Wolaita Television

Wolaita Television Media Service

ሰበር ዜናበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአደረጃጀት ሂደትን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያጭበረበሩ አመራሮች በህግ ቁጥጥር ስር መዋል ጀምረዋል።የቀድሞ ደቡብ ብሄር ብሄረ...
16/04/2024

ሰበር ዜና

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአደረጃጀት ሂደትን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያጭበረበሩ አመራሮች በህግ ቁጥጥር ስር መዋል ጀምረዋል።

የቀድሞ ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ሕዝቦች ክልል የአደረጃጀት ለውጥ ማድረጉን ተከትሎ በሚደረግ የሽግግር እንቅቃሴ ውስጥ መላው የመንግስት እና የሕዝብ አደረጃጀቶች ለዚሁ ሥራ ትኩረት መሰጠቱን እንደ ምቹ ሁኔታ የቆጠሩ የቀድሞው ደ/ብ/ብ/ህ ክልል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ቢሮ ሐላፊዎችና አመራሮች የ32 ሚሊዮን ብር ዘረፋ ማካሄዳቸው በምርመራ በመረጋገጡ ተጠርጣሪዎቹ ለህግ የማቅረብ ሥራ መጀመሩን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ታማኝ የመረጃ ምንጮች ከአርባምንጭ ገልፀውልናል።

እንደ መረጃ ምንጫችን ከሆነ የዚሁ የሙስና ሰንሰለት በዎላይታ ዞን የመንግስትን መዋቅር ተክተው በአቤ-ልጅ ኔትወርክ፣ በአከባባዊነት ኔትወርክ፣ በትውውቅ እና በጥቅም እንዲሁም በቤተሰባዊ ኔትዎርክ ካደረገው የምክትል ርዐስ መስተዳደር አቶ ተስፋዬ ይገዙ ህቡዕ አደረጃጀት ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያለው እንደሆነም የተነገረ ሲሆን ምርመራው ተጠናክረው እንደሚቀጥልም ተነግሯል ሲል ወላይታ ታይምስ ሚዲያ ዘግቧል።

ዎላይቶ...እርሰዎ ምን ይላሉ ? ክቡርነትዎ ዛሬ ትንሽ ነገር እስኪ እንጠይቀዎት🙏  ለእርሰዎ ምን ምላሽ አለዎት❓ለመሆኑ እርሶዎ የአንድ ሊቃ ትምህርት ቤት አጥር ግንባታ የመላው ዎላይታ ትምህ...
12/04/2024

ዎላይቶ...እርሰዎ ምን ይላሉ ? ክቡርነትዎ ዛሬ ትንሽ ነገር እስኪ እንጠይቀዎት🙏 ለእርሰዎ ምን ምላሽ አለዎት❓ለመሆኑ እርሶዎ የአንድ ሊቃ ትምህርት ቤት አጥር ግንባታ የመላው ዎላይታ ትምህርት ዘርፍ ስብራት ይጠግናል ብለው ይገምታሉ ? እርስዎ ከክንዶ ዲዳዬ እስከ ድምቱ፥ ከሀማሳ እስከ አቹራ ድረስ 99.99 ከመቶ በላይ ተማሪዎች ጉዳይ ትኩረት ተነፍጎ ለአንዱ ብቻ ከመንግሥት አመራር እስከ ዕድር መሪ መደበኛ ስራ ቁጭ አድርጎ ለአንድ ብቻ እየጮሁ ሲውሉ ጤናማ አካሄድ ይላሉ❓

ለመሆኑ እርስዎን በዎላይታ ቀጥታ ከመንግሥት ዩንቨርስቲ በዲግሪ የተመረቁ ወደ 150 ሺህ የሚጠጉ እንዲሁም ከ70 ሺህ በላይ ከግል ኮሌጆችና ከመንግሥት በዲፕሎማ የተመረቁ ስራ አጥ ወጣቶች፣ 10ኛ እና በ12 ኛ ክፍል አጠናቀው ወደ ዩንቨርስቲና ኮሌጅ ሳይገቡ የቀሩት ጉዳይ በጓዳ ተደብቀው ባለበት የሊቃ አጥር ግንባታ አጀንዳ መሆኑ አያስገርሞዎትም❓

ቆይ እርስዎን ሴቶችና ህፃናት በሚያሳዝን ሁኔታ በሀገሪቱ በሁሉም ጎዳናዎች ላይ ተበታትነው ቢገኙም በአከባቢው ከውትድርና ውጪ ያለው የቅጥር ሆነ ሌላ የስራ ዕድል ቢሆንም በገንዘብ፣ በአመራሮች ዝምድና፣ በአከባቢዊነት እንዲሁም በትውውቅ ሆኖ ሳለ በተቃራኒው ያ ተዳፍኖና ዝም ተብሎ የአንድ ትምህርት ቤት አጥር ግንባታ አጀንዳ ቅድሚያ ተሰጥቶት ሲያዩ ምንም አይሰማዎትም❓

የማከብርዎት እርስዎን እየጠየቅን ነውኮ፦ ቆይ በዎላይታ ለወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር የሚችል እንድም ኢንዱስትሪ ፓርክ እና ሌላ ፋብሪካዎች አለመኖር ብቻ ሳይሆን በፌደራል፣ በክልል ሆነ በዞኑ አመራሮች ይሄንን ችግር ለመቅረፍ ተብሎ የተቀረጸ ዕቅድ ሆነ አላማም አለመኖሩ ወጣቶቹ በከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ሁኔታ ውስጥ እንዲገቡ እያዳረገ መሆኑ ምንም አያስጨንቆዎትም ❓

ክቡርነትዎ የዎላይታ ታይምስ እንደ አንድ የአከባቢውን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለ እንደሚሰራ ሚዲያ እየጠየቀ የሚገኘው፦ በአከባቢው አብዛኛው አሰራር የመንግስትን መዋቅር ተክተው በአቤ-ልጅ ኔትወርክ፣ በአከባባዊነት ኔትወርክ፣ በትውውቅ እና በጥቅም ላይ በተመሰረተ እንዲሁም በቤተሰባዊ ኔትዎርክ እየተመራ የህዝብ አንድነት አደጋ ላይ እየወደቀ ስለመሆኑ ለእርስዎ መቼ ነው ጉዳዮዎት የሚሆነው ❓

99.99% የሚሆነዉ የዎላይታ ሕዝብ ልጆች የሚማሩት የመንግስት ት/ቤቶች አካላዊ ገጾታ ከታች ያለውን ይመስላል። ወይንም ከዚህ የከፋም ነዉ። ይሁን እንጂ ከላይ በዝርዝር የተነሳው አይነት የህዝብ አንገብጋቢ ጉዳዮች ተዳፍነው ሴራኞቹ ለማምለጥ በሊቃ አጥር ግንባታ አጀንዳ ውስጥ ተደብቀው የመንግስት መደበኛ ኃላፊነት ወደጎን በመተው ሊቃ፣ ሊቃ፣ ሊቃ ማለታቸው ለእርስዎ እውነትም ለሊቃ ውግንና የሚሆኑ ይመስሎታል❓

ቆይ እርሰዎን በዎላይታ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ባለፉት አራት አመታት "በቅርቡ ይሰራሉ" ተብሎ ለድዛይን ብቻ በርካታ ገንዘብ ወጥተው ይፋ የተደረጉ የአባላ አባያ Summer city፣ የዩንቨርስቲው ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ የአረካ የግብርና ልህቀት ማዕከል፣ የቦዲቲ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል በዝምታ መቆሙ ምንም አያሳስበዎትም ❓

ግድ የለዎትም እንጠይቀዎት እስኪ ጨምረንም፦ ቆይ ክቡርነትዎ ለእርሰዎ ከንግግር ያላለፉ ለድዛይን ብቻ በርካታ ገንዘብ የወጣበት የዎላይታ የቀድሞ ነገስታት መታሰቢያ ሀውልት፣ የወይቦ መስኖ ፕሮጀክት ግንባታ፣ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ በሶዶ ከተማ ይገነባል የተባለው የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ግንባታ፣ ዘመናዊ የመርካቶ ገበያ ማዕከል ግንባታ፣ መለስተኛ እንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ፣ ለምርጫ ቅስቀሳ ዜና የተሰራው ከግብርና ኮሌጅ እስከ ሌዊ ለምን አንጠይቅም❓

ለ8 ዓመታት ያልተጠየቀ ዕዳ በድንገት "አልከፈላችሁም" በሚል በዎላይታ ሶዶ የልጅ እናት ጨምሮ በርካቶች በማይታወቁ ፓሊስ ጣቢያዎች እየታሰሩ ስለመሆኑ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በዎላይታ ሶ...
10/04/2024

ለ8 ዓመታት ያልተጠየቀ ዕዳ በድንገት "አልከፈላችሁም" በሚል በዎላይታ ሶዶ የልጅ እናት ጨምሮ በርካቶች በማይታወቁ ፓሊስ ጣቢያዎች እየታሰሩ ስለመሆኑ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በዎላይታ ሶዶ በርካቶች በአፈሳ በህግ ባልታወቀ ማጎሪያዎች እየታሰሩ እንደሚገኙ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ቤተሰብ አባላት እስከ ቦታው ድረስ ሄደው እንደሚከተለው የአይን ምስክርነት መረጃ አድርሶናል።

"በአፈሳ በድንገት በዎላይታ ሶዶ ከተማ ከየቤታቸው ከታሰሩት መካከል ይህቺ ከታች በፎቶ የምንመለከታት እናት ትገኛለች። እናቷ በመታሰሯ ምክንያት ልጆቿ የዕለት ጉርስ በማጣት እሷ ወደ ታሰረችበት ቦታ ሌሎች ከእሷ ጋር የታሰሩትን ለመጠየቅ የሚመጡትን ስለምኑ ይታያሉ። ሁኔታውን ለመቃኘት በሄድኩበት ስጠይቃት ከእነ ልጆቻቸው አስር ሺ ብር ካልሰጠሽ በማለት አስረዋታል። ብሩን የወሰደችው በማህበር ተዘዋዋሪ ፈንድ የዛሬ 8 አመት በፊት ቢሆንም አንድም ሰው ከወሰድኩበት ቀን ጀምሮ መቶ እንደማያውቅና ወለድ እንዳለውም እንዳልነገሯት ትናገራለች።

በወሰደችውም ስራ ውጠታማ ሳትሆን ቀርታ እንደከሰረች የምትናገረዋ እናት ድንገት በጠዋት ለልጆቿ እንደወትሮው ሀገረ ሰላም ነው ብላ ስትወጣ ጣቢያ እንህድ ወይም እዳሽን በሙሉ ክፈይ ብለዋት እንዳመጧት ትናገራለች። ያለችኝን በሙሉ ዉሰዱና ልቀቁኝ ለልጆቹ ለምኜም ላብላቸው ብላ በእምባ ትለምናቸዋለች። ነገር ግን ከላይ የመጣ ነው ብለው ያላግጡ ነበር። ልጆቿም እዛው አከባቢ ጎዳና ላይ ወድቀዋል።

ለዕለት ጉርሻም እንደለላትም ድምፁዋን ከፍ በማድርግ በሚርት ትናገራለች። ባልም ዘመድም የለኝም እኔን እድመ ልክ ብታሰሪም ይሄን ገንዘብ የሚሰጣቹ አይኖርምና ለልጆቼ ይቀን ጉርሻ ልቀቁኝ ስትል አምሪራ ታነባለች። ይችህ እናት ድንገት ቀሪቢያት ሰማው እንጅ በርካታ ሰዎችንም ሳናግር ተመሳሳይ ህገ ወጥ እስር እንደሆነ ታዝቤዉ ህግን ማን ያስከብር በማለት ታዘብኩት።

የዎላይታ ህዝብ ደም የፈሰሰው ትግል ለካድሬ መፈንጫ ሳይሆን ህግ እንድከበርና ለዘመናት የታፈነው ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ እንድመለስ ነው። ይሁን እንጂ ካድሬው ከሞላ ጎደል በስንት ትግል የመጣችውን መቀመጫ እኛ አምጥተል በማለት ስፍነጩ የመንግሥት ካዝና አራቁተው ስጨርሱ ህዝብን ለራሱ በልቶ ለማደር የሚፍጨረጨር ሰው እዝዉ ዉለዱ በማለት ህግን በመጣስ በየ ማጎሪያው እያሰሩ ይገኛል።

ትላንት ህግን በመጣስ በየ ነጋደው ቤት በሌሊት ለፍተው ዉሎ የተንኙትን እየወሰዳቹ ስታስሩ ዝም ተባለ። በማሰር ይሄን ያህል ገንዘብ አምጡ ማለት ምናልባት ነጋዴዎች ጋር ሰርቶላችሁ ይሆናል ከገቢው አንፃር በጠበቃዉም ስለምከራከር። ነገር ግን ካቢኔ ስለተሰበሰበ ተብሎ ህግ አይጣስም። የሰው ሰብአዊ መብቱን በመጠበቅ በህግ ህደቱን ጠብቆ ይጠየቃሉ እንጅ ማንም ውንብድና በሚመስል መንገድ ና ዉጣ ብር አምጣ አስራሃለዉ ጫወታ ይበላቿል።

በየ ማጎሪያው ጣቢያ የታፈኑ እናቶቻችን አባቶቻችን ስራ አጥ ወጣቶችን ሳይ አነባው። አንዳንዶቹ ስጠየቁ የህግ አካል እንኳን አላመጣቸውም። "ገንዘብ በእጅህ ከለለህ ቀጥል እለፍ" ተብለን መጣን የሚል ብዛቱ የሰጠሄን ያንሳልና ሞልቶ ሚያመጣልህ እስኪመጣ እዝው ትቆያለህ የተባሉትንም አገኜው። የህግ አካላት ግራ ተጋብተው የካብኔ ውሳኔን ለብቻ ማየት ጀምረዋል። ያለ ህጋዊ ደረሰኝም ካለመታሰር ውትወታም የሰጡትም አሉ። ያለውን ነገ ምን በላለው ሳይል የሰጠው ያንሳል ጎሏል ብሎ ማሰር ትልቅ ኪሳራን ያመጣል።

ድግስ በማብዛት እና በስብሰባችሁ የሚመጣ ለውጥ የለም። በየወረዳው ያፈናቹትን የመንግሥት ሰራተኛ ደሞዝ ክፈሏቸው።

አስደንጋጭ መረጃ ስለ ባለበት አልባው ወላይታ ሶዶ ከተማ ❗️❗️አሳዳጊ የበደለው መልሶ ይናከሳል!! አቶ ጀገና አይዛ እና አቶ አበባየው ኡኩሞ በምን ስነልቦና ተገናኙ??ባለበት አልባው እና የ...
06/04/2024

አስደንጋጭ መረጃ ስለ ባለበት አልባው ወላይታ ሶዶ ከተማ ❗️❗️

አሳዳጊ የበደለው መልሶ ይናከሳል!! አቶ ጀገና አይዛ እና አቶ አበባየው ኡኩሞ በምን ስነልቦና ተገናኙ??

ባለበት አልባው እና የዘቀጠው የወላይታ ሶዶ ከተማ መዋቅር ከንቲባ አቶ ጀገና አይዛ እና ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበባየው ኡኩሞ ወዳጅነት የከተማ ልጆች በሚል እያባረሩ ዝርፊያ ውስጥ ገብተዋል።

የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው! ሁሌቱን ያስታረቀው ወዳጅነት፥ ያሳደገውን ማህበረሰብ የካዱ ባንዳ መሆናቸው እንደሆነ ይገለጻል።

የአቶ አበባየው ኡኩሞ አባት ባለመታወቁ ከእሱ በኃላ እናቱን ያገባው አባት በማሳደጉ እና አቶ ጀገና አይዛ ወላጅ አልባ በመሆን ወልማ ከጎዳና አንሶቶ ማሳደጉ፤ የቀበሌ ማዘጋጃ እኩል በመካፈል ጃጋና አይዛ 4 ቀበሌዎችን አበባየው ኡኩሞ 3 ቀበሌዎችን በመከፋፈል ይጠቀሳሉ።

አቶ ጃጋና አይዛ በሙጃል ዳውሮ ከተመደበበት መልሶ ዲዳዬ ላይ ከእኔ ሙጃሉ አሳድጎ ባሏ የሞተባትን የልጅ እናት እሱንና ልጆቿን አጥቦ እንድታሳድገው ብያጋቡም ክ/ድዳዬ ላይ ትም/ት ጽ/ቤት ኃላፊ ከሆነ በኃላ የሴትየዋን ልጆች ከቤት በማባረር ያንከራተተና ቤቷ ገብቶ የቀረ ስለመሆኑ የግል ማህደሩ ያስረዳል።

አቶ አበባየው ኡኩሞ እስስት እና አስመሳይ ሰው በመሆኑ አባቱን በአደባባይ ያዎረደ ያበላ ያጠጣ ጎሬበት በድንበር ሚክንያት የከተማው ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ነኝ ምን ትመጣላችሁ በማለት በእንብተኝነት ያሳሰረ ነውረኛ ነው።

አቶ አበባየው ኡኩሞ መርካቶ ቀበሌ ዪሹዋ ላይ 20፣ ፋና ዎምባ ላይ ብቻ 50 በላይ ህገወጥ መሬት በአጎት፣ በአክስት ልጅ በብዕርና በሞተ ሰው ስም ፋይል በማደራጀት ከቀበሌው ማዘጋጃ ጋር ተካፍሎ የበላ ስለመሆኑ በቂ መረጃ ደርሶናል።

አቶ አበባየው ኡኩሞ ሁሉንም ህገወጥ ግንባታ በራሱ እውቅና ማሰራቱ ግዜ ጠብቆ ማረሚያ ማስገባቱ የማይቀርለት መሆኑን በመለየት በቀን 15/03/16 ዓ/ም ከአያት ሪል እሰሰቴት ባለ 3 በመኝታ አፓርታማ በካሽ የገዛበትን ፋይል በቀጣይ ይፋ የምናደርግ ስሆን የሱ ጉዳይ አስፈጻሚው በእማኝ የፈረመበት ሙሉ ዶክመንት እኛ ብደርስም ጉዳይ አስፈጻሚው ካልታረመ በቀጣይ ለህዝብ እና ለምክር ቤት ተወካዮች ኮፕ ፋይል እንሰጣለን።

ግብር ስሰበሰብ ትታሰራላችሁ አትታሰሩም በማለት ከሁሉም ነጋድዎች 100,000 ሺህ ብር የተቀበሉ ስሆን ያኔ ደረሰኝ ባለመቁረጥ የታሰሩ ነጋዴዎች ቅጣት 50,000 ብር በአዋጁ መሠረት መክፈል ስኖርባቸው ድጋሚ እኛ ጋር ድርሽ እንዳትሉ ሁለቴ አንከፍልም በሚል አንገት በመድፋታቸው ነጋዴዎች እስካሁን በህግ የተወሰነውን የቅጣት ገንዘብ አልከፈሉም።

አቶ ጀገና አይዛ ድክመቱን እና ሌብነቱን ለመደበቅ በቤተክርስቲያን ሽፋን በማድረግ ከጎዳና አንስቶ ያሳደገውን ህብረተሰብ እየበዘበዘ ያለ ስሆን የዚህ ተኩላ ጉዳይ ስንዝር የማይሄድ በመሆኑ በቅርቡ ሁሉም ነገር መስመር ስይዝ ያኔ ወደ ቀደመው ስትመለስ የህግ የበላይነት ስከበር ያኔ ያስለቀስከው የወላይታ ህዝብ፣ የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪና ያንቴ ቡችሎችን ዝንብ ስበላ በአይን ታያለህ!!

የውሻ ንክሻ በዚህ ይቁም ካልሆኔ በቀጣይ በደማችን የገነባነውን ገጽታ ያለምንም ደም ክፍያ የምናፈርስ ይሆናል ሲል የከተማው የለውጥ አደረጃጀት አመራሮች ያደረሱት መረጃ ያመለክታል!!

በዎላይታ ሶዶ ከተማ ሀሰተኛ ደረሰኝ በመጠቀም ቤቷ ተሽጦ ከእነ ልጇ ጎዳና የወጣች እናት በከተማዋ ተጠርጥረው ባሳተመው ሐሰተኛ ደረሰኝና እሱ በሰራው ማጭበርበር ቤቷ በሕገወጥ መንገድ በባለቤቷ...
06/04/2024

በዎላይታ ሶዶ ከተማ ሀሰተኛ ደረሰኝ በመጠቀም ቤቷ ተሽጦ ከእነ ልጇ ጎዳና የወጣች እናት

በከተማዋ ተጠርጥረው ባሳተመው ሐሰተኛ ደረሰኝና እሱ በሰራው ማጭበርበር ቤቷ በሕገወጥ መንገድ በባለቤቷ ተሽጦባት ልጇን ይዛ ከቤቷ ተባርራ በሜዳ የሚትንከራተት እናት "ፍትህ ወደየት ነው" በሚል ለፈጣሪ፣ ለመንግስትና ለህዝብ ሁኔታውን በእምባ ታሰርዳለች።

ባለፈው ሳምንት በዎላይታ ሶዶ ከተማ ድል በገሬራ ቀበሌ አቶ ተስፋሁን በለጠ ( የአማራር ወንድም ) የተባለ ግለሰብ የሕገወጥ ደረሰኝ አመሳስሎ በማሳተም የቤት ሽያጭ ውል ማጽደቂያ በአራዳ ቀበሌ ገቢዎች የተከፈለ በማስመሰል ባለቤቱ ( ወይዘሮ ቤተልሔም ለማ ) ሳታውቅ ቤት ለመሸጥ የሰራው ሀሰተኛ ደረሰኝ ስለመሆኑ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ባደረገው ማጣራት በማረጋገጥ ያወጣው ዘገባ ተከትሎ ተጠርጣሪው ታስሮ የፍርድ ሂደት እንዲከታተል ተደርጎ ነበር።

ነገር ግን አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት ሀሰተኛ ደረሰኝ በማሳተም የፈጸመው ወንጀል ሳያንስ ባለቤቱ ሳታውቅ ቤት ለግለሰቦች በመሸጥ ከቤቷ በባዶ እጅ ወደ ጎዳና እንድትወጣ ያደረገው ግለሰብ በዞኑ የአንድ መምሪያ ኃላፊ ወንድም ተገን በማድረግ ዋስትና የማያሰጥ ከባድ ወንጀል ቢሆንም የፍርድቤት ቀጠሮ እንኳን ሳይደርስ ከእስር መለቀቁን ከተበዳይ ወገን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የዞን አቃቤ ሕግ ሙሉ መረጃ ደርሶበት ክስ ከመሰረተ በኃላ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ መጥሪያ ወጥቶለት ተጠርጣሪው በሶዶ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት እየሰራ ባለበት አሁን ያለው የዞን አመራሮችና የሶዶ ከተማ አስተባባሪዎች ጭምር ተሰብስበው የተነጋገሩ ቢሆንም "ጉዳዩ ይፋ ከወጣ በዘርፉ የተፈፀሙ በርካታ ጥፋቶች ይጋለጣሉ" በሚል በመፍራት ግለሰቡ ወደ ፍርድ ቤት እንዳይቀርብ ተደርጎ ቢቆይም ባለፈው ሳምንት ያወጣነውን ዘገባ ተከትሎ ተጠርጣሪው በፓሊስ ጣቢያ ሆኖ የፍርድ ሂደት እንዲከታተል ቢደረግም በጫና በድጋሚ እንዲፈታ መደረጉንም ከምንጮቻችን አረጋግጠናል።

አንድ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ የሚገኝና ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ ግለሰብ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ እንደገለፀው "የዞኑ የገቢዎች ኃላፊ ሆኖ የእሱ ወንድም ሐሰተኛ ደረሰኝ በማሳተም በከተማ ውስጥ ከፍተኛ የመንግስት ገቢ እንዲሰወር ብቻ ሴይሆን ከባለቤቱ በመደበቅ ቤቷን ሽጦ ጎዳና እንዲትወጣ እንዲሁም ተመሳሳይ ድርጊት በሌሎች ላይም እንደፈፀም ባደረገው ተጠርጣሪ ላይ ፖሊስ ምርመራ ካደረገ በኃላ ሙሉ መረጃ አሰባስቦ በከባድ ወንጀል ክስ እንዲመሰረት ለዞኑ አቃቤ ሕግ ቢቀርብም ክስ እንዳይመሰረት ጫና የፈጠረ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ ዘገባ እናንተ ከሰራችሁ በኃላ አቃቤ ሕጉ ደንግጠው ዋስትና በሚከለክል ከባድ ወንጀል የተጠረጠረው ግለሰብ በፓሊስ ጣቢያ ሆኖ የፍርድ ሂደት እንዲከታተል ቢደረግም በጫና ከእስር እንዲወጣ መደረጉ ለህገወጥ ተግባር ሽፋን እንደመስጠት ነው" ሲል አስረድተዋል።

በዚህ ሁሉ መሀል ተጠርጥረው ባሳተመው ሐሰተኛ ደረሰኝና እሱ በሰራው ማጭበርበር ቤቷ በሕገወጥ መንገድ ተሽጦባት ልጇን ይዛ ከቤቷ ተባርራ በሜዳ የሚትንከራተት እናት "ፍትህ ወደየት ነው" በሚል ለፈጣሪ፣ ለመንግስትና ለህዝብ ሁኔታውን በእምባ ጥሪ እያቀረበች ነው።

በአከባቢው የሚገኙ የፍትህ ተቋማት ይህንንና መሰል ወንጀለኞችን ተከታትሎ ወደ ሕግ እንዲያቀርብ እንጠይቃለን፤ ይህ ሳይሆን ስቅርና ለሚፈጸመው ወንጀል የመንግስት አመራር ሽፋን እየሰጠ የሚቀጥል ከሆነ ስርዓት አልበኝነት ይነግሳል" በሚል በርካቶች እየጠየቁ ሲሆን እኛም ለበርካቶች ትምህርት እንዲሆን በማሰብ ከላይ ያቀረብነው ጉዳይ የደረሰበትን ተከታትለን እንደምናቀርብ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ "የህዝብ ውክልና አንሷል" በሚል በውሸት በህዝብ ስም የግል ፍላጎት ካሳኩ በኃላ ለሌላ አሳልፈው መስጠቱ አነጋጋሪ ሆነ።በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳ...
03/04/2024

ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ "የህዝብ ውክልና አንሷል" በሚል በውሸት በህዝብ ስም የግል ፍላጎት ካሳኩ በኃላ ለሌላ አሳልፈው መስጠቱ አነጋጋሪ ሆነ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳዳርነት የቢሮ መቀመጫውን አርባምንጭ ከተማ በማድረግ የተሾሙት አቶ ተስፋዬ ይገዙ "ተጨማሪ ስልጣን ይሰጠኝ" በሚል ከፍተኛ ውዝግብ በኃላ ቢሰጣቸውም ከስራው ጋር ምንም ግንኙነት ለሌለው ሰው ከአሰራር ውጪ ውክልና መስጠታቸው ከፍተኛ ቅሬታ መፍጠሩን የክልሉ ኢንተርፕራይዞች ልማትና ሥራ እድል ፈጠራ ቢሮ ሰራተኞች ገልጿል።

ነገሩ እንዲህ ነው አቶ ተስፋዬ ይገዙ "በክልሉ አስፈፃሚ አካል ውስጥ የዎላይታ ውክልና ተገፋ እኔም ዎላይታ ስለሆንኩ ተገፍቼ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርነት ብቻ ተሰጥቶኝ አርባምንጭ የተወረወርኩት" በሚል በፌደራል ደረጃ ከፍተኛ ኃላፊነት ያላቸው አመራሮች ቢሮ በተደጋጋሚ በመመላለስ የዎላይታ ተወላጅ ከሆነው አቶ ብረጋ ብራሃኑ የኢንተርፕራይዞች ልማትና ሥራ እድል ፈጠራ ቢሮ ኃላፊነት ቦታ በመንጠቅ ተጨማሪ ስልጣን ማግኘቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያደረሱት መረጃ ያረጋግጣል።

አቶ ተስፋዬ "የህዝብ ውክልና አንሷል" በሚል በውሸት በህዝብ ስም የግል ፍላጎት ለማሳካት ባደረጉት ጥረት መልሰው የዎላይታ ተወላጅ የሆነውን ከስልጣን አስነስተው ቦታውን ነጥቀው ከምክትል ርዕሰ መስተዳደርነት ጋር ደርበው ለመስራት ተጨማሪ ሹመት ቢሰጣቸውም በተቃራኒው የኢንተርፕራይዞች ልማትና ሥራ እድል ፈጠራ ቢሮ ኃላፊነት ከአሰራር ውጪ በውክልና ለሌላ ብሄር መስጠቱ ተገቢ ያልሆነና የግለሰቡን በህዝብ ስም መነገድን እንዲሁም የተመደበበትን ቢሮ በጀት ለሙስና እንዲያመች ለማድረግ ስለመሆኑ የሚያመለክት እንደሆነ አንድ የክልሉ ከፍተኛ አመራር ትዝብቱን አካፍለዋል።

የመረጃ ምንጫችን ምክንያቱን ሲያስረዳ፦ እውነትም "የህዝብ ውክልና በአመራር ፑል ውስጥ አንሷል" በሚል ታግለው ተጨማሪ ያገኘ ሰው ውክልና አንሷል በተባለው ብሄር ተወላጅ የተያዘውን ኃላፊነት ቦታ በመንጠቅ ሳይሆን "ከሌላው ይሰጠኝ ይላል" ፤ በተጨማርም በህጉ መሠረት ውክልናውን በኢንተርፕራይዞች ልማትና ሥራ እድል ፈጠራ ቢሮ ምክትል ኃላፊ በመሆን እየሰሩ ለሚገኙት ለሆኑት አቶ ብርሃኑ ሙንኤ ( የዎላይታ ተወላጅ ) ይሰጣል እንጂ አሁን ከተጠቀሰው ቢሮ ጋር በምንም የማይገናኝ ኃላፊነት ለያዙ የምክትል ር/መስተዳድሩ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሄ ቦዳ መስጠት "አግባብነት የሌለውና የግለሰቡ ገደብ የለሽ ስልጣን ጥማት መሻት የሚያመለክት" ስለመሆኑም አስረድተዋል።

በዚህም በግልጽ ቋንቋ አቶ ተስፋዬ ይገዙ በህዝብ ስም ለመነገድ "ውክልና አንሷል" በሚል የሄደበት ርቀት ውሸት መሆኑ የሚረጋገጠው የዚህ ሽኩቻ ሰለባ የተደረጉት የኢንተርፕራይዞች ልማትና ሥራ እድል ፈጠራ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት የዎላይታ ተወላጅ አቶ ቢረጋ ብርሐኑ "ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሉዋት" እንደሚባለው ከሥር በፎቶው እንደምታዩት ቡሉኮ ተሸልመው የተሰናበቱ ሲሆን በውጤቱም ዎላይታ አንድ የአስፈፃሚነት ወንበሩን አጥቷል።

ይሄን ዜና ያቀረብንበት ዋናው አላማ በክልሉ "የዎላይታ ተወላጆች በቂ ውክልና አላቸው" የሚለውን ለማሳየት ወይንም የዎላይታ አመራርነት ቦታ "ለሌላ ብሄር ተሰጥቷል" የሚለውን ለማንፀባረቅ ሳይሆን የአቶ ተስፋዬ ይገዙ በህዝብ ስም ለመነገድ የሄዱበት ርቀትና ትግላቸውም፦ በአከባቢው የመንግስትን መዋቅር ተክተው በእሳቸው መርነት እንደተደራጀ የሚነገርለት የአመራር ምደባ ስርዓት ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ይከተላል ከሚባለው ዕሳቤና አሰራር ውጭ በአቤ-ልጅ ኔትወርክ፣ በአከባባዊነት ኔትወርክ፣ በትውውቅ ነው

በሀገር አቀፍ ደረጃ የዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ባስመዘገበው ውጤት ተጨማሪ ከጀርመን ድርጅት በተገኘ ድጋፍ በ 1.8 ቢሊዮን ብር እንዲገነባ የተመደበው ገንዘብ በግለሰቦች እጅ ለማስገባት ጥረ...
30/03/2024

በሀገር አቀፍ ደረጃ የዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ባስመዘገበው ውጤት ተጨማሪ ከጀርመን ድርጅት በተገኘ ድጋፍ በ 1.8 ቢሊዮን ብር እንዲገነባ የተመደበው ገንዘብ በግለሰቦች እጅ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ስለመሆኑ ተገለፀ።

ተጨማሪ ሊቃ አይነት እንዲገነባ በትምህርት ሚኒስትር በኩል ከጀርመን ሰው ለሰው ከተሰኘ ድርጅት በተገኘው ድጋፍ በዎላይታ ዞን የተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ በሆነበት ወረዳ እንዲገነባ ተብሎ አቅጣጫ ቢቀመጥም የአከባቢውን ፓለቲካ በጎጥ፣ በጎሳ እንዲሁም በጥቅም አደረጃጀት እየመሩ የሚገኙ በህገወጥ መንገድ ለሙስና በተጋለጠ አካሄድ ለማስገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

በዚሁም ተጨማሪ ሊቃ አይነት እንዲገነባ በትምህርት ሚኒስትር በኩል ከጀርመን ሰው ለሰው ከተሰኘ ድርጅት በአጠቃላይ 1.8 ቢሊዮን ብር ለመገንባት ከተያዘው በጀት በትናንትናው ዕለት 180 ሚሊዮን ብር ወደ ዎላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ገቢ መደረጉንም ከምንጮቻችን አረጋግጠናል።

ትምህርት ቤቱ ይገነባል የተባለው በአከባቢው ፓለቲካ በጎጥ፣ በጎሳ እንዲሁም በጥቅም አደረጃጀት ዘርጎተው በዋናነት እየመራ ይገኛል በተባለው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ ትውልድ መንደር ወረዳና ቀበሌ ካዎ ካይሻ መሆኑ ሌሎች ባለስልጣናትን ጨምሮ በርካቶችን እያነጋገረ እንደሚገኝም መረጃዎች ይጠቁማሉ።

አቶ ተስፋዬ ይገዙ በከፍተኛ ገንዘብ የሚሰራው ትምህርት ቤት በትውልድ መንደራቸው እንዲሰራ ያደረገበት ዋና ምክንያት ለአከባቢው ማህበረሰብ በማሰብ ሳይሆን ቀድሞው ከአርሶአደሮች መሬት በመግዛት ለቦታው የሚከፈል የካሳ ክፊያ ለመውሰድ ያመቻቸው እንዲሁም ለብልሹ ስራ እንዲመች ተደርጎ ራሱ ባዋቀረው ድርጅት ለማስገንባት ዝግጅት ማጠናቀቁን ከቅርብ ሰዎች ለመረዳት ተችሏል።

ባለፈው አመት በተመሳሳይ ትውልድ አከባቢ ከአርሶ አደሮች መሬት በመግዛት በዚያ ቦታ ላይ ትምህርት ቤት እንዲገነባ በማለት የመሬት ካሳ በእጅአዙር በመውሰድ ያለጨረታ ግንባታ እንዲከናወን ማድረጉንም ታማኝ ምንጭ እንደምሳሌነት ጠቅሷል።

በአከባቢው ከመንግሥት በላይ የራሳቸውን የጥቅም፣ የጎሳ፣ እንዲሁም የጎጥ አደረጃጀት በህቡዕ በማዋቀር ከህዝብ ይልቅ የግል ጥቅም በማስቀደም ህብረተሰቡ በመንግሥት ላይ እምነት እንዳይጥል በሚሰሩት ላይ የሚመለከታቸው አካላት በአስቸኳይ አስተማሪ እርምጃ እንዲወስድ ተጠይቋል።

ምንጭ Wolaita Times ምዲያ

የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና የቀድሞ የዎላይታ ዞን እንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ እንጂነር ተክሌ ቶማ ታሰረ።ለእስራቱ መነሻ ለዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት እየተሰበሰበ የሚገኘው ገንዘብ ግልፀኝነት በ...
29/03/2024

የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና የቀድሞ የዎላይታ ዞን እንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ እንጂነር ተክሌ ቶማ ታሰረ።

ለእስራቱ መነሻ ለዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት እየተሰበሰበ የሚገኘው ገንዘብ ግልፀኝነት በተሞላ መንገድ መሆን እንዳለበት በመጠየቁ በዛሬው ዕለት በፓሊስ ተይዞ መታሰሩን ከቅርብ ሰዎች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

የዎላይታ ሊቃ ት/ቤት የሁላችንም እንደመሆኑ መጠን ህዝባዊ የገንዘብ ሆነ የጉልበት እንዲሁም የማቴሪያል ድጋፍ መጀመር ካለበት ከማድረጋችን በፊት ቀዳሚ ተግባር እየተባለ ያለው:-

1,የት/ቤቱ ህንፃ ዲዛይን
2, የባንክ ሂሳብ ግልጽነት
3, የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ

-ከልማት ማህበሩ የተወጣጡ ፥
- ከንግድ ዘርፍ ማህበራት የተወጣጡ ፥
- ከሀይማኖትና ሀገር ሽማግሌዎች የተወጣጡ ፥
- ከፖለቲካ አደረጃጀት ገለልተኛ የሆኑ ወጣት፥
- ከምሁራን አደረጃጀት ዘርፍ የተወጣጡ ፥
- ሞዴል የሆኑ ግንባር ቀደመ አርሶአደር ፥
- ከሴቶች ዘርፍ አደረጃጀት ፥
- መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት የተወጣጡ ፥
-ከዎላይታ ዉጭ ያሉት የሚያስተባብር አካላት፥
- ከመንግሥት ሰራተኞች የተወጣጡ አካላት፥
- ከካድሬ ዉስጥም የተመረጡ መሆን አለበት እንጂ
ግለሰቦች ተነስቶ ስደት ሀገር ላይ ተይዞ /በታጣቂዎች የተያዘውን ሰው ለማስለቀቅ አይነት ገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ብሎ መሰብሰብ አይችልም ህገወጥም ነው ተብሏል።

በተጨማርም ዎላይታ ልማት ማህበር ሆነ ሊቃ የሁላችንም እንጂ የጥቂቶች ተቋም አይደለም በሚል በርካቶች እየጠየቁ ቢሆንም በአከባቢው አመራሮች ዘንድ ሰሞኑን የተጋለጠውን ስልጣን በጥቅም፣ በጎሳና በአከባቢያዊነት ስለመሆኑ ተጨባጭ መረጃ በመውጣቱ ያንን ለመሸፈንና አቅጣጫ ለማስቀየር በድንገት የተጀመረ ዘመቻ እንደሆነ እየተነገረ ይገኛል።
ምንጭ Wolaita Times ሚዲያ

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የአለምአቀፉ INBAR ተቋም ዋና ዳይረክተር በመሆን መሾማቸው ተገለፀ።በቅርቡ የመንግስት ኃላፊነትን በግል ምክንያት የለቀቁት አምባሳደሩ ዋና መስሪያቤቱን በቻይና አድርገ...
28/03/2024

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የአለምአቀፉ INBAR ተቋም ዋና ዳይረክተር በመሆን መሾማቸው ተገለፀ።

በቅርቡ የመንግስት ኃላፊነትን በግል ምክንያት የለቀቁት አምባሳደሩ ዋና መስሪያቤቱን በቻይና አድርገው ከ50 በላይ ሀገራት ላይ በተለያዩ ጉዳዮች ዘላቂ ልማትን በማበረታት እየሰራ በሚገኘው አለምአቀፉ ተቋም ዋና ዳይረክተር በመሆን የተሾሙት።

ተቋሙ እ.ኤ.አ. በ 1997 ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች እና አከባቢዎች ላይ በቀርከሃ ምርት፣ የተራቆተ መሬት ወደነበረበት በመመለስ፣ በአቅም ግንባታ ስራዎች እና በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ እንደሆነ ተገልጿል።

በቻይና ከሚገኘው ከተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት በተጨማሪ ማስተባባሪያ ቢሮችን በካሜሩን፣ በኢኳዶር፣ በኢትዮጵያ፣ በጋና እና በህንድ በማድረግ ከ45 በላይ ሀገራት እየሰራ የሚገኘው ይሄው ተቋም በግብርና፣ በምግብና ገጠር ልማት፣ በአቅም ግንባታ፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በልማት ትብብር፣ በትምህርት፣ በሥርዓተ-ፆታ እኩልነት እና ሴቶችን ማብቃት፣ በተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር፣ በሰላምና ልማት፣ በግሉ ዘርፍ ልማት፣ በስነ ተዋልዶ ጤና እንዲሁም በምርምር ዘርፎችም ላይ ዘርፈብዙ ስራ እየሰራ የሚገኝ ግዙፍ አለምአቀፍ ተቋም እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተለያዩ ሀገራት በዲፕሎማሲያው ዘርፍ ኢትዮጵያን በብቃት ያገለገሉት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የኢትዮጵያ መንግስት በሰጠው አውንታዊ ምላሽ ታክሎበት ከቀናት በኃላ አዲሱን ስራቸውን በቻይና ቤጂንግ ከሚገኘው ዋና መስሪያቤት በማድረግ ይጀምራሉ።

አምባሳደር ተሾመ በቅርቡ አአ ከጥር 6 ቀን 2023 እስከ መጋቢት 13 ቀን 2024 የኢትዮጵያ ብሄራዊ መልሶ ማቋቋሚያ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩ ሲሆን በረጅም የሙያ ዘመናቸው የመንግስት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር እና የወጣቶች ሚኒስትርን ጨምሮ በኢትዮጵያ መንግስት ውስጥ ከፍተኛ የአመራር ቦታዎችን ተሳትፈዋል።

አምባሳደሩ በዲፕሎማሲው በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ደረጃ ሰፊ ልምድ ያላቸው ሲሆን በጋና፣ ግብፅ፣ ኬንያ፣ ፈረንሳይ፣ ቤልጂየም እና ቻይናን ጨምሮ አገራቸውን በአምባሳደርነት በስድስት ሀገራት እና በሶስት አህጉራት እንዲሁም በብራስልስ ለሚገኙ የአውሮፓ ህብረት ተቋማት እውቅና ተሰጥቷቸው በዩኔስኮ እንዲሁም በUNEP እና UN-Habitat የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ሆነውም አገልግለዋል።

በተጨማሪም 120ኛውን የኢንተር-ፓርላማ ዩኒየን (አይፒዩ) አጠቃላይ ጉባኤን ጨምሮ በርካታ አለም አቀፍ ጉባኤዎችን መርተዋል እና 30ኛውን የአፍሪካ ፓርላሜንታሪ ህብረትን (APU)ን፤ እንዲሁም በተለያዩ አለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ላይ በመሳተፍ በመንግስትም ሆነ በዲፕሎማሲው መስክ ያካበቱትን ልምድ አመራር፣ የዕቅድ፣ የማሻሻያ እና የፖሊሲ ማውጣት ልምድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ሲል ተቋሙ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል።

Wolaita Times

የእንሰት አብዮት በወላይታ ዞን፤የእንሰት ምርት በዞኑ አብዛኛው አከባቢዎች በስፋት የሚመረትና ለረጅም ዘመናት ለምግብነት እየዋለ የመጣ "አረንጓዴ ወርቅ" ነው፡፡እንሰት ምግብ ዋስትናን ለማረጋ...
23/03/2024

የእንሰት አብዮት በወላይታ ዞን፤

የእንሰት ምርት በዞኑ አብዛኛው አከባቢዎች በስፋት የሚመረትና ለረጅም ዘመናት ለምግብነት እየዋለ የመጣ "አረንጓዴ ወርቅ" ነው፡፡

እንሰት ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የተመጣጠነ የሥነ ምግብ ስርዓትን ለመፍጠር ያግዛል፤ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታዎችን እየሰጠ ያለ ተክል ነዉ።

እንሰት የጎጆዎች ግርማ ሞገስ፣ የጓሮዎች ማድመቂያና አረንጓዴ ሰገነት ከመሆን ባሻገር “ለግሉኮስ” ማቀነባበሪያ ግብዓት እንደሚሆን በጥናት ተረጋግጧል፡፡

እንሰት 20 ሚሊዮን የሚሆነው ህዝብ በቀን ሦስት ጊዜ መመገብ የሚያስችል እንደ ሀገር ያልተጠቀምንበት ሲሳይ፤ እስካሁን በጣም ያጣነው ትልቅ ሀብት ነው።

በዘመናዊ መንገድ አምርቶ ለገበያ የሚቀርብበት መንገድ ቢኖር ከሀገር አልፎ ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም ገበያ መቅረብ የሚችል እምቅ ሀብት እንደሆነም ተጠቁሟል።

እንሰት ድርቅን የሚቋቋም፣ በውስን መሬት ላይ የሚለማ፣ ለምግብና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውል የተለያዩ ተዋፅኦዎቸን የሚሰጥ ተክል ነዉ።

የአየር ንብረት ሚዛንና የአካባቢን ለምነትን ጠብቆ ለማቆየትም ያግዛል የእንሰት ተክል። በምግብ ራስን ለመቻል በሚደረገው እንቅስቃሴም የበኩሉን እያበረከተ ይገኛል።

"ባህርዛፍን ከማሳ እንንቀል፤ እንሰትን እንትከል!!"

"በአሰራር ጉድለት ምክንያት ደሞዝ እየተከፈለን አይደለም፤ ተቆራርጦ የሚገባ ደሞዝም በፈረቃ እየቀረበ ነው" በሚል የዎላይታ ዞን የመንግሥት ሰራተኞች ቅሬታ አሰሙ።የደሞዝ ክፍያው መዘግየት በኑ...
22/03/2024

"በአሰራር ጉድለት ምክንያት ደሞዝ እየተከፈለን አይደለም፤ ተቆራርጦ የሚገባ ደሞዝም በፈረቃ እየቀረበ ነው" በሚል የዎላይታ ዞን የመንግሥት ሰራተኞች ቅሬታ አሰሙ።

የደሞዝ ክፍያው መዘግየት በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዳሳደረባቸው የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ በአብዘኛዉ መዋቅሮች ደመወዝ በጊዜ ባለመከፈሉ በዝህ የኑሮ ዉድነት የቤት ክራይ፣ የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያ እንዲሁም የቤተሰብ ቀለብ መግዣ በማጣት እየተቸገሩ እንደሆነ በመግለፅ የከፋ ጉዳት ከመድረሱ አስቀድመዉ ምላሽ እንዲሰጥበት" ሲሉም አክለው ጠይቀዋል።

"ደመወዝ የሚሰጥበት ወር ገደብ ቢያልፍም እስከዛሬ ድረስ የመንግስት ሠራተኛ ደመውዝ ተከፍለው እንኳን ኑሮ ውድነትን መቋቋም ባልቻለበት ወቅት ደመውዝ ተከልክለን በዝምድና፣ ከሰፈር፣ በጋብቻ እና በአይን አባትነት ትስስር የተዋቀረው የአከባቢው አመራር ቡድን በየቦታው ድግስ በማውጣትና በሙስና ተግባር ተጠምደው እኛ ተረስተናል" ሲሉ በተለያዩ መዋቅር እየሰሩ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ተመሳሳይ ቅሬታ አቅርበዋል።

በዞኑ ከሚገኙ 22 መዋቅሮች ማለትም 16 ወረዳዎች፣ 5 የከተማ አስተዳደር እና ከዞን መዋቅር የመንግስት ሰራተኞች የየካቲት ወር ደመውዝ በፈረቃ ተደርጎ የተከፈላቸው 3 ብቻ ስለመሆኑና የተለያዩ መዋቅሮች የስራ ማቆምና ለተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ የመውጣት ዘመቻ ለመጀመር እንቅስቃሴ መጀመራቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የዞኑ መንግስት በዞኑ የተፈፀሙ ህገወጥ ቅጥሮችና የማዳበሪያ ዕዳ ይህንን ችግር ማስከተሉን በመግለፅ ሰራተኛ ሳይሆኑ ደሞዝ የሚከፈላቸው ጭምር መኖራቸው ተረጋግጦ ለማስተካከልና የደሞዝ ችግሮችንም ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው" በሚል አንድ የዞኑ መንግስት ከፍተኛ አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ምላሽ የሰጠ ቢሆንም ዎላይታ ዞን በክልሉ ከፍተኛ ግብር የሚሰበሰብና የመሰብሰብ አቅም ያለው ቢሆንም በተቃራኒው ደግሞ ከህብረተሰቡ የሚሰበሰብ ገንዘብ በተለያዩ መንገዶች የሚመዘበር በመሆኑ ለአከባቢው ልማት ሆነ ለመንግሥት ሰራተኞችም ደመወዝ ሆነ ወደ መስክ የወጡበት ወጪ በግዜ መክፈል አለመቻሉ በበርካቶች ዘንድ ጥያቄ እየፈጠረ ስለመሆኑም ተገልጿል።

ምንጭ ወላይታ ታይምስ ሚዲያ

የሽግግር ፍትህ ብቁ የሰውሃይል የያዘ ጠንካራ የፍትሕ ሥርዓትን ለመገንባት ያስችላል - አቶ ጥላሁን ከበደአዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተ...
20/03/2024

የሽግግር ፍትህ ብቁ የሰውሃይል የያዘ ጠንካራ የፍትሕ ሥርዓትን ለመገንባት ያስችላል - አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በሽግግር ፍትህ ሪፎርም ተግዳሮቶች ዙሪያ ከክልሉ ከፍተኛ የፍትህ ተቋማት አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ርዕሰ መስተደዳሩ በውይይቱ እንደገለጹት÷ ክልሉ በአዲስ መልክ ከተደራጀ በኋላ የሽግግር ፍትህ ሪፎርም ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ ውይይቶች እየተደረጉ ነው።

የሽግግር ፍትህ ሪፎርም ዕውቀትና ሥነ ምግባር የተላበሰ የሰው ሃይል የያዘ ጠንካራ የፍትህ ሥርዓት በክልሉ ማስፈን የሚያስችል ፖሊሲ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

በክልሉ ከፍትህ አንጻር ብዙ መሻሻሎች ቢኖሩም አንዳንድ የሚታዩ ተግዳሮቶች እንዳሉ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል ሀገራዊ የሽግግር ፍትህ ሪፎርም ፖሊስ በክልሉ ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ አመራሮች በቁርጠኝነት መስራት እና ሒደቱን መምራት እንደሚገባቸውም ነው ያሳሰቡት።

ጠንካራ የፍትሕ ተቋማት እንዲኖሩና ነጻነታቸውን እና ገለልተኝነታቸውን እንደጠበቁ በፍትህ ስርዓቱ ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በቅንጅት መስራት እንደሚገባም በአጽንኦት ገልጸዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይ እምነት የሚጣልበት ጠንካራ የፍትህ ሥርዓት ለመገንባት መሰራት ያለባቸውን በመለየት ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡

በዎላይታ ሶዶ ከተማ የዞኑ ገቢ መምሪያ ኃላፊ ወንድም የቀበሌ ቤትን በሀሰተኛ ሰነድ እየሸጠ ተይዞ በአመራር ትዕዛዝ እንዳይከሰስ ተደረገ ሀሰተኛ የገቢ ደረሰኝ በማዘጋጀት የመንግስት ቀበሌ ቤት...
19/03/2024

በዎላይታ ሶዶ ከተማ የዞኑ ገቢ መምሪያ ኃላፊ ወንድም የቀበሌ ቤትን በሀሰተኛ ሰነድ እየሸጠ ተይዞ በአመራር ትዕዛዝ እንዳይከሰስ ተደረገ

ሀሰተኛ የገቢ ደረሰኝ በማዘጋጀት የመንግስት ቀበሌ ቤትን እየሸጡ የተያዙ ግለሰቦች በዎላይታ አመራር ትዕዛዝ እንዳይከሰሱ መደረጉም አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል።

የአቶ አሰፋ አድማሱ የተባለ ግለሰብ በሶዶ ከተማ ድል በገሬራ በተባለ ቀበሌ ለመንግስት ቤት ኪራይ የከፈለበት (0538901) ንምራ ቁጥር ያለው ሕጋዊ ደረሰኝ ተጠቅሞ አቶ ተስፋሁን በለጠ ( የአማራር ወንድም ) የተባለ ግለሰብ ከላይ ከተጠቀሰው ጋር ተመሳሳይ ንምራ ቁጥር (0538901) ያለው የሕገወጥ ደረሰኝ አመሳስሎ በማሳተም የቤት ሽያጭ ውል ማጽደቂያ በአራዳ ገቢዎች የተከፈለ በማስመሰል የመንግስት ቀበሌ ቤት ለመሸጥ የሰራው ሀሰተኛ ደረሰኝ ስለመሆኑ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጥ ችሏል።

ሀሰተኛ ደረሰኝ በማተም የተፈጸመው ወንጀል ሳያንስ ንብረትነቱ የመንግስት የሆነውን የቀበሌ ቤት ለግለሰቦች ለመሸጥ ሲሞክር የተያዘው ግለሰብ በዎላይታ ዞን ውስጥ አንድ የዞን መምሪያ ኃላፊ ወንድሞ መሆኑ የተፈጸመውን ወንጀሉ አሳሳቢ ከማድረጉም በላይ ወንጀለኛው በሕግህም ተጠያቂ እንዳይሆን ማድረጉም በመረጃው ተገልጿል።

የዞን አቃቤ ሕግ ሙሉ መረጃ ደርሶበት ክስ ከመሰረተ በኃላ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ መጥሪያ ወጥቶለት ተጠርጣሪው በሶዶ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት እየሰራ ባለበት አሁን ያለው የዞን አመራሮችና የሶዶ ከተማ አስተባባሪዎች ጭምር ተሳስቦ የተነጋገሩ ቢሆንም "ጉዳዩ ይፋ ከወጣ በዘርፉ የተፈፀሙ በርካታ ጥፋቶች ይጋለጣሉ" በሚል በመፍራት ግለሰቡ ወደ ፍርድ ቤት እንዳይቀርብ መደረጉንም ከምንጮቻችን አረጋግጠናል።

በዚህ መንገድ ሕገወጥ ደረሰኝ ሕትመት እንዲሁም የቀበሌ ቤት ለግለሰቦች ለመሸጥ በአደባባይ የሞከሩት ቢያዙም በአመራር ሽፋን እየተሰጠ ወንጀል ፈጻሚው በሕግ አለመጠየቁ በአከባቢው የህግ የበላይነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት እንደሆነ አጠያያቂ እንደማይሆን ይገለጻል።

በዎላይታ ዞን ይሁን በክልል ያሉ የፍትህ ተቋማት ይህንንና መሰል ወንጀለኞችን ተከታትሎ ወደ ሕግ እንዲያቀርብ እየጠየቅን ይህ ሳይሆን ስቅርና ለሚፈጸመው ወንጀል የመንግስት አመራር ሽፋን እየሰጠ የሚቀጥል ከሆነ ስርዓት አልበኝነት ይነግሳል" በሚል በርካቶች ይጠይቃሉ።

ዎላይታ ዞን በክልሉ ከፍተኛ ግብር የሚሰበሰብና የመሰብሰብ አቅም ያለው ቢሆንም አመራሮች ከጥቂት ነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር ሀሰተኛ ደረሰኝ ጭምር እንዲዘጋጅ እያሳተሙ በወንጀል ተግባር ስለመሰማራታቸው የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃዎች የደረሰን ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ ከህብረተሰቡ የሚሰበሰብ ገንዘብ በተለያዩ መንገዶች የሚመዘበር በመሆኑ ለአከባቢው ልማት ሆነ ለመንግሥት ሰራተኞችም ደመወዝ በግዜ መክፈል እንዳቃታቸው ተደርሶበታል።
ሀሰተኛ የገቢ ደረሰኝ በማዘጋጀት የመንግስት

የዜናው ምንጭ ከወላይታ ታይምስ ሚዲያ

መድረኩ የአመራሩን የፖለቲካ መበስበስ በተጨባጭ ያጋለጠ ታሪካዊ ቀን መሆኑን የዎላይታ ዞን የመንግስት ሰራተኞች የብልጽግና ፓርቲ አባላት ተናገሩ።በዎላይታ ዞን ፐብሊክ ሰርቫንት የብልፅግና አባ...
18/03/2024

መድረኩ የአመራሩን የፖለቲካ መበስበስ በተጨባጭ ያጋለጠ ታሪካዊ ቀን መሆኑን የዎላይታ ዞን የመንግስት ሰራተኞች የብልጽግና ፓርቲ አባላት ተናገሩ።

በዎላይታ ዞን ፐብሊክ ሰርቫንት የብልፅግና አባላት ኮንፈረንስ ላይ አባሉ በዘጠኝ መሠረታዊ ድርጅቶች ኮንፈራንስ በዛሬው ዕለት ያካሄደ ሲሆን "የአባሉ ትግል ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ወደ ላቀ ከፍታ የተሸጋገረበት ሆኖ ታይቷል" ሲሉም አባላቱ ገልጿል።

በአበልጅ (ጃላ) እና በአከባቢ፤ በሌብነት፤ በጎሳ፤ በጥቅም ላይ የተሳሰረ የስልጣን ኮሪቻ መፍረስ አንደምገባው አባሉ በሁሉም መሠረታዊ ፓርቲዎች በምሬት ያነሳ ሲሆን በዎላይታ ዞን መንግስት ሰራተኞች፣ መምህራን፣ ሶዶ ከተማ፣ አረካ ከተማ፣ ቦዲቲ ከተማ፣ ዳሞት ወይዴ ወረዳ፣ ድጉና ፈንጎ ወረዳ፣ ሁምቦ ከተማ፣ ገሱባ ከተማ፣ ጉኑኖ ከተማ፣ ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ በሁሉም መሠረታዊ ፓርቲዎች ላይ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች ከየአካባቢው ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ደርሷል።

አመራሩ አንዱ የአንዱን ልጅ አይን በመያዝ በአበልጅነት ወደ አመራር ፑል በኔትወርክ በመሳሳብ ሌብነታቸውንና የቆሸሸ ተግባራቸው እንዳይጋለጥ እንደ ቃል መገባቢያ መንገድ እየተጠቀሙ እንደሚገኙ በዛሬው ዕለት በርካታ መድረኮች ላይ በአባላቱ የተነሳ ቁልፍ ጉዳይ ስለመሆኑ ተገልጿል።

አረካ ከተማ የሚገኘው ቼንትሮ አዩቲ ፔር ለኢትዮጵያ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት በተስፋዬ ይገዙና በአበልጆቹ አማካይነት የተቋሙ የቀድሞ ህጋዊ ሳይት ፕላን እንዲመክን ተደርጎ በግለሰብ ስም አዘጋጅተው ማስተላለፋቸው በተጨባጭ በአባላቱ ከተነሱ ዋና ጉዳዮች አንዱ እንደሆነ ተገልጿል።

በዎላይታ ሶዶ ከተማ ሄሎ ሞተርስ መኪና መገጣጠሚያ የኢንቨስትመንት ቦታ ከግለሰቦች ገንዘብ ተቀብሎ ከስታንዳርድ ውጪ 100,000 ካሬ መሰጠቱን፤ የሶዶ ከተማ መርካቶ ገበያ ግንባታ በሚሊዮን ገንዘቦች መመዝበሩ፤ በሶዶ ከተማ አስተዳደር ላይ ቀዳማዊት እመቤት ያስገነባችው የዳቦ ፋብሪካ ላይ በከፍተኛ ገንዘብ ተገዝቶ የቀረበ የስንዴ ዱቄትን በአመራር ውሳኔ በሙሉ በመሸጥ ስርቆት መፈጸማቸው በተለያዩ መድረኮች በአባላቱ ተነስቷል።

የወይቦ መስኖ ግንባታ ላይ በካሳ ሰበብ የሙስና ወንጀል መፈጸማቸው፣ የህዝብ ተቋም የሆኑት ወልማ እና የወላይታ ቴሌቪዢን ተቋሞችን ሃብት እየመዘበሩ መሆናቸው፤ ቅጥር፣ ዝውውር፣ ደረጃ ዕድገትና ሹመት በኔትወርክ አደረጃጀት ማካሄድ፣ አመራሩ የአበልና የነዳጅ አጠቃቀም የፋይናንስ ደንብና አሰራር አለመከተሉ፣ በመላ መዋቅር የሚገኘው አመራር በመሬት ወረራና በሌላ የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር መዘፈቁ እና ሌሎችንም የአመራሩን ብልሽት አባላቱ ያለምንም ፍርሃት በአደባባይ በማስጣት ከፍተኛ ትግል አካሂደዋል።

እንደ መረጃ ምንጮቻችን ገለፃ በኮንፈረንሱ ቀድሞው ለህዝቡም ለፓርቲውም እኩይ አላማውና ድርጊቱ ገሃድ የወጣበት የኔትወርክ ቡድኑ በተለይ የመንግስት ሰራተኛውን በአበልና በጥቅማጥቅም ዝም ለማሰኘት የተደረገ ሙከራ በርካታ ቦታዎች ላይ የከሸፈ ሲሆን አባላቱ በግልጽ ቋንቋ በዞኑ እየሆነ ያለው "በመንግስት ላይ እምነት ለመጣል እንኳን የሚያስቸግር ነውና እውነትም የብልፅግና ፓርቲያችን ለህዝብ ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጥና የራሱ ፓርቲ ስም ጭምር የሚያጎድፍ እነዚህ ቡድኖች በዘረጉት የማይመጥን የግለሰቦች ኔትወርክ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ እርምት እርምጃ እንዲወስድ" የሚል ሀሳብም በሁሉም አከባቢዎች ያለልዩነት ማለት በሚቻል ደረጃ ተንፀባርቋል።

በአጠቃላይ ዎላይታ በአንድ ሰዉ እጅ መዳፍ በወደቀበት ሁኔታ በአከባቢው ብልጽግናን ለማረጋገጥና ሕዝቡን ማሻገር አስቸጋሪ ነው ብሏል።

የዎላይታ የፖለቲካ ንቅዘት ዛሬ በብልፅግና ፓርቲ አባላት ኮንፌራንስ መድረክ እንዴ ዴማሚቲ በዲጋሚ መፈንዳት  ጀምሯል፡፡ በተለይም አስነዋሪው የአበልጅ (ጃላ) ፖለቲካ በዎላይታ ጉድ ማፍላቱን ...
18/03/2024

የዎላይታ የፖለቲካ ንቅዘት ዛሬ በብልፅግና ፓርቲ አባላት ኮንፌራንስ መድረክ እንዴ ዴማሚቲ በዲጋሚ መፈንዳት ጀምሯል፡፡

በተለይም አስነዋሪው የአበልጅ (ጃላ) ፖለቲካ በዎላይታ ጉድ ማፍላቱን ቀጥሏል።

የአስተዳዳሪውና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃለፊው መሀላ ተደረሰበት። በዛሬው የብልጽግና አባላት ኮንፈረንስ ላይ በአበልጅነት በመሳሳብ ስልጣን የያዙ የዎላይታ አመራሮች አበልጅነት ዝምድናን ከስልጣን መሸላለም ባሻገር በህዝባቸውና በመንግስት ላይ እየፈጸሙ ላሉት የሙስና ወንጀል እርስ በርሳቸው ላለመከዳዳት እንደ ቃሌ-ማሀላ እየተገለገሉበት ይገኛሉ ተብሎ በከፍተኛ ሁኔታ እየተናጠ ይገኛል፡፡

በአበልጅ (ጃላ) እና በአከባቢ፤ በሌብነት፤ በጎሳ፤ በጥቅም ላይ የተሳሰረ የስልጣን ኮሪቻ መፍረስ አንደምገባው አባሉ በሁሉም መሠረታዊ ፓርቲዎች በምሬት እያነሳ መሆኑን ከውስጥ ምንጭ ተሰምቷል፡፡ ስጠናቀቅ በዝርዝር እንመለስበታለን፡፡

የመፍረስ አደጋ ተጋርጦ በአንድ ሰፈርና ጥቅም ተጋሪዎች እየተመራ የሚገኘው የመላው ዎላይታ ህዝብ ማህበር ቀጣይ ሳምንት ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚያካሂድ ተገለፀ።የህዝብ ውግንና ባላቸው ግለሰቦች ተ...
17/03/2024

የመፍረስ አደጋ ተጋርጦ በአንድ ሰፈርና ጥቅም ተጋሪዎች እየተመራ የሚገኘው የመላው ዎላይታ ህዝብ ማህበር ቀጣይ ሳምንት ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚያካሂድ ተገለፀ።

የህዝብ ውግንና ባላቸው ግለሰቦች ተመስርተው የመላው ህዝብ ኩራት የነበረው የዎላይታ ልማት ማህበር 23ኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤ በመጭው ቅዳሜ መጋቢት 14/2016 ዓ.ም እንደሚያካሄድ ተነግሯል።

ልማት ማህበሩ በአዲስ መልክ ከተቋቋመበት ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ ከመላው ዎላይታ ህዝብ፣ ከአባለት በሚሰበሰብ ሀብት፣ ከረጂ ድርጅቶች በሚያገኘው ድጋፍና ከገቢ ማስገኛ ተቋማት በሚሰበስበው ገቢ በዞኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ ያሳረፈው አሻራ እጅግ በጣም የሚደነቅና ለሌሎች አከባቢ ልማት ማህበራትም ተምሳሌት እየሆነ የመጣ በአጭር ጊዜ ተቋቁመው ውጤታማ የሆነ የሚሊዮኖች ሀብትና ኩራት ቢሆንም አሁን አሁን የፓለቲካ ማሽን የሌቦች ዋሻ በመሆን የተጀመረውን ዋና መስሪያቤት ህንፃ ግንባታ በሙስና በጅምር በማቆም ለሰራተኞቹ እንኳን ደሞዝ በጊዜ ለመክፈል እየተቸገረ ስለመሆኑ ማህበሩን በቅርበት የሚያውቅ ምንጭ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አስረድቷል።

በአሁኑ ወቅት በማህበሩ ስር የሚመሩ በርካታ ዳሞታ ኮንስትራክሽን ጨምረው ያሉት በተዋቀረው በሌብነት፣ በአከባቢያዊና ጥቅም አደረጃጀት፣ በተሰራው ሴራ የአባላት ድጋፍና እምነት ማነስ፣ ከዚህ በፊት የሚሰሩ አጋር ድርጅቶች መቀነስ እንዲሁሂ ልምድና እውቀት ያላቸው ሰዎች ተገፍተው ከማህበሩ መልቀቅ ምክንያት እንደ ከ1970ዎቹ ጀምሮ እስከ 1993 ዓ.ም በማህበሩ የተደቀነው አይነት በአንድ ሰፈር ልጆች እንዲመራ ተደርጎ ህዝቡ "ማህበሩ የሁሉም አይደለም" በሚል ድጋፍ እንዲያቆም ድብቅ ሴራ በመኖሩ የመፍረስ አደጋ እንደተጋረጠበትም አክሎ ጠቁሟል።

"አንጋፋው የዎላይታ ልማት ማህበር በሰው ሀብት ልማት፣ በዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ፣ በትምህርት እና በተቀናጀ ጤና የትኩረት አቅጣጫ ዘርፎች በዞኑ በተለያዩ ወረዳዎች ከራሳቸው በላይ ለህዝብ ጥቅም ቅድሚያ በሚሰጡ ታታሪ አመራሮችና ሰራተኞች ተዋቅሮ የመላው ህዝብ ኩራት የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ያ አመራርና አብዛኞቹ ሰራተኞች እንዲወጡ በማድረግ እስከ ቦርድ ሰብሳቢ ድረስ በአንድ ሰፈር፣ ትውውቅና ጥቅም እንዲደራጅ በመደረጉ ልማት ማህበሩ የነበረውን ግርማ ሞጎስ እያጣ ነውና ብቸኛው የህዝብ ሀብት የሆነውን ለመታደግ ሁሉም ዎላይታ ያለልዩነት መረባረብ እንዳለበት" ጥሪ አቅርቧል።

ማህበሩ ከ1957 ዓ.ም ጀምሮ በዎላይታ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ተሰማርቶ አያሌ ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ከቆየ በኋላ ከ1970ዎቹ ጀምሮ እስከ 1993 ዓ.ም ባለው ጊዜ አሁን ላይ በማህበሩ የተደቀነው አይነት በአንድ ሰፈር ልጆች እንዲመራ ተደርጎ ህዝቡ ማህበሩ የሁሉም እንዳይልና ድጋፍ እንዲያቆም ድብቅ ሴራ በመኖሩ፣ ለልማት የሚሰበሰብ ገንዘብ ግለሰቦች ተከፋፍለው ስለበሉ እንዲሁም በተለያዩ መንገዶች በማህበሩ ላይ ህዝቡ የእኔነት ስሜት እንዲያጠፋ በመደረጉ ተዘግቶና ተዳክሞ የቆየ ቢሆንም ያለልዩነት ከሁሉም አከባቢዎች የመላውን ህዝብ ጥቅም መነሻ ባደረገ መንገድ የተሰባሰቡ የህዝብ ልጆች በ1993 ዓ.ም ዳግም በአዲስ መልክ እንዲዋቀር በማድረግ ስራውን ጀምሮ በአጭር ጊዜ አስደማሚ ለውጦችን ማስመዝገቡን በርካቶች ይመሰክራሉ።

ባለቤትነቱ የመላው ህዝብ የሆነው ማህበሩ የዘንድሮውን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ከላይ የተዘረዘሩ ጥቂት ግለሰቦች የፈጠሩት ዘርፈብዙ ችግሮች ጫናና የመፍረስ አደጋ በተጋረጠበት በዚሁ ወቅት ለ23ኛ ጊዜ ያካሂዳል።

በዎላይታ ዞን "ያለልዩነት የተነሳውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ይደግፋሉ" የተባሉ ግለሰቦች እየታሰሩ ስለመሆኑ ተገለፀ።የዜጎች ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ ተፈጥሯዊና ህገመንግስታዊ መብት ተጠ...
16/03/2024

በዎላይታ ዞን "ያለልዩነት የተነሳውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ይደግፋሉ" የተባሉ ግለሰቦች እየታሰሩ ስለመሆኑ ተገለፀ።

የዜጎች ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ ተፈጥሯዊና ህገመንግስታዊ መብት ተጠቅሞ በዎላይታ ዞን ውስጥ የሚስተዋለውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መናገር፣ መንግስታዊ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ማጋለጥ እንዲሁም በአከባቢው መንግስታዊ መዋቅር በአቤ-ልጅ ኔትወርክና ጥቅም ላይ መመስረቱን በተመለከተ በአሁኑ ወቅት ያለልዩነት የተነሳውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ይፋ ለማድረግ የሚሞክሩና በእንቅስቃሴው ተሳትፈው አላቸው የተባሉ ግለሰቦች ከያሉበት ያለምንም ህጋዊ መጥሪያና አሰራር እየታሰሩ ስለመሆኑ ከየስፍራው የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ወጣቶቹና የመብት ተሟጋቾች የጅምላ እስራትና አፈሳ ለቤተሰቦቻቸው ጭምር እንዳይነገር ተብሎ በማስፈራራት በአረካ፣ ክንዶ ኮይሻ፣ ዳሞት ወይዴ፣ ሶዶ፣ ቦዲቲ ከተማ እንዲሁም ሌሎች መዋቅሮች ላይ የተጀመረ ሲሆን አንዳንድ የታሰሩ ግለሰቦች የሚያርፉበት እስርቤት ከመደበኛ ፓሊስ ጣቢያ ውጪ ስለመሆኑም ከአይን እማኞችና በአከባቢው ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተል ምንጭ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያስረዳው።

በትናንትናው ዕለት "ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና" በሚል መሪህ ቃል በዞኑ በሁሉም ቀበሌዎች በተካሄደው ህዝባዊ ኮንፈረንስ ላይ አባላቱ የዎላይታ ህዝብ በሌብነትና በጥቅም ትስስር በተደራጀው ኔትወርክ ምክንያት ከፍተኛ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ እጦት እንዲሁም በደል እየደረሰበት በመሆኑ በዞኑ "ፓርቲያችን ከሚከተለው ዕሳቤና አሰራር ውጭ የተዘረጋው መዋቅር በአስቸኳይ እንዲፈርስ፤ በአስናዋሪ ድርጊታችሁ በመንግስት ላይ እምነት ለመጣል እንኳን እየተቸገርን ነውና የፓርቲውንም መልካም ስም የሚያጎድፍ የግለሰቦች ኔትወርክ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ እርምት እርምጃ እንዲወስድ" በሚል የዎላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ አባላት ያለልዩነት በይፋ መጠየቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በተቃራኒው በአከባቢው ባልተለመደ ሁኔታ አባላት ጠንከር ያለ ትችትና ቅሬታ በተለይም የዎላይታ አመራር ምደባ ስርዓት ብልጽግና ፓርቲ ከሚከተለው ዕሳቤና አሰራር ውጭ ዞኑ ለተለያዩ ችግሮች ስለመጋለጡ ተጨባጭ ማብራሪያ በማሰማታቸው አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከኮንፈራንስ አዳራሽ በማውጣት ማሳር፣ ማስፈራሪያና ዛቻ ማድረግ እንዲሁም በአመራሮችና ፀጥታ አካላት ተገደው ይቅርታ ጠይቀው ከእንደገና ለተሰበሰቡ አባላት "ባለፉት ጊዜ በአካባቢያችን አስደማሚ ለውጥ ተመዝግቧል" ብለው እንዲያወሩ ከማድረጋቸው ባሻገር በዛሬው ዕለት ደግም "ለምን እንደዛ ተናገራችሁ ? " ተብሎ እስርና እንግልት እየደረሰባቸው ስለመሆኑ ከተለያዩ ምንጮች እየደረሰ የሚገኘው መረጃ ያመለክታል።

የዎላይታ ዞን ከየትኛውም አከባቢ በላይ ሚዲያዎች፣ ህዝብ ውግንና ያላቸው አመራሮች፣ የመብት ተሟጋቾች እንዲሁም ወጣቶች ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ ተፈጥሯዊ እና ህጋዊ መብት ተጠቅመው በአከባቢው የሚስተዋሉ መንግስታዊ አሰራርና ብልሽት ላይ በሰላማዊ መንገድ ትችት በሚያደርጉበት ወቅት በህገወጥ መንገድ በማፈን፣ በማሰር፣ ያለጥፋታቸው ፍርድቤት እንዲመላለሱ በማድረግ እንዲሁም በስደት ከአከባቢው እንዲሸሹ የሚያስገድድ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለፃችን ይታወሳል።

ምንጭ ወላይታ ታይምስ ሚዲያ

በዞኑ ፓርቲው ከሚከተለው ዕሳቤና አሰራር ውጭ የተዘረጋው መዋቅር በአስቸኳይ እንዲፈርስ የዎላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ አባላት ጠየቁ።በዎላይታ በዛሬው ዕለት በሁሉም መዋቅሮች የተካሄደው የብልፅ...
15/03/2024

በዞኑ ፓርቲው ከሚከተለው ዕሳቤና አሰራር ውጭ የተዘረጋው መዋቅር በአስቸኳይ እንዲፈርስ የዎላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ አባላት ጠየቁ።

በዎላይታ በዛሬው ዕለት በሁሉም መዋቅሮች የተካሄደው የብልፅግና ፓርቲ አባላት ጉባኤ ከወትሮው በተለየ መንገድ የለውጥ ሀሳቦችና ከፍተኛ ቅሬታ ጥያቄዎች የተንፀባረቀበት መሆኑን ከየአካባቢው የደረሰን መረጃ አመላክቷል።

ኮንፍራንሱ "ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና" በሚል መሪህ ቃል በዞኑ በሚገኙ በሁሉም ቀበሌዎች የተካሄደ ሲሆን አባላቱ የዎላይታ ህዝብ በሌብነትና በጥቅም ትስስር በተደራጀው የኔትወርክ ቡድን ምክንያት ከፍተኛ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ እጦት እንዲሁም በደል እየደረሰበት ስለመሆኑ በስፋት አንስተዋል።

የአመራሩ ምደባ ከብልጽግና ዕሳቤ እና አሰራር መሪህ ውጭ በአቤ-ልጅ ኔትወርክ፣ በአከባባዊነት ኔትወርክ፣ በትውውቅ እና በጥቅም ላይ የተመሰረተ የቤተሰባዊ ኔትወርክ በመሆኑ በየአካባቢው በተደራጀ ሁኔታ በከተማ እና በገጠር መሬት ዘረፋ፣ የህዝብ ሀብት ምዝበራ፣ ቃል የተገቡ ልማት አለመጀመር፣ እ-ፍታሀዊ የስልጣን ድልደላ፣ የተጀመሩና ለመጀመር የታቀዱ የተለያዩ ልማቶች የሚበጀተውን ገንዘብ ለአመታት እያጓተቱ ያለጠያቂ ተከፋፍለው መብላት እየተለመደ የመጣ እስኪሆን መድረሱንም አባላቱ አንፀባርቀዋል።

"ዎላይታ ላይ ልጆቻቸዉ ወደ ጎዳና ሳይወጡ በተወለዱበት አካባቢ የአባትና የእናት ፍቅር እያገኙ ቢያድጉ አይጠሉም፡፡ ግን ይህ እድል የለም፡፡ ከህፃናት ጀምሮ በየጎዳናው ለስቃይና ለስደት ኑሮ ተገዷል። የሚማሩ ልጆችም ተስፋ ቆርጠዉ በየሠፈራቸዉ ከተመረቁ 5 ዓመት እና በላይ የሆናቸዉን ከመቶ ሺህ በላይ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቁ ድግሪ ምሩቃን እና አሁንም ሥራ አጥ ሆነዉ በአከባቢው ምንም አይነት የስራ ዕድል የለም፦ ይህ ችግር ደግሞ የሚመነጨው የአከባቢውን ችግር ለመቅረፍ በመንግሥት አመራርነት የተመደቡ ግለሰቦች የራሳቸውን ጎሳና ዘመድ ብቻ ለመጥቀም እየሰሩ መሆኑ በፓርቲው ላይ እምነት እንዳንጥል እያደረገ ነው" ሲሉም አባላቱ ቅሬታ አቅርበዋል።

እንደ መረጃ ምንጮቻችን ገለፃ በኮንፈረንሱ ቀድሞው ለህዝቡም ለፓርቲውም እኩይ አላማውና ድርጊቱ ገሃድ የወጣበት የኔትወርክ ቡድኑ በተለይ የመንግስት ሰራተኛውንና ሌሎች አባላትን በአበልና በጥቅማጥቅም ዝም ለማሰኘት የተደረገ ሙከራ በርካታ ቦታዎች ላይ የከሸፈ ሲሆን አባላቱ በግልጽ ቋንቋ በዞኑ የህዝብ የልማትና የመልካም አሰተዳደር ጥያቄዎቹ በአበልጃዊና እና ጎሳዊ የስልጣን መረብ ተደፍቀው ምላሽ እንዳያገኙና ህብረተሰቡ በተጨባጭ በአይኑ እያየ ባለው አስናዋሪ ድርጊታቸው "በመንግስት ላይ እምነት ለመጣል እንኳን እየተቸገረ ነውና እውነትም የብልፅግና ፓርቲያችን ለህዝብ ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጥና የራሱ ፓርቲ ስም ጭምር የሚያጎድፍ እነዚህ ቡድኖች በዘረጉት የማይመጥን የግለሰቦች ኔትወርክ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ እርምት እርምጃ እንዲወስድ" የሚል ሀሳብም በሁሉም አከባቢዎች ያለልዩነት ማለት በሚቻል ደረጃ ተንፀባርቋል።

ይሁን እንጂ በአከባቢው ባልተለመደ ሁኔታ አባላት ጠንከር ያለ ትችትና ቅሬታ በተለይም የዎላይታ አመራር ምደባ ስርዓት ብልጽግና ፓርቲ ከሚከተለው ዕሳቤና አሰራር ውጭ ዞኑ ለተለያዩ ችግሮች ስለመጋለጡ ተጨባጭ ማብራሪያ በማሰማታቸው አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከኮንፈራንስ አዳራሽ በማውጣት ማሳር፣ ማስፈራሪያና ዛቻ ማድረግ እንዲሁም በአመራሮችና ፀጥታ አካላት ተገደው ይቅርታ ጠይቀው ከእንደገና ለተሰበሰቡ አባላት "ባለፉት ጊዜ በአካባቢያችን አስደማሚ ለውጥ ተመዝግቧል" ብለው እንዲያወሩ ስለመደረጉም ከተለያዩ ምንጮች የደረሰው መረጃ ያመለክታል

ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የተገዛ ስንዴ በግለሰብ ስም ውጪ ቢደረግም እስካሁን የገባበት እንደማይታወቅ ተገለፀ።አምና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ከሌላ ቦታ ዳቦ በማስመጣት ተመርቆ ለነበረው የዎ...
14/03/2024

ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የተገዛ ስንዴ በግለሰብ ስም ውጪ ቢደረግም እስካሁን የገባበት እንደማይታወቅ ተገለፀ።

አምና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ከሌላ ቦታ ዳቦ በማስመጣት ተመርቆ ለነበረው የዎላይታ ሶዶ ዱቀት ፋብሪካ "ስራ ለማስጀመርና ተጨማሪ አቅም ለመፍጠር" በሚል ከወራት በፊት ከዎላይታ ዞን አስተዳደር ቀጥታ ለስንዴ ግዢ ከሶስት ሚሊየን ብር በላይ ተመድበው በዎላይታ ገበሬዎች ዩኒየን በኩል ከተገዛ በኋላ በሶዶ ከተማ አንድ ፋይናንስ ባለሙያ አማካይነት ወጪ ሆኖ እንዲረከብ የተደረገ ቢሆንም ስንዴው የት እንደገባ አለመታወቁ ተነግሯል።

አንድ የዎላይታ ሶዶ ከተማ የኦዲት ባለሙያ ከዞኑ ገንዘብ ተመድቦ በዩኒየን በኩል የተገዛው ከ600 በላይ ኩንታል ስንዴ ከዩኒየኑ በሶዶ ከተማ ፋይናንስ ባለሙያ አቶ አየለ ማጣሎ በተባለ ግለሰብ ወጪ ተደርጎ ቢወጣም ወደ ፋብሪካው አለመግባቱን ማረጋገጣቸውን ተከትሎ የኦዲተሮች ቡድን በአሁኑ ሰዓት ሪፓርት ለማውጣት መቸገራቸውን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አስረድቷል።

ይህ ዳቦ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ሥራ ስጀምር በቀን 300,000 ዳቦ እና 420 ኩንታል ዱቄት የማምረት አቅም ያለው፥ በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ለ171 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርና ገበያን በማረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ተገልጾ እንደነበር ይታወቃል።

ይሁን እንጂ የፋብሪካው ሥራ አመራር ቦርድ ተደራጅቷል ቢባልም ሥራ ባለመጀመሩ፣ የአከባቢው አመራሮች በጥቅም ተሳስረው ከላይ የተገለፀ አይነት ስርቆት ውስጥ በመዘፈቁ፣ ለፋብሪካው በቂ የሥራ ማስኬጃ ካፒታል ባለመመደቡ፣ ለሥራው በቂ ክህሎትና ልምድ ያለው ሥራ አስኪያጅ በውድድር ባለመቀጠሩ፣ ለየሥራ ክፍሉ የሚያስፈልጉ በቂ ቴክኒካል ባለሙያዎች ባለመቀጠራቸው፣ ጥራት ያለው በቂ ስንዴ አቅርቦት ውስንነት፣ ፕሮጀክቱ ውጤታማ እንዲሆን ችግር ፈቺ የአመራር ሰጪነትና ድጋፍ ባለመኖሩ እንዲሁም ለሠራተኞችም ሆነ ግብዓትና ምርት ለማመላለስ በስጦታ የተሰጠ መኪና ለሌላ ዓላማ በመዋሉ የአከባቢው ማህበረሰብ ከፕሮጀክቱ መጠቀም አለመቻሉን ባደረግነው ማጣራት ለማረጋገጥ ተችሏል።

ፋብሪካው ግለሰቦች በሙስናና በብልሹ አሰራር ተወጥሮ ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠታቸው በአሁኑ ወቅት 15 (8.7% ብቻ) ሠራተኛ ብቻ ያለው ሲሆን በቀን በአንድ ፈረቃ ብቻ ከማምረት አቅሙ 1.7% ብቻ ዳቦዎችን እያመረተ ሲሆን በቂ ምርት ባለመኖሩ የተነሳ ለዳቦ መሸጫነት በከተማዋ ከተከፈቱ ሱቆች መካከል 90% የሚሆኑት ዝግ ናቸው። ይህ ፋብሪካ አሁን ባለው ሁኔታ ከቀጠለ አስተዳደራዊ ወጪዎችን እንኳን መሸፈን አቅቶት በቅርቡ ሊዘጋ እንደሚችልም ተጠቁሟል።
የዜናው ምንጭ Wolaita Times ሚዲያ ነው

"ጬላ ጭታፔነ አርባፔ ግዷን"....!የመንግስታዊ መዋቅር በግለሰባዊ አደራጃጀት መተካቱ በመረጃ ተረጋግጦ መጋለጡን ተከትሎ ውዝግቡ ቀጥሏል። የአፈና መዋቅር ስራውን ቀጥሏል። አርብ በዞኑ በሚጀ...
13/03/2024

"ጬላ ጭታፔነ አርባፔ ግዷን"....!

የመንግስታዊ መዋቅር በግለሰባዊ አደራጃጀት መተካቱ በመረጃ ተረጋግጦ መጋለጡን ተከትሎ ውዝግቡ ቀጥሏል። የአፈና መዋቅር ስራውን ቀጥሏል። አርብ በዞኑ በሚጀምረው የፓርቲው አባላት ስብሰባ ላይ ከአባል ሶሰት ሶስት ሰው ከዞን መዋቅር ለእያንዳንዱ 12,000 ብር እና ከከተማ መዋቅር 8,000 ብር ( ሶዶ፣ አረካ እና ቦዲቲ ) በየሴክተሩ ልየታ አድርገው ተጨማሪ ገንዘብ በመስጠት በቂ ኦሬንተሽን እንድያደርጉና በውይይት ዕለት ቀድመው እድል ወስደው ከአቶ ተስፋዬ ይገዙ ( ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ) ጀምሮ ያለ የዎላይታ አመራር ስራ ላይ እንዳለና ጠንካራ መሆናቸው ተገልጾ ከዚህ ቀደም በመድረክ የታገሉ የክልል አመራር ስልጣን ፈልገው የዞኑን ስም እንደሚያጠፉ እንድናገሩ ለሁሉም ካብኔ አባላት ተልዕኮ ተሰጥቷል።

የመዋቅር "በስብሷል" ስንል ያለምክንት አይደለም። ሌላው ማሳያ በሐሙሱ የክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ የፌደርሽን ምክር ቤት አዋጅ የሚፀድቀውን ተስፋዬ ይገዙ ይቃወማል ያንንም አቶ ተስፋዬ ለዎላይታ ህዝብ ጥቅም "እየታገለ ነው ብላችሁ ለሰራተኛው መረጃ ስጡ ሁሉም ይስማ" በማለት በትላንትናው ዕለት ውይይቱ ተጠናቋል።

ይሁን እንጅ በዎላይታ ዞን አይኔን ለአፈር ብል እንዴ ውሻ እነሱ የጣሉለትን ዳቦ በልቶ የህዝብን እውነት የምደፈጥጥ ሠራተኛ ይኖራል ተብሎ አይገመትም ግን ደግሞ በቤተሰብ፣ በዘመድ፣ በጥቅም የሚደለል ሰው ጊዜ ስደርስ የምናየው ሆኖ የዎላይታ ህዝብ ከለባ ጋር ጉዳይ የለውም። ሁሉም ሰው ይህን አሳፋሪ ስራቸውን ተገንዝቦ ለትግል ልዘጋጅ ይገባል።

የመንግስታዊ መዋቅር በግለሰባዊ አደራጃጀት በመተካቱ የዎላይታ አመራር ምደባ ስርዓት ከብልጽግና ዕሳቤ እና አሰራር መሪህ ውጭ የሆነው በአራት ዋና ዋና የኔትዎርክ ሰንሰለት እንደሆነ የተገለጸው ኔትወርክ፦ ማለትም👇

1ኛ. በአቤ-ልጅ ኔትወርክ፤
2ኛ. በአከባባዊነት ኔትወርክ፤
3ኛ. በትውውቅ እና በጥቅም ላይ የተመሰረተ፤
4ኛ. የቤተሰባዊ ኔትዎርክ ሲሆን የዎላይታ ህዝብ በዚህ በሌብነትና በጥቅም ትስስር በተደራጀው የኔትወርክ ቡድን የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ እጦት እንዲሁም በደል እየደረሰበት እንደሚገኝ በትናንትናው ዕለት በዝርዝር ስማቸውን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

ከገለልተኛ ህዝባዊ ለውጥ የተላለፈ መልዕክት

Address

S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Television posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wolaita Television:

Videos

Share

Category