Zebra Communications

Zebra Communications Zebra Communications works for the better enhancement of the community via communication platforms.

30/08/2024

#ትኩረት

የኦሞ ወንዝ የአፈር ክተራ ስራ ከህዝብ አቅም በላይ ሆኗል።

ውሃው እጅግ ከፍተኛ ግፊት ያለው በመሆኑ እየተሰሩ ያሉ የአፈር ክትሮችን በመስበር በድጋሜ በኦሞራቴ ከተማ ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል።

The one being carried is a Christian called Sameer, and the one carrying him is a blind Muslim called Muhammed.Sameer wo...
24/08/2024

The one being carried is a Christian called Sameer, and the one carrying him is a blind Muslim called Muhammed.

Sameer would depend on Muhammed for transportation in the busy streets of Damascus, and Muhammed also depended on Sameer to help him navigate, and pass obstacles.

Only one of them was able to walk and only one of them was able to see. They were both orphans and lived together in the same room. They were forever together.

When Sameer died, Muhammed stayed in his room crying for a week, and as a result he died after that week from sadness.

May God return world to being that place where the all religions can live side by side, in peace, comfort and friendship.

God's plan is always the best. Sometimes the process is painful and hard. But don't forget that when God is silent, He's doing something for you.
Source: Light of Rumi page

በ 6 ወር ዉስጥ የሚጠናቀቀው የአርባ ምንጭ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም በመፋጠን ላይ ነዉ።
24/08/2024

በ 6 ወር ዉስጥ የሚጠናቀቀው የአርባ ምንጭ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም በመፋጠን ላይ ነዉ።

23/08/2024
በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍራ የተገደለችው የ7 ዓመቷ ህጻን ሔቨን ታሪክ የበርካቶችን ልብ የሰበረ ጉዳይ ሆኗል።ይህ ድርጊት የተፈጸመው ከዛሬ   በፊት በባህርዳር ከተማ እንደሆነ ዛሬም ድረስ መሪር ...
17/08/2024

በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍራ የተገደለችው የ7 ዓመቷ ህጻን ሔቨን ታሪክ የበርካቶችን ልብ የሰበረ ጉዳይ ሆኗል።

ይህ ድርጊት የተፈጸመው ከዛሬ በፊት በባህርዳር ከተማ እንደሆነ ዛሬም ድረስ መሪር ሀዘን ውስጥ የምትገኘው እናት " ኢዮሃ " በተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቀርባ ተናግራለች።

ሕጻን ሔቨን የተደፈረችው ተከራይተው ይኖሩበት በነበረ ግቢ አከራይ ነው።

የተደፈረችበት መንገድም ወደ ሽንት ቤት በምትሔድበት ጊዜ ጠብቆ ወደ ቤት በማስገባት ነው። እጅግ በጣም አሰቃቂም ነበር።

ህጻን ሔቨንን የደፈረው ወንጀለኛ በምትደፈርበት ወቅት አንገቷን አንቆ ፤ አፏን አፍኖ ድርጊቱን የፈጸመ ሲሆን ወድቃ የሞተች ለማስመሰል ደሟን አንጠባጥቦ በር ላይ ጥሏት መሄዱን እናት ታስረዳለች።

እናት ልጇን ብቻ አይደለም ያጣችው ፤ ፍትህ ስትጠይቅ ይህንን ግፍ ሰምተው እንዳልሰማ የሆኑ ጎረቤት እና ቤተሰቦች ፤ በጥቅም ወንጀለኛውን ነጻ ለማስወጣት የሰሩ ፤ እናትን ጭምር ተባብረው ለማጥፋት ረጅም ርቀት የተጓዙ ፤ ማስፈራሪያ ደርሷቸው ቃላቸውን ከመስጠት የጠፉ ሁሉ ለእናት ፈተና ሆነውባታል።

ይህም ሆኖ ጥቂት የሚባሉ (የሴቶች እና ህጻናት ወንጀል መሪማሪ ፖሊሷ፤ የሴቶችና ህጻናት ቢሮ) አንዳንዶቹ ማስፈራሪያ ጭምር እየደረሳቸው አግዘዋት ከብዙ መከራ በኋላ ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት ይፈረድበታል።

እናት ግን ዛሬም ትኩስ ሀዘን ላይ ነች።

ሥራ እየሰራች መኖር አልቻለችም።

ነገ ከእስር ሲለቀቅ እሷንም ጭምር ለመግደል እንደሚፈልግ ፤ ለዚህም ደግሞ ዳግም ሥራ ከጀመረችበት ቦታ ቤተሰቦቹ ተከታትለዋት ጥላ መውጣቷን እናት አስረድታለች።

ዛሬም እውነተኛ ፍትሕ አጥታ ትንከራተታለች።

ግፍ ላይ ግፍ !

በመሰረቱ በዚህች ምስኪን አንድ ፍሬ ፤ ክፉ ደግ በማታውቅ ህጻን ላይ አሰቃቂ የመድፈር እና ኃሏም ህይወቷን ያሳጣ የወንጀል ድርጊት የፈጸመ ሰው እንዴት 25 ዓመት ይፈረድበታል ? እውነት ይህ ማስተማሪያ ነው ? ወይስ ሌላ ነው ዓላማው ?

የሔቨን ታሪክ የብዙ ህጻናት ታሪክ ጭምር ነው።

ከዚህ በፊት ሴቶች፣ ህጻናት ጭምር ሲደፈሩ የሚተላለፉ የፍርድ ውሳኔዎች ህዝቡን እያስቆጣ መሆኑን አሳውቀን ነበር።

ዛሬም ፍትሕ ተጓድሏል። ፍትሕ ይስፈን።

ዛሬ አጋጣሚ ይህ ጉዳይ አደባባይ ወጣ እንጂ ስንቷ እናት ቤቷ ዘግያ እያለቀሰች ይሆን ? ስንት ሴቶች በግፍ ሰለባ ሆነው እያነቡ ይሆን ?

 #በቃ ! #ፍትህ
17/08/2024

#በቃ !
#ፍትህ




12 Reasons Why Reading Books Should Be Part of Your Life:1. Knowledge Highway: Books offer a vast reservoir of knowledge...
11/08/2024

12 Reasons Why Reading Books Should Be Part of Your Life:
1. Knowledge Highway: Books offer a vast reservoir of knowledge on virtually any topic imaginable. Dive deep into history, science, philosophy, or explore new hobbies and interests.
2. Enhanced Vocabulary: Regular reading exposes you to a wider range of vocabulary, improving your communication skills and comprehension.
3. Memory Boost: Studies suggest that reading can help sharpen your memory and cognitive function, keeping your mind active and engaged.
4. Stress Reduction: Curling up with a good book can be a form of mental escape, offering a temporary reprieve from daily anxieties and a chance to unwind.
5. Improved Focus and Concentration: In today's fast-paced world filled with distractions, reading strengthens your ability to focus and concentrate for extended periods.
6. Empathy and Perspective: Stepping into the shoes of fictional characters allows you to develop empathy and gain a deeper understanding of different perspectives.
7. Enhanced Creativity: Reading exposes you to new ideas and thought processes, potentially sparking your own creativity and problem-solving skills.
8. Stronger Writing Skills: Immersing yourself in well-written prose can improve your writing style, sentence structure, and overall communication clarity.
9. Improved Sleep Quality: Swap screen time for a book before bed. The calming nature of reading can help you relax and unwind, promoting better sleep quality.







09/08/2024
ከሰልን ሲጠቀሙ መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎችበተለይም ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ሲኖር ከሰልን በአማራጭ የኃይል ምንጭነት መጠቀም የተለመደ ተግባር ነው፡፡በመሆኑም ከሰልን ሰዎች ለተለያየ አገልግሎት...
10/07/2024

ከሰልን ሲጠቀሙ መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎች

በተለይም ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ሲኖር ከሰልን በአማራጭ የኃይል ምንጭነት መጠቀም የተለመደ ተግባር ነው፡፡

በመሆኑም ከሰልን ሰዎች ለተለያየ አገልግሎት ሲጠቀሙ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

ምክንያቱም አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ የከሰሉ ጭስ ሞትን ጨምሮ የዕድሜ ልክ ህመም ለሆኑት የአዕምሮ ጉዳትና የልብ በሽታ ስለሚያጋልጥ ነው ይላሉ፡፡

በጉዳዩ ላይ የተካሄዱ ጥናቶች እንደሚያመላክቱትም÷ የከሰል ጭስ በዓይን የማይታይና ሽታ አልባ መርዛማ ጋዝ አለው፡፡

ይህ ጋዝ የሚፈጠረውም ጋዝ፣ ዘይት፣ ከሰል ወይም እንጨት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው ባለማለቃቸው መሆኑ ይጠቀሳል፡፡

የከሰል ጭስ ባለበት አካባቢ አየር ወደ ውስጥ በሚሳብበት ጊዜ÷ በደም ውስጥ በመግባት የቀይ የደም ኅዋስ አካል የሆነውና ኦክስጅን ተሸክሞ ለተያዩ የሰውነት ክፍሎች ከሚያደርሰው ሂሞግሎቢን ጋር በመቀላቀል ጉዳት ያስከትላል፡፡

ይህን ተከትሎም ደም ኦክስጅን መሸከሙን ያቆማል፤ በዚህ የተነሳ የኅዋሶቹ አነስተኛ ክፍሎች ይጎዳሉ፤ ብሎም ይሞታሉ፡፡

• በከሰል ጭስ (በካርበን ሞኖክሳይድ) የተጠቃ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች

የራስ ምታት፣ ራስ ማዞርና መታመም፣ የድካም ስሜትና ግራ መጋባት፣ ሚዛንን ለመጠበቅ መቸገር፣ የዕይታና የትውስታ ማጣት፣ ራስን መሳት፣ በአንድ ነገር ላይ አትኩሮት ማጣት፣ የሆድ ህመም እንዲሁም ለመተንፈስ መቸገር ምልክቶች ሊታዩበት እንደሚችሉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
• የከሰል ጭስን እንዴት መከላከል ይቻላል?

በከሰል ምግብ ማብሰል ሲያስፈልግ በቂ አየር እንዲያገኝ ከተቻለ ከቤት ውጭ ማብሰል፤ ከቤት ውጭ ማብሰል ካልተቻለ ደግሞ ሙሉ በመሉ ከተቀጣጠለና ጭሱ መጥፋቱ ሲረጋገጥ ወደ ቤት ማስገባት ይመከራል፡፡

በተጨማሪም የከሰል ምድጃ እየተጠቀሙ በር እና መስኮት አለመዝጋት፣ በከሰል ምግብ አብስለው ሲጨርሱ በውኃ ማጥፋትና በርና መስኮት በመክፈት ቤቱን ማናፈስ እንዲሁም ከሰል ቤት ውስጥ አለማቀጣጠልን ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

ከዚህ ባለፈም ከሰል ቤት ውስጥ አቀጣጥሎ ማሸለብ ወይም መተኛት አደጋው የከፋ በመሆኑ ከእነዚህ ድርጊቶች ይቆጠቡ።

07/07/2024

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የደረጃ 'ሐ' ግብር ከፋዮች ገቢ አሰባሰብ ከነገ ጀምሮ ለሚቀጥሉት 7 ተከታታይ ቀናት በሁሉም የክልሉ ማዕከላት ይካሄዳል ተባለ

ወላይታ ሶዶ፣ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም፦ የክልሉን የ 2017 ዓ.ም የገቢ ግብር ማስጀመሪያ ቀን በማስመልከት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ መግለጫ ሰጥተዋል።

በክረምቱ በልዩ ንቅናቄ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል ገቢ አሰባሰብ አንደኛው መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ ገልፀዋል።

በክልሉ በደረጃ 'ሀ'፣ 'ለ' እና 'ሐ' ከ 120 ሺ በላይ ግብር ከፋዮች መኖራቸዉን የጠቀሱት ኃላፊዋ 112 ሺ 448 ግብር ከፋዮች የተካተቱበት የደረጃ 'ሐ' ግብር ከፋዮች ገቢ አሰባሰብ ከ ሐምሌ 1 ጀምሮ ለሚቀጥሉት 7 ተከታታይ ቀናት በሁሉም የክልሉ ማዕከሎች እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

በበጀት ዓመቱ ከ ደረጃ 'ሐ' ግብር ከፋዮች ከ 500 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንና ለዚህም በየደረጃው ከሚገኙ 138 የታክስ ማዕከላት በተጨማሪ 50 የታክስ ማዕከላት በመክፈት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን አስረድተዋል።

በአጠቃላይ በሁሉም የግብር ደረጃዎች ያለዉን የገቢ አሰባሰብ እስከ ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም ድረስ ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑንና በተጠናቀቀው የበጀት ዓመትም 10 ሺ 712 አዳዲስ ግብር ከፋዮች መመዝገባቸውን ወ/ሮ አለምነሽ ገልፀዋል።

ተቋሙ ከ ኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በገባው ዉል መሰረት በዘንድሮው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በክልሉ የሚገኙ ከ 30 ሺ በላይ የደረጃ 'ሐ' ግብር ከፋዮች በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ግብራቸዉን እንደሚከፍሉም በመግለጫው ተብራርቷል።

በየአመቱ የሚከናወነዉን የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ምክንያት በማድረግ የቢሮዉ አመራሮችና ባለሙያዎችን በማስተባበር የ ሁለት አረጋዊያንና አቅመ ደካሞች የቤት ግንባታ እንደሚካሄድም ኃላፊዋ ጠቅሰዋል።

በክልሉ ያሉ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን በተገቢው መንገድ ለመመለስ ገቢ አሰባሰብ በአግባቡ መመራት እንዳለበት ገልፀዉ ህብረተሰቡም ሳይጨናነቅ በተዘጋጁ ማዕከላት በመምጣት ግብሩን በተቀመጠው ጊዜ እንዲከፍል ጥሪ አቅርበዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ 120 ሺ በላይ ግብር ከፋዮች መኖራቸዉ የተገለፀ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከ 20 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ መታቀዱ በመግለጫው ተመላክቷል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ሊንኮች፦
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/SouthEthiopiaRegionProsperityParty
ቴሌግራም፡ https://t.me/SouthEthiopiaProsperityParty
ቲክቶክ፡ https://vm.tiktok.com/ZMMkpaEUR
ኢ-ሜይል፡ [email protected]

01/03/2024

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ከተሞች የተካሄዱ ሕዝባዊ የዉይይት መድረኮች ዉጤታማ ናቸው ተባለ

ወላይታ ሶዶ፤ የካቲት 22/06/2016 የአመራሩና አባላትን የማስፈፀም አቅም የሚያጎለብቱ ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

በብልፅግና ፓርቲ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዮሐንስ በየነ በክልሉ በሚገኙ ከተሞች የተካሄዱ ሕዝባዊ የዉይይት መድረኮች የሕብረተሰቡን ጥያቄዎች ከመሰረቱ ተገንዝቦ ለመፍታት ዕድል የሰጡ መሆናቸውን ገልፀዋል።

"ሀብት የመፍጠር ጉዟችን ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች" በሚል መሪ ቃል በሁሉም የክልሉ ከተሞች የተካሄደዉ ሕዝባዊ የዉይይት መድረክ ተግባቦት የተፈጠረበት፣ ልምድ የተቀሰመበትና ግቦቹን ባሳካ መንገድ መጠናቀቁንም አቶ ዮሐንስ አስረድተዋል።

መድረኩ በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን ባላገናዘበ ሁኔታ በተግዳሮቶች ብቻ የታጠረ አከባቢ ያለ የሚመስላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች እራሳቸውን ያዩበትና መለወጥ እንደሚቻል እምነት የፈጠሩበት እንደነበር አቶ ዮሐንስ ጨምረው ገልፀዋል።

በቀጣይም በየመድረኮቹ የተለዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በአጭርና ረጅም ጊዜ ዕቅድ ዉስጥ በማካተት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምላሽ የመስጠት ሥራ እንደሚሰራም አስታዉቀዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፓርቲው "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ርዕስ ለአጠቃላይ አመራርና አባላት የሰጠው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጨባጭ ለዉጦችን ያመጣና የመፈፀም አቅማቸውን ያሳደገ መሆኑን አቶ ዮሐንስ ተናግረዋል።

ፓርቲዉ ያነገባቸዉን ራዕዮች የሚያሳኩና የአመራሩና አባላትን አቅም የሚያሳድጉ መሰል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ለማወቅ ተችሏል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ርዕሰ በተሰጠው ስልጠና በሁሉም ማህበራዊ መሠረቶች በአጠቃላይ 1 ሚሊዮን 222 ሺ 223 አመራርና አባላት ተሳታፊ መሆናቸው ይታወሳል።

Address

Bole
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zebra Communications posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share


Other Social Media Agencies in Addis Ababa

Show All