛን ውድድር ሽልማት የፊታችን ጥር 25 ይካሄዳል

2ኛው ዙር አለም አቀፍ የቁርአንና አዛን ውድድር ሽልማት 2025 የፊታችን ጥር 25 በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ አለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር ሽልማት በ 2014 ዓ/ም 56 ሀገራት በማሳተፍ በታላቅ ድምቀትና ዝግጅት መካሄዱ ይታወቃል::

ዘንድሮም ይሄንን አለም አቀፍ ውድድር ለሁለተኛ ጊዜ ጥር 25/2017 ዓ/ም በዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር አዘጋጅነትና በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የበላይ ጠባቂነት በአዲስ አበባ እስቴድየም እንደሚካሄድ ተገልጿል

በኢትዮጵያ ለ2ተኛ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ አለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር ሽልማት አሜሪካ ፣ ቱርክ ፣ ህንድ ፣ ሩሲያ ፣ ኳታር ፣ ሳውድ አረቢያን ጨምሮ ከ60 የአለም ሀገራት የተወጣጡ ተወዳዳሪዎችና የልዑካን ቡድን ተሳታፊዎች እንዲሁም ኢንቨስተሮችና ታዋቂ ግለሰቦች ይገኛሉ ተብሏል

ከ11 ሀገራት የተወጣጡ ዳኞችና ውድድሩን እንደሚዳኙ የተገለፀ ሲሆን 100 የሚሆኑ ከውጭ የመጡ እንግዶችም ይገኛሉ

በመግለጫው እንደተገለጸው ውድድሩ በሁለት መርሃ ግብር የተከፈለ ሲሆን ጥር 21/2017 የመክፈቻ ፕሮግራምና አለም አቀፍ የማጣሪያ ውድድር በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ሁለተኛውና የፍፃሜው ውድድር ደግሞ በአዲስ አበባ ስታዲየም ጥር 25/2017 ከማለዳዉ 12፡30 ጀምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የሀገራት አምባሳደሮች፤ የሐይማኖት አባቶች ህዝበ ሙስሊሙና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀትና ስነ-ስርዓት ይካሄዳል::

ይህ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር ሽልማት ፕሮግራም እንደ ሐገር ባህልን፣ ቱሪዝምን እና ኢንቨስትመንትን ከመሳብና ከማስተዋወቅ አንፃር ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ተብሏል
(በድሬ ትዩብ ሪፖርተር)

በጥምቀት በዓል በታቦተ ሕጉ ላይ የተሳለቁ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ አላስፈላጊ መልዕክት ያሠራጩ ግለሰቦች እና ቡድኖች በሕግ እንደሚጠየቁ ተገለጸየኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰሞኑን ግለሰቦች...
24/01/2025

በጥምቀት በዓል በታቦተ ሕጉ ላይ የተሳለቁ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ አላስፈላጊ መልዕክት ያሠራጩ ግለሰቦች እና ቡድኖች በሕግ እንደሚጠየቁ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰሞኑን ግለሰቦችና ቡድኖች ሃይማኖታዊ ቅራኔ እና ጥላቻ ሊፈጥሩ የሚችሉ በቪዲዮ የለቀቁትን አሉታዊ መልእክቶችን እና ተግባራትን በፍጥነት ለማረም በጽሕፈት ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ እና ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም ከእምነቱ ሥርዓት ባፈነገጠ መንገድ አንዳንድ ኃላፊነት የማይሰማቸው ግለሰቦችና ቡድኖች የሌላውን እምነትና ሥርዓት በማንቋሸሽ፣ ክብረ ነክ ተግባራትን በመፈጸም፤ በተለይም በጥምቀት በዓል ታቦተ ሕጉ ላይ በመሳለቅ፤ የኢስላማዊ አለባበስ መገለጫ የሆነውን ጀለቢያ በመልበስ ሙስሊሞች በመምሰል የትንኮሳ ስብከቶችና ዝማሬዎች በማቅረብ፣ የትንኮሳ አለባበሶች ጭምር በመጠቀም በማኅበራዊ ድረገጽ የለቀቁት አጫጭር ቪዲዮችዎች የእምነቱ ተከታዮችን ማስቆጣቱን አብራርቷል፡፡

"ይህ ዓይነቱ ተግባር በሀገራችን ለዘመናት የዘለቀውን የመከባበር፣ በሰላም አብሮ የመኖር እሴትን የሚሸረሽር ድርጊት" መሆኑን የገለጸው መግለጫው፤ በሁሉም ሃይማኖቶች የሚወገዝ የድፍረት ድርጊት በመሆኑ ይህን የፈጸሙ ግለሰቦችና ቡድኖች በሕግ ሊጠየቁ እንደሚገባ፣ መጠየቅም መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ማንኛውም ግለሰብም ይሁን ቡድን ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሌሎችን መብትና ጥቅም በሚጻረር አግባብነት የሌለውና ግጭት ቀስቃሽ ተግባራት የሚፈጽም ማንኛውም ሕገ ወጥ ተግባር በዝምታና ሊታለፍ እንደማይገባውም ገልጿል፡፡

በመጨረሻም ማኅበራዊ ድረገጾችን እና ሚዲያዎችን በመጠቀም የጥላቻ ንግግሮች፣ ትንኮሳዎችና ክብረ ነክ ድርጊቶች የሚፈጽሙ ግለሰቦችና ቡድኖች ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት፤ ከመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፣ ከፍትሕ የጸጥታ አካላት ጋር በቅርበት እየሠሩ እንደሆነ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቭዥን ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አያይዞም ይህ ዓይነቱን ተግባር ለመከላከል የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ሥርዐት ላይ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት እና ታቦት ላይ እየቀለዱ ቪዲዮ በመቀረፅ ቲክቶክ በተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ ላይ ማጋራታቸውን ተከትሎ፤ በበርካታ የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ቁጣና ተቃውሞ ፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በድርጊቱ የተሳተፉ እና በማህበራዊ ገጾች ላይ የለጠፉት ተማሪዎች በቁጥጥር ሥር ከመዋላቸውም በተጨማሪ፤ የአምቦ ዩኒቨርሲቲም የዲሲፕሊን ቅጣት ለማስተላለፍ አቅጣጫ ማስቀመጡን አስታውቋል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ድሬዳዋ ከተማ ገቡሚኒስተሯ ወደ ድሬዳዋ የገቡት የሳቢያን ሆስፒታልን ለመጎብኘት እንዲሁም የቀዳዴ ፋሚሊ ሆስፒታልን ለመመረቅ ነው።ሚኒስተሯ ...
24/01/2025

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ድሬዳዋ ከተማ ገቡ

ሚኒስተሯ ወደ ድሬዳዋ የገቡት የሳቢያን ሆስፒታልን ለመጎብኘት እንዲሁም የቀዳዴ ፋሚሊ ሆስፒታልን ለመመረቅ ነው።

ሚኒስተሯ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህና በመስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
(ድሬደዋ ኮምኒኬሽን)

በግማሽ ዓመት ከ2 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ መገዛቱ ተገለጸ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሥድስት ወራት በሀገር ውስጥ ለሽያጭ የሚውል 2 ሚሊየን 41 ሺህ 135 ነጥብ 332 ሜትሪ...
24/01/2025

በግማሽ ዓመት ከ2 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ መገዛቱ ተገለጸ

በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሥድስት ወራት በሀገር ውስጥ ለሽያጭ የሚውል 2 ሚሊየን 41 ሺህ 135 ነጥብ 332 ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ግዥ መፈጸሙ ተገለጸ፡፡

ለመግዛት ታቅዶ የነበረው 2 ሚሊየን 216 ሺህ 189 ሜትሪክ ቶን መሆኑን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር በቀለች ኩማ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በዚሁ መሠረት ቤንዚን 313 ሺህ 3፣ ነጭ ናፍጣ 1 ሚሊየን 283 ሺህ 801፣ የአውሮፕላን ነዳጂ 403 ሺህ 17፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 13 ሺህ 390 እና ከባድ ጥቁር ናፍጣ 26 ሺህ 925 ሜትሪክ ቶን ግዥ መፈጸሙን አብራርተዋል፡፡

የዕቅዱን 92 በመቶ መፈጸም መቻሉን ጠቁመው÷ አፈጻጸሙ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ1 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ጠቅሰዋል፡፡

በሌላ በኩል በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ 2 ሚሊየን 112 ሺህ 602 ሜትሪክ ቶን የተጣራ ነዳጅ ምርቶች ለመሸጥ ታቅዶ 2 ሚሊየን 48 ሺህ 687 ሜትሪክ ቶን ነዳጅ መሸጡን እና አፈጻጸሙም 97 በመቶ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የነዳጂ ሽያጭ ክንውን አፈጻጸም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ7 በመቶ ጭማሪ አለው ብለዋል፡፡

(ኤፍ ኤም ሲ)

የሰው ስጋን የከተፈው ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበትፀሃዬ ቦጋለ በየነ የተባለ ተከሳሽ ከነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 5፡00 እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 1...
24/01/2025

የሰው ስጋን የከተፈው ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት

ፀሃዬ ቦጋለ በየነ የተባለ ተከሳሽ ከነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 5፡00 እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 ድረስ ባለው ጊዜ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አርሴማ ፀበል አከባቢ ባለቤቱ የነበረችውን ሟች ወንበር ላይ ተቀምጣ እያለ ሳታየው ከኋላዋ በመምጣት በሊጥ ማዳመጫ ዱላ ማጅራትዋን በመምታት እራሷን እንድትስት ካደረገ በኋላ እዛው ትቷት ከቤት ወጥቶ በመሄድና ከተወሰነ ሰዓታት በኋላ ተመልሶ በመምጣት ሟች እራሷን ስታ ከወደቀችበት መሬት ለመሬት በመጎተት እቤት ውስጥ ወደሚገኘው መታጠቢያ ቤት በማስገባት አንድ እግሯን ከዳሌዋ ጀምሮ በመቁረጥና ሙሉ የእግሯን ስጋ አጥንቷ ባዶ እስኪሆን ድረስ መልምሎ በማውጣት ስጋዋን አድቅቆ በመክተፍና በመቆራረጥ ሽንት ቤት ውስጥ በመጨመር የቆረጠውን እግሯ ለሁለት በመስበርና በፌስታል በመቋጠር ፀጉሯን በመቀስ በመቁረጥ ቀሪ አስከሬንዋ ላይ ጨርቅና የተለያየ መዘፍዘፊያ በመጫን እዛው መታጠቢያ ቤት ውስጥ በማስቀመጥ እስከ 30/12/2014 ዓ.ም ድረስ ምንም እንዳልተፈጠረ እቤት ውስጥ እያደረ ከቆየ በኋላ ከ1/13/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 16/1/2015 ዓ.ም ድረስ ቤቱን ዘግቶ በመሰወሩ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ ሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ539/1/ሀ/ መሰረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሒደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም የመከላከያ ማስረጃ አቅርቦ የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የወሰነ የነበረ ቢሆንም ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ይግባኝ መሰረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የወሰነውን የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ውሳኔ በመሻር ተከሳሹ በሞት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

(የፍትህ ሚኒስቴር)

የልብ ህክምናን ለማሻሻል የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈረመጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኽርት አታክ ኢትዮጵያ የልብ ህክምናን ለማሻሻል እና በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸ...
24/01/2025

የልብ ህክምናን ለማሻሻል የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈረመ

ጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኽርት አታክ ኢትዮጵያ የልብ ህክምናን ለማሻሻል እና በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸው የሦስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ ፈረሙ፡፡

ለሦስተኛ ዙር ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ የመጣውን የሃኪሞች ቡድን በጽህፈት ቤታቸው የተቀበሉት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ÷ ቡድኑ እየሰጠ ስለሚገኘው በጎ ተግባር በተገልጋዩ ህብረተሰብ አመስግነዋል፡፡

የስምምነቱ መፈረም በኢትዮጵያ የሚሰጠውን የልብ ህክምና ለማሳደግ እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡

የኽርት አታክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ኦብስኔት መርዕድ ÷ኽርት አታክ ኢትዮጵያ ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከአየር መንገዱ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት መፈረሙ የሃኪሞች ቡድኑ የሚሰጣቸውን የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ለማስፋትና ኢትዮጵያውያን ሃኪሞችን ለማሰልጠን እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በትብብር መስራቱን እንደሚቀጥል የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ ለማ ናቸው፡፡

ኽርት አታክ ኢትዮጵያ ለሚሰጠው አገልግሎት አየር መንገዱ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡

የስምምነቱ መፈረም በኢትዮጵያ እየተሰጠ የሚገኘውን የልብ ህክምና አገልግሎት ለማሻሻል እንደሚረዳ በፊርማ መርሐ-ግቡሩ ተገልጿል፡፡

(ኤፍ ኤም ሲ)

የትራምፕ ውሳኔ በጊዜያዊነት ታገደዶናልድ ትራምፕ በመወለድ የሚገኝ ዜግነትን እንዲከለከል ያሳለፉትን ውሳኔ ዳኞች በጊዜያዊነት እንዲታገድ አድርገውታል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በነ...
24/01/2025

የትራምፕ ውሳኔ በጊዜያዊነት ታገደ

ዶናልድ ትራምፕ በመወለድ የሚገኝ ዜግነትን እንዲከለከል ያሳለፉትን ውሳኔ ዳኞች በጊዜያዊነት እንዲታገድ አድርገውታል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በነጩ ቤተመንግሥት በገቡ በሰአታት ውስጥ ካሳለፏቸው ውሳኔዎች አንዱ ሰነድ አልባ በሆኑ ስደተኞች የሚወልዷቸው ልጆች የሚያገኙትን በመወለድ የሚገኝ ዜግነት የሚያስቀር ትዕዛዝ ነበር።

ዋሺንግተንን ጨምሮ ሌሎች ሶስት ግዛቶች ለፍርድ ቤት ባቀረቡት ጥያቄ ውሳኔው በጊዜያዊነት እገዳ እንዲጣልበት ተደርጓል ።

ዳኞችም ውሳኔው ህገመንግስታዊ አይደለም በማለት ጊዜያዊ እገዳን የጣሉበት ሲሆን በቀጣይ ምርመራ እንደሚደረግበት ተገልጿል። (ቢቢሲ)

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደው...
24/01/2025

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል።

የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

የትግራይ ሐይል አዛዦች በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ያለው ሃምሳ ሲደመር አንድ ድርሻ እንዲረከብ እንደሚሹ አቋማቸውን ይፋ አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ያሉ ታጣቂዎች በትግራይ ሰላም እና ፀጥታ ሴክሬታሪያት ስር እንዲሆኑ፥ ከዚህ ውጪ በሆነ ላይ ግን እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

በሌላ በኩል ፓርቲውን ለማፍረስ እና አመራሩን ለመበተን እያሴሩ ነው በማለት ህወሓት የኢትዮጵያ መንግስትን እና የምርጫ ቦርድን ወንጅሏል። በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራዉ የህወሓት ክንፍ ቁጥጥር ኮምሽን ከትላንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ በአስቸኳይ የህወሓት ሕጋዊነት ሰውነት ሊመለስ ይገባል ብሏል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ትላንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ
የትግራይ ሐይል አዛዦች ያስተላለፉት ውሳኔ በትግራይ ሥርዓት አልበኝነትን የሚያነግስ ነው በማለት አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ መጥራቱን ይፋ አድርጓል።

መግለጫው እንደሚለው የትግራይ ሐይሎች ከፍተኛ አዛዦች "ከተልእኳቸው ውጭ ለአንድ ሕገወጥ ቡድን ወግነው ግዚያዊ አስተዳደሩን የማፍረስ፣ ስርዓት አልባነት የማንገስ እና ሰራዊት የመበተን ግልፅ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸውን አሳውቀዋል" ብሏል።

የትግራይ ሐይል አዛዦች በትላንትናው ዕለት ያስተላለፉትን ውሳኔ ግዚያዊ አስተዳደሩ የማያውቀውና "ሕጋዊ ይሁን ሞራላዊ ቅቡልነት የሌለው" ሲል ያመለከተው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር መግለጫ፤ ከዚህ በተጨማሪ የፕሪቶርያ ውልንም ለአደጋ የሚያጋልጥ እና ኃላፊነት የጎደለው ብሎታል።
(ከጀርመን ድምፅ ተወስዶ የተቀናበረ)

“አሞራው ካሞራ” - ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ ከሰሞኑ በለቀቀው የብዙዎችን ቀልብ በሳበው ነጠላ ዜማው “አሞራው ካሞራ” ሲል ያዜመላቸው ራስ አሞራው ውብነህ ተሰማ ማን ናቸ...
24/01/2025

“አሞራው ካሞራ”
- ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ

ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ ከሰሞኑ በለቀቀው የብዙዎችን ቀልብ በሳበው ነጠላ ዜማው “አሞራው ካሞራ” ሲል ያዜመላቸው ራስ አሞራው ውብነህ ተሰማ ማን ናቸው?

ግጥሞቹ ታሪካዊ ዳራ ያላቸው የአሞራው ውብነህ ተሰማን ታሪክና ጸባይ አብጠርጥረው የሚገልጹ ናቸው። ራስ አሞራው ውብነህ የፋሽስትን ጦር የሰማይ አሞራ ሆነው መቆሚያ መቀመጫ ያሳጡት ጀግና እንደነበሩ ታሪካቸው ያስረዳል።

ለዚህ ጀብዳቸው በሚመጥን መልኩ ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ “አሞራው ካሞራ” በተሰኘው ድንቅ የሙዚቃ ሥራው…

ያየም ሰው ይናገር የነበረም ያውጋ
ተጋጥሟል ይባላል አሞራው ከአሞራ
ጎንደር ጀግና ትውለድ ታሳድግ ፀንሳ
እንደአሞራው ውብነህ ስሙ ማይረሳ … ሲል ለጆሮ በሚስማማ ድምጹ ለጀግናው ይቀኛል። ታሪኩን እያነሳሳም ያወድሳል።

“አሞራው ውብነህ” ከ1928 እስከ 1933 ዓ.ም ፋሽስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት በምዕራብ በጌምድር ግዛት በተደረገው የፀረ-ፋሽስት ትግል ግንባር ቀደም መሪ ነበሩ።

ከሱዳን ጋር በሚያዋስነው ቆላማ አካባቢ የአርማጭሆ አውራጃ ተወላጅ የሆኑት ውብነህ ተሰማ ገና በ16 ዓመታቸው ነበር ትግል የጀመሩት።

በፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ ወቅት በጎንደር በኩል ታላቅ ጀብዱ ከፈጸሙ ስመ ጥር አርበኞች መካከል ውብነህ ተሰማ አንዱ ናቸው። አገርንና ወገንን የሚወዱ፣ ከአገር የሚበልጥብኝ ነገር የለም በማለት ራሳቸውን ያሳመኑ እና ጸሎተኛም እንደነበሩ የልጅ ልጃቸው ገብርኤላ አድማሱ ከፋና ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

ታዲያ ይህንን ሀገር ወዳጅ፣ አርበኛ እና ጸሎተኛ ባህሪያቸውን ጽምጻዊ አስቻለው ፈጠነ…

ያ የአርበኛው ምንጣፍ ያ ምጅምር ገጡ
የጦሩ መሳፍንት ፈሪሀ እግዜር ያለው
ከጦር መሀል ሲሄድ ይመስላል ክንፍ ያለው
አሞራው ከአሞራ … ሲል በተመጠኙ እና ውብ በሆኑ ቃላት ይገልጸዋል።

ልጃቸው ኢትዮጵያ ውብነህ ከፋና ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ ከነፃነት በኋላ እንግሊዞች ጎንደር ገብተው የራሳቸውን ሰንደቅ ዓላማ ሲሰቅሉ የተመለከቱት ራስ አሞራው ውብነህ፤ በአገሬ ላይ የውጭ ሀገር ሰንደቅ ዓላማ አይሰቀልም በማለት የእንግሊዞችን አስገድደው አውርደው በምትኩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዲሰቀል ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ከሱዳን ገዳሪፍ ተስቦ እንደ ሰርዶ
ኢትዮጵያን ሰቀላት ያን ሰንደቅ አውርዶ
የአበቅየለሽ ልጆች ዳር እስከዳር ኩሩ
ጎንደር ጀግና አታጣም አትጠራጠሩ … በማለት አስቻለው “አሞራው ካሞራ” በተሰኘው ሙዚቃ ላይ የተቀኘለትም ለዚሁ ነው።

አርበኛው ውብነህ ተሰማ ባለቤታቸውን ጨምሮ ቁጥራቸው ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ከመጣ ሀገር ወዳድ አርበኞች ጋር በዱር በገደል ስለተዋደቁ ፋሽስት ኢጣልያ በጌምድርን ተረጋግቶ መቆጣጠር ሳይቻለው ቀርቷል።

ራስ አሞራው ውብነህ በተወለዱ በ94 ዓመታቸው መስከረም በ1975 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ቀብራቸውም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
(FMC)

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ እየሰጠኝ አይደለም በሚል ወቀሰ- "የመጨረሻ" ያለውን ደብዳቤ ለሚኒስቴሩ ፅፏል፣የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም...
24/01/2025

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ እየሰጠኝ አይደለም በሚል ወቀሰ

- "የመጨረሻ" ያለውን ደብዳቤ ለሚኒስቴሩ ፅፏል፣

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ኢስላማዊ አልባሳት ስለለበሱ ብቻ በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች በሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለው የመብት ጥሰት በሀገር አቀፍ ደረጃ ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጠው የሚጠይቅ የመጨረሻ ያለውን ደብዳቤ ለትምህርት ሚኒስቴር ጽፏል፡፡

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከኢስላማዊ አለባበስ ጋር በተያያዘ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የሚደርስባቸውን ከፍተኛ ጫናና ከትምህርት መፈናቀል በዘላቂነት መፍትሄ እንዲያገኝ ውይይቶች ሲያደርግ መቆየቱንና በዚህ ወር ብቻ ለትምህርት ሚኒስቴር ሶስት ጊዜ ደብዳቤዎችን መጻፉን ጠቅሷል፡፡

ይሁን እንጂ ከችግሩ አሳሳቢነት አንፃር እስከ አሁን ተገቢ ምላሽ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዳላገኘና አሁንም ችግሩ በዲላ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ መፈፀሙን አመላክቷል፡፡

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የመጨረሻ ባለው በዚህ ደብዳቤ ኢስላማዊ ልብስ ስለለበሱ ብቻ ትምህርት የማግኘት ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተገፎ ወደ ቅጥር ግቢ እንዳይገቡ የተከለከሉ የዲላ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአፋጣኝ ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱና ለችግሩ ዘላቂ አስተዳደራዊ መፍትሄ እንዲሰጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጠይቋል፡፡

"ለበጎ ነገር ተባበሩ"============- " የቲክቶከሮቹ የእግር ኳስ ጨዋታ በጉጉት እየተጠበቀ ነው"ሎዛ ኦርቶዶክሳዊ ኹነቶች አዘጋጅ ከመቄዶኒያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማ...
23/01/2025

"ለበጎ ነገር ተባበሩ"
============
- " የቲክቶከሮቹ የእግር ኳስ ጨዋታ በጉጉት እየተጠበቀ ነው"

ሎዛ ኦርቶዶክሳዊ ኹነቶች አዘጋጅ ከመቄዶኒያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማእከል ጋር በመተባበር በቲክቶክ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ቤተክርስቲያንን በማገልገል በሚታወቁት ወንድሞች መካከል የእግር ኳስ ጨዋታ አዘጋጅቷል። ዋና ጨዋታው የሚካኼድበት ቀን ጥር 17/2017 ቅዳሜ ጠዋት 3፡00 ነው። የእግር ኳስ ጨዋታው የሚካኼድበት ቦታ ደግሞ 15 ሜዳ እየተባለ በሚጠራው ዘመናዊ ሜዳ ላይ ይኾናል። ይኽ ሜዳ ቤለር አካባቢ ከአዲስቪው ሆቴል ዝቅ ብሎ ይገኛል።

ዓላማውም መቄዶኒያ የካቲት 1 ለሚያደርገው የቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ለመሥራት እና መቄዶኒያን በገንዘብ እና በቁሳቁስ ለመርዳት ያለመ ነው ተብሎለታል። ወደ ጨዋታው ለመግባትም የሚያስፈልገው መግቢያ በጎ ልብ ሲኾን ከዚሁ ጋር ያገለገሉ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ የንጽሕና መጠበቂያዎች እንዲሁም የመቄዶኒያን ቲሸርት መግዛት ይኾናል። ይኽን ኹሉ ማድረግ ለማይችሉ ደግሞ በነፃ ገብተው ተጫዋቾችን ማበረታታት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የእግር ኳስ ጨዋታ ኃጢአትም ጽድቅም አይደለም። ልብስ እንደመልበስ፣ ጫማ እንደመጫማት፣ ንጽሕናን እና ጤናን እንደመጠበቅ፣ ራስን እና አካልን እንደመጠበቅ ነው። ዋናው ቁም ነገሩ ዓላማው እና አጠቃቀሙ ነው። እሳትን እህል ለማብሰልም ቤት ለማቃጠልም እንጠቀምበታለን። ጉዳዩ ሳይኾን ጉዳዩን የምንጠቀምበት መንገድ እና ዓላማ ነው - ጉዳዩ። እጃችን ክቡር የሰውን ልጅ ለማሳዘን እንጠቀምባታለን። ክቡር የኾነውን የሰውን ልጅ ለማዳንም እንጠቀምበታለን። እርሱ የሰጠንን አካል በንጽሕና ከተጠቀምንበት እግዚአብሔር በእኛ ይከብርበታል። መጽሐፉስ እንዲህ አይደል የሚለው “መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።” ማቴዎስ 5፥16 በዚኽም መሠረት የወዳጅነት ጨዋታው በወንድሞች መካከል እየተካኼደ መቄዶኒያን ደግሞ እናግዛለን።

ተጫዋቾቹ በዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ግቢ በሚገኘው ዘመናዊ ሜዳ ለሳምንታት ልምምድ እያደረጉ መሰንበታቸው ታውቋል። እግር ኳሱ ልሳነ ተዋሕዶ እና ሐዋርያዊ መልሶች በተሰኙ ቡድኖች መካከል የሚካኼድ ነው። እያንዳንዱ ቡድን ከነተቀያሪዎቻቸው አሥራ ስምንት ተጫዋቾችን ይዘዋል። አሰላለፋቸውም አሥር ተጫዋች አንድ በረኛ፣ አሥር ተጫዋች አንድ በረኛ ኹነው ወደ ሜዳ ይገባሉ። ጨዋታው በሁለት የመስመር ዳኞች እና በአንድ የመሐል ዳኛ የሚመራ ይኾናል። የጨዋታው ቆይታም ከእረፍት በፊት 45 ደቂቃ ከእረፍት በኋላ ደግሞ 45 ደቂቃ በድምሩ ለ90 ደቂቃ የሚቆይ ይኾናል።

በልሳነ ተዋሕዶ በኩል ዋና አሰልጣኙ ያያ ዘልደታ ( ያሬድ ወልደ ጻድቅ) መኾኑ ታዉቋል:: ቡድኑን አምበልነት እየመራ ወደ ሜዳ የሚገባው ደግሞ ጆሲ ( ዮሴፍ አስፋው) ነው። በሐዋርያዊ መልሶች በኩል ዋና አሰልጣኙ አኬ ( አክሊል መንግሥቴ ) ሲኾን አምበሉ ደግሞ ባሮክ ( ብሩክ ፈቃዱ ) ነው ። ጨዋታውም ኦርቶዶክሳዊ ጨዋነትን በተላበሰ መንገድ በጸሎት ተጀምሮ በጸሎት እንደሚፈጸምም አዘጋጁ ሎዛ ኦርቶዶክሳዊ ኹነቶች አዘጋጅ አስታውቋል። ጨዋታውን ለመታደምም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ የጥበብ ሰዎች፣ አገልጋዮች እና የሁለቱ ቡድኖች ደጋፊዎች እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

የጨዋታውን መርሐግብር በአካል ተገኝታችኹ መከታተል ላልቻላችኹ ኹሉ አስፈላጊ መሣርያዎችን ኹሉ አሰናድቶ በተጠንቀቅ በሚጠብቃችሁ በሎዛ ሚዲያ በኩል በቀጥታ ሥርጭት መከታተል እንደምትችሉ ተገልጿል።
https://youtube.com/?si=M9I77Jb6lYIkgrYl

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when DireTube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to DireTube:

Videos

Share

Our Story

DireTube is the Largest Ethiopian News & Video Platform. It has particularly proven its value when it comes to keeping the worldwide Ethiopian Diaspora connected to their home country.

In many parts of the world Ethiopians do not have direct access to Ethiopian news and entertainment, therefore, DireTube becomes their primary source for these. For this reason DireTube is now one of the most popular Ethiopian websites on the internet.