Ethiopian Media Network

Ethiopian Media Network እውነተኛ የመረጃ ምንጭ

13/01/2025

ስንቱን አስታወስኩት፣ ስንቱን አሰብኩት

ሰው ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው! በርታ 👍
08/01/2025

ሰው ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው!

በርታ 👍

Agriculture is 1st from top 5 profitable business in Africa. Human beings never eat Electronics except Organic food 🍲. A...
08/01/2025

Agriculture is 1st from top 5 profitable business in Africa.
Human beings never eat Electronics except Organic food 🍲.
Another female farmer meseret getachew wisely invested in Agriculture, from Hadiya, Ethiopia 🇪🇹

በሲዳማ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ71 ሰዎች ሕይወት አለፈ  በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን ቦና ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ  የ71 ሰዎች ሕይወት  አለፈ።የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮ...
29/12/2024

በሲዳማ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ71 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን ቦና ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ71 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ፣ አደጋው አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ሰርገኞችን ጭኖ ሲጓዝ በቦና ዙሪያ ወረዳ ጋላና ወንዝ ድልድዩን ስቶ ወደ ወንዝ በመግባቱ ነው የተከሰተው።

በዚህም እስካሁን የ71 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸው ፥ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በቦና አጠቃላይ ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተሉ ነው ብለዋል ።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ኮሚሽነሩ አመልክተዋል።

ትራምፕ ምርጫውን በ267 ድምጽ እየመሩ ነው47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ለመሆን ትራምፕ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን በ267 ድምጽ እየመሩ ነው፡፡270 ድምጽ ለማግኘት የ3 መቀመጫ ድምጽ ብቻ የቀራቸ...
06/11/2024

ትራምፕ ምርጫውን በ267 ድምጽ እየመሩ ነው

47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ለመሆን ትራምፕ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን በ267 ድምጽ እየመሩ ነው፡፡

270 ድምጽ ለማግኘት የ3 መቀመጫ ድምጽ ብቻ የቀራቸው የቀድሞ ፕሬዚዳንቱ በፍሎሪዳ ተገኝተው ለደጋፊዋቻቸው ንግግር እያደረጉ ነው፡፡

Ten Unknown Facts About   1. Founding and History: BMW, Bayerische Motoren Werke AG, was founded in 1916 in Munich, Germ...
06/10/2024

Ten Unknown Facts About

1. Founding and History: BMW, Bayerische Motoren Werke AG, was founded in 1916 in Munich, Germany, initially producing aircraft engines. The company transitioned to motorcycle production in the 1920s and eventually to automobiles in the 1930s.

2. Iconic Logo: The BMW logo, often referred to as the "roundel," consists of a black ring intersecting with four quadrants of blue and white. It represents the company's origins in aviation, with the blue and white symbolizing a spinning propeller against a clear blue sky.

3. Innovation in Technology: BMW is renowned for its innovations in automotive technology. It introduced the world's first electric car, the BMW i3, in 2013, and has been a leader in developing advanced driving assistance systems (ADAS) and hybrid powertrains.

4. Performance and Motorsport Heritage: BMW has a strong heritage in motorsport, particularly in touring car and Formula 1 racing. The brand's M division produces high-performance variants of their regular models, known for their precision engineering and exhilarating driving dynamics.

5. Global Presence: BMW is a global automotive Company

6. Luxury and Design: BMW is synonymous with luxury and distinctive design, crafting vehicles that blend elegance with cutting-edge technology and comfort.

7. Sustainable Practices: BMW has committed to sustainability, incorporating eco-friendly materials and manufacturing processes into its vehicles, as well as advancing electric vehicle technology with models like the BMW i4 and iX.

8. Global Manufacturing: BMW operates numerous production facilities worldwide, including in Germany, the United States, China, and other countries, ensuring a global reach and localized production.

9. Brand Portfolio: In addition to its renowned BMW brand, the company also owns MINI and Rolls-Royce, catering to a diverse range of automotive tastes and luxury segments.

10. Cultural Impact: BMW's vehicles often become cultural icons.

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በጎፋ ዞን ተገኝተው በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸዉን ወገኖች እያፅናኑ ነዉወላይታ ሶዶ፣ ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም፦ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/...
27/07/2024

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በጎፋ ዞን ተገኝተው በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸዉን ወገኖች እያፅናኑ ነዉ

ወላይታ ሶዶ፣ ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም፦ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በክልሉ ጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት ናዳ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውንና ህይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦችን በስፍራው ተገኝተው እያጽናኑ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በተፈጠረው የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸው ላለፉት ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀው ለሁሉም ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።

ፕሬዚዳንት ፑቲን በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁየሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የ...
25/07/2024

ፕሬዚዳንት ፑቲን በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ለኢትዮጵያ መንግስት ባስተላለፉት የሀዘን መልዕክት፤ በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ዜጎች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በፍጥነት እንዲያገግሙ ልባዊ ምኞታቸውን መግለጻቸውን በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ግለሰቦች እስከ ቅዳሜ ድረስ እንዲመልሱ አሳሰበየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ወይም ወደተለያየ ሂሳቦች ያስተላለፉ ግ...
21/03/2024

ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ግለሰቦች እስከ ቅዳሜ ድረስ እንዲመልሱ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ወይም ወደተለያየ ሂሳቦች ያስተላለፉ ግለሰቦች እስከ መጪው ቅዳሜ ድረስ በፈቃዳቸው እንዲመልሱ አሳስቧል፡፡

ሰሞኑን ባንኩ ካጋጠመው የሲስተም ችግር ጋር ተያይዞ የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ የወሰዱና ያልተገባ የገንዘብ እንቅስቃሴ ካከናወኑ ግለሰቦች መካከል ብዙዎች የተደረገላቸውን ጥሪ አክብረው ገንዘቡን ወደ ባንኩ ቅርንጫፎች እየቀረቡ እየመለሱ በመሆኑ ከስህተታቸው የመመለስ በጎ ምላሽነቱን እናደንቃለን ብሏል፡፡

ገንዘቡን ተመላሽ ያላደረጉ ግለሰቦችም እስከመጪው ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመቅረብ ተመላሽ እንዲያደርጉ የመጨረሻ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ይሁን እንጂ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ገንዘቡን ተመላሽ በማያደርጉ ግለሰቦች ላይ ጠንካራ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ ገልጿል፡፡

ከሕግ አካላት ጋር በመተባበር የግለሰቦችን ሥም ዝርዝር በየቅርንጫፎች እና እንደሁኔታው ግለሰቦቹ ሊታወቁ በሚችሉበት አካባቢ ይፋ በማድረግ ቀጣይ ሕጋዊ እርምጃዎች እንዲቀጥሉ እንደሚደረግም ነው ባንኩ የገለጸው፡፡

በእርምጃው መሰረት ቀርበው የማይመልሱ ከሆነ በሕጋዊ ሂደቱ ተገቢው ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በድርጊቱ የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ፎቶግራፍ እና ዝርዝር ማንነታቸውን የሚገልፁ መረጃዎች በብዙሀን መገናኛ መንገድ ለሕዝብ ይፋ የሚያደርግ መሆኑንም አሳስቧል፡፡

ከእርምጃዎች ጎን ለጎንም ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ የወሰዱትን ገንዘብ እስከ ቅዳሜ ተመላሽ የማያደርጉ ግለሰቦችን ከፍትህ አካላትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር ተገቢውን የወንጀል፣ የፍትሐ ብሔርና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ እንደሚያደርግ ባንኩ አሳስቧል፡፡

7.5 ሚልዮን ብር ወጭ የተደረገበት ሎጎ (አርማ) ለህዝብ ስናቀርብ በታላቅ ደስታ ነው።ሚድያው የደረሰበት ደረጃም ጭምር የሚመጥን ነው።
10/03/2024

7.5 ሚልዮን ብር ወጭ የተደረገበት ሎጎ (አርማ) ለህዝብ ስናቀርብ በታላቅ ደስታ ነው።

ሚድያው የደረሰበት ደረጃም ጭምር የሚመጥን ነው።

ወላይታ ሶዶ ከተማ እንግዶችን ለመቀበል በአዲስ መንፈስ ታድሳ፤ ብሩህ ተስፋ ሰንቃ እንዲህ ደምቃለች9ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም የምታዘጋጀው ወላይታ ሶዶ ከተማ አስፈላጊውን ዝግጅት በማጠናቀ...
13/02/2024

ወላይታ ሶዶ ከተማ እንግዶችን ለመቀበል በአዲስ መንፈስ ታድሳ፤ ብሩህ ተስፋ ሰንቃ እንዲህ ደምቃለች

9ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም የምታዘጋጀው ወላይታ ሶዶ ከተማ አስፈላጊውን ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ ትገኛለች።

ህብረብሔራዊቷ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአስተዳደርና የፖለቲካ ማዕከል የሆነችው ወላይታ ሶዶ ከተማ እንግዶቿን ለመቀበል ከወትሮ በበለጠ ሁኔታ አምራ ተውባ ደምቃለች።

የዳሞታ ጸዳል ነፋሻማ አየሯ፣ ለሁሉም ተስማሚ የሆነች የፍቅርና የሠላም ከተማ፣ እንግዳ አክባሪ እና ተቀባይ ህዝቦቿ እንግዶቻቸውን ለመቀበል እንዲህ ባማረ ሁኔታ ተዘጋጅታለች።

በከተማችን የሚገኙ አለምአቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች ወደ ውቢቷ ወላይታ ሶዶ ከተማ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።

ለኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለኦቦ ሽመልስ አብዲሳ የወላይታ ህዝብ ስጦታ አበረከተለኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለኦቦ ሽመልስ አብዲሳ የወላይታ ህዝብ ስጦታ አበርክቷል።ስጦታው የንጉስ ...
28/11/2023

ለኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለኦቦ ሽመልስ አብዲሳ የወላይታ ህዝብ ስጦታ አበረከተ

ለኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለኦቦ ሽመልስ አብዲሳ የወላይታ ህዝብ ስጦታ አበርክቷል።

ስጦታው የንጉስ ካዎ ጦና እና በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ የሆነው የአጆራ መንትያ ፏፏት ሲሆን ስጦታውን የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አሳምነው አይዛን ጨምሮ የሀገር ሽማግሌዎች በወላይታ ህዝብ ስም አበርክተዋል።

ለተደረገው ደማቅ አቀባበልና ለተወዳጁ ስጦታ ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በወላይታ ሶዶ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታ ከዕዳ ወደ ምንዳ የመንግስት አመራሮች ስልጠና ላይ በመገኘት የዕለቱን ማጠቃለያ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

"ጊፋታ" የወላይታ ህዝብ የማንነት መገለጫ የሆነ የህዝብ በዓል ነውጊፋታ አሮጌው ዓመት የሚሸኝበትና አዲስ ዓመት የሚቀበሉት የዘመን መለወጫ በዓል ትልቅ ቦታ ተሰጥቶ ከሚከበሩት በዓላት አንዱ ...
19/09/2023

"ጊፋታ" የወላይታ ህዝብ የማንነት መገለጫ የሆነ የህዝብ በዓል ነው

ጊፋታ አሮጌው ዓመት የሚሸኝበትና አዲስ ዓመት የሚቀበሉት የዘመን መለወጫ በዓል ትልቅ ቦታ ተሰጥቶ ከሚከበሩት በዓላት አንዱ ሲሆን በየአመቱ ጊፋታ ይከበራል።

በዓሉ ለማህበረሰቡ ያለው ፋይዳ የተለየ ሲሆን በተለይ የተኮራረፉት የተጣሉትና የተጋጩት ብሎም ደመኞች ጥላቸውን ይዘው ወደ አዲሱ አመት እንዳይሸጋግሩ ጥላቻና ኩርፊያ በፍቅር ተተክቶ ሰላምና ፍቅር እንዲሰፍን ሚናው ወደር የለውም።

በዓሉ ሁለት አላማዎችን ያነገበ ሲሆን በዋናነት አሮጌውን ዓመት በሰላም ላሸጋገረው ቤተሰብን ጎረቤትን አከባቢውንና አገርን በሙሉ ጠብቆ ላቆየው አምላክ እግዚአብሔር ምስጋና ውዳሴ ክብርና አድናቆትን የሚያቀርቡበት በዓል ነው።

በሌላ በኩል አዲሱ አመት የሰላም የደስታ የፍቅር የስኬት የድል እና የመተሳሰብ አመት እንዲሆን ለፈጣሪ እግዚአብሔር ፀሎት የሚያደርሱበት እና የሚማጽኑበት በዓልም ጭምር ነው።

ጊፋታ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ አእዋፋትና የቤት እንስሳትም ጭምር በጋራ የሚያከብሩት በዓል ነው፡፡ ምክንያቱም በጊፋታ ሰዎች በሬ አርደው ሥጋ እየበሉና እየጠጡ በዓሉን ሲያከብሩ የሰማይ ወፎችም ቅንጥብጣቢው ስለሚደርሳቸው ነው፡፡

በበዓሉ ወቅት ለቤት እንስሳት ከወትሮ በተለየ ሁኔታ የበዓል ወቅት እስከሚጠናቀቅ ድረስ የሚመገቡት በአሞሌ (aduwaa) የተለወሰ ልዩ ሳርና የእህል ዓይነት ይዘጋጃል፡፡ በመሆኑም ጊፋታ ለፍጥረት በሙሉ የደስታና የአዲስ ህይወት ጅማሮ እንደሆነም ይታመናል፡፡

የጊፋታን በዓል መቃረብ የሚያበስሩ የሰዎች የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ደግሞ በየቤቱ እና በየገበያ ቦታዎች የሚሰሙ የወንዴ እና ሴቴ (Adiyaanne Indde karaabiyaa) ድምጾች፣ በየአካባቢው የሚሰሙ ባህላዊ ዘፈኖች፣ ሰዎች እርስ በርስ ″እንኳን ከጨለማ ወደ ብርሃን በሰላም አሻገረህ (Hashshu Xumaappe Poo’uwaa Saro Pinnasa) እየተባባሉ መመራረቅ ከብዙ በጥቂቱ የሚታዩ ናቸዉ፡፡

የወላይታ ህዝብ በአከባቢው መኖር ከጀመረ ወዲህ ሲወርድ ሲዋረድ ዛሬን የደረሰው ጊፋታ በዓል ዘንድሮም ካለፋት ጊዜያት በተለየ መልኩ በድምቀት ሊከበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቋል።

ዮ ዮ ጊፋታ!! Yoo yoo gifaataa !!

በወላይታ ዞን በባይራ ኮይሻ ወረዳ የሚገኝ ሰው ሰራሽ ታሪካዊ  ይህ ሰው ሰራሽ   ከወላይታ ሶዶ ከተማ በ30 ኪ ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ታሪካዊ ስፍራን ነው።ሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ የተፈጥሮ...
16/08/2023

በወላይታ ዞን በባይራ ኮይሻ ወረዳ የሚገኝ ሰው ሰራሽ ታሪካዊ

ይህ ሰው ሰራሽ ከወላይታ ሶዶ ከተማ በ30 ኪ ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ታሪካዊ ስፍራን ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስዕብ ቦታዎች እንዳሉት ይታወቃል። በዋናነት ሰው ሰራሽ የመስዕብ ቦታዎች በተለያየ ጊዜ ለተለያየ አላማ ተብሎ የተሰሩ ስሆኑ በወቅቱ ለታለመለት አላማ ከዋሉ በኃላ ለቀጣይ ትውልድ የታሪክ ቦታና ቅርስ ከመሆኑም አልፎ በወቅቱ የነበሩ የአባቶቻችን ጥበብና ለአላማ ያላቸውን ፅናት የሚያሳይ ሆኖ ለዘመናት ይቆያል።

ከዚህም አልፎ ለአካባቢው የገቢ ምንጭ ሆኖ ሲያገለግሉም እናያለን። ከእነዚህ ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስዕብ ቦታዎች አንዱ የሆነውና #በባይራ #ኮይሻ #ወረዳ በሴሬ ባላካ ቀበሌ ፑላሳ አምባ ላይ የሚገኘውን አንድ ታሪካዊ #ዋሻ እናስተዋውቃለን።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ በሴሬ ባላካ ቀበሌ በፑላሳ አምባ መንደር ከባህር ወለል #በ2,302 ሜትር ከፍታ ስፍራ ላይ የሚገኘው ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስዕብ ቦታ የሆነው #የአሩጂያ #ዋሻ ታሪካዊ ቦታ ነው።

ይህ ዋሻ ከክርስቶስ ልደት በፊት የተቆፈረ እንደሆነና ዋሻው የተሰራበት የአሰራር ጥበብና በውስጡ ያሉ ክፍሎች እጅግ በጣም የሚደንቅ ናቸው።

በወቅቱ የነበሩ ሰዎች ልጆቻቸውንና ከብቶቻቸውን ከጠላት ለመጠበቅ፣ በጦርነት ድልን ለማግኘትና ለአደን ምቹ ቦታዎችን ለማግኘት በሚል ዓላማ የተሰራ እንደሆነ የታሪክ አዋቅዎች ይናገራሉ።

በአሩጂያ ንጉሰ ነገስታት ዘመን የነበሩ አባቶች ድንጋይን ከድንጋይ ጋር በማጋጨት እሳት አውጥቶ የተለያዩ የዱር እንስሳትን ቀንድ በመጠቀም የቆፈሩት ይህ አሩጂያ ዋሻ እጅግ ማራኪያ በርካታ ታሪኮችን ጠቅልሎ የያዘ እንደሆነ ይነገራል።

ይህ የአሩጂያ ዋሻ ሶስት መግቢያ በር ያሉት ስሆን በመሃል ያለው ትንሹ እንደ መስኮት እንደሚያገለግልና አንዳንደ ጠላትን አስቀድሞ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ ውሻ እንደ ሚታሰር አባቶች ይናገራሉ።

ወደ ውስጥ ስንገባ ከ300 ሰው በላይ መያዝ የሚችል ሰፊ ሳሎን ያለው ስሆን በሁሉም አቅጣጫ የተለያዩ ክፍሎች አሉት። በጣም የሚገርመው በዚህ ዋሻ ውስጥ #ከ30-40 ደቂቃ መንገድ መጓዝ የሚያስችል ሁለት መግቢያዎች ያሉት ስሆን፣

የመጀሪያው ወደ አፋ ወረዳ ወደ ሚባልበት ስፍራ የሚወስድ እንደሆነና ሌላኛው ደግሞ አሁንም ወደ አፋ ወረዳ እንደሚያስወጣ የታሪክ አዋቅ አባቶች ይናገራሉ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ የሚገኘውን የአሩጂያ ሰው ሰራሽ ዋሻ እስከ ቦታው ድረስ በመሄድ እንድትጎበኙና በታሪካዊ አሰራር እንዲትደነቁ ተጋብዛቿል በማለት የባይራ ኮይሻ ወረዳ ማህበራዊ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ዘግቧል።

የኮንሶ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 6ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ። የዞኑ ምክር ቤት ምክትል አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገረመው አያኖ እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ለምክር ቤ...
11/08/2023

የኮንሶ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 6ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ።

የዞኑ ምክር ቤት ምክትል አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገረመው አያኖ እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ለምክር ቤቱ ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ቀርበው ይፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የህዝቦች አብሮነትና አንድነት ይበልጥ እንዲጠናከር ከከፋፋይ አጀንዳ ተላቀን አንዳች ለሌላችን ድርና ማግ፤ ዋልታና ማገር መሆን ይገባናል።ጨለማን የሚገፈው ብርሃን ነው፡፡ ድካምን የሚያቀለው እ...
07/08/2023

የህዝቦች አብሮነትና አንድነት ይበልጥ እንዲጠናከር ከከፋፋይ አጀንዳ ተላቀን አንዳች ለሌላችን ድርና ማግ፤ ዋልታና ማገር መሆን ይገባናል።

ጨለማን የሚገፈው ብርሃን ነው፡፡ ድካምን የሚያቀለው እረፍት ነው፡፡ ጥላቻን የሚያስወግደው ፍቅር ነው፡፡ ቂምንና ቁርሾን ማስወገድ የሚቻለው ደግሞ በይቅር ባይነት ነው፡፡

ሰሞኑ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ ጥላቻን ያነገቡ መረጃዎች ለዘመናት የቆየውን የህዝቦች አብሮነትንና እሴቶች ለመሸርሸር ታልሞና ታቅዶ እየተሰራጨ ያለ ቢሆንም ህዝብን ከህዝብ ጋር ለማጋጨት መሞከር ወንጀለኛ እንጂ ጀግና አያስብልም፡፡

ታዋቂው የጥቁሮች ሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ማርቲን ሉተር ኪንግ በአንድ ወቅት እንዲህ ሲል መናገሩ ይታወቃል፤ "Darkness cannot drive out darkness; only light can do that. Hate cannot drive out hate; only love can do that". “ጨለማን በጨለማ ሳይሆን በብርሀን፤ ጥላቻንም በጥላቻ ሳይሆን በፍቅር” ልንቀይር እንደምንችል ያሳያል፡፡

ታዲያ እውነታው ይህ ከሆነ እኛ እየሆንን ያለነው የትኛውን ነው? ጥላቻን በጥላቻ ወይስ ጥላቻን በፍቅር? ማንም ሊረዳው የሚገባው እውነታ ግን ጥላቻ የበለጠ ሰውን ከሰው እያራራቀ ወዳልተፈለገ መንገድ ይመራል እንጂ ሰላምና አንድነትን ከቶውንም ቢሆን አምጥቶ አያውቅም፡፡

ስለዚህ በሰዎች ዘንድ የቱንም ያህል ክብራችንን የሚነካ ማንነታችንን የሚያጠለሽ ነገር እንኳ ቢፈጠር ክፉን በክፉ መመለስ ሳይሆን መጥፎውን በደግነት ቀይረን እኛነታችንን የበለጠ በመልካምነት ልናሳይ ይገባናል፡፡ የጽንፈኛ ኃይሎች መጠቀሚያ እንዳንሆን ራሳችንን እንጠብቅ፡፡

አንዳንድ ጽንፈኞች በማህበራዊ ሚዲያ በህዝቦች መካከል ያለው የእርስ በእርስ ትስስርን ለማጠላሸት፣ ወንድማማችነትና እህተማማችነት ለመከፋፈል የሚያሰራጩትን በጋራ መታገልና መቃወም ያስፈልጋል፡፡

ጥላቻን በጥላቻ፤ ስድብን በስድብ ሳይሆን በፍቅርና በመተሳሰብ ማሸነፍ ይገባል፡፡ የህዝቦች አብርነትና አንድነት ከጥንት ጀምሮ አባቶቻችን እንደሰርገኛ ጤፍ ህብር ፈጥረው ያመጡት በጥቂት ሴረኞችና የፌስቡክ አርበኞች የሚሻክር አይደለም፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ወንድማማችነትን መተክሉ አድርጎ ሲነሳ የሁሉም ችግሮች ማሰሪያ ውል እንደሆነ ስለሚያምን ነው፡፡ ማናቸውም ለፍትህ እና ለነፃነት የሚዳርጉ ትግሎች ፍሬያማ የሚሆኑትም በወንድማማችነት ዕሴት ውስጥ ብቻ ነው፡፡

የወንድማማችነት ዕሴት ባለበት ሁሉ አንዱ ሌላውን መረዳት አለ፤ ሆኖም ይህ እሴት በተሸረሸረ ቁጥር ደግሞ የሌላውን ሕመምና ፍላጐት መረዳት ከባድ ያደርገዋል፡፡

ሠላም እንዳያያዛችን ሁኔታ የሚወሰን እንጂ በየትኛውም ዓለም ስለተፈለገ ብቻ የሚገኝ ማህበራዊ ሀብት አይደለም፡፡ የመጠፋፋትና የመከፋፈል ስንክ-ሳሮች በብልጽግና ህክምና ይፈወሳሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ እያንዳንችን የራሳችንን ድርሻ መወጣት ይኖርብናል፡፡

አዲሱ "የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል" ሠላሙ የሰፈነበት፣ ህብረቱ እንደብረት የሚጠነክርበት፣ ፍቅር የሚጎለብትበት፣ ፍትህ የሚሰፍንበት፣ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚረጋገጥበት፣ አብሮነትና ወንድማማችነት የሚጸናበት፣ መተሳሰብና አብሮነት የሚታይበት፣ አግላይነት እና ጽንፈኝነት ከሥር መሠረቱ የሚነቀልበትና የሚጠፋበት፣ እውነት የሚነግስበት እና ኢትዮጵያዊነት የሚያጸናበት እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን አስተዋፆኦ ማበርከት ያስፈልጋል እንላለን፡፡

ዋልያዎቹ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን ማጣሪያ በምድብ አንድ ተደልድለዋል ✳️〰️〰️〰️〰️〰️➰〰️〰️〰️〰️〰️✳️አዲስ አበባ ሐምሌ 6/2015 ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2026 በሚካ...
13/07/2023

ዋልያዎቹ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን ማጣሪያ በምድብ አንድ ተደልድለዋል
✳️〰️〰️〰️〰️〰️➰〰️〰️〰️〰️〰️✳️
አዲስ አበባ ሐምሌ 6/2015 ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2026 በሚካሄደው 23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን ማጣሪያ በምድብ አንድ ተደልድላች።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) የዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ማጣሪያ የምድብ ድልድል ማምሻውን በኮትዲቭዋር አቢጃን ዛሬ ይፋ አድርጓል።

በዚህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድብ አንድ ከግብፅ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ሴራሊዮን እና ጂቡቲ ጋር ተደልድሏል።

54 የአፍሪካ አገራት በማጣሪያው በዘጠኝ ምድብ ተደልድለው የማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ እ.እ.አ 2026 በአሜሪካ፣ሜክሲኮ እና ካናዳ ጣምራ አዘጋጅነት ይካሄዳል።

በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 48 አገራት ይሳተፋሉ።

ዓለም አቀፋ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) አፍሪካ በዓለም ዋንጫው የምታሳትፈው አገራት ቁጥር ከአምስት ወደ ዘጠኝ ከፍ አድርጓል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳዉ እና ሌሎች የፌደራልና የደቡብ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን አስጀመሩ✳️〰️〰️〰️〰️〰️➰〰️〰️〰️〰️〰️✳️የፌደራልና የደቡ...
13/07/2023

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳዉ እና ሌሎች የፌደራልና የደቡብ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን አስጀመሩ
✳️〰️〰️〰️〰️〰️➰〰️〰️〰️〰️〰️✳️
የፌደራልና የደቡብ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን አስጀመሩ።

በማብሰሪያ ፕሮግራሙ የደም ልገሳ፣የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስና የችግኝ ተከላ ተካሂዷል።

መሰል የበጎ ተግባር ስራዎች በሁሉም አካባቢ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልእክት ተላልፏል።

Address

Arbaminch
S**o
GOVERNMENTAFFAIRS

Telephone

+251952634183

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian Media Network:

Videos

Share