Zemen Television

Zemen Television በሀቀኛ መረጃ ትውልድ ይሰራል. የሀገር አንድነት ይሰምራል :: 🇺🇸
(2)

ሄንግዳ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የትንሳኤ በአል ይመኛል።
05/04/2024

ሄንግዳ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የትንሳኤ በአል ይመኛል።

ቢሸፍቱ የዋሀ ሀብትትና ልማትን አጣጥማ ግስጋሴ ላይ ናት!    Tessema Denekeበላብ አደርች ቀን (ዛሬ) የደብረዘይት ከተማ ውሎዬ መንፈሳዊ ቅናት አጭሮብኛል። በውቡ ፕራሚድ ሆቴል ነበ...
05/01/2024

ቢሸፍቱ የዋሀ ሀብትትና ልማትን አጣጥማ ግስጋሴ ላይ ናት!
Tessema Deneke
በላብ አደርች ቀን (ዛሬ) የደብረዘይት ከተማ ውሎዬ መንፈሳዊ ቅናት አጭሮብኛል። በውቡ ፕራሚድ ሆቴል ነበር ብዙ የቆየነው። ከተንጣለለው ሀይቅ በ50 ሜትር ርቀት ዳር የተገነባ ነው። ይኸው ሆቴል ሁለተኛውን ግዙፍ ግንባታ አጠናቆ ለማስመረቅ ድግስ ላይ ነው። በውሀው ጠርዝ ላይ ቀርቦ መገንባቱን የተለየ ውበት እንደሰጠው እየተነጋገርን ሳለ እያስጎበኘን ያለው ጓጀኛችን በስራ ክተትል ላይ ወዳለው የፖሮጀክቱ መሀንዲስ ወስዶን ተዋወቅነው።

ከተዋወቅነው በኋላ የውሀውና የሆቴሉ አወንታዊ መስተጋብር እያደነቅን "የሆቴሉ ፍሳሾች የውሀውን ተፈጥሮ አይጎዳውም ወይ? የሚል ጥያቄ አነሳንለት። እሱም አንዲህ አለ:"ቀደም ሲል በ50 ሜትር በፈር ዞን ትተን ነበር የምንገነባው፣ አሁን ግን ቴክኖሎጂው ስለዘመነ በውሀው ጠርዝ ላይ ቢገነባም የሚፈጠር ችግር የለም፤ የሆቴሉ ፍሳሽ እያጣራ ወደ-ንጽህ ውሀነት የሚቀይርና ሌላውን ዝቃጭ ወደ-ማዳበሪያነት የሚለውጥ ቴክኖሎጂ ተገጥሟል። የተጣራው ውሀና ማዳበሪያው ደግም በሆቴሉን ዙሪያና በሀይቁ ጥግ ለሚገኙ ተክሎች ምግብ ስለሚሆን ሆቴሉ የዉሀ ሀብትን የማጎልበትም ሚና አለው።" አመስግነን ተለያየን።

የፕራሚድ ሆቴልን ተሞክሮ ጠቀስኩ እንጂ ብዙዎች እንደ ኩርፍቱ፣ አሻም፣... በተመሳሳይ ሁኔታ ውሀዎችን አቅፈው የተገነቡና በእኛም ሰፈር ቢኖሩ የሚል በጎ ቅናት የሚፈጥሩ ናቸው።ከተማዋ እስከ ሰኔ የሚጠናቀቁ ግዙፍ ልማቶች እየተከናወኑባት ያለችም ናት። (በመንግስትና በወጭ ባለሀብቶች)። የበሬ ግንባር በሚያካክሉ የአማራ ክልል ከተሞች የማህበረ-ፖለቲካው የልማት ደንቃራነት ተገፎ የደብረዘይትን፣ የገዳ ሲቲንና የናዝሬትን አይነት ጉዞ እንዲጀመር ተመኘሁ። ይህ ምኞቴ የሚሳካው የአማራ ክልል ከተሞች የበሬ ግንባር አክለው እንዲቆዩ ያደረጋቸው ሳቢ ያልሆነ የአስተዳደር ስርዓትና ከኋላ ቀርነት ጋር የሚያያዝ የአስተሳሰብ ውቅር መሆኑን ታሳቢ አድርገን ከሰራንነው የሚል ምልከታም አለኝ ።

የመራዊ ጭፍጨፋ(Merawi Massacre,Ethiopia)
02/14/2024

የመራዊ ጭፍጨፋ(Merawi Massacre,Ethiopia)

በአማራ ክልል መራዊ ከተማ ቢያንስ 45 ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ‼️በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ መራዊ ከተማ፤ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ቢያንስ 4...
02/13/2024

በአማራ ክልል መራዊ ከተማ ቢያንስ 45 ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታወቀ‼️
በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ መራዊ ከተማ፤ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ቢያንስ 45 ሲቪል ሰዎችን “ለፋኖ ድጋፍ አድርጋችኋል” በሚል ምክንያት “ከህግ ውጭ መግደላቸውን” ማረጋገጡን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። ኮሚሽኑ ለጊዜው ብዛታቸውን ለማረጋገጥ ያልቻላቸው ሰዎችም፤ “የፋኖ አባላት ናቸው” በሚል ተጠርጥረው ከተያዙ በኋላ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በተመሳሳይ ሁኔታ መደገላቸውንም ገልጿል።
👉በርካታ ተጨማሪ መረጃዎች አሉ፣ይህን የቴሌግራም ቻናል ከስር ባለው ሊንክ join በማደረግ እና ለሌሎች በመጋበዝ ይከታተላሉ👇👇

02/01/2024

# የህልም ቤትዎ ቁልፍ!



ኢትዮጵያ እየሰለቀች ያለችው የመከራ ዱቄት ያልበሰሉ ፊደል ቀመሶች ከዘሩት አዝመራ የተገኘ በመሆኑ ነው!ጥራዝ ነጠቁ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ሁሉንም የሽህ ዓመታት የሀገረ-መንግስት ግንባታ ሂደቶ...
01/17/2024

ኢትዮጵያ እየሰለቀች ያለችው የመከራ ዱቄት ያልበሰሉ ፊደል ቀመሶች ከዘሩት አዝመራ የተገኘ በመሆኑ ነው!

ጥራዝ ነጠቁ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ሁሉንም የሽህ ዓመታት የሀገረ-መንግስት ግንባታ ሂደቶች በዜሮ አጣፍቶና የነበረውን ወዳልነበር ለመለወጥ ያደረገው ውክቢያ የአሁኑ ትውልድ መሸከም ያልቻለው እዳ ሆኖ ቀጥሏል። ምናባዊ የብሄር ጭቆና ታሪክ በማዋለድና ከዚሁ ስሁት ትርክት የመነጨ ማንነት ተኮር ሀገራዊ ቀውስን በማነበር፤ በ1943 ዓ.ም. የተረጋገጠውን የባህር በር ባለቤትነት መብት በማጨናገፍ፤ የግዛት እንድነትን በማናጋት፤ ቅርብ አዳሪና ግብታዊ የሆነ የፖለቲካ አየር በማንገስ፤ ወዘተ የተማሪዎችን እንቅስቃሴ የሚስተካከለው የለም። አብዛኞቹ የንቅናቄው መሪዎች ከ3ኛ ዓመት የኮሌጅ ትምህርት ያልዘለሉና በለጋ እውቀታቸው ድፍረት ያገኙ፣ ሀገራዊ ሁኔታን ከሚማሩት ትምህርት ጋር አመጋግቦ የመረዳት ብስለቱና ስክነቱ ያልነበራቸው ነበሩ። ጥቂት አውቀት አንዲሉ የወቅቱ ቁልፍ አንንቂዎች ማንንም የማያዳምጡ እንደነበሩ ነው ታሪክ የሚያስረዳው። የተማሪው አመጽና ዘርፈ ብዙ ግዝገዛው የንጉሱ ዙፋን ከነቀነቀ በኋላ ተደራጅቶ ስልጣን ላለመረከቡ አንዱ መነሻ ተቀናጅቶ መስራት የሚያስችል ብስለትና ልምድ ማጣት፣ አለመደማመጥና ራዕይ አልባነት ነበር።

በተማሪው እንቅስቃሴ ተገዝግዞ በመመንገል ላይ ያለውን የዘውድ ስርዓት በመተካት ክፍቱን የተጠቀመው የደርጉ ኮሚቴ አባላትም ከሻለቃና ከሻለቃ በታች የሆኑ ወታደሮች ስለነበሩ እጅግ ጥንቃቄ በሚጠይቁ ጉዳዮች ላይ በደመነፍስና በጅምላ ሲወስኑ እንደነበር የሚታወቅ ነው። በአሁናዊ ምሳሌ ለማስረዳት የደርግ ስብስብ የሰው ኃይል ብቃትና አለምን የመረዳት ብስለት በምሬ ወዳጆ የፋኖ ሰራዊት በአንድ ሻለቃ ውስጥ ከሚገኙ መኮንኖች በእጅጉ ያነሰ ጥርቅም ነበር። የደርግም አቅምም "ልጅ ያቦካው ነገር" ሆኖ እርሾ በመድፋት ነበር ስራ የጀመረው። ኋላ ላይ ወታደሩ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ተዋናዮቹንና ግራ ዘመም "ተራማጆችን በማካትት በተማሪዎች ይቀነቀን የነበረውን አስተሳሰብ ከነሰንኮፉ መቀበልን ነበር የመረጠው። በእውነቱ በተማሪዎች ንቅናቄ ወቅት ከተዘሩ ስሁት ትርክቶችና የርዕዮተ-አለም ቅኝት ሊወጣ የሚችልበት እድል አልነበረውም። ገና በጠዋቱ ግንኙነቶች ሁሉ አስረሽ ምችው አይነት ወደመሆን ተቀይሮ አንዱ በሌላው ላይ ጦር በመስበቅ ውሎ ማደር ተዘወተረ። የሰክነት አየር ጠፋ። የሀገሪቱ እጣ-ፈንታ በነጭ-ቀይ ሽብር መናወጥ ሆነ።

የዛን ዘመን የልጅ ቡኮ በፈጠረው ሀገራዊ ቃር ምክንያት የእኛም ትውልድ ያልበላውን እዳ እየከፈለ ይገኛል። ዛሬም ልክ እንደትላንቱ በቡድኖች መካከል የማይጸና ወዳጅነትና ቅጽበታዊ መከዳዳት፣ እንደሀገር ለውጫዊ አደጋ መጋለጥ፣ የፖለቲካዊ ውሳኔዎች የግጭት መንስኤ መሆንና የጥይት ባሩድ የማይሸተው ቅዬ እየታጣ መምጣት ተጠቃሽ ኩነቶች ናቸው። በዶ/ር አብይ አህመድ እያራቡት ያለው አሁናዊ ተደማሪ ሀገራዊ መቃወስ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ተቀጽላና በጎረምሳ እብሪት የሚነዳ አይነት ክልፍልፍ የፖለቲካ እርምጃ የወለደው ነው። አብይ የዋለልኝ መኮንን አድናቂ መሆናቸው ላስተዋ ሰውየው የጥራዝ ነጠቅ እንቅስቃሴው ሎሌ ስለመሆናቸው አመላካች ነው።

መፍትሄው በጥራዝ ነጠቅ እውቀትና በልጅ አዕምሮ ሀገር ለመምራት የሚፈጥረውን አደጋ በመረዳት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ እርምጃ መቀነስ ነው። ማለትም ከአዘቅቱ መውጣት የሚቻለው ፖለቲካው "ልጅ ያቦካው አይነት" መሆኑ መቅረት ሲችል ነው።

10/17/2023

ወቅታዊ የአማራ ኃይሎች የፖለቲካዊ ድርድር አጀንዳዎች!
==+==++===++===
1). አማራ ከየተኛውም አካል ወረራና ጥቃት እንዳይደርስበት የፌደራል መንግስት ስለሚፈጽማቸው መዋቅራዊ ስራዎች የመተማመኛ ሰነድ መፈራረም፤ በለተይም በህወሀት ወረራ ላለመፈጸሙ ዋስትና የሚሰጥ የድርጊት መርሀ-ግብር እንዲኖር መስመማት፤
2). በክሌሉ በየተኛውም አደገኛ ወንጀል የተሳተፉ አካላትን ለመዳኘት የትብብር ስምምነት ማድረግ፤
3). በሰሜኑ ጦርነት የመንግስትን ጥሪ ተከትሎ በፋኖነት ተሰልፈው መሰዋዕት ሲከፍሉ የነበሩ ሀቀኞችን እጣ ፋንታን በተመለከተ ቁርጠኛ የፓለቲካ ውሳኔ የሚሻ ስምምነትን በመፈራረም፤
4). በውጊያው ወቅት ለሞቱና አካል ጉዳተኛ ለሆኑት የሚደረግን ድጋፍ እንዲሁም ያለምንም የመንግስት ድጋፍ ለሁለት ዓመታት የግል ኑሯቸውን ትተው በህግ ማስከበር ሲሳተፋ ለነበሩት የማቋቋሚያ መርሀ-ግብር እንዲዘጋጅና በተቋም እንዲመራ መስማማት፤

5). በሌሎች የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች በሚመለከቱ ቁልፍ ጉዳዩች ላይ ለመወያየት ለከናወን በታቀደው ሀገራዊ የምክክር መድረክ አካታች የተሳትፎ አካታችነት እንዲኖር መተማመን፤
6). በወልቃይት ለአማራ ህዝብ ህልውና ዋስትና የሚሰጥ የህግና የፖለቲካ ውሳኔ በሚሰጥበት አግባብ መምከርና መስማማት፤
7). የአማራን ህዝብ ከኦሮሚያ የማጽዳት ድርጊትን ለማስቆም የፌደራሉ መንግስት አዲስ የፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲያዘጋጅ መስማማት እና ለተፈናቃዮች የደህንነት ዋስትና የሚሰጥ እና መልሶ የሚያደራጅ ተቋማዊ አሰራር ዝርጋታ፤

የአፋር፣ የሶማሊ፣ የሲዳማ፣ የጉራጌ፣ የአማራ፣ የየም፣ የጋምቤላ፣.. ህዝብ ምንም አይኑረው በሚል እየተቀነቀነ ያለው የኦሮሞ ፖለቲካ በልኩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አንድ አካል መሆን እየተሳነው መ...
10/16/2023

የአፋር፣ የሶማሊ፣ የሲዳማ፣ የጉራጌ፣ የአማራ፣ የየም፣ የጋምቤላ፣.. ህዝብ ምንም አይኑረው በሚል እየተቀነቀነ ያለው የኦሮሞ ፖለቲካ በልኩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አንድ አካል መሆን እየተሳነው መሆኑ ማሳያ። ራሱን ጠልፎ የሚጠል ግፋ ሲልም የእርስ በእርስ ጦርነት አቀጣጣይ ነው።

10/16/2023

ለህዝብ የትኛው ሽግግር ይጠቅም ይሆን? ከፖለቲካ ወደ ፓስተርነት የሚደረግ ሽግግር ወይስ ከፓስተርነት ወደፖለቲካ? የሀሳቡ መነሻ የኃይለማሪያም ደሳለኝ ስብከት ነው

እኝህ አዛውንት የጦር ጀነራል ሀገር ቤት ቢመጡና እውነተኛውን ጨዋታ በእስታዲዮም ሆነው ቢያዩት መልካም ነበር።
08/13/2023

እኝህ አዛውንት የጦር ጀነራል ሀገር ቤት ቢመጡና እውነተኛውን ጨዋታ በእስታዲዮም ሆነው ቢያዩት መልካም ነበር።

08/12/2023

This is not a Satire

08/09/2023

ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳዬች የተሰጠ መግለጫ፥
*****
እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ በረጂሙ የሀገራችን ታሪክ ውስጥ ከሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በአንድነት ውጣ-ውረዶችን ያሳለፈ፣ አስደናቂ የሆኑ የአርበኝነት ገድሎችን፣ ማሕበራዊ እና ቤተሰባዊ እሴቶችን የሚጋራ ሀገር ወዳድ ህዝብ ነው።

ሆኖም አላዋቂ እና ፅንፈኛ የሆኑ የግራ ዘመም ኃይሎች በአማራ ህዝብ ላይ ፍፁም የተዛባና መሰረተ-ቢስ የሆነ የሀሰት ትርክት በመፃፍ ለበርካታ ዓስርተ-አመታት የጥላቻ እና የጥቃት ሰለባ እንዲሆን አድርገውታል። በዚህ ምክንያት የአማራ ህዝብ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመቶች ተፈፅመውበታል።

በተለይም አማራን መፈረጅና ማጥቃት መደበኛ የፖለቲካ ማደራጃ ያደረጉ ኃይሎች በታሪክ ክፍተት አልፈው ስልጣን ከያዙ በኋላ "አማራ-ጠልነትን" የሀገራዊ ስርዓት እና መዋቅር ማደራጃ አድርገውት ቆይተዋል። የአማራ ህዝብ ከመላው ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጋር በመተባበርና ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሎ ባደረገው መራር ትግልም በወቅቱ የነበረውን ዘረኛ መንግስታዊ ስርዓት ከስልጣን ለማስወገድ መቻሉ የቅርብ ትዝታ ነው።

ነገር ግን ከዚህ ድል በኋላ ታይቶ የነበረው የአማራ ህዝብ ተስፋ ያደረገበትና በስፋት የደገፈው "የለውጥ ሂደት" ከፍትህና እኩልነት አንጻር እንደታሰበው ውጤታማ ሊሆን ሳይችል ቀርቶ ህዝባችን ዛሬም በበዛ ምስቅልቅል ውስጥ እያለፈ ይገኛል። በመንግስት በኩል ከፍተኛ የአመራር ችግር፣ የጠራ ሀገራዊ ራዕይ ዕጦትና በዚህ ምክንያት የተፈፀሙት ሰፊ ማንነት ተኮር ጭፍጨፋዎችና ማፈናቀሎች እንዲሁም ችግሮችን በወቅቱ እና ባግባቡ መፍታት አለመቻል በሰፊው የታየበት ወቅት ነው።

በሀገራችን የተለያዩ አካባቢወች ከተፈፀሙት ብሄር ተኮር ጥቃቶች በተጨማሪ በአማራ ክልል ውስጥ በጦርነቱ ወቅት ለተፈፀሙ ሰብዓዊ ጥቃቶችና ቁሳዊ ውድመቶች በድህረ-ጦርነት ወቅት ተገቢው ስነልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ የመልሶ ማቋቋም ስራ አለመሰራቱ፣ የሰነበቱ ጥያቄዎች ዛሬም ድረስ ግልጽነት ያልተፈጠረባቸው በመሆኑ፣ አጠቃላይ ለህዝብ አጀንዳወች በቂ መድረክ ባለመፈጠሩ ምክንያት ህዝባችን ለብሶት እንዲጋለጥ ሆኗል። በተለይ በሰሜኑ ጦርነት ማግስት የተካሄዱ የሰላም ስምምነቶች የአፈጻጸም ግልጸኝነት የጎደላቸው በመሆናቸው ቀድሞ የነበሩ ችግሮችን ይበልጥ ማባባሱና ህዝቡንም ለከፍተኛ ጥርጣሬ በማጋለጥ የህዝቡ ተገቢ ጥያቄወች ለሴራ ትንተናና ለውዥንብር ጭምር ምቹ እንዲሆኑ አድርጓል።

የአማራ ክልል መንግስት በጦርነቱና በድህረ-ጦርነት ወቅት ያሳየው አጠቃላይ የአመራር ድክመት፣ የህዝብን ሰላም የሚያደፈርሱ በየሰፈሩ የሚስተዋሉ እንቅስቃሴዎችን ለማረም መድረክ ያለመፍጠር፣ ህግ ያለማስከበር፣ ህዝባችንን ለሴራ ትንተና ተጋላጭ እንዲሆን የሚቀነቀኑ አፍራሽ ጥሪወችና ከሌሎች ህዝቦች የሚነጥሉ ቅስቀሳወችን የሚያደርጉ ግለሰቦችና ሚዲያወች በህዝባችን ላይ የሚደፉት የየዕለት አጀንዳ ተገቢው ክትትልና የእርምት እርምጃ ስላልተደረገበት፣ ይህንን ለማድረግም ፍላጎት ባለማሳየት ህዝብን ለእረፍት የለሽ አለመረጋጋት በመዳረግ፣ የክልሉ መንግስት የመሪነት ሚናውን መወጣት ባለመቻሉ ብሎም አንዳንድ ላልተገቡ እንቅስቃሴወች መስፋፋት የተመቸ ሁኔታን በመፍጠሩና ተባባሪ የመሆን አዝማሚያዎችን ጭምር ማሳየቱ ለችግሮች መፈጠር እና መባባስ ዋና ድርሻ እንዳለው ሊሰመርበት የሚገባ ሲሆን የፌዴራል መንግስቱም ለነዚህ ሁሉ ችግሮች መፈጠር አቻ ተጠያቂ ነው።
በተለይም ከላይ እስከታች ያለው የክልሉ አመራር ለህዝባችን ተገቢውን መንግስታዊ አመራር ከመስጠት ይልቅ የሰፈርና የጎጥ አጀንዳወች ላይ ተቸክሎ በሚያደርገው የመነጣጠቅና የመጠላለፍ ስምሪት ህዝባችንን ጨርሶ በመርሳት ጥያቄወቹ ምላሽ አጥተው ለከፍተኛ ምሬት እንዲወድቅ አድርጎታል።

የክልሉ መንግስት በሀገር አቀፍ ደረጃ የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች በውይይትና በድርድር የማስፈፀም ቁርጠኝነትና ብቃት እንደሌለው እና በጭንቅ ወቅቶች ህዝቡን ከማረጋጋት ይልቅ ለመከራ ዳርጎ የሚሸሸና የሚሸሸግ መሆኑም በተደጋጋሚ ታይቷል፣ የአማራን ህዝብ አንድነት ከማጠናከርም ይልቅ ለጠባብ ግለሰባዊና የኋላቀር ፖለቲካ መገለጫ በሆኑ ቡድናዊ አጀንዳዎች የተወጠረ በመሆኑ ከህዝብ እንዲነጠልና ጨርሶ አመኔታ እንዲያጣ አድርጎታል።

የክልሉ አመራር ህዝቡን ለማወያየትም ይሁን ጥያቄዎቹን ለመስማትና ለመመለስ ፍቃደኛ ሳይሆን ቆይቷል። ስለሆነም የአማራ ህዝብ በየአካባቢው ለሚደርሱበት ዘር ተኮር ጥቃቶችና ላሉበት ውስብስብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍትሄ የሚሰጥ አካል መጥፋት፣ በጦርነት የደረሰበትን መጎሳቆልና ውድመት የሚያክም የተሟላ የመልሶ ማቋቋም መርሀግብር ያለመኖር ለተፈጠሩ ችግሮች ተጠቃሽ ምክንያትና አባባሽ ሆኗል ብለን እናምናለን።

ከሰሞኑ በአማራ ክልል ውስጥ የተከሰተው የሰላም መደፍረስ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ የማይጠበቅ ክስተት አልነበረም። ድርጅታችን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ይህንን አስቀድሞ በማየት መንግስት ከሚሰራቸው ተደጋጋሚና ተከታታይ ስህተቶች እንዲጠበቅና የመፍትሄ ጥረት እንዲያደር ስናሳስብ ስለመቆየታችን የቀደሙ መግለጫወቻችን ለዚሁ ምስክር ናቸው። ስለሆነም መፍትሄ ይፈልጉ የነበሩ ጥያቄወች አዳማጭ በማጣታቸው ግልጸኝነት ስላላገኙ፣ የክልሉ መንግስትና የገዥው ብልፅግና ደንታ ቢስነት ገደብ በማጣቱ የአማራ ህዝብ ለተለያዩ አጀንጃ ሰጭዎች ማለትም ህዝባችንን ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር የሚያቃቅሩ፣ ወጣቶቻችን ያልተገባ መሰዋዕትነት እንዲከፍሉ፣ ተቋማትንና የሀገር ሽማግሌዎችን፣ የእምነት አባቶችን የማክበር እሴት እንዳይኖረው በመቀስቀስ ለሚያወናብዱ አካላት መደላድል ፈጥሮላቸው ቆይቷል። የክልሉ መንግስት ብቃት ማነስና ወካይ አለመሆን ያስከተለው ምስቅልቅልም ነው። የአማራ ልሂቃን እና የፖለቲካ ሀይሎች እንዲሁም የተለያዩ የሲቪክ አደረጃጀቶች የራሳቸው ድክመት እንዳለ ሁሉ የክልሉ መንግስት እነዚህ አካላት በጋራ እንዳይመክሩና መፍትሄ እንዳያፈላልጉ በስልት መድረክ መነፈጋቸው ተደማሪ ችግር ሆኖ መቆየቱንም አብን ያምናል።

በተጓዳኝ በሰፊ ማእቀፍ ሊመከርባቸው የሚገቡ አንገብጋቢ የህዝብ ጉዳዬች ድንገት የተላለፉ ውሳኔዎች ያስከተሉት ውጤትም ነው። በዚህ ረገድ ሀገራችንና ህዝባችን ጥቃት በተፈጸመባቸው ወቅት የሕዝብ ደጀን በመሆን ከኢትዮጵያዊ ወገኖች ጋር በጋራ ቆመው የሀገር ህልውና በማስጠበቅ ታሪካዊ ሚና የተጫወቱትን የአማራ ልዩ ሀይል አባላት በድንገተኛ መንግስታዊ የውሳኔ እርምጃ ሰራዊቱን መልሶ ማዋቀር ባለመቻሉና ለውዥንብር ተጋልጦ እንዲበተን መሆኑ ከሰሞኑ ለተፈጠረው ችግር ተጨማሪ ምክንያትና አባባሽ ነው ብለንም እናምናለን።

በተመሳሳይ ለሀገር አንድነት፣ ለህዝብ ህልውና፣ ለክብርና ነፃነት የተዋደቁና ዋጋ የከፈሉ የፋኖ አባላቶች ድህረ ጦርነት ወደመደበኛ ህይወት የሚመለሱበት ግልጽና ፈጣን ሀገራዊም ሆነ ክልላዊ መርሀግብር ባለመዘጋጀቱ፣ ታጋዮቹንም ለማወያየትና መፍትሄ ለመፈለግ በቂ መድረክ ባለመፈጠሩ፣ ይልቁንም በችኩል መፈረጃቸው ብሎም የፋኖነት እሴት ከሌላቸውና በህልውና ትግሉ ወቅት ተሳትፎ ካላደረጉ አካላት ጋር አዳብሎ የፋኖን ትግልና አስተዋጽኦ ለማሳነስና በአሉታዊ መልኩ ለመበየን የተሄደበት መንገድና አያያዝ በብዙወች ዘንድ መከፋትን የፈጠረ መሆኑ ሊናቅ አይገባውም።

በተጨማሪም በሀገሪቱ ሰላም መደፍረስ በሁከትና በጥላቻ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የተሰማሩ ልዩልዩ አካላት እና በአማራ ህዝብ ስም እየማሉ ህዝባችን ጥያቄወቹን ብሎም ስርዓታዊ በደሉን በሰላማዊ መንገድ መታገሉን አቁሞ ይልቁንም ወደ እርስ በእርስ ግጭት እንዲገባ የሚቀሰቅሱ ኃይሎች ድርሻ ቀላል እንዳልሆነ አብን ያምናል።

ድርጅታችን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በተደጋጋሚ ላቀረባቸው ጥሪዎች ስርዓቱ ጆሮ ባለመሰጠቱ እና የተሰነዘሩ የመፍትሄ ሀሳቦችንም ገቢራዊ ለማድረግ ባለመሞከሩ ችግሮች እየተጠራቀሙ መምጣታቸው ክልሉን ወደ ለየለት ቀውስ ከቶታል።

በጥቅሉ ከላይ የተገለጹት ተደራራቢ ተግዳሮቶች ተዳምረው ህዝቡን ለውስብስብ ችግር ከመዳረግ ባለፈ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት ህዝባችን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተዳደር ስር እንዲወድቅ ሆኗል። ስለሆነም ድርጅታችን አብን እንደሚከተለው አቋሙን ያሳውቃል:-

1). የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አተገባበር በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲመራ፣ በአጭር ግዜ እንዲያልቅ፣ አዋጁን ለማስፈፀም የተሰማሩ አካላትም ከማንነት ተኮር ፍረጃዎች፣ ወከባዎች፣ ዘፈቀደ እስራትና አካላዊ ጥቃቶችን ባለመፈጸም እንዲሁም በየትኛውም አካል እንዳይፈጸሙ ጥበቃ የማድረግ ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አጥብቀን ከመጠየቅ በተጨማሪ የፌደራሉ መንግስት አካላት ሚና ለህዝቡ የሚመጥን አስተዳደር እንዲዋቀር መደላድል በመፍጠር እንዲወሰን፣ ህዝባዊ የውይይት መድረኮችም እንዲፈጠሩ፣ ህዝቡም የሰላም ጥረቶችን እንዲደግፍ ጥሪ እናቀርባለን። ክልሉ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተዳደር በአፋጣኝ እንዲወጣም አብን ይጠይቃል።

2). በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ልዩልዩ አዎንታዊና አሉታዊ ምክንያቶች ቢኖሩም በዋናነት የፌዴራሉና በተለይም የክልሉ መንግስት ሊሰሯቸው ሲገባ ያልሰሯቸው ስራወች ድምር ውጤት መሆኑ ታምኖ ኃላፊነትን በመውሰድ ችግሮቹን ለዘለቄታዊ ሰላም በውይይት ለመፍታት ትኩረት እንዲሰጥ ብሎም ዘላቂ ሰላም ሊያመጣ የሚችል መፍትሄ በህዝብ እጅ ያለ እና ከህዝብ የሚመነጭ በመሆኑ ሁሉንም ባለድርሻዎች ያካተቱ መድረኮች እየተዘጋጁ የህዝቡ የመደመጥ መብት እንዲከበር እንጠይቃለን።

3). በክልሉ የተከሰተው ችግር ዋነኛ ማጠንጠኛ የመንግስታዊ ስርዓቱ እና የክልሉ የአመራር ክፍተትና ብልሽት በመሆኑ በቀጣይ ማህበረሰቡን የሚመጥን እና በማህበረሰቡ የሚታመንበት አደረጃጀት በየደረጃው ተመስርቶ የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ተቆጥረው ግልጸኝነት እና መተማመን እንዲፈጠርባቸውና ተቋማዊ በሆነ አግባብ ምላሽ እንዲያገኙ እንዲደረግ አበክረን እናሳስባለን።

4). በተቻኮለ የአደረጃጀት ለውጥ ምክንያት የተበተነውን ልዩ ሀይል እና በህልውና ትግሉ ውስጥ አስተዋጽኦ የነበራቸውን የፋኖ አባላት በተመለከተ የፌደራልና የአማራ ክልል መንግስት የጋራ ኃላፊነት ወስደው በሀቀኛ ውይይቶች ላይ የተመሠረተ የሁለቱንም አካላት ክብርና አበርክቶ የሚመጥን መርሀ-ግብር በአስቸኳይ በመንደፍ ገቢራዊ ስራ እንዲሰሩ እንጠይቃለን።

5). በየትኛውም አሰላለፍ እና አግባብ ስለአማራ ህዝብ የተሰለፉ ሀይሎች ጦርነት ዘላቂ ጥቅምን ለማረጋገጥ አስቻይ ባለመሆኑና ይልቁንም ህዝብን ለተደራራቢ የማህበራዊ፣ ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ድቀት ስለሚዳርግ ለሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሄዎች ተገቢውን ስፍራ ሰጥተው ለክልሉ ሰላም መመለስ ታራካዊ ድርሻቸውን እንዲወጡ አብን አበክሮ ይጠይቃል።

6). መላው የአማራ ህዝብ ከሌላው የሀገሪቱ ህዝብ ጋር ያለውን የወንድማማችነት እሴቶች ከሚንዱ ቅስቀሳዎች፤ በራሱ እና በልጆቹ የተመሰረቱ ተቋማትን በተለይም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከሚያጠለሹ መልዕክቶች እንዲሁም የአማራ ህዝብ ማህበራዊ ረፍት እንዲያጣ ከሚመኙ አካላት በስልት የሚሰጡትን አጀንዳዎች በመጸየፍ ወደ ሰላም መድረክ የሚያመሩ መንገዶችን ሁሉ ለመጥረግ አቅሙ የፈቀደውን ርብርብ እንዲያደርግ በአደራ ጭምር እናሳስባለን።

7). መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች የሀሰት ትርክት እና መዋቅራዊ ስርዓት የወለዳቸው፣ ከለውጡ ማግስትም ወዲህ ቢሆን ምላሽ ያላገኙ ብሎም በጦርነት የተቀጠቀጠና ክልሉ አቅሙ ከሚችለው በላይ በተፈናቃይ ወገኖች የጎበጠበት፣ እንዲሁም ተፈናቃይ የታጨቀበት የሀገሪቱ ክፍል መሆኑን በማስታወስና የህዝባችንን ብሶት በተገቢው በመረዳት ህዝባችን ሲያነሳቸው ለቆዩ የከረሙ የፍትህና የእኩልነት ጥያቄወች አጋር ሆናችሁ እንድትቆሙ እንጠይቃለን።

8). ለሰብአዊ መብት ድርጅቶች
ከጦርነት ቅጥቀጣው ባላገገመው በአማራ ክልል ውስጥ የተከሰተው ግጭት እና የታወጀውን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አስተዳደር ተከትሎ የሚፈጠሩ ሰብአዊ ችግሮችን ለመከታተልና ልዩ ልዩ የህይወት አድን ድጋፎችን ታደርጉ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን።

9). ከወቅታዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በአዲስ አበባና በአማራ ክልል ለእስር የተዳረጉ ሰወች ጉዳያቸው በአስቸኳይ ወደ ህግ ቀርቦ እንዲጣራና ተገቢው መፍትሄ እንዲሰጣቸው ስንል እናሳስባለን።

11). ታውቀው ያደሩ የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚያገኙ በአደባባይ ዋሰትና እንዲሰጥ

12). አሁን በክልሉ ለተፈጠረው አጠቃላይ የጸጥታ መደፍረስ፣ ለደረሰው ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ መንግስት ኃላፊነት እንዲወስድ እና ህዝቡን ይቅርታ እንዲጠይቅ ጥሪ እናቀርባለን።

13). ግጭትና የሰላም እጦት ተወግዶ ዘላቂ ሰላምና ልማት ለሀገራችን ህዝቦች እውን እንዲሆን ሁላችንም ለዚሁ እንድንቆም እያሳሰብን መንግስት ለውይይት ክፍት እንዲሆንና የሰላም ጥረቶችን ሁሉ አሟጦ እንዲጠቀም እናሳስባለን።

14). የወልቃይትና የራያ ጉዳይ ግልጽ መፍትሄ አለማግኘቱ፣ ፍትሃዊ የመሰረተ ልማት ስርጭት ጥያቄ፣ ፍትሃዊ የበጀት ክፍፍል ጥያቄ ፣ የአርሶአደሩ የማዳበሪያ ጥያቄ፣ ገበሬው ያመረተውንም ወደገበያ እንዳይወስድ ተደጋጋሚ የመንገድ መዘጋትና መስተጓጎል ወዘተ ጉዳዮች በቂ መንግስታዊ ትኩረት ሳያገኙ መቆየታቸው ህዝባችንን ለከፍተኛ ምሬት ዳርገውት በመቆየታቸው ለአፍራሽ ፕሮፓንዳ እና ለከፍተኛ ጥርጣሬ ጭምር እንዲጋለጥ አድርገውታል። እናም መንግስት በነዚህ ጉዳዮች ከህዝብ ጋር ግልጽ ውይይት በማድረግ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ እንጠይቃለን።

15). በተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ንጹሀን ሰላማዊ ዜጎች የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን፣ አካላዊ ጉዳት ለደረሰባቸውም ቶሎ ማገገምን እንመኛለን።

****
በመጨረሻም ለፓርቲአችን የጠቅላላ ጉባኤ አባላት፤ ፓርቲአችን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ነሀሴ 6/7 ለማካሄድ ሲዘጋጅበት የቆየው ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በተፈጠረው ወቅታዊ የሰላም እጦት ምክንያት ላልተወሰነ ግዜ እንዲራዘም የአስፈጻሚ ኮሚቴው ባሳለፍነው እሁድ ሀምሌ 30 ተሰብስቦ የወሰነ መሆኑን እያሳወቅን የሰላሙ ሁኔታ ሲሻሻልና አስቻይ ሁኔታ ሲፈጠር የጉባኤ ቀን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን።

ነሀሴ 03/2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ሸዋ፣ ኢትዮጵያ

የተባበሩት መንግሥታት ባለሙያዎች ኢትዮጵያ ኤርትራውያን ስደተኞችን በግዳጅ ወደ አገራቸው መመለስ እንድታቆም ጠየቁ።የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ዛሬ ሐምሌ 06/201...
07/14/2023

የተባበሩት መንግሥታት ባለሙያዎች ኢትዮጵያ ኤርትራውያን ስደተኞችን በግዳጅ ወደ አገራቸው መመለስ እንድታቆም ጠየቁ።
የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ዛሬ ሐምሌ 06/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ ኢትዮጵያ በሰኔ ወር መጨረሻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያንን በግዳጅ ማባረሯን ጠቅሶ ድርጊቱን አውግዟል።
ተጨማሪ ስደተኞችን በግዳጅ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉ በአስቸኳይ እንዲቆም እንዲሁም የጥገኝነት ጠያቂዎች እና ስደተኞች እስር እንዲቆምም ጠይቀዋል።
“በዓለም አቀፍ የስደተኞች ሕግ መሠረት በጅምላ ስደተኞችን ማባረር የተከለከለ ነው” ያሉት ባለሙያዎቹ፣ ስደተኞቹ በጅምላ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ በመገደዳቸው ከሚገጥማቸው የደኅንነት ስጋት በተጨማሪ ወላጆች እና ልጆች እንዲሁም የቤተሰብ አባላት እንዲነጣጠሉ አደርጓል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በቅርቡ ባወጣው ሪፖርትም ሕጻናትን ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጉት ኤርትራውያን ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በኃይል ወደ ኤርትራ እንዲመለሱ ከተደረጉ በኋላ ደኅንነታቸው አሳሳቢ ነው ብሎ ነበር።
ሆኖም የኢትዮጵያ ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የተደረጉት ስደተኞች ወይም ጥገኝነት ጠያቂዎች አይደሉም ብሏል።
የተመድ ባለሙያዎች በርካታ ታማኝ ምንጮችን ጠቅሰው እንዳሉት ግን እንዲመለሱ ከተገደዱት መካከል በስደተኝነት የተመዘገቡ እንዲሁም ያልተመዘገቡ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ይገኙበታል።
ኤርትራውያኑ የኢምግሬሽንን ሕግ ጥሰዋል በሚል ያለክስ፣ ያለጠበቃ እና ያለፍርድ ሒደት የዘፈቀደ እስር መቀጠሉን የሚያሳዩ ሪፖርቶች መኖራቸውን የገለጹት ባለሙያዎቹ፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራውያን ያሉበት ሁኔታ እጅግ እንዳሳሰባቸው የመንግሥታቱ ድርጅት ባለሙያዎች ገልጸዋል።

07/11/2023

“ማኅበረ ሰላማ ዘትግራይ ቤተ ክህነት፤”
በተቀደሰው አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ስም ያልተቀ ደሰ ሥራ፤(ቀሲስ ሓጎስ ፍሥሐ ጽዮን ተክለ ማርያም በትግርኛ ጽፎት ወደ አማርኛ የተተረጎመ)።

አሁንስ ለሕዝቡ እንናገራለን
"ገንጥሎ ከትግራይ ኤጲስ ቆጶሳትን የማሾም” ፕሮጀክት
************
በሓጎስ ፍስሓ ጽዮን ተ/ማርያም (ቀሲስ)
ግንቦት 2015
ትርጉም በዝግጅት ክፍል

ለትግራይ ከትግራይ ዐሥር ኤጲስ ቆጶሳትን እንሾማ ለን ከተባለ ትንሽ ቆይቷል።ምን አልባት ብዙ ሰው የሰ ማው ግን ከሰሞኑ ግንቦት 24 2015 ዓ/ም በሚድያ ከተነገረ በኋላ ነው።እዚህ ትግራይ የምንገኝ ካህናት እርስ በርሳችን እንዲሁም ከብዙ ምዕመናን ጋር በዚህ ጉዳይ ተነጋግረናል።ሁላችንም በጋራ የጠየቅነው “ለመሆኑ ይህ ራስን ገንጥሎ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፈቃድ ውጭ የሚደረገው ሹመት ለትግራይ ሕዝብ የሚያመጣው ጥቅም ምንድር ነው?” የሚል ነው።በተሠራብን ግፍ ቤተሰቦቻችንን በክፉ ጦርነት ላጣን፤ተምረን እንዳልተማርንና እያለን እንደሌለን ሁነን እጅግ በሚያሳፍር ሁኔታ ልመና ለወጣን፤ በጦር ነቱ ምክንያት አካለ ስንኩል ሁነን የሰው እጅ አይተን እንድንኖር በግፍ ለተፈረደብን የሚደረገው የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ምንድር ነው ፋይዳው? የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ቤተ ክህነት ተመሥርቶ ያመጣ ልን ጥቅም ምንድር ነው? ምን ተቀየረ? ምንስ ተለወጠ? ዓላማውስ ምንድር ነው?

ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስን ቢቢሲ ትግርኛ:- “ኤጲስ ቆጶሳትን ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፈቃድ ውጭ መሾሙ ጥቅሙ ምንድር ነው?”ብሎ ሲጠይ ቃቸው እንዲህ ብለው መለሱለት። “ ለሕዝባችን ደስታ ነው፥የሕዝባችንን ልብ የሚያረሰ ርስ ነው ”።አይ ጋዜጠኛ! ምን ቢበድሉህ ነው እንዲህ ያሳጣሃቸው? እያወቅህ።እሳቸው ምንም እንደማያ ውቁ።ከሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት እንዳቸው እንኳን የዚ ህን ጥያቄ መልስ አያውቁትም።

የግንቦት 24ቱን ጨምሮ በየሚድያው ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት በንባብ የሚያቀርቡትን አንዱንም መግለጫ አልጻፉትም ወይመ‍እ አላጻፉትም።ረቂቁን እንዲያዩ ትና ለሚድያ ከመቅረቡ በፊት ሀሳብ እንዲሰጡበት እንኳን እድል አልተሰጣቸውም።ታድያ ማን ነው? እየ ጻፈ የሚያድላቸው።ማን ነው? ከኋላ ሁኖ የሚዘውራ ቸው።ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፈቃድ ውጭ እንዲሁም ቀኖና ቤተ ክርስትያን እየጣሰ ኤጲስ ቆጶሳ ትን እንዲሾሙ የሚወተውተው ማን ነው? የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ቤተ ክህነት የሚባል መሥርቶ የሚዘውረው ማን ነው? መሪዎቹና ዘዋሪዎቹ የተለ ያየ ዓላማ ያላቸው ሁለት አካላት ናቸው።

1ኛ/የፖለቲካ ዓላማ ያላቸው አካላት ናቸው፤ከአንድ ዓመት በፊት ሕወሃት በትግራይ የሚገኝ እያንዳንዱ ቤተ እምነት በሚድያ እየወጣ አዲስ አበባ ከሚገኘው ማዕከሉ መገንጠሉን እንዲያውጁ አደረገች ።”መን በረ ሰላማ የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት” የሚባልም ለኦርቶዶካሳዊት ቤተ ክርስትያን አቋቋ መች።የሌሎች ቤተ እምነቶች እንዲሁ አጃቢዎች ስለነበሩ ጦሩነቱ ቆሞ ጦረኞቹ ተቃቅፈው ሲሳሳሙ ቤተ እምነቶቹም ከማዕከላዊ አሰተዳደራቸው ጋር እንደገና ተስማምተው ቀጠሉ።ኦርቶዶካሳዊት ቤተ ክርስትያንን ግን ሕወሃት በደንብ ጠርንፋ በመያዝ በፖለቲካ ላልተሳካው ዓላማ ቤተ ክርስትያንን መያዣ አድርጋ ለወደቀው ፖለቲካ ማገገሚያ፥ለተበታተነው ደጋፊዎቿ መሰብሰብያ እና ለወደ ፊቱ ፖለቲካዋ መቀ ስቀሻ አድርገዋለች።ለዚህም ይረዳት ዘንድ አባቶችን ዕለት ዕለት የሚከታተል፥የሚያወጡትን መግለጫ ዎች የሚጽፍ ሦስት ብርቱ ካድሬዎች ያሉበት ቡድን አቋቁማለች።

ይህ በሓለቃ ጸጋየ የሚመራው የካድሬዎች ቡድን ሃይማኖታዊ ዓላማ ይዘው ሕወሃትን ተጠቅመው ኦርቶዶካሳዊት ቤተ ክርስትያንን የመበታትን አጀንዳ ለሚያራምዱት ተሃድሶ መናፍቃን የሚሠራ ነው።

2ኛ/ሃይማኖታዊ ተልዕኮ ያላቸው አካላት ናቸው፤
ይህ ሃይማኖታዊ የሆነው ገፊ ምክንያት ዋናው በትግ ራይ ለሚገኙ አባቶች ተገንጥለናል፥ተለይተናል፥ኤጲስ ቆጶሳትንም አንሾማለን እንዲሉ የሚያደርገው ነው። ተሃድሶ መናፍቃን በመላው ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ከብዙ ሥል ጠና በኋላ ጠንካራ አደረጃጀት ፈጥረው በ1990ዎቹ እጅግ ተጠናክረው በየሰንበት ትምህርት ቤቱ እና በየ ገዳማቱ ተበተኑ።ነገር ግን እንዳሰቡት ሳይሆን በማኅ በረ ቅዱሳን መሪነት ወጣቱ ከየቦታው እየለቀመ አጋ ለጣቸው።በትግራይ ደብረ ዳሞ ሳይቀር በመግባት መነኮሳትን ለማስኮብለል ሲሞክሩ፥ደብረ አባይ ተማሪ ዎችን ሲያግባቡ እና ከእንዳ ማርያም ጀምረው ሰን በት ተማሪዎችን ለመቀሰጥ ሲጥሩ ምንም ማጭበር በር በማይችሉበት መረጃ እየተያዙ ተለቀሙ።የተወሰ ኑት ሙሉ በሙሉ ተመ ለሱ።ሌሎች ተለይተው ሄዱ። የቀሩት በተለያየ ምክንያት እዚሁ እኛው ቤት ቀር ተው ቀሰ በቀስ መስፋፋት ጀመሩ።

እነዚህ በተለያየ ቦታ ተደብቀው የነበሩ መናፍቃን በትግራይ የበለጠ ተጠናክረው እንዲወጡ ማኅበረ ቅዱሳንን ማሰጠላት፥መበተንና ማፈራረስ ትልቁ ታክ ቲካቸው አደረጉ።ይህም በትግራይ ተሳካላ ቸው። በመቀጠል ትግራይ ያለችው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኃይልም ሆነ ጉልበት እንዳታገኝ ከማዕ ከሉ ከቅዱስ ሲኖዶስ በመለየት አስተዳደሩን መቆጣ ጠር ቻሉ።ጦርነቱ ትግራይን አወደመ።ተሃድሶ መናፍ ቃን ግን ጦርነቱን እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅመው የሀገረ ስብከቶችን አስተዳደር እስከሚችሉት ድረስ ተቆጣጠሩ።

በመቀጠልም “ማኅበረ ቅዱሳንን እንደ ድርጅት ከትግራይ አጥፍተነዋል፥አሁን ደግሞ የዘራውን የሸ ዋን እምነትና ተከታዮችን እናጠፋለን፤”ብለው በዚያ አሰቃቂ ጦርነት ወቅት ሳይቀር ብቸኛ መጽናኛ ቤታች ንን አማናዊት ምስካየ ኅዙናንን አመሷት።ልጆቿን አሳደዱ።የተወሰኑትንም ከቤተ ክርስትያን አባረሩ። “ማርያም አማላጃችን ናት፥ቅዱሳን ያማልዳሉ” የሚ ለው የሸዋ ትምህርት ነው አያሉ የሚቃወማቸውን ሁሉ “ሸዋ” “ማኅበረ ቅዱሳን” “ባንዳ” እያሉ ያሳድ ዳሉ።“አማላጃችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” እያሉ በቤተ ክርስትያን ዐውደ ምሕረት በይፋ ያስተምራሉ። መሠረታዊ የቤተ ክርስትያንን መጻሕፍት እየቆነጻጸሉ ወደ ትግርኛ እየተረጎሙ ነው።ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በትግራይ ለመቆጣጠር ከቅዱስ ሲኖዶስ ትግራይን ነጥለን የራሳችንን ኤጲስ ቆጶሳ ትን እንሾማለን ብለው ተነሥተዋል።በመቀጠል በአንድ ዓመት ውስጥ የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ይቋቋማል።የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ፓትርያርክ ይሾማል።እዚህ ላይ “ተዋሕዶ” የሚለው ስም እንደሚቀርም ወስነዋል።“በመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ሲኖዶስ አማካኝነት ትግራይ ወደ ጥንቱ እምነቷ ትመለሳለች። የሸዋ እምነት ይወገዳል”ይላሉ።

ይህ የጥንት እምነት የሚሉት ቅጥፈት ክርስቶስ አማላጃችን የሚል በወላዲተ አምላክ እና በቅዱሳን አማላጅነት የማያምን ጾም ጸሎትን የሚጸየፍ ስሙን ብቻ የቀየረ የፕሮስቴንታንት እምነት ነው።ምንም እንኳን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በትግ ራይ ለመገንጠልና ዐሥር ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመን በመ ንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ሲኖዶስ እናቋቁማለን የሚ ለው የመሰሪዎቹ የተሃድሶ መናፍቃን ልዩ ፕሮጄግት ቢሆንም ሕወሃትን ከወቀሳ ብፁዐን አባቶ ችን ከተ ጠያቁነት አያድንም።

ለሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት:-ለብፁዕ አቡነ መርሐ ክር ስቶስ፥ለብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ እና ለብፁዕ አቡነ ጴጥ ሮስ ፖለቲካን ሽፋን አድርጎ ስለሚንቀሳቀሰውና የቤተ ክርስትያን መገንጠል ፕሮጀክት ባለቤት ስለ ሆነው ተሃድሶ መናፍቃን በተፈለገው መጠን ባይሆንም በተለያየ መንገድ ተነግሮአችኋል.።በቀጣይነት ስንነ ግራችሁ ግን:-የነበረውን እየዘረዘርን፥መናፍቃንን በስም እየጠቀስን፥ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆነ ሁሉ እውነቱን እንዲያውቅ እንደርጋለን።

አንድ ጥያቄ እንጠይቃችሁ?
ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፈቃድ ውጭ እና ቀኖና ቤተ ክርስትያንን በመጣስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹሞ መንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን የሚባል ሲኖዶስ እናቋ ቁማለን የምትሉት ለትግራይና ለትግራውያን የሚሰ ጠው ጥቅም ምንድር ነው? ዛሬ እናንተን ማየት የም ንፈልገው ያለ አባት ለቀሩ ልጆች እንደወላጅ አባት ስትሆኑ፥ጧሪ ደጋፊ ልጃቸው አንደ ወጣ ለቀረባቸው አዛውንት ድጋፍ ስትሆኑ፥ልጇ ይኑር ይሙት ለማወቅ ተቸግራ ቀኑ ለጨለመባት እናት መፍተሔ ስትፈልጉ ነው።ከሰላም ስምምነቱ በኋላ እንኳን ስንቱ ትግራ አዊ በረሃብ አልቋል።መቼ ነው? እንደ ሊቃነ ጳጳሳት ከፍ ብላችሁ በዓለም መድረክ ተገኝታችሁ መድኃ ኒትና ምግብ የምትፈልጉልን።እኛ ካህናት በርሃብ እያለቅን ነው፥ልጆቻችን እንደወጡ ቀርተ ዋል፥ብዙ አብያተ ክርስትያናት በቀዳስያን እጥረት ተዘግተዋል። መቼ ነው? ለእኛና ለቤተ ክርስትያን ማሰብ የምትጀም ሩት።መጪው ግዜ በትግራይ ለምትገኘው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አጅግ አስፈሪ ነው።

ለመሾም የተሰለፉትን መነኳሳት እያወቅናቸው ነው።በእርግጠኝነት የምንነግራችሁ አንዳቸውም ቢሆኑ በየትኛውም ትግራይ በምትገኝ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ኤጲስ ቆጶሳት ሁነው አይገቡም።ቤተ ክርስ ቲያንን የመናፍቃን መነሃርያ ስታደርጉ፥የሀገረ ስብከታ ችሁን አስተዳደር ለተሃድሶ አስልፋችሁ ስትሰጡ፥ በጦርነት ወስጥ ስለነበርን ብዙ ገፍተን አልነገርናች ሁም።አሁንም በየሀገረ ስብከታችሁ የተሾሙላችሁ ተሃድሶ መናፍቃን አዲስ አበባ ከሚገኙ አለቆቻቸው ጋር ተቀናጅተው በየገዳማቱና አድባራቱ ሰዎችን እየ መለመሉ ሥልጠና እየሰጡ ነው።እናንተም ኤጲስ ቆጶሳት ልተሾሙላቸው ደፋ ቀና እያላችሁ ነው። ጽዋዉ ሞልቷል።ትግራይ ሰላም ይራቅሽ ተብላ የተረ ገመች ይመስል አሁን ደግሞ ሌላ ጦርነት።አሁን ደግሞ በእናንተ በሊቃነ ጳጳሳት የተቀሰቀሰ ጦርነት። አሁን ደግሞ በሃይማኖት ምክንያት የስንቱ ሰው ደም ይፈስ ይሆን? አንቺ መከረኛ እናት አሁንስ የትኛው ልጅሽ ይሆን እንደወጣ የሚቀረው?
(ከመምህር ፋንታሁን ዋቄ ገጽ የተገኘ)

ሄንግዳ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማየሰው ተኮር ኢንቨስትመንቶች ምልክት
07/07/2023

ሄንግዳ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማ
የሰው ተኮር ኢንቨስትመንቶች ምልክት

ሄንግዳ ሪል እስቴት ነገ እንፈጽማለን ያለውን ዛሬውኑ ሊከውን ስለመሆኑ ስናበስር ደስታችን እጥፍ ድርብ ነው። ሄንግዳ ከመኖሪያ መንደር ግንባታ በተጨማሪ በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሳ...
07/06/2023

ሄንግዳ ሪል እስቴት ነገ እንፈጽማለን ያለውን ዛሬውኑ ሊከውን ስለመሆኑ ስናበስር ደስታችን እጥፍ ድርብ ነው። ሄንግዳ ከመኖሪያ መንደር ግንባታ በተጨማሪ በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሳትፎዎችን በማድረግ የስራ እድል ፈጥሮ ለአካባቢያዊና ለሀገራዊ የኢኮኖሚ መነቃቃት አሻራ የማሳረፍ አላማውን ሊያሳካ እንቅስቃሴውን አሀዱ ብሎ ጀምሯል። ካምፓኒያችን ከትላንት ጀምሮ አሁንም ለርካታ ወገኖች የስራ እድል የፈጠረምና እየፈጠረ ያለም ነው።

ሄንግዳ የሰው ተኮር ቢዝነሶች የንግድ ምልክት ነው!!

ደብረብርሀን ዩኒቨርሲቲ የዘጋቸው አራት የትምህርት ክፍሎች በፌደራል መንግስት ትዛዝ እንደሆነ የሚነገረው ውሸት ነው። ትምህርት ሚኒስተር የትኩረት መስኮችን ለየ እንጂ ታሪካችሁን አታጥኑ ቋንቋ...
06/29/2023

ደብረብርሀን ዩኒቨርሲቲ የዘጋቸው አራት የትምህርት ክፍሎች በፌደራል መንግስት ትዛዝ እንደሆነ የሚነገረው ውሸት ነው። ትምህርት ሚኒስተር የትኩረት መስኮችን ለየ እንጂ ታሪካችሁን አታጥኑ ቋንቋችሁን አትማሩ ወይም ዲፓርትመንቶችን ዝጉ አላለም። እናም የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው ህዝብ እንዲመክርበት ማድረጉ የተሻለ ነው።
በነገራችን ላይ የተሻለ አቅም ያለውና የሙያው ባለቤት ተወዳድሮ ለመራው የሚገባውን የዩኒቨርሲቲውን "የአለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት" የግብርና ባለሙያ መድቦ የሚቀልድ ብቸኛ የአለማችን ዩኒቨርሲቲ ነው።

በይደር የሚተወውን ትተን በትብብር ለመቆም በቂ ምክንያት አለን!                    ==by   Tessema=====የፖለቲካ ኃይሎች በተለይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተክለ-ቁመና ደካማ በ...
06/28/2023

በይደር የሚተወውን ትተን በትብብር ለመቆም በቂ ምክንያት አለን!
==by Tessema=====
የፖለቲካ ኃይሎች በተለይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተክለ-ቁመና ደካማ በመሆኑ የተነሳ ህዝባችንን የዘረጋ ሁሉ እየዘገነው መሆኑ ቆጭቶን በህብረት ካልቆምን ችግር ችግርን እየወለደ ነው የሚሄደው። አዎ! በመካከላችን ልዩነቶች አሉ። ነገር ግን በይደር የሚተው ናቸውና ለትልቁ ስዕል (የህዝባችን መባከን፣ መጠቃትና ሰብሳቢ ማጣት ቀዳሚ አጀንዳ መሆኑ ላይ ተማምነን) ሲባል መሰባሰቡ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ሆኗል።

እየታገተ፣ አየተፈናቀለ፣ እየሞተ፣ ወዘተ ያለ ህዝብ ለገዳዮቹ የጦር መሳሪያ መግዣ ሚሊዮን ብሮችን ሲሰጥ ከማየት በላይ የሚያንገበግብ ነገር ያለ አይመስለኝም። ለዚህም ደረጃው ቢለያይም ሁላችንም የታሪክ ተወቃሾች መሆናችንን አምነን በህብረት ከህዝብ ጎን መቆም በሚያስችሉን ጉዳዮች ላይ ብቻ መክረን-ዘክረን የግልና የጋራ ስምሪት የመውሰዱ ጉዳይ ጊዜ የሚሰጠው አይደለም።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች  እንኳን ለ1 ሺ 444 ኛው የኢድ-አል አድሃ በዓል አደረሳችሁ!የሄንግዳ ሪል እስቴት ዳይሬክተሮች ቦርድ
06/27/2023

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺ 444 ኛው የኢድ-አል አድሃ በዓል አደረሳችሁ!
የሄንግዳ ሪል እስቴት ዳይሬክተሮች ቦርድ

ምናላቸው ስማቸው የግርማ የሽጥላን ግድያ ያቀነባበረ እና live እየተከታተለ የነበረ ጎጠኛ አሁን ደግም መላኩ አለበል መጣላች ለግድያ ተዘጋጁ እያለ ነው።
06/21/2023

ምናላቸው ስማቸው የግርማ የሽጥላን ግድያ ያቀነባበረ እና live እየተከታተለ የነበረ ጎጠኛ አሁን ደግም መላኩ አለበል መጣላች ለግድያ ተዘጋጁ እያለ ነው።

አፋር- አዋሽ  የእንቅስቃሴ መስተጓጎል ተከስቷል። አንድ የአፋር ክልል ፖሊስ በፌደራል የጸጥታ አካል መገደሉን ተከትሎ በተከሰተው የሰላም መደፍረስ የተነሳ ወደሀረር የሚወስደው መንገድም እክል...
06/17/2023

አፋር- አዋሽ የእንቅስቃሴ መስተጓጎል ተከስቷል። አንድ የአፋር ክልል ፖሊስ በፌደራል የጸጥታ አካል መገደሉን ተከትሎ በተከሰተው የሰላም መደፍረስ የተነሳ ወደሀረር የሚወስደው መንገድም እክል ገጥሞታል።

የሰ/ሸዋ መሪዎቻችን የመንዝን መንገድ አስመልክቶ ግልጽ ያለ አቋም ልትይዙ ይገባል። ለዓመታት ሲጓተት የነበረው የመንዝ መንገድ ግንባታ አሁን ላይ መኪና መቅበሪያ የሚመስሉ ጉድጎዶች ሳይት መም...
06/08/2023

የሰ/ሸዋ መሪዎቻችን የመንዝን መንገድ አስመልክቶ ግልጽ ያለ አቋም ልትይዙ ይገባል። ለዓመታት ሲጓተት የነበረው የመንዝ መንገድ ግንባታ አሁን ላይ መኪና መቅበሪያ የሚመስሉ ጉድጎዶች ሳይት መምሰሉን የመንዝ ወረዳዎች የመንግስት አፍ ነግሮናል። ስለሆነም የዝኑ አመራሮች አንድም ተቋራጭ ድርጅቱ ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ እንዲጠየቅና የመንገድ ግንባታው የሚጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ እንዲቀመጥ ማድረግ ሁለትም ከህዝብ ጎን በመቆም ህዝብን አታግሎ መብቱን እንዲያስከብር ማድረግ ይጠባችኋል። ካልሆነ ግን የህዝቡ ልጆች ከአዳራሽ ምክክር የሚመነጭ ትግል መጀመራቸው የግድ በመሆኑ በንቅናቄ መንገዳችን ላይ በመቆም አሉታዊ ጫና እንዳታሳድሩ ማለታቸው አይቀርም።
ከአክብሮት ጋር የቀረበ ጥሪ
!

ሰሜን ሸዋ ላይ የተፈራረቀው የዞን አመራር ሁላ ለህዝቡ እዳ እንጂ እዚህ ግባ የሚባል አበርክቶ አላሳየም። ይህ የሚታየው የመንዝ መንገድ መጠናቀቅ የነበረበት ጊዜ አልፏል። በየ100 ኪሎ ሜትር...
06/07/2023

ሰሜን ሸዋ ላይ የተፈራረቀው የዞን አመራር ሁላ ለህዝቡ እዳ እንጂ እዚህ ግባ የሚባል አበርክቶ አላሳየም። ይህ የሚታየው የመንዝ መንገድ መጠናቀቅ የነበረበት ጊዜ አልፏል። በየ100 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ የሚገኙ ማሽኖች የቆፈሩት ጭቃ ለንብረት ብልሽት ለህዝብ ስቃይ ነው የሆነው። የዞኑ አመራር ደግም ለክልል ሰዎች አረቄና ጋቢ ለመሸለም የተሾመ ይመስል የመንገዱን ጉዳይ ባላየ የሚያልፍ አይነት ነው።
በጸጥታው ረገድም በተለይ በመንዝና በይፋት ቀጠና ህዝቡ ራሱን ካልጠበቀ በስተቀር በአመራሩ ላይ መተማመን አዳጋች ነው። ለግርማ የሽጥላም መገደል የወረዳዎች ብሎም የዞኑ አመራር እንዝህላልነት የራሱ ድርሻ አለው። እነዚህ ሲደግፏቸው የሚንጋለሉ የብአዴን ሰዎች ህዝቡን በሁሉም መስከ መከራ ውስጥ እየከተቱት በመሆኑ ከህዝብ ጎን ሆኖ ፈር ማስያዙ የተሻለ አማራጭ እየሆነ ነው።

በሀገራዊ ምክክር፣ በሀገሪቱ ስርዓታዊና መዋቅራዊ ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ ********************(ኢ ፕ ድ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ አብን "ሀገራዊ ምክክር፣ የ...
06/04/2023

በሀገራዊ ምክክር፣ በሀገሪቱ ስርዓታዊና መዋቅራዊ ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ
********************
(ኢ ፕ ድ)

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ አብን "ሀገራዊ ምክክር፣ የሀገራችን ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ተግዳሮቶች በተለይ ከአማራ ሕዝብ አንፃር" በሚል የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ አካሂዷል።

በውይይት መድረኩ የአብን ምክትል ሊቀመንበር አቶ መልካሙ ሹምየን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ መልካሙ ሹምየ በመድረኩ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ ሀገሪቱ ለበርካታ ዓመታት በስርዓታዊና መወቅራዊ ችግሮች እየተፈተነች ትገኛለች ብለዋል።

ሀገሪቱ እየገጠሟት ካሉት ተግዳሮቶች ለመውጣት ሀገራዊ ምክክሩ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።

ሀገራዊ ምክክር ለኢትዮጵያ የሚኖረው አንድምታና የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ በሚል ሀሳብ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ መምህር ዶክተር ያሲን ሁሴን ጥናት አቅርበዋል። የምክክሩ የትግበራ ሂደት ምን መምሰል እንዳለበት በጥናት አቅራቢው ተገልጿል።

ምክክሩ የሚካሄድባቸው ሀገራት ያሉበት የፖለቲካ ሁኔታ፣ በሀገራቱ የሚኖረው የምክክር ባህል፣ ያለፉ ተሞክሮዎች፣ ውክልና አሰጣጥ፣ ዉሳኔ አሰጣጥ፣ ሂደቱን የሚመሩት ቁርጠኝነትና ሌሎች ጉዳዮች ሀገራዊ ምክክር እንዲሳካ ምክንያት እንደሚሆኑ አስረድተዋል።

በሄለን ወንድምነው

ሄንግዳ ሪል እስቴት
05/31/2023

ሄንግዳ ሪል እስቴት

Hikell የሚባለው "ድርጅት" በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና በፋና ቴሌቭዥን የፌስቡክ ገፆች ላይ ማስታወቂያዎቹን ለሚሊዮኖች እያደረሰ ነው። እነዚህን አሳሳቢ የሆኑ ጥያቄዎች በኢሜይል አድራሻዎቻቸ...
05/30/2023

Hikell የሚባለው "ድርጅት" በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና በፋና ቴሌቭዥን የፌስቡክ ገፆች ላይ ማስታወቂያዎቹን ለሚሊዮኖች እያደረሰ ነው።

እነዚህን አሳሳቢ የሆኑ ጥያቄዎች በኢሜይል አድራሻዎቻቸው አቅርቤላቸው ምላሽ ስላላገኘሁ እዚህ ላስቀምጠው።

1. "ፈጣን ከሆኑ እንደሌሎቹ በአመት ከ30,000 እስከ 60,000 ዶላር ይሰሩበታል፣ ከእርስዎ የሚጠበቀው ፎቶዎችን በሶሻል ሚዲያ ማስተዋወቅ ብቻ ነው" የሚለው በየትኛው ስሌት ነው? እንደዚህ ያገኘ ሰው አለ ወይ? ለምሳሌ ማቅረብ ይቻላል?

2. ድርጅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አድራሻው ወይም ቢሮው ያለበት ቦታ ማስታወቂያዎቹ ላይ የለም፣ የሚመሩት ሰዎች አድራሻም LinkedIn ላይ የለም፣ ወይም እንዲደበቅ ተደርጓል። ለምን?

3. ስራችን Dropshipping ነው፣ ይህም እቃዎችን ሳይሆን የእቃዎቹን ፎቶ መሸጥ ነው ይላል። ይሄ በአለም ዙርያ የተለመደ ስራ ነው፣ inventory ሳይይዙ የሌሎችን እቃ መሸጥ ማለት ነው። ታድያ ድርጅቱ የራሱ inventory አለው ወይስ እንደ አማዞን ያሉ የሌሎች ድርጅቶችን ይጠቀማል?

4. ድርጅቱ በ250 ሀገራት ስራ እንድትሰሩ ማድረግ እንችላለን ይላል፣ በአለም ላይ ይህን ያህል ሀገራትስ አሉ ወይ?

5. ድርጅቱ ራሱን ሲያስተዋውቅ "The world’s first combined online marketplace and ecommerce platform in one single place" ይላል። ገና የኦላይን ቢዝነስ እየተጀመረ ባለበት ሀገር ላይ ሆኖ በዘርፉ እጅግ የዳበረ እና በትሪሊየን ዶላሮች የሚገበያዩ ሀገራት እያሉ "በአለም የመጀመርያው..." የሚለው አይከብድም ወይ?

6. በእነዚህ ትልልቅ የመንግስት ሚድያዎች ላይ እየተዋወቀ እንዳለው ይህን የሚሰሩ ሰዎች ዶላር ከ200 ሀገራት መቀበል ይችላሉ (ምስሉ ላይ እንደሚታየው)። ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ህግ መሰረት አንድ ሰው ለማንኛውም የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ ግብይት በዶላር መቀበል ይችላል ወይ?

7. "በአለም የመጀመርያው..." ብሎ ራሱን ስለሚያስተዋውቀው ይሄ ድርጅት አንድም ሚድያ (የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ) ፅፎ ወይም አንድ እንኳን ዜና ሰርቶ አያውቅም። ለምን?

8. ድርጅቱ የኦንላይን ሱቅ ለመክፈት ከ $19.99 እስከ $189.99 ያስከፍላል። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ ድርጅት በዶላር ማስከፈል ይፈቀድለታል ወይ?

9. ድርጅቱ ተመዘገብኩበት ያለውን HikEL LLC, 30 N Gould St Ste R, Sheridan, Wyoming, United states ለማጣራት ሞክሬ አንድም በአድራሻው አይገኝም፣ የአሜሪካ ንግድ እና ቻምበር ቢሮ ዳታቤዝም ድርጅቱ እንደሌለ ይጠቁማል።

10. ድርጅቱ ስለ ስልጠናዎቹ የሚያሰራጫቸው ብሮሸሮች ላይ አንድ የፈረንጅ ምስል ደጋግሞ ይጠቀማል፣ ለማወቅ እንደቻልኩት ግለሰቡ ታዋቂው አሜሪካዊ ደራሲ ጆርዳን ማሊን ናቸው። Hikell ከእኝህ ግለሰብ ጋር አብሮ ይሰራል?

#ትዝብት እነዚህ ትልልቅ የመንግስት ሚድያዎች እንዲህ አይነት ጥርጣሬን የሚጭሩ ማስታወቂያዎች ሲቀርቡላቸው ምንም ማጣራት ሳያደርጉ ገንዘብ ብቻ ተቀብለው ካቀረቡ በኋላ ችግር ቢፈጠር ተጠያቂው ማን ነው?

#ማስታወሻ ድርጅቱ የሚሰጠው ምላሽ ካለ ለማግኘት በኢሜይል አድራሻዎቻቸው ([email protected] እና [email protected]) ብፅፍም ምላሽ አላገኘሁም።

ሄንግዳ ሪል እስቴት ሁሉም ቤት ፈላጊ እንደየምርጫው እና እንደየአቅሙ ፍላጎቱን የሚያረካበት እንዲሆን አቅዶ እየሰራ መሆኑን ስናበስር በኩራት ነው!
05/22/2023

ሄንግዳ ሪል እስቴት ሁሉም ቤት ፈላጊ እንደየምርጫው እና እንደየአቅሙ ፍላጎቱን የሚያረካበት እንዲሆን አቅዶ እየሰራ መሆኑን ስናበስር በኩራት ነው!

ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ እስከ 10 ሚሊዮን ብር ቀርጥፎ የበላ የሌባ ስብስብ በሸዋ ህዝብ ስም ዶላር እየለመነ እያየን በዝምታ እንደማለፍ ውርደት የለም። ከዛም ላይ ሸዋ የነውጥ ቀጠና እንዲሆን...
05/19/2023

ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ እስከ 10 ሚሊዮን ብር ቀርጥፎ የበላ የሌባ ስብስብ በሸዋ ህዝብ ስም ዶላር እየለመነ እያየን በዝምታ እንደማለፍ ውርደት የለም። ከዛም ላይ ሸዋ የነውጥ ቀጠና እንዲሆን እና የሸዋ ልሂቃን እንዲገደሉ ሲያስተባብር የከረመ ኃይል በደማችን ሲነግድ ዝም እንበል??

እነሀብታሙ አያሌው በሸዋ ህዝብ መለመናቸው ይቁም። የሸዋ ህዝብ በነሱ ምክንያት ለመከራ መዳረጉ ሳያንስ በህዝባችን ደም እየተነገደ መሆኑ እጅግ የሚያም ነው።   ባቀነባበራችሁት ግድያ የቆሰልነ...
05/19/2023

እነሀብታሙ አያሌው በሸዋ ህዝብ መለመናቸው ይቁም። የሸዋ ህዝብ በነሱ ምክንያት ለመከራ መዳረጉ ሳያንስ በህዝባችን ደም እየተነገደ መሆኑ እጅግ የሚያም ነው።
ባቀነባበራችሁት ግድያ የቆሰልነው ይበቃልና እባካችሁ ተውን ለማለት ነው!! ለሽቀላ ስትሉ ፍኖዎቻችንንም አታስገድሉበን።

05/13/2023

♦ ቤታቸው የፈረሰባቸው ትላንት ማታ
#በጥይት ተመተው ተገድለዋል።

በሰበታ ከተማ በኬንተሪ ደረቶ በሚባል ቦታ የአቶ መሀመድና የጎረቤቶቹ ቤቶች የፈረሱት ከትላንትበስቲያ ነበረ። ሙሉ ሰፈሩ ፈርሶ አልቋል ማለትም ይቻላል። አቶ መሀመድም እዛ ሰፈር ከገባ ወደ 18 አመት የሆነው ነዉ ።

ቤት ከፈረሰባቸው ሰዎች መሀከል የአቶ መሀመድ አብደላን ጨምሮ የሁለት ቤተሰብ አባላት ቤታቸዉ ከፈረሰባቸዉ በሆላ የሚሄዱበት አጥተው ተቸግረዋል። ትላንት ከሰአትም አብዛኛው እቃቸውን ወደ ገጠር ከጫኑ በኋላ ሰፈራቸዉ በሚገኝ አንድ ፊኒሽጉ ያላለቀ የሪልስቴት ፎቅ ግራወንዱ ላይ ቦታ ያለ በመሆኑ በባለቤቱ መልካም ፍቃድ "ቤት እስክታገኙ እዛ ግቡ" ብሎዋቸዉ ገቡ።

ማታ ፖሊሶች መጥተው እነመሀመድ የተኙበትን የህንፃውን ግራወንድ በር መደብደብ ጀመሩ። መሀመድም ማንነታቸውን ለማጣራት በመጠየቅ ላይ እያለ በሩ በሀይል ተሰበረ። በመቀጠልም አቶ መሀመድ አብደላ እንዲሁም ባለቤቱ ለቢባ ጀማል በጥይት ተመቱ ።

ጩኸቱን ሰምታ ከመጡት ጎረቤቶች መሀል አራስ የሆነችው ሉባባ ብላቱ በጥይት ተመታ ስትሞት ባለቤቷ ደግሞ ከቆሰለ በኋላ አምልጧል።

በጻውሎስ ሆስፒታል ያደረውን አስክሬን አሁን ተቀብለናል።

Tesfa G Neda - ከጳውሎስ ሆስፒታል

Address

Fairyland
Silver Spring, MD
20904

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zemen Television posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Nearby media companies


Other News & Media Websites in Silver Spring

Show All

You may also like