Brook Genene - Sports Page

Brook Genene - Sports Page I share my work here- mostly about football and sports in general… sometimes about health.

ኤሪክ ቴን ሃግ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ- " ኦናና ለሰኞው የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ ይደርሳል:: ለቶተንሃሙ ጨዋታ መሰለፉ አልታወቀም::" -" የዋን ቢሳካ ሊንደሎፍ እና ምጄብሪ ኮንትራት በአንድ ...
04/01/2024

ኤሪክ ቴን ሃግ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ

- " ኦናና ለሰኞው የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ ይደርሳል:: ለቶተንሃሙ ጨዋታ መሰለፉ አልታወቀም::"

-" የዋን ቢሳካ ሊንደሎፍ እና ምጄብሪ ኮንትራት በአንድ አመት ተራዝሟል:: የቨራን እና ማርሲያልን ለማራዘም እየተደራደርን ነው::"

- " ጄደን ሳንቾን በተመለከተ አዲስ ዜና የለም:: ሲኖር እናሳውቃለን::"

The Ethiopia U-20 Women’s national team will face its Morocco counterpart in their bid to qualify for the Women U-20 Wor...
27/12/2023

The Ethiopia U-20 Women’s national team will face its Morocco counterpart in their bid to qualify for the Women U-20 World Cup. Ahead of the two-legged ties coach Firew Hailegebriel has announced a 24-women squad expected to be cut down to 23 players.

👉https://tilafok.com/?p=377

Christmas Tree formation🐐 s Via
25/12/2023

Christmas Tree formation

🐐 s

Via

ይህን ተጫዋች ካስታወሳችሁ ትክክለኛ የእግር ኳስ ደጋፊ ናችሁ! ማነው? Comment 👇🏾
25/12/2023

ይህን ተጫዋች ካስታወሳችሁ ትክክለኛ የእግር ኳስ ደጋፊ ናችሁ!

ማነው?

Comment 👇🏾

እንዴት ይህ ግብ ሳይሆን ቀረ? የማይታመን!
23/12/2023

እንዴት ይህ ግብ ሳይሆን ቀረ? የማይታመን!

በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 በቀጥታ ተከታተሉን!
23/12/2023

በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 በቀጥታ ተከታተሉን!

የሉተን ታውን ተጫዋች የሆነው ቶም ሎክየር ባጋጠመው cardiac arrest ምክንያት ሜዳ ላይ በመውደቁ የሉተን እና ቦርንማውዝ ጨዋታ ተቋርጧል:: ቶም እራሱን ወደ ንቃት የተመለሰ ሲሆን በአ...
16/12/2023

የሉተን ታውን ተጫዋች የሆነው ቶም ሎክየር ባጋጠመው cardiac arrest ምክንያት ሜዳ ላይ በመውደቁ የሉተን እና ቦርንማውዝ ጨዋታ ተቋርጧል::

ቶም እራሱን ወደ ንቃት የተመለሰ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሆስፒታል ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገለት መሆኑን ክለቡ ገልፆል::

ሃሪ መጏየር ለሊቨርፑሉ ጨዋታ እንደማይደርስ ቴን ሃግ ገልፀዋል:: ሉክ ሾው ከጉዳት እና ማርከስ ራሽፎርድ ከህመም አገግመው የቡድኑ አባል እንደሚሆኑ ይጠበቃል:: አንቶኒ ማርሲያል ለጨዋታው አ...
15/12/2023

ሃሪ መጏየር ለሊቨርፑሉ ጨዋታ እንደማይደርስ ቴን ሃግ ገልፀዋል::

ሉክ ሾው ከጉዳት እና ማርከስ ራሽፎርድ ከህመም አገግመው የቡድኑ አባል እንደሚሆኑ ይጠበቃል::

አንቶኒ ማርሲያል ለጨዋታው አይደርስም::

ክርስቶፈር ንኩንኩ ቼልሲ ክሼፊልድ ዩናይትድ ጋር ነገ በሚያደርገው ጨዋታ የቡድኑ አባል እንደሚሆን ፖቸቲኖ ገልፀዋል::
15/12/2023

ክርስቶፈር ንኩንኩ ቼልሲ ክሼፊልድ ዩናይትድ ጋር ነገ በሚያደርገው ጨዋታ የቡድኑ አባል እንደሚሆን ፖቸቲኖ ገልፀዋል::

13/12/2023

ታህሳስ 3፤2016 – ታሪካዊው እግር ኳስ ተጨዋች ደጉ ደበበ ጫማውን መስቀሉን አስታወቀ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስን ለ22 አመታት በመጫወት ብቸኛው እግር ኳስ ተጨዋች ደጉ ደበበ ጫማውን መስቀሉን ለብስራት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ አስታወቀ፡፡ ደጉ ደበበ እስከተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ድረስ ላለፉት 22 አመታት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ለሦስት ክለቦች ብቻ በመጫወት አሳልፏል፡፡

ዘንድሮ ግን እግር ኳስ ተጨዋችነት በቃኝ በማለት ጫማውን መስቀሉን ዛሬ ከብስራት ቴሌቪዥን ጋር በስልክ ባደረገው ቆይታ ወቅት ገልፆል፡፡ ‹‹በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመኔ መጫወት እስካለብኝ ጊዜ ድረስ ተጫውቻለሁ አሁንም ጥቂት አመታትን ለመጫወት የሚያስችል አቅሙ አለኝ ግን ለወጣቶች ቦታውን መልቀቅ ስላለብኝ በቃኝ ብያለሁ›› ሲል ደጉ ደበበ ለብስራት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ከ22 አመት የሊግ ቆይታው በኋላ ከእግር ኳስ ተጨዋችነት አለም መገለሉን አስታውቋል፡፡

ደጉ ደበበ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለ22 አመታት በመጫወት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ለ10 ጊዜ ያህል በማንሳት ታሪካዊ እግር ኳስ ተጨዋች ነው፡፡ ደጉ በ22 አመት የተጨዋችነት ዘመኑ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተጫወተው ለሦስት ክለቦች ብቻ ነው፡፡ በተጨዋችነት ዘመኑም ከክለብ በተጨማሪ ከወጣት እስከ ዋናው ብሔራዊ ቡድን በተጨዋችነትና አምበልነት ለ10 አመታት ሀገሩን አገልግሎል፡፡

ኢትዮጵያ ከ31 አመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ስታልፍም የብሔራዊ ቡድኑ አምበል በመሆን ነበር፡፡ በሀገር ውስጥ ውድድሮች ሁሉንም ዋንጫዎች ደጋግሞ አንስቷል፡፡ በርካታ የሀገሪቱን የክለቦች ውድድር ዋጫዎችን በማንሳት ቀዳሚው ሰውም እሱ ነው፡፡ ሁለት ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉ የዓመቱ ምርጥ እግር ኳስ ተጨዋችነት ክብርን እንዲሁ አግኝቷል፡፡ በአህጉር አቀፍ ውድድሮችም በሴካፋ፤ በቻንና በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ በቅቷል፡፡

በአጠቃላይ ደጉ ደበበ ብዙዎች ማሳካት ያልቻሉትን እሱ ማሳካት ችሏል፡፡ በዚህም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ የራሱን ደማቅ ታሪክ ለመፃፍ በቅቷል፡፡
ደጉ ደበበ በያዝነው የውድድር ዘመን ጫማውን መስቀሉን ተከትሎ የትውልድ ከተማው ክለብ አርባምንጭ ከተማ የዋና ቡድኑ የቴክኒክ አማካሪና የቡድን መሪ አድርጎ ሹሟታል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ደጉ ደበበ በሀዋሳ ከተማ የከፍተኛ ሊግ ውድድሩን እያደረገ ከሚገኘው ከአርባምንጭ ጨርቃ ጨርቅ ቡድን ጋር በመቀላቀል ስራ መጀመሩን ለብስራት ቴሌቪዥን አስታውቋል፡፡

በጋዜጠኛ መላኩ ወልደሰንበት

https://bit.ly/3RHrStG



የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

Facebook: https://bit.ly/3Hng6Qt

Website: http://www.bisrat101.com/

Telegram: https://t.me/Bisrat101fm

YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB

Borussia Dortmund are set to host PSG in their final game of the UEFA Champions League group stage. The Black and Yellow...
12/12/2023

Borussia Dortmund are set to host PSG in their final game of the UEFA Champions League group stage. The Black and Yellows have already secured qualification to the last 16, but will aim to finish in top spot. The game is almost a must-win one for Kylian Mbappe and co., and they will likely do most of the attacking on Wednesday.

I take a look at how BVB can line up for the game.

Borussia Dortmund are set to host PSG in their final game of the UEFA Champions League group stage. We take a look at how they could line up.

በዛሬው ምሽት ጨዋታ ትኩረት የሚያርፈው ሃሪ ኬን ላይ ነው:: ነገር ግን ሊሮይ ሳኔ ከማንም በበለጠ ማንችስተር ዩናይትድን እንደሚፈትን አስባለሁ:: ሳኔ በቱህል ስር የተመቸው ተጫዋች ነው:: ...
12/12/2023

በዛሬው ምሽት ጨዋታ ትኩረት የሚያርፈው ሃሪ ኬን ላይ ነው:: ነገር ግን ሊሮይ ሳኔ ከማንም በበለጠ ማንችስተር ዩናይትድን እንደሚፈትን አስባለሁ::

ሳኔ በቱህል ስር የተመቸው ተጫዋች ነው:: ትራንዚሽን ላይ ያለው ፍጥነቱ እና ኳስ የመግፋት ችሎታው ነጥሮ ወጥቷል:: በግራ እግሩም ወደውስጥ እየገባ የሚመታቸው ኳሶች አደገኛ ናቸው:: ዛሬ ምሽት ዳሎም ሆነ ሬጊሎን ከባድ የቤት ስራ አለባቸው::

ሌላ ጊዜ ቢሆን ባየርን ተዝናንቶ ሊጫወተው የሚችለው ጨዋታ በአይንትራክት ፍራንክፈርት በደረሰበት ከባድ ሽንፈት ምክንያተ ተነቃቅቶ ለማሸነፍ ነው የሚገባው::

ቱህል ከጫወታው በፊት ኦልድ ትራፎርድ መጥቶ ተዝናንቼ እጫወታለሁ ብሎ ነገር የለም ብሏል::

12/12/2023

በቅርብ ቀን

Bisrat TV

Frequency 11545
Polarization Horizontal
Symbol Rate 45000

Congratulations to Tigist Assefa!
11/12/2023

Congratulations to Tigist Assefa!

የአለም የአመቱ ምርጥ አትሌቶች ሽልማት ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ይፋ ይደረጋል:: በሴቶቹ ምድብ የበርሊንን ማራቶን በሪከርድ ሰዓት ያሸነፈችው ትዕግስት አሰፋ ኢትዮጵያን ወክላለች:: ከዚህ በ...
11/12/2023

የአለም የአመቱ ምርጥ አትሌቶች ሽልማት ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ይፋ ይደረጋል::

በሴቶቹ ምድብ የበርሊንን ማራቶን በሪከርድ ሰዓት ያሸነፈችው ትዕግስት አሰፋ ኢትዮጵያን ወክላለች::

ከዚህ በፊት መሰረት ደፋር ገንዘቤ ዲባባ እና አልማዝ አያና በሴቶች ሃይሌ ገብረስላሴ እና ቀነኒሳ በቀለ በወንዶች ( 2 ጊዜ) ማሸነፋቸው ይታወሳል::

ከተወዳጁ ጋዜጠኛ አላዛር አስገዶም ጋር ያደረኩትን ቆይታ YouTube ላይ ተከታተሉ:: ስለግልህይወቱ ብዙ ነገሮችን አጫውቶኛል:: ላይክ እና ሰብስክራይብ ማድረግ አትርሱ! 👉🏾 https://y...
11/12/2023

ከተወዳጁ ጋዜጠኛ አላዛር አስገዶም ጋር ያደረኩትን ቆይታ YouTube ላይ ተከታተሉ:: ስለግልህይወቱ ብዙ ነገሮችን አጫውቶኛል::

ላይክ እና ሰብስክራይብ ማድረግ አትርሱ!

👉🏾 https://youtu.be/jInIdLqZr9s?si=xS5Bi3pRTKslWHD_

You have to admire Crystal Palace and the way they approached the game. Very physical, didn’t allow space for Liverpool ...
09/12/2023

You have to admire Crystal Palace and the way they approached the game. Very physical, didn’t allow space for Liverpool and hit them on quick counters by isolating their CBs, constantly targeted Endo in the first half… deserved something from the game.

But Liverpool’s individual brilliance came through. They have won 18 points from losing positions this season.

Mentality Monsters!

ማንችስተር ዩናይትድ እና ቦሩሲያ ዶርትመንድ ጄደን ሳንቾን እና ዶንዬል ማለንን ለመቀያየር እየተደራደሩ መሆኑን ቢልድ ዘግቧል::
08/12/2023

ማንችስተር ዩናይትድ እና ቦሩሲያ ዶርትመንድ ጄደን ሳንቾን እና ዶንዬል ማለንን ለመቀያየር እየተደራደሩ መሆኑን ቢልድ ዘግቧል::

ማንችስተር ዩናይትድ በሽልማት ተንበሽብሿል:: ሃሪ ማጏየር- የወሩ ምርጥ ተጫዋችቴን ሃግ- የወሩ ምርጥ አሰልጣኝጋርናቾ- የወሩ ምርጥ ግብ
08/12/2023

ማንችስተር ዩናይትድ በሽልማት ተንበሽብሿል::

ሃሪ ማጏየር- የወሩ ምርጥ ተጫዋች

ቴን ሃግ- የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ

ጋርናቾ- የወሩ ምርጥ ግብ

ጄሚ ካራገር: " ዴክለን ራይስ ሮይ ኪንን ያስታውሰኛል:: ከሮድሪ ይልቅ እርሱ ቡድኔ ውስጥ ቢኖር እመርጣለሁ::"
08/12/2023

ጄሚ ካራገር:

" ዴክለን ራይስ ሮይ ኪንን ያስታውሰኛል:: ከሮድሪ ይልቅ እርሱ ቡድኔ ውስጥ ቢኖር እመርጣለሁ::"

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ከሃምበሪቾ ዱራሜ በሚያደርጉት ጨዋታ 9:00 ላይ ይጀምራል:: ሰራተኞቹ በ5 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ ሃምበሪቾ በ2 ነጥብ 15ኛ...
07/12/2023

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ከሃምበሪቾ ዱራሜ በሚያደርጉት ጨዋታ 9:00 ላይ ይጀምራል::

ሰራተኞቹ በ5 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ ሃምበሪቾ በ2 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል::

ሃሪ መጏየር የህዳር ወር የፕሪሚየር ሊግ ምርጥ ተጫዋች በመባል ተመርጧል:: በደጋፊዎች እና ሚዲያ ከመብልጠልጠል... የmeme እና ቀልድ ቪዲዮ ማድመቂያ ከመሆን... ዩናይትድን ለቆ ከመውጣት...
06/12/2023

ሃሪ መጏየር የህዳር ወር የፕሪሚየር ሊግ ምርጥ ተጫዋች በመባል ተመርጧል::

በደጋፊዎች እና ሚዲያ ከመብልጠልጠል... የmeme እና ቀልድ ቪዲዮ ማድመቂያ ከመሆን... ዩናይትድን ለቆ ከመውጣት ጫፍ መልስ... በጋና የፓርላማ አባል እና የአረብ ኮሜንታተር መቀለጃ እስከመሆን ድረስ ደርሶ የነበረው መጏየር ይህንን ሁሉ ውጣ ውረድ አልፎ ለዚህ ሽልማት እና ለጥሩ ብቃት ደርሷል::

የሚላን ቡድን በአንድ ወቅት ይህን የመሰለ ስብስብ ነበረው:: 2003 ላይ ኦልድ ትራፎርድ ላይ በፍፁም ቅጣት ምት ዩቬንቱስን ያሸነፈው እና ከ2 ዓመት በኃላ ኢስታንቡል ላይ የተረታው የአንቸሎ...
06/12/2023

የሚላን ቡድን በአንድ ወቅት ይህን የመሰለ ስብስብ ነበረው::

2003 ላይ ኦልድ ትራፎርድ ላይ በፍፁም ቅጣት ምት ዩቬንቱስን ያሸነፈው እና ከ2 ዓመት በኃላ ኢስታንቡል ላይ የተረታው የአንቸሎቲ ቡድን ድንቅ ነበር::

እናንተ የምትወዱት ተጫዋች የትኛው ነበር?

ካርሎ አንቸሎቲ በዚዳን እና ቤሊንግሃም መካከል ስላለው ልዩነት ተናግረዋል: " ዚዳን የላቀ የግል ብቃት ነበረው:: ቤሊንግሃም ብዙ ሜዳን የሚያካልል ዘመናዊ ተጫዋች ነው:: ጎል አካባቢም በት...
30/11/2023

ካርሎ አንቸሎቲ በዚዳን እና ቤሊንግሃም መካከል ስላለው ልዩነት ተናግረዋል:

" ዚዳን የላቀ የግል ብቃት ነበረው:: ቤሊንግሃም ብዙ ሜዳን የሚያካልል ዘመናዊ ተጫዋች ነው:: ጎል አካባቢም በትክክለኛው ሰዓት መድረስ ይችላል::"

ቤሊንግሃም ትላንትም ግብ አስቆትሯል:: የጨዋታ ኮከብም ተብሏል::

ቦሩሲያ ዶርትመንድ አንድ ጨዋታ እየቀረ ከሞት ምድብ ማለፉን አረጋግጧል:: ወደ ሳንሲሮ በመጏዝ ሚላንን 3-1 ሲረታ ሮይስ ባዮነ ጊተንስ እና አዴያሚ ግቦቹን አስቆጥረዋል:: ማትስ ሃምልስ የጨ...
29/11/2023

ቦሩሲያ ዶርትመንድ አንድ ጨዋታ እየቀረ ከሞት ምድብ ማለፉን አረጋግጧል:: ወደ ሳንሲሮ በመጏዝ ሚላንን 3-1 ሲረታ ሮይስ ባዮነ ጊተንስ እና አዴያሚ ግቦቹን አስቆጥረዋል::

ማትስ ሃምልስ የጨዋታው ኮከብ ተብሏል::

የቀድሞው የጀርመን ብሄራዊ ቡድን አጥቂ ሚሮስላቭ ክሎሰ " ሃምልስን በዚህ ጊዜ መግጠም አልፈልግም" በማለት አድናቆት ችሮታል::

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Brook Genene - Sports Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Brook Genene - Sports Page:

Videos

Share