Wolayita times

Wolayita times የሀገራችን አንድነት እና ፍቅር ከምንም ጊዜ አስቀድመን ለእኛ አከባብያችን እውነተኛና አሰፈላጊ ጥያቄ መልስ ለማገኘት እንጥራለን

ለዛሬው ውጤት የትናንትነው አንተ ተጠያቂ ነህ!!ውጤቱን አትወደውም? እየኖረከው ነው! ታዲያ መቀየር ያለብህ ድርጊትህ ነው ድርጊትን ለመቀየር ደግሞ ደጋግሜ የምታስበውን ሀሳብን መቀየር ነው ደ...
02/11/2024

ለዛሬው ውጤት የትናንትነው አንተ ተጠያቂ ነህ!!

ውጤቱን አትወደውም? እየኖረከው ነው! ታዲያ መቀየር ያለብህ ድርጊትህ ነው ድርጊትን ለመቀየር ደግሞ ደጋግሜ የምታስበውን ሀሳብን መቀየር ነው ደጋግሜ ያሰበከው ሀሳብ ወደድክም ጠላህ ድርጊትህን በመቆጣጠር የትኛውንም ውጤት ይሁን እንድታገኘህ ያደርጋል። አሁን ላለህ ወይም ላገኘው ውጤት የትናንትነው አንተ ተጠያቂ ነህ!!

ውብ ቅዳሜን ተመኙሁላችሁ🙏

ሁሌም የአዕምሮ ስንቅ!

የብርሃኑ ነጋ ተሿሚ ፕረዚዳንት የ "ብትወዳደርም አትመረጥም!" ዘቻ እና ማስፈራሪያ ከምን የመነጨ ይሁን ? የትም ያልተሞከረ ሀገርአቀፍ አሰራር ያፈነገጠ የብርሃኑ ነጋ የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስ...
25/10/2024

የብርሃኑ ነጋ ተሿሚ ፕረዚዳንት የ "ብትወዳደርም አትመረጥም!" ዘቻ እና ማስፈራሪያ ከምን የመነጨ ይሁን ? የትም ያልተሞከረ ሀገርአቀፍ አሰራር ያፈነገጠ የብርሃኑ ነጋ የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ አመራሮች ሹመትና ጠልቃ ገብነት ምን ታስቦ ነው? እና ለሌሎችም ጥያቄዎች ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ምላሽ አላቸው

እንደተለመደው የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የፓለቲካ ወጌሻ ልዩ እንግዳ ዝግጅት በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፓለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ ከፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ ማድረግ ልዩ ዝግጀት አሰናድተው እነሆ እንደሚከተለው አቅርቧል ተጋበዙልን🙏

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንግዳችን እንደወትሮው ጥሪያችንን ተቀብለዉ በድጋሚ እንኳን ደህና መጡ። ያዉ ባለፈዉ እንዳሉት የሚዲያችን ቤተሰብ ስለሆኑ ቀጥታ ወደ ጥያቄ መግባት እችላለሁ ?
✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ተፈቅዷል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ዛሬ ስለ ዩንቨርስቲዎች እናወራለን።

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ መልካም ደስ ይለኛል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ዘመነ መንግስት ጀምሮ በመላዉ ኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንቶች በቀጥታ ከማዕከል የሚሾሙበት አሰራር ቀርቶ የአካዳሚክ ማህበረሰብ ጭምር በሚሳተፉበት ምርጫ እንዲሆን መደረጉ ይታወቃል። በአሁኑ ሰዓት ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ከዚህ ሀገር አቀፍ አሰራር ባፈነገጠ መልኩ በብርሃኑ ነጋ የተሾሙ አካላት እያስተዳደሩ ቀጥለዋል፤ ይህ በዩኒቨርስቲው እና በዩንቨርስቲው ማህበረሰብ ላይ የሚፈጥረዉ ተፅዕኖ ይኖር ይሆን ?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ በሚገባ። በመጀመሪያ በሐገር አቀፍ ደረጃ ያለዉ አሰራር በወጥነት በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች መተግበር አለበት። ሌላዉ ይህ የምርጫ አሰራር በተቋም ደረጃ ዲሞክራሲን ለመለማመድ እድል የሚሰጥ ነው። ከዛ ባለፈ ለዩኒቨርስቲው እድገት ያለዉ ሚና ማሰብ ከሚቻለዉ በላይ ነው።እጩዎቹ በዩኒቨርስቲው ለማምጣት ስላሰቡት እድገት በአጭርና በረዥም ጊዜ ግባቸዉ ምን እንደሆነ በማህበረሰብ አገልግሎት፣ በመማር ማስተማር ላይ ሥራ ላይ እና በመሳሰሉት ምን ለመሥራት እንዳቀዱ የሚያቀርቡበትና የተሻለ ሰዉ እንዲመረጥ እድል የሚሰጥ ነው።

በዚህ አይነት ቀድሞ በፖለቲካ ዉግንና ይደረግ የነበረዉ ሹመት በተወሰነ ደረጃ የተሻለ አቅም ያላቸዉ ሰዎች ዩኒቨረስቲዎችን እንዲመሩ እድል የፈጠረ አሰራር ነው። ይህ ጥሩ አሰራር በዎላይታ ሶዶ ብቻ እንዲቋረጥ መደረጉ በጣም አሳዛኝ ነው። ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ለሕግ የማይገዙ ፈላጭ ቆራጭነትን የሚሹ መሆናቸዉን ያሳያል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ በእርግጥ የሹመት ደብዳቤ የጻፉት ብርሃኑ ነጋ ናቸዉ፣ ጊዜያዊ በሚል፤ የተሾመዉ ግለሰብስ ላይ ችግር የሚሉት ነገር አለ ?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ጉዳዩ የግለሰብ አይደለም፥ የመርህ፣ የሕግና የአሰራር ነው። ምናልባት አንድ ዶክተር መድሕን ማርጮ የተባለ ምሁር በጉዳዩ ላይ አስተያዬት በመስጠቱ፣ የአሁኑ ፕሬዘዳንት በዉስጥ መሥመር "ብትወዳደርም አትመረጥም!" ብሎ ጽፎለት፣ የለጠፈዉን አይቸዋለሁ። እንግዲህ በዚህ ደረጃ ምርጫም ቢደረግ ያለዉን አሰራር ጠልፎ አለአግባብም ቢሆን ያስመርጠኛል ብለዉ የሚያምኑት አካል ይኖር ይሆን የሚል ጥርጣሬም የሚያጭር ነው።

እኔ በበኩሌ ግን የአሁኑም ፕሬዘዳንት፣ እቅዳቸዉን አቅርበዉ እድሉ ተሰጥቷቸዉ በሐቀኛ መንገድ ቢወዳደሩ ችግር የለብኝም። ጉዳዩ የግለሰብ ሳይሆን፣ የትዉልድ ተሻጋሪ ተቋም ግምባታ እና በሕግ የመመራት ጉዳይ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የምክትል ፕረዚዳንቶችም ጉዳይ የግለሰብ ሳይሆን፣ የትዉልድ ተሻጋሪ ተቋም ግምባታ እና በሕግ የመመራት ጉዳይ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የምክትል ፕረዚዳንቶችም ጉዳይ ተመሳሳይ ነው።
🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ ይህ የዩኒቨርስቲ ፕረዚዳንቶችን በምርጫ የመሾም አሰራር በተጨባጭ ለዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የሚፈይደዉ አሁናዊ ነገር ካለ ቢያስቀምጡልን ?✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ የዎላይታ ሕዝብ በኢትዮጵያ ሐገረ መንግስት ግምባታ አቅጣጫ ላይ ባለ ያለመግባባት ምክንያት ለዘመናት ሲቀጣና ለተንኮለኛ አሰራሮች ተጋልጦ የኖረ ሕዝብ ነው። ይህን ዩኒቨርስቲ ማስከፈቱም ከብዙ ፈተናዎች በኃላ ነው የተቻለዉ። አሁን ደግሞ መንግስት የትምህርት ጥራት ወድቋል ብሎ ተማሪዮችን በገፍ እየጣለ ነው።

ስለዚህ ነገ ከነገ ወዲያ የዩኒቨስቲዎች መዘጋት እና የደረጃ ማዉረድ ሥራ ሊሰራ ይችላል። ስለዚህ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ብቁ ፕረዚዳንቶችን አግኝቶ እራሱን ማሳደግ አለበት። ይሄን የምለዉ ግጭትን ከማስወገድ፣ አቅምን ለእድገት አሟጦ ከመጠቀም አንጻር ነው እንጂ መቼስ የዛ አይነት ዉሳኔም ከመጣ በአካባቢው ሲሰራ ከኖረዉ የብሔር ጭቆና አንጻር በተለዬ ሁኔታ መታየቱ የግድ ነው። በዋናነት ግን የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ እንዲያድግ፣ እንዲዘምንና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እናመሰግናለን።✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን። ሚዲያ, ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን, ስለዘውትር አብሮነታችሁ እናመሰግናለን🙏

 👉 በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ ማሪ ከተማ የሚስተዋለው የኔትወርክ መቆራረጥ ምክንያት በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ከፍተኛ የሆነ ችግሮችን እየደረሰ ይገኛል ።👉 በዚህ በሰለጠነ በ21ኛ...
24/10/2024



👉 በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ ማሪ ከተማ የሚስተዋለው የኔትወርክ መቆራረጥ ምክንያት በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ከፍተኛ የሆነ ችግሮችን እየደረሰ ይገኛል ።

👉 በዚህ በሰለጠነ በ21ኛ ክፍለ ዘመን ሁሉም ክንውኖችዎች በኔትወርክ በሆነበት ዘመን እኛ ግን ከቴክኖሎጂ ውጪ ሆነን ዘመናትን እየቆጠረን እንገኛለን ።

👉 በጣም ያሳዘነኝ ነገር ብኖር መንግሥት ሁሉም ስርዐቱን በድጅታል ዜዴ ለመምራትም ሆነ ለማስተዳደር እያደረገ ያለው ጥረት እጅግ በጣም ጥሩ ብሆንም እንደ እኛ አከባቢ ግን ከፍተኛ የሆነ እርምጃዎችን ወደኃላ ይጎትታል ።

👉 ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ በከተማው በቂ የኔትዎርክ ታዎር ካለመኖሩ የተነሳ በከተማው በሚኖሩ ማህበረሰቦች ላይ ብዙ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል።

👉 በሀገራችን ኢትዮጵያ በሁሉም ቦታ በሚባል ደረጃ ከ2G እሰከ 5G ድረስ የኔትወርክ ታዎር ዝርጋታ ተደርጓል ፦ ይሁን እንጂ እንደ እኛ ወረዳ አይደለም 5G 2G ኔትወርክ መኖሩ ያስጠራጥራል ።

👉 ከዚህ የተነሳ በከተማው የሚኖሩ ነዋሪዎች በማህበራዊ ሆነ በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች እጅግ በጣም ከፈተኛ የሆነ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል። ብዙዎች ታድሏሉ ከ2G ተነስተው በ5G እያሚበሻበሹ ይገኛሉ እኛ ግን አይደለም በ online የተለያዩ ስራዎችን መስራት እርስበርስ ለመደዋዎል እንቸገራለን ።

👉 በወረዳ መንግስት አቅም የሚፈታ ችግር አይደለም። ለዞኑም ሆነ ለክልል መንግሥት የማይቻል ችግር ስለሆነ እኛ የማሪ ማንሳ ወረዳ ማሪ ከተማ ነዋሪዎች ለኢትዮ ተሌኮሚ አቤት ብለናል ።

👉 ነዋሪዎቹ ሥራቸውን ለማቀላጠፍ ከመቸገራቸው ባሻገር ማህበራዊ ጉዳዮቻቸዉን በጊዜ ካለመፈጸማቸው የተነሳ ችግር ዉስጥ መግባታቸዉንም ብዙዎች እያነሱ ይገኛሉ ችግሩ በፍጥነት ካልተቀረፈ ይበልጥ እንደሚያሳስባቸዉ የሚመለከተው ክፍል አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አለበት ባይ ነኝ ።

👉 ከዚህ የተነሳ ማህበረሰቡ ቀልጣፋ የኢንተርኔት አግልግሎት በባንክ፣ በቢሮ፣በግልም ሆነ በተቋም ደረጃ ለማግኘት እየተቸገረን እንገኛለን ። ምንም አይነት ኔትወርክ በሌለበት ከተማ ተክኖሎጂ እንጠቀማለን ብሎ ማሰብ ራሱ አንድ ታርክ ነው። ይህ የአሁኑ ሳይሆን ከማህበረሰቡ ጋር የቆዬ ብሆንም እስካሁን ድረስ እልባት ማግኘት ሰማይ ከምድር እንደምርቅ ርቆ ይገኛል።

👉 የወረዳ መንግሥት በተለያዩ ሚድያ አማራጮችን በመጠቀም የከተማችን ነዋሪዎች ችግሮችን ይፈታል በማለት ለሚመለከተው ክፈል ሪፖርት ብያደርጉም ማንም ለዚህ ከተማ ያለው ችግር ምንድነው ብሎ የጠየቀ አካል የለም ።

👉 አጠቃላይ በማሪ ከተማና አካባቢው እየተስተዋለ ያለውን የኔትዎርክ መቆራረጥ ችግሮችን በዘላቂት ለመቅረፍ ተጨማሪ የኔትወርክ ታዎር ዝርጋታ መፈጸም እንደሚያስፈልግም በብዙ መድረኮች ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ እየተጠባበቅን እንገኛለን ።

👉 የወረዳ መንግስት ከራሱ የምጠብቀውን የቦታ ልየታ ጭምር ጨርሰው ከመቼ እስከ መቼ ይህ የገዘፈው ችግር ከጫንቃችን ይወርዳል ብሎ በጠባበቅም ኔትወርክ በሌለበት ከተማ ስም ካርድ ከመሸጥ ውጪ ማንም ዞር ብለው የማህበረሰብ ችግር ምን እንደሆነ ማየት ከብዳቸው በዝምታ ተውጧል ።

👉 ምላሽ እንፈልጋለን ‼ የሚመለከተው ክፈል ለዚህ ችግር አስቸኳይ የሆነ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን መፈለግና ለማህበረሰቡ ፈጣን የሆነ ምላሽ መስጠት አለበት ‼ሲል ይህን መልዕክት በውስጥ መስመር የሚዲያችን ተከታይ ልኮልናል።

Mari Mansa Woreda Government Communication Affairs Office

Dawuro Media Network

Dawu

22/08/2024
ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ የሄቨን እናትን በማግኘት አጽናንተዋል::ልጇን በግፍ ተነጥቃ ባለፈው አንድ ዓመት ፍትህ ሳታገኝ ለቆየችው እህታችን የፍትህ ...
21/08/2024

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ የሄቨን እናትን በማግኘት አጽናንተዋል::

ልጇን በግፍ ተነጥቃ ባለፈው አንድ ዓመት ፍትህ ሳታገኝ ለቆየችው እህታችን የፍትህ ሂደቱን ለመከታተል ፣ ያለችበት ሁኔታ የተሻለ እንዲሆንላት እና ተጋላጭነቷን ለመቀነስ እንዲመች የከተማ አስተዳደሩ አንድ የመንግስት የመኖሪያ ቤት እንዲሁም በሙያዋ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ እንድትሰራ መመቻቸቱን ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል::

የህፃን ሄቨን ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ በመሆኑ ድርጊቱ ተገቢውን ፍትህ ማግኘቱ የሌሎች ህፃናት ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስተዋፅዖ ያለው ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች የዚህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እንዳይፈፀም የማህበረሰቡ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ እና ችግሩ የጋራ ጉዳይ በመሆኑ ሁላችንም ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባልም ብለዋል::

ከስፖርት ዓለምየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2017 የውድድር ዓመት የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ወላይታ ዲቻ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ይገናኛል!!
21/08/2024

ከስፖርት ዓለም

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2017 የውድድር ዓመት የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ወላይታ ዲቻ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ይገናኛል!!

በኬንያ ሚስቱን ጨምሮ ከ40 በላይ ሴቶችን በመግደል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ከእስር እንዲያመልጥ አግዘዋል ያለቻቸውን አምስት የፖሊስ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ። የኬንያ ፖሊስ 12...
21/08/2024

በኬንያ ሚስቱን ጨምሮ ከ40 በላይ ሴቶችን በመግደል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ከእስር እንዲያመልጥ አግዘዋል ያለቻቸውን አምስት የፖሊስ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ።

የኬንያ ፖሊስ 12 ኤርትራዉያንን ጨምሮ ተጠርጣሪው ኮሊንስ ጁማይሲ ከእስር ማምለጣቸውን ትናንት ማክሰኞ አስታውቆ ነበር ። ትናንት ማለዳ የእስረኞቹን ማምለጥ የተረዳው የሀገሪቱ ፖሊስ መልሶ በቁጥጥር ስር ለማዋል መጠነ ሰፊ ዘመቻ መክፈቱን አስታውቆ ነበር።

የኬንያ ፖሊስ ኮሚሽን ተጠባባቂ ዋና አዛዥ ጊልበርት ማሴንጌሊ እንዳሉት እስረኞቹ እንዲያመልጡ ከፖሊስ አባላት ድጋፍ ሳያገኙ እንዳልቀሩ በምርመራ ተረጋግጧል።

በዚህም በሰዓቱ በጥበቃ ላይ ከነበሩ ስምንት የፖሊስ አባላት አምስቱ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

የፖሊስ መኮንኖቹ እስረኞቹን ለማስመለጥ የነበራቸውን ሚና ለማጣራትም ፖሊስ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መጠየቁን አዛዡ ተናግረዋል።

ከተጠርጣሪው ጋር ያመለጡት አስራ ሁለቱ ኤርትራዊያን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ የገቡ እንደነበር ፖሊስ አመልክቷል።

በርካታ ሴቶችን በመግደል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለው ጁማይሲ የስድስት ሴቶች አስክሬን በቆሻሻ ስፍራ ተጥሎ ከተገኘ በኋላ ባለፈው ሐምሌ 9 ቀን 2016 ዓ/ም ነበር በቁጥጥር ስር የዋለው ።

ስለሚመለከተው ክፍል አስቾካይ መፍሔት እንድሰጥ!!!
20/08/2024

ስለሚመለከተው ክፍል አስቾካይ መፍሔት እንድሰጥ!!!

በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ልዩ የክረምት አቅም ግንባታ ስልጠና የተመደቡ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ሥልጠናውን በከፍተኛ ደረጃ ተቃወሙ።እነዚህ አካላት ወደ ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ...
03/08/2024

በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ልዩ የክረምት አቅም ግንባታ ስልጠና የተመደቡ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ሥልጠናውን በከፍተኛ ደረጃ ተቃወሙ።

እነዚህ አካላት ወደ ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡት በዋናነት ከዎላይታ ዞን ከሁሉም ወረዳዎች፥ ከጎፋ ዞን እና ከጋሞ ዞን ከተወሰኑ ወረዳዎች የመጡ እንደሆነ ተገልጿል።

ከስፍራው የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በስልጠናው እንዲሳተፉ የተላኩት የ2ኛ ደረጃ የሳይንስ ትምህርቶች መምህራን፥ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን እና የት/ቤት አመራሮች ሲሆኑ ሰልጣኞች ተቃውሟቸውን እያሰሙ የቆዩት ከማክሰኞ 23 - እለተ አርብ ቀን 26/11/2016 ዓ.ም ድረስ መሆኑም ተነግሯል።

የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጉቼ ጉሌ እና የስልጠናው አስተባባሪዎች መምህራንን "ለማግባባት" በሚል ሁለት ዙር ስብሰባ ቢያካሂዱም "ሠልጣኞቹ በሁለቱም ስልጠና መግባባት ባለመቻላቸው ስልጠናውን ረግጦ ወጥተዋል" ሲል አንድ ሰልጣኝ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አስረድተዋል።

በተጨማሪም ሐሙስ ዕለት በቀን 27-11-2016 ዓ.ም ደግሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበባየሁ፥ የዎላይታ ዞን ትምህርት መመሪያ ኃላፊ እና የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ጎበዜ ጎዳ እና የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንቶች በጋራ ሆኖው ሦስተኛ ዙር አወያይተው የሰጡት ምላሽ አጥጋቢ ባለመሆኑ ሠልጣኞች ስብሰባውን አቋርጠው መውጣታቸውንም አክለው አብራርተዋል።

መምህራኑና የት/ቤቶች አመራሮች ስልጠናውን እንዲቃወሙ ካደረጉ ምክንያቶችን ሰልጣኞች ሲገልፁ "ስልጠናው ለስሙ ስልጠና ተብሎ ነገር ግን ውሎ አበል የሌለው በመሆኑ፥ አብዛኞቹ መምህራን እና የት/ቤቶች አመራሮች ከሚሠሩበት ወረዳ የግንቦት ወር ደመወዝ ጭምር ያልተከፈላቸው መሆኑ፥ የተከፈላቸውም ከ30% -50% ብቻ ሆኖ ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን አደጋ ጥሎ መምጣታቸው ነው"

ከዚያ ባሻገር "ሥልጠናው የተዘጋጀበት ዋና ዓላማ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርስቲ በተሠጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ተማሪዎች እጅግ በጣም ዝቅተኛ ውጤት በማምጣታቸው ለዛውም ምክንያቱ በዋናነት ለሁሉም የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት መ/ራን ዕውቀትና ክህሎት ስለሌለ ነው ተብሎ በመታሰቡም አለመግባባት ተፈጥሯል።

ከ20 ቀን ስልጠና በኋላ በኦን ላይን በሚሰጥ ፈተና 70% እና ከዛ በላይ ያላመጣ የደረጃ ዕድገት እና ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞችን አያገኝም መባሉ፥ ፈተናው በተጨባጭ መምህሩ በት/ቤት ከሚያስተምረው ትምህርት ይዘት ይልቅ በትዮሪ /በንድፈ ሀሳብ ላይ ብቻ ያተኮረ መሆን፣ ከኬጂ እስከ ማስተርስ ድግሪ ድረስ ተምረው አብዛኛው ከ25 ዓመት በላይ የሥራ ልምድ ኖሮት በርካታ ምሁርን ልፋቱንና አገልግሎቱን ውድቅ ለማድረግ መታሰቡ ተቋውሞ አስነስቷል።

ከሞላ ጎደል በዚህ ዕድሜ በቤቱ በተሻለ መኝታ የሚያድረውን መምህር ጥሩ ሽታ በሌለው፥ ሎኬር፥ ጠረጴዛ እና ወንበር በሌለበት ማጎር፥ በዩኒቨርስቲው የሚሰጠው የካፌ አገልግሎት ምቹ አለመሆን እና ነጋ ጠባ ሽሮ ማቅረብ፣ የተዘጋጁት ሁለት የስልጠና ሞጁሎች በውስጣቸው የያዟቸው የትምህርት ይዘቶች መምህሩ ከዚህ በፊት በተለያዩ ስልጠናዎች የሚያውቋቸው መሆኑ፥ በሞጁል ጥራት ላይም ችግር መኖሩ እንዲሁም ስልጠናው ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ሁኔታ ያልፈጠረ መሆኑ ተጠቅሷል።

ሌላው በኦን ላይን የተሰጠው ቅደመ ፈተና የተባለው እና በስልጠና ሞጁል ላይ የስልጠና ይዘቶች በብዛት የማይገናኙ መሆናቸው፣ መንግሥት ደመወዝ በጊዜ ባለመክፈል እና አስፈላጊ የትምህርት ቁሳቁሶችን ሳያቀርብ የትምህርት ሥራ እንዲወድቅ እያደረገ በተቃራኒው ችግሮችን ሁሉ በመምህራን በመዘፍዘፉ፣ የክልሉ መንግሥት ይህን ሁሉ ችግር እንደ ቀላል በማየት "ክልሉን እየመራሁ ነው" መባሉ ሠልጣኞችን ለተቃውሞ ያነሱት እነዚህ ከፍ ሲል የተጠቀሱ እና የመሳሰሉ ችግሮች እንደሆነም አስረድተዋል። Wolayita Times

እውነት ይህ ሰውን ምን ማለት እንዳለብኝ ቃላት ያጥረኛል
02/08/2024

እውነት ይህ ሰውን ምን ማለት እንዳለብኝ ቃላት ያጥረኛል

11/07/2024

 ወንድማችን አቶ ናጌሶ ጋሻላ በወላይታ ዞን በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ቦምቤ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሠራተኛ ስሆን ባደረበት ድንገተኛ በሽታ በተለያዩ በጤና ተቋም ሲታከም የቆዬ ቢሆንም በህክምና ...
08/07/2024


ወንድማችን አቶ ናጌሶ ጋሻላ በወላይታ ዞን በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ቦምቤ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሠራተኛ ስሆን ባደረበት ድንገተኛ በሽታ በተለያዩ በጤና ተቋም ሲታከም የቆዬ ቢሆንም በህክምና ምንም ዓይነት ለዉጥ ባለማሳየቱና ዉሎ እያደረ ሁለቱም ዓይን ብርሃንና ጨለማን መለየት ያቃተው በመሆኑ ወደ ተሸሌ ህክምና ተቋም ለመሄድ ከወላይታ ሶዶ አቶና Teaching and specialized ሆስፒታል ወደ አድስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለመሄድና ቀዶ ጥገና ለማስደረግ ረፐር የተደረገ ሲሆን ግለሰቡ የመንግሥት ሠራተኛ በመሆኑ ለላ መተዳደርያ ምንም የሌለ ሲሆን አሁን ለህክምና የተጠየቀውን ገንዘብ መጠን 700,000/ሳባት መቶ ሺህ /ብር አውጥተው ለመታከም ለእሱ ሆነ ለወላጅ ቤተሰቦች ምንም አቅም የሌላቸው መሆኑን እንገልፃለን።ወንድማችን አቶ ናጌሶ ጋሻላ የአንድ ልጅ አባት እና የወላጅ አባተን በዚሁ ሳምንት ውስጥ በሞት ያጣ ወንድማችን ነውና

አቶ ናጌስ ከዚህ ቀደም ህብረተሰብ በጤናው ዘርፍ በታማኝነትና በቅንነት በማገልገል ላይ እያለ በድንገት በሽታ ስለገጠመው ለወገን ደራሽ ወገን ነውና "እግ/ር" ሠላሙን ያበዛላችው ሁላችሁም ለወንድማችን ለአቶ ናጌሶ ጋሻላ ህይወት ለመታደግ አስፈላጊውን የሰባዊ ትብብርና ድጋፍ እንድታደርጉ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። Acc፦1000287303158

የቢዝነስ አማካሪና የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እኛ ጋ ስመጡ የሚያገኙት መልካም አጋጣሚዎች!!!አሁን ያለቡትን ሕይወት አልወደዱም? መቀየር መለወጥ እየፈለጋችሁ አማራጭ አጥተዋሉ?ቢዝነስ ለመጀመ...
06/07/2024

የቢዝነስ አማካሪና የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ

እኛ ጋ ስመጡ የሚያገኙት መልካም አጋጣሚዎች!!!

አሁን ያለቡትን ሕይወት አልወደዱም? መቀየር መለወጥ እየፈለጋችሁ አማራጭ አጥተዋሉ?

ቢዝነስ ለመጀመር አስበው ግን አማራጭ አጥተዋሉ? ከሆነ በዚህ ስልክ መደወል፦ +251987234366

ለመንግሥት መስሪያ ቤት፣ለግል ድርጅት ፣ለሆቴሎች የቢዝነስ የማማከር እንድሁም የግል ስብዕና/የሕይወት ክህሎት ስልጣናዎችን እንሰጣለን!

ሥራችን እናንተን በታማኝነት ማገለገል ነው
+251966554350

መተጋገዝ ባህላች አይደል
06/05/2024

መተጋገዝ ባህላች አይደል

የቢዝነስ አማካሪና የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እኛ ጋ ስመጡ የሚያገኙት መልካም አጋጣሚዎች!!!አሁን ያለቡትን ሕይወት አልወደዱም? መቀየር መለወጥ እየፈለጋችሁ አማራጭ አጥተዋሉ?ቢዝነስ ለመጀመ...
01/05/2024

የቢዝነስ አማካሪና የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ

እኛ ጋ ስመጡ የሚያገኙት መልካም አጋጣሚዎች!!!

አሁን ያለቡትን ሕይወት አልወደዱም? መቀየር መለወጥ እየፈለጋችሁ አማራጭ አጥተዋሉ?

ቢዝነስ ለመጀመር አስበው ግን አማራጭ አጥተዋሉ? ከሆነ በዚህ ስልክ መደወል፦ +251987234366

ለመንግሥት መስሪያ ቤት፣ለግል ድርጅት ፣ለሆቴሎች የቢዝነስ የማማከር እንድሁም የግል ስብዕና/የሕይወት ክህሎት ስልጣናዎችን እንሰጣለን!

ሥራችን በታማኝነት፣በትጋት በፍቅርና በአንድነት በመሠራት አድስቱ ኢትዮጰያን መፍጠር ነው

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋች በአርባምንጭ ከተማ በድንገት ህይወት ማለፉ ተገለፀ።የባሕር ዳር ከነማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው አለልኝ አዘነ በድንገት በሌሊት ህይወቱ ...
27/03/2024

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋች በአርባምንጭ ከተማ በድንገት ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

የባሕር ዳር ከነማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው አለልኝ አዘነ በድንገት በሌሊት ህይወቱ ማለፉን ቤተሰቦቹ ገልጿል።

እንደ ቅርብ ዘመዶች ገለፃ ተጫዋቹ ከ15 ቀን በፊት የተሞሸረ፣ በጉዳት ምክንያት ከክለቡ ስብስብ ጋር ያልነበረ ሲሆን በትውልድ ቦታው አርባ ምንጭ ሌሊት ምንም ፍንጭ ሳይኖረው በድንገት "ራሱን በማጥ'ፋት" ህይወት አልፏል ተብሏል።

ተወዳጁ ተጨዋች በአርባምንጭ እና በደጋፊዎቹ እጂግ የሚወደድ ነበር።

ለወዳጅ ለዘመዶቹ እና አድናቂዎቹ መፅናናትን እንመኛለን። Wolayita Times

ላንተ ለውጥ ምን ማለት ይሁን ?እንዴት ትገነዘባለህ ?አብዛኛው ሰው ለወጥ ማለት በልብስ እና በጫማ ይለካሉ ?አንተስ ታዲያ ለውጥ ስባል እንዴት ነው ለራሴ የምታምነው?መልካም ምሽት ተመኘሁላች...
26/03/2024

ላንተ ለውጥ ምን ማለት ይሁን ?እንዴት ትገነዘባለህ ?አብዛኛው ሰው ለወጥ ማለት በልብስ እና በጫማ ይለካሉ ?አንተስ ታዲያ ለውጥ ስባል እንዴት ነው ለራሴ የምታምነው?

መልካም ምሽት ተመኘሁላችሁ🙏

ሁሌም የአዕምሮ ስንቅ!

ነብስ ይማር 😭ልብ ይሰብራል😭                   በአስቸኳይ ቤተሰቦቿን ፈልጉልን🙏ይህች ሴት ስሟ ነፃነት ደሴ ቱጀሬ ነው! አዲስአበባ ቄራ አካባቢ የሚገኝ ምግብ ቤት ውስጥ በወጥ ሰሪ...
25/03/2024

ነብስ ይማር 😭

ልብ ይሰብራል😭

በአስቸኳይ ቤተሰቦቿን ፈልጉልን🙏

ይህች ሴት ስሟ ነፃነት ደሴ ቱጀሬ ነው! አዲስአበባ ቄራ አካባቢ የሚገኝ ምግብ ቤት ውስጥ በወጥ ሰሪነት ተቀጥራ እየሰራች ዛሬ ለሊት ድንገት የከሰል ጭስ አፍኗት ህይወቷ አልፏል😭

አስክሬኗ ዘውዲቱ ሆስፒታል የሄደ ሲሆን ቤተሰብ በአስቸኳይ ካልተገኘ መዘጋጃ እንደሚቀብራት ፖሊሶች አሳውቀዋል!

እህታችን ስራ የገባችው በደላላና መታወቂያዋ ብቻ ስለሆነ የቤተሰቦቿን አድራሻም ሆነ ስልክ ማግኘት አልተቻለም!!

መታወቂያዋ ላይ የእናቷ ስም አልማዝ_ላንጬ የትውልድ ቦታም ወላይታ ወረዳ ሆ/ቻ(ሆቢቻ) ይላል!!

ለቤተሰብ መርዶና ሀዘኑ ከባድ ቢሆንም ቢያንስ አስክሬኑን እንዲያገኙ ሼር በማድረግ ቤተሰቦቿን እንፈልግ🙏

* 0912852892

ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

Address

S**o
NOMORE

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolayita times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wolayita times:

Videos

Share