ከሀ እስከ ፐ Ke Ha Eske Pe

ከሀ እስከ ፐ  Ke Ha Eske Pe ስፖርታዊ ክንውኖችን በቀጥታ የሚስተላልፍ ፕሮግራም

እንኳን ለ1 ሺህ 441ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ!ኢድ ሙባረክ!
22/05/2020

እንኳን ለ1 ሺህ 441ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ!
ኢድ ሙባረክ!

እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሰን!
18/04/2020

እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሰን!

እንዴት አላችሁ የተወደዳችሁ የከሀ እስከ ፐ የሬዲዮ ፕሮግራማችን ተከታታዮች! የቅዳሜ፣ መጋቢት 26 ቀን 2012 ዓ.ም.   እናስተዋውቃችሁ፡፡እንግዶቻችን ታላቁ የሙዚቃ አቀናባሪ   እና ዝነኛ...
03/04/2020

እንዴት አላችሁ የተወደዳችሁ የከሀ እስከ ፐ የሬዲዮ ፕሮግራማችን ተከታታዮች! የቅዳሜ፣ መጋቢት 26 ቀን 2012 ዓ.ም. እናስተዋውቃችሁ፡፡

እንግዶቻችን ታላቁ የሙዚቃ አቀናባሪ እና ዝነኛው የግጥም እና ዜማ ደራሲ ናቸው።

የ #ኮሮናቫይረስ በአገራችን መከሰቱን ተከትሎ በሙያቸው ማህበረሰቡን የማንቃት እና የማስተማር ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ከሚገኙ የኪነ-ጥበብ ሙያተኞች መካከል በዋንኛነት ይጠቀሳሉ።

የተሰኘው በድምጻዊያን ትንሳኤ ጎበና እና ሚሚ ሙሉቀን የተቀነቀነው አዲስ ዘፈን የተሰራው በእንግዶቻችን ነው።

ዛሬ ደግሞ #አዋጅ የተሰኘ ሌላ አዲስ ስራ በጥምረት ሰርተው ለቀዋል።

በስራዎቹ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለማውራት በቅዳሜ የከሀ እስከ ፐ ፕሮግራማችን ላይ እንግዶቻችን ናቸው።

በወቅታዊው የኮሮናቫይረስ ምክንያት ግን ቆይታውን የምናደርገው ከያሉበት በቀጥታ ስልክ እያስገባናቸው ይሆናል። አድማጮቻችን የምታነሱላቸው ጥያቄ ካለ እንደተለመደው በዚሁ ገጻችን አድርሱን፡፡

የከሀ እስከ ፐ ፕሮግራማችን እንግዶቻችንን ጨምሮ ሌሎች ቅንብሮቹን ይዞ ቅዳሜ፣ መጋቢት 26 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ላይ ይጠብቃችኋል፡፡

የዛሬ እንግዳችን የ  #ስነልቦና ባለሙያዋ   ለሰጠችን ጊዜ እና ላጋራችን ቁምነገር  #እናመሰግናለን።የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦1 Fuad Hailu2 ይስሃቅ አብርሃም3 ማንኦፍ ዘ...
28/03/2020

የዛሬ እንግዳችን የ #ስነልቦና ባለሙያዋ ለሰጠችን ጊዜ እና ላጋራችን ቁምነገር #እናመሰግናለን።

የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦
1 Fuad Hailu
2 ይስሃቅ አብርሃም
3 ማንኦፍ ዘዊነር

የስልክ ቁጥራችሁን ላኩልን።

እንዴት አላችሁ የተወደዳችሁ የከሀ እስከ ፐ የሬዲዮ ፕሮግራማችን ተከታታዮች! የቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2012 ዓ.ም.   ችንን ልናስተዋውቃችሁ መጥተናል፡፡ እንግዳችን የስነ-ልቦና ባለሙያዋ ...
27/03/2020

እንዴት አላችሁ የተወደዳችሁ የከሀ እስከ ፐ የሬዲዮ ፕሮግራማችን ተከታታዮች! የቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2012 ዓ.ም. ችንን ልናስተዋውቃችሁ መጥተናል፡፡

እንግዳችን የስነ-ልቦና ባለሙያዋ ናት፡፡

ሰብለ ሃይሉ የተወለደችው አዲስ አበባ ነው፡፡ የ12ኛ ክፍል ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአመራርና ህዝብ አስተዳደር እንዲሁም ከወንጌላዊት መንፈሳዊ ኮሌጅ በመንፈሳዊ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪዎች ተቀብላለች፡፡ በማስተርስ ደረጃ ደግሞ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በስነ-ልቦና እንዲሁም በማማከርና የሰዎች ግንኙነት ደግሞ በአሜሪካው Liberty University ተምራ አጠናቃለች፡፡

በኤች. አይ. ቪ/ኤድስ፣ በጾታ፣ በማህበረሰብ ንቅናቄ እንዲሁም በምርምርና ስልጠና በተለያዩ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ውስጥ ከአባልነት እስከ አመራርነት አገልግላለች፡፡ በአሁን ወቅትም በስነ-ልቦና ምክርና ማማከር ላይ የሚሰራ ድርጅት ከፍታ እየሰራች ትገኛለች፡፡

ቅዳሜ ከኛ ጋር በሚኖራት ቆይታ በተለይ በ #ኮሮናቫይረስ ( #ኮቪድ19) ሰበብ ሊደርሱብን የሚችሉ ስነ-ልቦናዊ ጫናዎችን እንዴት ማለፍ እንደምንችል ሙያዊ ምክሮችን ታካፍለናለች፡፡

ለእንግዳችን ለሰብለ ሃይሉ የምታነሱላት ጥያቄ ካለ እንደተለመደው በዚሁ ገጻችን አማካኝነት ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡

የከሀ እስከ ፐ ፕሮግራማችን እንግዳችን ጨምሮ ሌሎች ቅንብሮቹን ይዞ፣ ቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት በፋና ኤፍ. ኤም 98.1 ላይ ይጠብቃችኋል፡፡

የዛሬ እንግዳችን   ገ/የሱስ ለሰጠን ጊዜ እና ላጋራን ቁምነገር  #እናመሰግናለን።የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦1. Ashu Demissie2. Bzuayehu Worku3. ማንኦፍ ዘዊነ...
21/03/2020

የዛሬ እንግዳችን ገ/የሱስ ለሰጠን ጊዜ እና ላጋራን ቁምነገር #እናመሰግናለን።

የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦
1. Ashu Demissie
2. Bzuayehu Worku
3. ማንኦፍ ዘዊነር

የስልክ ቁጥራችሁን ላኩልን።

እንዴት አላችሁ የተወደዳችሁ የከሀ እስከ ፐ የሬዲዮ ፕሮግራማችን ተከታታዮች! የቅዳሜ፣ መጋቢት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ጥቁር እንግዳችንን ልናስተዋውቃችሁ መጥተናል፡፡ እንግዳችን   ገ/የሱስ...
19/03/2020

እንዴት አላችሁ የተወደዳችሁ የከሀ እስከ ፐ የሬዲዮ ፕሮግራማችን ተከታታዮች! የቅዳሜ፣ መጋቢት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ጥቁር እንግዳችንን ልናስተዋውቃችሁ መጥተናል፡፡

እንግዳችን ገ/የሱስ ነው፡፡

ሼፍ ዮሃንስ የተወለደው አዲስ አበባ ነው፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ የተቀመሙና በተለይም ለበዓል ተብለው የሚዘጋጁ ምግቦች አዘገጃጀትና ቃና ይስቡት ነበር፡፡ ለዚህም ደግሞ ቤተሰቡ በባለቤትነት የሚያስተዳድረው #አንቲካ የተባለ ባርና ሬስቶራንት ውስጥ የምግብ አሰራርን ማስተዋሉና እናቱ የተዋጣላቸው የምግብ አሰራር ባለሙያ መሆናቸው ዋነኛ ምክንያቶቼ ነበሩ ይላል፡፡

ሼፍ ዮሃንስ የመጀመሪያ ዲግሪውን ፈረንሳይ ከሚገኝ ዩነቨርሲቲ በስነ-ስእል አግኝቷል፡፡ እዚያው ፈረንሳይ በሆቴል አስተዳደርና የምግብ አሰራር ዘዴ ሌላ የመጀመሪያ ዲግሪ ተቀብሏል፡፡ ከአመታት የፈረንሳይ ቆይታ በኋላ ወደ አሜሪካ በማቅናት በ5 ኮከብ ሆቴሎች ውስጥ በሙያው አገልግሏል፡፡ በቆይታውም በስነልቦና (Psychology) የማስተርስ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ ከመጣም በኋላ ከሼፍነቱ ጎን ለጎን በምግብ ዝግጅት ላይ ያተኮሩ ሁለት የቴሌቪዥን ሾዎች በማቅረብ የሀገራችን ባህላዊ የምግብ አዘገጃጀት በሳቢ መንገድ አስተዋውቋል፡፡ Ethiopia: Recipes and Traditions from the Horn of Africa የተሰኘ መፅሀፍ አሳትሞ በተለያዩ አለምአቀፍ የመፅሃፍ ሽልማቶች ላይ እጩ መሆን ችሏል፡፡

በአሁን ሰዐትም ከዋና ሼፍነት ጎን ለጎን በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል የምግብ ዝርዝር አማካሪነት እንዲሁም Seeds of Africa በተባለ ድርጅት ውስጥ የተማሪዎች ምገባ ላይ በአማካሪነት ይሰራል፡፡

አድማጮቻችን ለእንግዳችን ለሼፍ ዮሃንስ ገ/የሱስ የምታነሱት ጥያቄ ካለ እንደተለመደው በዚሁ ገጻችን አድርሱን፡፡

የከሀ እስከ ፐ ፕሮግራማችን እንግዳችንን ጨምሮ ሌሎች ቅንብሮቹን ይዞ ቅዳሜ፣ መጋቢት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት በፋና ኤፍ. ኤም 98.1 ላይ ይጠብቃችኋል፡፡

የዛሬ እንግዳችን  #ዳይሬክተር እና  #ሲኒማቶግራፈር   ለሰጠን ጊዜ እና ላጋራን ቁምነገር  #እናመሰግናለን።የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦1. Amanuel Yeshiwond2. Geti...
14/03/2020

የዛሬ እንግዳችን #ዳይሬክተር እና #ሲኒማቶግራፈር ለሰጠን ጊዜ እና ላጋራን ቁምነገር #እናመሰግናለን።

የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦
1. Amanuel Yeshiwond
2. Getie Zelalem
3. Eze Din ናቸው።

የስልክ ቁጥራችሁን ላኩልን።

እንዴት አላችሁ የተወደዳችሁ የከሀ እስከ ፐ የሬዲዮ ፕሮግራማችን ተከታታዮች! የቅዳሜ፣ መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም.   ችንን እናስተዋውቃችሁ፡፡እንግዳችን  #ዳይሬክተር እና  #ሲኒማቶግራፈ...
12/03/2020

እንዴት አላችሁ የተወደዳችሁ የከሀ እስከ ፐ የሬዲዮ ፕሮግራማችን ተከታታዮች! የቅዳሜ፣ መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም. ችንን እናስተዋውቃችሁ፡፡

እንግዳችን #ዳይሬክተር እና #ሲኒማቶግራፈር ነው፡፡

ሰውመሆን ይስማው ትውልድና እድገቱ ጎንደር ውስጥ ነው፡፡ የ12ኛ ክፍል ትምህርቱን በዚያው ካጠናቀቀ በኋላ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን በመቀላቀል ግዢና ንብረት አስተዳደር ተምሯል፡፡ በወቅቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ስራ ት/ቤት የተማሪዎች ማደሪያ ስላልነበረው ሰውመሆን የፎቶግራፍ ባለሙያ የሆኑት አጎቱ ጋር ተቀምጦ እየተመላለሰ ይማር ነበር፡፡ ይህም ከልጅነቱ ጀምሮ የፎቶግራፍ ሙያ ጥልቅ ፍላጎት ለነበረው ሰውመሆን ጥሩ አጋጣሚ ነበር፡፡ የተማረበትን ሙያ ወደ ጎን በመተውም በፎቶግራፍ ባለሙያነት ሰርቷል፡፡

ከ12 አመት በፊትም #ሳቢሳ የተባለ የፊልም ፕሮዳክሽን ድርጅት ከሁለት ጓደኞቹ ጋር አቋቁሟል፡፡ በዳይሬክቲንግ የመጀመሪያ ከሆነው #862 ፊልሙ ጀምሮ #ፔንዱለም፣ ፣ ፣ ፣ ፊልሞች ላይ ተሳትፏል፡፡ በ2008 ዓ.ም. በተካሄደው የጉማ ሽልማት ላይ #አለሜ በተሰኘው ፊልም በምርጥ ዳይሬክተርና በምርጥ ሲኒማቶግራፈር ዘርፍ ታጭቶ በምርጥ ሲኒማቶግራፈር አሸናፊ ሆኗል፡፡ በአፍሪካ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ደግሞ እውር አሞራ ቀላቢ የተባለ ፊልሙን ለዕይታ አቅርቧል፡፡

በአሁኑ ወቅትም በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያገኙ የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች ላይ እየሰራ ይገኛል፡፡

አድማጮቻችን ለእንግዳችን ዳይሬክተርና ሲኒማቶግራፈር ሰውመሆን ይስማው የምታነሱት ጥያቄ ካለ እንደተለመደው በዚሁ ገጻችን አድርሱን፡፡

የከሀ እስከ ፐ ፕሮግራማችን እንግዳችንን ጨምሮ ሌሎች ቅንብሮቹን ይዞ ቅዳሜ፣ መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ላይ ይጠብቃችኋል፡፡

የዛሬ እንግዳችን የአልባሳት ዲዛይነር    #ማፊ ለሰጠችን ጊዜ እና ላጋራችን ቁምነገር  #እናመሰግናለን።የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦1. Abu Kiya2. Yohannes Mulatu3...
07/03/2020

የዛሬ እንግዳችን የአልባሳት ዲዛይነር #ማፊ ለሰጠችን ጊዜ እና ላጋራችን ቁምነገር #እናመሰግናለን።

የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦
1. Abu Kiya
2. Yohannes Mulatu
3. Kidus Gitmaw ናቸው።

የስልክ ቁጥራችሁን ላኩልን።

እንዴት አላችሁ የተወደዳችሁ የከሀ እስከ ፐ የሬዲዮ ፕሮግራማችን ተከታታዮች! የቅዳሜ፣ የካቲት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ጥቁር እንግዳችንን ልናተዋውቃችሁ መጥተናል፡፡ የልብስ ዲዛይነር   ( ...
05/03/2020

እንዴት አላችሁ የተወደዳችሁ የከሀ እስከ ፐ የሬዲዮ ፕሮግራማችን ተከታታዮች! የቅዳሜ፣ የካቲት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ጥቁር እንግዳችንን ልናተዋውቃችሁ መጥተናል፡፡

የልብስ ዲዛይነር ( #ማፊ) ትባላለች።

ማፊ የሰባተኛ ክፍል ተማሪ እያለች ጀምሮ ድምጻዊ፣ ሞዴል እና ዲዛይነር፣ እንዲሁም የቅርጫት ኳስ ተጫዋች መሆን ከብዙ ህልሞቿ/ዝንባሌዎቿ መካከል ቀዳሚዎቹ ነበሩ፡፡

ገና በ16 ዓመቷ ሙዚቃ እና ሞዴሊንግን የጀመረችው ማፊ፣ በዮሴፍ ገብሬ (ጆሲ) #መጣኋ ( ) በተሰኘው ሙዚቃ ላይ በአጃቢ ድምጻዊነት (ፊውቸሪንግ) ተሳትፋ በብዙዎች ዘንድ መታወቅ ቻለች፡፡

እውቅናው ከመጣ በኋላ ከሙዚቃ እና ከልብስ ዲዛይኒንግ አንዱን ለመምረጥ ተቸግራ እንደነበር ታስታውሳለች፡፡ ነገር ግን በመጨረሻ የልብስ ዲዛይን ስራን መርጣ ይኸው ዛሬ ከአገር ውስጥ አልፎ በዓለም አቀፍ መድረኮች ያሳወቋትን የልብስ ዲዛይኖች እየሰራች ትገኛለች፡፡

በአለም የፋሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ታዋቂ በሆነው በኒውዮርክ የፋሽን ሳምንት ላይ ስራዎቿን ማቅረቧ ከስኬቶቿ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ TEDx Talk ን በመሳሰሉ መድረኮች ላይ በመገኘት ስለባህላችን እና ዘመናዊ የልብስ ዲዛይኖቿ ገለጻዎች አድርጋለች፡፡

በቅርቡ በመስቀል አደባባይ ታላቅ ኮንሰርቱ ያዘጋጀው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በማፊ ዲዛይን በተደረጉ አልባሳት ተውቦ ነበር በመድረክ ስራዎቹን ያቀረበው፡፡

ዛሬ ለደረሰችበት ደረጃ ያገዛት በራሷ መንገድ መጓዝ መምረጧ እና እስካሁን ከተሰሩ ስራዎች ለየት ያለ ስራ ይዛ መቅረቧ እንደሆነም ትናገራለች፡፡

የተወደዳችሁ አድማጮች ለእንግዳችን ዲዛይነር ማፊ የምታነሱት ጥያቄ ካለ እንደተለመደው በዚሁ ገጽ አድርሱን።

የከሀ እስከ ፐ ፕሮግራማችን እንግዳችንን ጨምሮ ሌሎች ቅንብሮቹን ይዞ ቅዳሜ፣ የካቲት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት በፋና ኤፍ. ኤም. 98.1 ሬዲዮ ላይ ይጠብቃችኋል፡፡

እንኳን ለ124ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሰን!!!ጊዜ መልቲሚዲያ
02/03/2020

እንኳን ለ124ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሰን!!!

ጊዜ መልቲሚዲያ

የቅዳሜ እንግዶቻችን የ   አባላት ለሰጡን ጊዜ እና ላጋሩን ቁምነገር  #እናመሰግናለን።የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦1. Meklit Desie2. Fuad Hailu3. Zerihun Te...
01/03/2020

የቅዳሜ እንግዶቻችን የ አባላት ለሰጡን ጊዜ እና ላጋሩን ቁምነገር #እናመሰግናለን።

የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦
1. Meklit Desie
2. Fuad Hailu
3. Zerihun Teznanu ናቸው።

የስልክ ቁጥራችሁን ላኩልን።

እንዴት አላችሁ የተወደዳችሁ የከሀ እስከ ፐ የሬዲዮ ፕሮግራማችን ተከታታዮች! የቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2012 ዓ.ም   ችንን ልናተዋውቃችሁ መጥተናል፡፡እንግዳዎቻችን የ   አባላት ናቸው፡፡ ...
27/02/2020

እንዴት አላችሁ የተወደዳችሁ የከሀ እስከ ፐ የሬዲዮ ፕሮግራማችን ተከታታዮች! የቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2012 ዓ.ም ችንን ልናተዋውቃችሁ መጥተናል፡፡

እንግዳዎቻችን የ አባላት ናቸው፡፡

ሞሰብ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን የተመሰረተው በ2005 ዓ.ም. በዋና መስራች ጣሰው ወንድም እና በባህላዊ የሙዚቃ መሳርያ ተጫዋቾቹ ቢኒያም ዳኛቸው፣ ይገረም ጉልላት፣ ሃዲስ አለማየሁ (ሃዲንቆ)፣ አበባው አበበ እና ዳዊት ልሳን አማካኝነት ነው፡፡

ባንዱ በሀገር ውስጥ የተለያዩ ትልልቅ መድረኮች ባህላዊ ሙዚቃዎችን በማቅረብ እውቅናን አትርፏል፡፡ በተለያዩ የዓለም ሀገራት እየተዘዋወረ ስራዎቹን ከማቅረብ ተጨማሪም በየወሩ የሚዘጋጅ #አንዲር የተሰኘ የሙዚቃ ፕሮጀክት በመጀመር እስካሁን 14 የሙዚቃ ድግሶችን አዘጋጅቶ አቅርቧል፡፡

ሞሰቦች በ2008 ዓ.ም #ጥሞና የተሰኘ በባህላዊ የሙዚቃ መሳርያዎች ብቻ የተቀነባበረ የመጀመሪያ አልበማቸውን ለህዝብ አድርሰዋል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ደግሞ የተሰኘ አዲስ አልበማቸውን ለገበያ አቅርበዋል፡፡

እንግዶቻችን ከኛ ጋር በሚያደርጉት ቆይታ ከቃለ-ምልልስ በተጨማሪ ተወዳጅ ሙዚቃዎቻቸውን በቀጥታ ከስቱዲዮ ያቀርባሉ።

እናም ለሞሰብ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን የምታነሱት ጥያቄ ካለ እንደተለመደው በዚሁ ገጻችን ላይ አድርሱን፡፡

የከ እስከ ፐ ፕሮግራማችን ከእንግዶቻችን በተጨማሪ ሌሎች ቅንብሮቹን አካቶ፥ ቅዳሜ፣ የካቲት 21 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት በፋና ኤፍ. ኤም. 98.1 ሬዲዮ ላይ ይጠብቃችኋል፡፡

የዛሬ እንግዳችን   ለሰጠን ጊዜ እና ላጋራን ቁምነገር  #እናመሰግናለን።የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦1. ይቻላል ይቻላል (Facebook)2. Alex Asferaw (Facebook)4...
22/02/2020

የዛሬ እንግዳችን ለሰጠን ጊዜ እና ላጋራን ቁምነገር #እናመሰግናለን።

የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦
1. ይቻላል ይቻላል (Facebook)
2. Alex Asferaw (Facebook)
4. Fuad Hailu (Facebook) ናቸው።

የስልክ ቁጥራችሁን ላኩልን።

እንዴት አላችሁ የተወደዳችሁ የከሀ እስከ ፐ የሬዲዮ ፕሮግራማችን ተከታታዮች! የቅዳሜ የካቲት 14 ቀን 2012 ዓ.ም   ችንን ልናተዋውቃችሁ መጥተናል፡፡እንግዳችን የሙዚቃ ድምፅ ውህደት ባለሙ...
21/02/2020

እንዴት አላችሁ የተወደዳችሁ የከሀ እስከ ፐ የሬዲዮ ፕሮግራማችን ተከታታዮች! የቅዳሜ የካቲት 14 ቀን 2012 ዓ.ም ችንን ልናተዋውቃችሁ መጥተናል፡፡

እንግዳችን የሙዚቃ ድምፅ ውህደት ባለሙያ ነው፡፡

ትውልዱ እዚሁ አዲስ አበባ፣ መርካቶ የሆነው ሰለሞን፥ የሙዚቃ ድምጽ ውህደት እና ማስተሪንግ (Music Mixing & Mastering) ስራን የጀመረው ከ15 ዓመት በፊት ነው።

ከዚያ አስቀድሞ ግን የሙዚቃ ቅንብር በመስራት ነበር ወደ ሙዚቃው ዓለም የተቀላቀለው። በዚህም ለአብነት አጎናፍር፣ ለምናሉሽ ረታ፣ ለኃይለየሱስ ግርማ እና ለአለምዬ ጌታቸው ሙዚቃዎች አቀናብሯል።

በሚክሲንግ እና ማስተሪንግ በኩል ደግሞ ከአስር በላይ ሙሉ አልበሞች እና ከ200 በላይ ነጠላ ዜማዎች የድምጽ ውህደት እና ማስተሪንግ ሰርቷል።

ለዚህ ሳምንት እንግዳችን ሰለሞን ኃይለማርም የምታነሱት ጥያቄ ካለ እንደተለመደው በዚሁ ገጻችን ላይ አድርሱን፡፡

የከ እስከ ፐ ፕሮግራማችን ከእንግዳችን በተጨማሪ ሌሎች ቅንብሮቹን አካቶ፥ ቅዳሜ፣ የካቲት 14 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት በፋና ኤፍ. ኤም. 98.1 ሬዲዮ ላይ ይጠብቃችኋል፡፡

የዛሬ እንግዳችን   ለሰጠችን ጊዜ እና ላጋራችን ቁምነገር  #እናመሰግናለን።የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦1. Beti Yilma2. ይግረማቸው ነጋሽ ይሉ 3. Samuel Abebe ናቸ...
15/02/2020

የዛሬ እንግዳችን ለሰጠችን ጊዜ እና ላጋራችን ቁምነገር #እናመሰግናለን።

የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦
1. Beti Yilma
2. ይግረማቸው ነጋሽ ይሉ
3. Samuel Abebe ናቸው።

የስልክ ቁጥራችሁን ላኩልን።

14/02/2020
እንዴት አላችሁ የተወደዳችሁ የከሀ እስከ ፐ የሬዲዮ ፕሮግራማችን ተከታታዮች! የቅዳሜ የካቲት 07 ቀን 2012 ዓ.ም   ችንን ልናተዋውቃችሁ መጥተናል፡፡እንግዳችን   ትባላለች፡፡ትውልድ እና ...
14/02/2020

እንዴት አላችሁ የተወደዳችሁ የከሀ እስከ ፐ የሬዲዮ ፕሮግራማችን ተከታታዮች! የቅዳሜ የካቲት 07 ቀን 2012 ዓ.ም ችንን ልናተዋውቃችሁ መጥተናል፡፡

እንግዳችን ትባላለች፡፡

ትውልድ እና እድገቷ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ ዲላ ከተማ ሲሆን ዩኒቨርሲቲ እስክትገባ ድረስ ትምህርቷን በዛው በዲላ ተከታትላለች፡፡

በመቀጠል፣ የከፍተኛ ትምህርት ቆይታዋን በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ አድርጋ በአካውንቲንግ ተመርቃለች፡፡ ከምርቃት በኋላ ደግሞ በሐዋሳ ከተማ የግሏን የሂሳብ/አካውንቲንግ ድርጅት ከፍታ ለተወሰነ ጊዜ ስትሰራ ቆይታለች፡፡

ወደ አዲስ አበባ ከመጣች በኋላም ትኩረቷን ከሂሳብ ስራ ወደ ሰው ኃይል ግንባታ በመቀየር በአስተሳሰብ እና ስብዕና ልቀት ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ ትገኛለች፡፡

በቅርቡም የተሰኘ መጽሐፏን ለንባብ አብቅታለች፡፡ በእውነተኛ ታሪክ ላይ መነሻውን ያደረገ ነው መጽሐፏ፡፡

የተሰኘ ብሎግም አላት፡፡

የሕይወት ፍልስፍናዬ "መኖር፣ ሌሎች ሰዎች እንዲኖሩ ማገዝ ነው" የምትለው ሕይወት፣ የዚህ ሳምንት እንግዳችን ናት፡፡ የምታነሱላት ጥያቄ ካለ እንደተለመደው በዚሁ ገጻችን ላይ አድርሱን፡፡

የከ እስከ ፐ ፕሮግራማችን ከእንግዳችን በተጨማሪ ሌሎች ቅንብሮቹን አካቶ፥ ቅዳሜ፣ የካቲት 07 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት በፋና ኤፍ. ኤም. 98.1 ሬዲዮ ላይ ይጠብቃችኋል፡፡

.

የዛሬ እንግዳችን የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ  #ኢንስትራክተር   ለሰጠን ጊዜ እና ላጋራን ቁምነገር  #እናመሰግናለን።የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦1. Af...
08/02/2020

የዛሬ እንግዳችን የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ #ኢንስትራክተር ለሰጠን ጊዜ እና ላጋራን ቁምነገር #እናመሰግናለን።

የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦
1. Afiya Mehammed (Facebook)
2. TG (Telegram)
3. ተስፋዬ ምህረቱ (Facebook) ናቸው።

የስልክ ቁጥራችሁን ላኩልን።

እንዴት ናችሁ የተከበራችሁ የከ ሀ እስከ ፐ አድማጮቻችን? የቅዳሜ፣ ጥር 30/ 2012 ዓ. ም.   ችንን እናስተዋውቃችሁ። #ኢንስትራክተር   ነው።የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የሆ...
07/02/2020

እንዴት ናችሁ የተከበራችሁ የከ ሀ እስከ ፐ አድማጮቻችን? የቅዳሜ፣ ጥር 30/ 2012 ዓ. ም. ችንን እናስተዋውቃችሁ።

#ኢንስትራክተር ነው።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የሆነው አብርሃም ተወልዶ ያደገው እዚሁ አዲስ አበባ፣ በቅሎ ቤት አካባቢ ነው።

በየመን የእግር ኳስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአገሪቱ ብሄራዊ ቡድንን ለኤዢያ ዋንጫ ማሳለፍ መቻሉ የቅርብ ጊዜ ትልቅ ስኬቱ ነው፡፡ እንዲሁም የየመን ከ22 አመት በታች (የኦሎምፒክ ቡድን) በማሰልጠንም ትልቅ ደረጃ አድርሷል፡፡

በክለብ ደረጃ በ1980ዎቹ የጉምሩክ ቡድንን በማሰልጠን በያኔው የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ላይ ድንቅ እንቅስቃሴን ማድረጉ ይታወሳል። የጉምሩክ ቡድንን ወደ አዲስ አበባ ከፍተኛ ዲቪዚዮን ያሳለፈበት መንገድ የተለየ ታሪክ አለው፡፡ ምን ይሆን? ቅዳሜ በሚኖረው ፕሮግራማችን ላይ ይነግረናል፡፡

አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ከጉምሩክ በተጨማሪ በልዩ ልዩ ደረጃዎች የተለያዩ ቡድኖችን እና የኢትዮጵያ ብሐራዊ ቡድንን አሰልጥኗል፤ ኢትዮጵያ ቡና፣ ኒያላ፣ ወንጂ ስኳር እና እህል ንግድ ተጠቃሽ ቡድኖች ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን እያሰለጠነ የሚገኘው አብርሃም ይህንን ኃላፊነት ከያዘ ሁለት ዓመት አልፎታል፡፡

በቅርብ የሚያውቁት ጠንካራ ሰራተኝነቱንና ትሁትነቱን ይመሰክሩለታል፡፡

የተወደዳችሁ አድማጮቻቸችን ለእንግዳችን ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የምታነሱለት ጥያቄ ካለ እንደተለመደው በዚሁ ገፃችን ላይ አድርሱን እንላለን፤ ምክንያቱም ጥሩ ጠያቂዎች ይሸለማሉ፡፡

የከ ሀ እስከ ፐ ፕሮግራማችን ከእንግዳችን በተጨማሪ ሌሎች ቅንብሮቹንም ይዞ፥ ቅዳሜ፣ ጥር 30/2012 ዓ. ም. ከቀኑ 7:30 - 10:00 ሰዓት በፋና ኤፍ. ኤም 98.1 ሬድዮ ይጠብቃችኋል።

የዛሬ እንግዳችን የሙዚቃ አቀናባሪ   ለሰጠን ጊዜ እና ላጋራን ቁምነገር  #እናመሰግናለን።የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦1. Zerihun Teznanu (Facebook)2. Samuel ...
01/02/2020

የዛሬ እንግዳችን የሙዚቃ አቀናባሪ ለሰጠን ጊዜ እና ላጋራን ቁምነገር #እናመሰግናለን።

የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦
1. Zerihun Teznanu (Facebook)
2. Samuel Abebe (Facebook)
3. Fuad Hailu (Facebook) ናቸው።

የስልክ ቁጥራችሁን ላኩልን።

እንዴት ናችሁ የተከበራችሁ የከ ሀ እስከ ፐ አድማጮቻችን? የቅዳሜ፣ ጥር 23/ 2012 ዓ. ም.   ችንን እናስተዋውቃችሁ።    ነው፡፡ አቤል ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ ከአገራችን ወጣት እና ታዋ...
31/01/2020

እንዴት ናችሁ የተከበራችሁ የከ ሀ እስከ ፐ አድማጮቻችን? የቅዳሜ፣ ጥር 23/ 2012 ዓ. ም. ችንን እናስተዋውቃችሁ።

ነው፡፡ አቤል ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ ከአገራችን ወጣት እና ታዋቂ ድምጻዊያን ጋር በመሆን ባቀናበራቸው በርካታ ነጠላ ዜማዎች እና ሙሉ አልበሞች ይታወቃል፡፡

በጄጄ ካሳ የሙሉ አልበም ቅንብር የኢትዮጵያን ሙዚቃ በአቀናባሪነት የተቀላቀለው አቤል በመቀጠል ፣ ፣ ፣ ን ጨምሮ በቅርቡ እስከወጣው የ አልበም ድረስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዘፈኖችን አቀናብሯል፡፡

ከሙዚቃ ቅንብሩ በተጨማሪ በ ተጫዋችነቱ የሚታወቀው አቤል፣ በሚያቀናብራቸው ዘፈኖች ላይ የዚህን የሙዚቃ መሳሪያ ስሜት አጉልቶ ይሰራል፡፡

በአሁኑ ወቅት ሰላሳ የሚደርሱ የአገራችን ድምጻዊያን ዘፈኖቻቸውን በአቤል ጳውሎስ ለማቀናበር በስቱዲዮ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የራሱን የቅንብር ቀለም ይዞ ከመጣው ወጣቱ የሙዚቃ ባለሙያ አቤል ጳውሎስ ጋር በዚህ ሳምንት ቅዳሜ የምናደርገውን የቀጥታ የስቱዲዮ ቆይታ እንድትከታተሉን እየጋበዝን፣ ለእንግዳችን የምታነሱለት ጥያቄ ካለ እንደተለመደው በዚሁ ገፃችን ላይ አድርሱን እንላለን፤ ምክንያቱም ጥሩ ጠያቂዎች ይሸለማሉ፡፡

የከ ሀ እስከ ፐ ፕሮግራማችን ከእንግዳችን በተጨማሪ ሌሎች ቅንብሮቹንም ይዞ፥ ቅዳሜ፣ ጥር 23/2012 ዓ. ም. ከቀኑ 7:30 - 10:00 ሰዓት በፋና ኤፍ. ኤም 98.1 ሬድዮ ይጠብቃችኋል።

.

የዛሬ እንግዳችን ድምጻዊ   ለሰጠን ጊዜ እና ላጋራን ቁምነገር  #እናመሰግናለን።የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦1. Abebe Yibeyin (Facebook)2. ይግረማቸው ነጋሽ ይሉ (...
25/01/2020

የዛሬ እንግዳችን ድምጻዊ ለሰጠን ጊዜ እና ላጋራን ቁምነገር #እናመሰግናለን።

የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦
1. Abebe Yibeyin (Facebook)
2. ይግረማቸው ነጋሽ ይሉ (Facebook)
3. Dawit Nebyu (Facebook)
4. Papio Papio (Facebook)
5. Zerihun Teznanu (Facebook) ናቸው።
የስልክ ቁጥራችሁን ላኩልን።

*ማስታወሻ፦ በፕሮግራማችን ላይ ለሶስት አድማጮች ሽልማት የምንሰጥ ቢሆንም ይሁኔ ቀሪዎቹን እሸልማለሁ በማለቱ ተጨማሪ ሁለት አድማጮች ተሸላሚ ሆነዋል።

እንዴት ናችሁ የተከበራችሁ የከ ሀ እስከ ፐ አድማጮቻችን? የቅዳሜ፣ ጥር 16/ 2012 ዓ. ም.   ችንን እናስተዋውቃችሁ።የዚህ ሳምንት እንግዳችን የባህል ድምጻዊው   ነው፡፡   የባህል ኪነ...
23/01/2020

እንዴት ናችሁ የተከበራችሁ የከ ሀ እስከ ፐ አድማጮቻችን? የቅዳሜ፣ ጥር 16/ 2012 ዓ. ም. ችንን እናስተዋውቃችሁ።

የዚህ ሳምንት እንግዳችን የባህል ድምጻዊው ነው፡፡ የባህል ኪነት ቡድን ካፈራቸው ድምጻዊያን መካከል አንዱ የሆነው ይሁኔ በላይ አስቀድሞ ከሙዚቃ አድማጩ ጋር የተዋወቀው #አንቱዬዋ በተሰኘው ስራ ነው፡፡

ራሱን ጨምሮ ሰማኸኝ በለው፣ ሀብቱ ንጋቱ (አንሙቴ) ብዙአየሁ ጎበዜ፣ አለመወርቅ አስፋው እና ሌሎች የግሽ አባይ ኪነት ቡድን የሙዚቃ ባለሙያዎች እና ተወዛዋዦች የተሳተፉበት ይህ የሙዚቃዊ ድራማ መልክ ያለው ስራ አዲስ አበባ ላይ ከተቀረጸ እና በቴሌቪዥን ከተላለፈ በኋላ ካሴት የመስራት ሃሳብ የጠነሰሰው ይሁኔ ብዙም ሳይቆይ ነበር የመጀመሪያ አልበሙን ያሳተመው፡፡ ከዚያ በኋላምተከታታይ አልበሞችን በግል እና በጋራ አሳትሟል፡፡

ከ1980ዎቹ አጋማሽ አንስቶ ኑሮውን በአሜሪካን አገር ያደረገው ይሁኔ በአማርኛ የባህል ዘፈኖቹ ከአገር አልፎ በአለማቀፍ መድረኮች ጭምር ይታወቃል፡፡

ከሙዚቃ ስራው ጎን ለጎን ወደ ኮሌጅ በመግባትም በኮምፒውተር ኢንፎርሜሽን ሲስተም ዘርፍ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡ በተማረበት የሙያ ዘርፍ እና በሌሎችም ከባለቤቱ ወ/ሮ የሺመቤት ተስፋዬ (ቱቱ) ጋር በመሆን በተሰማሩባቸው የቢዝነስ ዘርፎች ውጤታማ ሆነዋል፡፡

ለ26 ዓመታት በዘለቀው ትዳሩ ሁለት ልጆችን ያፈራው ድምጻዊ ይሁኔ ከመደበኛ ስራው በተጨማሪ በበጎ አድራጎት ተግባራት ላይ በመሳተፍም ይታወቃል፡፡

በዚህ ሳምንት ቅዳሜ አመሻሽ ላይ የሙዚቃ ኮንሰርቱን በአዲስ አበባ የሚያቀርበው ድምጻዊ ይሁኔ የከሀ እስከ ፐ ፕሮግራማችን እንግዳ ነውና የምታነሱለት ጥያቄ ካለ እንደተለመደው በዚሁ ገፃችን ላይ አድርሱን።

የከ ሀ እስከ ፐ ፕሮግራማችን ከእንግዳችን በተጨማሪ ሌሎች ቅንብሮቹንም ይዞ፥ ቅዳሜ፣ ጥር 16/2012 ዓ. ም. ከቀኑ 7:30 - 10:00 ሰዓት በፋና ኤፍ. ኤም 98.1 ሬድዮ ይጠብቃችኋል።

መልካም የጥምቀት በዓል!Happy Ethiopian Epiphany!
19/01/2020

መልካም የጥምቀት በዓል!
Happy Ethiopian Epiphany!

የዛሬ እንግዶቻችን የ   አባላት ለሰጡን ጊዜ እና ላጋሩን ቁምነገር  #እናመሰግናለን።የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦1. መላኩ አምባው (Phone)2. Samuel Abebe (Facebo...
18/01/2020

የዛሬ እንግዶቻችን የ አባላት ለሰጡን ጊዜ እና ላጋሩን ቁምነገር #እናመሰግናለን።

የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦
1. መላኩ አምባው (Phone)
2. Samuel Abebe (Facebook)
3. Yohannes Mulatu (Facebook) ናቸው።

የስልክ ቁጥራችሁን ላኩልን።

እንዴት ናችሁ የተከበራችሁ የከ ሀ እስከ ፐ አድማጮቻችን? የቅዳሜ፣ ጥር 9/ 2012 ዓ. ም.   ችንን እናስተዋውቃችሁ።የዚህ ሳምንት እንግዶቻችን የ  #ጃኖ የሙዚቃ ቡድን አባላት ናቸው፡፡ ...
16/01/2020

እንዴት ናችሁ የተከበራችሁ የከ ሀ እስከ ፐ አድማጮቻችን? የቅዳሜ፣ ጥር 9/ 2012 ዓ. ም. ችንን እናስተዋውቃችሁ።

የዚህ ሳምንት እንግዶቻችን የ #ጃኖ የሙዚቃ ቡድን አባላት ናቸው፡፡

፣ ፣ እና በዋና ድምጻዊነት የያዘው ኢትዮጵያዊ ዜማዎችን ጊታር ጠንከር ብሎ በሚሰማበት የሮክ ስልት በመጫወት የሚታወቅ ቡድን ነው፡፡

በታዋቂው የሙዚቃ ፕሮዲውሰር እና ፕሮሞተር አማካይነት የተሰባሰቡት ጃኖዎች #ኤርታሌ የተሰኘውን የመጀመሪያ አልበማቸውን በ2005 ዓ.ም ካሳተሙ በኋላ ተወዳጅነትን ለማግኘት ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ በተለይ በመድረክ ሙዚቃ በሚያቀርቡበት ጊዜ የሚያሳዩት የተለየ አቀራረብ ተወዳጅነታቸውን ጨምሮላቸዋል፡፡

ከመጀመሪያ አልበማቸው በኋላ በአገር ውስጥ እና በውጪ ተከታታይ ኮንሰርቶችን ሲሰሩ ቆይተው በ2009 ዓ.ም ሁለተኛ አልበማቸውን የሚል መጠሪያ በመስጠት ለገበያ አቅርበዋል፡፡ ነጠላ ዜማዎችንም እንካችሁ ብለውናል፡፡

በቅርቡ ወደ ኤርትራ ከተጓዘው የኢትዮጵያ የባህል ልዑክ ጋር በመሆን በተለያዩ ከተሞች የሙዚቃ ትርዒት አቅርበው መመለሳቸውም ይታወሳል፡፡

የተወደዳችሁ አድማጮቻችን፣ ለጃኖ ባንድ አባላት የምታነሷቸው ጥያቄዎች ካሉ እንደተለመደው በዚሁ ገፃችን ላይ አድርሱን።

የከ ሀ እስከ ፐ ፕሮግራማችን ከእንግዳችን በተጨማሪ ሌሎች ቅንብሮቹንም ይዞ፥ ቅዳሜ፣ ጥር 9/2012 ዓ. ም. ከቀኑ 7:30 - 10:00 ሰዓት በፋና ኤፍ. ኤም 98.1 ሬድዮ ይጠብቃችኋል።

የዛሬ እንግዳችን  #ድምጻዊ   ለሰጠን ጊዜ እና ላጋራን ቁምነገር  #እናመሰግናለን።የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦1. Han Yemaryam (Facebook)2. ተስፋየ ምህረቱ (Fac...
11/01/2020

የዛሬ እንግዳችን #ድምጻዊ ለሰጠን ጊዜ እና ላጋራን ቁምነገር #እናመሰግናለን።

የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦
1. Han Yemaryam (Facebook)
2. ተስፋየ ምህረቱ (Facebook)
3. Bisrat Tsehay (Facebook) ናቸው።

የስልክ ቁጥራችሁን ላኩልን።

እንዴት ናችሁ የተከበራችሁ የከ ሀ እስከ ፐ አድማጮቻችን? የቅዳሜ፣ ጥር 2/ 2012 ዓ. ም.   ችንን እናስተዋውቃችሁ። #ድምጻዊ፣ የግጥም እና ዜማ ደራሲ   ይባላል፡፡ድምጻዊ ካሳሁን፣ ተወ...
09/01/2020

እንዴት ናችሁ የተከበራችሁ የከ ሀ እስከ ፐ አድማጮቻችን? የቅዳሜ፣ ጥር 2/ 2012 ዓ. ም. ችንን እናስተዋውቃችሁ።

#ድምጻዊ፣ የግጥም እና ዜማ ደራሲ ይባላል፡፡
ድምጻዊ ካሳሁን፣ ተወልዶ ባደገባት #አርባምንጭ ከተማ አንድ ያለው የሙዚቃ ተሰጦን የማውጣት እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ለአስራ ስምንት ዓመታት የዘለቀ የምሽት ክበብ ስራን እንዲሰራ አስችሎታል፡፡ በምሽት ቤቶች ውስጥ የንዋይ ደበበን ዘፈኖች በመጫወት ይታወቃል።

የራሱን አዳዲስ ስራዎች እንካችሁ ከማለቱ አስቀድሞ ለሌሎች ድምጻዊያን የግጥም እና ዜማ ድርሰቶች ሲሰጥ የቆየው ካሳሁን፥ በመቀጠል (ከታደሰ በቀለ ጋር) ፣ (ከታደሰ በቀለ ጋር)፣ #አውዳመት (ከቆንጂት ሻንቆ ጋር)፣ የተሰኙ ወጥ ዘፈኖችን ወደ አድማጭ አድርሷል፡፡

ከዛ አስቀድሞም ግን በተሰኘ እና ቴዎድሮስ ካሳሁን ( )፣ ፣ ፣ እና ሌሎችም በተካተቱበት የኮሌክሽን ሙዚቃ አልበም ላይ ሁለት ዘፈኖችን ተጫውቶ ተሳትፏል፡፡

በሙዚቃ ውስጥ ለረዥም አመታት እንደመቆየቱ እስካሁን ለምን የራሱን ሙሉ አልበም አልሰራም? ካሳሁን እንደሚለው ከአስራ አምስት አመታት በፊት የሙዚቃ አልበም ለማሳተም ፕሮጄክት ቢጀምርም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ በምን ምክንያት? አሁንስ የአልበም ስራው በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

ለእነዚህ እና ለሌሎችም ለምታነሷቸው ጥያቄዎች መልስ ሊሰጥ የዚህ ሳምንት እንግዳችን ሆኖ ስቱዲዮ ይገኛል፡፡

ጥያቄዎቻችሁን እንደተለመደው በዚሁ ገፃችን ላይ አድርሱን።

የከ ሀ እስከ ፐ ፕሮግራማችን ከእንግዳችን በተጨማሪ ሌሎች ቅንብሮቹንም ይዞ፥ ቅዳሜ፣ ጥር 2/2012 ዓ. ም. ከቀኑ 7:30 - 10:00 ሰዓት በፋና ኤፍ. ኤም 98.1 ሬድዮ ይጠብቃችኋል።

09/01/2020

Gize Multimedia

ጊዜ መልቲሚዲያ በኢቴቪ መዝናኛ ቻናል በዕለተ ገና ባስተላለፈው ልዩ የበዓል ፕሮግራም ላይ የተሳተፋችሁ ሙያተኞች በሙሉ ከልብ እናመሠግናለን።

For all of you who took part in our Gena TV program which was aired on ETV Entertainment channel, we would like to say Thank You!!!

እንኳን ለገና በዓል አደረሰን!ከሀ እስከ ፐ ፕሮግራም ዝግጅት ክፍል
07/01/2020

እንኳን ለገና በዓል አደረሰን!

ከሀ እስከ ፐ ፕሮግራም ዝግጅት ክፍል

የዛሬ እንግዳችን  #ሠዓሊ   ለሰጠን ጊዜ እና ላጋራን ቁምነገር  #እናመሰግናለን።የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦1. ይስሀቅ ፀዳለ (Facebook)2. አደይ አበባ (Facebook)3...
04/01/2020

የዛሬ እንግዳችን #ሠዓሊ ለሰጠን ጊዜ እና ላጋራን ቁምነገር #እናመሰግናለን።

የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦
1. ይስሀቅ ፀዳለ (Facebook)
2. አደይ አበባ (Facebook)
3. እያሱ ጥቁር ሰው (Facebook) ናቸው።

የስልክ ቁጥራችሁን ላኩልን።

እንዴት ናችሁ የተከበራችሁ የከ ሀ እስከ ፐ አድማጮቻችን? የቅዳሜ፣ ታህሳስ 26/ 2012 ዓ. ም.   ችንን እናስተዋውቃችሁ። #ሰዓሊ   ነው። ሰዓሊ መዝገቡ ተሰማ ትውልዱ በሰሜን ሸዋ ሲሆን...
02/01/2020

እንዴት ናችሁ የተከበራችሁ የከ ሀ እስከ ፐ አድማጮቻችን? የቅዳሜ፣ ታህሳስ 26/ 2012 ዓ. ም. ችንን እናስተዋውቃችሁ።

#ሰዓሊ ነው። ሰዓሊ መዝገቡ ተሰማ ትውልዱ በሰሜን ሸዋ ሲሆን፣ አብዛኛውን የልጅነት ጊዜውን ያሳለፈው በጅሩ እነዋሪ ከተማ ነበር።

ያደገበት አካባቢ የተፈጥሮ አቀማመጥና መልከዓ ምድር ሥዕልን በልጅነቱ እንዲሞክር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ቢያደርግለትም ሰዓሊ መሆን እንደሚፈልግ ያወቀው ግን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወደ ደብረ ብርሃን ከሄደ በኃላ ነበር። በትምህርት ቤቱ መርጃ መሣሪያዎች፣ ካርታና ድርብ ፅሑፍ መጻፍን ጨምሮ የተለያዩ በዓላትን ማድመቂያ ሥራዎችን በማቅረብ እገዛ አድርጓል።

ከዚያም በ ፣ አለ የሥነጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ተምሮ በከፍተኛ ውጤት ተመረቀ፤ በመቀጠልም ሩስያ ወደሚገኘው ሬፒን የሥዕል፣ የቅርፃ ቅርፅና የህንፃ ጥበብ ትምህርት ቤት በማቅናት ሁለተኛ ዲግሪውን ተቀበለ።

መዝገቡ #ቤተሰብ ከተሰኘው የበኩር ሥዕሉ አንስቶ፣ 10 ስኩዌር (ካሬ) ሜትር ሸራ ላይ ያለው #ንግሥ የተሰኘ ሥራውን ጨምሮ ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፉ ሥራዎችን አሳይቷል። እና ንግሥ የተባሉት የሥዕል አውደ ርዕዮች ከፍተኛ ተወዳጅነት አትርፈውለት ነበር።

እውናዊ (Realistic) የአሳሳል ዘዬን የሚከተለው ሰዓሊ መዝገቡ፣ በአሁኑ ወቅት በተማረበት የአለ የሥነ ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት በመምህርነት እያገለገለ ይገኛል።

የተወደዳችሁ አድማጮቻችን ለ #እንግዳ ችን ለሰዓሊ መዝገቡ ተሰማ የምታነሱት ጥያቄ ካለ እንደተለመደው በዚሁ ገፃችን ላይ አድርሱን።

የከ ሀ እስከ ፐ ፕሮግራማችን ከእንግዳችን በተጨማሪ ሌሎች ቅንብሮቹንም ይዞ፥ ቅዳሜ፣ ታህሳስ 26/2012 ዓ. ም. ከቀኑ 7:30 - 10:00 ሰዓት በፋና ኤፍ. ኤም 98.1 ሬድዮ ይጠብቃችኋል።

የዛሬ እንግዳችን  #ድምጻዊት   ለሰጠችን ጊዜ እና ላጋራችን ቁምነገር  #እናመሰግናለን።የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦1. Henok Adinew (Facebook)2. Dubale Abat...
28/12/2019

የዛሬ እንግዳችን #ድምጻዊት ለሰጠችን ጊዜ እና ላጋራችን ቁምነገር #እናመሰግናለን።

የዕለቱ ምርጥ ጠያቂ አሸናፊ አድማጮች፦
1. Henok Adinew (Facebook)
2. Dubale Abate (Telegram)
3. Mehretesilassie (Phone) ናቸው።

የስልክ ቁጥራችሁን ላኩልን።

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251969959549

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ከሀ እስከ ፐ Ke Ha Eske Pe posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category