Afar times

Afar times news and promotion

05/08/2023

Afar Times Older traditional songs by subscribing to Media Also watch a variety of fun and funny videos.

ስር የሰደደውና መፍትሄ ያላገኜው የሰመራ ዩኒቨርስቲ የላይብረሪ ሰራተኞች ተቃውሞ_________________________________________-----------------------------...
24/07/2023

ስር የሰደደውና መፍትሄ ያላገኜው የሰመራ ዩኒቨርስቲ የላይብረሪ ሰራተኞች ተቃውሞ
_________________________________________
------------------------------------------------------------------

ሰመራ ዩኒቨርስቲ የላይብረሪ ሰራተኞች በየአመቱ የሚከፈላቸውን የክረምት ወራቶችን የኦቨር ታይም ክፍያዎች በየአመቱ እንደማይከፈላቸው የሰመራ ዩኒቨርስቲ የላይብረሪ ሰራተኞች ቅሬታቸውን የሚሰማቸውም ሆነ ለችግራቸው መፍትሄ የሚሰጥ የስራ ኃላፊዎች እንደለላቸውና ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ሰምተው እንዳልሰሙ በመሆን ትኩረት ባለመስጠታቸው የተነሳ በሰመራ ዩኒቨርስቲ በላይብረሪ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች በዚህ የተነሳ ክረምትን መስራት አንፈልግም ቢሉም ነገር ግን በግዴታ እንዲሰሩ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ድምፃቸውን በአሁን ሰአት በማህበራዊ ድህረ -ገፅ እያሰሙ ይገኛሉ ። የሰመራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት አቶ መሀመድ ዑስማን በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርገው ያሉትን ችግሮች ከአመት እስከ አመት ስር የሰደዱ ችግሮች በመሆናቸው ለዩኒቨርስቲው ለላይብረሪ ሰራተኞቻቸውን በቅርብ ተገናኝተው የሰራተኞቹ መብትና ግዴታቸው ተከብሮላቸው ያሉትን ማናቸውንም ችግሮች በቀላሉ እንዲፈቱና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲደረግበት ይገባል።

02/05/2023
ለሳፋሪኮም ኢትዮጲያ ጥብቅ ማሳሰቢያ__________________________________ሳፋሪኮም ኢትዮጲያ በአፋር ክልል በሎጊያ ከተማ ፣ ታዎሮችን በመትከል አገልግሎቱን በቅርብ እንደጀመረ ...
01/02/2023

ለሳፋሪኮም ኢትዮጲያ ጥብቅ ማሳሰቢያ
__________________________________

ሳፋሪኮም ኢትዮጲያ በአፋር ክልል በሎጊያ ከተማ ፣ ታዎሮችን በመትከል አገልግሎቱን በቅርብ እንደጀመረ ይታወቃል። ይሁንና ሰሞኑን በሎጊያ ከተማ የሳፋሪኮም የሽያጭ ወኪሎች ላይ የሲም ካርድ መሸጫ (ዲቫይስ) እጥረት ስላጋጠመን በማለት ስራ የጀመሩትን የሳፋሪ ኮም ወኪል ሱቆችና የንግድ ማዕከሎች ላይ በሳፋሪኮም ድርጅት ውስጥ የሽያጭ ቁጥጥርና ዘርፍ ሰራተኛ ናት የተባለች አይሻ አይቲሌ የምትባል የድርጅቱ ሰራተኛ ፣ በአንዳንድ ወኪሎች ላይ እየተዘዋወረች የሲም ካርድ መሸጫ ዲቫይሶችን በመቀበል፣ የድርጅታችን ሰራተኞች በቀን እስከ 40 ሲም ካርድ እና ከዚያም በላይ በመንገድ ላይ እየዞሩ መሸጥ ስላለባቸው በማለት የሲም ካረድ መሸጫቸውን ተቀብላቸዋለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአካባቢው ከሚገኙት የስራ ሀላፊዎችን ስለተፈጠረው ችግር ለመጠየቅ ሞክረን ነገር ግን በተደጋጋሚ ለማግኜት አልቻልንም። የሳፋሪኮም ድርጅት ይመለከተናል የምትሉ ባለድርሻ አካሎች ይህንን አሳፋሪ የሆነ ድርጊት ጉዳዮን እንደመረጃ በመያዝ ክትትልና ግምገማ በማድረግ ለድርጅቱ ወኪሎች የሲም ካርድ መሸጫ ዲቫይሶቹን በአስቸኳይ እንዲመለስላቸውና ስራቸውን በአግባቡ እንዲሰሩ ከማድረግ ባሻገር የዲቫይስ እጥረት በአካባቢው ካለ ለወኪሎቹ የስማርት ስልካቸው ላይ በቀላሉ የሳፋሪኮም የመሸጫ ሶፍትዌሩን ሊንክ በማድረግ ችግሩን በቀላሉ ማርገብ ይቻላል። ለማንኛውም በአካባቢው ላሉ ህብረተሰቦች የሳፋሪኮም ሲም ካርኮችን በሽያጭ መልክ ለማዳረስ የተሻለ አሰራርና ቁጥጥር እንዲያስፈልገው በቅርብ በመሆን የስራ ሀላፊዎች ስራውን በአግባቡ መስራት መቻልና ለህብረተሰቡ የሳፋሪኮም ኔትዎርኮችን በማስፋፋት ምቹና እንደ አማራጭ የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ግድ ይላል በማለት እንደ ሀሳብ ያየነውን እና ያጋጠሙንን ቅሬታዎች በማህበራዊ ገፆች ላይ ለማስተላለፍ ተገደናል።

ሩሲያና ቻይና የጆ ባይደንን ከፋፋይ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተቃወሙኅዳር 15/2014 (ዋልታ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመጪው ታኅሣሥ 1 እና 2 ‹ስለዴሞክራሲ› በሚል አጀንዳ ከ110 አ...
24/11/2021

ሩሲያና ቻይና የጆ ባይደንን ከፋፋይ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተቃወሙ

ኅዳር 15/2014 (ዋልታ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመጪው ታኅሣሥ 1 እና 2 ‹ስለዴሞክራሲ› በሚል አጀንዳ ከ110 አገራት መሪዎች ጋር ለማካሄድ ያሰቡት የበይነ መረብ ጉባኤ ከቻይናና ሩሲያ ጠንካራ ተቃውሞ ገጠመው፡፡

ጉዳዩን እየተቀባበሉት የሚገኙት ዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙኃን ጉባኤው ‹‹ዴሞክራሲ እና አምባገነን›› የሚሉ አጀንዳዎች ላይ የሚያተኩር መሆኑን ነጩን ቤተ መንግሥት ዋቢ አድርገው ዘግበዋል፡፡

በኋይት ሐውስ የጥሪ ዝርዝር መሰረት ለጉባኤው ከተጋበዙት ውስጥ የኢትዮጵያን ጨምሮ የሩሲያ፣ ቱርክ፣ ቻይና፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች፣ ሳዑዲ አረቢያና ኳታር መሪዎችም አልተካተቱም፡፡

የባይደንን አካሄድ ያወገዘችው ሩሲያ አገራትን ለመከፋፈል የሚደረግ ነው ስትል ተቃውሞዋን አሰምታለች፡፡

ቻይና በበኩሏ የግዛቷ አካል ታይዋን በጉባኤው እንድትሳተፍ በመጋበዟ ቁጧዋን ገልፃለች፡፡

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዣሆ ሊዢያን በሰጡት መግለጫ ያለችው አንድ ቻይና መሆኗን አስቀድመዋል፡፡

መላ ቻይና የምትወከለው ደግሞ በቻይና ሕዝቦች ሪፐብሊክ መንግሥት ብቻ እንጂ በስሯ ባሉ የግዛት አስተዳዳሪዎች እንዳልሆነ አፅንኦት በመስጠት የአገራቸውን አቋም አሳውቀዋል፡፡

በእርግጥም የአገራት መሪዎች በሚል ዝርዝር ውስጥ የቻይናን ራስ ገዝ አስተዳደር ታይዋን ገዥዎች የባይደን አስተዳደር ለጉባኤ መጥራቱ የተገንጣይነት እሳቤን ይዞ የቻይናን ሉኣላዊ ግዛት ጥያቄ ውስጥ ለመክተት የሚጥረውን አካል አሜሪካ እንደምትደግፍ ማረጋገጫ ሆኗል፡፡

ቻይና የታይዋንን ራስ ገዝ አስተዳደር ከቻይና መነጠል እንደማይቻል በማስመር ከኋላ ሆነው ግፋ በለው የሚሉ አካላት እንዲጠነቀቁ በተደጋጋሚ ማሳሰቧ የሚታወስ ነው፡፡

አሜሪካ የቅርብ አጋሬ ከምትላቸውና በኔቶ ማዕቀፍ ውስጥም የሚገናኙትን እንደነቱርክ ያሉ አገራት አለመጋበዟ የባይደን አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲን ጥያቄ ውስጥ ከቶታል፡፡

ከአፍሪካ አንጎላ፣ ቦትስዋና፣ ጋና፣ ሞሪሽዬስ፣ ናሚቢያ፣ ሴኔጋል፣ ሲሼልስ፣ ዛምቢያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ እና ኒጀር ናቸው ለበይነመረቡ ጉባኤ የተጋበዙት፡፡

ደሴን ለመያዝ አሰፍስፎ  የመጣውን ወራሪ ሃይል በመመከት አኩሪ ገድል እየተፈፀመ ነው - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎትአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መላው የጸጥታ ሃይል...
30/10/2021

ደሴን ለመያዝ አሰፍስፎ የመጣውን ወራሪ ሃይል በመመከት አኩሪ ገድል እየተፈፀመ ነው - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መላው የጸጥታ ሃይል ደሴን ለመያዝ አሰፍስፎ የመጣውን ወራሪ ኃይል በመመከት አኩሪ ገድል እየፈጸመ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ከሰዓት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡ -

በሃገር መከላከያ ሰራዊት እየተመራ ወራሪውን የሽብር ቡድንና ያሰለፈውን መንጋ እየመከተ የሚገኘው መላው የፀጥታ ሃይላችን በፀረ ማጥቃት እርምጃው ቀጥሏል።

በተለይ ደሴን ለመያዝ አሰፍስፎ የመጣውን ወራሪ ሃይል በመመከት አኩሪ ገድልን እየፈፀመ ይገኛል።

ሌሊቱን ሙሉ ከተለያዩ ግንባሮች ጠጋግኖ በማሰባሰብ ደሴን ለመያዝ በኩታበር; ቦሩ ስላሴና በሃይቅ መስመር የመጣውን ወራሪ መንጋ የፀጥታ ሃይላችን በታላቅ ጀብዱ መክቶታል። አሁንም ደሴና አካባቢዋ በፀጥታ ሃይላችን ስር ነው።

ቀደም ብለውም ስደተኛ በመምሰልና የመከላከያ ሃይላችንን ወታደራዊ አልባሳት ለብሰው ሊዘርፉ የሞከሩና ቡድኖችና በከተማዋ የሚኖሩ ለጥፋት ሃይሉ የሚሰሩ ባንዳዎች ከትናንት ጀምሮ የጁንታውን አላማ ለማስፈፀም ከግንባር ውጊያው ባልተናነሰ ሲሰሩ ውለዋል።

የደሴ ወጣቶችና መላው የፀጥታ ሃላችንም ይህንን ሃይል በተደራጀ መንገድ እየመከቱት ይገኛሉ። የከተማዋ ወጣቶችም በጀመሩት መንገድ ከተማቸውን ከባንዳ የመጠበቅ ተግባራቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል።

ያለውን ሃይል ሁሉ አሰባስቦ በዚሁ ግንባር ያመጣው የሽብር ቡድኑ በጦር ግንባር ያቃተውን በወሬ ለማግኘት አሁንም መፍጨርጨሩን ቀጥሏል።
አንዳንድ የውጪ መገናኛ ብዙሃንም የሽብር ቡድኑን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ እያስተጋቡ ይገኛሉ።

በወሬ የሚያዝ ከተማ የለም ሊኖርም አይችልም ብሎ መላው ህዝብ በደሴ ከተማ ዙሪያ ለሚነሳው አሉባልታ ጆሮ ሳይሰጥ አሁንም የሃገሩን ህልውና ለማስከበር የሚያደርገውን ተጋድሎ ቀጥሏል።

በዚሁ አጋጣሚ በተለይ ያልተጣራ መረጃን በመያዝ ህዝብን ለማሸበር እየተንቀሳቀሱ የሚገኙና የሽብር ቡድኑ መጠቀሚያ የሆኑ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት ያሳስባል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የከፍተኛ ባለሥልጣናት ውይይት በባሕር ዳር ከተማበጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ  የሚመራ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የሕግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ ዛሬ  ባሕር ዳር ከተማ ው...
29/10/2021

የከፍተኛ ባለሥልጣናት ውይይት በባሕር ዳር ከተማ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሚመራ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የሕግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ ዛሬ ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ በወቅታዊ ሁኔታ እየመከረ እንደሚገኝ ለመንግሥት ቅርበት ያላቸው መገናኛ አውታሮች ዘገቡ።

በዛሬው ምክክር ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የሁሉም ክልሎች ርእሳነ-መሥተዳድሮች፣ የከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል አመራር እንደተገኙበት ተጠቅሷል።

መድረኩ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍም ይጠበቃል ተብሏል። የክልል መንግሥታት የሕግ አስፈፃሚዎች የግንኘነት መድረክ የኢፌዴሪ የመንግሥታት ግንኙነት ሥርዓትን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1231/2013 መሰረት የተቋቋመ መሆኑም ተገልጧል። ዝርዝር መረጃዎችን እየተከታተልን ለማቅረብ እንሞክራለን።
ምስል፦ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት።

29/10/2021

በአሁን ሰአት የኢትዮጲያ ከፍተኛ የመከላከያ ጦር አመራሮች በአሸባሪው ህወአት ቡድን በገንዘብ እየተታለሉ ህዝባችንን እና አገራችንን ለከፍተኛ ውድመትና እልቂት እየተጋለጠ ይገኛል ስለሆነም መንግስት እንደዚህ አይነቶችን ከሀዲ ባንዳዎች የእናት ጡት ነካሾችን ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ጋር በተቀናጀ ሁኔታ በመስራት የኢትዮጲያን ጠላቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ሰአቱ አሁን ስለሆነ የህዝባችንን ሀሳብና እንግልት ከስጋት ለማውጣት በታማኝነት የኢትዮጲያ መከላከያ አመራሮችን ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገባቸው የተሰጣቸውን አገራዊ ግዴታቸውን አስበውና አልመው የህዝብ አደራን ተቀብለው በአግባቡ ስራቸውን እንዲሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዚህ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እንዲያደርጉ በማለት መልክታችንን እናደርሳለን።

የዛሬው የመቀሌ የዓየር ጥቃት ከጠዋቱ 5:30 ላይ ከመቀሌ ወደ ደቡብ አቅጣጫ በተለምዶ መቀሌ ዩኒቨርስቲ ኦሬድ ካምፓስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መፈጸሙን የመቀሌ ዘጋቢ ሚሊዮን ኃይለሥላሴ በስል...
22/10/2021

የዛሬው የመቀሌ የዓየር ጥቃት ከጠዋቱ 5:30 ላይ ከመቀሌ ወደ ደቡብ አቅጣጫ በተለምዶ መቀሌ ዩኒቨርስቲ ኦሬድ ካምፓስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መፈጸሙን የመቀሌ ዘጋቢ ሚሊዮን ኃይለሥላሴ በስልክ ለዶቼቬሌ ተናግሯል። ሚሊዮን በጥቃቱ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት መጠን ለማጣራት ቢሞክርም ያገኘው መረጃ እንደሌለ ገልጿል።ወደ ሆስፒታል የመጣ ቁስለኛም የለም ብሏል።ይሁንና በዚሕ ሳምንት በተደጋጋሚ የደረሰዉ የአዉሮፕላን ጥቃት ወትሮም መድኃኒትና ነዳጅን በመሳሰሉ ሸቀጦች እጥረት፣ በመገናኛና በባንክ አገልግሎቶች መቋረጥ ለችግር የተጋለጠዉን ሕዝብ ይበልጥ ማስፈራትና ማስጋቱን ዘጋቢያችን ጠቅሷል። ሚሊዮን በስልኩ ቃለ ምልልስ አብዛኛው የመቀሌና አካባቢዉ ህዝብ ችግሩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የሚፈልግ መሆኑን ገልጿል።

  🇪🇷🇪🇷የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት በአይነቱ የተለየ የተባለውን ወታደራዊ ልምምዷን አድርጋ ጨረች። ለሁሉም ነገር ተዘጋጅቻለሁ በማለት በኤርትራ ፕሬስ በፌስቡክ ፔጅ አስተላልፏል።በዚህ ትርኢት...
19/10/2021

🇪🇷🇪🇷

የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት በአይነቱ የተለየ የተባለውን ወታደራዊ ልምምዷን አድርጋ ጨረች። ለሁሉም ነገር ተዘጋጅቻለሁ በማለት በኤርትራ ፕሬስ በፌስቡክ ፔጅ አስተላልፏል።

በዚህ ትርኢት የኤርትራ አየር ሀይል ብቃቱን በተለየ ሁኔታ አሳይቶበታል። ከዛ ውጭ በርካታ ድሮኖችም ታይተውበታል፤ የቦሊስቲክ ሚሳይልና ሌሎች ሚሳይሎችም ሙከራም ተካሂዶበታል። የከባባድ መድፎች ታንኮች ትርኢት አስደማሚ ነበር ሲል ኤርትራ ፕሬስ በፁሁፍ አቅርቦታል።

ጆባይደን እና ኡሁሮ ኬንያታ በአፍሪካ ቀጠና ዙሪያእና ሰላም ባልተረጋጋባቸው የአፍሪካ አገሮች ዙሪያ ትናንት በነጩ ቤተ መንግስት ተመካከሩየዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የኬንያ አቻቸ...
15/10/2021

ጆባይደን እና ኡሁሮ ኬንያታ በአፍሪካ ቀጠና ዙሪያ
እና ሰላም ባልተረጋጋባቸው የአፍሪካ አገሮች ዙሪያ
ትናንት በነጩ ቤተ መንግስት ተመካከሩ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የኬንያ አቻቸው ኡሁሩ ኬንያታን ነጩ ቤተመንግሥት ውስጥ ትናንት ባነጋገሩበት ወቅት ኬንያ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት እንድታረግብ መጠየቃቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ የዜና ምንጭ ዘገበ። የኬንያ እና የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንቶች፦ ስለ ኬንያ እና ዩናይትድ ስቴትስ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ መምከራቸውን የሑዋይት ሐውስ መግለጫ ይጠቁማል።

ዴሞክራሲ እና ሰብአዊ መብቶች ስለሚከበሩበት፤ ቀጠናዊ ሠላም እና መረጋጋት ስለሚሰፍንበት ጉዳይ ብሎም በታዳሽ የኃይል ምንጮች እና ለከባቢ አየር ተስማሚ በሆኑ መፍትኄዎች የኤኮኖሚ እድገት ስለሚቀላጠፍበት መንገዶችም መክረዋል። የፋይናንስ ግልጽነትን አንስተው መወያየታቸውም ተጠቅሷል። የኬንያው ፕሬዚደንት እና ቤተሰቦቻቸው በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ከሀገር አሽሽተዋል የሚል ዘገባ ሰሞኑን መሰራጨቱ ይታወሳል። አፍሪቃ የኮሮና ተሐዋሲን ለመዋጋት በአኅጉሪቱ የጸረ ኮሮና ተሐዋሲ ክትባት ምርት እና ልማት ላይም መክረዋል።

በምሥራቅ አፍሪቃ ጸረ-ሽብር ትግል የዩናይትድ ስቴትስ አጋር የሆነችው ኬንያና አሜሪካ ፕሬዚደንቶች ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ውስጥ ያሉትን ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ስለመፍታት አስፈላጊነት ላይ እንዳሰመሩበትም ተጠቅሷል።

ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ኤርትራ የሦስትዮሽ ስምምነት ካደረጉ እና በሰሜኑ ኢትዮጵያ ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ በአካባቢው ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ የምዕራቡ ዓለም ሃገራት ትኩረታቸው ከፍ ብሏል።

በዛሬው ዕለት በሐራ እና ጭፍራ አጎራባች አካባቢ ላይ ከፍተኛ የሆነ የጦር መሳሪያ ድምፅ እንዳለ ወደ ጭፍራ በዛሬው ዕለት ስልክ ደውየ በማወራበት ሰአት በጆሮየ የተኩስ ድምፅ ሰምቼ ማረጋገጥ ...
14/10/2021

በዛሬው ዕለት በሐራ እና ጭፍራ አጎራባች አካባቢ ላይ ከፍተኛ የሆነ የጦር መሳሪያ ድምፅ እንዳለ ወደ ጭፍራ በዛሬው ዕለት ስልክ ደውየ በማወራበት ሰአት በጆሮየ የተኩስ ድምፅ ሰምቼ ማረጋገጥ ችያለሁ። ነገር ግን እስካሁን ከሁለቱም በኩል ያለውን መረጃ ለጊዜው ማግኜት አልቻልንም።

11/10/2021
በአሸባሪው ጁንታ ጦርነት ምክኒያት ከቀያቸው ንብረታቸውን ጥለው በተለየዩ ከተሞች በትምህርት ቤቶች እና በዱንካን እና በተለያዩ ቦታዎች ተጠልለው ለሚገኙ ነፍሰ ጡሮች፣ ህፃናቶች፣ ደም ግፊትና ...
11/10/2021

በአሸባሪው ጁንታ ጦርነት ምክኒያት ከቀያቸው ንብረታቸውን ጥለው በተለየዩ ከተሞች በትምህርት ቤቶች እና በዱንካን እና በተለያዩ ቦታዎች ተጠልለው ለሚገኙ ነፍሰ ጡሮች፣ ህፃናቶች፣ ደም ግፊትና ስኳር በሽተኞች በአሁን ሰአት ምንም እንኳን ከመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ የውጭ ድርጅቶች እንዲሁም ከአገር ውስጥ ባለሀብቶች የሚረጉት የተለያዩ ምግብ ነክ፣አልባሳትና እንዲሁም የገንዘብ እርዳታን ጨምሮ በአሁን ሰአት እያንዳንዱ ተፈናቃዮች የሚላክላቸውን ዕርዳታዎች በአግባብ እያገኙ አይደለም ። እነዚህ የሚያሳዝኑ ወገኖቻችን ከቻልን ያለንን ጨምረን መስጠት እንጂ የተረዱትን ማንኛቸውንም ዕርዳታዎች ማግኜት የሚገባቸውን ዕርዳታ ተቀናንሶ እየተሰጣቸው ነው የሚገኙትና መንግስት በዚህ አንገብጋቢ አሳዛኝ በሆኑ ችግረኞች ላይ ትኩረት በማድረግ ተገቢውን የዕርዳታ ድጋፍ በአግባቡ እንዲደርሳቸው ለእነዚህ ተፈናቃዮች የራሱ የሆነ ከሀይማኖት አመራሮች፣ከአካባቢው አመራሮች እና ከሌሎች አመራር ግብረ-ሐይል የተቀናጀ ተደርጎ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደርሳቸው በተለይ የገንዘብ እርዳታን በተመለከተ ለእያንዳንዱ ተፈናቃዮች እንደ አቅማቸው እየታየ የራሳቸው የባንክ አካውንት ተከፍቶላቸው በዚህ መሠረት በአግባቡ ማንኛቸውንም ዕርዳታዎችን እንዲያገኙ በማለት የበኩላችንን ሀሳብና አስተያየት ለሚመለከተው የመንግስት ባለድርሻ አካል ይህንን አስተያየት አስተውሮ በመመልከት ያለው አሰራር ተቀይሮ ተግባራዊ እንዲሆን እንፈልጋለን እና ከወዲሁ ትኩረት ይሰጠው እያልን በዚህ ላይ ለውጥ እንጠብቃለን።

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስትር ሆነው ተሽመዋል። መልካም የስራ ዘመን ይሁንልዎት!!
06/10/2021

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስትር ሆነው ተሽመዋል። መልካም የስራ ዘመን ይሁንልዎት!!

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረጂብ ጠይብ ኦርዶጋን እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ ረፋድ ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል። የመጡበትም ምክኒያት በነገው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ...
03/10/2021

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረጂብ ጠይብ ኦርዶጋን እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ ረፋድ ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል።
የመጡበትም ምክኒያት በነገው ዕለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚካሄደው የመንግስት ምስረታ ላይ በእንግድነት ለመካፈው መሆኑን የተሰሙ መረጃዎች ናቸው።

01/10/2021
ክብርት ወ/ሮ ዘሐራ ሁመድ የብልፅግናን ፓርቲ ወክላ ለክልል ምክር ቤት በእጩነት ተወዳድራ ምርጫውን በቂ ድምፅ አግኚታ ማሸነፏ ይታወቃል።ነገር ግን ትናንት በተካሄደው አዲስ የመንግስት የካቢኔ...
01/10/2021

ክብርት ወ/ሮ ዘሐራ ሁመድ የብልፅግናን ፓርቲ ወክላ ለክልል ምክር ቤት በእጩነት ተወዳድራ ምርጫውን በቂ ድምፅ አግኚታ ማሸነፏ ይታወቃል።
ነገር ግን ትናንት በተካሄደው አዲስ የመንግስት የካቢኔዎች ምርጫ ላይ ስሟ ሳይነሳ ምርጫውን በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ ማጠናቀቃቸው ይታወቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርብ ከሚሰሙ አዳዲስ መረጃዎች ለወ/ሮ ዘሐራ ሁመድ የማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ዋና ኃላፊ ሆና እንድትመራ ታስባለች የሚባል ኢንፎርሜሽን እየተሰማ ይገኛል።
በእርግጥ ወ/ሮ ዘሐራ ሁመድ ባላት የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ባሻገር ለክልሉ የተሻሉ ሪፎርሞች እሳየችና እንዲሁም በመልካም አስተዳደር እና በማህበራዊ በፖለቲካዊ ባላት ብቁ ችሎታዋ የሚነገርላት እንደሆነች ሳናስተውል አናልፋትም።

Address

Afar, Region
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Afar times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Afar times:

Share