01/01/2025
የተጫዋቾች የዝውውር ጭምጭምታዎች
………
ሊቨርፑል ከሪያል ማድሪድ የቀረበለትን የ26 አመቱን እንግሊዛዊ የቀኝ መስመር ተከላካይ ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድን በጥር ወር የማስፈረም ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል።
ጁቬንቱስ እና ናፖሊ የማንቸስተር ዩናይትድን የ23 አመቱን ኔዘርላንዳዊ አጥቂ ጆሹዋ ዚርክዚን የማስፈረም ፍላጎት አላቸው፡፡
ማንቸስተር ዩናይትዶች በጥር ወር ቡድናቸውን ለማጠናከር በጀት የላቸውም፤ ትርፋማነትን , ዘላቂነትን እና የፋይናንሺያል ፌር ፕሌይ ህጎችን ለማክበር ከመግዛታቸው በፊት በመጀመሪያ መሸጥ አለባቸው ተብሏል።
የ32 አመቱ ግብፃዊው መሀመድ ሳላህ እና የኔዘርላንዱ ተከላካይ ቨርጂል ቫንዳይክ የሊቨርፑል ቆይታቸውን በሁለት አመት ያራዝማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሊቨርፑል የ25 አመቱን ኡራጓዊ አጥቂ ዳርዊን ኑኔዝን ለመሸጥ እና የ 27 አመቱን የኢንተር ሚላን ፈረንሳዊ አጥቂ ማርከስ ቱራ እና የ25 አመቱን የኒውካስል ስዊድናዊ አጥቂ አሌክሳንደር ኢሳክን ተተኪ ሊያደርጉ አስበዋል ።
ሊቨርፑሎች የ 21 አመቱን ሃንጋሪዊ የግራ መስመር ተከላካይ ሚሎስ ኬርኬዝን ከበርንማውዝ በማስፈረም ማንቸስተር ዩናይትድን ሊፎካከሩ ይችላሉ።
ዎልቭስ የ25 አመቱ እንግሊዛዊ ተከላካይ ያፌት ታንጋንጋን በጥር ወር ለማስፈረም እንደሚፈልጉ አሰታውቀዋል ፡፡
ኖቲንግሃም ፎረስት የማንቸስተር ሲቲ ኢላማ ከሆነው የ28 አመቱ ናይጄሪያዊ ተከላካይ ኦላ አይና ጋር አዲስ ኮንትራት እንደሚፈራረም እርግጠኛ ሆነዋል።
ሪያል ማድሪድ የ19 አመቱን የቦርንማውዙን ስፔናዊ ከ21 አመት በታች ተከላካይ ዲን ሁኢጅሰንን የግላቸው ማድረግ ይፈልጋሉ።
አርሰናል፣ ሊቨርፑል፣ ቼልሲ እና ቶተንሃም ማንቸስተር ዩናይትድ እና ማንቸስተር ሲቲም ተቀላቅለዋል የባርሴሎናውን የ26 አመቱ ስፔናዊ የፊት መስመር አጥቂ ዳኒ ኦልሞ ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል።
ባርሴሎና ኦልሞን በውድድር አመቱ ሁለተኛ አጋማሽ ማስመዝገብ ካልቻለ የ27 አመቱን የቼልሲውን አጥቂ ክሪስቶፈር ንኩንኩን በውሰት ማዘዋወር ይችላል።
ኦልሞ ግን በምዝገባው ላይ እርግጠኛ ባይሆንም በባርሴሎና መቆየት ይፈልጋል።
ባየር ሙኒክ በዚህ ክረምት ሊያስፈርሟቸው የሚችሏቸውን በርካታ ግብ ጠባቂዎች ከስምምነት ዝርዝር ውስጥ ያስገባ ሲሆን ከነዚህም መካከል የብራይተኑ የ22 አመቱ ኔዘርላንዳዊ ባርት ቨርብሩገንን ጨምሯል።
በማንደፍሮ ታደሰ
(ታህሳስ 23/2017)
………….
Follow us
ፌስቡክ ፡- https://www.facebook.com/radioethiopia11?mibextid=ZbWKwL
በዌብሳይት ቀጥታ ፡- http://www.ebc.et/videolink.aspx?id=3
በዜኖ fm ቀጥታ ፡- https://zeno.fm/radio/ebc-ethiopia-radio/
መደበኛ ስርጭታችንን አዲስ አበባን ጨምሮ በአብዛኛዎቹ የአገሪቱ አካባቢዎች በFM 93.1 ፣ ባህር ዳር እና ሀገረ ሰላም (ሲዳማ) በFM 104.7 እንዲሁም ጎንደር በFM 97.1 መከታተል ትችላላችሁ፡፡ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ የመካከለኛ ሞገድ ማሰራጫ ጣቢያዎቻችንም ሥራ ላይ ናቸው።
ሳተላይት ላይ ደግሞ፡- ethio sat 11165 / symbol rate 4500 / vertical ላይ ያገኙናል ፡፡
እናመሰግናለን