Abyssinia Geʽez Amhara Voice AGAV

Abyssinia Geʽez Amhara Voice AGAV ethiopia music | ESAT TV | Ethiopia | New Amharic Drama | VOA Amharic | DW Amharic | Seifu on EBS,

25/09/2024

📍የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር 1948 ዓ.ም. በሸዋ አዲስ አበባ ኢትዮጲያ
Meskel /Demera/ celebration 1955 in Addis Ababa Shewa ) Ethiopia

#መስቀል

11/09/2024

እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴወስ በሰላም አደረሰን! 🌼🌼🌼🌼እንቁጣጣሽ እ🌼🌼🌼🌼 2017 🦁♥️

28/08/2024

የጠገቡ ለት ሞት አይገኝም

27/08/2024

⚠️🚨

የሟቾች ቁጥር 23

2700 በላይ ተፈናቃይ

48 ቤቶች ፈርሰዋል

1775 ሄክታር የተዘራ ሰብል ወድሟል

15/08/2024

📌ከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ
====================================
የደም ዋጋ የተከፈለበት የነፃነት መዋቅር በጠላት ሰርጎ ገቦችና ባንዳዎች አይፈርስም!

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ የማንነትና ወሰን ትግል ዛሬ ላይ በእጃችን የገባውን አማራዊ ነጻነት ለማግኘት ሁለት ትውልድ የተቆጠረበት መራር መሥዋዕትነት ተከፍሎበታል፡፡ እስካሁን በመጣንበት የትግል መንገድ፤ ከከፋኝ የአርበኞች ተጋድሎ እስከ የማንነት አስመላሽ ኮሚቴው ሰላማዊ የትግል መስመር፤ የሰሜን ዕዝ ከጀርባ መታረድን ተከትሎ በሕግ-ማስከበር ዘመቻው እንደአገር ኢትዮጵያን ከጥቃት፣ እንደ ወልቃይት ጠገዴ አማራ ሕዝብ ደግሞ ከወያኔ-ግፈኛ የባርነት አገዛዝ ነፃ ለማውጣት ክቡር መሥዋዕትነት ከፍለናል፡፡

በዚህም በእጃችን በገባው ነጻነት እስከ አሁን ድረስ የዘለቀው የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ምሥረታና ራስን በራስ የማስተዳደር ዕድል በጋራ መሥዋዕትነታችን፣ በትግል ዓላማ ጽናታችን እዚህ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

ወልቃይት-ጠገዴ በመላ አማራ ትግል ከጠላት ነጻ ወጥቶ፣ ሕዝባችንም የተነጠቀ ማንነቱን ዳግም በግፈኞች እንዳይነጠቅ ከምን ጊዜውም በላይ ራሱን አደራጅቶ እየጠበቀ ይገኛል፡፡

የትግሉ ባለቤት የሆነው የአማራ ሕዝብ፣ ከፍትሐዊው የማንነት ትግላችን ጎን የቆሙ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ዓለማቀፉ ማኀበረሰብ እንደሚያውቀው ዞናችን መደበኛ በጀት የሌለው ነገር ግን ‹ነጻነታችን በጀታችን› በሚል ወኔ፣ቁጭት፣እልህና ተስፋን የትግላችን ማዕከል አድርገን ከሕዝብ፤ ለሕዝብ፤ በሕዝብ፤ የሆነ አስተዳደራዊ የነፃነት መዋቅር ዘርግተን ለዘላቂ የህግ አሸናፊነት ትግል ላይ እንገኛለን፡፡

በጀት የማይበግረው፤ ወራሪ የማይደፍረው ማኀበረሰብ መገንባት የተቻለው፤ የማንነት ኮሚቴው፣ የዞኑ አስተዳደር እና ሕዝቡ አንድ ልብ መካሪ፤ አንድ ቃል ነጋሪ መሆን በመቻላችን ነው፡፡

ሆኖም ግን የጥፋት መንገዱ ብዙ የሆነው ወያኔ ዞኑን መልሶ በግፍ ለመውረር ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሙከራዎችን አድርጓል፡፡ ጥቃቱ የተልዕኮና ቀጥታ፤ የተቀናጀና የዕቅድ ደረጃዎች (Plan A, B, C) ያሉት ሆኖ ታይቷል፡፡

የወያኔ ወታደዊና የደህንነት ክንፍ በቀጥታ የወረራ ሙከራዎቹ በሱዳንና በተከዜ በኩል ተደጋጋሚ ጥረት አድርጎ አከርካሪውን እየተመታ በተደጋጋሚ ተመልሷል፡፡ በዚህ መልኩ እንደማይሳካለት ያወቀው ጠላት፥ በአንድ በኩል፣ የብረት በር የሆኑበትን የማንነት ኮሚቴና አስተዳደር ቁልፍ አመራሮች ከሕዝብ ለመነጠል በተደራጀ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ስም ማጠልሸት፤ በሌላ በኩል ደግሞ ለፖለቲካ ዓላማ በልዩ ሁኔታ ወታደራዊ ስልጠና የወሰደ ገዳይ ቡድን ከትግራይ መልምሎ ወደዞኑ በማስገባት ኮር አመራሩን የማጥቃት፣ ወዘተ... የጥፋት ሙከራዎቹን ቢያደርግም የእውነት አምላክ ከሕዝባችን ጎን በመቆሙ፣ በአመራሩና በጥምሩ የፀጥታ ሀይላችን ጥንካሬ በሕዝቡ አማራዊ አንድነት ብርታት የታቀዱ የጠላት ሴራዎች ሁሉ ከሽፈዋል፡፡

እነዚህ ሁሉ ሲሉ ሙከራዎቹ ሲከሽፉ፣ በክልላችን የተከሰተውን እጅግ አሳሳቢ የፀጥታ ችግር፣ የአማራ ሕዝብን ፈተና ላይ መውደቅን እንደዕድል በመጠቀም ወያኔ ወልቃይት-ጠገዴን ዳግም ለመውረር ያመቸው ዘንድ ለጥፋት ዓላማው ስምሪት ላይ ከርሟል፡፡

በዚህም አጠቃላይ ሕዝብና መዋቅራችን ላይ ያነጣጠረ የሰርጎ ገቦች ጥቃት ለመክፈት በትጥቅ፣ በገንዘብና በፕሮፖጋንዳ ድጋፍና የግንኙነት አመራር በመስጠት ነጻ በወጣ ምድራችን ላይ ቅጥረኞቹን/ባንዳዎችን መልምሎ ለጥፋት ዓላማ ማሰማራቱን ከኀብረተሰቡ ጋር ባደረግነው ውይይትና የመረጃ ክትትል አረጋግጠናል፡፡ ስለሆነም ከወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ የማንነት ሁለንተናዊ ትግል ፍላጎትና ስምሪት በተፃራሪ የግፈኛው-የወያኔ ቡድን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ፍላጎት የሆኑትን:-

1) አስተዳደሩ ጠላቱን የሚከላከልበትን ለአከባቢው ነዋሪዎች ያስታጠቀውን የጦር መሣሪያ ማስፈታት፤

2) የማንነትና የወሰን አስተዳደር መዋቅርን ማፍረስና ፀረ-ማንነት ትግል ሁኖ መታየት

3) በወረዳና በቀበሌ ደረጃ የተደራጀውን የማንነት አደረጃጀት ዶክመንቶችን፣ ፋይሎችንና ልዩ ልዩ ሰነዶችን ማቃጠል/ማውደም፤

4) በትግራይ በኩል በተከዜ ወሰን የወያኔ ታጣቂ ለወረራ ወሰን እንዳይሻገር የወልቃይት-ጠገዴ ተከዜ ዘብ ከሚጠብቅበት፤ በሱዳን የሚገኘው የታጣቂው ኃይል አካል የሆነው ‹የሳምሪ ገዳይ ቡድን› የአገር ዳር-ድንበር ሰብሮ ለወረራ እንዳይገባ ዘብ ሆኖ እየጠበቀ ባለው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ምንም ዓይነት ትንኮሳ እንዳይደረግ በዞናችን አስተዳደርና ሕዝብ የጋራ አቋም የተወሰደበትን ስምምነት በመጣስ በአውራ ወረዳ ሎሚ ወንዝ ቀበሌ ፣ ጠገዴ ወረዳ አዳይጦ እና በቃብትያ ሁመራ ወረዳ በእድሪስ ቀበሌዎች ባሉ ቀይመስመሮች በሕዝባችንና በፀጥታ ኃይሉ ላይ ትንኮሳ አድርገዋል፡፡

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ፀረ-አማራነት ተግባራት እና ይህን የሚያስፈጽሙ የታጠቁ ፀረ-ሰላም ሀይሎች ድርጊታቸው የጠላት ወታደራዊና ፖለቲካዊ ፍላጎት እንደሆነ፣ ለዚህም ከወያኔ ውክልና የወሰዱ መሆኑን በማስረጃ አረጋግጠናል፡፡

ለዚህም ሰፊ የሕዝብ ተሳትፎ እያረጋገጥን የመጣንበት በወረዳና በቀበሌ ደረጃ የተደራጀው የማንነት አደረጃጀት፣ የዞኑ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት፣ ከዋናው የማንነትና ወሰን ኮሚቴው ጋር በመቀናጀት በየደረጃው ካለው የኀብረተሰብ ክፍል ጋር በተደረገው ውይይትና ሕዝባዊ የመረጃ ልውውጥ ማስረጃዎች ተገኝተዋል፡፡

ስለሆነም የጠላትን ተልዕኮ በወሰዱ የሰርጎ ገቦች የጥቃት ሰለባ ከሆኑ ወገኖቻችን ጉዳትና ከሕዝባችን ተጨባጭ መረጃ በመነሳት፣ ከዚህ በፊት ከክልላዊ፣ አገራዊና ቀጠናዊ ሁኔታዎች በመነሳት ስትራቴጂካዊ ግምገማ በማድረግ እንዳይነኩ አቋም የወሰድንባቸው ወሳኝ ጉዳዩች ቀይ መስመሩ ታልፎ ሕዝባችንን ለዳግም ባርነት፤ ኢትዮጵያንም ለፍርሰት የሚዳርግ የምድር በሩን የማፍረስ ሙከራ በጠላት ሰርጎ ገቦች መሞከሩን አረጋግጠናል፡፡

የወልቃይት-ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ከሚታገልለት ሕዝብ ባሻገር፣ የመላው አማራ የትግል አስኳል የሆነውን ትግል፣ የኢትዮጵያን የምድር በር ብሔራዊ ደህንነቷን የመጠበቅ መልክዓምድራዊና ታሪካዊ የትግል አደራ ያለበትና በዚህም ብዙ መከራ ያሳለፈ መሆኑን ወዳጅም ጠላትም ይገነዘባል፡፡

ችግራችን ውስብስብ፣ የሁሉንም ወገን አገራዊ ትብብር የሚጠይቅ፣ ጊዜ የማይሰጥ፤ ምንም ዓይነት ስህተት ሊታይበት የማይገባ በመሆኑ፤ የወልቃይት-ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የትርምስ ቀጠና እንዳይሆን የፋኖ ኃይሎች ወደ ዞኑ ከመግባት ተቆጥበው ያሉ መሆኑ እየታወቀ፤ የወቅቱን የክልላችንን ሁኔታ እንደዕድል በመጠቀም ወያኔ ለወታደራዊና ፖለቲካዊ ፍላጎቶቹ መሳካት ሲል በትጥቅ፣ በገንዘብ፣ በፕሮፖጋንዳና የግንኙነት አመራር በመስጠት የሚደግፈው ሰርጎ ገብ ኃይል ስለመሆኑ እንዲታወቅልን እናሳስባለን፡፡

እነዚህ የጠላትን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን ለማሳካት የወልቃይት-ጠገዴ አማራ ሕዝባችንን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ተልዕኮ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች፡-

ከዚህ ታሪክ ይቅር ከማይለው የፀረ-አማራነት ድርጊት፤ ለወያኔ የ‹‹ታላቋ ትግራይ ሪፐብሊክ›› ምሥረታ አገር አፍራሽ መንገድ ጠራጊነታቸው የማይቆጠቡ ከሆነ ሕዝባችን ወደዳግም ባርነት ላለመመለስ፤ የደም ዋጋ የከፈለበትን አስተዳደራዊ መዋቅሩን በመጠበቅ አማራዊ ነፃነቱን ለማስከበር ሲል ሰርጎ ገቦችንና ባንዳዎችን በይፋ ይታገላል፡፡ እምቢ ለባርነት በማለት ሁሉም ሰው፣ ሁልጊዜምና በሁሉም ቦታ መታገል አስፈልጓል። የሰማዕታት አደራ አለብን!

መላ የወልቃይት-ጠገዴ ሕዝብ የዞኑ አስተዳደርን ከጠላት ሰርጎ ገቦችና ባንዳዎች ለመጠበቅ ሕግ የማስከበር እርምጃ እንዲሚወሰድ የዞን፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤቱ ወስኗል።

በመጨረሻም፤

በደም የፈካው ነጻነታችንን፤ እስከሞት የምንታመንለት አማራነታችንን የሚያፀናልንን የማንነት አስተዳደር እንዲፈርስ መቼውንም ቢሆን የሚፈቅድ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ሕዝብ የለም! ሕዝባችን በደምና አጥንቱ ያመጣውን ድል ራሱ ይጠብቀዋል እንጂ በጠላት የሴራ መንገድ አይራመድም! ወልቃይት-ጠገዴ በመላ አማራና በፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ትግል ከጠላት ነጻ ወጥቷል፤ ለዘላቂ የሕግ አሸናፊነት ፀንቶ ይቆማል፡፡ በየትኛውም ሁኔታ ወደዳግም ባርነት ሊመልሱት ተልዕኮ የወሰዱ የጠላት ሰርጎ ገቦችንነ‍ኣ ባንዳዎችን አይታገስም! የሚጠናከር እንጂ የሚፈርስ አስተዳደር የለንም!

በሌላ በኩል እጅግ ጥቂት የሚዲያ አካላት የጠላትን ተልዕኮ የወሰዱ ሰርጎ ገቦችን እንቅስቃሴ ከእውነታው ተቃራኒ በሆነ መንገድ መዘገባቸውን ተመልክተናል፡፡ በጠላት የተገዙ እንዳሉ ብናውቅም እውነታውን ባለማወቅ የተሳሳተ መረጃ ያሰራጫችሁ የሚዲያ አካላት ከዚህ በኋላ ላለው ዘገባችሁ ከእውነት ጎን እንድትቆሙ በትግሉ ሰማዕታት ስም አደራ እያልን፤ የጠላት የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ማሽን የሆኑትን ሚዲያዎች የትግሉ ባለቤት የሆነው መላው የአማራ ሕዝብና ፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እንዲታገሏቸው ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የወልቃይት-ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን በዘላቂነት የማስከበር ትግል ከመቼውም ጊዜ በላይ ሕዝባዊ አንድነትና ስትራቴጂካዊ አመራር ይጠይቃል፡፡ በወልቃይት ጠገዴ ነጻ ምድር ከጠላት ሰርጎ ገብና ባንዳ ቀጠናውን ለመጠበቅ ሁላችንም፣ ሁልጊዜምነ‍ኣ በሁሉም ቦታ ዝግጁ ሆኖ መገኘትና መታገል ነው:- የተከዜ ዘብ መርሁ እንጂ የተገኘውን ነፃነት ለጠላቶቻችን አሳልፎ መስጠት አይደለም።

ወልቃይት-ጠገዴ ቀይ መስመር ነው!

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር

ነሐሴ 06፤ 2016 ዓ.ም.
ሁመራ-አማራ፤ ኢትዮጵያ!

07/08/2024

እስክድር ጀግና ነው 💪🏾

04/06/2024
28/05/2024

💥University of Washington Students perform Amhara cultural dances.
#አማራዬ ♥️

Ato Mammo Tadesse, Governor for Ethiopia, Annual Meetings, World Bank Group, Washington, D.C., USA. 1969
27/05/2024

Ato Mammo Tadesse, Governor for Ethiopia, Annual Meetings, World Bank Group, Washington, D.C., USA. 1969

27/05/2024

🫶🏽እንግዲህ የኛዎቹ ወንዶች ሙያ እየተማራችው ኩሽና ገብቶ መስራት ክብር ነው ✊🏾😋

Ethiopian 10, 000m record holder Haile Gebrselassie with his fans in Birmingham to advertise his world record attempt at...
22/05/2024

Ethiopian 10, 000m record holder Haile Gebrselassie with his fans in Birmingham to advertise his world record attempt at the Indoor Arena, 22 November 1998

19/05/2024

♥️

Proud to be Amhara 🫶🏽

ሸዋ አዲስ አበባ አማራ 💎

#አማራዬ♥️ _ _ _ _ #አማራዬ♥️

18/05/2024

#ሰበር
የሸዋ ሰማይ ከመሬት ጋር ፀብ ያለው ይመስል እንደ መድፍ ሲያስገመግም ጀማና ወንጪት ጃራና ወለቃ ከሰምና አዳባይ የፍቼ ወንዝና ዜጋመል የጃማና ደጎሎ ጉም ሲጎምም በክረምቱ ወራት ሃምሌ በዕለተ ጊዮርጊስ በቀን 23 1944 ዓ/ም ከመሬ ሚዳ ከሸዋዋ ደርባባ ከእናቱ ወይዘሮ ሸዋየ ተካና ከአራሽ ገበሬው ከመንዜ መራኛው አባቱ ከአቶ አየለ ካሰኝ በመራቤቴ መራኛ ሸዋ ተወለደ።

እንደማንኛውም ልጅነቱን በእረኝነት፥ በግብርና እንዲሁም በቆሎ ተማሪነት እንደማንኛውም ልጅ የልጅነት ጊዜውን አሳልፏል። እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ ባአቅራቢያው በሚገኘው መራኛ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ ተምሯል።

ዳምጠው አየለ ህይወቱ እስካለፈችበት ጊዜ ድረስ ለረዥም ጊዜ አብሯት የኖረው ባለቤቱ አልማዝ ይመር ትባላለች። ከአልማዝ ይመር አብዩ ዳምጠውና ቤቴልሄም ዳምጠው የሚባሉ ሁለት ልጆችንም አፍርቷል።

ዳምጠው አየለ መራቤቴ እያለ በየባዕላቱ መዝፈን፣ ማቅራራት እንዲሁም መሸለል ይወድ እንደነበር ተናግሯል። በተለይም ጥምቀትን በማድመቅ ይታወቅ ነበር። የ 6ኛ ክፍል ተማሪ እያለ ክፍሌ ሞገስ የሚባል መምህሩ ወደ አዲስ አበባ ይዞት እንደመጣ ይናገራል። በአጣሚም የምድር ጦር ማስታወቂያ አውጥቶ ስለነበር ይፈተንና ያልፋል። የምድር ጦር ካምፕ ውስጥም እንዲኖር ይደረጋል። የዘፋኝነት ሙያው በዚህ አጋጣሚ ነበር የጀመረው። ዳምጠው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማዉና መነሻ የሆነው አበበ ተሰማ እንደሆነ ይናገራል። ዳምጠው አየለ በምድር ጦር ከ 30 አመት በላይ አገልግሏል። የኢትዮዽያ ምድር ጦር በ1927 አ/ም ተመስርቶ በ1983 አ/ም የፈረሰ የሙዚቃ ቡድን ነበር። ዳምጠው በመንግስት ለውጥ ምክንያት እስከፈረሰበት ጊዜ ድረስ አብሮ እንደነበር ይናገራል። ምድር ጦርም እያለ ከነታምራት ሞላ፣ ሲራክ ታደሰ፣ ተክሌ ደስታ ፣ ጥላየ ጨዋቃ፣ ክፍሌ አቦቸር እንዲሁም ሌሎች የጦሩ አባላት ጋር ሰርቷል።

ከሌሎች የሙዚቃ ቡድንም ጋር አብሮ ሰርቷል። ለምሳሌ ያክል ከነ ክቡር ጥላሁን ገሰሰ፣ ሙሃሙድ አህመድ፣ ብዙነሽ በቀለ ፣ ሙሉቀን መለስ፣ ፀሃየ ዮሃንስ፣ ቴድሮስ ታደሰ፣ቴድሮስ ካሳሁን እንዲሁም ሌሎችም ጋር ሰርቷል። የዳምጠው አየለ የመጀመሪያ የህትመት ስራው በ1963 አ/ም ሲሆን ወፌ ላላ የሚለው የሸክላ ስራ ነበር። ዳምጠው አየለ ባጠቃላይ 13 ሲዲዎችን ሰርቷል።

ድምፃዊ ዳምጠው አየለ ከብዙዎች ለየት የሚያደርገው የባህል ሙዚቃ ዘፋኝነቱ ብቻ ሳይሆን የአዘፋፈን ስልቱ በተለይ በዚያን ዘመን የህዝቡን ድምፅ እንደ ከያኒነቱ በቅኔም ሆነ በመጋፈጥ የተንጋደደ ስረዓትን ሲተች ማህበረሰብን ሲያነቃ እንደነበር ከዘፈኖቹ መረዳት እንችላለን።

ለየት ባለ ቱባ የሆነውን ባህል ሳይበረዝ ሳይሸራረፍ ከዳር እስከ ዳር የኢትዮጲያን አካባቢ ከምድር ጦር ጋር በመሆን የማይረሳ ጥበባዊ አሻራ አስቀምጦ ማለፉ ነው።

ለአብነትም ወደ ጎጃም አባይን ተሻግሮ

ግርማው ገቢ ነበር ዋ ጎጃም አዘነ
ዋ ጎጃም አዘነ

አገሬ ምን ነካው አዘነ ጎጃም
ቆላ ደጋ ዳሞት ፍኖት ሰላም
ሸማኔው አንበሳ አሰሪው ነብር
አሁን በምንጊዜው ቆረጡት ያን ድር
ወይ ሀገር ወይ ሀገር ወይ ሀገር ቢቸና
መላ አትለኝም ወይ ህመሜ ሲጠና
መፍተሉን ነው እንጂ አሳዩኝ ያልኩኝ
ነድፎ መጣሉማ እኔ መች ጠፋኝ
ሸማኔማ ብሆን እንዴት በአማረብኝ
በማጠንጠን ብቻ-------- ቀረብኝ
ሀገራችን ዳሞት ብር ነው ወንዛችን
ፍቅራችን ነው እንጂ አይመች ፀባችን

#
ወደ ወሎ በጃማ ደጎሎ ተሻግሮ
ነይ ደሞ ነይ ደሞ

ጨለማ ነው ያልሽው የታል ጨለማው
ደሴ ሙጋድ ሜዳ ይታየኛል ሰው
ከወልዲያ በላይ ስሙ ነው አብዬ
ቆቦ መግባቴ ነው አንቺን ተከትዬ

ዳምጠው አየለ ሸዋ አካባቢ በመወለዱ ያደገበትን ባህል ወግ ስረዓት በደንብ አስተዋውቋል።
ያመራኛ ነው ወይ ጉብል ጠንበለሌን አንረሳውም !
በደንጎሬ ማርያም በጉስቋማ እናቴ
አውጭኝ ከዳገቱ አልቻለም ጉልበቴ

ፈጣሪ በኮላሽ በአስወደደሽ ላይ
ደብር ግል ብትገቢ ግፍ አይሆንም ወይ !

ከሸዋ ምንጃር ተነስቶ ቡልጋን አንኮበር ተጉለትን መንዝን ከማማ እስከ ግሼ ራቤል ቃኝቶታል።ጅሩ አንጎለላ ጠራን ደራ እንሳሮ ማጀቴ ይፋትን ዳሶታል።
የምንጃር ልጅ ናት የቡልጋ
መቼም ሳላያት አይነጋ
የቀያ ልጅ ናት የግሸ
ማነው ከእርሷ ጋር ያመሸ
አገሯ ይፋት
ማንስ ሊደፍራት
ምኑን ይዤ እገባለሁ መንዝ
በእሷ ጉዳይ ጦር ሳልማዘዝ

ደሞ ለመንዝ ሰው ደሞ ለቡልጋ ሰው እኮ ለተጉለት
ምን ብለው ሊያሙት ነው ስም ሊያወጡለት !

ጎንደር ደንቢያ አርባያ በላሳ አላፋ ጣቁሳም ተሻግሮ እንዲህ ተቃኝቷል።
#
እደገቷ ነበር ጎንደር
እስራኤል ገብታ ባትቀር
ወገራ በላሳ መተማ ደባርቅ
ትዝታዋ ጠራኝ ከአይኔ ስትርቅ

ኧረ ገዳምዬ ኧረ ገዳሜዋ

አምላክ በጥበቡ የሰራት ቀድሞ
ምን ይወጣላታል ለጎንደር ልጅ ደግሞ

ማሞ ደብረታቦር ወገራ ጋይንት
ቀረች እንደወዛ የኔ መድሃኒት

ድምፃዊ ዳምጠው አየለ ስለ ምድር ጦር ትዝታው ወንድሞቹን እህቶቹን የጦረኞች ትዝታውን እንዲህ አስቀምጦት አልፏል።
ከማስልጠኛ እስከ መልከዓምድሩ በራሱ ግጥምና ዜማ _

ሂድ በለው ሂድ በለው ኮረኩረው ፈረሱን
*
አካሂዱን አይተው የፊት ኋላውን
አሁን ማን አወቀው የመጨረሻውን
መስኖ ማሰልጠኛ እንዴት ነው አጋርፋ
ቀና ማለቱ አይቀር አንገቱን የደፋ

እንደ ምነው ጎጃም ብር ሸለቆ ዳሞት
የጨነቀ ጊዜ ያወጣል ከዳገት

ሀገሬ ላይ ሆኜ ናፈቀኝ ሀገሬ
እንዲህ ይረሳል ወይ የትናንቱ ዛሬ
ሀዋሳ ሲዳሞ ብላቴ ጦረን
ከንጉስ ጦና ሀገር እንዴት መላጣን
ነቀምት ተምሮ ሊያውም በደዴዴሳ
ያለቀለት ነገር አይቀር ሳይነሳ
አዋሽ አርባ ሆኖ ሲፎክር ሲያቅራራ
ትዝ አለኝ ያጎበዝ አፋር አሊቢራ
ያም እየተነሳ ሱሪ ሲታጠቅ
ምንይልክ በሸዋ ትዝ አለኝ ታጠቅ !

እያለ ብሶቱን ትውስታውን በግሪም ዜማና ግጥም ሙዚቃዊ ውህደት ፈጥሮ አስቀምጦልናል።
እያለ ቃኝቶታል።ከእነ ገመልከ-ዓምድሩ ከእነ ባህል ወግ ስረዓቱ የማይረሳ የጥበብ አሻራውን አስቀምጦልናል።

በመከፋት በመገፋት በብስጭት በስደት ሀገሩን ቤተሰቡን ትቶ ወደ ኖርወይ ሄዶ ህይወቱ እስከ አለፈችበት ሰኔ 27/2006 ዓ/ም ድረስ እንዲሁ በናፍቆት እንደባባ በዚች አለም ለመኖር የተፈቀደለትን ጊዜ ጨርሶ ላይመለስ ሄዷል።

ድምፃዊ ዳምጠው አየለ የሰራውን ያበረከተውን ያክል ያልተወሳ ያልተነገረለት እንቁ የባህል ድምፃዊ ነበር።
በተለይ የአካባቢው ተወላጆች የሙያ አጋሮቹ ስራዎቹን ማስታወስ ልጆቹን መጠየቅ መደገፍ እንዳለባችሁ ይሰማኛል።

ዳምጠው ቆፍጣናና ለክብሩ ለሙያው ለሀገሩ የሚጨነቅ ጀግና እንደነበር ይታወቃል።
ወዳጆቼ ስለ ድምፃዊ ዳምጠው አየለ እናንተም የምታውቁትን አካፍሉን።
ድምፃዊ #ዳምጠውአየለ /ነፍስህ በሰላም ትረፍ 💐🥀

#አቤል ወርቁ ዘ-ኮተቤ

17/05/2024

ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ስለፍትሕ መጓደል፣ አላግባብ ስለሚገደሉ ንፁሃን እና ስለ ሰው ልጆች መብት ካለፍርሃት በግልፅ የሚናገሩ ሊቀጳጳስ ናቸው። የብልፅግናው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ እኚህ አዛውንት ላይ በካንጋሮ ፍርድ ቤቱ በኩል ክስ ከፍቶባቸዋል። ... ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ስለ ሁሉም ጉዳይ መልስ አላቸው ያድምጧቸው ።

የአማራ ባንክ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ባለሙያ የነበረው አቶ ኢሳያስ በላይ ከ8 ቀን በፊት በመንግሥት የፀጥታ አባላት ተይዞ ከተወሰደ በኋላ የነበረበት ቦታ አይታወቅም ነበር።  በዛሬው...
17/05/2024

የአማራ ባንክ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ባለሙያ የነበረው አቶ ኢሳያስ በላይ ከ8 ቀን በፊት በመንግሥት የፀጥታ አባላት ተይዞ ከተወሰደ በኋላ የነበረበት ቦታ አይታወቅም ነበር። በዛሬው እለት ፖሊስ ለቤተሰቦቹ በመደውል አስከሬን ውሰዱ ብሏቸዋል። ይሄ የአማራ ህዝብ በጨካኝ መዳፎች ስር ስለመውደቁ ተጨማሪ ማስረጃ ነው።

የአማራ ባንክ በሰራተኛው ሞት አዝኖ ለቤተሰቦቹ መፅናናትን ከመመኘት በስተቀር በመንግሥት የጸጥታ አካላት ተይዞ እንደነበር ወይም ስለ አሟሟቱ ያለው ነገር የለም። አቶ ኢሳያስ አማራ ባንክን ከመቀላቀሉ በፊት የ INSA ሰራተኛ እንደነበና እና በተደጋጋሚ ይታሰር እንደነበር ታውቋል። INSA ውስጥ የሳይበር ደህንነት ክፍል ይሰራ ነበር።

ለእስሩ ምክንያት ተደርጎ ይቀርብ የነበረው ምክንያት ደግሞ "የአማራን ወጣቶች ታደራጃለህ፣ ከፋኖ ጋር ግንኙነት አለህ" የሚል ሲሆን በዚህ ምክንያት በተደጋጋሚ ከደመወዝ እና ከስራም ሲታገድ ነበር። ይሁንና አቶ ኢሳያስ በተጠረጠረበት እና ለእስር ይዳረገበት በነበረው ጉዳይ መረጃ ሊገኝ ባለመቻሉ ክስ ሳይመሰረት መለቀቁን እና በመጨረሻም በሚደርስበት ጫና ተቋሙን ለቅቆ በመውጣት አማራ ባንክ ተቀጥሮ ይሰራ ነበር።

ሟች ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት እንደነበረ ተገልጿል። የሟች አቶ ኢሳያስ የቀድሞ የስራ ባልደረባ የነበሩ 15 የ INSA ሰራተኞች እንዲሁ ከስራ ቦታቸው እና ከመኖሪያ ቤተቸው በብሔራቸው ምክንያት ታፍነው መወሰዳቸውን እና ያሉበት ቦታ እና ሁኔታ እንደማይታወቅ መረጃዎች ያሳያሉ። እነዚህ የታፈኑ 15 የINSA ሰዎች በህወሓት ጦርነት ወቅት ከመንግሥት ጎን ተሰልፈው መዋጋታቸው የተገለፀ ሲሆን አሁን ግን ከፋኖ ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ታፍነው አድራሻቸው እንዲጠፋ ሆኗል።

እንዲህ ልጆችን ያላባት፣ አረጋዊያንን ያለ ጧሪ፣ ሚስትን ያለባል የሚያስቀሩ ጨካኝ የብልጽግና ግና ስዎች በየመንገዱ ሊስሮ ጋር ፎቶ በመነሳት "ሰብአዊ" ለመሆን ሲሞክሩ ይታያሉ። አልፎ አልፎም እኛ "ኢየሱስ ነን" ለማለት የሚዳዳቸው በግብራቸው ግን ሰይጣን ከነሱ ስር ቁጭ ብሎ ትምህርት የሚቀስማባቸው የክፋ- ነገሮች ትምህርት ቤት ናቸው።

የሸዋ አማራ ወብ ባህል  😘 አማራነት ይለምልም
07/05/2024

የሸዋ አማራ ወብ ባህል 😘 አማራነት ይለምልም

   #አማራዬ  -------ሸዋ ረገድ ገድሌየምታስፎክር ሰንጋ ገለሌበጦር መካከል ሳይሆኑ አያሌበጥይት ገዳይ ነጭ ብርገድሌየሴት ወንድ ናት ሸዋረገድ ገድሌተብሎ የተገጠመላቸውን፣ በአምስት ዓመቱ...
29/04/2024

#አማራዬ

-------ሸዋ ረገድ ገድሌ

የምታስፎክር ሰንጋ ገለሌ
በጦር መካከል ሳይሆኑ አያሌ
በጥይት ገዳይ ነጭ ብርገድሌ
የሴት ወንድ ናት ሸዋረገድ ገድሌ

ተብሎ የተገጠመላቸውን፣ በአምስት ዓመቱ የጠላት ወረራ ጊዜም አኩሪ ጀብዱ የፈጸሙትን የአርበኛዋን የሸዋረገድ ገድሌን ታሪክ የሚተርክ መጽሐፍ ሰሞኑን ቀርቧል፡፡ ‹ሸዋ ረገድ ገድሌ፣ የአኩሪ ገድላት ባለቤት› ይሰኛል፡፡ ሺበሺ ለማ ጽፎት ዶክተር ክፍሌ ማርቆስ ገድሌ አሳትመውታል፡፡

በአምስት ዓመቱ የፋሽስት ወረራ ጊዜ ለሀገራቸው አኩሪ ገድል በመፈጸምና ለነጻነታችን ዋጋ በመክፈል ስማቸው ከሚነሡ ሴቶች ሸዋረገድ ገድሌ ግንባር ቀደም ናቸው፡፡ በ1878 ዓም የተወለዱት ወ/ሮ ሸዋ ረገድ ገድሌ ሁለገብ እንደነበሩ ታሪካቸው ያሳያል፡፡ የቤተ ክህነቱን ትምህርት ተምረዋል፡፡ ትዳርን አልፈልግም ብለው ምናኔን መርጠው ኢየሩሳሌም ድረስ ተጉዘዋል፡፡ ከመጀመሪያዎቹ የባንክ ተጠቃሚዎች፣ የአክሲዮን ገዥዎች፣ የፋብሪካ ተካዮች መካከል አንዷ ነበሩ፡፡ የጉለሌ ቅዱስ ገብርኤልንም ያስተከሉት እርሳቸው ነበሩ፡፡

የሸዋረገድን ስም ይበልጥ ከፍ አድርጎ ያስጠራው አርበኛነታቸው ነው፡፡ የኢጣልያ ጦር ሊጎርሰን ማሰፍሰፉ ሲሰማ በአዲስ አበባ ከተማ በሀገር ተቆርቋሪ ዜጎች በተቋቋመው የሀገር ፍቅር ማኅበር አባልነት መጀመሪያ ከተመዘገቡት ጥቂት ሴቶች መካከል አንዷ እርሳቸው ነበሩ፡፡ ወራሪው ፋሽስት አዲስ አበባ ሲገባና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የኢጣልያ ባንዴራ ሲተካ ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ፡፡ በዚህ ምክያትም በኋላ ‹የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የገናናው የኢጣልያ ሰንደቅ ዓላማ ሲውለበለብ በማየትሽ አልቅሰሻል›› በሚል ተከሰው ነበር፡፡ ሸዋረገድም ያለምንም ፍርሃት ‹አዎ አልቅሻለሁ፤ ያገሬን መወረርና መዋረድ ያወቅሁት የኛ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የናንተ ሲውለበለብ በመታየቱ ነው፡፡ ሰው ለእናት ሀገሩ ቢያለቅስ ነውሩ የት ላይ ነው?›› ብለው ነበር የመለሱት፡፡

ወ/ሮ ሸዋረገድ ለአርበኞች ስንቅ በማቀበል፣ መሣሪያ በመግዛት፣ መረጃ በማሰባሰብ፣ መድኃኒት በመላክና ሞራል በመስጠት አምስቱን ዓመት በተጋድሎ ነው ያሳለፉት፡፡ በዚህ ምክንያት በተከሰሱ ጊዜም ‹‹ለአርበኞች ስንቅ ማቀበሌ እውነት ነው፤ይህንንም ያደረግኩት ለሀገሬ ክብር ብዬ ነው፡፡ ሰው እንኳን ለሀገሩ የእናንተ ወይዛዝርት ሀገራቸው ያልሆነቺው ኢትዮጵያን ለመውረር የጣታቸውን ቀለበት ሳይቀር መስጠታቸውን ትናገራላችሁ፡፡ እኔም ለሀገሬ የሠራሁት ሲያንሰኝ እንጂ አይበዛብኝም›› ነበር ያሉት፡፡

ወ/ሮ ሸዋረገድ ከሚጠቀሱላቸው ሥራዎቻቸው አንዱ ለቀይ መስቀል ማኅበር የነበራቸው ድጋፍ ነው፡፡ በጦርነቱ ዋዜማ ሐምሌ 1 ቀን 1927 ዓም ለተቋቋመው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ንብረታቸውን ሸጠው አስረክበዋል፡፡ እሥር ቤት በገቡ ጊዜ ከተከሰሱበት ወንጀል አንዱም ‹ቀይ መስቀልን ትረጃለሺ› የሚል ነበር፡፡ ሸዋረገድ ቀይ መስቀልን ከመርዳትም ባሻገር ኢትዮጵያውያን ወይዛዝርት እራፊ ጨርቅ እንዲያሰባስቡ በማድረግ ለአርበኞች ቁስል ማሸጊያ ይልኩላቸው ነበር፡፡

ሸዋረገድ ከርዳታው ጎን ለጎን ለአርበኞቹ የመረጃ ምንጭም ነበሩ፡፡ በከተማው የሚገኙ የጠላት መረጃዎችን በማሰባሰብና ወደ አርበኞች በምሥጢር በመላክ አርበኞች እንዲጠቀሙባቸው አድርገዋል፡፡ በዚህና በሌሎች ገድሎቻቸው ምክንያትም የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ነበር፡፡ በፈጣሪ ቸርነት ግን ሳይፈጸምባቸው ቀርቷል፡፡ የሞት ፍርዱ ባይፈጸምባቸውም የኢጣልያን እሥር ቤት ከሚያዘወትሩት አንዱ ሸዋረገድ ሆነዋል፡፡ በየጊዜው ይታሠራሉ፤ ይፈታሉ፡፡ በመጨረሻ ግን አዚናራ ወደምትባል ከሰርዲኒያ ሰሜናዊ ምዕራብ ወደምትገኝ ደሴት ታሥረው ተልከዋል፡፡

እዚያም ቢሆን ጽናታቸው አልተሰበረም፤ ወኔያቸውም አልተሰለበም፡፡ የሚያደርጉት ቢያጡ በእሥር ቤት የሚቀርብላቸውን የተበላሸ ምግብ በአሣሪዎቻቸው ፊት በመድፋትና ጦማቸውን በመዋል ፋሽስትን ይቃወሙ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታም ለአንድ ዓመት ከመንፈቅ ታሥረው ተፈቱ፡፡ አዲስ አበባ ሲገቡ ግን ትግላቸውን ቀጠሉ እንጂ አላቆሙም፡፡ ሕዝቡም
የዘበኛ ሱሪ ካኪና ገምባሌ
እንኳን ደኅና መጣሺ ሸዋረገድ ገድሌ
ብሎ ተቀበላቸው፡፡

በተለይም በጅቡቲ የነበረ አንድ ኢትዮጵያዊ የሰጣቸውን ‹የይሁዳ አንበሳ› የሚል ጽሑፍና ዓርማ ያለበትን ወረቀት ከንጉሡ የተላከ የሚመስል መልእክት እየጻፉ ወደ በረሐ በመላክ አርበኞችን አበረታተውበታል፡፡ የአዲስ ዓለም የጣልያን ምሽግ ኅዳር 5 ቀን 1933 ዓም በአርበኞች ሲሰበር ዋናውን መረጃ የሰበሰቡትና ዐቅድ የነደፉት ሸዋረገድ ነበሩ፡፡ ከምሽጉ ሰበራ በኋላም ደጀን መሆኑን ትተው ራሳቸው ወደ ውጊያ ዐውድማ ገቡ፡፡ በተለይም መቂ አካባቢ ከሻለቃ በቀለ ወያ ጦር መካከል ተሰልፈው ተዋግተዋል፡፡ በኋላም ጅማ አካባቢ ከነበረው ከገረሱ ዱኪ ጦር ጋር ለመገናኘት ተጓዙ፡፡ በዚያ እያሉም ጠላት ድንገተኛ አደጋ ጥሎ ገጠማቸው፡፡ ለአራት ሰዓት ያህልም ተዋግተው ተማረኩ፡፡ ወደ እሥር ቤት ተወስደውም የፊጥኝ ታሠሩ፡፡

በ1933 ዓም ሀገሪቱ ከፋሽስት ኢጣልያ ወረራ ነጻ ስትወጣ ሸዋረገድ ገድሌ አርበኞችን ወደመርዳትና የበጎ አድራጎት ሥራን ወደ መሥራት ገቡ፡፡ በንግዱም መስክ ተራመዱ፡፡ ሀገራቸውን እስኪበቃቸው አገልግለው፤ ግሼን ማርያም ሄደው ሥጋወደሙን ተቀብለው፤ ከዚያም ወደ ላሊበላ ተጉዘውና ተሳልመው፤ የመጨረሻቸው መሆኑን እየተናገሩ ጥቅምት 22 ቀን 1942 ዓም ዐረፉ፡፡ ሕዝቡም

እናንት ወጥ ቤቶች በርበሬ ቀንጥሱ
እናንት ሥጋ ቤቶች ሰንጋውን ምረጡ
ሸዋረገድ ገድሌ ለገና ሲመጡ፡፡
ቤተሰቧ ሰፊ ገናና ጥምቀት
ሸዋረገድ ገድሌ እንደምን ትሙት፡፡ ብሎ ገጠመላቸው፡፡

ሰፊ ነው ታሪካቸው፡፡ ልብ የሚያሞቅ፤ ወኔ ቀስቃሽ፤ አስደማሚ፤ ከዐለት የበረታ ጽናት፤ ከእቶን የጋለ አርበኝነት፤ ከትንታግ የተንቀለቀለ የሀገር ፍቅር ታገኙበታላችሁ፡፡ ምናለ አደባባዮቻችን በንግድ ኩባንያዎች ስም ከሚጠሩ በነ ሸዋረገድ ገድሌ ስም ቢሰየሙ ብላችሁም ትቆጫላችሁ፡፡

 #ወታደራዊ ልምምድ፣ ሰልፍና ሙዚቃ ሸዋ አማራ አዲስ አበባ - 1926 ዓ.ምAmhara History, Culture and Tourism
19/04/2024

#ወታደራዊ ልምምድ፣ ሰልፍና ሙዚቃ ሸዋ አማራ አዲስ አበባ - 1926 ዓ.ም

Amhara History, Culture and Tourism

15/06/2022
ነፍሱን በቅዱሳኑ ጎን ያሳርፍ!!
12/06/2022

ነፍሱን በቅዱሳኑ ጎን ያሳርፍ!!

12/06/2022
12/06/2022

Historical photo:- Contemporary portrait of Emperor Lebna Dengel (ልብነ ድንግል) of Ethiopia from 1508–1540 by Cristofano del...
05/06/2022

Historical photo:- Contemporary portrait of Emperor Lebna Dengel (ልብነ ድንግል) of Ethiopia from 1508–1540 by Cristofano dell'Altissimo at the Uffizi Museum in Florence , Italy, 1532.
( Emperor Lebna Dengel or Dawit II, also known as Wanag Segad. He was the son of Emperor Na'od and Queen Na'od Mogasa )

02/06/2022
02/06/2022


Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abyssinia Geʽez Amhara Voice AGAV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share