Wolaita Times

Wolaita Times This is the official WT Media - Where you can get all the latest news. Stay Connected👐

Wolaita Times Media is an Ethiopian digital media platform; have been designated public forum for its readers to inform and educate as well as for the discussion of issues of concern to its audience. It is registered with the Media Authority of the Federal Democratic Republic of Ethiopia. Providing its growing audience with independent, reliable news through its platform options.

በዎላይታ ሶዶ ከተማ ከ168 ሚሊዮን ዶላር የአፍሪካ ሀገራትን ጨምሮ ተጠቃሚ የሚያደርግ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ሊገነባ መሆኑ ተገለፀ።በፕሮጀክቱ አተገባበር፣ የዲዛይን እና የሳይት ገለጻ ላይ ...
11/12/2023

በዎላይታ ሶዶ ከተማ ከ168 ሚሊዮን ዶላር የአፍሪካ ሀገራትን ጨምሮ ተጠቃሚ የሚያደርግ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ሊገነባ መሆኑ ተገለፀ።

በፕሮጀክቱ አተገባበር፣ የዲዛይን እና የሳይት ገለጻ ላይ ውይይት መድረክ ተካሂዷል።

የሔልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ (HAWE) መስራችና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ አለውበል አልማው ስለፕሮጀክት ዓላማና አተገባበር ላይ ገለጻ አድርገዋል።

ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በባህርዳር እና ዎላይታ ሶዶ ከተማ የሚገነባ ሲሆን ሔልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ (HAWE) የተሰኘ አለም አቀፍ እውቅና ያለው ድርጅት ድጋፍ የሚተገበር መሆኑን ገልጸዋል።

ዎላይታ ሶዶ የተመረጠችበት አስተማማኝ ሠላሟ የተሰፈነበት፣ ሌሎች አጎራባች ክልሎችና ዞኖችን ያማከለ እና በዕድገት ላይ የሚትገኝ ከተማ መሆኗን ነው የገለጹት።

ፕሮጀክቱ በውስጡ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሁሉ-አቀፍ ልማቶች ያቀፈ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ኢንተርናሽናል ሆስፒታሉ ከ168 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ የሚገነባ መሆኑንና የመጀመሪያው ደረጃ ህንጻ በ20,000 ካሬ ሜትር መሬት ላይ እንደሚያርፍ ጠቅሰዋል።

ፕሮጀክቱ የአፍሪካ ሀገራትን ጨምር ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን የኩላሊት ነቀላ፣ የኦክስጅን ማምረት፣ የጤና ምርምር ማዕከል፣ የኢንተርናሽናል ስብሰባ አድራሻ የያዘ ነው ብለዋል።

ፕሮጀክቱ ከሁለት ዓመት ከስድስት ወር እንደሚጠናቀቅ የተናገሩት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ግንባታው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጋር ውሉን በማጠናቀቅ በቅርቡ እንደሚጀምርም አስታውቀዋል።

ፕሮጀክቱ ለብዙ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር እና የቱሪዝም ዘርፍ አንጻርም የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም አንስተዋል።

የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ፕሮጀክት በዎላይታ ሶዶ ከተማ እንዲገነባ በማድረጉ የተሰማውን ደስታ በዞኑ አስተዳደርና በራሴ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

ይህ ለዎላይታና አጎራባች ህዝብ ትልቅ ዕድል ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በማህበራዊ ዘርፍ አንጻር የሚያበረክተው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዞኑ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ፕሮጀክቱ ውጤታማ እንዲሆን የዞኑ አስተዳደርና መላው የወላይታ ህዝብ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጣለሁ ብለዋል። Wolaita Times

2 የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወንዝ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው አለፈ።በዎላይታ ዞን " ሁምቦ " እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ዳርቻ ፎቶግራፍ በመነሳት ላይ የነበሩ ሁለት ተ...
10/12/2023

2 የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወንዝ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው አለፈ።

በዎላይታ ዞን " ሁምቦ " እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ዳርቻ ፎቶግራፍ በመነሳት ላይ የነበሩ ሁለት ተማሪዎች ተንሸራተዉ ወደወንዙ በመግባታቸዉ ህይወታቸው አልፈዋል።

ሁለቱም ህይወታቸው ያለፈው የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የ3ኛ ዓመት ተማሪዎች መሆናቸው ተነግሯል።

የዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ለአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በጠየቀዉ ድጋፍ መሰረት የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች የወጣቶቹን አስከሬን ዛሬ ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም አዉጥተዉ አስረክበዋል።

ተማሪዎችና ወጣቶች ፎቶ ግራፍ ለመነሳትና ለመዝናናት በሚል ወንዝ አካባቢ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ መሰል አደጋዎች የሚያጋጥሙ በመሆኑ ወንዝ አካባቢና የመዋኛ ስፍራዎች አካባቢ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነው ያገኘው። Wolaita Times

ከ4 አመት በላይ ከሥራ ገበታ በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ተፈናቅለው የቆዩ ረ/ፕሮፌሰር አሰፋ ወዳጆ ከፍተኛ ተማራማሪ በመሆን ተመደቡየዲላ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞው መምህር ረ/ፕሮፌሰር አሰፋ ዎዳጆ...
09/12/2023

ከ4 አመት በላይ ከሥራ ገበታ በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ተፈናቅለው የቆዩ ረ/ፕሮፌሰር አሰፋ ወዳጆ ከፍተኛ ተማራማሪ በመሆን ተመደቡ

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞው መምህር ረ/ፕሮፌሰር አሰፋ ዎዳጆ ከታህሳስ 1/2016 ዓ.ም ጀመሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የዲሞክራሲ እና መልካም አስተዳደር ከፍተኛ ተመራማሪ ሆኖ መሾሙን የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንሰቲትዩት በቀን 27/03/2016 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ገልጿል።

የፓለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ፣ የመብት ተሟጋችና የቀድሞ የድላ ዩንቨርስቲ መምህር ረ/ፕሮፌሰር አሰፋ ዎዳጆ ላለፉት አራት አመታት በዎላይታ ህዝብ የሚደርሰውን ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ መብት እንዲከበር በተለያዩ መንገዶች በመታገሉ ከስራ ተፈናቅለውና በተደጋጋሚ ለእስር ከተዳረገ በኃላ ከእነ ሙሉ ቤተሰብ ለችግር ተጋልጠው የመከራ ህይወት እየገፉ እንደነበር ይታወቃል። Wolaita Times

በዎላይታ ዞን ለጥቂት ጊዜ ቀዝቅዞ የነበረው በማህበራዊ ሚዲያ ሀሳባቸውን የሚገልጹ ወጣቶችና የመብት ተሟጋቾችን ማሰርና መደብደብ ማገርሸቱ ተገለፀ።በዞኑ ባለፈው ሳምንት በጤና ሙያ ተመርቆ ለአ...
08/12/2023

በዎላይታ ዞን ለጥቂት ጊዜ ቀዝቅዞ የነበረው በማህበራዊ ሚዲያ ሀሳባቸውን የሚገልጹ ወጣቶችና የመብት ተሟጋቾችን ማሰርና መደብደብ ማገርሸቱ ተገለፀ።

በዞኑ ባለፈው ሳምንት በጤና ሙያ ተመርቆ ለአራት አመታት ስራ በማጣት የቆየው ምህረቱ ዱኮ የተባለ ወጣት በማህበራዊ ሚዲያው በአከባቢው ፍትሀዊ የሆነ የቅጥር ስርዓት ባለመኖሩና ቅጥር በገንዘብና በዘመድ በመሆኑ በርካቶች በዚሁ ምክንያት ችግር ላይ እንደሆነ የሚገልጽ ሀሳብ በተደጋጋሚ በመፃፉ ከፍተኛ ድብደባና ሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞ በሆስፒታል እንደሚገኝ ለዎላይታ ታይምስ አስረድቷል።

ወጣቱ የድብደባውና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በማንና በምን አይነት ሁኔታ የገለፀ ሲሆን በጤና ሙያ ተመርቆ በአከባቢው ኢፍትሐዊ አሰራር በመኖሩ ለአራት አመታት ስራ በማጣት በመቆየቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን በተለያዩ ጊዜ በማህበራዊ ሚዲያ መፃፉ ከመንግሥት አመራሮች በተደጋጋሚ ዛቻና ማስፈራሪያ ከደረሰ በኃላ መሆኑን ገልጿል።

በሌላ በኩል ከትናንት በስቲያ በዞኑ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደርና ሌሎች ችግሮችን በማህበራዊ ሚዲያ በማጋለጥ የምታውቀው መምህር ወንድማገኝ ሀይለማርያም ( አሩጂያ ታይምስ ) የፓሊስ ልብስ የለበሱ አካላት ወደ የሚያስተምርበት ትምህርት ቤት ክፍል ዘልቆ በመግባት ከተማሪዎች ፊት ወደ አባላ አባያ ወረዳ ወስደው ማሰራቸውን ባለቤቱ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጸዋል።

በዎላይታ ዞን በማህበራዊ ሚዲያ ሀሳባቸውን የሚገልጹ ወጣቶችንና የመብት ተሟጋቾችን ለእስርና ድብደባ ማድረግ ለጥቂት ጊዜ ጋብ ያለ ቢመስልም አሁን ላይ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ መልሶ አገርሽቷል። Wolaita Times

የጦና ንቦቹ አፄዎቹን በሰፊ ጎል ልዩነት ልዩነት አሸነፉ።በዛሬው ዕለት ዎላይታ ድቻ ፋሲል ከነማ ጋር ያገናኘው ጨዋታ ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ7ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሁለት ጨ...
07/12/2023

የጦና ንቦቹ አፄዎቹን በሰፊ ጎል ልዩነት ልዩነት አሸነፉ።

በዛሬው ዕለት ዎላይታ ድቻ ፋሲል ከነማ ጋር ያገናኘው ጨዋታ ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ7ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሁለት ጨዋታዎች በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂደዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ሀምበርቾን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፤ የወልቂጤ ከተማን የመሸነፊያ ግብ አሜ መሀመድ በ86ኛ ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡

በሌላ በኩል ምሽት 12 ሠዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ዎላይታ ድቻ ፋሲል ከነማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ለዎላይታ ድቻ የማሸነፊያ ግቦቹን ቢኒያም ፍቅሬ በ36ኛው ደቂቃ እንዲሁም ዘላለም አባቴ በ45ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ Wolaita Times

በሲዳማ ክልል ከደረጃ በታች የሆኑና በህገ-ወጥነት የተገመገሙ 17 የግል ኮሌጆች ተዘጉ።የክልሉ ስራ፣ ክህሎትና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ እንዳስታወቀው የመንግስት እና የግል ኮሌጆች የ2015 ዓ.ም ...
07/12/2023

በሲዳማ ክልል ከደረጃ በታች የሆኑና በህገ-ወጥነት የተገመገሙ 17 የግል ኮሌጆች ተዘጉ።

የክልሉ ስራ፣ ክህሎትና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ እንዳስታወቀው የመንግስት እና የግል ኮሌጆች የ2015 ዓ.ም ክትትልና ግምገማ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓዋል።

የቢሮዉ ሀላፊ ሀገረፅዮን አበበ በወቅቱ እንደገለፁት÷ ከደረጃ በታችና በህገ-ወጥ መንገድ ሲያሰለጥኑ የቆዩ 17 የግል ኮሌጆች እንዲዘጉ ተደርገዋል።

እንዲሁም 7 ኮሌጆች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማሻሻል ከቻሉ ማሰልጠን ይችላሉ ተብለው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ነዉ ያሉት።

ስለሆነም አትላስ ኮሌጅ ሀዋሳ፣ ፊሪላንድ ኮሌጅ ሀዋሳ፣ ራዲካል ኮሌጅ ሀዋሳ፣ ስፓርክ አፍሪካ አለታ ጩኮ፣ ዩኒክ ስታር አለታ ጩኮ፣ ዛክቦን ኮሌጅ በንሳ ዳዬ፣ ሪፍት ቫሊ ኮሌጅ ሀዋሳ፣ ዩኒክ ስታር ኮሌጅ በንሳ ዳዬ፣ ኦሞ ቫሊ ኮሌጅ ሞሮቾ፣ አፍኒ ፎር አፍሪካ አለታ ወንዶ፣ ዩኤስ ኮሌጅ በንሳ ዳዬ፣ ዩኒክ ስታር ኮሌጅ አርቤጎና፣ ፋርማ ኮሌጅ ለኩ፣ ሮሚክ ኮሌጅ ሀዋሳ፣ ካይዘን ዲዲ ኮሌጅ ሁላ ወረዳ፣ ዩኒክ ስታር ኮሌጅ ለኩ፣ ሂሊኬን ኮሌጅ ጭሬ ከነገ ጀምሮ የሚዘጉ ኮሌጆች መሆናቸው ተገልጿል።

ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ኮሌጆች ደግሞ ሰባት ሲሆኑ እነዚህም፦ ፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ ሀዋሳ፣ ፉራ ኮሌጅ ይርጋለም፣ ዳዲሞስ ኮሌጅ ለኩ፣ እናት ኮሌጅ አለታ ወንዶ፣ ታቦር ቢዝነስ ኮሌጅ ሀዋሳ፣ ዛይን ኮሌጅ ሀዋሳ፣ ኒው ግሎባል ቪዥን ኮሌጅ ሀዋሳ ናቸው ተብሏል።

ገበያ ላይ ተፈላጊነት የሌላቸው ናቸው የተባሉ የሙያ ዘርፎች እንደሚዘጉም ሃላፊዋ ጠቁመዋል ስል ኤፍቢሲ ዘግቧል። Wolaita Times

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለተወጣጡ አስተባባሪ አካላት የሚሰጠው ስልጠና በዎላይታ ሶዶ ከተማ ተጀመረ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን "ሀገራዊ ምክክር ለሀገ...
06/12/2023

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለተወጣጡ አስተባባሪ አካላት የሚሰጠው ስልጠና በዎላይታ ሶዶ ከተማ ተጀመረ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን "ሀገራዊ ምክክር ለሀገራዊ መግባባት" በሚል መርህ ሀሳብ ለሚደረገው ሀገራዊ ምክክር የተባባሪ አካላት ስልጠና ከዛሬ ህዳር 26-28/ 2016 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሁሉም የክልሉ ዞኖች ለሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ሰባት መቶ የሚጠጉ ሰልጣኞች ተሳታፊዎች ናቸው።

ስልጠናውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ መላኩ ወ/ማርያም በተለያዩ ምክንያቶች በአገራችን የፖለቲካ መሪዎች መካከል ያሉ ልዩነቶች እየሰፉ መምጣታቸውን ገልጸዋል።

አያይዘውም አቶ መላኩ እንደተናገሩት አንድ ሀሳብ እንድናስብ የተፈጠርን አይደለንም፤ የልዩነት ሀሳቦችን በመድረክ ዙሪያ በመነጋገር መግባባት መፍጠር አለብን።

አገራችን መከተል በሚገባት መርህ ላይ ተወያይተን አናውቅም ያሉት ኮሚሽነሩ ያገኘነው ዕድል ሊያመልጠን አይገባም ሲሉ አሳስበዋል።

አቶ መላኩ አክለውም ምንም አይነት ልዩነት ቢኖረን ሀገራችንን ለማስቀጠል መመካከር አለብን፤ በመመካከር መግባባት አለብን ሲሉ ተናግረው የስልጠናው ተሳታፊዎች ለእውነት እና ለሀገር እንዲወግኑ አሳስበው ለፈጣሪ በመፍራት፣ ለህሊናቸው በመገዛት፣ ለሀገር በማሰብ በታላቅ አደራ እና ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በስልጠናው ተባባሪ አካላትን የሚወክሉ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ ከክልሉ ሲቪክ ማህበራት ምክር ቤት፣ በክልሉ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ፖሌቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምከር ቤት፣ ከክልሉ መምህራን ማህበር፣ ከክልሉ ዕድሮች ማህበራት ጥምረት፣ ከወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ተወካዮች እና ከየመዋቅሮቹ የተወከሉ ዳኞች መገኘታቸውን ከዞኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። Wolaita Times

በምስራቅ አፍርካ በአይነቱ ለየት ያለ በዎላይታ በበሎሶ ቦምቤ ወረዳ አጆራ ቀበሌ የሚገኝ ውብ "አጆራ" መንታ ፏፏቴዎች፤ ከረጅም ርቀት ወደ ምድር የሚንደረደሩ ናቸው።ሁለቱ ፏፏቴዎች የተመሰረቱ...
03/12/2023

በምስራቅ አፍርካ በአይነቱ ለየት ያለ በዎላይታ በበሎሶ ቦምቤ ወረዳ አጆራ ቀበሌ የሚገኝ ውብ "አጆራ" መንታ ፏፏቴዎች፤ ከረጅም ርቀት ወደ ምድር የሚንደረደሩ ናቸው።

ሁለቱ ፏፏቴዎች የተመሰረቱት ሶኬ እና አጀቾ ተብለው በሚጠሩ ወንዞች ነው፣ ሶኬ ወንዝ በሰሜን፣ አጀቾ ደግሞ በስተደቡብ በኩል ይገኛሉ፡፡

ስያሜያቸው ከሚንደረደሩበት ትልቅ ገደል ውሰጥ ለዘመናት ይኖሩ ከነበረው አጆራ ወይም ያጋ የተባሉ ጎሳዎች ነው የሚሉ አሉ፡፡

እየሮጡ የሚዘምሩ፤ ቁልቁለቱን ሲንደረደሩ የማያዳፋቸው፡፡

ሲጤሱ የኖሩ ውብ ሁለት ሆነው አንድ ውበት አንድ መልክ አንድ መደመም መፍጠር የቻሉ ጸጋዎች ናቸው፡፡

የሶኬ ፏፏቴ 170 ሜትር ገዳማ ከሰማይ ወደ ጥልቁ ይወርዳል፡፡

አጀቾ ከሶኬ የበለጠ ተንደርዳሪ ነው፡፡

210 ሜትር ቁልቁል ይወርዳል፡፡

በሁለቱ ፏፏቴዎች መሀከል ያለው ርቀት በቀጥታ መስመር ሲለካ 650 ሜትር (2,133 ጫማ) እንደሚሆን ይገመታል፡፡

ወርደው ምድር ሲነኩ የተለየ ድምጽ ያሰማሉ፡፡

ገና ምድሩን ሳይነኩት የሚተፉት ጭስ በተለይም በክረምት ናፍጣ የበዛበት መኪና፣ በበጋ ደግሞ ጉም የሚንደባለልበት ሰማይ ያስመስላቸዋል፡፡

አካባቢው አረንጓዴ ነው፡፡

የተለያየ ብዝሃ ህይወት መኖሪያ መሆን ችሏል፡፡

ወንዞቹም ከፏፏቴዎቹ አለፍ ብለው ውህደት ይፈጥሩና፣ ለተጨማሪ 10ኪሜ (6 ማይል) ወደ ምዕራብ አቅጣጫ በማምራት፣ ከኦሞ (ጊቤ) ይቀላቀላሉ።

በምስራቅ አፍርካ በአይነቱ ለየት ያለው #አጆራ #ፏፏቴ ሁለት ወንዞች ውጤት ሲሆን #ሶኬና #እጃቾ ይባላሉ፤

#የሶኬ ፏፏቴ 170 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን #የእጃቾ ፏፏቴ 210 ሜትር ከፍታ አለው፡፡

ሁለቱ ወንዞች ተገናኝቶ አንድ ትልቅ ሌላ ተጨማሪ ፏፏቴ የሚፈጥር ሲሆን ስያመውም #ቡቡቃ ይባላላ፡፡ አጠገቡ ለሚደርስ ሰው የሚያሰማው ድምጽ እጅግ ይማሪካል፤ ነፍስና ስጋን ይማሪካል፡፡

ቦታውን የተለያዩ ሀገር መሪዎች በተላይም አጼ ኃይሌስላሰ፣ ኮሌኔል መንግስቱ ኃይሌማሪያም አቶ ኃይሌማሪያም ደሳለኝ፣ አቶ ግርማ ወ /ጊዮርጊስና ሌሎች የሀገራችን ታዋቂ ግለሰቦች በተለያዩ ጊዜያት ደጋግመው ጉብኝት ማድረጋቸውን ከተለያዩ መረጃ ምንጮች ለመረዳት ችለናል፡፡

ፏፏቴው አጠገብ እጅግ የሚገርም #ዋሻና ከተራራው የሚወረወሩ #ምንጮች ትንፋሽ ቀጥ ያደርጋሉ፡፡

ይህ በኢትዮጵያ ትልቅ የቱሪስት መዳረሻ በመሆን አከባቢውን ከማስተዋወቅ ባለፈ ለተለያዩ አካላት ስራ ዕድል ተፈጥሮ ገቢ ምንጭ በመሆን የውጭ ምንዛሪ ሊያሰገኝ የሚችል የቱሪስት መስህብ ከግንዛቤ ማነስና ትኩረት ከመነፈጉ የተነሳ እጅግ አስቸጋሪ ሁነታ ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የፌደራል፣ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ባለሀብቶች ይህን ቦታ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን #በአከባቢው የተለያዩ መሰረተ ልማት እንዲሰራ የበኩላቸውን ቢወጡ መልካም እንላለን።

በዛሬው ዕለት በዎላይታ ሶዶ ስልጠና ማዕከል አራተኛ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ እየተሳተፉ ያሉ የመንግስት አመራሮች አጆራ መንትያ ፏፏቴን የቱሪስት መስህብ ስፍራ ጉብኝት ማድረጋቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። Wolaita Times

Ajjora Falls-The only East twin falls, Its the most spectacular waterfall with the most stunning view one can ever come across. As everything looks more exquisite when soaked in the rain, planning to visit some places is not a bad idea.

During the rainy season, the water level of the fall rises and the surroundings turn even more green which adds up to its charm.

“ያለፍኩበት የህይወት መንገድ” - አቶ ብርሃኑ መናአቶ ብርሃኑ መና ይባላሉ፡፡ በዎላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ነዋሪ እና ባለሀብት ናቸው፡፡ የ85 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ሲሆኑ ለበርካታ ሰዎች ተሞክ...
01/12/2023

“ያለፍኩበት የህይወት መንገድ” - አቶ ብርሃኑ መና

አቶ ብርሃኑ መና ይባላሉ፡፡ በዎላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ነዋሪ እና ባለሀብት ናቸው፡፡ የ85 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ሲሆኑ ለበርካታ ሰዎች ተሞክሮ ሊሆናቸው የሚችል የህይወት ልምድ አላቸው፡፡ በቀድሞ አጠራር የገጠር መድሀኒት ቤት አሁን የመድሃኒት መደብር ለ56 ዓመታት ያህል ሰርተዋል፡፡ በሶዶ ከተማ ምንም የመድሀኒት ቤት ባልነበረበት ወቅት ነበር እርሳቸው የህክምና ሙያቸውን ይዘው ወደ ስራው የገቡት፡፡ ከእርሳቸው ጋር ያደረግነውን ቆይታ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡ መልካም ንባብ፡፡

ንጋት፡- በቅድሚያ ለንጋት እንግዳ ለመሆን ፈቃደኛ ስለሆኑ በጋዜጣው ዝግጅት ክፍል ስም ከልብ አመሰግናለሁ፡፡
አቶ ብርሃኑ፡- እኔም እድሉ ስለተሰጠኝ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡

ንጋት፡- እራስዎን ያስተዋውቁን?

አቶ ብርሃኑ፡- ተወልጄ ያደኩት በዎላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ ልዩ ስሙ ጮጫ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ ነው፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቴን ከ1ኛ እስከ 2ኛ ክፍል ድረስ ቦዲቲ ነው የተማርኩት። ከዚያን በኋላ አጎቴ ጋር ወደ ይርጋለም በመሄድ በራስ ደስታ ኖርጂያን የሚሲዮን ትምህርት ቤት ነው የተከታተልኩት፡፡ እዛው ትምህርት ቤት እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ከተከታተልኩ በኋላ ዘጠነኛ እና አስረኛ ክፍል ድርስ እዛው በመማር በወቅቱ ከ10ኛ ክፍል በህክምናው ሙያ የድሬሰር ኮርስ በመማር ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ በጤና ሚኒስቴር ፈተና አልፌ ወደ ኮንሶ በመመደብ ለአንድ ዓመት የመስክ ልምምድ ካገኘው በኋላ በዲኘሎማ ተመረኩኝ፡፡

የአድቫንስ ዲፕሎማ ትምህርት ከጨረስኩ በኋላ ይርጋለም ሆስፒታል ለጥቂት ጊዜ አገልግያለሁ፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ ጤና ሚኒስተር በመሄድ በቲቪ ሴንተር ተወዳድሬ በጥሩ ውጤት አልፌ እዛው በባለሙያነት ተቀጠርኩ፡፡ በ1955 ዓ.ም በባለሙያነት ለአምስት ተከታታይ ዓመታት ከሰራሁ በኋላ የራሴን መድኀኒት ቤት ለመክፈት ወሰንኩ፡፡

ንጋት፡- የመድሀኒት ቤት ሥራ እንዴት ጀመሩ?

አቶ ብርሀኑ፡- በምሰራበት መስሪያ ቤት የመድሀኒት ክፍል ኃላፊ የሆኑትን ባልደረባዬን አማከርኩ፡፡ በስራዎች ሁሉ ያበረታታኝ እና ያማክረኝ ነበር፡፡ ስራ ለመጀመር ፈቃድ ስጠይቅ አሁን አይሰጥህም ግን ወኪል ሆኖ ወደ አካባቢህ መሄድ ትችላለህ በማለት መከረኝ፡፡ በባልደረባዬ ምክር እና ሀሳብ ተስማምቼ በ1960 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ወደ ትውልድ አካባቢዬ ተመለስኩ፡፡ በወቅቱ ወላይታ ሶዶ ከተማ የመድሀኒት ቤት ብዙም አልነበረም፡፡ በተለምዶ አሮጌ አራዳ ተብሎ በሚጠራው ከተማ በተደራጀ ሁኔታ ስራ ጀመርኩ፡፡ ስኬት እስካለ ድረስ ተግዳሮቶች ይኖራሉ፤ ነገር ግን ያጠነክራሉ፡፡

በስራው ላይ ተግዳሮቶች ገጠመኝ፡፡ በመድሀኒት ቤት ስራ የሚተዳደር አንድ ባልደረባዬ ቅሬታ በማቅረብ ከሰሰኝ፡፡ በጅምላ ለማከፋፈል ፈቃድ ወስዶ በችርቻሮ እየሸጠ ነው በማለት ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከሰሰኝ፡፡ በኋላም ይህንን ሰምተው እርምጃ ከሚወስዱ በማለት እራሴም ማመልከቻ አስገባሁ፡፡ በወቅቱም ፈቃዱ የገጠር መድሀኒት ቤት ነበር የሚባለው፡፡ በዚህም መሰረት የገጠር መድሀኒት ቤት ፈቃድ ይሰጠኝ ብለህ ስትጠይቅ በጅምላም ይሁን በችርቻሮ መሸጥ ትችላለህ በማለት የነበረውን ችግር በመፍታት አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ጨርሼ ዎላይታ ሶዶ ተመለስኩኝ፡፡

በዚያን ወቅት ዎላይታ መድሀኒት ቤት እምብዛም ስላልነበር ብዙዎችን የመድሀኒት ቤት ስራ እንዲጀምሩ እመክራቸው ነበር። በዚህም ብዙ ሰዎች ከፈጣሪ በታች የእንጀራችን አባት ነህ ይሉኛል፡፡ ጥሩ ስራ መስራት ለራስ ነው፡፡ የህሊናም እርካታው ከፍ ያለ ነው፡፡ እስከዛሬ ድርስ ገጠር መድሀኒት ቤት የሚባለው ቀርቶ የመድሃኒት መደብር በሚል ፈቃድ ለማውጣት ፋርማሲስት ይፈልግ ስለነበር በድግሪ የተመረቀ ባለሙያ አግንቼ እርሱ ባለ ፈቃድ እኔ ባለንብረት በመሆን በወር 12ሺ አንድ መቶ ብር ደሞዝ ከነአበሉ እስከ 15ሺ ብር በመክፈል ስራውን እያሰራሁ እገኛለሁ፡፡

ሌላው በመድሀኒት ቤቱ ለአራት ሰዎች የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ሲሆን ሁለት ካሸሮች እና አንድ ጥበቃን ጨምሮ ለረጅም ዓመት እንደ አባት እና ልጅ ያህል ተሳስበን ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን፡፡ በዚህም ደስተኛ ነኝ፡፡ በእኔ ድርጅት የበላይ እና የበታች የለም፤ ሁሉም ሰው በኃላፊነት ሳይጠባበቅ ይሰራል፡፡ የቤተሰብ ያህል ነው የምንተሳስበው፡፡

ንጋት፡- የትዳር ሁኔታዎስ ምን ይመስላል?

አቶ ብርሃኑ፡- በ1962 ዓ.ም ነው ወደ ትዳር ዓለም የገባሁት፡፡ ከቀድሞ ባለቤቴ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት በድምሩ ሁለት ልጆችን አፍርተናል፡፡ እርሷም ዛሬ በህይወት የለችም። ሁለቱም ልጆች ባሁኑ ሰዓት ባለሀብት ናቸው። ከሀገር ውጪ ይነግዳሉ። ኑሮአቸው አዲስ አበባ ነው፡፡ ከሁለተኛዋ ባለቤቴ ሶስት ልጆችን አፍርተናል፡፡ የ5 ልጆች እና 15 የልጅ ልጆች፣ በአጠቃላይ የ20 ልጆች አባት ነኝ፡፡ በዚህም እጅግ ደስተኛ ነኝ። ለወግ ማዕረግ አድርሻለሁ፡፡ ልጆቼ ሁሉም በጥሩ ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ ከአምስት ልጆች አራቱ በህይወት ሲኖሩ ለሁሉም በስማቸው መሬት እና ቤት ሰርቼ ሰጥቻለሁ ለ15ቱም የልጅ ልጆች በየራሳቸው የሂሳብ ደብተር ከፍቼ በቂ ገንዘብ እያጠራቀምኩላቸው ነው፡፡

ምክንያቱም እኔ ልጆቼን ያስተማርኩበት እና አሁን ያለበት ጊዜ አስቸጋሪ በመሆኑ ልጆቼ እንዳይጨናነቁ በማሰብ ነው፡፡ ቡዲቲ ላይ ማንዴላ ትምህርት ቤት እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ያለው በወር 12ሺ ብር የሚከራይ አለኝ እርሱንም ለታላቅ ልጄ አስተላልፌያለው፡፡ ሀዋሳም የጋራ መኖሪያ ቤት ባለሁለት መኝታ ለተከታዩ ልጅ አስረክቤያለሁ፡፡ ልጆቼ ነገ እንዳይጋጩ የየራሳቸውን ሀብት እና ንብረት ሰጥቻለሁ፡፡ በልጆቼ መካከል ፍቅር እንዲኖር እና ነገ እኔ ባልፍም እርስ በርሳቸው እንዲተሳሰቡ እንጂ በንብረት የተነሳ እንዳይቃቃሩ ከእነርሱ ጋር በመመካከር ሴቶችን ጨምሮ ለሁሉም የድርሻቸውን በስማቸው አኑሬያለሁ፡፡ በዚህም ምንም ቅር የሚለኝ ነገር የለም፡፡

ንጋት፡- የእርስዎን አርዓያ የተከተሉ ልጆችስ አሉ?

አቶ ብርሀኑ፡- በሙያው ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ ለ56 ዓመታት በመንግስት መስሪያ ቤት ለአምስት ዓመታት በግል በድምሩ በስራ ላይ ለ61 ዓመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል እስከ ዛሬ ድረስ ሰርቻለሁ፡፡ ጠንካራ እና ስራ አክባሪ ልጆችንም አብቅቻለሁ፡፡ በዚህም እጅግ ደስተኛ ነኝ፡፡ ፈጣሪ ይመስገን ታላቅ ልጄ ከእኔም የተሻለ የስራ ባህል ያለው እና እስከ ውጪ ሀገር ተንቀሳቅሶ ይሰራል፡፡ እኔን የሚጠብቁ ልጆች የሉኝም፡፡ እኔ በአባትነት ለልጆቼ ጭማሪ ነገር አደርጋለሁ እንጂ ልጆቼ በቂ እና ከበቂ በላይ የሆነ ነገር አላቸው፡፡

ከራሳቸው አልፈው የሚያከራዩት ህንፃዎች አሉአቸው፡፡ በዚህም ፈጣሪን ሳላመሰግን አላልፍም፡፡ ዓይኔን በዓይኔ አይቻለሁ፡፡ ድካሜ መና እና ከንቱ አልቀረም። በትዳር ለ54 ዓመታት ያህል የቆየሁ ሲሆን የትዳር አጋሬ ዛሬን ለማየት ትልቁን ድርሻ የተጫወተችው እርሷ ናት ብዬ እውቅና ልሰጣት እወዳለሁ፡፡ ባለቤቴ ብዙ ነገሬ ናት፡፡ ባለቤቴ እዚህ ቦታ ለመድረሴ ልጆችን ከማሳደግ ባሻገር ዛሬን እንዳይ አግዛኛለች፡፡ ትልቁንም ስፍራ ትይዛለች፡፡ ከጠንካራ ወንድ ጀርባ ጠንካራ ሴት አለች የሚለው አባባል ባለቤቴን ይገልፃታል፡፡ በእርሷም እጅግ እኮራባታለሁ፡፡

ንጋት፡- ለስኬትዎ የቤተሰብዎ አስተዋጽኦ ምን ነበር?

አቶ ብርሀኑ፡- ቤተሰቤ በመነጋገር እና በመመካከር ያምናል፡፡ ለዚህም ነው ስኬት ማማ ደርሻለሁ ብዬ የማምነው፡፡ በእያንዳንዷ የስኬት ጎዳና ባለቤቴ እና ልጆች ትልቁን ስፍራ ይይዛሉ፡፡ እድሜዬ እየገፋ ሲሄድም ልጆቼ ተነጋግረው እና ተሳስበው ታላቅ ታናሽን አድምጦ እና ተመካክረው ነው የሚሰሩት፡፡ ከትምህርታቸው ጎን ለጎንም የፋርማሲውን ስራ ከእኔ ባልተናነሰ ነበር ያግዙኝ የነበረው። እኔም ልጆቼ ትምህርታቸውን በአግባቡ ተምረው ይጨርሱ እንጂ ተቀጣሪ እንዳይሆኑ ብርቱ ፍላጎት ነበረኝ፡፡ በመንግስት ስራ የተሰማሩ ልጆች የሉኝም፡፡ ይህም ምኞቴ ነበር፡፡ ፈጣሪ ይመስገን ብዙዎቹ ባለሀብት ናቸው፡፡ በዚህም ፈጣሪን ሳላመሰግን አላልፍም፡፡ ከወላይታ ሶዶ አልፈው አዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ጭምር በአግባቡ ሀብታቸውን አካብተው ህብረተሰቡን እያገለገሉ ናቸው፡፡

አልፎ ተርፎም አራት ልጆች አሜሪካን ሀገር ናቸው፡፡ እርስ በርሳቸውም ይረዳዳሉ፡፡ ዛሬ ለዚህ መድረሳቸው ዋናው መተጋገዛቸው ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ አንድም ልጅ ከስራ ውጪ የሆነ ልጅ የለኝም፡፡ ዛሬ የ85 ዓመት የዕድሜ ባለጠጋ ብሆንም በእግሬ እንቀሳቀሳለሁ፡፡ ነገር ግን መኪና አጥቼ አይደለም፡፡ ለጤናዬ በማሰብ ነው፡፡ በዚህም ዕድሜ ምንም ዓይነት በሽታ የለብኝም፡፡ አሁንም ብዙ ዕቅደች አሉኝ፡፡ ፈጣሪ ከረዳኝ፡፡ ልጆቼ ከእኔ የወረሱት ብዬ የማስበው ሰዎችን በመርዳት ትልቅ የመንፈስ እርካታ ያገኛሉ፡፡ ይህንንም ባህሪ ወርሰዋል የሚል ጽኑ እምነት አለኝ፡፡

ንጋት፡- መጽሐፍም አሳትመዋል ስለመጽሐፉ የሚሉት ነገር ካሎዎት?

አቶ ብርሃኑ፡- የመጽሐፉ ርዕስ ያለፍኩበት መንገድ ይላል፡፡ ይህንን መጽሐፍ ያሳተምኩበት ዋናው ምክንያት ልጆቼ እድሜ እየገፋ ሲሄድ ይህንን ዓይነት የህይወት ተሞክሮ ይዘህ ለብዙዎች ህይወት ሊሆን ስለሚችል መጽሐፍ እንድጽፍ አሜሪካ ያለችው ልጄ አበረታታችኝ፡፡ እግረ መንገዴንም የጋብቻችን 48ኛ የእዮቤልዩ በዓል ጋር ባሳለፍነው ዓመት ሙሉ ቤተሰብ እና አብሮ አደጎች፣ ቤተዘመድና አድናቂዎች ባሉበት ሚዲያ ሽፋን አግኝቶ ነው መጽሐፉ የተመረቀው፡፡ ብዙ ሰዎች ካሳለፍኩት ህይወት ትምህርት ወስደዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በዚህም በጣም ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ ያሳለፍኩትን እና የደከምኩትን የህይወት ውጣ ውረድ ወደ ኋላ መለስ ብዬ እንዳይ አድርጎኛል፡፡ የመከራ ጊዜ እንደ ቀላል ያልፋል፤ ደግሞም ካለፈ በኋላ እንደ ህልም ይታያል፤ ካለፈ በኋላ እንደ ቀላል እናየዋለን፡፡ ዛሬም ሰዎች ከእኔ ሊማሩ የሚገባው ነገር ቢኖር በዚህም ዕድሜ በአንድ ሰዓት ፋርማሲዬን እከፍታለሁ፡፡ “መቀመጥን ለአፍታም አልፈልግም፡፡”

ንጋት፡- ከህብረተሰቡ ጋር ያልዎት ማህበራዊ ህይወትዎ እንዴት ይገልፁታል?

አቶ ብርሃኑ፡- እቁብ እሰበስባለሁ፤ እስከ ዛሬ ድረስ በሳምንት 10ሺ ብር በመጣል ከአንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ሀምሳ ሺ ብር በላይ እቁብ ሰብሳቢ ነኝ፡፡ በእድርም በተለምዶ የዳሞት ዕድር ተብሎ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ይታወቃል። የዚህም እድር መስራች እና ለእድሩ ከግል መኖሪያ ቤት የይዞታ ቦታ 3ሺ ካሬ ቦታ ሰጥቻለሁ፡፡ በገንዘብም በርካታ አስተዋጽኦ አበርክቻለሁ፡፡ በዚህም እጅግ ደስተኛ ነኝ፡፡ የአካባቢው ማህበረሰብም በጣም ይወደኛል ፤ ያከብረኛል፡፡ ከህብረተሰቡ ጋር ያለኝ ቁርኝት የቤተሰባዊነት ያህል ነው፡፡

ንጋት፡- በዎጋጎዳ( ዎላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ዳውሮ) ወቅት የነበርዎት አስተዋጽኦ ምን ነበር?

አቶ ብርሃኑ፡- በወጋጎዳ ወቅትም በርካታ ተሳትፎ ነበረኝ፡፡ በሀብትም ይሁን በሀሳብ አግዛቸው ነበር፡፡ ህብረተሰቡንም በማሳተፍ የበኩሌን አስተዋጽኦ አበርክቻለሁ፡፡ የዎላይታ ባህልና ቅርሳቅርስ የሚባለው ድርጅት ውስጥም ሰብሳቢ ነበርኩ፡፡ በዚህም ከየአካባቢው ቅርሶችን በመሰብሰብ በማሰባሰብ የበኩሌን አስተዋጽኦ አበርክቻለሁ:: ወንታ በሚባለው ድርጅትም ተሳትፎ ነበረኝ፡፡ ከህብረተሰብም አልፎ ለመንግስት በጀት እስኪመጣ ድረስ በማበደር ስራ እንዳይቆም እና እንዳይስጓጎል የምችለውን ያህል ሰርቻለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ ፈጣሪ እድሜ እና ጤና ሰጥቶ የክልሉ መቀመጫ ሶዶ ከተማ በመሆኑም ከልብ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ በዚህም ፈጣሪን ሳላመሰግን አላልፍም፤ በህይወት በመኖሬ ለዚህ በቅቻለሁ፡፡

ንጋት፡- የሚያስተላልፉት መልዕክት ካልዎት?

አቶ ብርሃኑ፡- ፈጣሪ እድሜ እና ጤና ከሰጠኝ ባለ አራት ወለል ህንፃ ቤት ሰርቼ የመድሀኒት ቤቱን ማስፋፋት እፈልጋለሁ። እኔ የምድር ቤቱን እፈልጋለሁ፡፡ ልጆቼ አንድነት እና ህብረት እንዲኖራቸው ቀሪውን ሶስት ወለል እነርሱ እንዲሰሩ እያበረታታሁ ነው፡፡ ዛሬ ለሰዎች የማስተላልፈው የዕድሜ ቁጥር ምንም ማለት አይደለም፡፡ መስራት እና ማልማትን አይከለክልም፡፡

ጤና እና እድሜ ከሰጠን ብዙ መስራት ይቻላል፡፡ ከመስራት አትቦዝኑ፤ ለልጆቻችሁም እዳ አታትርፉ ጤና ካለ ስራን አትናቁ፡፡ ሁሉም ነገር የእኔ ነው አትበሉ፡፡ በህይወት እያላችሁ ለልጆች እና ለልጅ ልጆች እዳ አታስቀምጡ እላለሁ፡፡ ሌላው ብዙ ቤተሰብን ሳይ በህይወት በራሳቸው ስም ሀብት ንብረት ያስቀምጣሉ። ነገ ግን ቢያልፉ ልጆች ያላቸውን ፍቅር እና እርስ በርስ መረዳዳት ብሎም መተሳሰብን ትተው ለሀብት ንብረት በፍርድ ቤት እንደባዳ ሲቆሙ ይታያሉ፡፡

ይህም ቤተሰብ በህይወት እያለ ማስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች በግድ የለሽነት ተዘንግተው ለልጆቻቸው ጡስ ስለሚሆን ነገ የሚሆነው ነገር ስለማይታወቅ በህይወት እያላችሁ ሀብት ንብረት ለልጆቻችሁ እኩል በስማቸው አስቀምጡ እና አስማሟቸው በማለት መልዕክቴን እቋጫለሁ፡፡ በንጋት መፅሄት Wolaita Times

ከሁለት ዓመት በላይ ታግዶ የነበረው የቀድሞ የዎላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ውዝፍ ደሞዝ ተከፈለ።ከሶስት አመት በፊት የዎላይታ ህዝብ ህገመንግስታዊ በክልል የመደራጀት መብት ጥያቄ...
29/11/2023

ከሁለት ዓመት በላይ ታግዶ የነበረው የቀድሞ የዎላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ውዝፍ ደሞዝ ተከፈለ።

ከሶስት አመት በፊት የዎላይታ ህዝብ ህገመንግስታዊ በክልል የመደራጀት መብት ጥያቄ እንዲመለስ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በመደገፍ "ህገመንግስትንና ህገመንግስታዊ ስራዓትን በኃይል ማፈረስ" በሚል ከሌሎች ጋር ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተደርገው ለእስርና ከስራ ተፈናቅለው የነበሩት የቀድሞ የዎላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥበቡ ዮሐንስ ውዝፍ ደሞዝ ከሁለት ዓመት በላይ ከታገደ በኃላ እንዲከፍል በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከተሰጠ የቆየ ቢሆንም በትናንትናው ዕለት አዲሱ በተደረሰው ስምምነትና አቅጣጫ መሠረት መደረጉን አንድ ሁኔታውን በቅርበት የሚያውቅ አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አስረድተዋል።

እንደ መረጃ ምንጫችን ከሆነ "ባለፈው ሳምንት ከፌደራል ጀምሮ በተለያዩ ደረጃ በአመራርነት የሚገኙ የአከባቢው ተወላጆች በዎላይታ ሶዶ ከተማ ከዞን እና ከክልል አመራሮች ጋር ባደረጉት ምክክር መድረክ ባለፉት ሶስት አመታት በፓለቲካ ልዩነት ምክንያት ከስራቸው የተፈናቀሉና የተሰደዱ ወደ ስራቸው የሚመለሱበት ሁኔታ ትኩረት ተሰጥቶት ተግባራዊ እንዲሆን በተደረሰው ስምምነት መነሻ ያንን የሚመራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱንም" ገልጸዋል።

በአከባቢው በተለይም ባለፉት አራት አመታት ህገመንግስታዊ በክልል የመደራጀት መብት እንዲከበር ወጣቶች፣ ምሁራን፣ በመንግሥት መዋቅር የሚገኙ ባለስልጣናት፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የትግሉ አካል በመሆን የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል፣ አካል በማጉደል፣ ከስራና ከስልጣን በመነሳት፣ ለእስርና ለስደት ህይወት በመዳረግ መስዋዕትነት የከፈሉ ሲሆን እስከዛሬም በዛ ምክንያት ከስራቸው ተፈናቅለው ቤተሰብን ለችግር አጋልጠው የስደት ህይወት እየገፉ የሚገኙ በርካቶች መሆናቸው ይታወቃል።

በመሆኑም ምሁራን፣ ፓለቲከኞች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም በየደረጃው ተሰምነት ያላቸው ግለሰቦች በዞኑ የፓለቲካ አካሄድ ልዩነት ምክንያት ብቻ ዳርና ዳር ሆነው የሚገኙ ወገኖች ወደ አንድነት፣ መደማመጥ፣ መተባበር እንዲሁም በጋራ ጉዳይ በሆኑ የህዝብ የልማት ፍላጎቶች ላይ የበኩላቸውን እንዲወጡና በአንድነት በመሰለፍ ለአጎራባች ህዝቦች ጭምር በጎ ሚና ሊወጡ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንዲደርሱ ለማድረግ አሁን የተጀመሩ በጎ እንቅስቃሴ አይነት ከማን ምን ይጠበቃል የሚለው ሀሳብም ለጊዜው ምላሽ አላገኘምና በያለንበት እንወያይበት። Wolaita Times

ከጥንት ጀምሮ እስካዛሬ የቀጠለው የታላቁ ኦሮሞ እና ዎላይታ ህዝብ የወዳጅነት ምስጥር 👇የታላቁ ኦሮሞ ህዝብ የጀግንነት ተምሳሌት የነበሩ የጅማው ንጉሥ አባጅፋርና የዎላይታው ንጉሥ/ካዎ ጦና እ...
28/11/2023

ከጥንት ጀምሮ እስካዛሬ የቀጠለው የታላቁ ኦሮሞ እና ዎላይታ ህዝብ የወዳጅነት ምስጥር 👇

የታላቁ ኦሮሞ ህዝብ የጀግንነት ተምሳሌት የነበሩ የጅማው ንጉሥ አባጅፋርና የዎላይታው ንጉሥ/ካዎ ጦና እጅግ የጠነከረ መልካም ግንኙነት በመኖራቸው ከጓደኝነትም አልፎ አማቾች ነበሩ። አንዳቸው አንዳቸውን ለማስገበር ብሎ አንድንም ጦርነት አላካሄዱም። ዛሬ ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር የዎላይታ ህዝብ በኦሮሚያ ክልል እንደ ቤታቸው አድርገው የሚኖሩበት ምስጥርም ከዚሁ የመሪዎቻቸው ከገነቡት ታሪካዊና ከማይበጠስ ወዳጅነት የመነጨ እንደሆነ ብዙዎች ይመሰክራሉ።

በተጨማሪም ያኔ የተገነባው የዎላይታዎች የአንድነት እና ከየትኛውም ህዝብ ጋር ተስማምተውና አብሮ ሰርተው ጠንክረው የመኖር ስነልቦና የተገነባው በንጉሥ ጦና ጊዜ መሆንንም የታሪክ አዋቂዎች ያስረዳሉ።

ይሄ ስነልቦና ዎላይታዎች ከኢትዮጵያዊያን🇪🇹ወንድሞች ጋር ስቀላቀሉም ሳይቸገሩ እንዲያውም ለሌሎች በአንድነት እና አብረው በመኖር ረገድ ተምሳሌት በመሆን የዘለቁበት ምስጥርም ያኔ በተገነባው ከሌሎች ህዝቦች ጋር አብረው ተስማምተው ለመኖር ያደረጉበት ጠንካራ የካበተ ልምድ መሆኑም ይነገራል።

በነገራችን ላይ ንጉሥ ጦና ጋጋ ዎላይታ ሀገር በነበረበት ወቅት ከጅማው ንጉሥ አባ ጅፋር ጋር የነበረው ጠንካራ ዲፕሎማሲ ብቻ ሳይሆን ከአጎራባች ህዝቦች ጋር፣ አልፎም በሀገር እና ሀገርአቀፍ ደረጃ የነበረው አንድነት፣ አብረው መኖር፣ የህዝቦች ወዳጅነትን ለማጠንከር የተወሰዱ ስታራቴጂክ መንገዶች ዛሬ ዘመናዊ አሰራር በሰፈነበት ወቅትም ጠቃሚ መሆናቸው ይነገራል።

ካዎ (ንጉሥ) ጦና ጋጋ እና ንጉስ አባ ጅፋር አማቾች ከመሆናቸው ባሻገር የልብ ወዳጆችና ጓደኛሞች ነበሩ። ከዚህ በተጨማሪ #ዎላይታና #ኦሮሞ የምያመሳስለው ተፈጥሯዊ ጉዳይ፦ ደግነት፣ የዋህነት፣ በጎነት፣ ሰው ወዳድነት እንዲሁም የሰው አክባሪነት በፉጹም ያመሳስላቸዋል ስል የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ።

በሚሊዮን የሚቆጠር የዎላይታ ህዝብ በኦሮሚያ ክልል እንደ ቤታቸው አድርገው የሚኖሩበት እየመራ የሚገኘው ፕረዚዳንት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ በሳምንት ለሁለተኛ ጊዜ ለመንግስታዊ ስራ ወደ ዎላይታ በዛሬው ዕለት ሲገቡ የተለየ ደማቅ አቀባበል በአከባቢው አመራሮችና ነዋሪዎች የተደረገበት ምስጥርም ከዚሁ የመሪዎቻቸው ከገነቡት ታሪካዊና ከማይበጠስ ወዳጅነት የመነጨ ነው። Wolaita Times

"በብልሹ አሰራር የቆሸሽዉን የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ገጽታ" የማደስና የመገንባት ኃላፊነት ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ረ/ፕሮፌሰር አሰፋ ዎዳጆ አሳሰቡ።የፓለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ፣ የመብት ተሟ...
27/11/2023

"በብልሹ አሰራር የቆሸሽዉን የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ገጽታ" የማደስና የመገንባት ኃላፊነት ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ረ/ፕሮፌሰር አሰፋ ዎዳጆ አሳሰቡ።

የፓለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ፣ የመብት ተሟጋችና የቀድሞ የድላ ዩንቨርስቲ መምህር ረ/ፕሮፌሰር አሰፋ ዎዳጆ የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ከፍተኛ አመራሮች በብልሹ አሰራር ምክንያት ከስልጣናቸው መባረራቸውን ተከትሎ ከዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ ምክር አዘል ማስጠንቀቂያ ለሚመለከታችው ሁሉ አስተላልፈዋል።

ረዳት ፕሮፈሰር አሰፋ በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ሲሰጡ "ታከለ ታደሰና ግብረአበሮቹ በስልጣን ዘመናቸዉ የፈለጉትንና የወደዱትን ለማድረግ አገራዊ፣ ክልላዊና ዞናዊ የፖለቲካ ዉጥንቅጥ፣ ደካማ፣ አድርባይ፣ ጥገኛ ቦርድ፣ አካዳሚክ ካዉንስልና ሴኔት እንደዚሁም አብላጫዉ የዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ (በተለይም የአካዳሚክ ስታፍ) የማምለጥ ባህሪ እንደ ምቹ አጋጣሚ ተጠቅመዋል" በሚል አብራርተዋል።

"ሙስናና ብልሹ አሰራር በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች አልነበረም ማለት አይደለም። ነገር ግን በሌሎች የኢትዮ-ዩኒቨርሲቲዎች ባልተለመደ መልኩ የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ አሉታዊ ገበናዎች ብቻ በየዕለቱ በማህበራዊ ሚዲያዎች ይሰጣ ነበር" ስሉ የመብት ተሟጋቹ ሁኔታውን ገልጸዋል።

እንደ ረ/ፕሮፈሰሩ ገለፃ "በማህበራዊ ሚዲያዎች ስለ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሙስና ቅሌትና ብልሹ አሰራር የማይራገበዉ ችግሮችን በየዩኒቨርሲቲዉ መደበኛ ቻናል በዉይይት፣ በክርክር ብሎም በግምገማ የሚፈታበት አሰራርና ልምድ ስላለ ነዉ" በሚል አብራርተዋል።

ሁለተኛዉና ዋነኛዉ ምክንያት የየዩኒቨርስቲዉ ማህበረሰብ ተቋማዊ ችግሮችን በፌስቡክ መንደር በመዘርገፍ መፍትሔ ማግኘት የማይቻል ከመሆኑም በላይ ተቋማዊ ጉዳት የሚያስከትልና የዩኒቨርሲቲውን ገጽታ የሚያበላሽ መሆኑን በመገንዘብ የተቋማዊ ባለቤትነት የሚሰማቸዉ በመሆኑ እንደሆነ የፓለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ፣ የመብት ተሟጋችና የቀድሞ የድላ ዩንቨርስቲ መምህር ረ/ፕሮፌሰር አሰፋ ዎዳጆ ያብራሩት።

"የተቋማዊ ገጽታ ተበላሸ ማለት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ገጽታ ይበላሻል። በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለጠፉ፣ ብሮድካስት የሚደረጉ መረጃዎች፣ ዘገባዎች ዓለማቀፍ፣ አገርአቀፍ፣ ሎካል ማህበረሰብ አቀፍ ተደራሽነት ያላቸዉ መሆኑ አይካድም። መጥፎ ገጽታዎቹ ብቻ በብዙ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በተከታታይ ብሮድካስት የሚደረግበት ዩኒቨርስቲ ተቋማዊ ሕልዉናዉ አደጋ ዉስጥ ይገባል" ስሉም ረ/ፕሮፌሰሩ ስለሁኔታው አሳሳቢነት ተናግረዋል።

"እያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ የተመሠረቱበትን ሶስቱን ዋና ዋና ተልዕኮዎችን በአግባቡ በመወጣት ለብሔራዊ፣ ክልላዊና አከባቢያዊ ሁለንተናዊ የልማት ሂደት ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ በሚል በየዓመቱ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ኢንቬስት የሚያደርገዉ መንግስታዊ አካል አሉታዊ እርምጃ ሊወስድ ይችላል" ብለዋል።

"በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲዎችን የሳይንሳዊ ምርምር፣ ዘመናዊና ችግር ግኝቶች፣ የእውቀት ማዕከላት ናቸዉ ብሎ የሚያምነዉ ተራዉ ማህበረሰብ አደገኛ የጋርዮሽ አመለካከት ሊያዳብር እንደሚችል መገመት እንደሚቻል በመግለፅ በተጠቃሽ ዩኒቨርሲቲ አቅራቢያ ባሉ አከባቢዎች የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች ስለ ዩኒቨርስቲ ትምህርት የተዛባ ወይንም አሉታዊ እይታ ያዳብራሉ" በሚል አብራርተዋል።

ረ/ፕሮፌሰሩ ከዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ያደረጉትን ቆይታ ሲያጠቃልሉ "አዳዲስ መምህራን፣ ተመራማሪዎችና ተማሪዎች ወደ ተጠቃሹን ዩኒቨርሲቲ ለመቀላቀል ደስተኛ- ፈቃደኛ አይሆኑም። ከተጠቃሽ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዉ የሚወጡ ተማሪዎች ሀፍረት ይሰማቸዋል። እነኚህን ምሩቃን የመቀጠር ዕድላቸዉ ዉስን ይሆናል። በጣም ብዙ ሕዝብ በሚጠቀማቸዉ ማህበራዊ ሚዲያዎች በማወቅ ባለማወቅ የቆሸሽዉን የዩኒቨርስቲ ገጽታ ማደስ-መገንባት በጣም ከባድ ይሆናል። በመሆኑም ትኩረታችን የዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ገጽታ ማደስ--መገንባት ላይ ያገባኛል የሚል ሁሉም ትኩረት እንዲያደርጉ" በሚል ጥሪ አቅርበዋል።

የፓለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ፣ የመብት ተሟጋችና የቀድሞ የድላ ዩንቨርስቲ መምህር ረ/ፕሮፌሰር አሰፋ ዎዳጆ ላለፉት አራት አመታት በዎላይታ ህዝብ የሚደርሰውን ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ መብት እንዲከበር በተለያዩ መንገዶች በመታገሉ ከስራ ተፈናቅለውና በተደጋጋሚ ለእስር ከተዳረገ በኃላ ከእነ ሙሉ ቤተሰብ ለችግር ተጋልጠው የመከራ ህይወት እየገፉ እንደሆነ ይታወቃል። Wolaita Times

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ የዎሕደግ ፖለቲካ ፓርቲ አመራር፣ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መምህር፣ ታጋይ   ወደ መደበኛ ስራ የሚመለስበት ሁኔታ እንዲመቻች የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጠየቀ።መምህር አ...
26/11/2023

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ የዎሕደግ ፖለቲካ ፓርቲ አመራር፣ የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ መምህር፣ ታጋይ ወደ መደበኛ ስራ የሚመለስበት ሁኔታ እንዲመቻች የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጠየቀ።

መምህር አሸናፊ ከበደ ላለፉት ሶስት አመታት በዎላይታ ህዝብ የሚደርሰውን ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ መብት እንዲከበር በተለያዩ መንገዶች በመታገሉ ከስራ እንዲባረር ተደርጎ ከእነ ቤተሰቡ እንዲሰደድ መደረጉ ይታወሳል።

በአከባቢው በተመሳሳይ መንገድ እንደ መምህር አሸናፊ ከበደ ሌሎች የህዝብ መብት ተሟጋቾች በግፍ ለስደትና ከስራ ተፈናቅለው ህይወታቸውን እየገፉ እንደሆነ ይታወቃል። Wolaita Times

"በዎላይታ ህዝብ ዘንድ ስራ የተከበረ ነው"! አቶ ተፈራ ሙንኤከታች ዝቅ ብዬ ነው የጀመርኩት!ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ። ሀረርጌ ክፍለ ሀገር ሳልባጅ በመሸጥ ነው የጀመርኩት። ይህንን ስሰራ ከአስ...
25/11/2023

"በዎላይታ ህዝብ ዘንድ ስራ የተከበረ ነው"! አቶ ተፈራ ሙንኤ

ከታች ዝቅ ብዬ ነው የጀመርኩት!

ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ። ሀረርጌ ክፍለ ሀገር ሳልባጅ በመሸጥ ነው የጀመርኩት። ይህንን ስሰራ ከአስር አመት በላይ ቆይቸ የስርዓት ለውጥ መጣ። የስርዓት ለውጡ ብዙዎችን የሚያስፈራ ነበር። እኔ ግን በእግዚአብሔር አጋዥነት በብዙው የሚመካ ሰው ነበርኩ እና አልፈራሁም። ውስጤ ፍርሀት የሚባል ነገር አልገባኝም። በእግዚአብሔር እገዛ እሱ የሚያደርገኝን እሱ እራሱ ያውቃል ብዬ ወደ ትውልድ ከተማየ ቦዲቲ መጣሁ። ቦዲት መጥቼ የቡና ንግድ ጀመርኩ። እሱም አዋጣኝ። ከቀደመው የሳልባጅ ስራዬ ለውጥ እያመጣሁበት ሄድኩኝ። በአጭር ጊዜም እራሴ ሹፌር እና ረዳት ሆኘ የምሰራበት መኪና ገዝቸ መስራት ጀመርኩ።

ከዎላይታ አዲስ አበባ

ከዎላይታ አዲስ አበባ በማደርገው ምልልስ መነገዱን ተያያዝኩት ንግዱን ይበልጥ ወደድኩት። እያተረፍኩ ብቻ ሳይሆን ለማህበረሰቡ አገልግሎት እየሰጠሁ እንደሆነ ሲሰማኝ ደግሞ ደስተኛ ሆንኩ። በዚሁ ቀጥየ የተሻሀ ገቢ እና የኢኮኖሚ እድገት አመጣሁ። በወቅቱ የታወጀው ነፃ ገበያ ደግሞ እኔን ይበልጥ ተጠቃሚ አደረገኝ። በዚህም ጠንክሬ በመስራት በህይወቴ እና በስራዬ ለውጥ አመጣሁ።

የባለቤቴ አጋዥነት

ባለቤቴን ያገኘኋት በስራ አጋጣሚ እና በእግዚአብሔር ፍቃድ ነው። ዘውዲቱ መንገሻ ትባላለች። እግዚአብሔርን የምታከብር እና ቤተሰቧን የምትወድ ሴት ነች። የእሷ ፀሎት ለእኔ ብርታት ነው። አጥንቴን ያጠነከረው የእሷ ፀሎት ነው። እሷ ብዙ ነገሮችን የምትቆጣጠር የእኔም ጥላ የሆነች ሴት ነች። ከእሷ ጋር 7 ልጆችን ወልደናል። በሰላም እና በፍቅር እየኖርን ነው።

አዲሱ "ዎላይታ ቱሪስት ሆቴል"

ዎላይታ ቱሪስት ሆቴል ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል ነው። ዎላይታ ሶዶ ለሚመጡ በሙሉ በተመቸ ሁኔታ ዘና ብለው ጥሩ ጊዜ አሳልፈው እንዲሄዱ ሁሉንም ነገር አዘጋጅተን የከፈትነው ሆቴል ነው። ሁሉም ሰው አገሩን ይመለከታል፤ ያያል። ወደ ዎላይታ ሲመጡም ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ሆቴሎች ያስፈልጋሉ ይህንን በሚያሟላ መንገድ ሰርተን ጨርሰን አስመርቀናል።

አቶ ተፈራ ሙንኤ በተመለከተ፣

የከተማው ከንቲባ አቶ ጃጋና አቶ ተፈራ ሙንኤ በከተማው ውስጥ የፈጠሩት መነቃቃት የማይናቅ መሆኑን ገልፀዋል። የስራ እድል በመፍጠር እና የከተማው ሆቴሎች ፅዳታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ለማድረግም ጥረዋል ብለዋል። ባለሀብቱ ለአካባቢ የፈጠሩት የተሻለ ገፅታ ፈጠራንም አመስግነዋል። በቀጣዩ ከተማ ለምታስተናግደው የከተሞች ቀን ይህ ሆቴል የሚኖረው አገልግሎት የሚናቅ እንዳልሆነ ጠቅሰዋል። Wolaita Times

የዎላይታ ህዝብ ጥቅምና ክብር እንዲጠበቅ ሳይሰለቹ የሚሟገቱ የመብት ተሟጋቾች ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ምን መምሰል አለበት❓ በአከባቢው በተለይም ባለፉት አራት አመታት ህገመንግስታዊ በክልል የመ...
25/11/2023

የዎላይታ ህዝብ ጥቅምና ክብር እንዲጠበቅ ሳይሰለቹ የሚሟገቱ የመብት ተሟጋቾች ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ምን መምሰል አለበት❓

በአከባቢው በተለይም ባለፉት አራት አመታት ህገመንግስታዊ በክልል የመደራጀት መብት እንዲከበር ወጣቶች፣ ምሁራን፣ በመንግሥት መዋቅር የሚገኙ ባለስልጣናት፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የትግሉ አካል በመሆን የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል፣ አካል በማጉደል፣ ከስራና ከስልጣን በመነሳት፣ ለእስርና ለስደት ህይወት በመዳረግ መስዋዕትነት ከፍሏል።

መስዋዕትነት የከፈሉት ጉዳይ ለጊዜው ባይመለስም መንግስት በራሱ መንገድ ለህዝቡ ይበጃል በሚለው በማቀድና በማስፈፀም የአደረጃጀት ጥያቄ ምዕራፍ በመዝጋት "ደቡብ ኢትዮጵያ" የተባለ አዲስ ክልል በይፋ መስርቷል።

በአከባቢው የሚገኙ ህዝብ ጥቅምና ክብር እንዲጠበቅ ሳይሰለቹ የሚሟገቱ የመብት ተሟጋቾች የአደረጃጀት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ከወትሮው በተለየ ሁኔታ መንግስት ለህዝብ መስራት አለበት ባላቸው የተለያየ ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ በርካታ የመንግስት አቅጣጫዎችን እስከማስቀየር ድረስ በጎ ሚና ተጫውተዋል።

ለምሳሌ ሁሉም ነገር ለጊዜው መስመር ባይዝም ከተልዕኮው ውጪ የዩኒቨርስቲውን ስልጣንና ሀብት በመጠቀም ለህብረተሰቡ የመፍትሄ አቅጣጫ ጠቋሚ መሆን ሲገባቸው በአከባቢውን ፓለቲካ ውስጥ ጠልቃ በመግባት ድብቅ ፍላጎታቸውን በማራመድ መዝረፍና ማዘረፍ፣ በአከባቢው መንግስት ትኩረት እንዳያደርግ የማይሰራ የውሸት ፕሮጀክቶች ይሰራሉ የሚል የማዘናጋት ወሬ በማባዛት፣ የሀሳብ ልየነት ያላቸው የለውጥ ኃይል በማሰርና በማሳሰር እንዲሁም ከስራና ከኃላፍነት ተባርረው እንዲሰቃዩ በማድረግ የተሰማሩ የዩንቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች ከስልጣን ተወግደው የህግ ተጠያቂነት እንዲኖር የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጨምሮ ሌሎች የአከባቢው የለውጥ ናፋቂዎች እና የውስጥ አርበኞች ባደረጉት የሞት ሽረት ትግል ጉዳዩ የሀገር አጀንዳ እስከመሆን ደርሶ እርምጃ ተወስዶባቸዋል። ምንም እንኳን ከኃላፊነታቸው የተነሱ ሰዎች ቦታ የተተኩ ግለሰቦች አካሄድና ተያያዥ ተግባር ብርቱ ትግል የሚጠይቅ የቤት ስራ ከፊት ቢኖርም።

ሌላው ከዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ በተጨማሪ የዎላይታ ዞን መንግስታዊ መዋቅር ከሌሎች አከባቢዎች በብዙ መንገድ የሚለይ ነገር አለው። ስልጣን በትውውቅ፣ በዝምድና እንዲሁም በጥቅማጥቅም ትስስር የተመሠረተ በመሆኑ በአከባቢው ዘመድ የለለው ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት የማይችልበት፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በከፍተኛ ውጤት የተመረቀ እያለ የአመራር ዘመድ ያለው ያለውድድር ወረቀት በግዢ ያመጣ የሚቀጠርበት፣ ጉቦና ብልሹ አሰራር የተለመደ አሰራር እየሆነ የመጣበት ሁኔታ ውስጥ ይገኛል።

በተጠቀሱ ጉዳዮች ዙሪያ ባለፉት ጊዜያት የተለያዩ በመረጃ የተደገፉ ተጨባጭ መረጃዎችን ለእናንተ ስናደርስ እንደነበር ይታወቃል። አሁን አሁን እንደዛ አይነት መንግስታዊ ስልጣን በመያዝ ህገወጥ የግልና የቡድን መዋቅር በመዘርጋት ህብረተሰቡን እያሰቃዩ የሚገኙትንና ከተለያዩ የለውጥ ናፋቂ ኃይል ጋር በቅንጅት ባደረግነው መራር የሚዲያ ትግል "የዋናዎቹ ቀንድ" የተሰበረ ቢሆንም እስካሁን ህብረተሰቡ ከፌደራል እስከ ቀበሌ ድረስ በስውር እነሱ ከፈጠሩት አደገኛ ህቡዕ አደረጃጀት ቀንበር ነፃ ባለመውጣቱ ዘርፈብዙ ችግር እያስከተለ ይገኛል።

እንደሚታወቀው የዎላይታ ዞን በሀገሪቱ ከየትኛውም አከባቢ በላይ ወደ ሁለት መቶ ሺህ የሚጠጋ ከታወቁ ከፍተኛ ዩንቨርስቲዎችና ኮሌጆች የተመረቁ የስራ አጥ ወጣቶች የሚገኙበት ነው። በጨቅላ ዕድሜያቸው ከእናታቸው ተለይተው በሀገሪቱ ጎዳናዎች ሁሉ የስቃይ ህይወት እየገፉ የሚገኙት ህፃናት ፍልሰትም የችግሩ ስፋት የሚያመለክት ይሆናል። በአከባቢው በመንግስት ትኩረት ተሰጥቶት የወጣቶች የስራ ዕድል ከፍ የሚያደርጉ እንዱስትሪና ሌሎች ተቋማት አለመኖር ችግሩን ከጊዜ ወደ ጊዜ አባብሶታል።

በአከባቢው ያለውን ፀጋ በመጠቀም ሀገር ውስጥና ውጪ የሚገኙትን እንዲሁም ሁሉንም ህብረተሰቡን ለአንድ አላማ በማሳለፍ ችግሩ ከስሩ እንዲቀረፍ ለማድረግ የመምራት፣ የማስተባበርና የማስተዳደር ብቃት ያላቸው በተለያዩ ኃላፊነት ቦታዎች እንዳይኖር ግለሰቦች በጥቅምና በዝምድና ተሳስረው ከፍተኛ ችሎታና ልምድ ያላቸው በየትኛውም ኃላፍነት ቦታ እንዳያገለግሉ በማግለል የዘረጉት አደረጃጀት ከፍተኛ ማነቆ እየፈጠረ ይገኛል።

ለመሆኑ እንደዚህ አይነት ህዝብን ለማገልገል ኃላፊነት ወስደው በጥቅምና በዝምድና ሰፊውን ማህበረሰብ በመግፋት የራሳቸው የሆነ ጥቂት አደረጃጀት በመዘርጋት ዘርፈብዙ ችግር እያስከተሉ የሚገኙትን በማስወገድ በእውነተኛ ለውጥ የሚተጉትን እንዴት መተካት ይቻላል❓

በአከባቢው ላለፉት አራት አመታት በአጋጣሚ በተገኙ የለውጥ ኃይሎች ከውስጥ የመነጨ ህዝባዊ ውግንና አስተባባርነት በአንድነት ለአንድ አላማ ያለ ምንም ልዩነት በሚያስደንቅ ሁኔታ ቆመው የነበረውን ህዝብ በድንገት የበተነውን ኃይል በመለየት በድጋሚ መስመር በማስያዝ ረገድ የህዝብ ጥቅምና ክብር እንዲጠበቅ ሳይሰለቹ የሚሟገቱ የመብት ተሟጋቾች ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ምን መምሰል አለበት❓የአዲሱ ክልል ሆነ የዞን አመራሮች እንዲሁም በአከባቢው የምንቀሳቀሱ ፓለቲካ ፓርቲዎች ይሄንን ህዝባዊ አላማ ከግብ ለማድረስ ቅንጅታዊ አሰራር እንዴት ማመቻቸት አለባቸው❓

እንዲሁም የዎላይታ ምሁራን፣ ፓለቲከኞች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም በየደረጃው ተሰምነት ያላቸው ግለሰቦች ባለፉት እራት አመታት በዞኑ የፓለቲካ አካሄድ ልዩነት ምክንያት ብቻ ዳርና ዳር ሆነው የሚገኙ ወገኖች ወደ አንድነት፣ መደማመጥ፣ መተባበር እንዲሁም በጋራ ጉዳይ በሆኑ የህዝብ የልማት ፍላጎቶች ላይ የበኩላቸውን እንዲወጡና በአንድነት በመሰለፍ ለአጎራባች ህዝቦች ጭምር በጎ ሚና ሊወጡ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንዲደርሱ ለማድረግ ከማን ምን ይጠበቃል የሚለው ሀሳብም ለጊዜው ምላሽ አላገኘምና በያለንበት እንወያይበት። Wolaita Times

በየደረጃዉ የሚገኙ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተወላጅ አመራሮች የክልሉን ሠላምና ልማት በጋራ በማጠናከር ዙሪያ በዎላይታ ሶዶ ከተማ የተደረገው ምክክር መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።የክልሉ ርዕ...
24/11/2023

በየደረጃዉ የሚገኙ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተወላጅ አመራሮች የክልሉን ሠላምና ልማት በጋራ በማጠናከር ዙሪያ በዎላይታ ሶዶ ከተማ የተደረገው ምክክር መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተደድር አቶ ጥላሁን ከበደ በሁሉም ዘርፍ የማህበረሰቡን ህይወት የሚቀይሩ ስራዎች ላይ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

ክልሉን ለመለወጥ አመቺ ሁኔታዎች መኖራቸውን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም ጠንካራ የስራ ባህልን ማዳበር እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።

የመቻቻልና የሰላም ክልል ለመፍጠር ህብረብሔራዊ አንድነትን ማጽናት እንደሚገባም አመላክተዋል።

ክልሉን የማልማት አቅሙን በመለየት ጥናት የማድረግ ስራ መጀመሩን በመገለጽ በአተገባበር ላይ በየደረጃው የሚገኙ አካላት በሙያውና በልምድ ማጋዝ እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ ም/ርዕሰ መስተደድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ ለጋራ ውጤትና ስኬት በመደማመጥና መተሳሰብ ተጋግዘን መስራት አለብን ብለዋል።

በየደረጃው ያሉ ችግሮችን ፈጥነን እየፈታን የህዝቡን ጥያቄዎች መመለስ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ተስፋዬ ህዝባችንን ተጠቃሚ ማድረግ የምንችለው ተቀናጅተን ስንሰራ ብቻ እንደሆንም ጠቅሰዋል።

ውጤታማና ሞዴል ክልል ለመፍጠር እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራት አስፈላጊ ነው ያሉት አቶ ተስፋዬ በጋራ ከሰራን እንለውጣለን፣ እንበልፅጋለንም ብለዋል።

የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባውዴ በበኩላቸው ሁሉም ህዝቦች ተወያይቶና ተመካክረው የመሰረቱትንው ክልል ለማጽናት አቅም የፈጠረ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል።

ህዝቦቻችን በአግባቡ ለማገልገል አውንታዊ መስተጋብሮችና በጋራ መተጋገዝ ማዕቀፎችን ማዕከል ያደረገ መሆን እንደሚገባ አንስተዋል።

በክልሉ በብዙ ነገር የተጋመዱና የተሳሰሩ ህዝብ አለን ያሉት አቶ አለማየሁ ይህንን የህዝቦች አብሮነትን፣ ባህልን፣ ታሪክንና እሴት እንደ ዕድል መጠቀም አለብን ብለዋል።

በስልጣን እያለ፣ ከስልጣን ተነስተው በእስርም፣ ከእስር ተፈተው ከስራና ከስልጣን ተፈናቅለው በሚኖርበት፣ ተመልሰው ወደ ስልጣን ሲመለስም የህዝብ ፍቅርና አመኔታ የቀጠለው የቀድሞ የዎላይታ ዞን...
24/11/2023

በስልጣን እያለ፣ ከስልጣን ተነስተው በእስርም፣ ከእስር ተፈተው ከስራና ከስልጣን ተፈናቅለው በሚኖርበት፣ ተመልሰው ወደ ስልጣን ሲመለስም የህዝብ ፍቅርና አመኔታ የቀጠለው የቀድሞ የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የአሁኑ የፈደራል ሰነዶች ማረጋገጫ ዋና ዳይረክቴር አቶ ዳጋቶ ኩምቤ በትናንትናው ዕለት በይፋ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ማብሰሪያ ባደረገው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዝግጅት ላይ የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ሆኗል። በእጅ የኢትዮጵያ ባንድራ ይታያል፣ ከፊት ወኔና እልህ ቁጭት ይነበባል። Wolaita Times
📷 Ab photo

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማብሰሪያ ዝግጅት አምባሳደሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የፈደራልና የክልል አመራሮች፣ ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከንቲባዎች፣ የብሄር ብሄረሰቦች ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች እንግዶች በተ...
23/11/2023

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማብሰሪያ ዝግጅት አምባሳደሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የፈደራልና የክልል አመራሮች፣ ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከንቲባዎች፣ የብሄር ብሄረሰቦች ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች እንግዶች በተገኙበት በክልሉ መዲና ዎላይታ ሶዶ ከተማ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተካሂዷል። Wolaita Times

ከሶስት ቀናት በኃላ "ደቡብ ኢትዮጵያ" ተብሎ በቅርቡ የተመሰረተው ክልል በይፋ የስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ለሚያካሂደው ከተለያዩ አከባቢዎች የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል የክልሉ መዲና ዎላይታ ...
21/11/2023

ከሶስት ቀናት በኃላ "ደቡብ ኢትዮጵያ" ተብሎ በቅርቡ የተመሰረተው ክልል በይፋ የስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ለሚያካሂደው ከተለያዩ አከባቢዎች የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል የክልሉ መዲና ዎላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በየአካባቢው በማስቀመጥ እየተጠባበቁ ይገኛሉ። Wolaita Times

የኦሮሞ ታጋዮች “ፖለቲካ አያውቁም” ብንባልም ኃያላን ባሉበት ለድርድር ተቀምጠናል" - ጃል ሜሮበኢትዮጵያ መንግሥትና መንግሥት 'ሸኔ' ብሎ የሚጠራው እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ ከሚጠ...
20/11/2023

የኦሮሞ ታጋዮች “ፖለቲካ አያውቁም” ብንባልም ኃያላን ባሉበት ለድርድር ተቀምጠናል" - ጃል ሜሮ

በኢትዮጵያ መንግሥትና መንግሥት 'ሸኔ' ብሎ የሚጠራው እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ ከሚጠራው መካከል ላለፉት 10 ቀናት እየካሄደ የዘለቀው የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ በታንዛንያ የሚገኘው የጦሩ ዋና አዛዥ ኩምሳ ድሪባ (ጃል ሜሮ) ስለሁኔታው ለመጀመሪያ ጊዜ ለደጋፊዎቹ ሀሳብ ሰጥተዋል።

ዋና አዛዥ ጃል መሮ ከአገር ሲወጣ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን በማስረዳት ዝርዝር መረጃ ቢቢሲ እንደሚከተለው ያተተው ዜና ልንክ በኮሜንት መስጫ ተቀምጧል።👇

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር ከዎላይታ ሶዶ ከተማ እና አካባቢው ማህበረሰብ ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ ናቸው።ርእሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በክልሉ የማብሰሪያ ፕሮግራም ቅድመ ዝግ...
20/11/2023

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር ከዎላይታ ሶዶ ከተማ እና አካባቢው ማህበረሰብ ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ ናቸው።

ርእሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በክልሉ የማብሰሪያ ፕሮግራም ቅድመ ዝግጅት ላይ አፅንኦት የሰጡት ሲሆን በስራ እና ፍቅር ወደ ፊት እንሄዳለን ሲሉም ተናግረዋል።

አቶ ጥላሁን ክልሉ ተመስርቶ ይስራ ጀምረናል በይፋ ታሪኳዊ የማብሰሪያ ቀኑን በጋራ እናበስራለን ሲሉም ተናግረዋል።

ይበልጥ መቀራረብ እና አብሮ በመስራት ከምስረታው ማግስት ጀምሮ ህዝቡን የለውጥ ማእከል በማድረግ ብልፅግናችንን እያረጋገጥን ነው ያሉት ክቡር ርእሰ መስተደድር አቶ ጥላሁን ከበደ።

የዎላይታ ዞን አስተዳደሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ይፋዊ የክልል ማብሰሪያ ፕሮግራም ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ እንግዶች እየተጠበቁ እንደሚገኝ አቶ ሳሙኤል አስረድተዋል።

በአሁኑ ሰአት የመድረኩ ተሳታፊዎች የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ በሚሰጡት አስተያየት ላይ እየገለፁ ይገኛሉ ስል የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

በዎላይታ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ባለፉት አራት አመታት "በቅርቡ ይሰራሉ" ተብሎ በዲዛይን ደረጃ ተበልቶ ለምን ቀሩ❓👉በዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ለድዛይን ብቻ በርካታ ገንዘብ ወጥተው ይፋ የተደረጉ...
19/11/2023

በዎላይታ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ባለፉት አራት አመታት "በቅርቡ ይሰራሉ" ተብሎ በዲዛይን ደረጃ ተበልቶ ለምን ቀሩ❓

👉በዎላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ለድዛይን ብቻ በርካታ ገንዘብ ወጥተው ይፋ የተደረጉ👇

♦️ አባላ አባያ Summer city፣

♦️ የዩንቨርስቲው ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣

♦️ የአረካ የግብርና ልህቀት ማዕከል፣

♦️ የቦዲቲ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከልና ሌሎች በርካታ ፕሮጀክቶች ለህብረተሰቡ "በቅርቡ ተጀምሮ ለአገልግሎት እንዲበቁ እናደርጋለን" ተብሎ ለፕሮጀክቱ ጥናትና ድዛይን በርካታ ሚሊዮን ገንዘብ ከመንግስት ካዝና በግለሰቦች ወጪ ተደርጎ ተሰርቶ ይፋ ቢደረግም ወደ ተግባር ሊቀየር አልቻለም።

👉 እንዲሁም በዎላይታ ዞን አስተዳደርና አጋሮቹ ባለፉት 4 አመታት ከንግግር ያላለፉ ለድዛይን ብቻ በርካታ ገንዘብ የወጣበት ፕሮጀክት ምንድነው❓👇

🔴 የዎላይታ የቀድሞ ነገስታት መታሰቢያ ሀውልት፣

🔴 የአየር ማረፍያ ግንባታ፣

🔴 የወይቦ መስኖ ፕሮጀክት ግንባታ፣

🔴 ስራ ሳይጀምር በጠቅላይ ሚኒስቴሩ የተመረቀው የዳቦ ፋብርካ፣

🔴 ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ በሶዶ ከተማ ይገነባል የተባለው የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ግንባታ፣

🔴 ዘመናዊ የመርካቶ ገበያ ማዕከል ግንባታ፣

🔴 መለስተኛ እንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ፣

🔴 ለምርጫ ቅስቀሳ ዜና የተሰራው ከግብርና ኮሌጅ እስከ ሌዊ/ኮካቴ የሚገነባው የመንገድ ግንባታ፣

🔴 በየከተማ አስተዳደርና ወረዳዎች "በቅርቡ ይጠናቀቃል" በሚል ለህዝብ ቃል ተገብቶ መሠረት ድንጋይ የተቀመጡና ሌሎች በርካታ ፕሮጀክቶች ለህብረተሰቡ "በቅርቡ ተጀምሮ ለአገልግሎት እንዲበቁ እናደርጋለን" ተብሎ ይፋ ቢደረግም ከቃል አላለፉም።

ከላይ የተጠቀሱ ችግሮች መንሰኤ "ጠንካራ መዋቅር እውን ባለመደረጉ፣ እውነተኛ የህዝብ ተወካዮችና ከግል ጥቅም ይልቅ የህዝብ ውግንና ያላቸው እንዲሁም ህብረተሰቡን ለልማት ማነሳሳትና ማሳተፍ የሚችል ቁርጠኛ አመራሮች ከማዕከላዊ መንግስት ጋር ያለማንም ጠልቃ ገብነት ቀጥታ ግንኙነት ባለማድረጋቸው ስለመሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ።

በዚህ ጉዳይ ላይ እርሶዎ የችግሩ መንሰኤ ምን ይላሉ ❓መፍትሔውስ❓ Wolaita Times

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ያለአግባብ ምላሽ ሳያገኝ የታፈነው የዘይሴ ብሔረሰብና ሕዝብ የልዩ ወረዳ አስተዳደራዊ መዋቅር ጥያቄ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሕገ መንግስቱ መሰረት እንዲፀድቅ ጥያቄ ቀረ...
17/11/2023

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ያለአግባብ ምላሽ ሳያገኝ የታፈነው የዘይሴ ብሔረሰብና ሕዝብ የልዩ ወረዳ አስተዳደራዊ መዋቅር ጥያቄ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሕገ መንግስቱ መሰረት እንዲፀድቅ ጥያቄ ቀረበ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ ከተማ በሆነችሁ ዎላይታ ሶዶ ከተማ ከዘይሴ ጭቁኑ ብሔረሰብ የተውጣጡ የማኅበረሰቡ አካላት ሰለማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።

ዘይሴ ብሔረሰብና ሕዝብ ከ1987 ዓ.ም. ጀምሮ በሰፈረበት መልክአ ምድር ራሱን በራሱ ለማስተዳደር ሲል የቀድሞውን የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 39(3)፣ አንቀጽ 88(1) እና በቀድሞው የደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 45(2) መሠረት የልዩ ወረዳ አስተዳደራዊ መዋቅር ጥያቄን እጅግ በሰላማዊ መንገድ በተደጋጋሚ ለበርካታ ዓመታት ማቅረቡ የሚታወቅ ነው።

በዚህም ምክንያት የክልሉ መንግሥት በብሔረሰቦች ምክር ቤት በኩል በ2011 ዓ.ም. ሳይንሳዊ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ አዲስ በሚዋቀረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ምላሽ ይሰጥበታል በማለት ለዘይሴ ብሔረሰብና ሕዝብ አዎንታዊ ምላሽ መሰጠቱ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ በወቅቱ በተመሳሳይ ጊዜ ከዘይሴ ብሔረሰብ ጋር የመዋቅር ጥያቄ የተጠናላቸው የወንድም ቀቤና፣ ማረቆ፣ እና የጠምባሮ ብሔረሰቦች አዲስ በተመሠረተው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የልዩ ወረዳ አስተዳደራዊ መዋቅር በጥያቄያቸው መሠረት የፀደቀላቸው ሲሆን የዘይሴ ብሔረሰብ ጥያቄ አዲስ በተደራጀው የደቡብ ኢትዮጽያ ክልላዊ መንግስት ሥር ይፀድቃል ተብሎ ሲጠበቅ ቆይቶ ያለአግባብ ኢ-ሕገመንግታዊ በሆነ መንገድ በመታፈኑ ምክንያት ሕዝቡ እጅጉን አዝኗል።

ራስን በራስ ማስተዳደር የአንድ ሕዝብ ሕገ መንግሥታዊና ተፈጥሯዊ የሆነ የእኩልነት መብት መሆኑን የዓለም አቀፍ ህጎች፣ የኢፈዴሪ እና የክልሉ ሕገ መንግሥታት ይደነግጋሉ።

ይህንንም ተከትሎ በትናንትው ዕለት በቁጥር ከ1000 በላይ የሚሆኑ የዘይሴ ብሔረሰብና ሕዝብን የወከሉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የጎሳ መሪዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ወጣቶች እና ሴቶች የክልሉ ርዕሰ ከተማ ወደ ሆነችው ዎላይታ ሶዶ በማቅናት ከ30 ዓመታት በላይ ያስቆጠረውን የልዩ ወረዳ ጥያቄያቸው አሁንም በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እና በቅርቡ የምሥረታ ሥነ-ሥርዓቱ በሚካሄደው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ያለምንም ቅደመ ሁኔታ በሕገ መንግሥቱ መሠረት እንዲፀድቅላቸው ጥያቄያቸውን ለክልሉ የመንግሥት አካላት አቅርበዋል።

Address

S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wolaita Times:

Videos

Share