14/02/2024
ሰላም ወዳጆቼ ይህ
ተውዳጁ #የከእርስዎ #ለእርስዎ.. .ዝግጅቴ ነው!
-በዚህ አምድ ዘውትር በሣምንት አንድ ቀን ወደ እናንተ የሚደርስ ዝግጅት አምድ ክፍል ነው!
#ማህበረሰባዊ #ግለነካዊ... #ኢኮኖሚያዊ #ፖለቲካዊ
#ሽሙጥ #ወጋ #ወጋ #ጥያቄዎች #ከእርስዎ #ይላካሉ ለእርስዎ.. .ከአዘጋጁ ምላሽ ያገኛሉ!
-እየተዝናኑ ሃሳብዎን ያጋሩ
ጥያቄዎትን...በዚሁ ገፅ ያጋሩ.. .በ09 11 85 57 62
ከእርስዎ ለእርስዎ ብለው ይደውሉ!
በጋዜጠኛና ፕረሞተር፡-ወንድወሰን(ማዕላፍ)ኃይሉ/W.H.K/
የዕለተ ዕሮብ 07/06/ 2016 ዓ.ም
፨ ከዘንድሮ የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ምን እንጠብቅ❓
♦መሳፍንት (ከቸርቸር)
♥ፎቶ ብቻ ተነሳስቶ አለመመለስን❗
፨ ለመኖር ብላ ለመብላት አትኑር ...የሚሏት ጥቅስ ዘንድሮ በምን ተቀየረ❓
♦ምንያርጋቸው(ከጎተራ)
♥ተኖረና ተሞተ
፨ ይሄ ህዝብ ፖስፖርት ስለመጣለት የተደሰተ ከነ ነፃ ቪዛ ጋር ቢመጣለት ምን ሊሆን ነው❓
♦አደፍርስ(ከለገሃር)
♥ የሃገር ውስጥ ዲያስፖራ
፨ በፊት ቢቸግር ጤፍ ብድር ይባላል ዘንድሮስ❓
♦ቤቴልሄም(ከአራብሳ)
♥ስንዴ አለኝ ከማሳ ላይ ዱቄቱን ግን እላይ
፨ የዘንድሮ ፍቅር ሲይዝ ምንድንነው የሚያደርገው❓
♦ማንያዘዋል(ከአብነት)
♥የተሰጣ ልብስ...ቂ...ቂ...ቂ...
፨ ያፈቀርኳት ልጅ ሚስት አለችህ አለችኝ ምን ልበላት❓
♦እያደርአዲስ(ከመርካቶ)
♥ሸጊት በአንቺ ላይ በአንቺ ላይ ይደረባል ወይ በአንቺ ላይ
፨ፖለቲካ+ኑሮ ውድነት=ይሆናል ምንድን ነው?
♦ሰው አለው(ከኳስ ሜዳ)
♥አግኝቶ ማጣት
፨ እየሄድን ያልሄድነው ለምንድንነው?
♦አምሳል(ከኬላ)
♥እኛ ወደ ቤታችን እንጂ ቤታችን ወደ እኛ ስለማይመጣ❗