Tare Sport

Tare Sport አዳዲስ ስፖርታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ከፈለጉ Groupን ይቀላቀሉ

ወላይታ ድቻ በሙሴ ቱሳ ካፍ ላይ ድንቅ ብቃት ያሳዪት ሁለት ድንቅ ተጨዋቾች የግሉ አድረገዋል።ብስራት በቀለበረከት ተሾመእንኳን ደስ አላችሁ ወንድሞቼስለ እናንተ በጣም ደስ ብሎኛልTere M
16/08/2023

ወላይታ ድቻ በሙሴ ቱሳ ካፍ ላይ ድንቅ ብቃት ያሳዪት ሁለት ድንቅ ተጨዋቾች የግሉ አድረገዋል።
ብስራት በቀለ
በረከት ተሾመ
እንኳን ደስ አላችሁ ወንድሞቼ
ስለ እናንተ በጣም ደስ ብሎኛል
Tere M

በዲቻ_ቤት_ያለውን_የአጥቂ_መስመር_ችግር ይቀርፋል_የሚል_አስገራሚ_መልክት_ለወላይታ_ዲቻ_አሰልጣኝ_ለያሬድ_ገመቹ...........................የቀድሞ_የመከላከያ_እና_አሁኑ_ደሞ_ቤ...
08/08/2023

በዲቻ_ቤት_ያለውን_የአጥቂ_መስመር_ችግር ይቀርፋል_የሚል_አስገራሚ_መልክት_ለወላይታ_ዲቻ_አሰልጣኝ_ለያሬድ_ገመቹ...........................

የቀድሞ_የመከላከያ_እና_አሁኑ_ደሞ_ቤንቺ ማጂ_ቡና_አጥቂ_ከፍተኛ_ጎል_አስቆጣሪ_ለሆነው ዘላለም_በየነ_ዕድል_በመስጠት_እንድታይልን።
👉እነሆ እግር ኳስን የህይወቱ አንድ አካል አድርጎ የጀመረው ተጨዋች ወይም #ዞላ በመባል ይታወቃል፣ ተወልዶ ያደገው በወላይታ ዞን አረካ ከተማ፣ወደ ኳስ ህይወት የገባው በልጅነቱ ከሰፈር ክለብ ሲሆን ከልጅነቱ ጀምሮ በኳስ የሚያሳየው የኳስ ችሎታው ለተመልካች አስደማሚ እና ዉብ እንደነበረ የቀድሞ የአረካ ከነማ ተጨዋቾች ይመሰክሩለታል።

👉ዘላለም በየነ/"Zola" በአሁኑ ሰዓት ለቤንቺ ማጂ ቡና ክለብ እየተጫወተ ይገኛል፣በዘንድሮም ወድድር ዘመን በክለቡ ደረጃ ከፍተኛ ጎል በማስቆጠር ለክለቡ ጥሩ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።ዘላለም በየነ"Zola" ለኳስ እና ለኳስ ብቻ የተፈጠረ ተጨዋች ነው ይህን ያልኩት ምክንያት በሜዳው በሚያሳየው ችሎታ እና ብቃት ነው፣ ሁሉም ቦታ ይገኛል፣ድካም በጭራሽ አይሰማውም...........................

ዘላለም_በየነ_ወይም_ዞላ_ከዚህ_በፊት:-
✔ለአረካ ከነማ/በብሔራዊ ሊግ/
✔ለኢትዮጵያ መከላከያ ክለብ /ፕሪሚየር ሊግ/
✔ለጋሞ ጨንቻ/ከፍተኛ ሊግ/
✔ለቤንቺ ማጂ ቡና/ከፍተኛ ሊግ/ አሁን እየተጫወተ ይገኛል።

👉ዘላለም በየነ/Zola" ምኞቱ የኢትዮጵያን እግር ኳስ ከፍ ማድረግ እና የኢትዮጵያ በሔራዊ ቡድን በመቀላቀል በሔራዊ ቡድናችንን በአለም ደረጃ ተፎካካሪ ቡድን ማድረግ ነው።
👉ዘላለም በየነ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የማይመጥን ተጨዋች ነው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ካሉ ተጨዋቾች ጋር በአቋም እና በችሎታ በቦታው ለእኔ ተሽሎ ወይም በልጦ ይገኛል፣፣ ስለዚህ ይህን ታዳጊ ተጨዋች በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በቅርቡ እንደማየው ተስፋ እናደርጋለን ።

ይህን መልክት ለአሰልጣኙም ሆነ ለሚመለከተው አካል እንድደርስ ሼር ሼር አድርጉት 🙏🙏🙏🙏
Tere Negn❤️

ይህንን ብሏቹህ ሄዷል!!ዴህያ 🗣️ ለመላው የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች የማስተላልፈው የስንብት መልእክቴ ይህ ነው።ላለፉት 12 ዓመታት ላሳያቹህኝ ፍቅር ያለኝን ከፍ ያለ ምስጋናና አድናቆት...
08/07/2023

ይህንን ብሏቹህ ሄዷል!!

ዴህያ 🗣️ ለመላው የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች የማስተላልፈው የስንብት መልእክቴ ይህ ነው።

ላለፉት 12 ዓመታት ላሳያቹህኝ ፍቅር ያለኝን ከፍ ያለ ምስጋናና አድናቆት መግለጽ እፈልጋለሁ።

ውዱ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ወደዚህ ክለብ ካመጡኝና ይህን ማልያ እንድለብስ እድል ከሰጡኝ በኋላ ብዙ ስኬት አጣጥሜያለሁ።

ይህንን ማልያ በለበስኩ ቁጥር የማይታመን ኩራት ይሰማኛል። በአለም ላይ ትልቁ ክለብ የሆነውን ይህንን ክለብ መወከል ለጥቂት እድለኛ እግር ኳስ ተጫዋቾች ብቻ የተሰጠ ክብር ነው።

እዚህ ከመጣሁበት ጊዜ ጀምሮ የማይረሳ እና የተሳካ ጊዜ አሳልፌያለሁ፣ አሁን አዲስ ፈተና ለመጋፈጥ፣ እራሴን በአዲስ ቦታ፣ በአዲስ ጅምር ለመፈተን ትክክለኛው ጊዜ ነው።

ማንቸስተር ቀርጾኛል አይተወኝም፣ ይህ ክለብ፣ ኦልድትራፎርድና አስደናቂ ደጋፊዎቹ ለዘለዓለም በልቤ ይኖራሉ።

በማንችስተር ዩናይትድ ሁሉንም አይቻለሁ፣ ሰላም ሁኑ 🙏

✍️ Tare M

 #የሚማር ካለ  #መማሪያ ሞልቷልበጎረቤት ኬንያ የታዬ ጥግ የደረሰ ሩህሩህነት❤በኤሌክትሪክ እንጨቱ ላይ የምታይዋት ግንደ ቆርቁር ወፍ  ገና መብረር ያልጀመሩ ልጆች ያሏት አራስ ናት። የኤሌክ...
21/05/2023

#የሚማር ካለ #መማሪያ ሞልቷል

በጎረቤት ኬንያ የታዬ ጥግ የደረሰ ሩህሩህነት❤

በኤሌክትሪክ እንጨቱ ላይ የምታይዋት ግንደ ቆርቁር ወፍ ገና መብረር ያልጀመሩ ልጆች ያሏት አራስ ናት። የኤሌክትሪክ ምሰሶዉን ቆርቁራ በሰራችዉ ጎጆ ለአመታት ኖራለች። ......
ከእለታት በአንዱ ቀን የኬንያ መብራት ሀይል መስሪያ ቤት ይህን ያረጀ ምሰሶ በኮንክሪት ለመቀየር ፈልጎ ሰራተኞቹን ይልካል። ሰራተኞቹ አገር አማን ብለዉ የተለመደ ስራቸዉን ይጀምራሉ። ያረጀዉ ምሰሶ መዝመም ሲጀምር ፡ አንዲት ወፍ በመዉደቅ ላይ ካለዉ ምሰሶ የሆነ ክፍል አፈትልካ ትወጣለች።

ሰራተኞቹ አላስተዋሏትም ነበርና ስራቸዉን ቀጥለዋል። ወፏ ግን ከዚያ አካባቢ መራቅ አልሆነላትም ነበርና ከወዲያ ወዲህ ትቅበዘበዛለች። በመጨረሻም ወፏ የፈራችዉ ደረሠ ሰራተኞቹ አሮጌዉን ምሰሶ ነቅለው መሬት ላይ ጣሉት። የወላድ አንጀቷ ያንሰፈሰፋት አራሷ ወፍ ትጮኻለች ግና በዚያ አካባቢ ወፍኛ ቋንቋ የሚሠማ አልነበረምና ትኩረት የሠጣት አልነበረም። በዚህ መሃል የሠራተኞቹን ቴኩረት የሳቀ አንድ ነገር ተከሰተ ወፏ ስትበር መጥታ በወደቀዉ ምሰሶ የሆነ አረፈችበት። በሁኔታዉ የተገረሙት ሰራተኞች ቀርበው ሲያዩ ተቆርቁሮ በተሰራው የወፍ ቤት ውስጥ ጫጩቶችን ተመለከቱ።

የመብራት ሀይል ሰራተኞቹ ልብ ይገርማል በሆነዉ ነገር አዘኑ። እናም ወፏን መጠለያ ማሳጣትም ሆነ ቤተሰቧንም መበተን አግባብ እንዳልሆነ በማመን ከረዥሙ የመብራት ምሰሶ ላይ የወፏ ቤት ያለበትን ክፍል ቆርጠው በምስሉ በምታዩት መልኩ አዲስ የተከሉት የኮንክሪት ምሰሶ ላይ አጣብቀዉ አሰሩት። አራሷ ወፍ ከነቤተሠቦቿ ቀሪ ጊዜያቸዉን በሰላም እንዲኖሩ ተዋቸዉ።

እና ምን ለማለት ፈልጌ ነዉ........🤔

#የሚማር ካለ #መማሪያ ሞልቷል
Tere Negn

 ።የቤትኪግ የኢትዮጵያ ፕሪየሚየር ሊግ 2015 መርሃግብሮች ከነገ ቅዳሜ ሚያዚያ 28 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 27ኛ ሳምንት መርሃግብር ድረስ በሐዋሳ ዮኒቨርስቲ ስታድየም መደረግ እንደሚጀም...
06/05/2023



የቤትኪግ የኢትዮጵያ ፕሪየሚየር ሊግ 2015 መርሃግብሮች ከነገ ቅዳሜ ሚያዚያ 28 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 27ኛ ሳምንት መርሃግብር ድረስ በሐዋሳ ዮኒቨርስቲ ስታድየም መደረግ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ፕሪየሚር ሊግ አክሲዮን ማህበር ይፋ አድርጓል።
ክለባችን ወላይታ ድቻም ከ23ኛው ሳምንት መርሃግብር ጀምሮ አስከ 27ኛው ሳምንት መርሃግብር ድረስ የሚያደርጋቸውን ወሳኝ ጫውታዎች በሐዋሳ ዮኒቨርሲቲ ስታድየም በበርካታ የጦና ንቦቹ ደጋፊዎች ታጅቦ የሚከውን ይሆናል።
💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
💚💚💚💚💚🐝🐝 ድል ለጦና ንቦች 🐝🐝💚💚💚💚💚

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ድቻ ለገጣፎ ለገዳዲን አሸነፈ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ስንታየሁ መንግስቱ በ37ኛው እንዲሁም አበባየሁ አጂ...
01/05/2023

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ድቻ ለገጣፎ ለገዳዲን አሸነፈ

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ስንታየሁ መንግስቱ በ37ኛው እንዲሁም አበባየሁ አጂሶ በ49ኛው ደቂቃ ለወላይታ ድቻ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ ነጥቡን ወደ 30 ከፍ ቢያደርግም ተመሳሳይ ነጥብ ባለው ፋሲል ከነማ በግብ ክፍያ ተበልጦ በነበረበት 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በአንጻሩ ለገጣፎ ለገዳዲ በ11 ነጥብ የመጨረሻውን 16ኛ ደረጃ ይዟል።

በ22ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ-ግብር ፋሲል ከነማ ከሀዲያ ሆሳዕና ከምሽቱ 12 ሰአት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
Tere Negn

17/04/2023

Who hasn't cried after watching this video?😥😥😥
🙏💖 Please do not pass without seeing💖🙏

ልጅ ወደ መቃብር ሄዶ የትምህርት ቤቱን ቦርሳ በእናቱ መቃብር ላይ ጣለው እና በስሜት እያለቀሰ እንዲህ አለ፡-- እማ ፣ በቂ እንቅልፍ ተኝተሻል ፣ ነቅተሽ ነገ ከእኔ ጋር ወደ ትምህርት ቤት ...
14/04/2023

ልጅ ወደ መቃብር ሄዶ የትምህርት ቤቱን ቦርሳ በእናቱ መቃብር ላይ ጣለው እና በስሜት እያለቀሰ እንዲህ አለ፡-
- እማ ፣ በቂ እንቅልፍ ተኝተሻል ፣ ነቅተሽ ነገ ከእኔ ጋር ወደ ትምህርት ቤት እንሂድ እና ለጠየቀኝ ለአስተማሪው መልስ ስጪ ፥
- እናትህ በጣም ቸልተኛ ነች፣ ያለ ምሳ እቃ ወደ ትምህርት ቤት ትልክሃለች፣ ጥሩ አለባበስ አታለብስህም ንጽህናህን እንኳን አጠብቅም እና የቤት ስራም
አትረዳህም።
ህይወት አንድ አይነት አይደለም አንደበታችንን እንቆጥብ ፣ ከመናገራችን በፊት እናስብ።
ክብር ለእናቶች !

  ✝️የጥያቄና የትምህርት ቀን✝️ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰኞ ባደረገው አንጽ ሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት ሹመትን ወይንም ስልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን ስለ ስልጣኑ በጻህፍት...
11/04/2023



✝️የጥያቄና የትምህርት ቀን

✝️ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰኞ ባደረገው አንጽ ሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት ሹመትን ወይንም ስልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን ስለ ስልጣኑ በጻህፍት ፈሪሳዊያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል በዚህም እለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሰቀሉ አስቀድሞ ለመጨረሻ ጊዜ አስተማረ

✝️ደቀ መዛሙርታቸውንም ከሔሮድስ ወገን ጋር ላኩበት እነርሱም መምሕር ሆይ እውነተኛ እንደሆንህ በእውነትም የእግዚአብሔርን መንገድ እንደምታስተምር እናውቃለን ለማንም አታደላም የሰውን ፊት አትመለከትምና እንግዲህ ምን ይመስልሀል ንገረን ለቄሳር ግብር መስጠት ተፈቅዷል ወይስ አልተፈቀደም አሉት

✝️ኢየሱስም ክፋታቸውን አውቆ እናንተ ግብዞች ስለ ምን ትፈትኑኛላችሁ አላቸው የግብሩን ብር አሳዩኝ አላቸው እነርሱም ዲናር አመጡለት እርሱም ይህች መልክ ፅሕፈቲቱስ የማን ናት አላቸው የቄሳር ነው አሉት በዚያን ጊዜ እንኪያስ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር አስረክቡ አላቸው ማቴ 22:16-22

✝️አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰሙነ ህማማቱን በሠላም አስፈፅሞ ለብርሐነ ትንሣኤው ያድርሰን "አሜን"

👉ሠናይ ቀን
Negn

ይህ የምታዩት የቤልጂየምና የኔዘርላንድ ድንበር ነው! ከመስመሮቹ ወደዚህ ቤልጂየም ከመስመሮቹ ወደዛ ደግሞ ኔዘርላንድ! ወታደር የለም! ታንክ የለም! መትረየስ የለም!..የሰው ልጅ እንዲህ ሰል...
31/03/2023

ይህ የምታዩት የቤልጂየምና የኔዘርላንድ ድንበር ነው! ከመስመሮቹ ወደዚህ ቤልጂየም ከመስመሮቹ ወደዛ ደግሞ ኔዘርላንድ! ወታደር የለም! ታንክ የለም! መትረየስ የለም!..
የሰው ልጅ እንዲህ ሰልጥኖ ድንበሩን በነጭ ቀለም ብቻ በሚያሰምርበት በዚህ ዘመን አንተ የገዛ ወንድምህን በክልሌ አትማርም እያልክ ስትሰግጥ ትውላለህ።
Tere Negn

✍️የ12ኛው ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ ወላይታ ዲቻ ከሲዳማ ቡና ጋር ነገ እሁድ ጥሪ 28 2015ዓ.ም በ9:ዐዐ ሰዓት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲ...
04/02/2023

✍️የ12ኛው ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ ወላይታ ዲቻ ከሲዳማ ቡና ጋር ነገ እሁድ ጥሪ 28 2015ዓ.ም በ9:ዐዐ ሰዓት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም ይፋለማሉ!!!

✍️በአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም የሚመራው ወላይታ ዲቻ ከጉዳት ጋር በተያያዘ ከሁለቱ ተከላካዮች አንተነህ ጉግሳ እና ደጉ ደበበ ወጭ ለሎች ተጨዋቾች በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ።

✍️በየሳምንቱ ከቡድናቸው ጎን በመሆን ክለቡን ሲያበረታቱ የሚታዩት የወላይታ ዲቻ የልብ ደጋፊዎች ለነገው ፍልሚያም በተለየ መልኩ ከንቦቹ ጎን ሆነው ድል ለማስመዝገብ ዝግጅቻቸውን አጠናቋል።

ልብ ይበሉ!

ወላይታ ዲቻ🐝 ከ ሲዳማ ቡና☕️
📆ነገ እሁድ ጥሪ 28/2015 ዓ.ም
⏰ከቀኑ 9:00 ሰዓት
🏟️በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታድየም
🙏ኑናራ ዲያጌ ኡባ ጦኒያጋ💪ድል ለወላይታ ዲቻ/ለጦና ንቦቹ🐝
💖Tere Negn💖

👀👀👀የጥር የዝውውር መስኮት ዛሬ ይጠናቀቃል እኛም በመጨረሻ ቀን የተሰሙ ሊጠናቀቁ የደረሱ የዝውውር ወሬዎችን እናቀርብላቹሀለን 👉በርንማውዝ ዩክሬናዊውን የመሀል ተከላካይ ኢሊያ ዛባርኒን ከዲና...
31/01/2023

👀👀👀የጥር የዝውውር መስኮት ዛሬ ይጠናቀቃል እኛም በመጨረሻ ቀን የተሰሙ ሊጠናቀቁ የደረሱ የዝውውር ወሬዎችን እናቀርብላቹሀለን

👉በርንማውዝ ዩክሬናዊውን የመሀል ተከላካይ ኢሊያ ዛባርኒን ከዲናሞ ኪዬቭ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል ዝውውሩ በቀጣይ ሰአታት ይጠናቀቃል የህክምና ምርመራ ለማድረግ እና ዝውውሩን ዛሬ ለመጨረስ ወደ እንግሊዝ ይበራል

👉ዩኒየን በርሊን ኢስኮን በነፃ ዝውውር ሊያስፈርም ነው ስምምነቱን ለማጠናቀቅ እና የሕክምና ሙከራዎች ለማድረግ ዛሬ ቀጠሮ ተይዞለታል ኢስኮ ከተለያዩ ክለቦች የመጡለትን ብዙ ጥያቄዎችን ካየ በኋላ ምርጫውን ጀርመን አርጓል

👉ፒኤስጂ እና ቼልሲ በሃኪም ዚያች ዝውውር ጉዳይ አሁንም እየተወያዩ ነው በሁለቱ ክለቦች መካከል እስካሁን ምንም አይነት ስምምነት የለም ዚያች ፒኤስጂ ለመቀላቀል ተስፋ አድርጓል ቀድሞውንም ጥያቄያቸውን ተቀብሏል ግን ዛሬ በመጨረሻ ሰአት ንግግሮች ቀጥለዋል

👉ፔድሮ ፖሮ "ለስፖርቲንግ አመስጋኝ ነኝ ክለቡን እወዳለሁ ሁልጊዜ ክለቡን አመሰግናለሁ ፖሮ ወደ ቶተንሀም ሚያደርገው ዝውውር ተረጋግጧል

👉ሌስተር ሲቲ የ21 አመቱን አጥቂ ናታን ኦፖኩን ከዩናይትድ ስቴትስ ሲራኩስ ዩኒቨርስቲ ማስፈረሙን ይፋ አርጓል

👉ኖቲንግሃም ፎረስት ቢያንስ ሁለት ተጨማሪ ፊርማዎችን ዛሬ ሊያሳውቁ ነው ሼልቪን ከኒውካስትል ማስፈረማቸውንም አረጋግጠዋል ሌላኛው ፈራሚ ፌሊፔ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ነው

👉ሌስተር አሁንም ድርድሩን ከሊድስ ጋር ሲቀጥል ጃክ ሃሪሰንን ለማስፈረም እየጣሩ ነው ስምምነቱ ሚወሰነው ሊድሶች አዲስ ተጫዋች ዛሬ ሚያስፈርሙ ከሆነ ብቻ ነው

👉ባርሴሎና ስፖርቲንግን የሚቀላቀለውን ቤለሪን ለመተካት ጁሊያን አራውጆን ለማስፈረም ለኤልኤ ጋላክሲ ለማስፈረም ይፋዊ ፕሮፖዛል አቅርቧል ባርሳ የብድር ክፍያ እና የግዢ አማራጭ አንቀጽ አቅርቧል ተጨዋቹ ባርሳን መቀላቀል ይፈልጋል

👉ማርኪንሆስ አርሰናልን ለቆ ኖርዊች በውሰት ውል እስከ የውድድር አመቱ መጨረሻ ተቀላቅሏል

👉ፓትሪክ ቫን አንሆልት ወደ ፒኤስቪ አምርቷል ተጨዋቹ አሁን ጋላታሳራይን ለቆ ለህክምና ምርመራ ወደ ሆላንድ አምርቷል ዝውውሩ አልቋል

👉የባርሴሎና የመክፈቻ ፕሮፖዛል ለሶፊያን አምራባት አቅርበዋል ጥያቄው የውሰት ነው የውሰት ክፍያው ወደ €3/4m ቢጠጋም ፊዮረንቲና ጥያቄውን ውድቅ አድርገዋል

👉አትሌቲኮ ማድሪድ ማት ዶሄርቲን ከቶተንሃም በውሰት ውል ለማስፈረም ተዘጋጅተዋል ንግግሮች ቀጥለዋል ስምምነቱ ላይ የመግዛት አማራጭ የለም ዝውውሩ በቀጣይ ሰአታት ውስጥ ይጠናቀቃል

👉ጆአዎ ካንሴሎ የህክምና ምርመራ ካጠናቀቀ በኋላ ኮንትራቱን ፈርሟል ከማንቸስተር ሲቲ ጋር በተደረገው ስምምነት €70m የግዢ አማራጭን ያካትታል

👉አሁንም በኤንዞ ፈርናንዴዝ ላይ ላይ ምንም ለውጦች የሉም ነገሮች እንዳሉ ናቸው ከቤንፊካ ምንም አረንጓዴ መብራት የለም ቼልሲዎች አሁንም እየሞከሩ ነው €120m ለመክፈል ዝግጁ ናቸው ነገር አዲስ ነገር የለም

👉አርሰናል እና ቼልሲ የጀርጊንሆ ውል በማዘጋጀት ላይ ናቸው ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በይፋ ይፈርማል የመጨረሻውን ክፍያ £10m እና £2m ሲሆን ሁሉም ነገር ተጠናቋል

👉ክሪስታል ፓላስ አልበርት ሳምቢ ሎኮንጋን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል ዝውውሩም እስከ ሰኔ ድረስ በውሰት ሲሆን ንግግሮች እየተካሄዱ ነው የመጨረሻ ውሳኔ የአርሰናል እና ተጫዋቹ ነው ተጨዋቹ ወደ ፓላስ የሚያመራበት እድል ሰፊ ነው

👉ሊድስ ዩናይትድ ኒኮሎ ዛኔሎን ከሮማ በውሰት ለማስፈረም በቅርብ ሰአታት ሞክረዋል ጥያቄውን ሮማዎች አልተቀበሉትም

👉ኖቲንግሃም ፎረስት ለኬይለር ናቫስ ጥያቄ አቅር

 #ክርስቲያን ኤሪክሰን ከጫወታው መጠናቀቅ በኃላ በክራንች ነበር ከኦልትራፎርድ የወጣው በተለይ አንዲ ካሮል የገባበት ታክል ከባድ ነበር የጉዳቱ መጠን ያልተገለፀ ቢሆንም ለዚህ ተጠያቂው ኤሪክ...
29/01/2023

#ክርስቲያን ኤሪክሰን ከጫወታው መጠናቀቅ በኃላ በክራንች ነበር ከኦልትራፎርድ የወጣው በተለይ አንዲ ካሮል የገባበት ታክል ከባድ ነበር የጉዳቱ መጠን ያልተገለፀ ቢሆንም ለዚህ ተጠያቂው ኤሪክ ቴንሀግ ነው በተለይም በማታው ጫወታ ለክርስቲያን ኤሪክሰን ከእድሜው አንፃር እና ከጤናው ሁኔታ አንፃር እረፍት ሰጥቶት ጫወታውን በፍሬድ መጀመር ይችል ነበር
💖Tere Negn💖

  ✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥ፕትርክና አይገባኝም ስላሉ ብቻ መንበራቸውን ጥለው እንዳይሄዱ በወታደር ይጠበቁ የነበረት ከወላይታ የተገኙት ወላይተኛ ተናጋሪው ቅዱስ ፓትርያሪክ***የቀደመው ስማቸው አ...
24/01/2023


✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥

ፕትርክና አይገባኝም ስላሉ ብቻ መንበራቸውን ጥለው እንዳይሄዱ በወታደር ይጠበቁ የነበረት ከወላይታ የተገኙት ወላይተኛ ተናጋሪው ቅዱስ ፓትርያሪክ
***

የቀደመው ስማቸው አባ መልአኩ ይባላሉ። ምንም እንኳን ውልደታቸው በጎንደር ጋዢን በምትባል ስፍራ ቢሆንም ረጅም ዕድሜያቸውን ያሳለፉት እና አብረው የኖሩት ማህበራዊ ስነልቦና ወላይታ ምድር ላይ ነው።

ከሀገሬው በላይ ወላይተኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ። ከውልደት ስፍራቸው በቀር አኗኗር እና አዋዋላቸው ሙሉ በሙሉ ከአንድ ወላይታ ገበሬ የተለየ አልነበረም።

የመጽሐፍት ትርጓሜ በእዚሁ በወላይታ ምድር ባሉ ጉባኤ ቤቶች አጠኑ።ስርዓተ ገዳም ከተማሩ በኃላ በእዚያው ወላይታ በሚገኘው ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖ ገዳም መኖከሱ። የብህትህና ህይወታቸው በወላይታ ምድር ጀመሩ።

ከ1926-1968 ለ42 ዓመታት ወላይታ ላይ በወላይተኛ እና አማረኛ ቋንቋ ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽመው ከ300,000 በላይ ኢ- አማንያንን እንዳስጠመቁ እና ከ65 በላይ አብያተክርስቲያናትን አሳንጸዋል።

የደርግ መምጣትን ተከትለ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን 2ኛው ቅዱስ ፓትርያሪክ የነበሩት ብጽኡ አቡነ ቴዎፍሎስን ተገደሉ።

በመሆኑም 3ኛው ቅዱስ ፓትርያሪክ ለመምረጥ 909 አከባቢያቸውን የሚወክሉ አባቶች ተሰባሰቡ። ከ565 ወረዳዎች ለማዕረገ ፕትርክና መንፈስቅዱስ የሚመርጠውን አባት ይገኝ ዘንድ ሁለት ሁለት ተወካይ ተላከ።

ገና ማዕረግ ጽጽስና ያልተቀበሉት በቁምስና ያሉት መኖክሴው የወላይታው አባት የሆኑት አባ መላእኩ ከወላይታ "ተወካይ ሆኜ አልሄድም" እያሉ በጭቅጭቅ በገዳሙ አባቶች እና ውግዘት የወላይታ አውራጃን ወክለው ተላኩ።

ገና ማዕረግ ጽጽስና ሳይቀበሉ በቁምስና ማዕረግ መሆናቸው ደግሞ ለዬት ያደርገዋል።

በስተመጨረሻም የመጨረሻው 5 ዕጩ ውስጥ ስማቸው ተካተተ። ከአንድ ቆሞስ እና ከሶስት ሊቃነጳጳሳት ጋር ለ3ተኛው የፕትርግና አገልግሎት ለውድድር ተቀመጡ።

ከየወረዳው ለመጡት ለመራጩ ተወካዮችም

>

ብለው ለጉባኤው በተደጋጋሚ እየጮኹ ቢነግሩም ሰሚ አጡ።

በስተመጨረሻም ከሊቃነጳጳሳት ጋር ተወዳድረው በአብላጫ ድምጽ መኖክሴው መናኝ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን 3ኛው ፓትርያሪክ ሆነው ተመረጡ።

በ1968 ሐምሌ ወር ላይ መዓረገ ጽጽስና ተቀብለው ከወር በኃላ በጉባኤው ምርጫ መሰረት" አባ ተክለሃይማኖት ሣልሳዊ የኢትዮጽያ ፓትርያሪክ" ተብለው ተሾሙ።

መንበራቸው ጥለው ሊሸሹ በተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርጉም የደርግ ወታደሮች እየያዟቸው መለሱ። በስተመጨረሻም መንበራቸውን ጥለው እንዳይሄዱ በመኖርያ ቤታቸው ጥበቃ ተመደበ።

ወዳጄ...መንፈስቅዱስ ሲመርጥ እንዲህ ነው። ዳዊትን ከእረኝነት ንጉስ ያደረገ አምላክ፣ሳሙኤልን ከመካኒቷ ማህጸን አውጥቶ ነብይ ብሎ የሾመ ጌታ፣ሙሴን ከውሃ ላይ ታድጎ ነጻ አውጭ አድርጎ የቀባ እግዚአብሔር ....ምርጫው ኮታ ሳይሆን ጸጋ ነው።

እግዚአብሔር ይመስገን !!!

💖Tere Negn💖

ኤሪክ ቴን ሃግ ለዮናይትድ እያደረገው ባለው ነገር አሁንም ቢሆን ለኔ እጅግ ድንቁ አሰልጣኝ ነው አምና ምን አይነት ቦታ ላይ እንደነበርን ማስታወስ ግድ ይለናል በቴን ሃግ የ 6 ወር ቆይታ ው...
23/01/2023

ኤሪክ ቴን ሃግ ለዮናይትድ እያደረገው ባለው ነገር አሁንም ቢሆን ለኔ እጅግ ድንቁ አሰልጣኝ ነው አምና ምን አይነት ቦታ ላይ እንደነበርን ማስታወስ ግድ ይለናል በቴን ሃግ የ 6 ወር ቆይታ ውስጥ ነገሮችን በምን ያህል ፍጥነት እንደተቀሩ እና የቴን ሃጉ ሰራዊት የሚከተለው ፍልስፍና ከጨዋታ ጨዋታ በሚገባ በደንብ እየተሻሻለ እንደመጣ በምንመለከታቸው ጨዋታዎች ውስጥ መመልከት ችለናል።
.. በቴን ሃግ ስር ዮናይትድ ከእዚህም በላይ የማድረግ አቅም አለው ቲሙ መሉ ለሙሉ ከቴን ሃግ ፍልስፍና ጋር Organized ከሆነ ፕላስ የሚፈልገውን ተጫዋች በቶሎ ከፈረመለት እጅግ የምንወደውን ዮናይትድ በቅርቡ እንመለከታለን።

GGMU🔴💪💖Tere Negn💖

ወንድሜ በእግር ኳስ አለም በእነዚህ ሁለት ነግስታት ስር በሀዘናቸዉ አዝነን ፣ በተደሰቱበት ሰአት ደግሞ እጅግ ተደስተን ዉብ ጊዜያትን አሳልፈናል ፤ ከእነርሱ በኋላ የሚመጡ በርካቶች ይኖራሉ ...
19/01/2023

ወንድሜ በእግር ኳስ አለም በእነዚህ ሁለት ነግስታት ስር በሀዘናቸዉ አዝነን ፣ በተደሰቱበት ሰአት ደግሞ እጅግ ተደስተን ዉብ ጊዜያትን አሳልፈናል ፤ ከእነርሱ በኋላ የሚመጡ በርካቶች ይኖራሉ ግን የእነዚህን ጫፍ እንኳን አይደርሱም።

በእግር ኳስ ዘመን እጅግ የታደልን የሁለቱን ጥበብ ፣ ሀያልነት ፣ ወኔ ፣ ቋሚ ብቃት ፣ ዉብ ግቦች ፣ በርካታ የደስታ መገለጫዎቻቸዉን የተመለከትን ፍጥረቶች ነን

እናመሰግናለን ❤️Tere Negn💖

Address


Telephone

+251928730796

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tare Sport posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tare Sport:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share