Job seeker

Job seeker

 #የ4ተኛው ቅዱስ ፓትርያርክ ሥርዓተ ቀብር ዕለት የተጻፈ---------------------------------------------------በእግዚአብሔር ቸርነት፤ማንም ሊመረምረው በማይቻል መን...
07/08/2022

#የ4ተኛው ቅዱስ ፓትርያርክ ሥርዓተ ቀብር ዕለት የተጻፈ
---------------------------------------------------

በእግዚአብሔር ቸርነት፤ማንም ሊመረምረው በማይቻል መንገድ እራሱ መንፈስ ቅዱስ ባሰማራቸው ሠራተኞች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ዳግም አንድ አድርጏታል። ይህ ይሆን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ መሳርያው አድርጎ የተጠቀመባቸው ደግሞ እነ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አይነቱን ነው።ማንም ሰው አጀንዳ ብሎ በማያነሳው ወቅት ቤተ ክርስቲያን ተከፍላ እኛ ዝም ብለን መኖራችን አደጋ እንደሆነ ትውልዱን ከቀሰቀሱት ካነቁት ሐዋርያ አንዱ የመጀመሪያው እርሱ ነው። አንድ ሁሌም የማልረሳው፤ በውስጤ የሚያቃጭልብኝ ነገር፤ ቤተ ክርስቲያን በምን ምክንያት እንደተከፈለችና ወደፊትስ እንዴት አንድ መሆን እንዳለባት ሲያስተምረን፤ የማልረሳው ስለ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሲያነሳ "በረከታቸው ይደርብንና፤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ" ብሎ ልዩ ቃና ባለው አክብሮት ነበር የሚያነሣቸው። ስማቸውን አጠራሩ ብቻ ብዙ ጥልቅ ነገር እንድናስተውል ያደርገን ነበር። ፖለቲካውን ከሃይማኖት ለይተን እንድንረዳ ያደርገን ነበር። የቱኛው ተሀድሶ ምንፍቅና ያመጣው የትኛው ፖለቲካ ያመጣው ተግዳሮት እንደሆነ በጥናት አስደግፎ ያሰለጥነን ነበር ያስተምር ነበር። "ሲኖዶስ አትሰደድም" ብሎ አቋም መያዝ የቅዱስ አባታችንን በግፍ መሰደድ፤ የቅዱስ አባታችን ተጋድሎ መዘንጋት እንዳልሆነ ስማቸውን በተለየ ክብር ሲጠራቸው ብቻ ብዙ እንማርበትም ነበር። ከምንም በላይ በቤተ ክርስቲያን አንድነት ላይ የእኔ ብለን እንድንሠራ ያሠለጥነን ነበር። "ጸልዩ በእንተ ሰላም ቤተ ክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባዔ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኀበ እግዚአብሔር፤ የሐዋርያት ጉባዔ ስለሆነች፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ስለቀናች ፤ ስለ አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም ጸልዩ" የሚለውን የቅዳሴ ፀሎታችንን በየትምህርት ርዕሱ እያስገባ ያስታውሰን ነበር። ሙሐዘ ጥበባት ካለው ልዩ ስጦታዎች አንዱ፤ ወንጌልን ሲያስተምር ከወቅቱ የቤተ ክርስቲያን ፈተና ጋር አሰናስሎ የተኛው እንዲነቃ ያላወቀው እንዲረዳ አድርጎ ተጽዕኖ የሚያመጣ ንቅናቄ የመፍጠር ጸጋ አለው። ስብከቶቹ የሚያነቁ ብቻ ሳይሆን፤ አንቅቶ ወደ መንፈሳዊ ሥራዎች የሚያዘምቱ ነበሩ። በዚህ ትምህርቶቹ ከአንዳንድ አቢያተ ክርስቲያናት ሳይቅር የተባረረበት ጊዜ ነበር፤ አይምጣብን የተባለበት ከተሞች ነበሩ። እርሱ በረገጠባቸው ከተሞች ሁሉ ግን ሥራ ይሠራ ነበር። ለ አንድ ሰዓት የተሰጠች ስብከቱ ዓመት ሙሉ ያነጋግር ነበር፤ ለ45 ደቂቃ ያቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ ለሚቀጥሉት አምስት፤አሥርት ዓመታት
ተጽዕኖ ይፈጥሩ ነበር። ለምሳሌ ከስብከቶቹና ጥናታዊ ጽሁፎቹ አንዳንዱን ለመጥቀስ ያህል፤

+ለጥፋት የታዘዘች ከተማ ነጋሪት ቢጎሰም አትሰማ
+አንድ ሆነን ችግሩን እንፍታ ወይስ ችግሩ ሲፈታ አንድ እንሁን
+ ምንም እንኳ
+ የምትሄድበት መንገድ እሩቅ ነውና ተነሥተህ ብላ

እነዚህ በጥቂቱ በቤተ ክርስቲያን አንድነት ዙሪያና በወቅቱ ፈተናዎች የተሰጡ ትምህርቶችና ጥናታዊ ጽሑፎች ናቸው። እነዚህ በጉባዔ መልክ የተሠጡ እንጂ፤ ሦስት ሰዎችም ይኑሩ አምስትም ሰዎች፤ ምክሮቹም ተግሳጾቹም፤ ውይይቶቹም በእናት ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ነበሩ። ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው ይህች ቀን እንደምትመጣ ቅዱስ አባታችን ሳይሞቱ በፊት በክብር ወደ መንበራቸወ እደሚመለሡ ተገልጦለት ነበር ወይ ያስብለኛል።

ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይደንቀኛል። ሙሐዘ ጥበባት ለዚህም ነው ጸሎቱን፤ ትጋቱን፤ አገልግሎቱን መድኃኔዓለም ቆጥሮለት፤ የአንድነት አጀንዳ

Ortho lezelalem tinur!!
06/08/2022

Ortho lezelalem tinur!!

21/05/2022
21/02/2021

ልቤ የሚያሰደሰት መዝሙር ተጋበዙልን

21/02/2021

ኢትዮጵያዊቷ ዶ/ር ውለታ ለማ ዓለም አቀፉን የቴክኖሎጂ የስራ ፈጠራ ውድድር አሸነፉ!የላሊበላ ግሎባል ኔትወርክስ ድርጅት ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ (...
05/12/2020

ኢትዮጵያዊቷ ዶ/ር ውለታ ለማ ዓለም አቀፉን የቴክኖሎጂ የስራ ፈጠራ ውድድር አሸነፉ!

የላሊበላ ግሎባል ኔትወርክስ ድርጅት ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ (ዶ/ር) ዓለም አቀፉን ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ አዲስ የስራ ፈጣራ ውድድር አሸነፉ። ኢትዮጵያዊቷ በየዓመቱ የሚካሄደውን ዓለም አቀፉን ፒአይቲሲኤች (PITCH) አዲስ የስራ ፈጠራ ውድድር በትላንትናው እለት ማሸነፉቸው ይፋ ሆኗል።

በውድድሩ 2500 ስራ ፈጣሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ወደ መጨረሻው ዙር ያለፉት ደግሞ 700 የሚሆኑ አዲስ ፈጣሪዎች ነበሩ።ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ(ዶ/ር) በጤና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያቀረቡት አዲስ የስራ ፈጠራ በቅርበት ተፎካካሪ ከነበሩት የአሜሪካና የእንግሊዝ የስራ ፈጣሪዎችን በመብለጥ የዓመቱ ውድድር አሸናፊ ሆኗል።

ውለታ ለማ (ዶ/ር) ለውድድሩ ያቀረቡት የስራ ፈጠራ አባይ ሲ ኤች አር (ABAY CHR) የተባለ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ህክምና ዘርፍ ያለውን ሰፊ የወረቀት ስራ ወደ ዲጂታል በመቀየር ስራን የሚያቀልና የሚያቀላጥፍ እንዲሁም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪን የሚያስቀር የሥራ ፈጠራ ነው ተብሏል። "የአፍሪካን የጤና ዘርፍ ስርዓት ለማዘመን ለ28 ዓመታት ሰርቻለሁ ፤ እናም ውድድሩን በማሸነፌ በጣም ተደስቻለሁ" ሲሉ ውለታ ለማ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

01/12/2020

✳️ ስልካችሁ እየተንከረፈፈ ወይም ስታክ እያረገ ላስቸገራችሁ እነዚህን መፍትሄዎችን ይተግብሩ፡

💢 ስልኮ ከተለመደዉ በላይ ይዘገያል ወይስ ከናካቴዉ አልሰራም ብሎ ቀጥ ብሎ ይቆማል፡፡ እንግዲህ ስልኮ በጣሙን የሚዘገይ አልያም አልታዘዝ ካሎት ስልኮ የሆነ ችግር ገጥሞታል ማለት ሲሆን ለዚህ አይነት ችግር መንስዔ የሚሆኑ መነሾዎችን ከነመፍትሄዎቻቸዉ ጋር እንደሚከተሉት አቅርበንሎታልና ይተግብሯቸዉ፡፡

💢 ከስልኮ ላይ የአላስፈላጊ አፕሊኬሽኖች መኖር ከስልኮ ላይ አላስፈላጊ አፕሊኬሽኖችን ያጥፉ፡፡ ስልኮ ላይ ብዙ አላስፈላጊ አፕሊኬሽኖች ለምሳሌ ጌሞች ፣ የፎቶ እና ቪዲዮ ማሳመሪያ (ኤዲትኢንግ) ሶፍትዌሮች የተለያዩ የሙዚቃም ይሁን የቪዲዮ ማጫወቻ(ፕሌየሮች) ስልኮ ላይ ካለ በተቻለ መጠን የሚፈልጉትን አፕሊኬሽን ሶፍሮች ብቻ ትተዉ ሌላዉን በአብዛኛዉ የማይጠቀሙባቸዉን አፕሊኬሽኖች ያጥፉ፡፡

💢 የስልኮ ዳታ መያዣ (ስቶሬጅ) በፋይሎች መጨናነቅ በስልኮ ሜሞሪ ላይ ብዛት ያላቸዉ ሙዚቃዎች ፣ ቪዲዮች ፣ ያልጫኑት ሶፍትዌር አፕሊኬሽኖች አስቀምጠዉ ከሆነ በተቻለ መጠን የማይፈልጉትን ቢያጠፉ አልያም ከቆይታ በኋላ ብፈልጋቸዉ አላገኛቸዉም ካሉ በሌላ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ቋት (ሜሞሪ) ያስቀምጡት፡፡

💢 የስልኮን ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና ስልክዎ ላይ ያለን ሶፍትዌር አለማደስ ስልኮ ያሉትን ሶፍተዌሮች እና ስልኮን ያለማደስ ስልኮን ለሌላ ቫይረስ አልያም ጎጂ ሶፍትዌር ያጋልጣል ይህም የስልኮን ፐሮግራሞች ሳይዘጉ ከኋላ እንዲነሳ (Background Play) ስለሚያደርገዉ ስልኮንና የሚጠቀሙበትን ሶፍትዌር ያደሱት፡፡

💢 ካች (Cache) ዳታን አለማፅዳት ካች ዳታ የምንላዉ አብዛኛዉን ጊዜ የምንጠቀምባቸዉን ሶፍትዌሮችና ፋይሎች ስልካችን የሚያስቀምጥበት ቦታ ሲሆን ስልካችንን መረጃን በማመላለስ (loading data) ጊዜን እና ቦታ ተጣቦ ከመዘግየትና ከመቆም ያደናል ስለዚህ የስላካችንን ከች ማፀዳት ተቃሚ ያደርገናል።

💢 Widgets መጠቀምን ማብዛት አንድሮይድ ስልኮች ከሚሰጡን የተለየ ጥቅም አንዱ ዊጄትስ ቢሆንም ያን ያህልም የሚሰሩትን ካልገደብን ስልካችንን በማጨናነቅና እንዲቆም (ስታክ) እንዲያደርግ በማድረግ ረገድም ከፍ ያለ ድርሻ ያላቸዉ በመሆናቸዉ ዊጄትስን በመቀነስ ካልሆነም በማጥፋት ስልኮ በየጊዜዉ መቆሙን አላያም መንቀራፈፉን ማስቆም አማራጭ ነዉ፡፡

💢 ፋብሪካዉ ሲያመርተዉ ወደነበረበት ማሰተካከያ መመለስ (Reset Factory Setting) የስልኮ ማርጀት አልያም ለብዙ ጊዜያት መጠቀም ስልኮን እንዲቀራፈፍ አልያም በየማሃሉ እንዲቆም ለመሆኑ ምክንያት ላይሆን ይችላል፡፡

💢 አንዳንድ የማስተካከያ (ሴቲንግ) ለዉጦች ወይም አቅጣጫ መጠቆምያ ጂፒስ ኦን ማድረግ (ማብራት) ለስልኮ መንቀራፈፍ ምክንያት ሊሆኑ ስለሚችሉ የስልኮ በመሃል በመሃል መቆም (ስታክ) ሲያጋጥሙ ስልኩ ሲዘጋጅ ወደነበረበት መመለስ (reset factory setting) ችግሩን ሊቀርፍ ይችላል፡፡

💢 ዋልፔፐር (Wallpaper) መጠቀም ስልኮ ለዓይን እንዲስብ አልያም በአንድ አንድ አቋራጭ ቴክኒኮች ምክንያት ስልኮ ላይ ላይቭ ዎልፔፐር (Live Wallpaper) መጠቀም አንዱ የአንድሮይድ ስልኮች ገፀ-በረከት ቢሆንም ለስልኮ መዘግየትም ይሁን መቆም (ስታክ ማድረግ) ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ማጥፋቱ መንቀራፈፉን አልያም ሰታክ ማድረጉን ሊያስቆም ይችላልና ይሞክሩት፡፡

💢 ስልኮ አቧራ ከሞላዉ የሚሰሩበት ቦታ አልያም የሚዉልበት አከባቢ አቧራማ ከሆነ ስልኮን ማፅዳትና ከተፀዳም በኋላ መልሶ በአቧራ እንዳይሞላ መከላከያ መጠቀም፡፡

💢 ከላይ ከተጠቀሱት አማራጮች ዉስጥ

19/11/2020

Address

S**o
385037

Telephone

+251921548566

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Job seeker posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share