World News

World News Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from World News, Media/News Company, wolaita, Sodo.

ዶ/ር መብራቱ መካከለኛ ክሊኒክየምንሰጣቸው አገልግሎቶች:-1. አጠቃላይ የውስጥ ደዌ ምርመራና ህክምና2. የማህፀንና ፅንስ ምርመራና ህክምና3. የሕፃናት ምርመራና ህክምና4. የመለስተኛ ቀዶ ህ...
25/03/2023

ዶ/ር መብራቱ መካከለኛ ክሊኒክ

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች:-
1. አጠቃላይ የውስጥ ደዌ ምርመራና ህክምና
2. የማህፀንና ፅንስ ምርመራና ህክምና
3. የሕፃናት ምርመራና ህክምና
4. የመለስተኛ ቀዶ ህክምናና የወንድ ልጅ ግርዛት
5. ከአንገት በላይ ምርመራና ህክምና
6. የአይን ምርመራና ህክምና
7. የስኳርና የደም ግፍት ምርመራ ህክምናና ክትትል
8. የደም ማነስ ምርመራ ህክምናና ክትትል
9. የልብና የኩላሊት በሽታ ምርመራ ህክምናና ክትትል
10. የደም መርጋት በሽታ ምርመራና ህክምና
11. የኮለስትሮል ምርመራ ህክምናና ክትትል
12. የርህ እና ሌሎች የመገጣጠሚያ በሽታዎች ምርመራ ህክምናና ክትትል
13. የጨጏራ የአንጀት ቁስለት የጉበት ቫይረስ በሽታ ምርመራ ህክምናና ክትትል
14. የኤችአይቪ እና የአባላዘር በሽታዎች ምርመራ ህክምናና ክትትል
15. የቲብ በሽታ ምርመራ ህክምናና ክትትል
16. የነርብ በሽታ ምርመራ ህክምናና ክትትል
17. የቅድመ ወልድ ምርመራ ህክምናና ክትትል
18. የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራና ህክምና
19. የጡት ቅድመ ካንሰር ምርመራ ህክምናና ክትትል
20. የማህፀን ወደ ውጭ መውጣት ምርመራና ህክምና
21. የወር አበባ መዛባት ምርመራ ህክምናና ክትትል
22. የእንቅርት ምርመራ ህክምናና ክትትል
23. የድንገተኛ አደጋ ምርመራና ህክምና

በተጨማሪም ለመንግሥት ተቋማት እና ለግል ድርጅቶች የዱቤ ህክምና አገልግሎት እንሰጣለን እንዲሁም ተኝተው ለሚታከሙ ሕሙማን ደረጃን የጠበቀ የመኝታ አገልግሎት መስጠታችን ልዩ ያደርግናል::

ልዩነትታችን " ለእርሶ የሚገቦትን ህክምና መስጠታችን ነው!!"
ዶ/ር መብራቱ መካከለኛ ክሊኒክ
ጉኑኖ

የተሟላ ጥብቅና አገልግሎት እንዲሁም የህግ አማካሪ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ አቶ ነብዩ ማርቆስ በማናቸውም ፈደራልና ክልል ፍ/ቤቶች ጠበቃ እና የህግ አማካሪ ዘንድ ጎራ ይበሉ!! ለተገልጋይ እር...
10/11/2022

የተሟላ ጥብቅና አገልግሎት እንዲሁም የህግ አማካሪ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ አቶ ነብዩ ማርቆስ በማናቸውም ፈደራልና ክልል ፍ/ቤቶች ጠበቃ እና የህግ አማካሪ ዘንድ ጎራ ይበሉ!!

ለተገልጋይ እርካታ ከልብ እንተጋለን!!!

Call@0919725180/0945009819
Wolita soddo

22/10/2022
ኢትዮጵያ የስንዴ ፍላጎቷን በአገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን የምታደርገው ጥረት ትክክለኛ አቅጣጫ የተከተለና ለውጤት እያበቃን ስለመሆኑ በርካታ ማሳያዎችን መጥቀስ ይቻላል። ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስ...
15/10/2022

ኢትዮጵያ የስንዴ ፍላጎቷን በአገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን የምታደርገው ጥረት ትክክለኛ አቅጣጫ የተከተለና ለውጤት እያበቃን ስለመሆኑ በርካታ ማሳያዎችን መጥቀስ ይቻላል።

ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውን ስንዴ በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት በርካታ ሥራዎች እያከናወነች ትገኛለች።
ለዚህም ደግሞ የኩታ ገጠም የግብርና ሥራና የመስኖ ልማት ሥራዎች እየተካሄዱ በመሆናቸው አገሪቱ በትክክለኛ የግብርና አቅጣጫ ላይ መሆኗን የሚያሳይ ንቅናቄ መፍጠር ተችሏል፡፡

ኢትዮጵያ ለስንዴ ምርት የሚሆን ከፍተኛ የውኃና የመሬት አቅርቦት እንዳላት በዘርፉ የተሰማሩ ምሁራን ሲናገሩ ይደመጣል፤ይህንን ዕድል በአግባቡ ተጠቅሞ ከራስ ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው፡፡

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ኢትዮጵያ የስንዴ ፍላጎቷን በአገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን ብሎም ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬን ለማግኘት እንዲቻል በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲው አመራሮች ልዩ ትኩረት ሰጥተው ክትትል እንዲያደርጉ አቅጣጫ ከመስጠታቸው ባሻገር በተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ የደረሰበትን ደረጃ እየጎበኙ ይገኛሉ፡፡

አገሪቱ በስንዴ እርሻ ሥራ ላይ እያሳየች ያለውን ጥረት ማስፋት ከቻለች በአጭር ጊዜ ውስጥ ‘በምግብ ራስን መቻል’ የሚለውን ትልቅ እቅድ ማሳካት እንደሚቻል ከመጠቆሙም በላይ ለውጭ ንግድ የሚቀርቡ የግብርና ምርቶችም ሊኖሩ እንደሚችሉ ያሳዬ ነው።

በወላይታ ዞን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የወላይታ ዞን ዋና አፌ ጉባኤ ጽ/ቤት አስታወቀወላይታ ሶዶ፤መስከረም 5/2015 በወላይታ ዞን ውስጥ ባሉ ሴ...
15/10/2022

በወላይታ ዞን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የወላይታ ዞን ዋና አፌ ጉባኤ ጽ/ቤት አስታወቀ

ወላይታ ሶዶ፤መስከረም 5/2015 በወላይታ ዞን ውስጥ ባሉ ሴክተሮች እንዲሁም በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች የሰንደቅ ዓላማ ቀን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የወላይታ ዞን ዋና አፌ ጉባኤ ወ/ሮ ካሴች ኤልያስ አስታወቁ።

"ሰንደቅዓላማችን የብዝሃነታችን መገለጫ፤ የሉዓላዊነታችን ምሰሶ ነው!" በሚል መሪ ቃል
የሰንደቅ ዓላማ ቀን ሰኞ ጥቅምት 7/ 2015 ዓ.ም ከጧቱ 4:30 በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል።

የወላይታ ዞን ዋና አፌ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ካሴች ኤልያስ በዓሉን በማስመልከት በሰጡት ማብራሪያ በወላይታ ዞን ማዕከልና በሁሉም መዋቅሮች የሰንደቅ ዓላማ ቀን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ተናግረዋል ።

በበዓሉ ዕለት በሁሉም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ውስጥና በትምህርት ቤቶች በድምቀት እንደሚከበር አፌ-ጉባኤ ገልጿል ።

ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በተሻሻለው የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር863/2006 አንቀጽ 2 ላይ በተደነገገው መሠረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያ ሳምንት ይከበራል

ከብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 3 ላይ እንደተቀመጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ከላይ አረንጓዴ ፣ ከመሐል ቢጫና ከታች ቀይ ሆኖ ሦስቱም ቀለማት እኩል ሆነው በአግድም የሚቀመጡ ስሆን በመሐል ብሔራዊ ዓርማ እንዳለው ጠቁመዋል

በሰንደቅ ዓላማ ላይ የተቀመጠው ብሔራዊ ዓርማ የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦች ፣ ሕዝቦች እና ሃይማኖቶች በእኩልነትና በአንድነት ለመኖር ያላቸውን ተስፋ እንደሚያንፀባርቅ አስረድተዋል ።

ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ትውልድ ተሻጋሪ የልማት ቱርፋት ነው።ይህ ትውልድ  እድለኛ ነው እንዲህ ያለ ዘመን ተሻጋሪ አገራዊ ፕሮጀክት መገንባት በመቻሉ። ይህ ትውልድ እንደታላቁ የኢትዮጵ...
14/10/2022

ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ትውልድ ተሻጋሪ የልማት ቱርፋት ነው።ይህ ትውልድ እድለኛ ነው እንዲህ ያለ ዘመን ተሻጋሪ አገራዊ ፕሮጀክት መገንባት በመቻሉ።

ይህ ትውልድ እንደታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያለ ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ፕሮጀክት ላይ አሻራውን ማሳረፍ የሚችልበት አጋጣሚ ስለተፈጠረለት ደስታው ልዩ ነው።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታ ለአገራችን ዜጎች ብሔራዊ መግባባት በመጫር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትንና የትብብር መድረክ የፈጠረ ነው።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ መሠረት ከተጣለ ጀምሮ የተወሰኑ መሰናክሎች ቢኖሩም ዕድገት እያሳየ መጥቶ እነሆ 3ኛው ዙር የውሃ ሙሌት ላይ ደርሰናል ፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት አራት ዓመታት ከሰራቸው ውጤታማ ተግባራት አንዱ የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ አንድነታችንን ያረጋገጥንበት ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መካከል ያለው መልካም ግንኙነት እንዲዳብር እና የህዝቦችን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ለማሳየት እድል የሚፈጥር ነው፡፡

በቅርቡ ኃይል ማመንጫት የጀመሩት ሁለት ዩኒቶች እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን÷ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 411 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል በማመንጨት ወደ ብሔራዊ ኃይል ቋት ማስገባት ተችሏል፡፡

13/10/2022
08/10/2022

የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ በየነ ለነብዩ መሐመድ የመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1497ኛው የነብዩ መሐመድ የመውሊድ በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

ዛሬ በፈተና ላይ ሆነን የምናከብረው በዓል ነገ በታላቅ ደስታና ተድላ ላይ ሆነን እንደምናከብር ሙሉ እምነት አለኝ፡፡

ደካማ ኢትዮጵያን ማየት ዓላማ ያደረገው አሸባሪው ህወሐት ቡድን በሀገራችንና በህዝባችን ላይ ለ3ተኛ ጊዜ የተከፈተብን ጦርነት በድል ለማጠናቀቅና ለመቀልበስ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ከሠራዊቱ ጀርባ ያለው የህዝብ ማዕበልና ደጀንነት የሚደነቅና የሚመሰገን ነው፡፡

በየመንገዳችን ላይ እንቅፋት እንደሚኖር እንረዳለን” ስለዚህ “ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች እና ሌሎችም፣ እንደተለመደው እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ ፈተናዎቻችንን ሁሉ እንደምንሻገራቸው ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያውያን ዕድል በኢትዮጵያውን እጅ እንዳለ በፍጹም እናምናለን፡፡

ጥላቻን ነቅለን ፍቅርን እየተከልን የጀመርነውን የለውጥና የዕድገት ጉዞ እንድናስቀጥል ብሎም የሕዝባችንን ችግር ደረጃ በደረጃ እየለየን እንድንፈታ ከምንጊዜም በተለየ መልኩ የለውጥ ሀሳብን በማመንጨትና በመተግበር አጠቃላዩ የዞናችን ማህበረሰብ እንዲንቀሳቀስ፣ ተግቶም እንዲሰራ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ከቃል ባለፈ ሁላችንም እንደ አንድ ልብ ሀሳቢ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነን እጅ ለእጅ ተያይዘን ለተግባራዊነቱና ለውጤታማነቱ መትጋት ይኖርብናል፡፡

የመረዳዳት በዓለችን በመውሊድ ቀን ብቻ ሳይሆን የእለት ተዕለት ተግባራችንና በትውልድ ቅብብሎሽ የሚቀጥል በመሆኑ የዘንድሮውን በዓል ስናከብር የመረዳዳት፣ የመተዛዘንና በጋራ መስራት የሚያስፈልግበት ወቅት መሆኑን መረዳት እንደሚያስፈልግ በዚሁ አጋጣሚ ላሳስባችሁ እወዳለሁ።

እንዲሁም በበዓሉ አቅመ ደካሞችን፥ ረዳት የሌላቸውን አረጋውያን፥ አዛውንቶችን እንዲሁም ወላጅ አጥ የሆኑ ሕፃናትን እንድንደግፍ እና ካለን እንድናካፍል ቤተሰባዊ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

በድጋሚ በዓሉ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የሰላም፤ የፍቅርና የደስታ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡

ዮሐንስ በየነ
የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

10/09/2022

“አዲሱ ዓመት አቅደን የሚንፈጸምበትና ሰርተን የሚንለወጥበት፣ ሠላምና ፍቅር የሚነግስበት እንዲሆንልን እመኛለሁ”፡- አቶ ዮሐንስ በየነ

የተወደዳችሁ መላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች!!

የተወደዳችሁ መላው የዞናችን ህዝቦች፤ የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች!

እንኳን ለ2015 አዲሱ ዓመት/እንቁጣጣሽ/ በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን!!

አሮጌው ዓመት አልፎ አዲስ እየተተካ የክረምት፣ የጭቃ፣ የዝናብ፣ የብርድና የጨለማ ጊዜ አልፎ የብርሃን ጊዜ እየመጣ ሁሌም እየተደሰትን ከአንዱ ዘመን ወደ ሌላ ዘመን በየእድሜያችን ቁጥር ልክ ተሸጋግረናል። ይህንን ዕድል ሳያገኙ ወደ አዲሱ ዘመን መሻገር ያላቻሉ ብዙዎች አሉና።

አዲስ ዘመን ሲመጣ ዘመኑ ካለፈው ዘመን የተለየና እንደ ስያሜው አዲስ እንዲሆንልን ከፈለግን በሚመጣው ዘመን ውስጥ አዲሰ ሆነን ሲንገኝ ነው። ስለ አዲስ ዘመን ስናወራ ራሳችንም ማደስ ይገባናል።

ከዘመን ወደ ዘመን ስንሸጋገር አሮጌ ባህሪያችንንና አስተሳሰባችንን ቀብረን አዲስ ሕይወት ይዘን አዲሱን ዓመት ልንቀበለው ይገባል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከብዙ ውጣ ውረዶች ውስጥ አልፈን ትላልቅ ስኬትና ውጤት እንድናስመዘግብ በሀሳብ፣ በሞራል፣ በጊዜና በዕውቀት እንዲሁም በሁሉም መስክ ያላሰለሰ ድጋፍ ያደረጋችሁ በሙሉ በያለችሁበት ቦታ ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናና አክብሮት ይደርሳችሁ፡፡

የምንፈልገውን ልማት፣ ዴሞክራሲ፣ሁለንተናዊ ሠላምና ብልጽግናን በአጭር ጊዜ ዕውን ለማድረግ የድል ብልጽግናን የሚያበሰሩ ነባራዊ እውነቶች ላይ ቆመን በአዲስ መንፈስ መረባረብ እንዳለብን ይሰማኛል፡፡

ውድ የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች ፓርቲያችን ብልጽግና በምርጫ ወቅት ለህዝባችን ቃል የገባውን ማኒፌስቶን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚጠበቅባችሁን ኃላፊነት በትጋት እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

ከወግ አጥባቂነትና ከጽንፈኝነት ዝንባሌዎች እንዲሁም አፍርሰን ከመገንባት አስተሳሰቦች ተላቅቀን መካከለኛውን መንገድ ይዘን ለሁለንተናዊ ብልጽግና መትጋት አለብን፡፡

የተከበራችሁ የዞናችን ህዝቦች፡- በዞኑ ውስጥ የሚደረጉ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና የልማት እንቅስቃሴዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የድርሻችሁን ያልተቆጠበና የላቀ ተሳትፎ እንድታደርጉ ላሳስባችሁ እወዳለሁ፡፡

የምንወዳትና እንደዐይናችን ብሌን የምንሳሳላት ሀገራችን ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን የሚያለያዩ ሁኔታዎችን ከማጉላት ይልቅ የሚያቀራርቡና የሚያስተሳስሩንን እውነታዎች ላይ ማተኮርና መጠንከር ያስፈልጋል፡፡

ጥላቻን ነቅለን ፍቅርን እየተከልን፤ አንዳችን ለሌላችን ዋልታ እና ማገር፣ ድርና ማግ ሆነን የጀመርነውን የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን መላው የዞናችን ማህበረሰብ ተግቶ እንዲሰራ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

አሸባሪው ህወሐት የሠላም አማራጮችን አሻፈረኝ ብሎ ለ3ተኛ ጊዜ የከፈተብንን ጦርነት ለመቀልበስ ውድ ህይወታቸውን ሳይሰስቱ በዱርና በበረሃ እየተዋደቁ ላሉ ለሀገር መከላከያ ሠራዊትና ለጥምር ጦሩ የዞኑ ህዝብ ላደረገው ድጋፍ ልዩ ክብር አለኝ።

ሰላም የሁሉ መሠረት ነውና ሰላማችንን እንጠብቅ፣ ያላወቅነውን ለማወቅ፣ ያወቅነውን በጎ ነገር ለሌሎች ለማሳወቅ እንትጋ፣ አካባቢያችንን ብሎም አገራችንን ለማልማትና ወደ ብልፅግና ማማ ለማውጣት ተግተን እንሥራ የሚለው ዋና መልዕክቴ ነው፡፡

በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትንና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖቻችንን በመርዳት፣ በመተሳሰብ፣ በይቅር-ባይነት፣ በመግባባት፣ በወንድማማችነት፤ በእህታማማችነትና በአብሮነት መንፈስ ልናከብር ይገባል፡፡

በድጋሚ ለመላው የሀገራችንና የወላይታ ህዝብ አዲሱ አመት የሰላም፣ የጤና፣ የብልጽግናና የከፍታ ዓመት እንዲሆን ልባዊ ምኞቴ ነው፡፡

እንኳን በሠላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!! መልካም አዲስ ዓመት!!

ዮሐንስ በየነ
የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!

 ።በአራቱ ክላስተር ከተሞች የተደረገ 20 ቢሮች ድልደላ ተብለው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ውሸት ስለሆን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።እንደዚህ አይነት መረጃ በመንግሥት በኩ...
22/07/2022



በአራቱ ክላስተር ከተሞች የተደረገ 20 ቢሮች ድልደላ ተብለው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ውሸት ስለሆን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

እንደዚህ አይነት መረጃ በመንግሥት በኩል ተጠንቶ የቀረበ እንደሌለ ህዝብ ማወቅ ያስፈልጋል።

ራሳቸውን አክቲቪስት ነን ባዮቹ በየጊዜው በህዝቡ መካከል አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመፈጠር በየቀኑ አዳዲስ አሉባልታዎችን እያሰራጩ ይገኛሉ።

ግለሰቦቹ ተስፋ የቆረጡትና መንግስት በየጊዜው ሲያሰራቸው ራሳቸውን እንደጀግና ሰው አድርጎ የሚያስቡ ናቸው።

ዕድሜ ልካቸውን ህዝቡ ለማሸበርና ከሰው ተወልደዋሉ ለማለት የሚከብዱ ጥቅት ግለሰቦች ሀሰተኛ እና ምንጩ ያልታወቀበት መረጃዎችን ስያሰራጩ የኖሩት አሁን ቀጥለዋል።

ህዝቡ እነዚህን ግለሰቦችን መለየትና የፌስቡክ አካውንቶቻቸውን Block በማድረግ ከሀሰተኛ መረጃ ራሱን መከላከል ያስፈልጋል።

ወጣቱ ተጨዋች ኢዮብ አለማየሁ!!!✔️ኢዮብ በልጅነቱ ባገኘው ምርጥ ተስጥኦ በወላይታ ዞን ከሚገኘው ጉኑኖ ከተማ ተነስቶ project..Dicha B....Dicha A....ጅማ አባጅፋር...እስከ...
20/06/2022

ወጣቱ ተጨዋች ኢዮብ አለማየሁ!!!

✔️ኢዮብ በልጅነቱ ባገኘው ምርጥ ተስጥኦ በወላይታ ዞን ከሚገኘው ጉኑኖ ከተማ ተነስቶ project..Dicha B....Dicha A....ጅማ አባጅፋር...እስከ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫውቷል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታርክ ዕድሜ ትንሹ ፈጣን ጎል ያስቆጠረ ተጨዋች ነው ኢዮብ አለማየሁ።ኢዮብ አለማየሁ በዚህ ትንሹ ዕድሜው ሀትሪክ ሰርቷል፣በርካታ ጎሎችን ከመረብ አሳርፈዋል።

ኢዮብ በረኛ ከመሆን ውጪ አጥቂ፣ተከላካይ፣መሀል አማካይ፣የክንፍ ተመላላሽ ሁሉም ቦታ ላይ የመጫወት አስደናቂ ልምድ አሐው።

መልካም ዕድል ምርጡ ልጃችን ካንተ ብዙ እንጠብቃለን ዎዜ!!

ዕውቅና ባልተሠጠው የትም/ት መስክ ሲያሰለጥኑ የነበሩ ኮሌጆችን መዝጋቱን የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ አስታወቀወላይታ ሶዶ፤ ሰኔ 10/2014 ዕውቅና ባልተሠጠው የትም/...
17/06/2022

ዕውቅና ባልተሠጠው የትም/ት መስክ ሲያሰለጥኑ የነበሩ ኮሌጆችን መዝጋቱን የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ አስታወቀ

ወላይታ ሶዶ፤ ሰኔ 10/2014 ዕውቅና ባልተሠጠው የትም/ት መስክ ሲያሰለጥኑ የነበሩ ኮሌጆችን መዝጋቱን የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ አስታውቋል።

ግሎባል ብሪጅ ኮሌጅ አረካ ካምፓስ ፣ ዳሞታ ቴክኖሎጂና ቢዝነስ ኮሌጅ አረካ ካምፓስ ፣ ካላቻ አረካ ካምፓስና ፊንላንድ ተቋም አረካ ፣ቦዲታና ቦምቤ ካምፓስ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆቹ ባልተፈቀደላቸው የሙያ መስኮች ስልጠና ሲሰጡ በመገኘታቸው የተሰጣቸው ፍቃድ የተነጠቀ ባቸው ና የተዘጉ መሆናቸውን ቢሮው ገልጿል፡፡

ከተፈቀደላቸው ሙያ እና የስልጠና ደረጃ ውጪ እያሰለጠኑ በመሆናቸው፣ ከመመሪያ እና ደንብ ውጪ በርካታ ችግሮች ሲፈጽሙ በመገኘታቸውና በተለያዩ ጊዜ ግብረ-መልስ ቢሰጣቸውም ለማረም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ተቋማቱ እንዲዘጉ የውሳኔ ሀሳብ ተላልፎባቸዋል፡፡

ዘገባው፡- በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ የኮሚዩኑኬሽን ዱዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወላይታ ሶዶ ገቡ ወላይታ ሶዶ፤ ሰኔ 10/2014 ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወላይታ ሶዶ ገብተዋል።ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ወደ ሶዶ ከ...
17/06/2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወላይታ ሶዶ ገቡ

ወላይታ ሶዶ፤ ሰኔ 10/2014 ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወላይታ ሶዶ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ወደ ሶዶ ከተማ ሲደርሱ የከተማ የዞን እና የደቡብ ክልል ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በወላይታ ሶዶ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታ የልማታዊ ስራ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ከከተማ ከዞን እና ከደቡብ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከአገር ሽማግሌዎች እና ከሀይማኖት አባቶች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ላለፉት ሁለት አመታት ህገመንግስታዊ ስርዓትን በኃይል መናድ በሚል ስከሰሱ የነበሩ የቀድሞ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ ጨምረው ሌሎችም ከተጠረጠሩበት ወንጀል ነፃ ወጡበዛሬው...
16/06/2022

ላለፉት ሁለት አመታት ህገመንግስታዊ ስርዓትን በኃይል መናድ በሚል ስከሰሱ የነበሩ የቀድሞ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ ጨምረው ሌሎችም ከተጠረጠሩበት ወንጀል ነፃ ወጡ

በዛሬው ዕለት በአርባምንጭ ከተማ በዋለው የፈደራል ተዘዋዋሪ ችሎት በቀድሞ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በእነ ዳጋቶ ኩምቤ የተከሰሱ 17 ግለሰቦች እና በእነ ቡዛየሁ ቡቼ የተከሰሱ 6 ግለሰቦች የአቃቤ ህግ ማስረጃ በተገቢው ባለመቅረቡ በሚል ተከሳሾቹ በነፃ እንዲሰናበቱ መደረጉን ጠበቆቻቸው አቶ ተመስገን ዋጃና ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ተናግረዋል።

ላለፉት ሁለት አመታት ህገመንግስታዊ ስርዓትን በኃይል መናድ በሚል የቀድሞ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ ጨምሮ ሌሎች አመራሮች እና የመብት ተሟጓቾች በፍርድቤት ጉዳዮቻቸውን ስከታሉ ነበር።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አክልሉ ለማ የሰራ መልቀቂያ አስገብተዋል ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ፍፁም ከእውነት የራቀና ሀሰት መሆኑን እንገልፃለን።
13/06/2022

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አክልሉ ለማ የሰራ መልቀቂያ አስገብተዋል ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ፍፁም ከእውነት የራቀና ሀሰት መሆኑን እንገልፃለን።

የጋቶች ፓኖም ዉለታ.........................አንድ ተጫዋች የአንድን ክለብ የማጥቃት እና የመከላካል ሙሉ ስፍራን እንዴት መሸፈን ይችላል?  ...........ከአንድ የተከላካይ ...
10/06/2022

የጋቶች ፓኖም ዉለታ.........................

አንድ ተጫዋች የአንድን ክለብ የማጥቃት እና የመከላካል ሙሉ ስፍራን እንዴት መሸፈን ይችላል? ...........

ከአንድ የተከላካይ አማካይ የሚጠበቀዉ በተቃራኒ ተጋጣሚዎች የሚመጣ የማጥቃት እንቅስቃሴን ማጨናገፍ እና ማስተጓጎል ሲሆን ጋቶች ፓኖም ከዚህ በተጨማሪ ተሻጋሪ የማጥቃት ሂደትን እየመራ ነበር ፤ ባለዉ የሰዉነት አቋሚ ኳስ ማስጣሉን በቀላሉ የተካነበት ሲሆን የግብ እድሎችን ( ሹቶችን ) እንኳን ሲያደርግ ተመልክተነዋል።

ኢትዮጵያ እንደርሱ ያሉ ምርጥ የተከላካይ አማካዮች ያስፈልጓታል ፤ ጋቶች የእዉነት ይችላል 👏

የምትወዱት 👍

''ኢትዮ-ሰላም ሩጫ በወላይታ'' በሚል መሪ ቃል በሰኔ አራት (4) መጪው ቅዳሜ በወላይታ ሶዶ ከተማ ይካሄዳልወላይታ ሶዶ፤ ግንቦት 29/2014 ''ኢትዮ-ሰላም ሩጫ በወላይታ'' በሚል መሪ ቃ...
06/06/2022

''ኢትዮ-ሰላም ሩጫ በወላይታ'' በሚል መሪ ቃል በሰኔ አራት (4) መጪው ቅዳሜ በወላይታ ሶዶ ከተማ ይካሄዳል

ወላይታ ሶዶ፤ ግንቦት 29/2014 ''ኢትዮ-ሰላም ሩጫ በወላይታ'' በሚል መሪ ቃል በሰኔ አራት (4) መጪው ቅዳሜ በወላይታ ሶዶ ከተማ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

ሩጭው የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎችና ታላላቅ አትሌቶች በተገኙበት ሰኔ 04/2014 ዓ/ም እንደሚካሄድ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

የሩጫ ዓላማው የቀድሞው ዳሞታ አትሌቲክስ ክለብን መልሶ ለማደራጀትና ለማቋቋም ዓላማ አንግቦ የተዘጋጀ ነው፡፡

የህዝቡን ሠላማዊነትና አብሮነትን እንድሁም ለሁለንተናዊ ብልጽግና ለአገርና ለዓለም ህዝቦች በስፖርቱ ለመግለጽ የተያዘ ትልቅ ዓላማ እንዳለውም ተገልጿል፡፡

በሩጫ ፕሮግራሙ ላይ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ መንግስት ሥራ ኃላፊዎችና ታላላቅ አትሌቶች በክብር እንግድነት እንደሚታደሙ በሺህዎች የሚቆጠሩ የስፖርት አፍቃሪያን ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሩጫው በሰኔ 04/2014 ዓ/ም ከጧቱ 12፡00 ሰዓት ከሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ህንጻ ፊት ለፊት መነሻውን በማድረግ መድረሻውን ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በሚያደረገው በዚህ ሩጫ በደረጃ ለሚወጡ ተፎካካሪዎች ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡

ኢትዮ ሰላም ሩጫ በወላይታ በሚል መሪ ቃል ታላቅ ተልዕኮውን ለመፈጸም ለሚካሄደው ለዚህ ሩጫ ፕሮግራም ስኬታማነት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

01/05/2022

የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ዮሐንስ በየነ ለኢድ አል ፈጥር በዓል ያስተላለፉት መልዕክት

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

እጅግ የተከበረውና ቅዱስ ቁርአን ከሰማይ የወረደበት ወርሃ ረመዳን ሙስሊም ወንድሞቻችን በፆም፣ በፀሎት፣ የተቸገሩትን በመርዳት በማሰብና አላህ ለሃገራችንና ህዝቦቿ መልካም ነገርን ያደርግላቸው ዘንድ ዱዓ የሚያደርጉበት ታላቅ ወር ነው፡፡

ከጠዋት እስከ ማታ በጾም፣ በጸሎት እና በመልካም ምግባር ማሳለፍ ከባድ ፈተና ነው። በጾሙ ወቅት የሚገኘው ስጦታ ደግሞ በረከት ነው። አንድን ወቅት ጥሩ ወቅት ነው የምንለው እየተፈተንን የምናልፍበት፣ አልፈንም የምንሸለምበት ጊዜ ሲሆን ነው።

ጥላቻን ነቅለን ፍቅርን እየተከልን የጀመርነውን የብልጽግና ጉዞ እንድናስቀጥል ብሎም የሕዝባችንን ችግር ደረጃ በደረጃ እየለየን እንድንፈታ ከምንጊዜውም በተለየ መልኩ የለውጥ ሀሳብን በማመንጨትና በመተግበር አጠቃላዩ የዞናችን ማህበረሰብ እንዲንቀሳቀስ፣ ተግቶም እንዲሰራ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

የመጠፋፋት ፖለቲካ ለዚህች አገር እንደማይጠቅም ያለፉትን 27 ዓመታት ጉዞ መመልከት በቂ ነው፡፡ ዛሬ ላይ በአገራችን እዚህም እዚያ የሚታዩ ችግሮች የትላንት የሴራ ፖለቲከኞች እና ለውጡ መጣብን በሚሉ ኃይሎች የተቀበረ ፈንጅ እንደሆነ ሃቅ ነዉ።

ሰላም የሁሉ መሠረት ነውና ሰላማችንን እንጠብቅ፣ ባህላዊ ዕሴቶቻችን የማንነታችን መገለጫዎችና የቀደምት ወገኖቻችን ውድ ስጦታዎች ናቸውና እንከባከባቸው፣ ለትውልድም እናሻግራቸው፤ የቤተሰብ፣ የአካባቢያችንን ብሎም የአገራችንን ሰላምና ደህንነትን ከወጣቶችና ከአባቶቸቻችን ጋር በጋራ እንጠብቅ፣ ያላወቅነውን ለማወቅ፣ ያወቅነውን በጎ ነገር ለሌሎቸ ለማሳወቅ እንትጋ፣ አካባቢያችንን ብሎም አገርን ለማልማትና ወደ ብልፅግና ማማ ለማውጣት ተግተን እንሥራ የሚለው ዋነኛ መልዕክቴ ነው፡፡

የምንጽፋቸው፣ የምንናገራቸውና በሌሎች የተግባቦት ዘዴዎች የምናሰራጫቸው መረጃዎች ከአሉባልታ ይልቅ ጀግንነታችንን፣ ልማታችንን፣ የሐገራችንን ሉአላዊነት፣ የህዝባችንን አንድነትና ብሩህ ተስፋችንን የሚያጎሉ ሊሆኑ ይገባል፡፡

የብሔር፣ የሀይማኖትና የፖለቲካ ጽንፈኝነትን በመቃወም አንዳችን ለአንዳችን ዋልታ እና ማገር፤ ድርና ማግ መሆን ያስፈልጋል። ሀገራችን አንድ ብቻ ናት፥ ለሁላችንም ትበቃለች። ስለዚህ የሠላም ጉዳይ የእኔ፣ ያንተ፣ ያንቺ፣ የሁላችንም ጉዳይ መሆን አለበት፡፡

በረመዳን ወር መላው ህዝበ ሙስሊሙ ያሳየው መደጋገፍ፣ መጠያየቅ፣ ፍቅርና ትህትና በቀጣይ ጊዜያት በመድገም ሀገራችን የጀመረችው የብልፅግና ጉዞ እውን እንዲሆን የበኩላችሁን ሚና በመጫወት አርአያነታችሁን እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ አደራ እላለሁ።

በድጋሚ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ እህት ወንድሞቸ እንኳን አደረሳችሁ፡፡

ኢድ- ሙባረክ!

ዮሐንስ በየነ
የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!

22/04/2022

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!- አቶ ዮሐንስ በየነ

የተወደዳችሁ መላው የሀገራችን ሕዝቦች!!

የተወደዳችሁ መላው የዞናችን ህዝቦች!

በጾምና በጸሎት ስለራሳችሁና ስለአገራችሁ ብሎም ለዓለም ሰላም ከፈጣሪ ጋር በመገናኘት ካሳልፋችሁ በኃላ እንኳን ለዚህች ለተቀደሰች ቀን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

የትንሳኤ በዓል ጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤዛነቱ ለሰው ልጆች ጥልቅ ፍቅሩን የገለጸበት የፍቅር ተምሳሌት በመሆኑ አርያነቱን ተከትለን አንድነታችንንና ህብረታችንን ይበልጥ ልናጎለብት እንደሚገባ በዚህ አጋጣሚ ላሳስባችሁ እፈልጋለሁ።

ኢትዮጵያን ብሎም አከባቢያችን ወደ ብልጽግና ማማ ላይ ማውጣት የምንችለው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በእኩልነት፣ በፍቅር፣ በወንድማማችነት ተከባብረው፣ ተፈቃቅደው እና ተዋድደው መትጋት ሲችሉ ብቻ ነው፡፡

በክርስቶስ የማዳን መንገድ የአዳም ዘር በሙሉ ለደስታ ቢታጭም እንደ ይሁዳ ያሉት በመንገዱ ተሸንፈው ስለወደቁ የድሉ ባለቤት አልሆኑም። ስለዚህ የተስፋ መንገዳችን በስኬት እንዲቋጭ ዛሬም ሆነ ነገ ፈተናውን በድል መወጣት ይኖርብናል። በየመንገዳችን የሚገጥሙን ፈተናዎች ወደ ተስፋ መሻገሪያ በሮቻችን ናቸው፡፡

የፋሲካ በዓል ጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጥል ግድግዳን በማፍረስ እርቅ ያወረደበት የእርቅና የሰላም በዓል በመሆኑ ከዚህ በዓል ብዙ የምንማርበት ነው፡፡

የዘንድሮን የፋሲካ በዓል ስናከብር የበደሉህንን ይቅር በማለት አብሮ ማዕድ መጋራት፣ የመንፈስ ጥንካሬን በመገንባት መሆን ይገባል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ የያዛቸው አቋሞች ህዝባችንን በማህበራዊ፤ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ተጠቃሚ ለማድረግና በጥቂት ጊዜ ውስጥ ባስመዘገባቸው ሀገራዊ የለውጥ ድሎችን ማስቀጠልና መተግበር የሁላችንንም ጥንካሬ ይፈልጋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ 1ኛ ጉባኤ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ዙሪያ ህዝቡ የተለያዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ማንሳቱ ይታወሳል፡፡

ለዚህም የህዝባችንን መሠረታዊ ጥያቄዎችን ለመመለስ የ90 ቀናት ዕቅድ ታቅደው ምላሽ እንዲያገኙ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ በዚሁ አጋጣሚ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ!

ከቃል ባለፈ ሁላችንም እንደ አንድ ልብ መክረን እና እጅ ለእጅ ተያይዘን ለተግባራዊነቱ መትጋት ይኖርብናል።

ህብረ ብሔራዊነት ልዩነቶችንና የሚከፋፍሉ፣ የሚያጣሉ ሁኔታዎችን ከማጉላት ይልቅ የሚያቀራርቡና የሚያስተሳስሩንን እውነታዎች በማጉላት፣ ከትናንትና ይልቅ ዛሬና ነገ ላይ ማተኮርና መጠንከር ያስፈልጋል፡፡

ቀጥ ያለ ብረት ዉሃ ዉስጥ ሆኖ ሲታይ የተጣመመ መስሎ ይገኛል፡፡ የብረቱን መጣመም የሚፈጥረው የሰዎች የእይታ ግድፈት ነው፡፡ ስለዚህ የእይታ አድማሳችንን በማስፋትና አመለካከታችንን በማስተካከል ለአንድ ዓላማ መቆም አለብን፡፡

የተከበራችሁ የዞናችን ህዝቦች፡- በዞኑ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍንና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጠናከር ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ በሰላም እንዲገባ ድርሻችሁን እንዲትወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

መረዳዳትና መደጋገፍ የብልፅግና አንኳር እሴት ነው! ስለዚህ በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትንና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖቻችን በመርዳት፣ በመተሳሰብ፣ በይቅር-ባይነት፣ በመግባባት፣ በወንድማማችነትና በአብሮነት መንፈስ ልናከብር ይገባል፡፡

በድጋሚ የዘንድሮ የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል ለሁሉም የክርስትና እምነት ተከታዮች የሰላም፤ የፍቅርና የደስታ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡

ዮሐንስ በየነ
የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

ነጻነታችንን በአግባቡ እንጠቀም፤ አለበለዚያ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል!ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለማስከበር የህግ ጥሰቶች እንዳይኖር የሌሎች ሰዎች መብት ማክበር አለብን። መብትና ግደታው ከኃላፊ...
20/04/2022

ነጻነታችንን በአግባቡ እንጠቀም፤ አለበለዚያ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል!

ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለማስከበር የህግ ጥሰቶች እንዳይኖር የሌሎች ሰዎች መብት ማክበር አለብን። መብትና ግደታው ከኃላፊነት ጋር የሚመጣ ጉዳይ ነው። ስንታሰር በግፍ ታስራያለሁ ከማለታችንን ይልቅ ነገሮችን በሴከነ መንግድ የህዝባችንና ሀገራችን ህልውና አደጋ ላይ ከሚጥሉ ጉዳዮች መቆጠብ አለብን።

መንግስት ከመሬት ተንስቶ ማንንም ዝም ብሎ አላሰረም። ወንጀል ሰርቶ ከክልል ጥያቄ ጋር አገናኝቶ ማውራት ተገቢነት የለውም። ወላይታ ክልል እንዲሆን የሚቃወም ወላይታ የለም። ከዚህ ውጪ የሚደረግ ጨኸት ተቀባይነት አይኖርም።

ከጭፍን ጥላቻ ወጥተን ለህዝባችን የሚጠቀሙና ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ፍጹም ሰላማዊና ህዝባዊ በሆኑ መንገድ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል፡፡

በሀሰተኛ አካውንት ተደብቀህ ስለጻፍክ ከህግ ጥላ ስር ማምለጥ አትችልም።

ማህበራዊ ሚዲያ የራሱ የሆኑ ህጎች አሉ፡፡ የጥላቻ ንግግር በአዋጁ ቁጥር 11/85 መሠረት በህግ ተጠያቂ ያስደርጋል፡፡

በየአከባቢው ህብረተሰቡን የሚሸብሩ ግለሰቦችን ህዝቡ ለይተው ያዉቃል፡፡ ስለዚህ ነጻነታችንን በአግባቡ እንጠቀም፤ አለበለዚያ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላልና፡፡ መብትና ግደታችንን ለየትን መጠቅም አለብን፡፡

Address

Wolaita
S**o

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when World News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Nearby media companies