የወላይታ ዜና

የወላይታ ዜና News

የወላይታ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን በማካሄድ ላይ ይገኛል በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ዉይይት ይደረጋል ፣ በዉይይቱ ዙሪያ የሚነሱ ነጥቦችን ወደ እናንተ የሚናደርስ ይሆናል ።
29/03/2024

የወላይታ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን በማካሄድ ላይ ይገኛል

በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ዉይይት ይደረጋል ፣ በዉይይቱ ዙሪያ የሚነሱ ነጥቦችን ወደ እናንተ የሚናደርስ ይሆናል ።

ባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል ስርቆት ስፈፅም እጅ ከፍንጅ የተያዘ ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የአረካ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ።በወላይታ ዞን በአረካ ከተማ ባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል ስርቆት ...
27/03/2024

ባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል ስርቆት ስፈፅም እጅ ከፍንጅ የተያዘ ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የአረካ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ።

በወላይታ ዞን በአረካ ከተማ ባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል ስርቆት የፈፀመ ግለሰብ በ4 ዓመት እስራት መቀጣቱን የአረካ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የከተማው ፓሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር እንደ ወንድሙ ወልዴ ገለፃ ግለሰቡ አቶ አስገኘው አበበ ዕድሜ 19 ነዋሪነቱ የአረካ ከተማ መሀል ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን አፓች ሞተር ስሰርቅ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ እጅከፍንጅ ተይዞ በህግ ቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉንም ገልፀዋል፡፡

ግለሰቡ በህግ ጥላ ስር ከዋለ በኃላ በቂ ምሪመራ ተደርገው መጋቢት 17/2016 ዓ/ም በአረካ መጀመርያ ደረጃ ፍ/ቤት በዋለው ችሎት 4 ዓመት የእስራት ቅጣት እንደተወሰነበት ተገልፀዋል።

አያይዘው መስል ወንጀለ የሚፈፅሙ አካላትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የከተማው ፓሊስ አዛዥ አብራርተዋል።

ህብረተሰቡ የፖሊስ ቀኝ እጅ በመሆኑ ማንኛውንም አጠራጣሪ ጉዳዮችን ባአገኘ ወቅት ለፖሊስ ጥቆማዎችን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ :- የአረካ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ነው፡፡

ልብ ሰባሪ ዜናየሀዘን ዜና ! የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ስፍራ ተጨዋቹ አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል። በቅርቡ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በቤተክርስቲያን ስርዓት የፈፀመው...
27/03/2024

ልብ ሰባሪ ዜና

የሀዘን ዜና !

የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ስፍራ ተጨዋቹ አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

በቅርቡ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በቤተክርስቲያን ስርዓት የፈፀመው ተጫዋቹ ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቹ አርባምንጭ በሄደበት ድንገት ዛሬ ለሊት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል ።

ለአርባምንጭ ከነማ ታዳጊ ቡድን፤ ለሀዋሳ ከተማና አሁን ለባህርዳር ከነማ በሊጉ የሚጫወተው አለልኝ አዘነ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ተደርጎለት ማገልገል ችሏል ።

የወላይታ ዜና ድረገፅ በአለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።

የወላይታ ዞን ካቢኔ አባላት በ2016 በጀት ዓመት እስካሁን የተከናወኑ ተግባር አፈጻጸምን እየገመገመ ይገኛልየወላይታ ዞን የፕላንና ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ኃይሌ ስላስ በጀት ዓመቱ የእስካሁ...
16/03/2024

የወላይታ ዞን ካቢኔ አባላት በ2016 በጀት ዓመት እስካሁን የተከናወኑ ተግባር አፈጻጸምን እየገመገመ ይገኛል

የወላይታ ዞን የፕላንና ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ኃይሌ ስላስ በጀት ዓመቱ የእስካሁን የተከናወኑ የአስፈጻሚ ሴክተር መሥሪያቤቶች ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እያቀረቡ ናቸው።
በመድረኩ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ እና የዞኑ አጠቃላይ የካቢኔ አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ወላይታ በሁሉም መስኮች ለኢትዮጵያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተች ያለች መሆኗን የሚያሳይ ይመስለኛል ።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ብድን አሰልጣኝ ጥሪ ካደረገላቸዉ 26 ተጫዋቾች 4ቱ የወላይታ ፍሬ ና...
20/02/2024

ወላይታ በሁሉም መስኮች ለኢትዮጵያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተች ያለች መሆኗን የሚያሳይ ይመስለኛል ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ብድን አሰልጣኝ ጥሪ ካደረገላቸዉ 26 ተጫዋቾች 4ቱ የወላይታ ፍሬ ናቸዉ።

በሁሉም መስኮች ተባብረን ከሰራን ከወላይታ አልፈን ለኢትዮጵያ የሚበቃ እምቅ ሀይል ያላት "ወላይታ "።

ወላይታ ደምቃለችየጊፋታ አደባባይ በአሁኑ ሰዓት ይህንን ይመስላል ።               ዎላይታ ዎርቃ ማይዛና!
16/02/2024

ወላይታ ደምቃለች

የጊፋታ አደባባይ በአሁኑ ሰዓት ይህንን ይመስላል ።

ዎላይታ ዎርቃ ማይዛና!

ወላይታ ዲቻ ድል ቀንቶታል ጨዋታው ተጠናቋል በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ስታዲየም በተካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ጨዋታ ወላይታ_ዲቻ 1--0 ሀምበርቾ_ዱራሜ ውጤት...
01/02/2024

ወላይታ ዲቻ ድል ቀንቶታል

ጨዋታው ተጠናቋል

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ስታዲየም በተካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ጨዋታ ወላይታ_ዲቻ 1--0 ሀምበርቾ_ዱራሜ ውጤት በማምጣት ጨዋታው በስከት ተጠናቋል።

ድልና ድምቀት _ለታላቁ_ጦና ክለባችን_ለሆነው ለወላይታ_ዲቻ🐝🐝

ጥር 23/2016 ዓ/ም

በቦሎሶ ሶሬ የማይመጥን ወሬ የሚያሰራጩ እና ትችት ሱስ የሆነባቸው ግለሰቦችን ሊናስጠናቅቃቸው እንፈልጋለን! እስከዛሬ ለህዝባችን ጠብ ያለ ስራ መስራት ያልቻሉ የማህበራዊ ሚዲያ አንበሶች በሰሞ...
30/01/2024

በቦሎሶ ሶሬ የማይመጥን ወሬ የሚያሰራጩ እና ትችት ሱስ የሆነባቸው ግለሰቦችን ሊናስጠናቅቃቸው እንፈልጋለን!

እስከዛሬ ለህዝባችን ጠብ ያለ ስራ መስራት ያልቻሉ የማህበራዊ ሚዲያ አንበሶች በሰሞኑ ወረዳችን ለምን ተሸለመ በማለት የሰይጣን ተልዕኮ የሚመስል አጀንዳ የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት እየጣሩ ይገኛሉ።

እነዛ ደካሞች old fashion/ ጊዜ ያለፈበትን ፤ተራና ውጤት አልባ የሆነ ድርጊት ተሰማርቶ በተለያዩ ስራ ዘርፎች (gradual change) ለማምጣት መሠረት የሆኑ አመራሮችን ለመንካት ሲሞክሩ ሊያመን ይገባል።

የዚህ እርካሽ ተግባር ባለቤት የሆኑ አካላት በግልጽ የሚታወቁና በቅርቡ ወደ መቀመቅ እንደሚወርዱ ልገልፅላችሁ እፈልጋለሁ።

ከሽልማቱ የራቀው ወረዳ በሰድስት ወር ወስጥ 2 ዋንጫ ሲያመጣ የሚያማቸው አካላት የሰይጣን ተልዕኮ የሚፈጽሙ ከመሆን ባለፈ የጭንቅላት የሚመሩ አይደሉም።

በተለያዩ መንገድ ህዝብን ስያሸብሩ የቆዩ ባንዳዎችና የግል ጥቅማቸውን ብቻ የሚያሳድዱ ቀለብተኞች በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ህዝብን በቅንነትና በታማኝነት እያገለገሉ ያሉ አመራሮቾን ለማሸማቀቅ መሞከር ምነኛ ያማል!

ለማንኛውም እየተደረገ ያለው ድርጊት ማንበብና መጻፍ የሚችል ማንኛውንም አካል መሸወድ የማይችል እጅግ ተራ ድርጊት ነው።

# የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ የሆኑ አካላት በሙሉ እንዲህ አይነት ተንኮል ከዚህ በፊትም የተለመደ ተራ ነገር ስለሆነ ለጉዳዩ ምንም አይነት ቦታ እንዳትሰጡ ላሳስባችሁ እፈልጋለሁ!! በተጨማሪም like, share እና comment በማድረግ ለሌላው እንዲታደርሱ አሳስበዋል።

👉 የዛሬው መልዕክቴ ነው!

ወላይታ የከፍታዋ ዘመን መቷል ...የአባቶቻችን ፀሎት ተሰምቶ ወላይታ በኢኮኖሚ የሚትበለፅግበት ፣ አባቶች እና እናቶች ለሰላሟና ለእድገቷ ያለቀሱበት ለቅሶው ፍሬ አሀዱ ብሎ ማፍራት ጀምሯል ።...
23/11/2023

ወላይታ የከፍታዋ ዘመን መቷል ...

የአባቶቻችን ፀሎት ተሰምቶ ወላይታ በኢኮኖሚ የሚትበለፅግበት ፣ አባቶች እና እናቶች ለሰላሟና ለእድገቷ ያለቀሱበት ለቅሶው ፍሬ አሀዱ ብሎ ማፍራት ጀምሯል ።

ወላይታ ሶዶ የደቡብ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ

ሌላ ቦታ እንዳይመስላችሁ በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ በዘመናዊ መስኖ የለማ ማሳ ነዉ።በርካታ የፍራፍሬ ምርቶችን እያስገኝ የሚገኝ የመስኖ ማሳ ሲሆን ፣ ለሌሎች ወረዳዎች ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ...
14/11/2023

ሌላ ቦታ እንዳይመስላችሁ በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ በዘመናዊ መስኖ የለማ ማሳ ነዉ።

በርካታ የፍራፍሬ ምርቶችን እያስገኝ የሚገኝ የመስኖ ማሳ ሲሆን ፣ ለሌሎች ወረዳዎች ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ሆኗል ። ከፍተኛ ገቢ ከማስገኘቱ በተጨማሪ በአጭር ጊዜ ምርታማነትን በመስጠት ላይ የሚገኝ የግብርና ዉጤት ነዉ።

ዎላይታ ዎርቃ ማይዛና!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ወደ ወላይታ ሶዶ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው ።
14/11/2023

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ወደ ወላይታ ሶዶ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው ።

ሰበር ዜናየሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደር...
03/11/2023

ሰበር ዜና

የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል።

ከላይ በተራ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የRemedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡

☑ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 255 ያመጡ

☑ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 234 ያመጡ

☑ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 218 ያመጡ

☑ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 200 ያመጡ

☑ ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 224 ያመጡ

☑ ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 210 ያመጡ

☑ ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 192 ያመጡ

☑ ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 180 ያመጡ

☑ አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 210 ያመጡ

☑ አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ700 ነጥብ 210 ያመጡ

☑ አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 180 ያመጡ

☑ አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ600 ነጥብ 180 ያመጡ

☑ ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ከ500 ነጥብ 150 ያመጡ

☑ ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ከ500 ነጥብ 150 ያመጡ መሆን አለባቸው ተብሏል።

መረጃው የኤፍቢሲ / የትምህርት ሚኒስቴር ነው።

ጥንቃቄ ለወላይታ ህዝብሴት በመምሰል በአታላይነት ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ፡፡ወላይታ ሶዶ፣ጥቅምት 12/2016 ዓ.ም በወላይታ ዞን በአረካ ከተማ በአንድ በሆቴል ውስጥ ሴት በ...
23/10/2023

ጥንቃቄ ለወላይታ ህዝብ

ሴት በመምሰል በአታላይነት ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ፡፡

ወላይታ ሶዶ፣ጥቅምት 12/2016 ዓ.ም በወላይታ ዞን በአረካ ከተማ በአንድ በሆቴል ውስጥ ሴት በመምሰል በአታላይነት ወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በአንድ ዓመት እስራት መቀጣቱን የአረካ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።

የከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ረ/ኢ/ር እንደ ወንድሙ ወልዴ ገለጻ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው ነሐሰ 7/2015 ዓ/ም ዕለተ ቅዳሜ ከለሊቱ 6፡00 ሰዓት በአንድ ሆቴል ውስጥ ጾታውን ሴት በማስመሰል ሰወችን ስያጨበረብር የነበረው ግለሰብ በህብረተሰብ ጥቆማ መያዝ መቻሉን ተናግረዋል።

ግለሰቡ ስም አቶ ታመኔ ማርቆስ ተሾሜ የተባለ ሲሆን ነዋሪነቱ ካንባታ ዞን ሽንሽቾ ዕደሜው 22 መሆኑን ገልፀዋል።

ግለሰቡ የማታለል ወንጀሉን ከፈፀመ በኋላ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ ሲደረግበት ቆይቶ ጥቅምት 7/2016 በዋለው ችሎት ግለሰቡ በፈፀመው በአታላይነት ወንጀል የአንደ ዓመት እስራት ውሳኔ ተላልፎበታል።

ህብረተሰቡም እንድ ዓይነት እኩይ ተግባር ላይ የሚሳተፉ አካላትን መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ረ/ኢ/ር ወንድሙ ወልዴ ጥሪ አቀርበዋል።

በወላይታ እና አከባቢው ለሚትገኙ መልካም ዜና*ለተሻለ ፀጉር እድገት  @ሮዝመሪ ቅባት ይጠቀሙ 👌የምትፈልጉ inbox me or call as 0945011474
10/10/2023

በወላይታ እና አከባቢው ለሚትገኙ መልካም ዜና

*ለተሻለ ፀጉር እድገት
@ሮዝመሪ ቅባት ይጠቀሙ 👌
የምትፈልጉ inbox me or call as 0945011474

ወላይታዎች በኢሬቻየኦሮሞ ወንድሞች እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !
07/10/2023

ወላይታዎች በኢሬቻ
የኦሮሞ ወንድሞች እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

Woze Wozeወላይታ ዲቻ በድል ጀምሯል      ወላይታ ዲቻ 1፡0 ሻሸመኔ ከነማ
06/10/2023

Woze Woze
ወላይታ ዲቻ በድል ጀምሯል
ወላይታ ዲቻ 1፡0 ሻሸመኔ ከነማ

ጉሊያላይታፔ ላይታ ሳሩዋን ጋቶ!
24/09/2023

ጉሊያ

ላይታፔ ላይታ ሳሩዋን ጋቶ!

ዴንዶይ ያና ኑ ቢታዉማንትያራ           መልካም አዲስ ዓመት!
24/09/2023

ዴንዶይ ያና ኑ ቢታዉ
ማንትያራ

መልካም አዲስ ዓመት!

ዎላይቶ ሃሹ ጋቴስየኢትዮጵያ ድምቀትና ዉበት ወላይታ!
24/09/2023

ዎላይቶ ሃሹ ጋቴስ

የኢትዮጵያ ድምቀትና ዉበት ወላይታ!

Yo Yo Gifata!Hashu Gatesi Ubakka!
24/09/2023

Yo Yo Gifata!
Hashu Gatesi Ubakka!

ዮዮ ጊፋታ!
20/09/2023

ዮዮ ጊፋታ!

የሲቢኢ ብር መተግበሪያ በወላይትኛ ቋንቋ  አገልግሎት መስጠት ጀምሯል!                          መልካም አዲስ ዓመት!
13/09/2023

የሲቢኢ ብር መተግበሪያ በወላይትኛ ቋንቋ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል!

መልካም አዲስ ዓመት!

ዜና ሹመት!የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳር ለዞን ማዕከል አመራር አካላት በሽግሽግና በአዲስ መልክ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጠ። በዚህም መሠረት1. ወ/ሮ መስከረም አካለወልድ የወላይታ ዞን ምክር ቤ...
11/09/2023

ዜና ሹመት!
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳር ለዞን ማዕከል አመራር አካላት በሽግሽግና በአዲስ መልክ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጠ።

በዚህም መሠረት

1. ወ/ሮ መስከረም አካለወልድ የወላይታ ዞን ምክር ቤት ም/አፈ-ጉባኤ፣
2. አቶ ጎበዜ ጎኣ የዞኑ ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢ/ል/መምሪያ ኃላፊ፣
3. አቶ ማንደፍሮ ግርማ የዞኑ ቴክኒክ ሙያና ትምህርት ስልጠና መምሪያ ኃላፊ፣
4. አቶ ኃይሌ ስላስ የዞኑ ፕላን ኮሚሽን መምሪያ ኃላፊ
5. አቶ መሪሁን መና የዞኑ ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ
6. አቶ ጳውሎስ ጩምኣ የዞኑ ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ
7. ዶ/ር መሠረት በቀለ የዞኑ ውሃ መስኖና ማዕድንና ልማት መምሪያ ኃላፊ
8. አቶ ዘውዱ ሣሙኤል የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ
9. ዶ/ር ማርቆስ ጩምቡሮ የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ
10. ወ/ሮ ጤናዬ ትራንጎ የዞኑ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ
11. አቶ ወንድማገኝ አበራ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ
12. ወ/ሪት ድርሻዬ በለጠ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ
13. አቶ ታደለ ሜጋ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ
14. አቶ ምህረቱ ሳሙኤል የዞኑ ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ
15. አቶ ፀጋዬ ኤካ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ

16. አቶ ጌታቸው ገቡ የዞኑ ህ/ስራ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ
17. አቶ ዳዊት ደሣለኝ የዞኑ ግብርና መምሪያ ም/ኃላፊና የአደጋ ስጋትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ
18. አቶ ሲሳይ ሳሙኤል የዞኑ ግብርና መምሪያ ም/ኃላፊና እርሻ ዘርፍ ኃላፊ
19. አቶ ደሣለኝ በቀለ የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ም/ኃላፊና የትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊ
20. አቶ ጴጥሮስ ወ/ማሪያም የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ም/ኃላፊና ዩራፕ ዘርፍ ኃላፊ
21. አቶ አለማየሁ ገልዳ የዞኑ ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ም/ኃላፊና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ኃላፊ
22. ወ/ሮ ብሩክ ባልቻ የዞኑ ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ም/ኃላፊና ከተማ ሥ/ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ
23. አቶ ደስታ ዳና የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ም/ኃላፊና የማስፈጸም ዘርፍ ኃላፊ
24. ወ/ሪት ብሩክ ጰጥሮስ የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ም/ኃላፊና ቤቶች ዘርፍ ኃላፊ
25. አቶ ንጉሴ መንግሥቱ የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ም/ኃላፊና ስፖርት ዘርፍ ኃላፊ
26. ወ/ሪት ዝናቧ በየነ የዞኑ ብልጽግና ፓር ኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ም/ኃላፊ
27. አቶ አሸናፊ ዓለሙ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ም/ኃላፊ
28. አቶ አዲሱ ሶርሳ የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ም/ኃላፊና የልማት ዕቅድ ዘርፍ ኃላፊ
29. አቶ ወንድሙ ተክሌ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ም/ኃላፊ
30. አቶ ታረቀኝ ያንጋጎ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ
31. ዶ/ር አሸናፊ ጳውሎስ የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ም/ኃላፊና ካዳስተር ዘርፍ ኃላፊ
32. አቶ ወንድሙ ደረጀ የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ም/ኃላፊና ወጣት ዘርፍ ኃላፊ

የተከበሩ አቶ አዝማቹ ዳዊት የባይራ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሹመዋል፣መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንልህ ከልብ እመኛለሁ!!
11/09/2023

የተከበሩ አቶ አዝማቹ ዳዊት የባይራ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሹመዋል፣

መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንልህ ከልብ እመኛለሁ!!

አቶ ደመቀ ኩኬ የዳሞት ፑላሳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ ወላይታ ሶዶ፤ጳጉሜ 06/2015 የዳሞት ፑላሳ ወረዳ ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 11ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አሰቾካይ ጉባኤው ...
11/09/2023

አቶ ደመቀ ኩኬ የዳሞት ፑላሳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ

ወላይታ ሶዶ፤ጳጉሜ 06/2015 የዳሞት ፑላሳ ወረዳ ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 11ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አሰቾካይ ጉባኤው አቶ ደመቀ ኩኬ የዳሞት ፑላሳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

አቶ ደመቀ ኩኬ ከወረዳ ጀምሮ በዞን መዋቅር በተለያዩ መስሪያ ቤቶች በኃላፊነት ባገለገሉበት ጊዜ ሁሉ ከህዝብና መንግሥት የተሰጣቸውን ሀደራ በትጋትና ታማኝነት የተወጡ በሳል አመራር መሆናቸው ተገልጿል።

አቶ ጀገና አይዛ የሶዶ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል የሶዶ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት  2ኛ ዙር 11ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ጀገና  ይዛን የሶዶ ከተማ ከንቲባ ሆነው ሾሟል...
11/09/2023

አቶ ጀገና አይዛ የሶዶ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል

የሶዶ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ ዙር 11ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ጀገና ይዛን የሶዶ ከተማ ከንቲባ ሆነው ሾሟል።

ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ባደረገው አስቸኳይ ጉባኤ የሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆኖ እንዲሾም ያቀረቡት አቶ መስፍን ዳዊት ሲሆኑ የምክር ቤት አባላት ሙሉ ድምፅ አጽድቋል ።

Address

S**o
00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የወላይታ ዜና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የወላይታ ዜና:

Videos

Share

Category


Other Newspapers in S**o

Show All

You may also like