አብሮነት/Abronet

አብሮነት/Abronet አብሮነታችን የሚያጎሉ በርካታ አዝናኝ፣ አስተማሪና መረጃ ሰ?

አብሮ መሆን መልካም ነውና አብረን ስለቴአትር፣ በየዘመኑ ሥላሉን የትምህርት ሥርዓቶች፣ በየዘመኑ ያሉ የእናቶቻችን የልጅ አስተዳደግ፣ በየዘመኑ የነበሩ የአስተማሪና ተማሪ ግንኙነት፣ በየዘመኑ የሚታዩ የወላጅና ልጅ ግንኙነቶች፣ በየዘመኑ የተሰሩ የሙዚቃ ስራዎች፣ በየዘመኑ የተጻፉ ግጥሞቻችን፣ በየዘመኑ የነበሩ/ያሉ የአኗኗር ዘዬ… እና ሌሎችም የየዘመኑ ድርጊቶች ዘና እያረጉ ያስተምሩን ዘንድ ይደመጣሉ፡፡
ሥራዎቻቸው ለኅትመት ያልበቃ ገጣሚያን አብሮነታችንን በሚያጎላ መልኩ ግጥሞቻቸውን በቀጥታ ለአድማጭ ያቀርባሉ፤ ድምጻውያውንም እንደዛው፡፡ የአድማጮች ተሳትፎ ደግሞ የዝግጅቱን ውበት የበለጠ ያጎሉታል፡፡

01/09/2024

አብረን ስንሆን ያምርብናል!!

20/12/2022

መንግስት Vs ሕጻናት

09/12/2022

ዓለም ሚዛናዊ አይደለችም ወደፊትም አትሆንም!! ሚዛናዊ የሆነ ህይወት ለመኖር ውስጣችንን ማዳመጥ አለብን!!

08/12/2022

የበደሉንን ይቅር ስንል ጥላቻ ከውስጣችን ተነቅሎ ይወጣል!!

08/12/2022

የሰው ልጅ ከነስብራቱም ቢሆን ጠንክሮ መኖር ይችላል ምክንያቱም ምሉዕ ሆኖ ስለተፈጠረ!!

08/12/2022

ሁሌም ቢሆን ከምንወደው ሰው ጋር ካላወራን ምን እንደሚያስብ ማወቅ አይቻልም!!

08/12/2022

በህይወታችን ቀዳሚው ነገር ዛሬ በህይወት መኖራችን ነው!!

08/12/2022

ብዙዉን ጊዜ ሌሎች ሰዎች እንደሚሞቱ ነው የምናስበው!!

18/11/2022

Don't you stop loving!!

18/11/2022

የምንበላው የምንጠጣው ሳይጎልብን የተራቡትን ማብላት ምኑ ነው መስጠት የሚባለው?!?! ይሄ አብሮ መብላት ነው የሚባለው!!

#አብሮነት

04/11/2022

ልቤ ፊት... አትቅጣኝ
[ ]

ልትቀጣኝ አስበህ እንደሁ...
የመብረቅ ጅራፍ ገምደህ - ጀርባዬን ግረፍ ፤ ምታ፥
ቀላያትን ተርትረህ ለኔ ብቻ ክፈት ፤ ፍታ፥
ግን እባክህ...
ልቤ ፊት እንዳይሆን ጌታ።

ልቤንማ...
የተስፋ ድንጋይ አስነክሼው፥
አይዞህ እያልኩ እየገፋሁ፥
ከበረሀ ሐሩር መሐል
ስንቴ ሲያምነኝ ጥዬው ጠፋሁ።

ልቤንማ...
ዐይኖቹን በጨርቅ እያሰርሁ፥
ደሞ በጥፊ እያጣፈርሁ፥
"ማነው የመታህ?" እያልሁት ፥ ስስቅበት ፣ ስተፋበት፥
(ያውም'ኮ ከካደው ጋር
ያውም'ኮ ከሸጠው ጋር)፡ ስሳለቅ ስዘብትበት፥

በአእምሮዬ ተከልዬ፥
ከገዳዮቹ መሐል ቆሜ - 'ስቀለው ስቀለው' ብዬ'፥
መስቀሌን አሸክሜው፡ ጎለጎታዬን ሲወጣ፥
(በሰራሁት እንዳልቀጣ)
የምጥ ስቃዩን ሳጋፍር፥
ከሕዝቡ ጋር ስጨፍር፥
ስጣደፍ ሞቱን ለማክበር፥
አካሌ'ኮ አይመስልም ነበር።
ያሸከምኩት መስቀል ላይ ፥ እርቃኑን ቸንክሬ ብሰቀለው፥
ከሰዉ መሐል እያየኝ...
"የሚያደርገውን አያውቅም ፤ አባት ሆይ ይቅር በለው፥"
ብሎ ለኔው ለምኖህ ፥ ደጋግሞ እንደመሞቱ፥
ደሞ ቀና ቀና እያለ...
ሊጎበኘኝ በምህረቱ
አሁን ገና መነሳቱ
አሁን ገና መቃናቱ
አሁን ገና መበርታቱ...

ደሞ ዛሬ...
በአይታረም ገላዬ...
የሰጠኸኝን ትሩፋት፥
መልሼ በእጄ ስገፋት፥
እንደልጅ ልብሴን አውልቀህ ፥ ስትገርፈኝ በማጣት ሳማ፥
አፌን በእጅህ አፍንልኝ ፤ ጩኸቴን ልቤ እንዳይስማ።
በሺ ቁስል ተወርሬ ፥ ላዝግመው እንጂ ወደፊት፥
ይሄን አካል ተሸክሜ ፥ አልችልችልም መቆም እሱ ፊት።

ቅጣቴን ነው ጌታዬ...
አንክተኝ፡ ጣለኝ፡ ስበረኝ!
ግን በእናትህ..!
በድኔን እንዳያይብኝ፡........ከልቤ አርቀህ ቅበረኝ.....

[ ሚካኤል ምናሴ ]

03/11/2022

"ለማሰብ ማሰብ ያስፈልጋል"

28/10/2022

ደህና ነን ደህና መሆን ተስኖታል!!

በቅርብ ቀን!!
22/10/2022

በቅርብ ቀን!!

12/09/2022

በሕይወት ውስጥ የሚገጥሙን ሁነቶችና እኛ ለተፈጠረው ነገር የምንሰጠው ምላሽ በአዕምሮአችን ውስጥ ልክ እንደ አጭር ቪዲዮ ይጫወታል፡፡
የቪዲዮ ማጫወቻው ሁሌም ሥራውን ይቀጥላል። የምናያቸው አብዛኞቹ ምስሎች ታዲያ የቆሻሻ መኪኖች ናቸው:: በአዕምሮአችን ያስቀመጥናቸው
ሁነቶች የተጎዳንባቸውን፣ያፈርንባቸውን፣የተጨነቅንባቸውን፣የተሰላቸንባቸውንና የተናደድንባቸውን ጊዜያት ያስታውሱናል።
የሥነ-ልቡና ባለሙያው ሮይ ባምስተርና የሥራ ባልደረቦቹ በፍሎሪዳ ስቴት ዩኒቨርስቲ Bad is Stornger than Good በሚለው የጥናት ፅሑፋቸው ላይ መጥፎ ሁኔታዎች በመልካሞቹ ላይ ያላቸው ታላቅ ተፅዕኖ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ላይ ይንፀባረቃል፡፡ - --መጥፎ ስሜት- - - እና መልካም ያልሆነ ግበረ መልስ ተፅዕኖአቸው ከመልካሙ ልቆ ይታያል፡፡ መጥፎ መረጃ ከመልካሙ በላይ በዝርዝርይተነተናል- - - መጥፎ አስተሳሰቦችና የተዛቡ አመለካከቶች ለመፍጠር ፈጣንና ለውጥን ለመገዳዳር ቅርብ ናቸው፡፡

ዓባይ ኪዳኔ

12/09/2022

እኛስ ከማን ይሆን
የመታገስ ፅዋ በገፍ የወረስን፤
በሀዘን ገፃችን ላይ አመድ ሲጠብቁ
አደይ ነሰነስን።

/በቀላሉ አልኖርንም/

ሞት በክፋት እጁ ጥብቅ አርጎ ሲያቅፈን
እኛ መች ቀፈፈን

ሲገድሉን አልሞትንም
ሲገፉን አሎደቅንም

መች በቀላል ጣለን
መከራ እንደፈንግል፤
ታግለን ጨረስንና
እንደገና ትግል!

ዓለም ድል ባይሰጠን ለሹመት ባያጨን
እኛ መች ሊቆጨን!

/አለን እቺን ታህል/
ኑሮ ሸማ አስዎቦ ባያስነሰንሰን
ደሞ ላዲስ ትግል እንኳን አደረሰን።

10/09/2022

በሕይወታችን ውስጥ የሚገጥሙንን ችግሮች፣ አለመረጋጋቶች ወይም መሰላቸቶች እንድናስተናግዳቸው የምንመከረው ሁነቶቹን በመተው ነው፡፡ ነገር ግን ይህ አካሄድ የቆሻሻ መኪኖች በሚገጥሙን ጊዜ አይሰራም ይልቁንም መልካም ያልሆነ ምግባራቸው እንዲያልፈን ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ነገሮችን መተው በመጀመሪያ ሁነቱን እንድንቀበለውና ቦታ እንድንሰጠው ያደርገናል፡፡ ነገሩን ብንተወውም ተፅዕኖው ግን በውስጣችን ውስጥ ይቆያል፡፡ አልፎም እንድናስታውሰው ያስገድደናል፡፡ በጊዜ ሂደት ውስጥ መልካም ያልሆነ ትዝታችንን ለማጥፋት ኃይላችንን
ማሰባሰብ የምንችል ከሆነ ተፅኖው ይቀንሳል:: አለበለዚያ ግን የቀደመው መልካም ያልሆነ ትውስታ የዛሬ አቅማችንን አዳክሞ በሕይወታችን ውስጥ ረብ ያላቸውን ውሳኔዎች እንዳናሳልፍ ያግደናል:: እንዲህ ዓይነቱን ልምድ እያዳበርን ቆይተን ነገሩን ለመተው በጣርን ቁጥር ደግሞ ያልተፈለገ ንዴት፣ መሰላቸትና ተስፋ መቁረጥ መንገዳችንን ይቆጣጠሩታል፡፡

ዓባይ ኪዳኔ

10/09/2022

መልካም ለማሰብ እቅድ አያስፈልገውም!!

10/09/2022

የቆሻሻ መኪና ሕግ
"ትዕግስተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፣ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስዱ ይበልጣል፡፡" መፅሐፈ ምሳሌ 16÷32

ትርጉም የሌለው የሰዎች ድርጊት ስሜታችሁን እንዲረብሽ ምን ያህል ትፈቅዳላችሁ? ባህሪ ብልሹ አሽከርካሪ፣ ራስወዳድ አስተናጋጅ፣ ሁነቶችን የማያገናዝብ አለቃ ወይም ስሜት አልባ ሠራተኛ ምን ያህል ቀናችሁን እንዲረብሹ ዕድል ትሰጣላችሁ? ነገሮች እንዲያበቁ እስካልወሰናችሁ ድረስ ምናልባትም ጉዟችሁ የኋልዮሽ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ስኬታችሁ በሕይወታችሁ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረታችሁን በመሰብሰባችሁ ላይ ይመሰረታል፡፡

የዚህ መጽሐፍ ፀሐፊ ለሀሳቡ መነሻ የሆነውን ነገር ያገኘው ከሃያ ዓመታት በፊት ታክሲ ይዞ በሚሄድበት ወቅት በተፈጠረው ሁነትና በታክሲው አሽከርካሪ ምላሽ በመማረክ ነበር፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው

ፀሐፊው ይዞት የነበረው ታክሲ መንገዱን ጠብቆ በሚሄድበት ወቅት ከየት መጣ የተባለ ሌላ መኪና በድንገትና ህጉን ባልጠበቀ መልኩ ከማቆሚያው በመውጣቱ ለጥቂት የከፋ አደጋ ሳይደርስ ይቀራል፡፡ በዚህ ጊዜ ጥፋተኛ የሆነው አሽከርካሪ ድምፁን ከፍ አድርጎ መናገርና አልፎም የመሐል ጣቱን አውጥቶ በማሳየት መሳደቡን ይቀጥላል፡፡ ይሄኔ የታክሲው አሽከርካሪ ፍፁም በሆነ ፈገግታ ተሞልቶ እጁን በሰላምታ አውለበለበለት። ፍፁም ወንድማዊና በፍቅር የተሞላ ምላሽ ነበር:: ፀሐፊው የአሽከርካሪው ድርጊት ከአዕምሮ በላይ ሲሆንበት ጥያቄ አነሳ “ለምን እንደዚህ አደረክ? ሰውዬው እኮ ሊገለን ነበር” አሽከርካሪው መለሰ፡፡ “ብዙ ሰዎች እንደቆሻሻ መኪና ናቸው። መሰላቸት፣ ንዴት እና ተስፋ መቁረጥ ተሞልተው ይንቀሳቀሳሉ፡፡ የሰበሰቡትንም ቆሻሻ የሚያራግፉበት ቦታ ይፈልጋሉ፡፡ ከፈቀድክላቸው ማራገፊያ ያረጉሃል፡፡ ስለዚህ እንዲህ ዓይነት ሰው ሲገጥምህ የግል ጉዳይ አታድርገው፡፡ ይልቅ ፈገግ ብለህ መልካሙን ተመኝላቸውና አልፈሀቸው ሂድ፡፡ እመነኝ ደስተኛ ትሆናለህ፡፡”

@የቆሻሻ መኪና ህግ
ዓባይ ኪዳኔ

10/09/2022

.......የመቶ ብር ፎብያ........

"ማንም አለምን መቀየር ባይቻለውም ነገን ውብ እንዳያደርጋት ግን ማን ይከለክለዋል" ያልታወቀ
ስለፎቢያ ሲነሳ ብዙ ዓይነቶችን መዘርዘር ይቻል ይሆናል፡፡ ነገር ግን በሳይንስ የተረጋገጠ መቶ ብር የመዘርዘር ፎቢያ ስለመኖሩ እርግጠኛ ባልሆንም እኔን ግን ይዞኝ ነበር፡፡
የኋላ ታሪክ
በሕይወቴ ውስጥ ላመንኩበት ነገር እንኳን ነገ በኋላ የሚባል ነገር የለም፡፡ ሁሌም አሁን በሚል አመለካከት ውስጥ ራሴን ለመቃኘት እሞክራለሁ፡፡ አንድ ስራ ላይ ተቀጥሬ የምቆየው የሥራ አካባቢዬ ፍላጎቴን አጥፍቶ የመፍጠር አቅሜን አስካልገደበው ድረስ ብቻ ነው፡፡
ጠዋት ስነሳ ውሎዬ ካስጠላኝ፤ ሄጄም ከመቀመጥ ያለፈ አበርክቶ በሥራዬ ላይ ከጠፋብኝ ወዲያው እወስናለሁ። ስርዓቱን ተከትዬ ሥራዬን እለቃለሁ፡፡ ከአንድም ሶስት ጊዜ በዚህ ሁኔታ ውስጥ አልፌአለሁ፡፡ በቅጥር ከሁለት ቀናት
ያላነሰ ከስምንት ወራት ያልበለጠ ጊዜ የነበረኝም በእነዚህ ምክንያቶች ነው፡፡
ለሦስተኛ ጊዜ ሥራ መልቀቄን ተከትለው የመጡት ሦስት ዓመታት ግን መቶ ብር ለመዘርዘር ፎቢያ አጋለጡኝ፡፡ ሥራ አቁሜ የሁለተኛ ዲግሪዬን መማር ጀመርኩ፡፡ በጊዜው ሌላ ድግሪም እየተማርኩ ነበርና ወጭው ከበደ፡፡ ወቅትን መሰረት ያደረጉ ሥራዎችን እየሰራሁ ትምህርቴን ብቀጥልም ለመንቀሳቀሻ እጄ ላይ የሚቀር ብር አልነበረም። በደህና ጊዜ የገዛኋቸውን ልብሶችና የሞባይል ቀፎ ጨምሮ የትኛውንም ዋጋ የሚያወጣ ነገር ሁሉ መሸጥ ጀመርኩ፡፡ ሺህ ብሮች የወጡባቸው ዕቃዎችና ልብሶች ከመቶና ሁለት መቶ ባልዘለለ ዋጋቸው ወድቆ ተሸጡ፡፡ ለኔ ግን ትንሽ አልነበሩም፡፡
ለተወሰነ ቀናት ችግሬን ይጋሩኝና አንድ መቶ ድፍን ብር ሲቀረኝ ፎቢያዬ (ፍራቻዬ) ይነሳል፡፡ ብዘረዝረው ይጠቅመኛል፡፡ ግን ደግሞ ቶሎ ያልቅብኛል እልና ስጋት ያድርብኛል፡፡ ታክሲ ስሳፈር አስራ አንድ ሰው እስኪገባ ጠብቄ አስራ ሁለተኛ እገባለሁ፡፡ ከራሴ ተርፎ ለማቃቸው ሰዎች የምከፍለው ስለሌለኝ ያን ሽሽት መሆኑ ነው እንግዲህ፡፡
ያኔ ማሰብ እጀምራለሁ፡፡ ሌላ የብር ኖቶች የሚገኙበትን መንገድ እፈጥርና ያን ቀን እሻገረዋለሁ፡፡
ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሱ እንጂ እየቀነሱ አልመጡም፡፡ ከጊዜ በኋላ የሚሸጥም ጠፋ፡፡ አልፎ አልፎ እየመጡም የገቢ ምንጭ ይሆኑኝ የነበሩት ሥራዎች በተለያዩ ከኔ በላይ በሆኑ ምክንያቶች ከእጄ ወጡ፡፡ ተስፋ፣ በራስ መተማመንና በምንም የማይቀንስ ደስተኝነት ግን ከኔ ጋር ነበሩ፡፡ ምንም ለመሞከር የማይፈራ፣ በራሱ የሚቆም፣ ባለው ነገር የተሻለ ነገን የመፍጠር አቅም ያለው ወጣት ግን ተወልዶ ጎለመሠ፡፡ ሼክስፔር እንዳለው ገዢ በሌለበት
ገበያ ሐዘኔን ለሽያጭ አላቀረብኩም፡፡

ዛሬ

ብሩሕ ነው- - - - - ተመስገን!

ነገ

ከባድ ማዕበል ቢመጣ እንኳን አልፈራም፡፡ ትናንት መቅዘፍን ለምጃለሁ፡፡

"ሕይወት መልካም የምትሆነው በእድል ሳይሆን ለለውጥ በመዘጋጀት ነው፡፡" ያልታወቀ

ዓባይ ኪዳኔ

10/09/2022

ባሕር ማዶ በአንድ ት/ቤት ውስጥ ለአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች የሚከተለው
ጥያቄ ቀረበ::
ጥያቄ፡- ስለእናታችሁ 200 ፊደላትን በመጠቀም አንድ ድርሰት ፃፉ
የተፈቀደው ጊዜ፡- 1፡30
አንድ ልጅ ገና በመጀመሪያው ደቂቃ መልሱን ሰርቶ ጨረሰ፡፡
የፃፈው አንድ ዐ.ነገር ቢሆንም እንኳ ሙሉ ነጥብ አገኘ፡፡
ዐ. ነገሩ እንዲህ ይል ነበር
“የትኛውም የእንግሊዘኛ 26 ቃላት ቅንብር የእኔን እናት በጭራሽ አይገልፅም”

@መሳይ

03/09/2022

የአእምሮ ጤንነት ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ነው። ብዙ ጊዜ አብሮን ያሳለፈ ሰው በድንገት ሲርቀን፣ "ምን አድርገን ነው" እንጂ፣ "ምን ሆኖ ነው?" አንልም። ሰው ስልክ ሳያነሳ ሲቀር ወይ ለመገናኘት አይመቸኝም ሰበብ ሲያበዛ፣ ወረተኝነቱን እንተርካለን እንጂ ምን ውስጥ እያለፈ እንደሆነ አናውቅም።

ስናከብረው የነበረ ሰው ከመሬት ተነስቶ ሲሰድበን ወይ ባልጠበቅንበት ሲያውለን፣ ጠንካራ የሚመስለን ሰው ሆድ ብሶት ተስፋ ቆርጦ ስናየው፣ ክፉ ሲናገር፣ ሁሉ ምን አድርገን ነው ከማለት ጎን ለጎን "ምን ሆኖ ይኾን" ማለት መልካም ነው። በየፌስቡክ ፖስቶቻችን ሥር በማይገናኝ መልኩ የስድብ ናዳ የሚያወርዱት ሁሉ ምን ሆነው ይሆን ማለት አለብን።

በየትኛውም ቤተ እምነት ውስጥ መኖር ያለውን ስነልቡናዊ ጥቅም ማቃለል ዘመናዊነት ተደርጎ ቢቆጠርም፣ ውሎ አድሮ ብዙ ያስከፍለናል። በተለይ የማታምኑ ሰዎች የሚያምኑ ሰዎች የሚታከሙበትን እምነት ማቃለል እርባና ቢስ ነው። ለእናንተ ሞኝነት ነው። ለሚያምኑት ግን ሕይወት ነው። መስቀላቸውን የማትሸከሙላቸውን ሰዎች፣ በአውቀናል በሰልጥነናል ባይነት አትዝለፏቸው።

የምናምን ሰዎች ሸክማችን በከበደ ጊዜ ወደ ልጅነታችን አምላክ፣ ወደመሰረታችን እንሩጥ። ሄደን እንተንፍሰው። ሰላማችንን መልሰን እናግኝ። ቀላል ነገር ሊመስል ይችላል። ግን አይደለም። በዚህ ወረትና ጩኸት በበዛበት ዓለም ከመቅበዝበዝ በቀር ደስታም ትርፍም የለንም። ከፊልሙ፣ ከዜናው ጎን የእግዚአብሔርን ነገር ካላሰብን ከባድ ነው።

በጦርነት፣ በችግር፣ በድህነት እየተቆላን ነውና ፈርጀ ብዙ የአእምሮ እና የባህርይ ህመም ሊያጋጥመን ይችላል። የማኅበራዊ ፋይዳ ያላቸውን ቡና መጠራራት፣ እቁብ፣ እድር፣ ጽዋ ወዘተ አናቃል። እንጠቀምባቸው። ሰው ከሰው ጋር ይገናኝ። ከቴክኖሎጂ ፋታ እንውሰድ።

ዛሬ አራብሳ ኮንዶሚነም የተፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል ጉዳይም ስነ ልቡናዊ ምንጭ ያለው መሰለኝ። ወላጆቻቸው መጽናናቱን ይስጣቸው። እንዲህ ያለ ዱብ ዕዳ ሲገጥም በእግዚአብሔር እንጂ በማን መመካት እና ክፉ ቀንን ማሳለፍ ይቻላል? አቅም ይስጣችሁ። ለሰማነውም ከባድ ነው። 😔😔😔

P.S. ማንንም ለመምከር አይደለም። ለራሴም ጭምር ነው።
@ ዮሐንስ ሞላ

የምወደው እና የማከብረው ገጣሚ፣ ተዋናይ፣ ብዙ ነገር እና ጥሩ ሰው Wasihun Belay ዛሬ ልደቱ ነው። በሚታወቁና በማይታወቁ ብዙ ምክንያቶች የተነሳ፣ 'ገጣሚ የሚለው ማዕረግ ጥሩ ነው አ...
30/08/2022

የምወደው እና የማከብረው ገጣሚ፣ ተዋናይ፣ ብዙ ነገር እና ጥሩ ሰው Wasihun Belay ዛሬ ልደቱ ነው። በሚታወቁና በማይታወቁ ብዙ ምክንያቶች የተነሳ፣ 'ገጣሚ የሚለው ማዕረግ ጥሩ ነው አይደለም' ብዬ በምወዛገብበት የጉርምስና ዕድሜዬ ከሩቅ አይቻቸው "እንደነሱም መሆን ይቻላል እኮ። እንደነሱም ተከብሮ ሙያን ማስከበር ይቻላል" ብዬ በልቤ ለምልክት አኑሬያቸው ከነበሩት ጥቂቶች አንዱ ነው። መፈጠሬን ሳያውቁ በመኖራቸው እና ደርዛቸውን በመጠበቅ ሕይወታቸው ካገዙኝ መካከል አንዱ ዋሲሁን ነው። በእኔና በግጥም መሀል ዋስ ሆኖ አሸማግሎናል። የመጀመሪያው መጽሐፌን እንዳነበበውና እንደወደደው ያወቅኩ ቀን ደግሞ፣ ፈረስ ባይኖረኝም "አበደ ፈረሴ" ብያለሁ። 🐎 🤗

ወደ ኋላ ላጠንጥንና... ከአርባት በአንዱ አርብ ቀን ፑሽኪን ከዝግጅት ታድመን ስንወጣ ከጓደኞቹ ጋር ቆመው ሲያወሩ አይቼው፣ ቆይ ዛሬ ሄጄ ላናግረው። እጅ ልንሳው። ብዬ ወደዚያ ያለ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብዬ አፈር ላይ በእንጨት እየሳልኩ ስጠብቀው ቆይቼ፣ ቀና ብል የሉም። ሄደዋል። ያኔ ፌስቡክም የፌስቡክ ወደረኞቼም አልነበራችሁም እንጂ፣ "እርሟን ብታፈላ ጋን ሙሉ አተላ" የተባለው ለእኔ ነው ብዬ እለጥፍ ነበር። :)

መልካም ልደት ዋስዬ። እንደተወደድኽ፣ እንደተከበርኽ ኑር። ሀሳብህ ሁሉ ይሙላልህ። ❤️

@ዮሐንስ ሞላ

07/07/2022

4ቱ የመ መርሆች
#መቆጠብ - የዘር ፍጅት የሚፈጽሙትን ህጋዊ
እርምጃ ከመውሰድ መቆጠብ
#መጠቀም - ሠላማውያንን ለመፍጀት መሳሪያ
መጠቀም
#መወሰን - በቦታ መወሰን
#መከልከል - ዜጎች በመረጡት ቦታ እንዳይኖሩ
መከልከል

Address

Addis Ababa
122121

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 12:30

Telephone

+251913555977

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አብሮነት/Abronet posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አብሮነት/Abronet:

Videos

Share

Category