SHEGER FM 102.1 RADIO

SHEGER FM 102.1 RADIO SHEGER 102.1FM 'Yenanetew Radio' is the first private radio station in Ethiopia. We are proud to be Ethiopian and we love our country more than anything!
(1)

Hear us live on www.ShegerFM.com, dedicated phone numbers, and mobile Apps. ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ መስከረም 23፣2000 ዓ.ም ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡

ይህ ከአዲስ አበባ በ250 ኪሎ ሜትር ክበብ ውስጥ ፕሮግራም እንዲያሰራጭ ፈቃድ አግኝቶ የረጅም ጊዜ የሬዲዮ ሥራ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተቋቋመው ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአድማጮች ዘንድ ተወዳጅነትን ሊያተርፍ ችሏል፡፡

ሸገር 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡

፡ የሸገር ዓላማ ከወገናዊነት የነፃ ትክክለኛ የሕዝብ ድምፅ መሆን፣ ሥነ ምግባርን የጠበቀ የጋዜጠኝነት መርህን መከተልና የተሣካለት የኢንፎቴይመንት (Information & Entertainment) ሬዲዮ ጣቢያ መሆን ነው፡፡

ጣቢያችን ለማንም ባለመወገን ለሁሉም በታማኝነትና በመልካም ሥነ ምግባር መልካም አገልግሎት በመስጠት የሚያምንና ለእነዚህም እሴቶች ትልቅ ክብር የሚሰጥ ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

ሸገር ዓለም አቀፍ ትንታኔ  - ሚያዝያ 9፣2016   ላለፉት አስርት አመታትም ካብ ለካብ ሲተያዩ የቆዩት እስራኤልና ኢራን ከሰሞኑ ደግሞ የጥላቻ ደረጃቸው ከፍ ብሎ ጦር እስከመማዘዝ ደርሰዋል...
17/04/2024

ሸገር ዓለም አቀፍ ትንታኔ - ሚያዝያ 9፣2016

ላለፉት አስርት አመታትም ካብ ለካብ ሲተያዩ የቆዩት እስራኤልና ኢራን ከሰሞኑ ደግሞ የጥላቻ ደረጃቸው ከፍ ብሎ ጦር እስከመማዘዝ ደርሰዋል፡፡

ኢራን በእስራኤል ላይ የፈፀመችው ጥቃት ለዓለም ምን አሳየ?

እሸቴ አሰፋ

https://youtu.be/oHYuQIm-Y5s

#

,sheger fm news,sheger maleda,sheger,sheger sport,shegernews,shegercafe,shegerradio,shegershelf,shegerfmyoutube,shegermeaza,shegermek...

ሚያዝያ  9፣2016የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሽግግር ፍትሕ  ፖሊሲን አጸደቀ፡፡ በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብአዊ መ...
17/04/2024

ሚያዝያ 9፣2016

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲን አጸደቀ፡፡

በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በእርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርክቶች እና በደሎችን ለመፍታት የተለያዩ ሙከራዎች መደረጋቸውን ም/ቤቱ አስታውሷል፡፡

ሆኖም እነዚህ አሰራሮች በእውነት፣ በዕርቅ፣ በምህረት እና በፍትሕ ላይ የተዋቀረ እና በግልፅ ፖሊሲ የሚመራ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ ስልትን አካታች፣ ሰብአዊ መብት ተኮር በሆነ እና በተሰናሰለ መንገድ ባለመተግበራቸው የሚፈለገውን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልቻሉም ብሏል።

ስለሆነም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱን በተደራጀ፣ በተቀናጀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመምራትና ለመተግበር እንዲቻል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በዛሬው እለት ባደረገው ስብሰባ በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ተናግሯል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከዚህ በተጨማሪም የመንግስት ሠራተኞች አስተዳደርን ነጻ፣ ገለልተኛ፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽነት እና ተጠያቂነት ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት፤ እንዲሁም ከጊዜው ጋር የሚራመድ የአስራር ስርአት ለመዘርጋት የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ተወያይቶ ለህዝብ አንደራሴዎች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ተሰምቷል፡፡



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

ሚያዝያ  9፣2016በኢትዮጵያ ያለው አጠቃላይ የኤች አይ ቪ ኤድስ የሥርጭት ምጣኔ 0.9 ቢሆንም  በቦታ፣ በእድሜ፣ በጾታ እንዲሁም በሌሎችም ምክንያቶች ከፍተኛ የስርጭት ልዩነት እየታየ ነው ...
17/04/2024

ሚያዝያ 9፣2016

በኢትዮጵያ ያለው አጠቃላይ የኤች አይ ቪ ኤድስ የሥርጭት ምጣኔ 0.9 ቢሆንም በቦታ፣ በእድሜ፣ በጾታ እንዲሁም በሌሎችም ምክንያቶች ከፍተኛ የስርጭት ልዩነት እየታየ ነው ተባለ፡፡

የኤች አይ ቪ መከላከል ስራ ተጋላጭ ዜጎች እና ከፍ ያለ የሥርጭት ምጣኔ የሚታይባቸውን አካባቢዎች በመለየት የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረጉ ጥረቶች አሁንም ሊቀጥሉ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል።

ሀገር አቀፍ የኤች አይ ቪ ኤድስ ፕሮግራም የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም የጋራ ግምገማ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ኢትዮጵያ ኤች አይ ቪ ኤድስ አሁን ያለበትን ስርጭት መጠን ለመቀነስ በመጪዎቹ አራት አመታት የሚተገበር ስትራቴጂክ እቅድ አዘጋጅታ በስራ ላይ እንደምትገኝ በጤና ሚኒስቴር የኤች አይ ቪኤድስ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ያደታ ተናግረዋል።

በሀገሪቱ ያለው የኤች አይ ቪ የስርጭት ምጣኔ 0.9 ቢሆንም በቦታ፣ በእድሜ፣ በጾታ እንዲሁም በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ልዩነቶች እንደሚታይ አቶ ፍቃዱ ጠቅሰዋል፡፡

የኤች አይ ቪ ዘርፈ ብዙ https://tinyurl.com/5fnap95f



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

በኢትዮጵያ ያለው አጠቃላይ የኤች አይ ቪ ኤድስ የሥርጭት ምጣኔ 0.9 ቢሆንም በቦታ፣ በእድሜ፣ በጾታ እንዲሁም በሌሎችም ምክንያቶች ከፍተኛ የስርጭት ልዩነት እየታየ ነው ተባለ፡፡ የኤች አ...

ሚያዝያ  9፣2016በምስራቅ አፍሪካ የድንበር አካባቢዎች ጭምር በመጪዎቹ ወራት የሚኖረው የአየር ጠባይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ተነገረ፡፡ለእዚህም ጠንካራ ትብብርና አስቀድሞ የአየር ...
17/04/2024

ሚያዝያ 9፣2016

በምስራቅ አፍሪካ የድንበር አካባቢዎች ጭምር በመጪዎቹ ወራት የሚኖረው የአየር ጠባይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ተነገረ፡፡

ለእዚህም ጠንካራ ትብብርና አስቀድሞ የአየር ጠባይ ሁኔታ ትንተናን የሚፈልግ ነው ተብሏል፡፡

https://tinyurl.com/268xjzc4

የኔነህ ሲሳይ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ 9፣2016 በምስራቅ አፍሪካ የድንበር አካባቢዎች ጭምር በመጪዎቹ ወራት የሚኖረው የአየር ጠባይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ተነገረ፡፡ ለእዚህም ጠንካራ ትብብርና አስቀድሞ የ....

ሚያዝያ  9፣2016በኢትዮጵያ በተለያየ ምክንያት እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው በ10 ሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፍ ለማቅረብ እስከ መጪው ጥር ወር ድረስ 3.24 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ፡፡በ...
17/04/2024

ሚያዝያ 9፣2016

በኢትዮጵያ በተለያየ ምክንያት እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው በ10 ሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፍ ለማቅረብ እስከ መጪው ጥር ወር ድረስ 3.24 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ፡፡

በመጪዎቹ 5 ወራት የነፍስ አድን እርዳታ ለማቅረብ እና ምግብ ነክ ድጋፍም ለማድረግ 1 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተናግሯል፡፡

የኢትዮጵያ አለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ከዚሁ አላማ ጋር በተገናኘ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ትናንት ፈንድ ማሰባሰቢ ስብሰባ አካሄዷል፡፡

በዚህም በመጭዎቹ 5 ወራት ያስፈልጋል ከተባለው 1 ቢሊየን ዶላር መካከል 630 ሚሊየን ዶላር ቃል መገባቱን በስብሰባው ላይ የተሳተፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በኤክስ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

ይህም ከሚያስፈልገው የተገኘው 5 በመቶ ብቻ መሆኑን ያሳያል ብሏል የተባበሩት መንግስት ድርጅት በድረ ገፁ ባወጣው መረጃ፡፡

የገቢ ማሰባሰቢ ፕሮግራሙን የኢትዮጵያና የእንግሊዝ መንግስት በጋራ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በመተባበር የተካሄደ ነው ተብሏል፡፡

በድርቅ፣ በጎርፍና በግጭት ምክንያት የምግብ እጥረት አጋጥሟቸው እርዳታ የሚያስልጋቸው ሰዎች ቁጥር እስከመጪው መስከረም ወር ወደ 10.8 ሚሊየን https://tinyurl.com/ysam7w5b

#ድጋፍ #እርዳታ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ  9፣2016የአማራ ክልላዊ መንግስት ሕወሃት በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ አሳሰበ፡፡የክልሉ ሕዝብም ሕወሃት የከፈተውን ጥቃት እንዲመክት ጥሪ አስተላልፏል፡፡የአማራ ክልላዊ...
17/04/2024

ሚያዝያ 9፣2016

የአማራ ክልላዊ መንግስት ሕወሃት በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ አሳሰበ፡፡

የክልሉ ሕዝብም ሕወሃት የከፈተውን ጥቃት እንዲመክት ጥሪ አስተላልፏል፡፡

የአማራ ክልላዊ መንግስት ይህን መግለጫ ያወጣው ሕወሃት የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ የራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ የኮረም እና ዛታ አካባቢዎች ላይ ወረራ ፈፅሟል ብሎ ነው፡፡

የሕወሃት የወረራ ድርጊት፣ የፕሪቶሪያውን ስምምነት የጣሰ፣ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ እና ከፌዴራል መንግስቱ የተደረገውን የሰላም አማራጭ ውይይት የገፋ ነው ብሎታል፡፡

ሕወሖትና ለአራተኛ ጊዜ የጀመረውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ከማድረግ እንዲታቀብና የፕሪቶሪያውን ስምምነት አክብሮ፣ በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ የአማራ ክልል መንግስት ጠይቋል፡፡፡

ያ ካልሆነ፣ የክልሉ መንግስትና ሕዝቡ ከሌሎች ኢትዮጵያዊን ጋር ሆነው፣ አገርን ከመፍረስ ሕዝብንም ከጥቃት ለመከላከል እንደሚገደድ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል፡፡

በየደረጃው ያሉ የክልሉ የፖለቲካና የፀጥታ መዋቅር አባላትም እንዳለፈው ጊዜ ሁሉ ሕዝቡን በቁርጠኝነት እንዲያደራጁና እንዲጠብቁ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

የክልሉ ሕዝቡም ከየአካባቢው ከሚገኙት የአስተዳደር መዋቅሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝነት እንዲፈጠርና እንዳለፈ ጊዜ ሁሉ የተከፈተውን ጥቃት እንዲመክት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የፌዴራሉ መንግስትም ሕወሃት ከወረራቸው አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ በማድረግ፤ https://tinyurl.com/yz8npp9a

#ራያ #አላማጣ #ግጭት

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ  9፣2016አሰራሮችና የመረጃ ቋቶች ሁሉ ዲጂታል ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ፤ የግለሰቦች እና የመንግስት መረጃዎች ደህንነት ጉዳይ ይነሳል፡፡ለመረጃዎቹ ጥበቃና ደህንነት የሚሰሩ የመረጃ ተ...
17/04/2024

ሚያዝያ 9፣2016

አሰራሮችና የመረጃ ቋቶች ሁሉ ዲጂታል ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ፤ የግለሰቦች እና የመንግስት መረጃዎች ደህንነት ጉዳይ ይነሳል፡፡

ለመረጃዎቹ ጥበቃና ደህንነት የሚሰሩ የመረጃ ተቋማት እየበረከቱ ሲሆን መንግስትም እስፈላጊውን መሰረተ ልማት አሟልቻለሁ እያለ ነው፡፡

https://tinyurl.com/m9yrh7cz

ፍቅሩ አምባቸው



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ 9፣2016 አሰራሮችና የመረጃ ቋቶች ሁሉ ዲጂታል ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ፤ የግለሰቦች እና የመንግስት መረጃዎች ደህንነት ጉዳይ ይነሳል፡፡ ለመረጃዎቹ ጥበቃና ደህንነት የሚሰሩ የመ....

ሚያዝያ  9፣2016በግጭቶችና ጦርነቶች ምክንያት የኢትዮጵያ ቱሪዝም መቀዛቀዙ ይነገራል፡፡ለ2 አመት በዘለቀው የሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የቱሪስት ማረፊያዎች ሁሉ የፈረሱበት የአፋር ክልል የቱሪ...
17/04/2024

ሚያዝያ 9፣2016

በግጭቶችና ጦርነቶች ምክንያት የኢትዮጵያ ቱሪዝም መቀዛቀዙ ይነገራል፡፡

ለ2 አመት በዘለቀው የሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የቱሪስት ማረፊያዎች ሁሉ የፈረሱበት የአፋር ክልል የቱሪስት እንቅስቃሴ አንዲያንሰራራ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

በዚህም በ8 ወራት ውስጥ ከሁለት ሺህ በላይ የውጭ ቱሪስቶች ጉብኝት አድርገዋል ተብሏል፡፡

https://tinyurl.com/mr3e38rr

በረከት አካሉ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ  9፣2016በኢትዮጵያ ህክምና ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማት ከሚሄዱ ሴቶች ውስጥ በገንዘብ ችግር ምክንያት ህክምናቸውን የሚያቋርጡና ለሌሎችም ቀውሶች የሚዳረጉት ብዙዎች ናቸው ተባለ፡፡ይህ...
17/04/2024

ሚያዝያ 9፣2016

በኢትዮጵያ ህክምና ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማት ከሚሄዱ ሴቶች ውስጥ በገንዘብ ችግር ምክንያት ህክምናቸውን የሚያቋርጡና ለሌሎችም ቀውሶች የሚዳረጉት ብዙዎች ናቸው ተባለ፡፡

ይህንንም ለማገዝ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ህክምና ባለሞያዎች ስብስብ የበጎ አድራጎት ድርጅት መመስረቱ ተነግሯል፡፡

https://tinyurl.com/6k4uz45c

ምህረት ስዩም



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ 9፣2016 በኢትዮጵያ ህክምና ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማት ከሚሄዱ ሴቶች ውስጥ በገንዘብ ችግር ምክንያት ህክምናቸውን የሚያቋርጡና ለሌሎችም ቀውሶች የሚዳረጉት ብዙዎች ናቸው ተባለ፡....

ሚያዝያ  8፣2016ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን የሚገኙ ተፈናቃዮች በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀያቸው ይመለሳሉ ቢባልም እንደታ...
16/04/2024

ሚያዝያ 8፣2016

ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን የሚገኙ ተፈናቃዮች በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው፡፡

እነዚህ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀያቸው ይመለሳሉ ቢባልም እንደታሰበው አልሆነም፡፡

ተፈናቃዮቹ በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡

የፌዴራል መንግስት በበኩሉ የድጋፍ ጥያቄ ከክልሎች ሲቀርብልኝ እሰጣለሁ፤ እያደረኩ ያለሁትም ይህንኑ ነው ብሏል፡፡

ተፈናቃዮቹ ለአራት ወራት ምንም አይነት የምግብም ሆነ ሌሎች ድጋፎች እንዳልተደረገላቸው እና በዚህም የሞቱ ሰዎች እንዳሉ ሰምተናል፡፡

በአንድ የመጠለያ ጣቢያ ብቻ ከ 12 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ተጠልለው እንደሚገኙ እና ከነዚህም ውስጥ አብዛኛው ህፃናት፣ አዛውንት እንዲሁም የሚያጠቡ እናቶች እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

መንግስት ‘’የእነዚህ ተፈናቃዮች ሀላፊነት እኔ እወስዳለሁ’’ ቢልም ለተከታታይ አራት ወራቶች ግን ምንም የእህል ዘር አይተው እንደማያውቁ በሶስት የመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች ነግረውናል፡፡

ችግሩ ከከፋ ረሃብም አልፎ ለሞት እየተዳረጉ እንደሆነ እና ግብረሰናይ ድርጅቶች ቦታው ድረስ በመምጣት ድጋፍ ለማድረግ ቢሞክሩም እንዳልሆነላቸው ሸገር ከተፈናቃዮች ለማወቅ ችሏል፡፡

‘’ሶስት አመት ሙሉ ያለምንም ዘላቂ መፍትሄ እየተሰቃየን ነው መንግስት ሊያየን ይገባል’’ም ይላሉ ተፈናቃዮቹ፡፡

በክልሉ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀያችሁ ትመለሳላችሁ ተብለው በከፊል ቢመለሱም በድጋሚ ተመልሰው ወደ ደብረብርሃን ቻይና ካምፕ ለመግባት ቢሞክሩም መመለስ እንደማይችሉ እና ስማችሁ መሰረዙን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

አረጋዊያን ህፃናት እንዲሁም ሴቶች ወጥተው መስራት ስለማይችሉ ወጣቶች ወጥተን እንዳንሰራ የመታወቂያ ጉዳይ ሌላ እንቅፋት ሆኖብናል ብለዋል፡፡

https://tinyurl.com/ymkzwfc8

ማርታ በቀለ

#ተፈናቃዮች

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ 8፣2016 ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን የሚገኙ ተፈናቃዮች በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀያቸው ይመለሳሉ ቢባልም እ....

ሚያዝያ  8፣2016የሞቃዲሾው ጥልማሞት - በእሸቴ አሰፋhttps://youtu.be/nspYKTHN29s     #ዲፕሎማት  የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…Telegram:  Y...
16/04/2024

ሚያዝያ 8፣2016

የሞቃዲሾው ጥልማሞት - በእሸቴ አሰፋ

https://youtu.be/nspYKTHN29s

#ዲፕሎማት

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

የሞቃዲሾው ጥልማሞት - በእሸቴ አሰፋየፖሊስ መኮንኑ፣ መምህሩ፣ ዲፕሎማቱ እንዲሁም የመረጃ እና ደህንነት ባለሞያው የዶ/ር አስማማው ቀለሙ ማን ነበሩ? (ተያያዥ ዘገባ)https://tinyurl.com/mx5t93uuሚ.....

ሚያዝያ  8፣2016በጄኔራል ዊንጌት ት/ቤት አካባቢ የሚገኘው ይስሐቅ ኦቲዝም ማዕከል የአዕምሮ እድገት ውሱንት ላለባቸውን ህፃናት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናገረ፡፡ https://tinyurl....
16/04/2024

ሚያዝያ 8፣2016

በጄኔራል ዊንጌት ት/ቤት አካባቢ የሚገኘው ይስሐቅ ኦቲዝም ማዕከል የአዕምሮ እድገት ውሱንት ላለባቸውን ህፃናት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናገረ፡፡

https://tinyurl.com/ynhfsvsy

ወንድሙ ሀይሉ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ 8፣2016 በጄኔራል ዊንጌት ት/ቤት አካባቢ የሚገኘው ይስሐቅ ኦቲዝም ማዕከል የአዕምሮ እድገት ውሱንት ላለባቸውን ህፃናት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናገረ፡፡ ወንድሙ ሀይሉ ...

ሚያዝያ  8፣2016ጅቡቲን እንደመሸጋገሪያነት በመጠቀም ወደ ተለያዩ ሀገራት ለመሄድ፤ በዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ መታሰቡ ተሰምቷል፡፡ በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገል...
16/04/2024

ሚያዝያ 8፣2016

ጅቡቲን እንደመሸጋገሪያነት በመጠቀም ወደ ተለያዩ ሀገራት ለመሄድ፤ በዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ መታሰቡ ተሰምቷል፡፡

በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎ ዋና ዳይሬክተር የተመራ የልዑክ ቡድን ለዚሁ ጉዳይ ጅቡቲ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

https://tinyurl.com/ye2y3x33

ንጋቱ ሙሉ ያሰናዳውን በያሬድ እንዳሻው

#ጅቡቲ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ 8፣2016 ጅቡቲን እንደመሸጋገሪያነት በመጠቀም ወደ ተለያዩ ሀገራት ለመሄድ፤ በዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ መታሰቡ ተሰምቷል፡፡ በኢሚግሬሽን እና ዜግነት...

ሚያዝያ  8፣2016  በኢትዮጵያ በማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ የሚተላለፍ የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ መጠኑ ጨምሯል ተባለ።የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ይህንን ያለው፤ ዛሬ...
16/04/2024

ሚያዝያ 8፣2016

በኢትዮጵያ በማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ የሚተላለፍ የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ መጠኑ ጨምሯል ተባለ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ይህንን ያለው፤ ዛሬ በማህበራዊ የትስስር ገጾች የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ ሀገራዊ ሪፖርትን ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው።

ጥናቱ የተካሄደው 5 የማህበራዊ ገፆችን ትኩረት አድርጎ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ፣ ኤክስ፣ ቴሌግራም እና ቲክቶክ ላይ ጥናቱ እንደተካሄደ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሲናገር ሰምተናል።

በሪፖርቱም የጥላቻ እና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭቱ ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር ብሄር ተኮር እና የፖለቲካ ጉዳዮች ይበዙ እንደነበር የተናገው ባለስልጣኑ በ2016 ግማሽ አመት ከብሄር ጉዳዩች ይልቅ የፖለቲካ ሀሰተኛ መረጃ ስርጭቶች እንደጨመረ ጥናቱ ያሳያል ተብሏል።

በኤክስ ገፅ 66 በመቶ፣ በፌስቡክ 63 በመቶ፣ በቴሌግራም 59 በመቶው በፅሁፍ የተሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች ሲሆኑ በምስል እና በፅሁፍ የተላለፉት ደግሞ በኤክስ 12 በመቶ እና በቴሌግራም 18 በመቶ መሆኑ ተነግሯል።

በቪዲዮ ከተላለፉ ሀሰተኛ መረጃዎች መካከል ደግሞ በቲክቶክ https://tinyurl.com/32xf9a45



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

በኢትዮጵያ በማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ የሚተላለፍ የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ መጠኑ ጨምሯል ተባለ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ይህንን ያለው፤ ዛሬ በማህበራዊ...

ሚያዝያ  8፣2016  የፖሊስ መኮንኑ፣ መምህሩ፣ ዲፕሎማቱ እንዲሁም የመረጃ እና ደህንነት ባለሞያው የዶ/ር አስማማው ቀለሙ የቀብር ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት ይፈፀማል፡፡ዶ/ር አስማማው ቀለሙ...
16/04/2024

ሚያዝያ 8፣2016

የፖሊስ መኮንኑ፣ መምህሩ፣ ዲፕሎማቱ እንዲሁም የመረጃ እና ደህንነት ባለሞያው የዶ/ር አስማማው ቀለሙ የቀብር ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት ይፈፀማል፡፡

ዶ/ር አስማማው ቀለሙ ማን ነበሩ?

እሸቴ አሰፋ

https://tinyurl.com/mx5t93uu

#ዲፕሎማት

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ  8፣2016  በዩኔስኮ የተመዘገበው የሸዋል ኢድ በዓል ከዛሬ ጀምሮ በሀረሪ ክልል መከበር ይጀምራል፡፡ እንግዶችም ወደ ሀረር እየገቡ ነው ተብሏል፡፡https://tinyurl.com/mt...
16/04/2024

ሚያዝያ 8፣2016

በዩኔስኮ የተመዘገበው የሸዋል ኢድ በዓል ከዛሬ ጀምሮ በሀረሪ ክልል መከበር ይጀምራል፡፡

እንግዶችም ወደ ሀረር እየገቡ ነው ተብሏል፡፡

https://tinyurl.com/mtfhbedt

በረከት አካሉ

#ሀረር

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ 8፣2016 በዩኔስኮ የተመዘገበው የሸዋል ኢድ በዓል ከዛሬ ጀምሮ በሀረሪ ክልል መከበር ይጀምራል፡፡ እንግዶችም ወደ ሀረር እየገቡ ነው ተብሏል፡፡ በረከት አካሉ #ሸዋ....

ሚያዝያ  8፣2016  በአማራ ክልል በአማካኝ አንድ መፅሐፍ ለ70 ተማሪዎች የደረሰበት አካባቢዎች መኖራቸዉን፤  የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አረጋግጫለው አለ፡፡የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የባህ...
16/04/2024

ሚያዝያ 8፣2016

በአማራ ክልል በአማካኝ አንድ መፅሐፍ ለ70 ተማሪዎች የደረሰበት አካባቢዎች መኖራቸዉን፤ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አረጋግጫለው አለ፡፡

የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት፤ ክልሉ የትምህርት ጥራትን በተመለከተ ያደረገውን የክትትል ሪፖርት ለሸገር ራድዮ ተናግሯል፡፡

በዚህም በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች የመፅሐፍ ጥምርታ በአማካኝ አንደ መፅሐፍ ለ60 ተማሪ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ አንድ መፅሐፍ ለ70 ተማሪ ነው የሚሰጠው ያሉን የህዝብ እንባ ጠባቂ የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጋሻነው ደሴ ናቸዉ፡፡

ለተማሪዎች የመማሪያ መጽሐፍት በሶፍት ኮፒ ቢሰጥም ተማሪዎች ማንበብያ ማለትም እንደ ስልክ ፣ ታብሌት እና ላፕቶፕ ሰለሌላቸው እየተቸገሩ ነው፤ ይህም በትምህርት ጥራት ላይ ችግር እያስከተለ ነው ተብሏል፡፡

ጽህፈት ቤቱ ሌላው ግኝቴ ነው ያለው፤ በባህርዳር ዙሪያ በ71 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ባረደኩት ክትትልም ከ71ዎቹ ትምህርት ቤቶች 50ዎቹ ምንም ዓይነት መጸዳጃ ቤት የሌላቸው ሲሆን https://tinyurl.com/327mzxp5

#ተማሪዎች #ባህርዳር

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

በአማራ ክልል በአማካኝ አንድ መፅሐፍ ለ70 ተማሪዎች የደረሰበት አካባቢዎች መኖራቸዉን፤ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አረጋግጫለው አለ፡፡ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የባህርዳር ቅርንጫፍ ...

ሚያዝያ  7፣2016  የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ከእንግዲህ የተለያዩ ማህበራዊ ውይይቶችን ስትጠቀሙ አንዳች ክፍያ የማትጠየቁበትን አገልግሎት ጀምሮላቹሀል ተባለ። ይህ የተባለው ዛሬ ኢትዮ ቴሌኮ...
15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016

የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ከእንግዲህ የተለያዩ ማህበራዊ ውይይቶችን ስትጠቀሙ አንዳች ክፍያ የማትጠየቁበትን አገልግሎት ጀምሮላቹሀል ተባለ።

ይህ የተባለው ዛሬ ኢትዮ ቴሌኮም ፅሁፍ ለመላላላክ ቪዲዮና ሌሎችንም ማህበራዊ ጉዳዮች የሚያበረታ አገልግሎት መጀመሩን በተናገረበት ጊዜ ነው ።

ስልካችሁ ውስጥ ሳንቲም ኖረም አልኖረም ክፍያ ሳትጠየቁ ከወዳጅ ቤተሰብ ጋር ወግ ለመሰለቅ የቀጥታ ውይቶችንም(online chat) ለማድረግ እንደሚቻል ዛሬ የተጀመረው አገልሎት ይፈቅዳል ተብሏል።

ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞቹ ማህበራዊ ውይቶችን እና ወጎችን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ የሚገናኙበትን አገልግሎት በቴሌ ብር ሱፐር አፕ ምንም አይነት ተጨማሪ የኢንተርኔት ክፍያ ሳይጠይቅ ጀምሯል።

ደንበኞች መረጃዎችን መቀባበል የሚችሉበትና ማህበራዊ ወጎቻቸውን የሚያቀላጥፉበት አገልግሎት ለደንበኞች መቅረቡንም ሰምተናል።

አገልግሎቱም "ቴሌ ብር ኢንጌጅ" ተብሏል።

በዚህ አገልግሎት ደንበኞች ከቴሌብር አገልግሎት ባለፈ ስለ ቢዝነስ፣ ስለማህበራዊ ጉዳይና ሌሎችንም ወግ ማድረግ የሚችሉበት ነው ተብሏል።

በ ቴሌ ብር ኢንጌጅመንት ፅሁፍ ለመላላክ፣ ቪዲዮና የድምፅ ፉይሎችን ለመቀባበል እንዲሁም ሰነዶችን ለመጋራት የሚያስችል እንደ ማህበራዊ ትስስር ገፅ አይነት አመቺ አገልግሎት መሆኑን ኩባንያው አስረድቷል።

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ይህ አገልግሎት ኢትዮዽያ በራሷ ልጆች ያዘጋጀችው ፣ከቴሌ ብር እና አገልግሎቱ ባለፈ መረጃና አብሮነትን ፣ማህበራዊ ህይወትን የሚያበረታ ነው ብለዋል ።

የቴሌ ብር ኢንጌጅ ግለሰብም ሆኑ የቢዝነስ ደንበኞች የተናጠል ወይም የቡድን የቀጥታ ውይይቶችን
(online chat) ለማድረግ ያስችላል ተብሏል ።

የግብይት መረጃ ለመቀባበል በውይይት ወቅት ደንበኞች ከመተግበርያው ሳይወጡ ስልክ ሳይደውሉ እዛው ገንዘብ ለመጠየቅ ለመላክና ለመቀበል ሂሳብም ለመጋራት ያስችላል ተብሎለታል።

ይህ አገልግሎት መረጃን ከመለዋወጥ ባለፈ ማህበራዊ ህይወትን የሚያጠነክር መሆኑም ተሰምቷል።

ኢትዮ ቴሌኮም በዲጅታል አለም የትብብር ባህል እንዲዳብር ፣ክህሎትና ሌላውም ለሁሉ እንዲደርስ የዴቨሎፐሮች ማህበረሰብ እንዲፈጠሩ የሚያግዝ የዴቨሎፐር ፖርታል ማዘጋጀቱን ተናግሯል።

ኩባንያው የዲጅታል ስነ ምህዳሩን ለማስፋት ዴቨሎፐሮች ከቴሌ ብር ሱፐር አፕ ጋር ሲስተሞቻቸውን በማስተሳሰር ምርትና አገልግሎቶች ባጠረ ግዜ ተደራሽ ለመማድረግ የዴቨሎፐር ፖርታል ጀምሯል ተብሏል።

ተህቦ ንጉሴ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

መቆያ - ቅስቀሳ የዘራው ጥላቻ እና ጥላቻ ያጋጋለው እልቂት! በእሸቴ አሰፋ ሚያዝያ 5፤2016. https://youtu.be/lY9dLv2q-yM           ውድ የሸገር ቤተሰቦች፣ ሌሎች ማ...
15/04/2024

መቆያ - ቅስቀሳ የዘራው ጥላቻ እና ጥላቻ ያጋጋለው እልቂት! በእሸቴ አሰፋ ሚያዝያ 5፤2016.

https://youtu.be/lY9dLv2q-yM



ውድ የሸገር ቤተሰቦች፣ ሌሎች ማራኪ የመቆያ መሰናዶቻችን ይመልከቱ…👇👇👇👇👇👇👇

https://www.youtube.com/watch?v=Cq676-5oCak&list=PLep9COCl9DsZHLRzElVug3fSDuMJwYujJ

Mekoya - ቅስቀሳ የዘራው ጥላቻ እና ጥላቻ ያጋጋለው እልቂት! Rwandan Genocide በእሸቴ አሰፋ Eshete Assefa በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት የተፈፀመበትን 30ኛ ዓመት she...

ሚያዝያ  7፣2016  ኢትዮጵያ በውሀ ሀብቷ አጠቃቀም ዙሪያ ከነግብፅና ሱዳን ጋር የገባችበት ውዝግብ በሀገር ውስጥም በክልሎች መካከል ሊነሳ የሚችልበት እድል እንደሚኖር ባለሞያዎች ይናገራሉ፡...
15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016

ኢትዮጵያ በውሀ ሀብቷ አጠቃቀም ዙሪያ ከነግብፅና ሱዳን ጋር የገባችበት ውዝግብ በሀገር ውስጥም በክልሎች መካከል ሊነሳ የሚችልበት እድል እንደሚኖር ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡

የውሃ አስተዳደር ስራን በተቀናጀ መንገድ መምራት ካልተቻለ በክልሎች መካከል ያመግባባት ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡

https://tinyurl.com/yaffjufk

ቴዎድሮስ ወርቁ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ  7፣2016  በኦሮሚያ ክልል ባለው የሰላም እጦር ምክንያት 240 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ተሰማ፡፡ ትምህርት ቤቶቹ፤ ከ131 ሺህ በላይ ተማሪዎች ይማሩባቸው የነበሩ መሆናቸውን ሰም...
15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016

በኦሮሚያ ክልል ባለው የሰላም እጦር ምክንያት 240 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ተሰማ፡፡

ትምህርት ቤቶቹ፤ ከ131 ሺህ በላይ ተማሪዎች ይማሩባቸው የነበሩ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

https://tinyurl.com/2k7cpc6p

ፋሲካ ሙሉወርቅ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ 7፣2016 በኦሮሚያ ክልል ባለው የሰላም እጦር ምክንያት 240 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ተሰማ፡፡ ትምህርት ቤቶቹ፤ ከ131 ሺህ በላይ ተማሪዎች ይማሩባቸው የነበሩ መሆናቸውን ሰምተናል፡...

ሚያዝያ  7፣2016  ሀይማኖቶች፤ ለሰላም፣ ለሰብአዊ ክብርና ነፃነት መጠበቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡ ሁለተኛው አለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡...
15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016

ሀይማኖቶች፤ ለሰላም፣ ለሰብአዊ ክብርና ነፃነት መጠበቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡

ሁለተኛው አለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

https://tinyurl.com/r3dxh25b

ያሬድ እንዳሻው

#ሀይማኖት

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ 7፣2016 ሀይማኖቶች፤ ለሰላም፣ ለሰብአዊ ክብርና ነፃነት መጠበቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡ ሁለተኛው አለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው.....

ሚያዝያ  7፣2016  - ዓለም አቀፍ ትንታኔኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት መክፈቷ ለአሜሪካ የፈሩት ይደርሳል ሆኖባታል፡፡ኢራን በእስራኤል ላይ የሚሳየል እና የድሮን ዶፍ አዝንባባታለች፡፡ የአሜ...
15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016 - ዓለም አቀፍ ትንታኔ

ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት መክፈቷ ለአሜሪካ የፈሩት ይደርሳል ሆኖባታል፡፡

ኢራን በእስራኤል ላይ የሚሳየል እና የድሮን ዶፍ አዝንባባታለች፡፡

የአሜሪካ ጦርም እስራኤልን ከጥቃት ለመጠበቅ በአየር መከላከያው ከጎኗ ተሰልፋለች፡፡

https://youtu.be/t6NssY5CRpk

የኔነህ ከበደ

#አሜሪካ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ 7፣2016 ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት መክፈቷ ለአሜሪካ የፈሩት ይደርሳል ሆኖባታል፡፡ኢራን በእስራኤል ላይ የሚሳየል እና የድሮን ዶፍ አዝንባባታለች፡፡ የአሜሪካ ጦርም እስራኤል.....

ሚያዝያ  7፣2016 ደመናን ተጠቅሞ ዝናብ የማዝነብ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ መሰራት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ መላውን በሀገሪቱ ለማስፋፋት እና ችግር ፈቺ ለማድረግ የተለያዩ ተቋማት በጋራ እየሰሩ ነ...
15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016

ደመናን ተጠቅሞ ዝናብ የማዝነብ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ መሰራት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡

መላውን በሀገሪቱ ለማስፋፋት እና ችግር ፈቺ ለማድረግ የተለያዩ ተቋማት በጋራ እየሰሩ ነው ተብሏል፡፡

https://tinyurl.com/yjvckpm8

ምንታምር ፀጋው



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ  7፣2016 በኢትዮጵያ የፍትህ ተቋማት መካከል ተግባብቶ መስራት ፈተና እየሆነ መምጣቱ ይነገራል፡፡ ከዚህም ውስጥ በፍርድ ቤቶች የተወሰኑ ጉዳዮች በፖሊስ ተፈፃሚ አለመደረጋቸው አንዱ ...
15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016

በኢትዮጵያ የፍትህ ተቋማት መካከል ተግባብቶ መስራት ፈተና እየሆነ መምጣቱ ይነገራል፡፡

ከዚህም ውስጥ በፍርድ ቤቶች የተወሰኑ ጉዳዮች በፖሊስ ተፈፃሚ አለመደረጋቸው አንዱ ነው፡፡

ይህም በተለይ በፍ/ቤቶች አሰራር ላይ ጫና መፍጠሩን የክልል ፍ/ቤቶች ተናግረዋል፡፡

https://tinyurl.com/y5etuc9t

በረከት አካሉ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ 7፣2016 በኢትዮጵያ የፍትህ ተቋማት መካከል ተግባብቶ መስራት ፈተና እየሆነ መምጣቱ ይነገራል፡፡ ከዚህም ውስጥ በፍርድ ቤቶች የተወሰኑ ጉዳዮች በፖሊስ ተፈፃሚ አለመደረጋቸው አን....

ሚያዝያ  7፣2016 ኢትዮጵያዊያን ሴት ባለፀጎች በአለም ገበያ በሚፈለገው ልክ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንዲሁም በተገቢው መንገድ ጥራት ያለው ምርት እንዲያመርቱ  ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ተብሏ...
15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016

ኢትዮጵያዊያን ሴት ባለፀጎች በአለም ገበያ በሚፈለገው ልክ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንዲሁም በተገቢው መንገድ ጥራት ያለው ምርት እንዲያመርቱ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል፡፡

https://tinyurl.com/42vmfjrm

ፋሲካ ሙሉወርቅ

#ሴቶች #ድጋፍ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ 7፣2016 ኢትዮጵያዊያን ሴት ባለፀጎች በአለም ገበያ በሚፈለገው ልክ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንዲሁም በተገቢው መንገድ ጥራት ያለው ምርት እንዲያመርቱ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ተብ....

ሚያዝያ  7፣2016 በባህር ዳር አካባቢ ዘረፋ እና ቃጠሎ የደረሰባቸው የአበባ እርሻዎች ወደ ስራ አልገቡም ተብሏል፡፡https://tinyurl.com/mr2786uxያሬድ እንዳሻው         ...
15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016

በባህር ዳር አካባቢ ዘረፋ እና ቃጠሎ የደረሰባቸው የአበባ እርሻዎች ወደ ስራ አልገቡም ተብሏል፡፡

https://tinyurl.com/mr2786ux

ያሬድ እንዳሻው

#ቃጠሎ #ዝርፊያ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ 7፣2016 በባህር ዳር አካባቢ ዘረፋ እና ቃጠሎ የደረሰባቸው የአበባ እርሻዎች ወደ ስራ አልገቡም ተብሏል፡፡ ያሬድ እንዳሻው #ቃጠሎ #ዝር...

ሸገር ካፌ፦ የትውስታ ፖለቲካ በወቅታዊት ኢትዮጵያ ተግባሩ ያሬድ እና ዮናስ አሽኔ ከመዓዛ ብሩ ጋር  - ሚያዝያ 6፤2016 https://youtu.be/f5VrEPY8ia4              ...
14/04/2024

ሸገር ካፌ፦ የትውስታ ፖለቲካ በወቅታዊት ኢትዮጵያ ተግባሩ ያሬድ እና ዮናስ አሽኔ ከመዓዛ ብሩ ጋር - ሚያዝያ 6፤2016

https://youtu.be/f5VrEPY8ia4

#ፖለቲካ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…Telegram: t.ly/ShegerWebsite: t.ly/ShegerFM YouTube: t.ly/SHEGERTiktok: https://bit.ly/44Dd6Il Sheger FM 102.1 Radio is The F...

የጨዋታ እንግዳ፦ ለጥበብ ታማኝ ሆኖ የኖረው ሠዓሊ ጥበበ ተርፋ መታሰቢያ! ከመዓዛ ብሩ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ክፍል 2 - ሚያዝያ 5፣2016https://youtu.be/CY_aq2Pj5zw     ...
13/04/2024

የጨዋታ እንግዳ፦ ለጥበብ ታማኝ ሆኖ የኖረው ሠዓሊ ጥበበ ተርፋ መታሰቢያ!

ከመዓዛ ብሩ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ክፍል 2 - ሚያዝያ 5፣2016

https://youtu.be/CY_aq2Pj5zw

#ጥበብ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Yechewata Engida -“ለስዕል ነፍስ የሚሰጠው የእያንዳንዱ ሰው እውነታ ነው”Artist Tibebe Terffa With Meaza Birru P...

ትዝታ ዘ አራዳ - ባለቅኔው መንግስቱ ለማ ወደ ኪነ-ጥበብ ያመላከታቸውን የልጅነት ህይወት! በተፈሪ ዓለሙ - ሚያዝያ 5፣2016https://youtu.be/nt4FrGZ1u-A
13/04/2024

ትዝታ ዘ አራዳ - ባለቅኔው መንግስቱ ለማ ወደ ኪነ-ጥበብ ያመላከታቸውን የልጅነት ህይወት! በተፈሪ ዓለሙ - ሚያዝያ 5፣2016

https://youtu.be/nt4FrGZ1u-A

Sheger Tizita ze Arada - ባለቅኔው መንግስቱ ለማ ወደ ኪነ-ጥበብ ያመላከታቸውን የልጅነት ህይወት! Mengistu Lemma በተፈሪ ዓለሙ...

Address

Addis Ababa Bahirdar Road
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 00:00
Tuesday 08:00 - 00:00
Wednesday 08:00 - 00:00
Thursday 08:00 - 00:00
Friday 08:00 - 00:00
Saturday 08:00 - 01:00
Sunday 08:00 - 00:00

Telephone

+251111272754

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SHEGER FM 102.1 RADIO posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to SHEGER FM 102.1 RADIO:

Videos

Share

Category



You may also like