27/10/2022
በ 2.4 ሚሊዮን ብር በIOM UN MIGRATION ድጋፍ እየተገነባ ያለው የገበያ ማዕከል ያለበት ደረጃ በከተማ አስተባባሪ አካላት ጉብኝት ተደርጓል ።
ጥቅምት 17/02/2015 ዓ.ም በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር በ IOM UN MIGRATION ድጋፍ በ 2.4 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተሰራ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ የደረሰው የገበያ ማዕከል ያለበት ደረጃ በከተማ አስተባባሪ አካላት ጉብኝት ተደርጓል ።
በጉብኝቱ ወቅት የቦዲቲ ከተማ ከንቲባ አቶ ደስታ ዳና:ከ IOM UN MIGRATION ድርጅት የግንባታ ስራውን የተረከበው YENOL CONSTRACTION ግንባታውን ወደ መጨረሻ ምዕራፍ ማድረሱንና ጨርሶ ለማስረከብ እያደረገ ያለውን ጥረት በማድነቅ በቀጣይ ርክክብ ለማድረግ የሚያስችሉ ውስን ስራዎች በፍጥነት ሊጠናቀቁ እንዲሚገባ አሳስበዋል።
የግንባታ ሂደቱን በቅርበት በገንዘብ ከመደገፍ ውጭ ግንባታው ተጠናቆ ርክክብ እንዲደረግ ክትትል እያደረጉ ያሉ የድርጅቱ ተወካዮችና የከተማው ኮንስትራክሽን ዘርፍ ባለሙያዎች ዕውቅና ያስፈልጋቸዋል ሲሉም ገልፀዋል።
ድርጅቱ የሰራው መልካም ስራ በከተማችን ዕድገት ላይ የራሱ የሆነ አዎንታዊ አሻራ ከማሳረፉ በላይ የስራ አጥነት ቁጥር የሚቀንስ እንደሆነም አቶ ደስታ አክለው ገልፀዋል ።
የገባያ ማዕከሉ ከስደት ተመላሽ ለሆኑ ሴቶች ታልሞ የተገነባ ሲሆን ግንባታው ተጠናቆ ርክክብ ሲደረግ ለታለመለት ዓላማ የማዋል ስራ እንደሚሰራ የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት ኃላፊና ም/ከንቲባ አቶ በረከት በላይነህ አሳውቀዋል ።