Nuer nation zone press secretary

  • Home
  • Nuer nation zone press secretary

Nuer nation zone press secretary የኑዌር ብሔረሰብ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጵ/ቤት

በጋምቤላ ክልል የጎርፍ አደጋ ሥጋት ያለባቸው አካባቢዎች ከወዲሁ አደጋ እንዳይፈጠር ኅብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር አገልግሎት አስታወቀ።( ጋምቤላ ...
05/07/2022

በጋምቤላ ክልል የጎርፍ አደጋ ሥጋት ያለባቸው አካባቢዎች ከወዲሁ አደጋ እንዳይፈጠር ኅብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር አገልግሎት አስታወቀ።

( ጋምቤላ 28/10/2014 ) ሰሞኑን የባሮ ወንዝ ሞልቶ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ከ1 ሺህ 600 ሄክታር በላይ ሰብል ላይ ጉዳት መድረሱም ተመልክቷል።

በጋምቤላ ክልል የክረምት ወቅት ሲመጣ ሥጋት ከሚሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ የጎርፍ አደጋ መከሰት ነው።

በተለያዩ ጊዜያት በገጠራማ የክልሉ አካባቢዎች የሚጥለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የሚከሰት የጎርፍ አደጋ በሰዎችና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርስ ተስተውሏል።

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር አገልግሎት ኃላፊ አቶ ጋትቤል ሙን እንዳሉት በክልሉ በኑዌር ዞን የሚገኙ አምስት ወረዳዎችና በአኙዋ ዞን የጆር ወረዳ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ፣ በወንዞችና ተዳፋትማ አካባቢዎች የሚገኙ በመሆኑ የጥንቃቄ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል።

ለጎርፍ ስጋት ተጋላጭ ለሆነው ማህበረሰብ የቅድመ ጥንቃቄና በክልሉ በስፋት በሚነገሩ ቋንቋዎች አማካኝነት ወቅታዊ መረጃ ተደራሽ እየተደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

የጎርፍ አደጋ በላሬና በመኮይ ወረዳ በ1 ሺህ 650 ሄክታር በሰብል ማሣዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን ጠቁመው አርሶ አደሩ የጎርፍ መቀልበሻ ቦዮችንና ውኃን ከማሣ ውስጥ የመቀነስ ሥራዎችን ማጠናከር እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ሰብል የወደመባቸው አርሶ እና ከፊል አርብቶ አደሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚደርሱ የሰብል አይነቶችን እና የጓሮ አትክልቶችን ማልማት እንደሚጠበቅባቸውም አቶ ጋትቤል ተናግረዋል።

በክልሉ ለጎርፍ ተጋላጭ ተብለው ለተለዩ ቦታዎች መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ዕቅድ በማውጣት ወደ ተግባር መገባቱን የገለፁት አቶ ጋትቤል÷ህብረተሰቡም በክረምቱ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የተለየ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

እየጣለ ያለው የክረምት ዝናብ ጋምቤላን ጨምሮ በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲደረግ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ማስገንዘቡ ይታወሳል።
@የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን

14/11/2021

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nuer nation zone press secretary posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share