Wolaita Broadcasting Corporation - WBC

Wolaita Broadcasting Corporation - WBC NEWS

ቤተልሔም ወልዴ በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ሻምፒዮና ተጋጣሚዋን በበቃኝ አሸነፈች ሚያዝያ 9፣ 2016 ዓ.ም በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ካፕ ሻምፒዮና ከደቡብ አፍሪካ አቻዋ ጋር የተጋጠመችው...
18/04/2024

ቤተልሔም ወልዴ በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ሻምፒዮና ተጋጣሚዋን በበቃኝ አሸነፈች

ሚያዝያ 9፣ 2016 ዓ.ም በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ካፕ ሻምፒዮና ከደቡብ አፍሪካ አቻዋ ጋር የተጋጠመችው ቤተልሄም ወልዴ በበቃኝ አሸንፋለች፡፡

የመላው አፍሪካ ሻምፒዮኗ ቤተልሄም ወልዴ በሁለተኛ ዙር ላይ ተጋጣሚዋ ላይ ሀይለኛ ቡጢ በማሳረፍ ነው በዳኛ ውሳኔ ያሸነፈችው፡፡

በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያን የወከሉት አቡዱሰላም አቡበከር፣ አቡበከር ሰፋን እና ኤርሚያስ መስፍን በተጋጣሚዎቻቸው መሸነፋቸውን ከኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 #1,000,000.00ልማትን መደገፍ የማይሰለቸው፣ ታታሪዉ፣ ሁልጊዜ በወልማ እና ወላይታ ጎን ያለዉ ባለሀብቱ ያዕቆብ አልታዬ ሊቃ ድጋፍ ጠይቆ እንዴት መሰሰት ይቻላል!? በማለት እንደወትሮም...
04/04/2024

#1,000,000.00
ልማትን መደገፍ የማይሰለቸው፣ ታታሪዉ፣ ሁልጊዜ በወልማ እና ወላይታ ጎን ያለዉ ባለሀብቱ ያዕቆብ አልታዬ ሊቃ ድጋፍ ጠይቆ እንዴት መሰሰት ይቻላል!? በማለት እንደወትሮም አጅግ በጣም በሚደንቅ ሁኔታ 1,000,000.00 ብር ድጋፍ አበርክቻለሁ ብለዋል። ጀግናችን እግዚአብሔር ይስጥልን፤ እጅግ በጣም እናመሰግናለን

በሴቶች ዘርፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ወርቅ በቦክስ ያመጡ የመጀመሪቹ ናቸው!ቤቴል እና ቤተልሔም በSeifu EBS ላይ!ለባለ ወርቆቹ በመጪው እሁድ በታላቁ ዎላይታ ጉተራ አዳራሽ የጀገና አቀባበል ከ...
01/04/2024

በሴቶች ዘርፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ወርቅ በቦክስ ያመጡ የመጀመሪቹ ናቸው!
ቤቴል እና ቤተልሔም በSeifu EBS ላይ!

ለባለ ወርቆቹ በመጪው እሁድ በታላቁ ዎላይታ ጉተራ አዳራሽ የጀገና አቀባበል ከ8 ሰዓት ጀምሮ ተዘጋጅቷል ማንም እንዳይቀር!

ትላንት Seifu EBS በዎላይታ ልጆች ደምቆ አምሽቷል! 💪
Betel Wolde

በማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃና ጥላቻ መልዕክቶችን የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የቦሎሶ ሶሬ  ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አሳሰበ። መጋቢት 20/2016 ዓ.ም በማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ...
29/03/2024

በማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃና ጥላቻ መልዕክቶችን የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አሳሰበ።

መጋቢት 20/2016 ዓ.ም በማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃና ጥላቻ መልዕክቶችን የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት በአጽንኦት አሳስቧል።

ሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ Fake አካውንትና ፔጅ ተገን በማድረግ የውሸትና የተዛቡ መረጃዎችን በማሰራጨት የወረዳውን ሠላም ለመረበሽና የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶች ተረጋግተው እንዳይሰሩ ሁከት ለመቀስቀስ እንዲሁም የተለያዩ ግለሰቦች ስብዕና የሚነኩ ፕሮፖጋንዳ የሚያሰራጩ አካላት ላይ መንግስት የማይዳግም እርምጃ ይወስዳል።

የወረዳችን ገጽታ ለማጠላሸት ጭንብል ማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን ከፍተው ሀሰተኛና የተቀነባበሩ መረጃዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር ሃላፊነት የማይሰማቸው አካላት መኖራቸውንም ደርሰንበታል፡፡

ማንኛውም ዜጋ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎችን ከመቀበሉ በፊት ከተረጋገጠና ከትክክለኛ ምንጭ የተገኙ መሆናቸውን በጥንቃቄ ማጣራት አለበት፡፡

ህዝቡ ለወደፊቱም ከተመሳሳይ የሆኑ ሀሰተኛ ወሬዎች ምንጩ ያልታወቁ መረጃዎች መጠንቀቅ ይኖርበታል፡፡

ህብረተሰቡን የማደናገርና ውዥንብር የመፍጠር ዓላማ ይዘው ሃሰተኛ ወሬዎችን እየፈበረኩ የሚያሰራጩ የጥፋት አካላትን በጥብቅ ተከታትሎ የህግ ተጠያቂ ማድረግ የመንግሥት ሃላፊነት ይሆናል፡፡

ተደብቆ የህዝብን ሠላምና አንድነት ለማደፍረስ የውሸት ፕሮፖጋንዳ በሚጽፉት እና ፀረ-ሠላም ኃይሎች የሚያሰራጩትን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በማህበራዊ ሚዲያ ላይክ፣ ኮሜንትና ሼር በማድረግ ተባባሪ የሚሆኑ አካላት ላይ በህግ አግባብ ተጠያቂ ይሆናሉ።

በህዝብ ሠላምና ፀጥት ላይ ተጽዕኖ ለመፈጠር የሚሯሯጡ አካላትን መንግስት በጥብቅ እየፈለገ ሲሆን በየአካባቢው የሚታወቁትን ለፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል።

የዕለት ተዕለት ተግባር ጥላቻ ማሰራጨት ፣ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎችንና የተለያዩ አካላትን አውሬ በማድረግ በሀሰተኛ ፔጅ እና አካውንት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚለጥፉ አካላትን በዓይነ ቁረኛ እየተከታተልን ስለሆነ የዚህ አስነዋሪ ድርጊት ባለቤቶች ላይ መረጃ እና ማስረጃ አደራጅተን በህግ አግባብ ተጠያቂ እናደርጋለን።

ግለሰቦቹ የግል ፍላጎታቸውን እና ጥላቻን መነሻ ያደረጉና ኃላፊነት የጎደላቸው መሆኑን ሚዲያ ከሚሰራጩ መልዕክቶች ማረጋገጥ ችለናል።

ተክኖሎጂውን ለዘላቂ ሰላምና ልማት መጠቀም ሲገባ ዲጂታል ተክኖሎጂውን በእንዲህ አይነት ሁኔታ መጠቀም እጅግ አሳዘነኝ ነው።

በዚህ ተግባር ተሰማርተው አከባቢውን የሚረብሹ አካላት ላይ መንግስት በደረሰበት ሰዓት ህጋዊና እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል።

የተረጋጋ ሠላምን፣ ኢኮኖሚንና ልማትን ለማስቀጠል የሚዲያ አጠቃቀማችን አዉንታዊና ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ሊሆን ይገባል።

ሻምበል አረጋው ፈለቀ
የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ
መጋቢት 20፤2016 ዓ.ም

ልብ ሰባሪ ዜናየሀዘን ዜና ! የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ስፍራ ተጨዋቹ አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል። በቅርቡ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በቤተክርስቲያን ስርዓት የፈፀመው...
27/03/2024

ልብ ሰባሪ ዜና

የሀዘን ዜና !

የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ስፍራ ተጨዋቹ አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

በቅርቡ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በቤተክርስቲያን ስርዓት የፈፀመው ተጫዋቹ ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቹ አርባምንጭ በሄደበት ድንገት ዛሬ ለሊት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል ።

ለአርባምንጭ ከነማ ታዳጊ ቡድን፤ ለሀዋሳ ከተማና አሁን ለባህርዳር ከነማ በሊጉ የሚጫወተው አለልኝ አዘነ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ተደርጎለት ማገልገል ችሏል ።

የወላይታ ዜና ድረገፅ በአለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።

 #የእግርኳስ ጥበበኛ አበባየሁ ሀጂሶ
26/03/2024

#የእግርኳስ ጥበበኛ አበባየሁ ሀጂሶ

የእግርኳስ ጥበበኛ አሸናፊ በቀል ቅጽል ስሙ አሰንስኦ ተወልዶ ያደገው ወላይታ /አረካ / ሲሆን የእግርኳስ ችሎታው በእጅጉ የሚደነቅ ወጣት ተጨዋች ነው። የእግርኳስ ጥበበኛው ለሀላባ ከነማ ፊር...
25/03/2024

የእግርኳስ ጥበበኛ አሸናፊ በቀል ቅጽል ስሙ አሰንስኦ ተወልዶ ያደገው ወላይታ /አረካ / ሲሆን የእግርኳስ ችሎታው በእጅጉ የሚደነቅ ወጣት ተጨዋች ነው።

የእግርኳስ ጥበበኛው ለሀላባ ከነማ ፊርማውን አኑሮ ቡድኑን እያገዘ የሚገኝ ድንቅ የተስጦ ባለቤት ነው።

ተጨዋቹ አረካ ከተማ እና በሌሎች ክለቦች በነበረበት ወቅት ባሳየው ድንቅ ብቃት በርካታ አሰልጣኞች አይን ያረፈበትም ሲሆን በአሁን ሰዓት ለበርበሬዎቹ ግልጋሎት እየሰጠ ይገኛል።

ምታተኛው ተጫዋች ከዚህ አልፎ ከፍተኛ ደረጃ እንደሚደርስ የእግርኳስ ተንታኞች ይናገራሉ።

የእግርኳስ ችሎታ የተቸረው ወጣቱ ተጨዋች በየዕለቱ ራሱን እያበቃ የሚያገኝና ፊርማ ላኖረው ለአለባ ከነማ የእግርኳስ ጨዋነትን ተላብሶ ግልጋሎት እየሰጠ ይገኛል።

አመለ ሸጋው ወጣቱ ተጨዋች ከቡድን አባላት ጋር ያለው ጥምረት በእጅጉ የሚደነቅና ተጨዋቹ ማንኛውም ቲም ጋር ብቀላቀል ራሱን ማዋሀድ የሚችል መሆኑን ማሳያ ነውና በርታ ብለናል።

የ68 ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት* ከወላይታ ጦና ቦክስ ክለብ እስከ ኢትዮጵያ ኩራት   | ኢትዮጵያዊቷ ድንቅ ቦክሰኛ ቤቴል ወልዴ፥ በ66 ኪ.ግ ከሞዛምቢኳ ቦክሰኛዋ ጋር ለፍፃሜ ተገናኝታ በሚገርም...
24/03/2024

የ68 ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት

* ከወላይታ ጦና ቦክስ ክለብ እስከ ኢትዮጵያ ኩራት

| ኢትዮጵያዊቷ ድንቅ ቦክሰኛ ቤቴል ወልዴ፥ በ66 ኪ.ግ ከሞዛምቢኳ ቦክሰኛዋ ጋር ለፍፃሜ ተገናኝታ በሚገርም ብቃት 5 ለምንም በሆነ ውጤት በጋና አክራ ከተማ በተካሄደው በዘንድሮው የመላው አፍሪካ ጨዋታ ለኢትዮጵያ 2ኛ የሆነ የወርቅ ሜዳልያ በማስመዝገብና ለራሷ ደግም የወርቅ ሜዳልያ ቁጥር ከፍ በማድረግ ስሟን በደማቁ የታሪክ ማህደር መሰነድ ችላለች።

ከዎላይታ-ኢትዮጵያ እስከ አለምአቀፍ ቦክስ ስፓርት ውድድር ከ67 በላይ ወርቅ ተሸላሚ እንዲሁም ለአራት ዙር የቤልት ውድድር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቦክሰኛ ሻምፒዮና የሆነችው ቤቴል ወልዴ 68ኛውን የወርቅ መዳሊያ በመላው አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድር በማግኘት አዲስ ታሪክ ማስመዝገብ መቀጠሏን በአደባባይ አረጋግጣለች።

ቤቴል ወልዴ ውልደትና ዕድገቷ ዎላይታ ሶዶ ነው፥ በቦክስ ስፓርት የተመሰከረላት ወጣት ናት፣ አብዛኞቹን ተጋጣሚዎችን በበቃኝ ማሸነፏ ደግሞ ለየት ያደርጋታል፤ እስከአሁን ድረስ ባደረገችው በቦክስ፣ በኪክ ቦክስና ሞይንታይ ውድድሮች አሸናፊ በመሆን የ67 ሜዳሊያዎች ባለቤት ናት።

ለየት የሚያደርገው ደግሞ ከእነዚህ ሜዳሊያዎች አንዱ ብቻ የነሀስ ሲሆን ሌሎች በሙሉ የወርቅ ብቻ መሆኑንም ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ማረጋገጧ ይታወሳል።

መነሻውን የጦና ቦክስ ቡድን ያደረገችሁ ይህቺ ብርቷ ሴት ከዓመታት በፊት ዎላይታ ዞንን ወክላ በክልልና በአገርአቀፍ ደረጃ በሴቶች ቦክስ ስፖርት ሻምፒዮን በመሆን ትታወቃለች።

ቀጥሎ ባሉ ጊዜያት ለአካዳሚ፣ ለኒያላና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ስፖርት ክለብ በመጫወትም በርካቶችን በበላይነት በማሸነፍ እንዲሁም የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት በመሆን እውቅና ያተረፈች እንቁ ወጣት ናት።

በቅርቡ መስከረም ወር 2015 ዓ.ም ኢትዮጵያን ወክላ በተሳተፈችበት የሞይንታይ ኢንተርናሽናል ውድድር የቤላሩሱዋን ተወዳዳሪ በበላይነት አሸንፋ የሀገሯን ስም ከፍ አድርጋ አስጠርታለች።

በጋና አክራ በተካሄደው 13ኛ መላው የአፍሪካ ጨዋታ ላይ ኢትዮጲያ በቦክስ ውድድር ከ37 ዓመት በኋላ አዲስ ታሪክ ለሀገራቸው የወርቅ ሜዳሊያ ካሸነፈችሁ ከሌላኛዋ ብርቱ ቦክሰኛ ቤቴሌሄም ገዛሃኝ አሁን በሚያሳዩት አስደናቂ አቋም ቀጣይ በአለምአቀፉ መድረክ ለኦሎምፒክ በማለፍ የመጀመሪያዋ ሴት ቦክሰኛ ይሆናሉ በሚል በርካቶች ይመሰክራሉ።

ላለፋት አምስት ቀናት በጋና አክራ ሲካሄድ የቆየው 13ኛው የመላ አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድር ከ50 የአፍሪካ ሀገሮች ከ640 በላይ አትሌቶች መሳተፋቸው የተገለፀ ሲሆን ኢትዮጵያ በ47 ወንድ፣ በ40 ሴት በድምሩ በ87 አትሌቶች የተወከለች ሲሆን 7 የወርቅ፣ 7 የብር እና 4 የነሐስ በድምሩ 18 ሜዳልያዎችን ማስመዝገብ ናይጄሪያን ተከትላ በሁለተኛነት ማጠናቀቋን ከአፍሪካ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በወላይታ ዞን የብልፅግና ፓርቲ አባላት ዞናዊ ማጠቃለያ ኮንፍራንስ እየተካሄደ ነውመጋቢት 11/2016 በወላይታ ዞን "ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ አ...
20/03/2024

በወላይታ ዞን የብልፅግና ፓርቲ አባላት ዞናዊ ማጠቃለያ ኮንፍራንስ እየተካሄደ ነው

መጋቢት 11/2016 በወላይታ ዞን "ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ አባላት ዞናዊ ማጠቃለያ ኮንፍራንስ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።

ኮንፍራንሱ ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል በፓርቲ መሪነት የተገኙ ወረቶችን ለማስቀጠል እና ተግዳሮቶችን በማረም በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ አመራሩና አባላት የጋራ አረዳድ እንዲኖረው ያለመ ነው።

ፓርቲው ለህዝብ ቃል በገባው መሠረት ባለፋት ሁለት አመት ተኩል በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ የልማት አፈጻጸምና ስኬቶች የተመዘገቡ ሲሆን በቀሪ ጊዜያት የቀሩ ስራዎች ላይ ርብርብ ለማድረግ የሚያስችል አቅም የሚፈጥር ኮንፍረንስ እንደሆነም ተገልጿል።

በኮንፈረንሱ የፓርቲው የሁለት ዓመት ተኩል አፈፃፀም ሪፖርት እና የአመራርና አባላት የዲሲፕሊን መመሪያ ቀርቦ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ በተቀመጠው አሠራር መሠረት ኮንፍራንሱ ከቀበሌ ጀምሮ በየመሰረታዊ ድርጅት የተካሄደ ሲሆን ዛሬ ዞናዊ ማጠቃለያ እየተደረገ ይገኛል።

በኮንፍረንሱ የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ፣ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የዞኑ ብልፅግና ፓርት ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛን ጨምሮ የፓርቲው አመራርና አባላት እየተሳተፉ ይገኛል።

ንግድ ባንክ በቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።በሲስተም ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት በቅርንጫፎቹ  መስጠት የጀመረ መሆኑን  ባንኩ አስታውቋል።የ...
16/03/2024

ንግድ ባንክ በቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

በሲስተም ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት በቅርንጫፎቹ መስጠት የጀመረ መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።

የባንኩ ቅርንጫፎች ዛሬ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጡም ገልጿል።

በተመሳሳይ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን (ኢንተርኔት ባንኪንግ፥ ሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም ሲ ቢኢ ብር) ለማስጀመር እየሠራ መሆኑን ገልጾ፤ ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል ባንኩ ይቅርታ ጠይቋል።

መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም

ክልል አቀፍ የወጣቶች መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ መካሄድ ጀመረወላይታ ሶዶ፤ መጋቢት 7/2016 ክልል አቀፍ "እኔ ለሀገሬ የሰላም ዘብ ነኝ" በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አ...
16/03/2024

ክልል አቀፍ የወጣቶች መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ መካሄድ ጀመረ

ወላይታ ሶዶ፤ መጋቢት 7/2016 ክልል አቀፍ "እኔ ለሀገሬ የሰላም ዘብ ነኝ" በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አባላትና ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች መድረክ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በክልሉ "እኔ ለሀገሬ የሰላም ዘብ ነኝ" በሚል መሪ ቃል በየደረጃው የተካሄደ ሲሆን ዛሬ ላይ ማጠቃለያ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተደድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ፣ የክልሉ የወጣቶች ሊግ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚካኤል ዋዳ፣ የሁሉም ዞኖች የተወጣጡ ወጣት ሊግ አባላትና ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች እየተሳተፉ ናቸው።

ከመንገድ ግንባታ አኳያ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች፣ የድልድይ ግንባታ መጓተት፣ የጤናና በክልሉ የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ለማሳደግ በተሰሩ በርካታ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ ቢ...
13/03/2024

ከመንገድ ግንባታ አኳያ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች፣ የድልድይ ግንባታ መጓተት፣ የጤናና በክልሉ የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋን ለማሳደግ በተሰሩ በርካታ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ ቢቻልም፥ አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ያለው የንጹ መጠጥ ውሃ ሽፋን በዘላቂነት መፍትሔ ሊሰጠው እንደሚገባ የምክር ቤት አባላት አንስተዋል።

የማህበራዊ ተቋማት ግንባታ መዘግየት፣ የመብራትና የኔትወርክ መቆራረጥ፣ የወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ ያሉ ውስንነቶች የህዝብ የመልካም አስተዳደር የቅሬታ ምንጭ እየሆኑ በመምጣታቸው ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጣቸው የምክር ቤቱ አባላት ጠይቀዋል።

 !
13/03/2024

!

የገዥ ትርክትን በመገንባት ክልላችን የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፦ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት  የሥራ...
13/03/2024

የገዥ ትርክትን በመገንባት ክልላችን የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፦ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት ክልሉ በአዲስ ዕሳቤ ተደራጅቶ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ የልማት ዕቅዶችን በማዘጋጀት ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል።

በክልሉ ያሉ ጸጋዎችን በመለየት ሀብት የመፍጠር ስራ እየተሰራ ይገኛል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ህብረተሰቡን ከጎን በማሰለፍ ከከፋፋይ አጀንዳዎች በመለየት በልማት ትኩረት እንዲያደርጉ መደረጉን ገልጸዋል።

በዚህም የገዢ ትርክት በመገንባት ክልላችን የሠላም የመቻቻልና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በተሰራው ስራ አበረታች ውጤቶች ተመዝግቧል ነው ያሉት።

የህዝብ ለህዝብ ትስስርን በመፍጠር ከዕዳ ወደ ምንዳ ለመቀየር በተሰራው ስራ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ያወሱት ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ጥላሁን የለውጥ ተቃዋሚዎች የሚፈጥሩትን ፈተናዎች በመጋፈጥ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉት የልማት ስራዎች ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።

አጠቃላይ በተከናወኑ የልማት ስራዎች በግብርና በኢንዱስትሪ፣ በቴክኖሎጂ በባህልና ቱርዝም እንዲሁም በሌሎች ተግባራት በተሰራው ስራ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን አብራርተዋል።

በቀጣይም ምክር ቤቱ በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይቶችን በማድረግ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ባለ ሁለት ራስ ጥጃ በደቡብ ወሎ ዞን በደሴ ዙሪያ ወረዳ በ017 ቀበሌ ልዩ ስፍራ ቀይ አፈር በሚባለዉ አካባቢ ከተፈጥሮ ህግ ባፈነገጠ መልኩ ባለሁለት ራስ ጥጃ መወለዱ ታዉቋል፡፡     ንብረ...
12/03/2024

ባለ ሁለት ራስ ጥጃ

በደቡብ ወሎ ዞን በደሴ ዙሪያ ወረዳ በ017 ቀበሌ ልዩ ስፍራ ቀይ አፈር በሚባለዉ አካባቢ ከተፈጥሮ ህግ ባፈነገጠ መልኩ ባለሁለት ራስ ጥጃ መወለዱ ታዉቋል፡፡

ንብረትነቷ የአቶ አወል ሰይድ የሆነች ላም ባለሁለት ራስ ጥጃ የተወለደ መሆኑንና ልዩ አፈጣጠር ያለዉ ይህ ጥጃ እስከ አሁን ድረስ በህይዎት እንዳለ የተረጋገጠ ሲሆን ጉዳዩን አስመልክቶ ባለቤቷ እንዳሉት ላሟ የመጀመሪያዋ እንደሆነና የተወለደዉም ጥጃ በሁለቱም አፎቹ የተሰጠዉን ፈሳሽ ምግብ መዉሰድ የሚችል መሆኑን ገልጸዉ የተፈጠረዉ ክስተት ለራሳቸዉም እንዳስደነቃቸዉ ገልጸዋል፡፡

በደሴ ዙሪያ ወረዳ እስሳትና አሳ ሀብት ጽ/ቤት የእስሳት ሀብት በሽታ ቅኝትና ቁጥጥር ባለሙያ የሆኑት ጌትናት ሰፊው (ዶክተር) እንዳሉት የወንድና የሴት ዘር በሚዋሀዱበት ጊዜ አንድ ጽንስ ወይም ሁለትና ባላይ ጽንሶች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡

አሁን ላይ የተፈጠረው ጽንስ አንድ ሴል ለሁለት ሲከፈል የተከሰተ ተመሳሳይ መንትያ መሆኑን የገለፁት ጌትናት ሰፊው (ዶክተር) ፅንሱ በሚፈጠርበት ወቅት ያለተሟላ የሴል ክፍፍል በመከሰቱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የዚህ አይነት ባለሁለት ጭንቅላት አፈጣጠር በሳይሳዊ ስሙ ዳይሴፋለስ እንደሚባልም ባለሙያው አብራርተዋል፡፡

ይህ ችግር ሊፈጠር የሚችልባቸው ሁኔታዎች ያልተመጣጠነ የማእድናት በሰውነት መኖር፣ የአካባቢ ብክለት፣ አሲዳማ የሆኑ እፀዋትን በመመገብ፣ አሲዳማ ኬሚካል ወደሰውነት ሲገባና በመድሀኒት ምክንያቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ጌትናት ሰፊው (ዶክተር) ገልፀው በዚህ ሁኔታ የሚፈጠሩ ጽንሶች ከተወለዱ በኋላ በህይዎት የመቆየት እድላቸውም አጭር መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የደሴ ዙሪያ መንግስት ኮሚኒኬሽን ዘገባነዉ

በስዊድን የታየው የሰማይ ላይ ትንግርት‼️➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖በሰሜናዊው የስዊድን ክፍለ ግዛት ውስጥ በምትገኘው የኪሩና ከተማ ሰማይ ላይ ከሰሞኑ የታየው የብርሃን ህብረ ቀለማት የብዙዎችን ቀልብ...
10/03/2024

በስዊድን የታየው የሰማይ ላይ ትንግርት‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
በሰሜናዊው የስዊድን ክፍለ ግዛት ውስጥ በምትገኘው የኪሩና ከተማ ሰማይ ላይ ከሰሞኑ የታየው የብርሃን ህብረ ቀለማት የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ነው፡፡

ክስተቱ በጠፈር ተመራማሪዎች አገላለፅ "አውሮራ" እየተባለ የሚጠራ ሲሆን፤ ከፀሀይ ወለል ላይ የሚነሱ በአይን የማይታዩ ቅንጣቶች ከምድር የመግነጢሳዊ መስክ ጋር በሚፈጥሩበት ሰበቃ ወይም ፍሪክሽን የሚፈጠር ክስተት ነው፡፡

ተመራማሪዎች እንደሚገልፁት በተለያዩ ግዜያት ከፀሀይ ወለል ላይ የሚነሱ በአይን የማይታዩ "ፕላስማ" የተባሉ ቅንጣቶች ያሉ ሲሆን፤ እነዚህ ቅንጣቶች በሰአት 1,609,344 ኪ.ሜ የመጓዝ ፍጥነት አላቸው።

ቅንጣቶቹ ወደ ምድራችን የሚመጡት በነፋስ መልክ ሲሆን ይህ ነፋስ (Solar wind) ወይንም ሞቃት የፀሀይ ነፋስ ተብሎ ይጠራል።

እነዚህ ነፋሳት ከምድራችን ውጫዊ ከባቢ አየር እና የመግነጢሳዊ መስክ (Magnetic field) ጋር ሰበቃ (friction) በሚፈጥሩበት ጊዜ ሰማዩ ላይ የተለያየ ህብረቀለማት ያላቸው ነፋሳት ሲነፍሱ ሰማዩ ላይ አውሮራ (Aurora) ተከሰተ ይባላል።

አውሮራ በሰሜናዊው እና ደቡባዊው ዋልታ ላይ ብቻ አልፎ አልፎ የሚከሰት የሰማይ ላይ ትንግርት ሲሆን ከምድር የከባቢ አየር ጋዞችም ጋር ጥብቅ ቁርኝት አለው።

እነዚህ ጋዞች በዋነኝነት ናይትሮጅን እና ኦክስጅን ሲሆኑ አንዳንድ ጊዜ ሌሎች የጋዝ አይነቶችም ይካተታሉ።

የአውሮራን ቀለም የሚወስነው ፕላስማ፣ ሰበቃ የፈጠረበት የከባቢ አየር ጋዝ እና ሰበቃው የተፈጠረበት ቦታ ከምድር ወለል ያለው ከፍታ ትልቅ ነው።

ፕላስማው ሰበቃ የፈጠረው ከምድር ወለል እስከ 96 ኪ.ሜ ርቆ ከሚገኝ የናይትሮጅን ጋዝ ጋር ከሆነ አውሮራው ሰማያዊ ቀለም ይኖረዋል።

ፕላስማው ከ96ኪ.ሜ በላይ ርቆ ከሚገኝ የናይትሮጅን ጋዝ ጋር ሰበቃ ከፈጠረ አውሮራው ወይነጠጅ ቀለም በውስጡ ይይዛል።

ፕላስማው ከምድራችን ወለል ከ 96ኪ.ሜ እስከ 241ኪ.ሜ ርቆ ከሚገኝ የኦክስጅን ጋዝ ጋር መስተጋብር ከፈጠረ አውሮራው አረንጓዴ ቀለም ይይዛል።

ፕላስማው መስተጋብር የፈጠረው ከምድር ወለል ከ241ኪ.ሜ በላይ ከሚገኝ የኦክስጅን ጋዝ ጋር ከሆነ አውሮራው ቀይ ቀለም በውስጡ ይይዛል።

ከላይ እንደተጠቀሰው አውሮራዎች በሁለት አይነት መልኩ ሊከሰቱ ይችላሉ። አንደኛው በሰሜናዊው ዋልታ ብቻ የሚታየው አውሮራ ቦሪያሊስ (Aurora Borealis) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በደቡባዊው ዋልታ ላይ ብቻ የሚታየው አውሮራ አውስትራሊስ (Aurora Australis) የሚባለው ነው።

አውሮራዎች ጠንካራ በሚሆኑበት ጊዜ የራዲዮ፣ ቴሌቪዥን እና የስልክ ሞገዶችን በማወክ ሊያስተጓጉሉ እንደሚችሉ የዋይልስዊድን ዘገባ ያመለክታል።

ባለፋት በ30 ቀናት በተከናወነው በተፋሰስ ልማት ስራ ከ79.6 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ማልማት ተችሏል፦ አቶ መስፍን ዳዊትየካቲት 30/2016 በወላይታ ዞን ባለፉት ለ30 ቀናት ሲከናወን የ...
09/03/2024

ባለፋት በ30 ቀናት በተከናወነው በተፋሰስ ልማት ስራ ከ79.6 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ማልማት ተችሏል፦ አቶ መስፍን ዳዊት

የካቲት 30/2016 በወላይታ ዞን ባለፉት ለ30 ቀናት ሲከናወን የነበረው የተፋሰስ ልማት ዞናዊ መዝጊያ መርሃግብር በጉኑኖ ሐሙስ ከተማ ተካሂዷል።

የወላይታ ዞን ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ዳዊት በዞኑ ባለፋት በ30 ቀናት በተከናወነው በተፋሰስ ልማት ስራ ከ79.6 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ማልማት መቻሉን ገልጸዋል።

በዚህም 361 ንዑስ ተፋስስ ከተለየው ህዝብ ከ957 ሺህ በላይ ህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን አስታውቀዋል።

የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ለግብርናችንና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገርና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለውም ጠቁመዋል።

ህዝቡ የተፋሰስ ጥቅሙን በውል በመረዳት በነቂስ ወጥቶ ተሳትፏል ያሉት ም/አስተዳዳሪው በተፋሰስ ስራ በተሰሩ ስራዎች ዘርፈብዙ ጠቀሜታ ማግኘት መቻላቸውን ጠቅሰዋል።

በአንዳንድ አከባቢዎች በተፋሰስ ልማት ስራ የተሰሩ ስራዎች ለቱሪስት መስህብነት ጨምር የሚያገለግል መሆኑን ገልጸዋል።

ከተፋሰስ ስራ ጎን ለጎን በንቅናቄው ከ950 ሄክታር በላይ ማሳ ባህርዛፍን የማስወገድ ስራ መስራቱን የገለጹት ም/አስተዳዳሪው ይህም የአፈር ለምነትና የእርሻ ማሳ ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።

እንደዞን በታቀደው ዕቅዱ መሠረት በተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ የተሻለ አፈጻጸም አስመዝግበናል ያሉት አቶ መስፍን በዚህ የተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች በዞኑ አስተዳደርና ግብርና መምሪያ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የዞኑ ምክርቤት ምክትል አፌ-ጉባኤ ወ/ሮ መስከረም አካለወልድ የውሃና አፈር ጥበቃ ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር እና የተሻለ ምርት እንዲናገኝ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ በተቀናጀ ተፋሰስ ልማት የተሰሩ ስራዎችን በዘላቂነት የማስጠበቅና መንከባከብ ስራ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

የጉኑኖ ሐሙስ ከተማ አስ/ር ከንቲባ አቶ ብርሃኑ ዋጃ በበኩላቸው በአከባቢያችን ላለፉት ዓመታት የተሠራዉ የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ሥራ ተጨባጭ ለዉጦችን በአርሶ አደራችን ምርትና ምርታማነት ላይ አምጥቷል ይህም ተጠናክሮ ልቀጥል ይገባል ብለዋል።

ከንቲባው አክለውም በዘንድሮ የተፋሰስ ልማት በሁለቱም ቀበሌያት 563 ሄክታር በላይ መሬት ለመሸፈን ታቅዶ 578.8(103%) ለማሳካት መቻሉን ገልጸዋል።

 #ምርጡ ልጃችን እንወድሃለን !
09/03/2024

#ምርጡ ልጃችን እንወድሃለን !

የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ከተወካዮቻቸው ጋር ተወያዩ---------------------የካቲት 29 ቀን፣ 2016 ዓ.ም፤ በደቡብ ኢትዮጽያ ክልል በወላይታ ዞን የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር...
09/03/2024

የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ከተወካዮቻቸው ጋር ተወያዩ
---------------------
የካቲት 29 ቀን፣ 2016 ዓ.ም፤ በደቡብ ኢትዮጽያ ክልል በወላይታ ዞን የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ከፌደራልና ከክልል ምክር ቤት የህዝብ ተወካዮች ጋር በልማትና በመልካም አስተዳደር እንዲሁም በሠላም ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሂደዋል።

ውይይቱን የመሩት የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ ወ/ሮ መቅደስ ደስታ መንግስት የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የሠላም ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የተለየ ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ገለፀዋል።

የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት፣ ሥራ አጥነትነን ለመቀነስ፣ የግብርና ሥራን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በአጠቃላይ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች እንዲሁም የህዝብ ሠላምና ደህንነትን በተመለከተ በመንግስት በኩል በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አክለው ገልፀዋል።

ለውጤቱም የህብረተሰቡ ተሳትፎና ድጋፍ ወሳኝ ነው ያሉት የተከበሩ ወ/ሮ መቅደስ እያደገ የመጣውን የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መንግስት በአጭር በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ አቅዶ ህዝብን በሚጠቅም መልኩ ምላሽ እንደሚሰጥም ነው ያመላከቱት።

በውይይቱም የከተማው ከንቲባ አቶ እሸቱ ታደሰ ባለፉት የውይይት መድረኮች ከህዝብ የተነሡ ጥያቄዎችን በተመለከተ ምላሽ ያገኙ በሂደት ያሉ እንዲሁም በቀጣይ ዕቅድ የተያዘላቸው መሆኑን ሪፖርት አቅርበዋል።

የክልል ምክር ቤት አባል እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህብረት ሥራ ኤጀንሲ ም/ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ክፍሌ ዋና በበኩላቸው ለመልማት፣ ለማደግና ለመበልፀግ አንድነት ወሳኝ መሆኑን ገልፀው፤ የተነሱ የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት ህብረተሰቡና የከተማው አስተዳደር በትብብር መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች መንግስት የከተማው መሠረታዊ ችግር የሆነውን የሥራ -አጥነት ችግርን ለመፍታት፣ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በትኩረት እንዲሰራ እንዲሁም ግንባታቸው ተጀምሮ ሳይጠናቀቅ ዓመታትን ያስቆጠረው በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የቦዲቲ ካምፖስ እና የቦዲቲ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ እንዲጠናቀቅ ጠይቀዋል።

ምርጥ የወላይታ ፍሬ ፣ የህዝብ ልጅ ፣ የልማት አርበኛ ተዋወቁት አቶ ጴጥሮስ ወልደማሪያም ይባላል ላለፉት ሁለት ዓመታት የአረካ ከተማ ከንቲባ ሆኖ በትጋትና በታማኝነት ሌት ተቀን ሲሰራ የነበ...
21/08/2023

ምርጥ የወላይታ ፍሬ ፣ የህዝብ ልጅ ፣ የልማት አርበኛ

ተዋወቁት አቶ ጴጥሮስ ወልደማሪያም ይባላል ላለፉት ሁለት ዓመታት የአረካ ከተማ ከንቲባ ሆኖ በትጋትና በታማኝነት ሌት ተቀን ሲሰራ የነበረ ድንቅ መሪ ነዉ ። ለልማታ ያለዉ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነትን መላዋ የአረካ ነዋሪ ይመሰክሩለታል ።

በአረካ ከተማ የመንገድ ፣ የዉሃ ፣ የመብራትን ጨምሮ የተለያዩ የህዝብ ጥያቄዎችንና ፍላጎቶችን ከሞላ ጎደል ሲመለሱ እንደሱ ቁልፍ ሚና የተጫወተ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንብኝም ። ህገወጥ እና ብልሹ አሰራሮችን ድምጥ ማጡን ያጠፋዉ ይህ አንበሳ ለ ሙሰኞች እራስ ምታት ሆኖ ሰንብቷል ።

በቀጣይ ለወላይታ ከዛም አልፎ ለሀገር ጭምር በርካታ ሥራዎች እንደሚሰራ ምንም ጥርጥር የለዉም ። በእዉነቱ የአረካ ህዝብ ሲያመሰግንህ ይኖራል ።

ለእዉነትና ለሥራ ያለህ ቁርጠኝነት ለዚህ ስኬት አድርሶሀልና ቀጥልበት ።

የሚሰራዉን ማመሰገን ለቀጣይ ተግባር የበለጠ ያነሳሳልና ሁሌ ከመተቸት ይልቅ ጠንካራ አመራሮችን ማወደስ ይልመድብን ።

በነገራችን ላይ አረካ ከተማ በበርካ ተግባሮች በዞን ደረጀ ከፍተኛ አፈፃፀም በማስመዝገብ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ መዋቅር ነዉ ፣ በህዝበ ዉሳነዉም ምርጫ 100% በማሳካት የተጨበጨበለት መዋቅር ሲሆን ለዚህም የአንበሳውን ድርሻ የተወጣዉ ይህ ከንቲባ ነዉ።

ትላንት በዉስጥ መስመር በርካቶች ይዘን እንዲንቀርብ በጠየቁን መሰረት አቶ ጴጥሮስን ይዘን ቀርበናል በቀጣይ ማንን ማቅረብ እንዳለብን በዉስጥ መስመር አሳዉቁን ።

የአረካዉ አንበሳ በረታ የወላይታ ህዝብ ከጎንህ ነዉ !

የንጉስ ጦና ሀገር ወላይታ💪💪
07/08/2023

የንጉስ ጦና ሀገር ወላይታ💪💪

  ተጠቃሚዎች ሰሞኑ   የሚባል ማህበራዊ ሚዲያ ፔጅ አዲስ የሚደራጀውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ማዕከልና በሌሎች ጉዳይ ጋር ተያይዞ የህዝቡን ቀልብ በውሸትና የተቀነባበረ መረጃ በማሰራጨት...
03/08/2023

ተጠቃሚዎች

ሰሞኑ የሚባል ማህበራዊ ሚዲያ ፔጅ አዲስ የሚደራጀውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋና ማዕከልና በሌሎች ጉዳይ ጋር ተያይዞ የህዝቡን ቀልብ በውሸትና የተቀነባበረ መረጃ በማሰራጨት ትኩረት ስቧል።

በገጹ የሚለጥፉ አብዛኛው መረጃዎች አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታና አዝማሚያውን በመጠቀም ከእውነት የራቀ እና የተቀነባበሩ መረጃዎች እያሰራጨ በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ምክንያቱም በዚህ ፔጅ የተለጠፉ አብዛኛው መረጃዎች ከሁለትና ሶስት ቀን በኃላ እየጠፋ ነው። በተጨማሪም የቆዩ ፎቶችን በመወሰድ አንድ ቀን በስብሳባም(በውሳኔውም) ላይ ያልተሳተፉ ግለሰቦችን እየሞገሰ ይውላል።

ይህ ፔጅ ከዚህ በፊት በሌላ ሰው ስም ስያሜ ያለና አሁን ወደ የተቀየረ ነው። በዚህ ፔጅ ከዚህ በፊት የወላይታ ህዝብ ስም የሚጠላሹና ውሸት መረጃዎችን ሲያሰራጭ ነበር። ከ4.5 ሺህ ተከታያ ያለው ሲሆን ከ8 ሺህ በላይ ተከታይን በአንድ ወር ውስጥ በማግኘት ከ13 ሺህ በላይ ተከታይ አፍርቷል።

የዚህ ፔጅ ዋና ዓላማው የወላይታ ህዝብ ጥቅም ለማጠልሸት ከወንድም ህዝቦች ጋር ለማሻከርና ከሌሎች አጋሮባች ዞኖች ጋር ያለውን አብሮነትና አንድነትን ለማፋለስ እየሰራ መሆኑን መረጃዎች እያሳዩ ናቸው።

እንዲሁም አምስት ዞኖችና ስድስት ልዩ ወረዳዎች ህዝቦች በየምክር ቤቶቻቸው በአንድ ክልል ተደራጅተው ለመኖር የተስማሙትን መልካም ሀሳባቸውን በተሳሳተ ሁኔታ አደገኛና ስጋት የሚጫሩ መረጃዎችን እያሰራጨ መሆኑን እንመለከታለን።

ለወላይታ ህዝብ ጠቃሚ መረጃዎችን እያሰራጨ በማስመሰል የወላይታ ህዝብን ዳግም ዋጋን ለማስከፈል እየሰራ መሆኑን ህዝቡ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መቀመጫዎች ወላይታ የድርሻውን ማግኘቱ አይቀርም ሌሎችም እንደዛው። እውነታው ይህ ነው ከዚህ ውጪ አዲስ ነገር አንጠብቅ።

በዚህ ፔጅ የተቀነባበረና ውሸት መረጃውን የሚያሰራጨውን ግለሰብ ማንነት እየተጣራ ጫፍ ላይ የደረሰ ሲሆን የግለሰቡን ማንነት በቅርቡ ለህዝቡ ይፋ እናደርጋለን።

በአጠቃላይ በዚህ ፔጅ ላይ የሚሰራጩ
ጨው ምንጩ ያልታወቀና ያልተረጋገጠ መረጃዎችን ላይክ፣ ኮሜንትና ሼር የሚያደርጉ ግለሰቦች እንድትቆጥቡ እናሳስባለን።

New York እንዳይመስላችሁ የሁሉ ኢትዮጵያዊያን ቤት የሆነችው ወላይታ ሶዶ ነች።
30/07/2023

New York እንዳይመስላችሁ የሁሉ ኢትዮጵያዊያን ቤት የሆነችው ወላይታ ሶዶ ነች።

በዓሉን ስናከብር መልካም እሴቶቻችንን በማጠናከር እና የተቸገሩ ወገኖቻችንን በመርዳት መሆን ይገባል ፦ አቶ ጴጥሮስ ወልደማርያም በወላይታ ዞን የአረካ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ዓመት በዓልን ...
11/09/2022

በዓሉን ስናከብር መልካም እሴቶቻችንን በማጠናከር እና የተቸገሩ ወገኖቻችንን በመርዳት መሆን ይገባል ፦ አቶ ጴጥሮስ ወልደማርያም

በወላይታ ዞን የአረካ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ለዘማች ቤተሰቦች፣ ለወላጅ አጥና ተጋላጭ ሕዓናት እንዲሁም ለአቅመ ደካማ አረጋውያን የተለያዩ ድጋፎችን አድርጓል።

የተደረጉ ድጋፎችም የተሰበሰቡት በወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በሴቶች አደረጃጀት ፣ በተለያዩ ግለሰቦች እና በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ከሦስቱ ቀበሌዎች ድጋፍ የተገኙት ሲሆኑ እነዚህም አልባሳት፣ የትምህርት ቁሳቁሶች፣ የምግብ ዘይትና ዱቄት፣ እንዲሁም የቅርጫ ሥጋ መሆኑን ለማወቅ ትችሏል።

በመርሀግብሩ የተገኙት የአረካ ከተማ ከንቲባ አቶ ጴጥሮስ ወልደማማሪያም የእንኳን በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን መልዕክት አስተላልፈዋል።

የተራበን ማብላት፣ የተቸገረን መርዳት እንዲሁም የታረዘን ማልበስ የኢትዮጵያዊያን መገለጫ መሆኑን ጠቅሰው ፣ ማህበረሰብም እንደ ከዚህ ቀደሙ የጋራ አንድነቱን በማጠናከር እምነቱ በሚያዘው መሰረት አቅመ ደካሞችን በመርዳት ያለውን በማካፈል በዓሉን እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል በዓሉን በማይመች ሁኔታ ላይ ለሚያሳልፉ ወገኖች ማዕድ በማጋራት አለኝታነትን ማሳየት ይገባልም ነው ያሉት ክቡር ከንቲባዉ።

የአረካ ከተማ ዋና የመንግሥት ተጠሪ አቶ ንጉሴ መንግሥቱ በበኩላቸው እኛ ኢትዮጵያውን ልዩ ባህል አለን-የመተሳሰብና የመከባበር፤ ልዩ እሴት አለን-የመረዳዳትና የመደጋገፍ፤ ድህነት ውርስ አይደለምና እጅ ለእጅ ከተያያዝንና ከተባበርን እንሻገራለን፣ ድህነትንም ታሪክ እናደርገዋለን ገልፀዋል

በዕለቱ ለሁሉም ታዳሚዎች የምሣ ግብዣ የተደረገ ሲሆን የድጋፉ ተጠቃሚዎችም የከተማ አስተዳደሩ አቅዶ ባደረገላቸው ድጋፍ ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል።

እንኳን አደረሳችሁ !

“አዲሱ ዓመት አቅደን የሚንፈጸምበትና ሰርተን የሚንለወጥበት፣ ሠላምና ፍቅር የሚነግስበት እንዲሆንልን እመኛለሁ”፡- አቶ ዮሐንስ በየነ የተወደዳችሁ መላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች!!የተወደዳችሁ መላ...
10/09/2022

“አዲሱ ዓመት አቅደን የሚንፈጸምበትና ሰርተን የሚንለወጥበት፣ ሠላምና ፍቅር የሚነግስበት እንዲሆንልን እመኛለሁ”፡- አቶ ዮሐንስ በየነ

የተወደዳችሁ መላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች!!

የተወደዳችሁ መላው የዞናችን ህዝቦች፤ የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች!

እንኳን ለ2015 አዲሱ ዓመት/እንቁጣጣሽ/ በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን!!

አሮጌው ዓመት አልፎ አዲስ እየተተካ የክረምት፣ የጭቃ፣ የዝናብ፣ የብርድና የጨለማ ጊዜ አልፎ የብርሃን ጊዜ እየመጣ ሁሌም እየተደሰትን ከአንዱ ዘመን ወደ ሌላ ዘመን በየእድሜያችን ቁጥር ልክ ተሸጋግረናል። ይህንን ዕድል ሳያገኙ ወደ አዲሱ ዘመን መሻገር ያላቻሉ ብዙዎች አሉና።

አዲስ ዘመን ሲመጣ ዘመኑ ካለፈው ዘመን የተለየና እንደ ስያሜው አዲስ እንዲሆንልን ከፈለግን በሚመጣው ዘመን ውስጥ አዲሰ ሆነን ሲንገኝ ነው። ስለ አዲስ ዘመን ስናወራ ራሳችንም ማደስ ይገባናል።

ከዘመን ወደ ዘመን ስንሸጋገር አሮጌ ባህሪያችንንና አስተሳሰባችንን ቀብረን አዲስ ሕይወት ይዘን አዲሱን ዓመት ልንቀበለው ይገባል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከብዙ ውጣ ውረዶች ውስጥ አልፈን ትላልቅ ስኬትና ውጤት እንድናስመዘግብ በሀሳብ፣ በሞራል፣ በጊዜና በዕውቀት እንዲሁም በሁሉም መስክ ያላሰለሰ ድጋፍ ያደረጋችሁ በሙሉ በያለችሁበት ቦታ ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናና አክብሮት ይደርሳችሁ፡፡

የምንፈልገውን ልማት፣ ዴሞክራሲ፣ሁለንተናዊ ሠላምና ብልጽግናን በአጭር ጊዜ ዕውን ለማድረግ የድል ብልጽግናን የሚያበሰሩ ነባራዊ እውነቶች ላይ ቆመን በአዲስ መንፈስ መረባረብ እንዳለብን ይሰማኛል፡፡

ውድ የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች ፓርቲያችን ብልጽግና በምርጫ ወቅት ለህዝባችን ቃል የገባውን ማኒፌስቶን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚጠበቅባችሁን ኃላፊነት በትጋት እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

ከወግ አጥባቂነትና ከጽንፈኝነት ዝንባሌዎች እንዲሁም አፍርሰን ከመገንባት አስተሳሰቦች ተላቅቀን መካከለኛውን መንገድ ይዘን ለሁለንተናዊ ብልጽግና መትጋት አለብን፡፡

የተከበራችሁ የዞናችን ህዝቦች፡- በዞኑ ውስጥ የሚደረጉ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና የልማት እንቅስቃሴዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የድርሻችሁን ያልተቆጠበና የላቀ ተሳትፎ እንድታደርጉ ላሳስባችሁ እወዳለሁ፡፡

የምንወዳትና እንደዐይናችን ብሌን የምንሳሳላት ሀገራችን ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን የሚያለያዩ ሁኔታዎችን ከማጉላት ይልቅ የሚያቀራርቡና የሚያስተሳስሩንን እውነታዎች ላይ ማተኮርና መጠንከር ያስፈልጋል፡፡

ጥላቻን ነቅለን ፍቅርን እየተከልን፤ አንዳችን ለሌላችን ዋልታ እና ማገር፣ ድርና ማግ ሆነን የጀመርነውን የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን መላው የዞናችን ማህበረሰብ ተግቶ እንዲሰራ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

አሸባሪው ህወሐት የሠላም አማራጮችን አሻፈረኝ ብሎ ለ3ተኛ ጊዜ የከፈተብንን ጦርነት ለመቀልበስ ውድ ህይወታቸውን ሳይሰስቱ በዱርና በበረሃ እየተዋደቁ ላሉ ለሀገር መከላከያ ሠራዊትና ለጥምር ጦሩ የዞኑ ህዝብ ላደረገው ድጋፍ ልዩ ክብር አለኝ።

ሰላም የሁሉ መሠረት ነውና ሰላማችንን እንጠብቅ፣ ያላወቅነውን ለማወቅ፣ ያወቅነውን በጎ ነገር ለሌሎች ለማሳወቅ እንትጋ፣ አካባቢያችንን ብሎም አገራችንን ለማልማትና ወደ ብልፅግና ማማ ለማውጣት ተግተን እንሥራ የሚለው ዋና መልዕክቴ ነው፡፡

በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትንና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖቻችንን በመርዳት፣ በመተሳሰብ፣ በይቅር-ባይነት፣ በመግባባት፣ በወንድማማችነት፤ በእህታማማችነትና በአብሮነት መንፈስ ልናከብር ይገባል፡፡

በድጋሚ ለመላው የሀገራችንና የወላይታ ህዝብ አዲሱ አመት የሰላም፣ የጤና፣ የብልጽግናና የከፍታ ዓመት እንዲሆን ልባዊ ምኞቴ ነው፡፡

እንኳን በሠላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!! መልካም አዲስ ዓመት!!

ዮሐንስ በየነ
የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ አክሊሉ ለማ የ2015 ዓ/ም አዲስ ዓመት በዓል በማስመልከት የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ፡፡ ለመላው ወላይታ ብሔረሰብና ለሀገራችን ህዝቦች ...
10/09/2022

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ አክሊሉ ለማ የ2015 ዓ/ም አዲስ ዓመት በዓል በማስመልከት የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ለመላው ወላይታ ብሔረሰብና ለሀገራችን ህዝቦች እንኳን ለኢትዮጵያዊያን የዘመን መለወጫ አዲሱ አመት በዓል በሠላም አደረሳችሁ!አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤናና የብልጽግና እንዲሆን በራሴና በወላይታ ዞን አስተዳደር ስም መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ።

አገራችን ኢትዮጵያ የብዝሃ ብሔር፣ ኃይማኖት፣ ባህልና ቋንቋ ሀገር ስትሆን ሁሉም ብሔረሰቦች፣ ኃይማኖቶች፣ ባህሎችና ቋንቋዎች ለዘመናት ተቻችለው የሚኖሩባት የሁሉ እናት የሆነች ሀገር ነች።

ሆኖም የኢትዮጵያ ጠላት ሆኖ ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ሲያስተዳድራት የቆየው የጁንታው ቡድን በ"ከፋፍለህ ግዛ" የቅኝ ገዢዎች እሳቤ እርስ በርሳችን እንድንከፋፈልና እንድንናቆር አድርጎን ቆይቷል።

ከዛሬ አራት ዓመት በፊትም በህዝብ ማዕበል ሥልጣኑን ከለቀቀ በኋላ "እኔ የማልመራት ኢትዮጵያ ትፍረስ" በሚል አስተሳሰብ የአገራችን ምልክት የሆነውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ በመውጋት መንግስት ተገዶ ወደ ጦርነት እንዲገባ አድርጓል።

በዚህም ጦርነት ጁንታው ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ከሆኑ ሀገራትና ኢትየጵያን እንደፈለግን ካላሾርናት ከሚሉ ምዕራባውያን ጋር በማበር በኢኮኖሚና በሚዲያ የከፈቱብን ወረራ በመመከት የሀገራችን አንድነትና ሉአላዊነትን በማስስከበር በፈተናዎች ውስጥ ሆነንም አኩሪ የልማት ድሎችን ማስመዝገብ ችለናል።

ያለጦርነት መኖር የማይችለው የትህነግ ጁንታው ቡድን ለዜጎች ደህንነት ሲባል የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት በማፍረስ የአለም አቀፍ የጦር ህግና ስምምነት በተፃረረ መልኩ ዕድሜያቸው ያልደረሱ የትግራይ ህፃናትን ከፊት በማሰለፍ ለሶስተኛ ጊዜ በአማራና በአፋር ክልሎች ጦርነት በመክፈት በርካታ ንፁኃን ዜጎች ሕይወታቸውን እንዲያጡ፣ ከቤት ንብረታቸውና ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬአቸው እንዲፈናቀሉና ከፍተኛ መሠረተ ልማቶች እንዲወድሙ እያደረገ ይገኛል።

የዞናችን ህዝብ የመጀመሪያውን ወረራ ለመቀልበስ በሀብትና በገንዘብ ድጋፍና ለሠራዊቱ ስንቅ ዝግጅት በማድረግ እንደደገፈ ሁሉ አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ በተቃጣብን ወረራ የዞኑ መንግስትና ህዝብ በገንዘብና በዓይነት ከ34 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ ድጋፍ ለሠራዊቱ በማድረግ ደጀንነቱን እያረጋገጠ ይገኛል።

ለዚህም ለዞናችን አርሶ አደሮች፣ ለመንግስት ሠራተኞች፣ ለነጋዴዎች፣ ለባለሀብቱና ላስተባበሩ አመራሮች በራሴና በዞኑ አስተዳደር ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ፤ ወደ ፊትም ጦርነቱ እስኪቀለበስ ድረስ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነቴ የጸና ነው።

ሁሉም የልማት ዕቅዶች የሚሳኩት ሠላም ሲኖር ብቻ በመሆኑ ሁላችንም የአካባቢያችንን ሠላም ለመጠበቅ ዘብ ልንቆም ይገባል።

በአገራችን ላይ የተከፈተብን ጦርነት በግንባር ውጊያ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚ መስክ አንዳንድ አጋጣሚውን በመጠቀም በአቋራጭ ለመክበር በሚፈልጉ ስግብግብ ነጋዴዎች ዋጋ በመጨመርና ምርት አላግባብ በማከማቸት እንዲሁም በፕሮፓጋንዳው የማህበራዊ ሚዲያና የምዕራባውያን ሚዲያዎች በሚነዟቸው የሐሰት ወሬዎች ሳንሸበር አካባቢያችንን በትጋት ልንጠብቅ ይገባል።

የወላይታ ብሔር የብሔሩ መገለጫ የሆነው የዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓልም በዚህ ወር የሚከበር በመሆኑ ድርብ ደስታ የሚሰጥ ነው።

በበዓል የተጣላ የሚታረቅበት፣ የተራራቀ የሚቀርብበት፣ ያዘነ የሚፅናናበት በመሆኑ ሁሉም የዞናችንና የሀገራችን ሕዝብ የበዓሉን ዕሴቶች ተግባራዊ እንዲያደርግ ጥሪ አቀርባለሁ።

የምናከብረው በዓል ምሉዕ ደስታ የሚሰጠን የተቸገሩትን ስንረዳ፣ የተራቡትን ስናበላ፣ የታረዙትን ስናለብስ በመሆኑ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አረጋውያንንና የተቸገሩትን ለመርዳት ያሳየነውን በጎነት በበዓላቱም አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል። በድጋሚም በዓሉ የሠላም የጤናና የብልጽግና እንዲሆን እመኛለሁ።አመሰግናለሁ!

09/09/2022
የጊፋታ በዓልን ከወንድም ወላይታ ህዝብ ጋር አንድላይ ለማክበር በመጋበዜ እጅግ ደስ ብሎኛል፦ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜ 4/2014 የጋሞ ዞን ዋና አስ...
09/09/2022

የጊፋታ በዓልን ከወንድም ወላይታ ህዝብ ጋር አንድላይ ለማክበር በመጋበዜ እጅግ ደስ ብሎኛል፦ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜ 4/2014 የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በጊፋታ በዓል ላይ እንዲታደሙ ከወላይታ ዞን አስተዳደር የቀረበላቸውን ጥሪ በአክብሮት ተቀብለው በዕለቱ እንደሚመጡ ተናገሩ።

ዋና አስተዳዳሪው "ዮዮዮ ጊፋታ" በማለት ለወንድም ወላይታ ሕዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከወዲሁ አስተላልፈዋል።

በአጎራባች አከባቢዎች የተጀመረው የህዝብ ለህዝብ ትስስር የወላይታ ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል የራሱን ሚና እንደሚጫወት ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።

አያይዘውም ዋና አስተዳዳሪው የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን እንደሚጠናከርም አስረድተዋል።

የወላይታ ዘመን መለወጫ የሆነው "ጊፋታ በዓል" የሠላም፣ የጤና፣ የአንድነትና በጋራ የሚንበለጽግበት አድስ ዓመት እንዲሆንልን እመኛለሁ ብለዋል።

የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል በወላይታ ብሔር ዜንድ አሮጌውን ዓመት በመሸኘት አዲሱን ዓመት የሚቀበሉበት የዘመን መለወጫ በዓል ነው፡፡

Address

S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Broadcasting Corporation - WBC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wolaita Broadcasting Corporation - WBC:

Share