Wolaita Television Office /ወላይታ ቴሌቪዥን ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Sodo
  • Wolaita Television Office /ወላይታ ቴሌቪዥን ጽ/ቤት

Wolaita Television Office /ወላይታ ቴሌቪዥን ጽ/ቤት This is the official Wolaita Television page where you can get all the latest news.
(2)

This is the official Wolaita Television page - where you can get all the latest news in different language. You can follow us on:
https://t.me/wolaitatelevision

ቤተልሔም ወልዴ በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ሻምፒዮና ተጋጣሚዋን በበቃኝ አሸነፈች ወላይታ ሶዶ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ወቴቪ) በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ካፕ ሻምፒዮና ከደቡብ አፍሪካ አቻ...
18/04/2024

ቤተልሔም ወልዴ በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ሻምፒዮና ተጋጣሚዋን በበቃኝ አሸነፈች

ወላይታ ሶዶ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ወቴቪ) በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ካፕ ሻምፒዮና ከደቡብ አፍሪካ አቻዋ ጋር የተጋጠመችው ቤተልሄም ወልዴ በበቃኝ አሸንፋለች፡፡

የመላው አፍሪካ ሻምፒዮኗ ቤተልሄም ወልዴ በሁለተኛ ዙር ላይ ተጋጣሚዋ ላይ ሀይለኛ ቡጢ በማሳረፍ ነው በዳኛ ውሳኔ ያሸነፈችው፡፡

በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያን የወከሉት አቡዱሰላም አቡበከር፣ አቡበከር ሰፋን እና ኤርሚያስ መስፍን በተጋጣሚዎቻቸው መሸነፋቸውን ከኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Wolaytta moottan Sooddo yuushuwa allaanaa goshshaa xaafo keettby dere asaa namisaa hirggaappe la'a oottiya uuttaa beni b...
18/04/2024

Wolaytta moottan Sooddo yuushuwa allaanaa goshshaa xaafo keettby dere asaa namisaa hirggaappe la'a oottiya uuttaa beni ba sohuwawu zaaridi ehanawu minttidi oottiiddi de'iyogaa qonccissiis.

Wolaytta Soodeo; Gabbaa 10/2016(WTV)

Sooddo yuushuwa allaanaa goshshaa xaafo keettaa huuphe gadbayiya godattiyaw Ballaxxa Abarasha giidoogaadan uuttay wolaytta asay dumma dumma ogiyan giigissidi miyonne gita sohoy imettiyo katta qommo.

Itimaa, goodiya, golaanne hara mhyiyo kattati uuttaa muruta gidiyoga godattiya Abarasha haasayidosona.

Uuttay awaanne iraa geenna ubba carkkuwa hanotaarakka meezetiya katta qommo.

Uuttaa wolaytta asay kattadan manawunne gujuwanikka mehiyaassi miyiyobadankka go'ettees.

Ha cora go'ay de'iyo uuttay dere asaa darkkuwappe lee'i lee'i yiido gaasuwan gelida namisaappe dere asaa kessi ekkanawu tishshatettan oottiiddi de'ettees giidosona

Sooddo yuushuwa allaanan goshshaa eranchchatika erabninne hiillan goshshanchchata kabfidi uuttaa beni basohuwawu zaariyo oouwa oottiiddi de'ettees giidosona.

Sooddo yuushuwa allaanan gulgula shuchchaa goshshanchchatikka uuttay bantta darkkuwappe labllamin namisay gelidoo qonccissidi uutta beni ba sohuwawu zaaranawu minnidi oottiiddi de'ettees giidosona.
Jaagiso amaanu'eela
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በዚህ በጀት አመት 16 የገጠር መንገድ ድልድዮችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ለማብቃት እየተሰራ ነው።ወላይታ ሶዶ፤ሚያዚያ 10/ 2016(ወቴቪ)በጉራጌ ዞን ለአመታት ህ...
18/04/2024

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በዚህ በጀት አመት 16 የገጠር መንገድ ድልድዮችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ለማብቃት እየተሰራ ነው።
ወላይታ ሶዶ፤ሚያዚያ 10/ 2016(ወቴቪ)
በጉራጌ ዞን ለአመታት ህዝቡን ሲያስቸግሩ በነበሩ ወንዞች ላይ እየተገነቡ ያሉ ሶስት ድልድዮች ግንባታ በመገባደድ ላይ መሆኑን የክልሉ መንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተቋራጮች በግንባታ ሂደት ላይ ካሉ ድልድዮች ውስጥ 16 ቱን በዚህ በጀት አመት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ለማብቃት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ መንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል።

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ምስጋና ማቲዎስ እንደገለጹት በ2015 በጀት አመት በተለያዩ ዞኖች ተጀምረው በነበሩ የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ልዩ ትኩረት በማድረግ በዚህ በጀት አመት አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት በቅንጅት እየተሰራ እየተሰራ ይገኛል።

ድልድዮቹ በ13 ፓኬጆች ለተቋራጮች ተላልፈው ግንባታቸው እየተፋጠነ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ አካባቢዎቹ ከፍተኛ የተደራሽነት ችግር የነበረባቸው ናቸው ብለዋል።ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው ለአገልግሎት ሲበቁ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸው የጎላ እንደሚሆንም ተናግረዋል ።

ክልሉ ይህን ማህበረሰባዊ ፋይዳ መነሻ በማድረግ አብዛኛዎቹን ግንባታዎች ለማጠናቀቅ ግብ አስቀምጦ በልዩ ሁኔታ እየሰራ እንደሚገኝም አቶ ምስጋና አስታውቀዋል ። ለዚህ ድኬትም የተቋራጮቹን አቅምና የዝናብ ስርጭቱን ታሳቢ ያደረገ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚሁ መሰረትም በጉራጌ ዞን ቸሃና ኢነሞር ወረዳዎች ለአመታት ህዝቡን ሲያስቸግሩ በነበሩ ወንዞች ላይ እየተገነቡ ያሉ ሶስት የገጠር መንገድ ድልድዮች ግንባታ በመገባደድ ላይ ይገኛል። ከእነዚህ ድልድዮች ውስጥ አንዱና ዋነኛው የዊንቄ ወንዝ ድልድይ ሲሆን ሁለቱን ወረዳዎች በቀላሉ በማገናኘት የአካባቢውን ማህበረሰብ የዘመናት ችግር የሚቀርፍ ነው።

የአካባቢው አርሶ አደሮች እንደገለጹት በየአመቱ ክረምት ወቅት ወንዙ ላይ የሚፈጠረው ከፍተኛ ጎርፍ እስከ አሁን የ26 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።

በተለይ እናቶች ላይ ሲያሳድር የነበረው ዘርፈ ብዙ ጫና ከፍተኛ እንደነበር የገለጹት ነዋሪዎቹ የድልድዩ መገንባት እፎይታ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል ።

ወላጅ አባቱን በወንዙ ውሃ ሙላት ያጣው ወጣት እንደሚለው የአባቱ ሀዘን እንዳለ ሆኖ የድልድዩ ለስኬት መብቃት የራሱንም ሆነ የልጆቹን ዋነኛ ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚቀርፍ ነው።
የድልድይ ግንባታው ቶሎ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የአካባቢው ነዋሪዎች ጠይቀዋል።

የግንባታ ተቋራጮቹ በበኩላቸው ፕሮጀክቶችን በውሉ መሰረት አጠናቀው ለማስረከብ እየሰሩ መሆኑን ጠቁመው ከክፍያ ጋር ተይይዞ የሚታየው መዘግየት መቀረፍ እንዳለበት አስረድተዋል ። የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የገጠሙትን ፈተናዎች ተቋቁሞ እድገትን እያስመዘገበ ነው - አቶ አህመድ ሺዴወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 10/2016(ወቴቪ)፦ባለፉት ጥቂት ዓመታት የኢትዮጵያ ...
18/04/2024

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የገጠሙትን ፈተናዎች ተቋቁሞ እድገትን እያስመዘገበ ነው - አቶ አህመድ ሺዴ

ወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 10/2016(ወቴቪ)፦ባለፉት ጥቂት ዓመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ያጋጠሙትን የተለያዩ የውጭ እና የውስጥ ፈተናዎች ተቋቁሞ ዕድገት እያስመዘገበ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ገለጹ።

ዋሽንግተን ዲ.ሲ.የሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ኤምባሲ ከዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ-አሜሪካ ቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በዋሽንግተን ዲሲ ተካሒዷል።

ሚኒስትሩ በዚህ ጊዜ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተለያዩ የውጭ እና የውስጥ ፈተናዎች ቢገጥሟትም ኢኮኖሚው እነዚህን ተግዳሮቶች ተቋቁሞ አሁንም ዕድገት እያስመዘገበ ነው።

የዚህ ዋነኛ ምክንያት ደግሞ በመንግስት እየተተገበረ ያለው መጠነ ሰፊ የሪፎርም ስራና በመሰረተ ልማቶች ላይ በተከናወኑ ትልልቅ የኢንቨስትመንት ስራዎች መሆኑን ገልጸዋል።

የአየር ንብረት ለውጥን ከመቋቋም፣ በምግብ ራስን ከመቻል እንዲሁም ዘላቂ የግብርና ምርታማነትን ከማሳደግና ከተቀናጀ የውሃ ሃብት አስተዳደር ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን በዘላቂነት ከመፍታት አንጻር ትልቅ ድርሻ የሚይዘው የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛልም ብለዋል።

አሜሪካውያን ባለሀብቶች ኢትዮጵያን መጥተው እንዲጎበኙ እና ያሏትን ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲያዩ ግብዣቸውን አስተላልፈዋል።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ክቡር ዶክተር ስለሺ በቀለ በበኩላቸው አገራችን ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ያላት መሆኗን ገልጸዋል።

በተለያዩ ጊዜያት የከፍተኛ ባለስልጣናት የስራ ጉብኝቶች የተካሄዱ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ባለፈው ዓመት በዩ.ኤስ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ተሳትፎ ማድረጉን አንስተዋል።

በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሜሪካ አስተዳደር፣ ኮንግረስ፣ እና በግሉ ኤኮኖሚ ዘርፍ ከተሰማሩ አካላት ጋር ውጤታማ ውይይቶች ማድረጋቸውንም አስታውሰዋል።

በዚህ ፎረም ላይ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ ሀብት እና የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሁም ኢንቨስተሮች ሊያገኙ የሚችሉትን የተለያዩ ማበረታቻዎችን አስመልክቶ ሰፊ ገለጻ ቀርቧል።

በተጨማሪም በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ስኬታማ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና የተለያዩ አሜሪካውያን የስራ ሃላፊዎችን ያካተተ የፓናል ውይይትም ተካሂዷል።

ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ የተሰጠ መሆኑም በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

በፎረሙ የተሳተፉ አሜሪካውያን ባለሀብቶች መንግስት እያካሄደ ያለው ሪፎርም በተለይም የውጭ ኢንቨስተሮች መዋእለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የሚያደርገውን ጥረት ማድነቃቸው ተገልጿል። #ኢዜአ
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

ክልሉ በዘጠኝ ወራት የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገለፀወላይታ ሶዶ፤ ሚያዚያ 09/2016(ወቴቪ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በተለያዩ ...
17/04/2024

ክልሉ በዘጠኝ ወራት የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገለፀ

ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዚያ 09/2016(ወቴቪ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ዉጤታማ ተግባራትን እያከናወነ የመጣ መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን በመግለጫቸው ገልፀዋል።

የቢሮ ኃላፊዋ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሀሳብ አመንጪነት ''አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ'' በሚል ለ2017 ዓ.ም በክልሉ የሚገኙ የአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች መፅሐፍ ማግኘት እንዳለባቸው በሰፊው እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም የክልሉ መንግስት ለመነሻ እንዲሆን 300 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በማድረግ ያስጀመሩት ሲሆን ሁሉም የክልሉና የዞኖች የመንግስት አመራሮች የአንድ ወር ደመወዝ በመልቀቅ እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ የሀብት ማሰባሰቡ ሂደት በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንደሆነ ገልፀዋል።

ክልሉ ከህዝብ በተለያዩ ጊዜያት የተነሱ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ እየሰራ መሆኑን ገልፀው ለዚህም አይነተኛ መሳሪያ የሚሆነው ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ እንደሆነ አሳስበዋል።

ከዘንድሮ በጀት ዓመት 75% የሚሆነውን በጀት በውስጥ ገቢ መሸፈን አለብን ብሎ እንዲሁም የእድገትና ልማት ጥያቄዎቻችንን መመለስ ሚቻለው ከሁሉም ዘርፎች የሚሰበሰቡ የገቢ አማራጮችን አሟጦ ለመሰብሰብ ይረዳ ዘንድ ለንግዱ ማህበረሰብ በተለያዩ ጊዜያት የሂሳብ መዝገብ አያያዝና የደረሰኝ አጠቃቀም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ እየተሰጠ መምጣቱንም አውስተዋል።

በኢንቨስትመንት ክልሉ ባለ ብዙ አማራጮች ክልል ከመሆኑም አንፃር የኢንቨስትመንት ፈቃድ አዲስ ወስደው ወደ ስራ የገቡትንና ከዚህ ቀደም የወሰዱት ምን ደረጃ ላይ እንዳሉም የፌደራል ሱፐርቪዥን ቡድንም የመስክ ምልከታ በማድረግ ተስፋ ሰጪ ዉጤቶች እየተመዘገቡ እንደሆነም ግብረመልስ ሰጥተዋል።

የሜትሮዎሎጂ መረጃ እንደሚያመላክተው በክልሉ አብዛኛው ዞኖች ላይ ከባድ የጎርፍና የናዳ አደጋ በተለያዩ ወቅቶች ሊከሰቱ እንደሚችል አሳስበዋል ብለው በክልሉ ስጋት ባለባቸው አከባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍልም ልዩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በመግለጫቸው አሳስበዋል።

በመጨረሻም ክልሉ እንደ አዲስ ክልል ሳይሆን በዘጠኝ ወራት አፈፃፀም በዉጤታማነት እያከናወነ እንደሚገኝም ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን ገልፀዋል።
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

የከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም /UIIDP/ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከተጀመረ ወዲህ የተመዘገቡ ለዉጦችን ለማስቀጠል ያለመ መድረክ  እየተደረገ ይገኛል።ወላይታ ሶዶ: ሚያዚያ 09/201...
17/04/2024

የከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም /UIIDP/ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከተጀመረ ወዲህ የተመዘገቡ ለዉጦችን ለማስቀጠል ያለመ መድረክ እየተደረገ ይገኛል።

ወላይታ ሶዶ: ሚያዚያ 09/2016(ወቴቪ) በመድረኩ ከአለም ባንክ የምስራቅ አፊሪካ ተወካዮች፣የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች፣ የክልል ፣ የዞን እና የከተማ አመራሮች ተገኝተዋል።

በከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዋና ዋኬ በወላይታ ሶዶ ከተማ ላይ የዜጎች የልማት ፍላጐት እየተሟላ የመጣው መንግስት እና UIIDP በቅንጅት ከህብረተሰቡ ጋር በመስራታቸው መሆኑን ገልፀዋል።

በሚኒስቴር መስሪያቤቱ የመሰረተ ልማት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዋና ዋኬ የተቀመሩ ገንቢ ተሞክሮዎችን ማስፋፋት ይገባል ነው ያሉት።

በመድረኩ ማስጀመሪያ የወላይታ ሶዶ ከተማን በማልማትና የስራ እድል በመፍጠር የከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ UIIDP ፕሮግራም የማይተካ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ገልፀዋል።

በወላይታ ሶዶ ከተማ የተዘረጉ የልማት አውታሮች የህዝቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ፈተዋል ሲሉ አቶ ሳሙኤል ተናግረዋል።

የተከበሩ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ ጀገና አይዛ በፕሮግራም በመመራት የከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ UIIDPተወዳዳሪ እና ተመራጭ ከተማ ለመገንባት አስችሏል ብለዋል።

አቶ ጀገና አክለው የከተማውን የውስጥ ገቢ በማሳደግ ቀጣይነት ያለውን ልማት ለማረጋገጥ ከ UIIDP ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት ገልፀዋል።

በአሁኑ ሰአት ባለፉት 5 አመት አፈፃፀም የተከናወኑ የመንገድ ፣ የጎርፉ ማፋሰሻ ፣ የገበያ ማእከላት ፣ አረንጓዴ ስፍራዎች እና ሌሎም እንቅስቃሴዎች ላይ ምክክር እየተደረገ ሲሆን በቀጣይ የተሰሩ መሰረተ ልማቶች ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

በዱባይ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ መዝነቡን ተከትሎ በጎርፍ ተጥለቅልቃለችወላይታ ሶዶ፣ ሚያዝያ 8/8/2016(ወቴቪ)በበዱባይከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መጠን ነፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ መ...
17/04/2024

በዱባይ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ መዝነቡን ተከትሎ በጎርፍ ተጥለቅልቃለች

ወላይታ ሶዶ፣ ሚያዝያ 8/8/2016(ወቴቪ)በበዱባይከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መጠን ነፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ መዝነቡን ተከትሎ ከተማዋ በጎርፍ ተጥለቅልቃለች።

ጎርፉን ተከትሎ የዱባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያን ጨምሮ የከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች ከባድ ጎርፍ እያስተናገዱ መሆኑ ተገልጿል።

በተለይም ከዚህ ቀደም በርከታ በረራዎችን ሲያስተናግድ በነበረው የዱባይ አየር መንገድ በረራዎች ተስተጓጉለዋል።

ነፋስ የቀላቀለው ከባድ ዝናብ በኦማን ተከስቶ 18 ሰዎች ህይወታቸው ካለፈ በኋላ አሁን ደግሞ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና በባህሬን ጉዳት እያስከተለ እንደሚገኝ የአልጀዚራ ዘገባ ያመለክታል።
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁhttps://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509...
17/04/2024

አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

ዩኒቨርሲቲዉ ከአጋር ተቋማት ጋር በመተባበር ያስተከለዉን የፀሐይ ታዳሽ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት (Solar PV Project) ለነዋሴ 1ኛ እና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርክክብ አደረ...
17/04/2024

ዩኒቨርሲቲዉ ከአጋር ተቋማት ጋር በመተባበር ያስተከለዉን የፀሐይ ታዳሽ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት (Solar PV Project) ለነዋሴ 1ኛ እና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርክክብ አደረገ፡፡

ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዚያ 9/2016(ወቴቪ)
የተተከለዉ የፀሐይ ታዳሽ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 1000 ያክል ተማሪዎችንና መምህራንን ተጠቃሚ የሚያደርግ 9 ባለ 9 ኪሎ ዋት የመብራት ኃይል መሆኑ ተመላክቷል።

ዩኒቨርሲቲዉ ከኢፌዴሪ ውሃና ኢኔርጂ ሚኒስቴር፣ ከቻይናው ግብርና ዩኒቨርሲቲ እና ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ጋር በአጋርነት ያስተከለዉን የፀሐይ ታዳሽ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት (Solar PV Project) ለነዋሴ 1ኛ እና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርክክብ አደርጓል፡፡

የፀሐይ ታዳሽ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱ የቻይና መንግስት በደቡብ-ደቡብ ትብብር ማዕቀፍ በኢትዮጵያ የታዳሽ ሃይል ቴክኖሎጂ ሽግግረን በመደገፍ ለአየር ንብረት ለዉጥ የማይበገር እና ከአካባቢ ብክለት የፀዳ ኢኮኖሚን እንዲሁም ጤናማ ማህበረሠብን የመፍጠር ስትራቴጂ አካል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዘውድነህ ቶማስ እንደገለጹት በወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ነዋሴ 1ኛ እና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተተከለዉ የፀሐይ ታዳሽ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 1000 ያክል ተማሪዎችንና መምህራንን ተጠቃሚ የሚያደርግ 9 ባለ ኪሎ ዋት የመብራት ኃይል ፕሮጀክት ነዉ፡፡

በትምህርት ቤቱ ከተተከለው የፀሐይ ታዳሽ ኃይል የሚገኘዉ መብራት ለትምህርት ተደራሺነት እና ጥራት መረጋገጥ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው የገለጹት ዶ/ር ዘውድነህ ፕሮጀክቱ ከሀይል እጥረት ጋር ተያይዞ በትምህርት ቤቶች የሚስተዋሉትን የሳይንስና የኮምፒዉተር ቤቴ-ሙከራ ችግሮች ከመቅረፍ ረገድም ሰፊ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ አገራችን ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂ ሽግግርን በማጠናከር ለአየር ንብረት ለዉጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እና የመብራት ኃይል ባልተዳረሠባቸዉ ገጠራማ አካባቢዎች ታዳሽ ኃይልን ተደረሽ በማድረግ ማህበረሠባዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማፋጠን የያዘችዉን ዕቅድ ከማሳካት አንፃር ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዉ፤ፕሮጀክቱ የመብራት ኃይል ከማመንጨቱ በተጨማሪ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የቻይና ግብርና ዩኒቨርሲቲ ጥምር ምርምርና ኤክስቴንሺን ማዕከል (Joint Research and Extension Centre-JREC) ሆኖ እንደሚያገለግልም ዶ/ር ዘዉድነህ አብራርተዋል፡፡

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የፕሮጀክቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ በቅርበት ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርግም ኃላፊነት መዉሰዱ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል በዩኒቨርሲቲዉ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሥር የማህበረሠብ ጉዲኝት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ዳዊት ዳልጋ በነዋሴ ትምህርት ቤት የተተከለው የፀሐይ ታዳሽ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ትምህርት ቤቱን ጨምሮ በአካባቢው የሚገኙ 100 ያክል ቤተሰቦችን የመብራት ኃይል ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ዶ/ር ዳዊት አክለዉም የነዋሴ ትምህርት ቤት ተሞክሮን በገጠራማ አካባቢዎች ላሉ ሌሎች ትምህርት ቤቶችእና አገልግሎት መሥጫ ተቋማት (ለምሳሌ ጤና ጣቢያዎች) ተደራሽ ለማድረግ ከአጋር ቋማቱ ጋር የተጀመረዉን የትብብር ማዕቀፍ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ በውሃና ኤኔርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሱልጣን ወሊን ጨምሮ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እና የወላይታ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
# የዩኒቨርሲቲው ኮሚዩኒኬሽን ዳይረክቶሬት
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

ኢኮኖሚን በዘላቂነት ለማከም የባህር ዛፍን ከእርሻ ማሳ ላይ መንቀል እና በምትኩ የመሬት ለምነትን የማይጎዱ የፍራፍሬ ዛፎችና በሌሎች ሰብሎች መተካት ለነገ የማይባል ጉዳይ መሆኑን የሁምቦ ወረ...
17/04/2024

ኢኮኖሚን በዘላቂነት ለማከም የባህር ዛፍን ከእርሻ ማሳ ላይ መንቀል እና በምትኩ የመሬት ለምነትን የማይጎዱ የፍራፍሬ ዛፎችና በሌሎች ሰብሎች መተካት ለነገ የማይባል ጉዳይ መሆኑን የሁምቦ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ

ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዚያ 08/2016(ወቴቪ) በወላይታ ዞን በሁምቦ ወረዳ ያልተቋረጠ የባህር ዛፍ ነቀላ ከእርሻ ማሣ እና ከዉሃ ምንጮች ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ዘመቻው በንቅናቄ ከተጀመረበት ጀምሮ በእርሻ ማሳ አጠገብ የሚገኝ ባህረዛፍ በሰብል ምርት ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖን በሚመለከት የአርሶአደሩ ግንዛቤ እየተለወጠ እንደሆነ የገለፁት የሁምቦ ወረዳ ም/አስተዳዳሪ እና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተገኝ ታደመ፣ የአከባቢውን ኢኮኖሚን በዘላቂነት ለማከም የባህር ዛፍን ከእርሻ ማሳ ላይ መንቀል እና በምትኩ የመሬት ለምነትን የማይጎዱ የፍራፍሬ ዛፎችንና በሌሎች ሰብሎች መተካት ለነገ የማይባል ጉዳይ እንዳልሆነ አሳሰቡ።

አቶ ተገኝ ታደመ ይህንን ያሉት በዛሬው እለት በቦሳ ዋንቼ ቀበሌ ከአርሶ አደር እርሻ ማሳ አጠገብ የሚገኘውን እና በምርት እና ምርታማነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያደረሰውን ባህር ዛፍ በመንቀል በምትኩ በማሳው የሙዝ ተከላ በተካሄደበት ወቅት ነው።

በወረዳዉ የግብርናዉን ዘርፍ ለመደገፍ የባህር ዛፍን ከእርሻ ማሳ እና ዉሃ ምንጮች አቅራቢያ ለማንሳት ታስቦ የተጀመረዉ ሥራ በአርሶ አደሩ ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትንና ድጋፍ ያገኘ ተግባር ሆኗል።

በዚህም በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለ ከሳይንሳዊ እዉቅና በእርሻ መሃል እና ዉሃ ምንጮች ላይ ተተክለዉ ለምርትና ምርታማነት ጸር በመሆን አምራች አርሶ አደርን ለርሃብ እያጋለጠ ያለዉን ባህር ዛፍ ከእርሻ ማሳ የማስወገድ ሥራ ተያይዘዋል።

አንድ የባህር ዛፍ ብያንስ የማገር ደረጃ ለመድረስ የሚፈጀዊ ጊዜ፣ ከከርሰምድር የሚመጠዉ የዉሃ መጠን እና በሥሩ አማካኝነት የሚወስዳቸዉ ማዕድናት እጅግ በጣም ለእርሻ ማሳ አስጊነቱን የሚገልጡ ናቸዉ።

እንደ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ገለጻ በዘንድሮው ምርት ዘመን በወረዳው ከ43 ሄ/ር በላይ ባህር ዛፍን ከእርሻ ማሳ ለመንቀል ታቅደው ወደ ተግባር በመግባት በሁሉም ቀበሌያት በአጭር ጊዜ ውጤታማ ተግባር ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል።

በዛሬው እለት በቦሳ ዋንቼ ቀበሌ በንቅናቄው የተሳታፉ አርሶአደሮችም ለምርትና ምርታማነት እንዲሁም ለምንጭ ማጎልበት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድረውን ባህር ዛፍ ከእርሻ ማሳ ዘመቻውን ሳይጠብቁ ለመንቀል ተስማምተዋል።

በዘመቻው የሁምቦ ወረዳ ም/አስተዳደር እና ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተገኝ ታደመን ጨምሮ ለሎች የዘርፍ ኃላፊዎች፣ የወረዳ ደጋፊ አመራር አቶ ዘላለም ለማ እና ለሎች ባለድርሻ አካላትም ተሳትፈዋል። የወረዳው ኮሚዩኒኬሽን
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የቆንቶ  ፍራስቺስካዊያን  ሲስተሮች ገዳም አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረገ ።ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዚያ 8/2016(ወቴቪ)ወላይታ ሶዶ ከተማ ...
16/04/2024

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የቆንቶ ፍራስቺስካዊያን ሲስተሮች ገዳም አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረገ ።
ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዚያ 8/2016(ወቴቪ)

ወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኘው ፍራስቺስካዊያን ካቶሊክ ሚሽን ሲስተሮች ገዳም አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የከተማው ከንቲባ አቶ ጀገና አይዛ በተገኙበት ድጋፍ አደረገ።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ ጀገና አይዛ እንደተናገሩት ፍራስቺስካዊያን ካቶሊክ ሚሽን ሲስተሮች ገዳም አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላደረጉት ደጋፍ አመስግነው አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ አካላት ሌሎችም በከተማው ነሚገኙ መሰል ተቋማት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

ከንቲባው አክለውም የሶዶ ከተማ ካቶሊካዊት ቤተከርስቲያን በበርካታ በከተማችን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ የልማት ጉዳዮች ያላቸውን መልካም ተሳትፎ የሚያሰመሰገን መሆኑን ተናግረዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ አለምገና ፍቃዱ በበኩላቸው ከተቋሙ ጋር በመቀናጀት ተጋላጭ የሆኑትን አቅም የሌላቸው ወገኖች ቤት ለቤት ልየታ በማድረግ የበጎ ተግባሩ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን ተናግረዋል ።

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን መደገፍ ከሁሉም የሚጠበቅ በመሆኑ በበጎነት ለሌሎች መልካም ማድረግ እንደሚገባ ሃላፊዋ ጥሪ አቅርበዋል።

ወ/ሮ አለምገና አክለውም ፍራስቺስካዊያን ካቶሊክ ሚሽን ሲስተሮች ገዳም አቅም ለሌላቸው ወገኖች ላደረገው ደጋፍ እና መልካምነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የእመቤታችን ፍራቺስካዊያን ካቶሊክ ሚሽን ሲስተሮች ገዳም ኃላፊ ሲስተር ማሪያ አንጦኒዮስ ድሆችን መርዳት ከተረፈ ሳይሆን ካለን ማካፈልን የሚጠይቅ ጉዳይ በመሆኑ ሌሎች አጋሮችን በማስተባበር የእለት ደራሽ እርዳታ ለሚሹ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች የእህል ድጋፍ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም ዋጋቸውን ከፈጣሪ ለማግኘት ብለው ድጋፍ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።

አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ለማድረግ በተደረገው የጋራ ጥረት ከ200 በላይ ዜጎችን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ለማወቅ ተችሏል ።

# የወላይታ ሶዶ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት።
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንሰና ሕክምና ኮሌጅ ለነበረበት የኦዲት ግኝት አበረታች እርምት እያደረገ መሆኑ ተመላከተ ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዝያ 08/2016(ወቴቪ)  በሕዝብ ተወካዮች ምክር ...
16/04/2024

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንሰና ሕክምና ኮሌጅ ለነበረበት የኦዲት ግኝት አበረታች እርምት እያደረገ መሆኑ ተመላከተ
ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዝያ 08/2016(ወቴቪ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንሰና ሕክምና ኮሌጅ ለነበረበት የኦዲት ግኝት አበረታች እርምት እያደረገ መሆኑን በመስክ ምልከታ አረጋግጧል::

ቋሚ ኮሚቴው በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2013 በጀት ዓመት የሂሳብ ኦዲት ግኝትን መነሻ በማድረግ እያካሄደ ያለውን የመስክ ምልከታ እንደቀጠለ ነው።

በዛሬው ዕለት በቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሰቢና በቡድኑ አስተባባሪ የተከበሩ ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ የተመራው ቡድን በዩኒቨርሲቲው የጤና ሳይንሰና ሕክምና ኮሌጅ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የትምህርትና ሕክምና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ላይ ምልከታ አድርጓል።

ቀደም ሲል የኦዲት ግኝት የነበሩት የጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት ክፍያ እና የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው የህክምና ግብአቶች ሰፊ ምርመራ ተደርጎባቸዋል።

የተከበሩ ወ/ሮ አራሬ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው መድሀኒቶችን በማስወገድ እና ኮሌጁ የማይጠቀምባቸውን ንብረቶች ለሌሎች የህክምና ተቋማት እንዲሰጥ መደረጉ አበረታች እርምት መሆኑን ገልፀዋል።

ይሁንና የህክምና ግብአቶች አቀማመጥ ግን አሁንም ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው ተናግረዋል::

ለጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ የታየው የኦዲት ግኝትን በተመለከተ ችግሩ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ላይ ያለ መሆኑ የተከበሩ ወ/ሮ አራሬ አስረድተው፤ ለችግሩ እልባት ለመስጠት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል::

በምክትል ፕሬዘዳንት ማዕረግ የኮሌጁ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር ወኪል ወልዴ በበኩላቸው የ2013 በጀት ዓመት የሂሳብ ኦዲት ግኝቱን የፌዴራል ዋና ኦዲተር ባስቀመጠው የማሻሻያ ሀሳብ መሰረት እርምት የተደረገ መሆኑን ለቋሚ ኮሚቴው አስረድተዋል።

ይሁንና ለጤና ባለሙያዎች የተከፈለው የትርፍ ሰዓት ክፍያ ከጠቅላይ ሚንስቴር ቢሮ በተፃፈ ደብዳቤ መሰረት የተከናወነ መሆኑን ዶ/ር ወኪል ገልፀዋል::

በተመሳሳይ ዜና ሆስፒታሉ በርካታ ታካሚዎችን እንደሚያስተናግድና ከታካሚዎች ፍሰት አኳያ አገልግሎቱን ይበልጥ ለማሻሻል ብሎም ለማስፋፋት የበጀት ውስንነት ዋነኛው ተግዳሮት እንደሆነም ለቋሚ ኮሚቴው አባላት አስረድተዋል።

በቀጣዮቹ ቀናት የቋሚ ኮሚቴው አባላት በዩኒቨርሲቲው ስር በሚገኙ ሌሎች ኮሌጆች ላይ ተመሳሳይ ምልከታ ካደረጉ በኋላ አጠቃላይ ግብረ መልስ የሚያቀርቡ ይሆናል::

#የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

በወላይታ ዞን ከ6.9 ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኝ ለመትከል በቂ ዝግጅት መደረጉን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጸወላይታ ሶዶ፤ ሚያዝያ 8/2016 (ወቴቪ)በወላይታ ዞን ከ6.9 ሚሊዮን በላይ የቡና...
16/04/2024

በወላይታ ዞን ከ6.9 ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኝ ለመትከል በቂ ዝግጅት መደረጉን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጸ

ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዝያ 8/2016 (ወቴቪ)በወላይታ ዞን ከ6.9 ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኝ ለመትከል በቂ ዝግጅት መደረጉን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል።

የወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ዳዊት ተወዳዳሪና ጥራት ያለውን የወላይታ ቡናን ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ለዚህም የቡና ምርጥ ዘር ከሌሎች አከባቢዎች በማምጣት የማባዛት ስራ በመስራት ለቡና አብቃይ አርሶ-አደሮች እንደሚሰጥም ገልጸዋል።

ያለውን ችግኝ ያለ በቂ ቅድመ ዝግጅት መትከል ሳይሆን ቴክኖሎጂን በአግባቡ በመጠቀም፣ ከሶስት ወር ቀደም ብሎ ጉድጓድ እና ኮምፖስት የማዘጋጀት ስራ መስራቱንም ጠቅሰዋል።

ዘንድሮ በጀት ዓመት ከ6.9 ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኝ ለመትከል በቂ ዝግጅት መደረጉንም አስታውቀዋል።

ተከላው ውጤታማ እንዲሆን አንድ አርሶ-አደር ከ250 በላይ ችግኝ እንዲተከል በክላስተር መልኩ እንደሚከናወንም ገልጸዋል።

በሚያዝያ ወር የሚተከለው ችግኝ አርሶ-አደሩ ለመትከል ከወዲሁ ዝግጅት ማደረግ እንዳለበትም ጥሪ አቅርበዋል።

የወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ ቡናና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክፍሌ ታውሌ በቡና ልማት ዘርፍ ምርትና ምርታማነቱን ለማሳደግ በምርታማነቱ የሚታወቅ ምርጥ ቡና ዝሪያዎችን የማቅረብ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ዘንድሮ በጀት ዓመት ቡና ለመትከል ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ዝግጅት ተጀምሮ መሰራቱን በመገለጽ ምርጥ ዘሩን ከሌላ አከባቢ በማምጣት በሁሉም የቡና አብቃይ አከባቢዎች የማባዛት ስራ መሰራቱንም ገልጸዋል።

እንደ ዞን ከ6.9 ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኝ ለመትከል መዘጋጀቱን የተናገሩት አቶ ክፍሌ በዚህም በሚያዚያ ወር ብቻ ከ5.9 ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኝ እንደሚተከል አስታውቀዋል።

ለዚህም ከጥር ወር ጀምሮ በቂ የጉድጓድ ዝግጅት መደረጉንም በመጠቀም የኮንፖስት ዝግጅትም በዛው ልክ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል።

በዚህም ዓመት ከሌሎች ዓመት በተለየ ሁኔታ እንደ አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ልክ እንደሚከናወንም ጠቅሰዋል።

የሚያዝያ ወር የቡና ችግኝ ተከላ ለማካሄድ አስፈላጊውን ቅደመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቁን የገለጹት አቶ ክፍሌ ዞናዊ የቡና ችግኝ ተከላ ሚያዚያ 14 በሁሉም ቡና አብቃይ አከባቢዎች "ላውንችንግ" እንደሚደረግም አስታውቀዋል።
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

ቀይ መስቀል ለሕዝቦች በሕዝቦች ከሕዝቦች የሚል መርህ አንግቦ የሚሰራ ሰው ተኮር ማህበር ነው አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደወላይታ ሶዶ፤ ሚያዚያ 8/2016(...
16/04/2024

ቀይ መስቀል ለሕዝቦች በሕዝቦች ከሕዝቦች የሚል መርህ አንግቦ የሚሰራ ሰው ተኮር ማህበር ነው አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ

ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዚያ 8/2016(ወቴቪ)
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምስረታ ጠቅላላ ጉባኤ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በምሰረታ ፕሮግራሙ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን በሕዝቦች ፍቃድ መስርተን በርካታ የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ እየሰራን በሚንገኝበት በዚህ ወቅት በክልሉ የቀይ መስቀል ማህበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምስረታ ጉባኤ ማካሄዱ ለክልሉ መንግስት እና ህዝብ አስደሳች ዜና ነው ብለዋል።

ቀይ መስቀል "ለሕዝቦች ከሕዝቦች በሕዝቦች" የሚል መርህ ለአለም ሕዝብ የሚሰራ ሰው ተኮር ማህበር ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የሰው ልጆችን በቅንነት ለማገልገል ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው በሚል የደከመውንም፣ የተራበውንም፣ በሰው ሰራሽና ተፈጥሮ አደጋ፣ በጦርነት ለተጎዳው ለሁሉም የሰው ልጆች እኩል የሚያገለግል ማህበር መሆኑን ገልፀዋል።

የማህበሩ መመስረት ክልሉ መደጋገፍን መርህ አድርጎ ለሚሰራው ስራ አጋዥ እንደሆነ ጠቅሰው በአዲስ መልክ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቀይመስቀል ማህበር በመመስረቱ በክልሉ ህዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ማህበሩ ህዝብን በአግባቡ ማገልገል እንዲችል ጠንካራ አባላትን በማፍራት በተጠናከረ መንገድ ማደራጀት እንደሚገባም ገልፀዋል።

በምስረታ ፕሮግራሙ አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ፀሐይ ወረሳ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ቶላን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል።
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት ሁሉም አካላት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መውጣት አለበት፦ አቶ ተመስገን አለማየሁወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 8/2016(ወቴቪ) የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ "የማህበ...
16/04/2024

የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት ሁሉም አካላት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መውጣት አለበት፦ አቶ ተመስገን አለማየሁ

ወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 8/2016(ወቴቪ) የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ "የማህበረሰብ መሪነት ለላቀ የኤች አይቪ/ኤድስ መከላከል በሚል መሪ ቃል ዞናዊ ንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

ማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡት የወላይታ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ተመስገን አለማየሁ የኤች አይቪ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁሉም አካላት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መውጣት እንዳለበት አሳስበዋል።

በሽታውን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የጋራ አቋም መያዝ እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል።

የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር የበሽታውን ሰርጭት ለመታደግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በትኩት መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የኤች አይቪ/ኤድስ በሽታ ስርጭትን በመቆጣጠር ረገድ ያለውን መቀዛቀዝ ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ብርቱ ጥረት ሊያደርጉ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ከተደቀነው አደጋ ህዝባችንን የመከላከል ስራ ቀዳሚ አጀንዳችን ሊሆን ይገባልም ብለዋል።

የሚኒሚዲያ እና የተለያዩ ውይይት መድረኮች መጠናከር ያስፈልጋል ያሉት አቶ ተመስገን ዛሬ የተጀመረው ንቅናቄ ውጤታማ እንዲሆን ርብርብ መደረግ ይገባል ብለዋል።

የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ የኤች አይቪ ስርጭትን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነቱን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በሽታውን ለመከላከል የመከላከያ መንገዶችን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ፀጋዬ መከላከል ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

አሁን በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው መዘንጋቱ በሽታው እንዲባባስ አድርጓታል ያሉት አቶ ፀጋዬ ህብረተሰቡ የኤች አይቪ አስከፊነቱ በሚገባ በመረዳት እንዳለበትም አሳስበዋል።

የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ያለበትን ሁኔታ የተመለከተ ሪፖርት ይፋ እያደረገ ነው።ወላይታ ሶዶ፣ ሚያዝያ 8/2016(ወቴቪ)የኢትዮጵያ መገ...
16/04/2024

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ያለበትን ሁኔታ የተመለከተ ሪፖርት ይፋ እያደረገ ነው።

ወላይታ ሶዶ፣ ሚያዝያ 8/2016(ወቴቪ)የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በማህበራዊ ሚዲያ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ያለበትን ሁኔታ የተመለከተ ሀገራዊ ሪፖርት ለህዝብ ይፋ እያደረገ ይገኛል።

*በመገናኛ ብዙኃን ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ በ9192 ነፃ የስልክ መስመር ደውለው ማሳወቅዎን አይርሱ፡፡

ምንጭ ባለሥልጣን መስሪሩቤቱ
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

"ቀይ መስቀል ለሕዝቦች በሕዝቦች ከሕዝቦች የሚል መርህ አንግቦ የሚሰራ ሰው ተኮር ማህበር ነው"- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 08/2016 ዓ.ም(ወቴቪ) በኢትዮጵያ ቀይ...
16/04/2024

"ቀይ መስቀል ለሕዝቦች በሕዝቦች ከሕዝቦች የሚል መርህ አንግቦ የሚሰራ ሰው ተኮር ማህበር ነው"- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 08/2016 ዓ.ም(ወቴቪ) በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምስረታ ጠቅላላ ጉባኤ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በምሰረታ ፕሮግራሙ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን በሕዝቦች ፍቃድ መስርተን በርካታ የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ እየሰራን በሚንገኝበት በዚህ ወቅት በክልሉ የቀይ መስቀል ማህበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምስረታ ጉባኤ ማካሄዱ ለክልሉ መንግስት እና ህዝብ አስደሳች ዜና ነው ብለዋል።

ቀይ መስቀል "ለሕዝቦች ከሕዝቦች በሕዝቦች" የሚል መርህ ለአለም ሕዝብ የሚሰራ ሰው ተኮር ማህበር ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የሰው ልጆችን በቅንነት ለማገልገል ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው በሚል የደከመውንም፣ የተራበውንም፣ በሰው ሰራሽና ተፈጥሮ አደጋ፣ በጦርነት ለተጎዳው ለሁሉም የሰው ልጆች እኩል የሚያገለግል ማህበር መሆኑን ገልፀዋል።

የማህበሩ መመስረት ክልሉ መደጋገፍን መርህ አድርጎ ለሚሰራው ስራ አጋዥ እንደሆነ ጠቅሰው በአዲስ መልክ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቀይመስቀል ማህበር በመመስረቱ በክልሉ ህዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ማህበሩ ህዝብን በአግባቡ ማገልገል እንዲችል ጠንካራ አባላትን በማፍራት በተጠናከረ መንገድ ማደራጀት እንደሚገባም ገልፀዋል።

በምስረታ ፕሮግራሙ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ቶላን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች መገተቸዉን በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላከታል።
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎችን ከፍላጎታቸው ጋር በማጣመር አዳዲስ ፈጠራ እየሰሩ ያሉትን በእውቀት መደገፍ እንደሚገባ የወላይታ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ምህረ...
16/04/2024

ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎችን ከፍላጎታቸው ጋር በማጣመር አዳዲስ ፈጠራ እየሰሩ ያሉትን በእውቀት መደገፍ እንደሚገባ የወላይታ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ምህረቱ ሳሙኤል ገለፁ።

ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዚያ 8/2016(ወቴቪ)
መምሪያው ባዘጋጀው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስልጠና ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎች በዘርፉ የተሰማሩትን በእውቀት ለመደገፍ ስልጠናው ሁነኛ ሚና አለው ብለዋል።

እያንዳንዱ ሴክተር መስሪያ ቤት አገልግሎትን ዲጂታል በሆነ መንገድ ቀልጣፋ ግልጋሎት መስጠት ይገባል ተብሏል።

የወላይታ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ከወረዳና ከከተማ መዋቅሮች የመጡ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ዘርፍ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ሳይንሳዊ ማህበረሰብን ለመፍጠር የሚያግዘው ቴክኖሎጂ ስራ ላይ ወጣቶች በመሳተፍ ግዚያቸውን አሉባሌ ቦታ ከሚያጠፉት ይልቅ አዳድስ ሀሳብን በማመንጨት ለለውጥ መትጋት ያስፈልጋልም ተብሏል።
በሰናይት አብርሃም
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ በመጀመሪያ ዙር ያስለጠናቸው 1 ሺህ 35 እጩ የፖሊስ መኮንኖች የምረቃ መርሃ ግብር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በወላይታ ሶዶ ከተማ ...
16/04/2024

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ በመጀመሪያ ዙር ያስለጠናቸው 1 ሺህ 35 እጩ የፖሊስ መኮንኖች የምረቃ መርሃ ግብር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

እስራኤል በኢራን ላይ በምትወስደው የአጻፋ እርምጃ እጇን እንደማታስገባ አሜሪካ አስታወቀች ወላይታ ሶዶ፣ ሚያዝያ 8/2016(ወቴቪ)ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ...
16/04/2024

እስራኤል በኢራን ላይ በምትወስደው የአጻፋ እርምጃ እጇን እንደማታስገባ አሜሪካ አስታወቀች

ወላይታ ሶዶ፣ ሚያዝያ 8/2016(ወቴቪ)ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በስልክ በተወያዩበት ወቅት እስራኤል በኢራን ላይ በምትወስደው የአጻፋ እርምጃ እጇን እንደማታስገባ መግለጻቸው ነው የተነገረው።

ለዚህም እስራኤል ለምትወስደው የአጻፋ እርምጃ ጥንቃቄ ልታደርግ እንደሚገባ ማሳሰባቸው ተገልጿል።

ከዚያ ውጭ ባላው ወታደራዊ ድጋፍ ግን እስራኤል የአሜሪካ ድጋፍ እንደማይለያት ተገልጿል።

ኢራን በበኩሏ አሜሪካም የእስራኤልን መልሶ ማጥቃት የምታግዝ ከሆነ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ወታደራዊ ጣቢያዎቿ ላይ ጥቃት እንደሚትፈጽም ማሳሰቧን የሮይተርሰ ዘገባ ያመለክታል።
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

የፌደራል ከፍተኛ ልዑክ በክልሉ ያካሄደውን የክህሎት መር ሥራ ዕድል ፈጠራ ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን አጠናቆ ግብረመልስ ሰጥቷልወላይዩያ ሶዶ፣ ሚያዝያ 7/2016(ወቴቪ)በኢፌዴሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴ...
16/04/2024

የፌደራል ከፍተኛ ልዑክ በክልሉ ያካሄደውን የክህሎት መር ሥራ ዕድል ፈጠራ ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን አጠናቆ ግብረመልስ ሰጥቷል

ወላይዩያ ሶዶ፣ ሚያዝያ 7/2016(ወቴቪ)በኢፌዴሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ልዑክ በክልሉ ባካሄደው ድጋፋዊ የመስክ ምልከታና ክትትል ዙሪያ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት አጠቃላይ ግብረ መልስ ሰጥቶ ውይይት ተደርጎበታል።

ቡድኑ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በክልሉ በኣሪ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ፣ ወላይታ እና ጌዴኦ ዞኖች በመዘዋወር በክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራትና ተቋም ግንባታ ዙሪያ ድጋፋዊ የመስክ ምልከታ ሲያካሂድ ቆይቷል።

ቡድኑ በመስክ ቆይታው ከክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመቀናጀት በኢንዱስትሪ ዘርፍ፣ በመካከለኛ፣ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ ማህበራት እንቅስቃሴን ተመልክቷል፡፡

ድጋፍዊው የመስክ ምልከታና ክትትሉ በተለይ በክልሉ የተቋም ግንባታ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የክህሎት ሥራ መር ግንዛቤ፣ በኢንዱስትሪ የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት እና በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ስልጠና ያለበት ሁኔታ ለይቶ መደገፍ ላይ ትኩረት ያደረገ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስትዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ የክልሉ መንግስት ለክህሎት መር ሥራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ መሆኑን ገልጸው በተለይ በክልሉ የቀሪ 100 ቀናት ዕቅድ ውስጥ በማካተት በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማብራሪያቸው በቀሪ ጊዜያት ክልሉ የስራ ባህልን በማሳደግና ያሉ ፀጋዎችን አሟጦ በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ አቅምን በማጎልበት የስራ እድል ፈጠራ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የክልሉ መንግስት በክልሉ የስራ አጥ ቁጥርን በመቀነስ የተረጋጋ ፖለቲካና ማህበረሰብ እንዲኖር የማስቻል ስራዎች ላይ በልዩ ትኩረት ርብርብ የሚያደርግ መሆኑንም ገልጸዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ቡድኑ በክልሉ ለነበረው የድጋፋዊ ክትትል ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

የክልሉ መ/ኮ
አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ

https://www.facebook.com/Wolaita-Television-Office-ወላይታ-ቴሌቪዥን-ጽቤት-100509191530481/

የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UC1BT_6xDzGufgELD-TUznmw

ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/wolaitatelevision

ትኩስና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የቲውተር አካውንታችንን ይከተሉ

https://twitter.com/WolaitaTV?s=09

ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

Address

S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Television Office /ወላይታ ቴሌቪዥን ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wolaita Television Office /ወላይታ ቴሌቪዥን ጽ/ቤት:

Videos

Share