Durame times

Durame times We stand together

06/12/2022

Go go Morocco.🇲🇦

05/11/2022

የውልደሃኔ- ዱርጊ - ዱራሜ መንገድ የተጫራች ልየታ በኢትዮዽያ መንገዶች አስተዳደር ቦርድ ይሁንታ አግኝቶ ወደ ሥራ እንዲገባ መፈቀዱ ተገለፀ።

ጥቅምት 25/2015 (የዳውሮ ዞን የመን/ኮ/ጉ/መምሪያ)

የዳውሮ እና የካምባታ ህዝቦች ለዓመታት ሲጠይቁ የቆየው የውልደሃኔ- ዱርጊ - ዱራሜ መንገድ የተጫራች ልየታ በኢትዮዽያ መንገዶች አስተዳደር ቦርድ ይሁንታ አግኝቶ ወደ ስራ እንዲገባ መፈቀዱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት የውልደሃኔ- ዱርጊ - ዱራሜ መንገድ የተጫራች ልየታ በኢትዮዽያ መንገዶች አስተዳደር ቦርድ ይሁንታ አግኝቶ ወደ ሥራ እንዲገባ መፈቀዱን ገልጸዋል ::

ይህም ክቡር ጠ/ሚኒስትራችን ለሁለቱ ዞኖች ህዝቦች የገቡት ቃል እነሆ በተግባር እየታዬ ነው ብለዋል ::

ሁለቱንም ዞኖች ህዝቦችን እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እወዳለሁ ሲሉም ተናግረዋል :: ዘመኑ የሠላምና የልማት ነውም ብለዋል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ።

ለሀገር ክብር በጋራ እናብር!

03/11/2022

ሰበር ዜና

የህወሓትና የመንግስት ስምምነት የሚከተሉት ናቸው።

1. ህወሓት ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱን፦ በስምምነቱ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንደሚፈታ፤ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በ24 ሰዓት ውስጥ አመቺ ቦታ መርጠው ንግግር ያደርጋሉ፤

2. ስምምነቱ በተፈረመ አምስት ቀናት ውስጥ የሁለቱ ወገን ወታደራዊ አመራሮች የትጥቅ ማስፈታት ሂደቱ የሚመራበትን ዝርዝር አፈጻጻም በጋራ በማውጣት ተግባራዊ ሥራዎችን መሥራት ይጀምራሉ፤

3. የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በተገናኙ አስር ቀናት ውስጥ ህወሓት ያሉትን ሁሉንም የቡድን እና ከባድ መሣሪያዎች ለመከላከያ ሠራዊት ያስረክባል፤

4. ስምምነቱ በተፈረመ ሰባት ቀናት ውስጥ የፌደራል መንግሥት መቀሌን ተረክቦ በከተማው ውስጥ እና ዙሪያ ሁሉንም አይነት የጦር መሣሪያ ያስፈታል፤

5. በአጭር ቀናት ውስጥ አሁን ያለው የህወሓት መዋቅር ፈርሶ የፌደራል መንግሥት የሚመራው የጊዜያዊ አስተዳደር ይቋቋማል። በሚዋቀረው ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥም የትግራይን ሕዝብ የሚወክል አካል ይሳተፋል፤

6. የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከጎረቤት ሀገራት የሚያዋስኑ የድንበር አካባቢዎችን ደኅንነትና ሰላም የሚያረጋግጥ ስምሪት የሚያደርግ ይሆናል። መከላከያ ሠራዊቱ በማንኛውም የትግራይ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ ሕግ የማስከበር ስልጣኑን ከህወሓት ሙሉ በሙሉ ይቀበላል። ህወሓት ለተግበራዊነቱ ምንም አይነት እንቅፋት እንደማይፈጥር ተስማምቷል።

7. የሚመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች የማኅበራዊ አገልግሎቶች በፍጥነት እንዲጀመሩ ሁኔታዎች ያመቻቻል፤ ተግባራዊነታቸውን ያረጋግጣል፤

8. ህወሓት ያለ ፌደራል መንግሥት እውቅና ከማንኛውም የውጭ አካል ጋር ግንኙነት ማድረግ ያቆማል። እንዲህ አይነት ተግባር የሚፈጹ ግለሰቦች ካሉ በሀገሪቱ ሕግ የሚጠየቁ ይሆናል።

ኢትዮዽያ አሸንፋለች

26/10/2022

ተዋቅው የGIS በለሙያ ወንድማችን ደገሎ ሰንዳቦ ከዝህ ዓለም በሞት ተለዩ ።

በ Addis Ababa University, School of Earth Sciences :Director, Remote Sensing and GIS Directorate,Lecturer of Remote Sensing, GIS, Mapping and Photogrammetry

በ Ethiopian Mapping Agency
Director, Remote Sensing and GGIS Directorate

Dec 2011 - Present 10 years
His Major tasks,

👉GIS activities planning,
👉Digital Image Processing of Remotely Sensed data of different satellite systems,
👉Land use land cover planning and interpretation, spatial analysis, urban planning,
👉training on GIS and remote sensing,
👉 watershed management area analysis and interpretation, spatial distribution of features analysis,
👉environmental modelling, change detection, land administration and cadaster mapping,
👉Atlas preparation, eco-tourism maps preparation, cartographic designing and layout preparation, geo0database development, any geo-information related activities and etc

ሲሆኑ የኢትዮጵያ ካርታ ድርጅት ከፍተኛ በለሙያ ሆነው የሙያ ግዴታቸውን ተወጥተዋል ። በአከባቢያችን ጉዳዮች ይሳተፉ ነበር ።

https://www.facebook.com/100076112173869/posts/197323446148060/?flite=scwspnss&mibextid=EIh8GqnfXx6Qcdns
15/10/2022

https://www.facebook.com/100076112173869/posts/197323446148060/?flite=scwspnss&mibextid=EIh8GqnfXx6Qcdns

ጋዜጠኛ - "በአንተ የጨዋታ ዘመን ከነበሩ የፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች ከየትኛው ቡድን ጋር መጫወት ይበልጥ ያስደስትህ ነበር? ከማን ሲቲ? አርሴናል? ወይስ ቼልሲ?"

ኤቭራ - "ከሁሉም ጋር መጫወት ያስደስተኛል። ግን አንድ ነገር ልንገርሽ፣ ከሁሉም ጋር ስጫወት እያንዳንዱን ግጥሚያ የምረዳበትን የራሴን ፍልስፍና ወይም የግል እይታ ነው የምነግርሽ። ከአርሴናሎች ጋር ስንጫወት ከህፃናት ጋር እንደምንጫወት ነው የማስበው፣ ከማን ሲቲ ጋር ስንጫወት ከጩህታም ጎረቤቶቻችን ጋር እንደምንጫወት ነው የማስበው፣ ከሊቨርፑል ጋር ስንጫወት ከጠላቶቻችን ጋር እንደምንጫወት ነው የማስበው፣ ከቼልሲ ጋር ስንጫወት የሊጉን ዋንጫ ለማሸነፍ እንደምንጫወት ነው የማስበው። ምክንያቱም በእኔ ግዜ የነበረው የቼልሲ ቡድን በጥንካሬው ከማን ዩናይትት ጋር በጣም ተቀራራቢ ነበር። ቼልሲዎች በተሰጥኦ ብቻ ሳይሆን በአእምሮም የበሰሉ ፣ ጠንካራ አካላዊና ስነልቦናዊ ማንነት ባላቸው ተጨዋቾች የተሞላ ስብስብ ነበራቸው። ድሮግባን፣ ማካሌሌን፣ ኢሲየን፣ ላምፓር፣ ቴሪ፣ ባላክ እና ሌሎችንም አስታውሳለሁ። እነዚህ ተጨዋቾች በሜዳ ውስጥ በጣም የሚደንቅ ጠንካራ ማንነት ነበራቸው። እነሱን ካሸነፍን የሊጉን ዋንጫ እንደምናሸንፍ እያሰብኩ የምጫወተው።

ጋዜጠኛ - "አርሴናሎችን ግን እንደ ህፃናት ናቸው ማለትህ ገርሞኛል"

ኤቭራ - "እም… ምን መሰለሽ… ለሄነሪ ክብር አለኝ፣ እሱ ጥሩ ወንድሜ ነው። ግን ሁልግዜ ከአርሴናሎች ጋር ስጫወት ለመጫወት የሚያነቃቃኝ ምክንያት አጣለሁ"

ጋዜጠኛ - "ለምን?"

ኤቭራ - "ምክንያቱም አንዳንድ የአርሴናል ተጨዋቾች … ካስፈለገ ስም መጥራት እችላለሁ… ገና ጨዋታው ሳይጠናቀቅ 35ኛው ደቂቃ ላይ ወደ እኔ መጥተው "ሄይ ኤቭራ እባክህ በኋላ ማሊያህን ልትቀይረኝ ትችላለህ?" ይሉኛል። ልክ እንዲህ እንዳሉኝ የመጫወት ሀሞቴ ይፈሳል"
………………………………………………………………………………

💙👇🏿 👇🏿 👇🏿

https://t.me/beakal_chelsea

08/09/2022
25/08/2022
22/08/2022
ክለስቴር ለእርሸ ነው።   No more cluster KRS
15/08/2022

ክለስቴር ለእርሸ ነው። No more cluster KRS

14/08/2022

ከፍታ ያለ ነውጥ፤ ያለ ሽግግርና ያለ ትግል አይመጣም። እንዳንድ ሰዎች "የከፍታ ዘመን ለኢትዮጵያ" ሲባል የሚያስቡት "ከፍታውን" ብቻ እንጂ በዚያው መጽሐፍ የተጻፈውን "የምጥ" "የሽግግር" "የችግር" "የነውጥ" የሚለውን ትንቢት አያስተውሉም። የሆነ ችግር ምድሪቱ ላይ ሲከሰት "የከፍታው ዘመን" አላሉምን? ይሉኛል። ሰዎቹ ከመጽሐፉ ያነበቡት ወይም የሚፈልጉት ከፍታውን "ብቻ" ስለሆነ ነው እንጂ በመጽሐፉ ውስጥ እግዚአብሔር ያልተናገረው በኢትዮጵያ ምድር የሆነ አንዳችም ነገር የለም። እውነታው በወረቀት የተጻፈ በአካል ሲገለጥ ያስደነግጣል ምክንያቱም የእግዚአብሔር አሰራር እኛ በጠበቅነው መንገድ ስላይደለ። ኢትዮጵያ ሆይ የምጡ፣ የችግር፣ የነውጡና የሽግግሩ ዘመን አብቆቶ ጉዞ ወደ ከፍታ ጀምረናል። ወሬን ትተን ስራ ላይ እናተኩር፣ ቤተክርስቲያን ሆይ መመቻቸትን ትተን ወንጌል እንስብክ፤ እነሆ በሁሉ አቅጣጫ የመስራት ዘመን ነው። የከፍታው ዘመን ተጀምሯልና። በአገሪቱም ላይ የምናየው መልካም ጀማሬ ሁሉ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያሰበውና የተናገረው ትንቢት አካል መሆኑን እናስተውል። ቤተክርስቲያን ሆነ ተነሺ፣ ኢትዮጵያ ሆይ ተነሺ።

“ብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፥ አብሪ።”
— ኢሳይያስ 60፥1

" የፊተኛውን ነገር አታስተውሉ፥ የጥንቱንም ነገር አታስቡ። እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፥ እናንተም አታውቁትምን? በምድረ በዳም መንገድን በበረሀም ወንዞችን አደርጋለሁ።"
ኢሳይያስ 43:18-19

ቄስ በሊና ሳርካ

(በድጋሚ የተለጠፈ)

07/08/2022

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ ይሰጣል
****************************

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የአገልግሎቱ መረጃ እንደሚያመለክተው ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/

06/08/2022
01/08/2022
31/07/2022

Breaking News ‼️
🇪🇹 Ethiopia just completed the 3rd round filling of the GERD. Congratulations Ethiopia 🇪🇹 👏🏽

31/07/2022
31/07/2022

ማንም ተንጫጫ ማንም ተመቀኘ አባይ እንደ ኑክሌያር ቦንብ አስፈሪ ሆኗል።

እድለኛው ግድብ፣
…………………………………………………………………
« የአልጀዚራ ጋዜጠኛ »

ተፈጥሮ ተገዳ ሳይሆን አገሪቱ አስገድዳ እድለኛ አድርገዋለች። ወታደርም መሳሪያም ዘበኛም አያስፈልገውም ። ማንም የምድራችን ሀይለኛ ነኝ የሚል መሳሪያ አይነካውም።

ምናልባት አንድ አውቶሚክ ሊዳፈረው ይችላል

ለሱ የተላከው ቦንቡ አንድ ግድብ ብቻ ነው የሚነካው። ጥቃት የተሰነዘረበት ግድብ ግን ለጥቃቱ የሚሰጠው መልስ ከ40 ሚሊዮን በላይ ዜጎችንና የሁለት አገር ትልልቅ ከተሞችን ማለትም የሱዳንን ዋና ከተማ ካርቱምን ፣ የግብፅን ዋና ከተማ ካይሮን ያለምንም ከልካይ፣ አፍረሶ ወደ አፈር ቀይሮ ከውሀ ጋር ቀላቅሎ ነጭ ባህር ይጨምራል

ማንኛው የአለማችን መሳሪያ ነው ከኢትዮጵያ እስከ ነጭ ባህር ድረስ ከተሞችንና የመሰረተ ልማቶችን ህዝቦችን እየጠራረገ ነጭ ባህር የሚዶለው .? እስካሁን ድረስ ይህ መሳሪያ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ጉባ ተራራ ሸለቆ ላይ የተጠመደ፣ አንድ አፍሪካዊ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ፣ መሳሪያም ወታደርም ዘበኛም የማያስፈልግ እድለኛው የአባይ ግድብ ብቻ ነው። አዎ አንተ እድለኛ ነህ
በአለማችን ላይ ከህፃናት እስከ አዋቂዎች ስምህን የሚያውቁት ! ራስን በራስህ ያስከበርክ!!

CcDaily News Egypt
ሱልጣን አህመድ

31/07/2022
31/07/2022

ኢ ት ዮ ጵ ያ ዬ እንኳን ደስ አለሽ!

የአባይ ግድብ ሶስተኛው ሙሌት የግድቡን ከፍታ አልፎ ውሀው መፍሰስ ጀምሯል። ሶስተኛው ሙሌታችን በስኬት ተጠናቋል።

( ምስል ግድቡ የባለፉት ወራት ግንባታ ላይ )

28/07/2022
27/07/2022

የ2015 በጀት ዓመት በጀት ድልድልን አስመልክቶ ከደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የተሰጠ ማብራሪያ

ሐምሌ 20/2014 ዓ.ም ሀዋሳ

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት ያፀደቀውን የ2015 በጀት ዓመት በጀት አዋጅ በቢሯችን ድረ ገጽና ፌስ ቡክ አካውንት የተጠቃለለ መረጃ ይፋ ማድረጋችን ይታወሳል፡፡ ሆኖም መረጃው ከተለቀቀ በኋላ የተለያዩ የማብራሪያ ጥያቄዎችና የበጀት ድልድሉ በተወሰኑ አስተዳደራዊ መዋቅሮች ላይ ኢፍትሐዊ እንደሆነ ተደርጎ የተሰጡ አስተያየቶች እንደተሰነዘሩ አስተውለናል፡፡

በጀቱ የተደለደለው በፌዴሬሽን ምክር ቤት ፀድቆ ከ2010 በጀት ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ በተደረገው ቀመር ሲሆን በክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ በኩል ተዘጋጅቶ ለዞንና ልዩ ወረዳዎች አመራሮች ቀርቦ ውይይት ተደርጎና ሥልጠና ተሰጥቶ በፀደቀ የቀመር መረጃ መሠረት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ከፌዴራል መንግሥት ለክልሉ የተሰጠ የድጎማ በጀት ብቻ በቀመሩ አከፋፍሎ በክልሉ ምክር ቤት ያስፀድቃል፡፡ በዚህ ክፍፍል ውስጥ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የሚሰበስቡት የገቢ ዕቅድ አይካተትም፡፡ ገቢውን የሚሰበስበው አካል ሰብስቦ የሚጠቀመው የገቢ በጀት ማለት ነው፡፡ (ይህ ማለት ከፌዴራል መንግሥት የሚገኘው የበጀት ድጎማ በቀመር ሲከፋፈል፣ ገቢውን ከፍ አድርጎ የሰበሰበ አስተዳደራዊ መዋቅር የተሻለ የበጀት መጠን የሚያገኝ ሲሆን ከፍና ዝቅታው የመጣውም ከገቢ መጠን መበላለጥ ጋር በተያያዘ ነው)፡፡

የ2015 በጀት ዓመት በጀት ድልድል ካለፉት ዓመታት ጋር እንዲሁም መዋቅር ከመዋቅር ጋር ያገኘውን ልዩነት ማነጻጸር በመሠረታዊነት ስህተት ላይ የሚጥል ከመሆኑም በላይ ድምዳሜውም አሳሳች ስለሚሆን አጠቃላይ መረጃውን ማገናዘቡ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ከዚህ አኳያ ክልል ማዕከልም ሆነ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ራሳቸውን እንዲችሉ ባደረገው ጥረት የክልሉ መደበኛ ገቢ ካለፈው ዓመት የ48 በመቶ ዕድገት ያሳየ ሲሆን መደበኛ ባልሆኑ ገቢዎችም በተመሳሳይ ዕድገት ተመዝግቦባቸዋል፡፡ ስለዚህ በየአስተዳደራዊ መዋቅሩ የታየው ከፍና ዝቅታ ከዚሁ አንፃር መሆኑ ታሳቢ ቢደረግ መልካም ነው፡፡ የታየው የገቢ ዕድገት ከየበጀቱ ያለውን ድርሻ ለመረዳት ከዚህ ጋር ተያይዞ የቀረበውን ሠንጠረዥ ይመልከቱ፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት:-
www.snnprsbof.gov.et/
https://t.me/SNNPRSfinancebureau

26/07/2022

የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ መንግስት የ2015 በጀት ይህን ይመስላል።

23/07/2022

ሰበር ዜና
*******
የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና ብቃትና ጥራት ያላቸውን መምህራን ለማፍራት የሚያስችሉ ደረጃቸውን የጠበቁ አረት የመምህራን ኮሌጆችን(TTC) በ2015 በጀት ዓመት በክልሉ በሚገኙ አረት ዞኖች እንደሚያስገነባ ሰሞኑን በተካሄደው የክልሉ ምክር ቤት ይፋ መደረጉ ይበል የሚያሰኝ መልካም ተግባር በመሆኑ የሚመለከተው አካል በፍጥነት ወደ ተግባር ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።
ኮሌጆቹ የሚገነቡባቸው ዞኖች
1ኛ ከምባታ ጠምባሮ ዞን... ዱራሜ
2ኛ ወላይታ ዞን... ሶዶ
3ኛ ጉራጌ ዞን... ወልቅጤ
4ኛ ጎፋ ዞን.... ሰውላ ናቸው። የክልሉን መንግስት እናመሰግናለን። የሞዴል ትምህርት ቤቱም ጉዳይ እንድፈጥንልን ይደረግ።

Via zewudu alemu

21/07/2022

" ‼️". . .
---------¶¶🔸🔴🔶🛐🔷🔵🔹¶¶------------
ነገሮች በፍጥነት እንዲሳኩልህ አትፈልግ! መዘግየትህን አትጥላው! በትምህርት፣ በሥራ፣ በሀብት፣ በአገልግሎት፣ በፍቅር ግንኙነት ወይ በትዳር አንተ እንዳሰብከው አለመሆኑ ለበጎ እንደሆነ አስብ።

:
1፤ በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፤ የሚናገረኝንም፥ ስለ ክርክሬም የምመልሰውን አውቅ ዘንድ እመለከታለሁ። . . . . 4፤ እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ።"

ወደ ኋላ የተንደረደረ ረጅም ርቀት እንደሚተኮስ አስብ፤ ወዳጄ ጥያቄህ ቶሎ ያልተመለሰው ጊዜው ስላልደረሰ ወይ ደግሞ ፈጣሪ የተሻለውን ሊሰጥህ ይሆናል። አንተ ብቻ ጥረትህን ሳታቋርጥ ታገስ፤ የሕይወትህ ፀሐይ መውጣቷ አይቀርም።

" ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ትወጣላችኋለች፥ #ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፤ እናንተም ትወጣላችሁ፥ ትፈነጫላችሁ። " (ሚልክ. 4:2)
_________________
[ወዳጆቼ የተባረከችሁ ሁኑ]

21/07/2022
21/07/2022
20/07/2022

⭐️ ደግም ወደ ከፍታው ዘመን 🌟

🇪🇹 ከምባታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት 🌍

ፎቶግራፍ credit ጡማ Media 🙏

16/07/2022

Address

Durame

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Durame times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Durame times:

Share