EyohaMedia

EyohaMedia Official Page of EyohaMedia, The premier destination to watch and share original videos related to Ethiopia.
(103)

በአዲስ አበባ ከኮሪደር ስራው ጋር በተያያዘ ከመገናኛ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ ከሃያት ሆስፒታል በኋላ ከነገ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ሙ...
28/06/2024

በአዲስ አበባ ከኮሪደር ስራው ጋር በተያያዘ ከመገናኛ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ ከሃያት ሆስፒታል በኋላ ከነገ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ሙሉ ቀንና ምሽትን ጨምሮ ለማንኛውም አይነት ተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረግ ተገልጿል።

አሽከርካሪዎች ሃያት ሆስፒታል ጋር ሳይደርሱ በፊት እና ከሆስፒታሉ አጠገብ ያሉትን የቀኝ መታጠፊያዎችን እንዲጠቀሙ የአ/አ ከተማ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ጥሪ አቅርቧል።

ኢትዮጵያ ገብተዋል   | ናይጄሪያዊው የቀድሞ እግርኳስ ኮከብ ካኑ በቀጣይ ቀናት በሚክያሄደው የሸነን አፍሪካ ፌስቲቫል ላይ ለመሳተፍ ኢትዮጵያ ገብቷል::የቱሪዝም ሚንስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫ...
28/06/2024

ኢትዮጵያ ገብተዋል
| ናይጄሪያዊው የቀድሞ እግርኳስ ኮከብ ካኑ በቀጣይ ቀናት በሚክያሄደው የሸነን አፍሪካ ፌስቲቫል ላይ ለመሳተፍ ኢትዮጵያ ገብቷል::
የቱሪዝም ሚንስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ አቀባበል አድርገውለታል::
ከካኑ በተጨማሪ ሄንሪ ካማራ፣ ኢማኑኤል አሞካቺ እና በርካታ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋቾች ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል::
በፌስቲቫሉ የውጭ ሀገራት የእግር ኳስ ተጫዋቾች፣ተዋናዮች፣ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ ዲዛይነሮች፣ ሞዴሎች፣ የቴክኖሎጂ ባለሞያዎች፣ ባለ ሃብቶች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም በሌሎች የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ግለሰቦች ይሳተፉሉ።

መንግስት በቢራና በትንባሆ ምርቶች ላይ የጣለውን ኤክሳይዝ ታክስ በመከለስ ከዚህ ቀደም ከነበረዉ የክፍያ ምጣኔ ላይ ጭማሪ አደረገየገንዘብ ሚኒስቴር በቁርጥ በተጣለ የኤክሳይዝ ታክስ ማስከፈያ ...
27/06/2024

መንግስት በቢራና በትንባሆ ምርቶች ላይ የጣለውን ኤክሳይዝ ታክስ በመከለስ ከዚህ ቀደም ከነበረዉ የክፍያ ምጣኔ ላይ ጭማሪ አደረገ
የገንዘብ ሚኒስቴር በቁርጥ በተጣለ የኤክሳይዝ ታክስ ማስከፈያ ምጣኔ ላይ ባደረገው ማስተካከያ በቢራ ፣ የትንባሆ እንዲሁም የፕላስቲክ ከረጢት ምርቾች ላይ ጭማሪ አድርጓል።
ከአንድ ዓመት በኃላ በተከለሰዉ የኤክሳይዝ ታክስ ላይ ውሃን ሳይጨምር ቢያንስ ከክብደቱ 75% የሚያህለው በአገር ውስጥ ግብዓት የተመረተ ቢራ 30% ወይም 21 ብር በሊትር ከሁለቱ ከበፊቱ 30% ወይም 8 ብር በሊትር ጭማሪ ተደርጎበታል ።
የሚፈሉ መጠጦች (ሲዳር፣ ፔሪ፣ ኦፓክ ቢራ፣ የሩዝ አልኮል መጠጥ)፣ የሚፈሉ መጠጦችና የአልኮል አልባ መጠጦች ድብልቅ፣ ስታውት፣ ሌሎች ከቢራ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ መጠጦች፣ ዱቄት ቢራ፣ የአልኮል ይዘታቸው ከ7% ያልበለጠ 40% ወይም 28 ብር በሊትር ሲሆን ከበፊቱ 80 በመቶ ጭማሪ ያሳየ መሆኑ ተመላክቷል። ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ተመርቶ በበቀለ ገብስ የተመረተ ቢራ 35% ወይም 23 ብር በሊትር እንደሆን ሲደረግ ከበፊቱ 35% ወይም 9 ብር በሊትር ብልጫ አሳይቷል።
ከዚህ ቀደም 20 ፍሬ ሲጋራ ሰላሳ በመቶ እና 5 ብር የነበረዉ የክፍያ መጠን በተሻሻለው መመሪያ ሰላሳ በመቶ እና 20 ብር ሲሆን ሌሎች የትንባሆ ምርቶች በኪሎ ግራም ሰላሳ በመቶ እና 250 ብር ከነበነረበት ወደ ሰላሳ በመቶ እና 644 ብር እንዲሆን ተደርጓል። በተመሳሳይ የፕላስቲክ ከረጢት (ፌስታል) 40 ብር በኪሎግራም የነበረዉ 103 ብር መሆኑን ካፒታል ከመመሪያው መመልከት ችሏል።
(Capital)

በአዲስ አበባ የሚታየው የነዳጅ እጥረት በቀጣይ ቀናት እንደሚፈታ የኢትዮጵያ የነዳጅ አቅራቢዎች ድርጅት አሳውቋል።የነዳጅ እጥረት በከተማዋ መከሰቱን የገለጸው ድርጅቱ " እጥረቱ ያጋጠመው በዒድ...
27/06/2024

በአዲስ አበባ የሚታየው የነዳጅ እጥረት በቀጣይ ቀናት እንደሚፈታ የኢትዮጵያ የነዳጅ አቅራቢዎች ድርጅት አሳውቋል።

የነዳጅ እጥረት በከተማዋ መከሰቱን የገለጸው ድርጅቱ " እጥረቱ ያጋጠመው በዒድ አል አድሃ አረፋ በዓል ምክንያት እሑድ ሰኔ 9 በማግሥቱ ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ/ም ነዳጅ ከጂቡቲ ባለመጫኑ ነው " ብሏል።

የነዳጅ ማጓጓዝ ሒደቱ አምስት እና ስድስት ቀናትን የሚወስድ መሆኑንና አሁን የሚስተዋለው እጥረት በመጪዎቹ ቀናት እንደሚፈታ አሳውቋል።

ከሱሉልታ መጠባበቂያ ቤንዚን ከአዋሽ መጠባበቂያ ደግሞ ናፍጣ እየተጓጓዘ መሆኑንም በማመልከት የነዳጅ ችግሩ በእርጠኝነት በ2 ቀናት እንደሚፈታ ተናግሯል።

በየተለያዩ የነዳጅ ማደያዎች ላይ ከሚታየው የነዳጅ እጥረት ባለፈ ማደያዎች ነዳጅን ከተጠቃሚዎች እንደሚደብቁ አሽከርካሪዎች ለሪፖርተር በሰጡት ቃል ገልጸዋል፡፡

ሕገወጥ በሆነ መንገድ በውኃ ፕላስቲኮች ጭምር የሚሸጡ መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡

በዚህም ምክንያት ባለፉት ሳምንታት በመዲናዋ ነዳጅ ለመቅዳት የሚጠብቁ ረዣዥም የተሽከርካሪ ሠልፎች መታየታቸውንና አሁንም እጥረቱ እንዳለ አክለዋል፡፡ #ሪፖርተር

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሰኔ 17/2016 ዓ/ም አንዲት መና ከበደ የተባለች የ26 ዓመት ወጣት ሴትን በመኪና ስርቆት ወንጀል በመጠርጠር በቁጥጥር ስር አውሏል።ፖሊስ፥ ግለሰቧ ጥዋት 12:30 ገደ...
27/06/2024

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሰኔ 17/2016 ዓ/ም አንዲት መና ከበደ የተባለች የ26 ዓመት ወጣት ሴትን በመኪና ስርቆት ወንጀል በመጠርጠር በቁጥጥር ስር አውሏል።

ፖሊስ፥ ግለሰቧ ጥዋት 12:30 ገደማ ' ቤተል ቢጫ ፎቅ ' አካባቢ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-B32912 አ.አ የሆነች ተሽከርካሪን የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤቱ ደጃፍ ላይ ሞተር ሳያጠፋ አቁሞት ጃኬት ለመደረብ በገባበት ይዛ መሰወሯንና ከግማሽ ቀን ፍለጋ በኋላ ሰሚት አካባቢ መያዟን አስረድቷል።

ፖሊስ ግለሰቧንም ከነተሽከርካሪው ፎቶ በማንሳት አሰራጭቷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ግለሰቧን እናውቃታለን ያሉ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ፤ መኪናውን መውሰድ አለመውሰዷን በግልጽ ባያሰፍሩም የሃብታም ልጅ እንደሆነች ፣ ስህተት እንደተፈጠረና ከወንጀሉ ነጻ ተብላ ወደ ቤት መግባቷን ጽፈዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይፋ ባደረገው መረጃ በተሽከርካሪ ስርቆት የተጠረጠረችው ግለሰብ መና ከበደ ክስ እንደተመሰረተባት አሳውቋል።

በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት መቅረቧንም አመልክቷል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ግለሰቧ ተሽከርካሪውን በመስረቋ ፓሊስ ምርመራ አጣርቶ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ልኮ ክስ እንዲመሰረትባት ማድረጉን አስረድቷል።

" በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ' ግለሰቧ ተለቃለች ' እና ' ወንጀሉን ሳታውቅ ነው የፈፀመችው ' የሚሉ መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛል " ያለው ፖሊስ የግል ተበዳይ መኪናቸው መሰረቁን ለፖሊስ እንዳመለከቱ ግለሰቧም ተሽከርካሪውን ለረጅም ሰዓት ይዛ መሰወሯ ታሳቢ በማድረግና ድርጊቷም በማስረጃ በመረጋገጡ ዓቃቤ ህግ በተሽከርካሪ ስርቆት ክስ መመስረቱን አሳውቋል።

አርቲስት አብርሐም ወልዴ በኢትዮጵያ ውስጥ ከተከፈሉ ክፍያዎች ሁሉ ትልቁ ክፍያ ተከፍሎት አምባሳደር ሆነከ30 አመት በፊት ወደ ቤት ግንባታ ገብቶ በርካታ የመኖሪያ ቤቶችን በመሥራት ለቤት ፈላ...
26/06/2024

አርቲስት አብርሐም ወልዴ በኢትዮጵያ ውስጥ ከተከፈሉ ክፍያዎች ሁሉ ትልቁ ክፍያ ተከፍሎት አምባሳደር ሆነ
ከ30 አመት በፊት ወደ ቤት ግንባታ ገብቶ በርካታ የመኖሪያ ቤቶችን በመሥራት ለቤት ፈላጊዎች ያሥረከበው ጊፍት ሪል ስቴት በዛሬው ዕለት ሰኔ 19/2016 ዓ/ም ተወዳጁን አርቲስት አብርሐም ወልዴን ለሶስት አመት በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አርቲስቶች ከተከፈላቸው በላይ ትልቁን ክፍያ ከፍሎ የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ።
በፕሮግራሙ ላይ ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
አብርሐም ወልዴ ጊፍት ሪልስቴትን አሁን ካለበት ስሙ ከፍ ለማድረግ እና ለማስቀጠል ኃላፊነትን ተቀብሎ ተፈራርሟል።
አርቲስት አብርሐም ወልዴ በመልዕክቱ ጊፍት የምኮራበትና ምርጫዬ ስለሆነ በደስታ ነው አምባሳደርነቴን የተቀበልኩት ስለመረጣችሁኝ ሁላችሁንም አመሠግናለሁ የተጣለብኝን አደራም በብቃት ለመወጣት በብቃት እወጣለሁ። ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

የጀበና ቡና የምታፈላው የ3 ሚሊዮን ብር ሎተሪ እድለኛ ሆነችየአዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ለምለም ሽፈራው የጀበና ቡና በመሸጥ የሚተዳደሩ ሲሆን ሲበዛ ደጋግመው ሎተሪ የመቁረጥ ልምድ አላ...
26/06/2024

የጀበና ቡና የምታፈላው የ3 ሚሊዮን ብር ሎተሪ እድለኛ ሆነች
የአዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ለምለም ሽፈራው የጀበና ቡና በመሸጥ የሚተዳደሩ ሲሆን ሲበዛ ደጋግመው ሎተሪ የመቁረጥ ልምድ አላቸው ፡፡ ታዲያ እንደተለመደው የሎተሪ አዟሩው ቡና በሚያፈሉበት ቦታ ድረስ በመሄድ የልዩ ሎተሩ ቲኬት እንዲገዙት ይሰጣቸዋል ዕድልም ከሳቸው ነበረችና በገዙት ሙሉ ዕጣ የ3 ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሆነዋል ፡፡ ወ/ሮ ለምለም የሁለት ልጆች እናት ሲሆኑ ገንዘብ በሚያስፈልገኝ ጊዜ የሎተሪ ዕድል ደረሰልኝ በማለት በደስታ ገልጸዋል ፡፡

የተለያዩ  የመኪና ባትሪዎችን ሲሰርቁ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀየተለያዩ  የመኪና ባትሪዎችን ሲሰርቁ የነበሩ ተጠርጣሪዎች  በቁጥጥር ስር ው...
26/06/2024

የተለያዩ የመኪና ባትሪዎችን ሲሰርቁ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ
የተለያዩ የመኪና ባትሪዎችን ሲሰርቁ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሰሚት ንጋት የጋራ መኖሪያ ቤት (ኮንዶምኒየም )ግቢ ውስጥ ሁለት የተሽከርካሪ ባትሪዎችን በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 76991 አ/አ ሚኒባስ ተሽከርካሪን በመጠቀም ሰርቀው ለማምለጥ ሲሞክሩ አንዱ ተጠርጣሪ ከነ ኤግዚቢቱ በስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ እንደተያዘና ሁለቱ ደግሞ ፖሊስ ባደረገው ምርመራ እና ክትትል በቁጥጥ ስር መዋላቸውን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የበሻሌ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከዚህ ቀደም የሰረቁትን ንብረት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሚገኘው ወንድማቸው መኖሪያ ቤት አከማችተው መገኘቱን እና በዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳትፎ ያላቸው አራት ተጠርጣሪዎችን ፖሊስ ጣቢያው በቁጥጥር ስር አውሎ የተለያዩ የተሽከርካሪ ባትሪዎችን በኤግዚቢትነት ይዞ ምርመራውን አጠናክሮ መቀጠሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡
የተሽከርካሪ ባትሪ ተሰርቆብኛል የሚል ግለሰብ ሆነ ተቋም በሻሌ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመሄድና ትክክለኛ ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መረከብ እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
(አዲስ አበባ ፖሊስ)

ተሽከርካሪ ሰርቃ የተሰወረችው ግለሰብ በሰዓታት  ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለች***ተጠርጣሪዋ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመችው ሰኔ  17 ቀን 2016 ዓ.ም  በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ...
25/06/2024

ተሽከርካሪ ሰርቃ የተሰወረችው ግለሰብ በሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለች
***
ተጠርጣሪዋ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመችው ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ቢጫ ፎቅ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡
በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ከቤተል አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በወቅቱ በግምት ከጠዋቱ 12:30 ሰዓት ገደማ የግል ተበዳይ በስፍራው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-B32912 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪያቸውን መኖሪያ ቤታቸው በር ላይ ሞተር አስነስተው እያሞቁ የነበሩ ሲሆን ወደ ስራ ለመሄድ ጃኬት ሊደርቡ ወደ ቤት በገቡበት ቅስፈት ተሽከርካሪያቸውን ከቆመበት ቦታ እንደሌለ አረጋግጠው ለፖሊስ ሪፖርት ያደርጋሉ።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አቤቱታው ከደረሰው ሰዓት ጀምሮ ተሰውሮ የነበረውን ተሽከርካሪ ለማግኘት ግማሽ ቀን በፈጀ ጠንካራ ክትትልና መረጃ የማሰባሰብ ሥራ ተጠርጣሪዋን ከነተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር አውሏታል።
ግለሰቧ የግል ተበዳይ ወደቤት በገቡበት ቅስፈት ተሽከርካሪውን አስነስታ ብትሰወርም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ልዩ ቦታው ሰሚት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በግምት ከቀኑ 9 ሰዓት ገደማ ከነተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውላለች ። የተለያዩ ዘዴዎችንን በመጠቀም የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ የሁሉም ስው ኃላፊነት መሆኑን ያሳሰበው ፖሊስ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ መኪናቸውን አቁመውና የተሽከርካሪውን ቁልፍ በውስጡ ትተው በሚሄዱበት አጋጣሚ ለተመሳሳይ የስርቆት ወንጀል ሊዳረጉ ስለሚችሉ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል
(ዘገባ ፦ ዋና ሳጅን ዘላለም አበበ -አ/አ ፖሊስ)

የአዕምሮ ህመምተኛ በመምሰል እና ሌሎች ዘዴዎችን በመፈፀም የመኪና ዕቃ ሰርቀዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ ተያዙ፡፡ አንደኛው ግለሰብ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ወንጀል ተጠርጥሮ  በፍ...
25/06/2024

የአዕምሮ ህመምተኛ በመምሰል እና ሌሎች ዘዴዎችን በመፈፀም የመኪና ዕቃ ሰርቀዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ ተያዙ፡፡ አንደኛው ግለሰብ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ወንጀል ተጠርጥሮ በፍርድ ቤት በዋስትና የተለቀቀ መሆኑ ታውቋል፡፡
***
የመኪና ዕቃ ስርቆትና ሌሎች ወንጀሎችን ለመከላከል ፖሊስ እያከናወነው ያለው ተግባር ምቹ ሁኔታ ያሳጣቸው አንዳንድ ወንጀል ፈፃሚዎች ከፖሊስ ጥርጣሬ ውጪ ለመሆን በማሰብ የተለያዩ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ ወንጀል ለመፈፀም እንደሚንቀሳቀሱ ታውቋል፡፡ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 ነዋሪ መሆኑን በኪሱ ውስጥ የተገኘው የነዋሪነት መታወቂያ የሚያስረዳው አንደኛው ተጠርጣሪ ፈፅሟል የተባለው ወንጀል የዚህ ማሳያ ነው፡፡
ግለሰቡ የአዕምሮ ህመምተኛ መስሎ እየተንቀሳቀሰ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ፊጋ አካባቢ መሲ ህንፃ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ቆሞ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2- C34174 አ.አ ከሆነ ተሽከርካሪ ላይ የግራ ስፖኪዮ መስታወት ነቅሎ ለማምለጥ ሲሞክር እጅ ከፍንጅ እንደተያዘ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር አባይ ወርቁ ገልፀዋል፡፡
እራሱን የአዕምሮ ህመምተኛ በማስመሰል ከተጠያቂነት ለማምለጥ ጥረት አድርጎ ያልተሳካለት ይኸው ግለሰብ ሚያዚያ 3 ቀን 2016 ዓ/ም በዚሁ ክፍለ ወረዳ 8 ሰሚት ሳፋሪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የዋጋ ግምቱ 60 ሺ ብር የሚያወጣ የተሽከርካሪ ስፖኪዮ ሰርቆ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በፍርድ ቤት በመዋስትና መለቀቁን እና የተለያዩ ስሞችን እንደሚጠቀም ኢንስፔክተር አባይ አስረድተዋል፡፡ በተጠርጣው ላይ የምርመራ መዝገብ ተደራጅቶ ጉዳዩ በህግ አግባብ እየታየ እንደሚገኝም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በተመሳሳይ ዜና አንዲት ግለሰብ ቤተ ክርስቲያን የመጣች በመምሰል ነጠላ ለብሳ የመኪና ዕቃ ስርቆት ስትፈፅም እጅ ከፍንጅ ተይዛለች፡፡
ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን ፈፅማለች የተባለው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ነው፡፡
በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ከቤተል አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው እሌኒ ታደሰ የተባለችው ግለሰብ ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 8 ሰዓት ገደማ ቤተክርስቲያን የመጣች በመምሰል ነጠላ ለብሳ እየተንቀሳቀሰች በአካባቢው ቆሞ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2- C49561 አ.አ ከሆነ ተሽከርካሪ ላይ 16 ሺህ ብር የዋጋ ግምት ያለው ስፖኪዮ ነቅላ ለመሰወር ስትሞክር በፖሊስ አባላትና በህብረተሰቡ ትብብር እጅ ከፍንጅ ተይዛለች፡፡
ወንጀል ፈፃሚዎች በየጊዜው ልዩ ልዩ ስልቶችን በመቀያየር ወንጀል እንደሚፈፅሙ ተገንዝቦ ተገቢውን የመከላከል ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ያስታወሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ህብረተሰቡም ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገበት በግሉ ለሚወስደው የጥንቃቄ እርምጃ ትኩረት መስጠት እንዳለበት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

አሳካሚ አጥታ የነበረችዋ የሀገር ባለውለታዋ ቦክሰኛ ልበ ቀና አሳካሚዎች አገኘችምክትል ሳጅን ቤተልሔም ገዛኸኝ በጋና አክራ በተካሄደው 13ኛው መላው አፍሪካ ጨዋታ ለሃገሯ የወርቅ ሜዳሊያ በማ...
25/06/2024

አሳካሚ አጥታ የነበረችዋ የሀገር ባለውለታዋ ቦክሰኛ ልበ ቀና አሳካሚዎች አገኘች

ምክትል ሳጅን ቤተልሔም ገዛኸኝ በጋና አክራ በተካሄደው 13ኛው መላው አፍሪካ ጨዋታ ለሃገሯ የወርቅ ሜዳሊያ በማምጣት በታሪክ መዝገብ ስሟን ሰንዳለች። ቤተልሔም በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የማንዴላ ካፕ ውድድር ላይ ባጋጠማት የትከሻ ውልቃት ምክንያት በውድድሩ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ መሆኗ ይታወቃል።

ይቺ ብርቅዬ ልጅ ለሃገሯ የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘችው ቦክሰኛ የሚያሳክማት አጥታለች የእኛን ድጋፍ ትሻለች የሚል የእርዳታ መልዕክት በሶሻል ሚዲያ መለቀቁ የሚታወቅ ነው። ለእዚህም ለሕክምና ወጪ የሚያሥፈልጋት እና የተጠየቀችው 500,000 ( አምስት መቶ ሺህ ብር መሆኑ ተገልጾ ነበር።

ቤተልሔም ትላንት የሚያሳክማት አጥታ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ላይ ግን ደጋግና ቀና ኢትዮጵያውያን አለንልሽ ብለዋት እርብርብ ጀምረዋል። ከደጋግ ኢትዮጵያውያንና ድጋፍ ካደረጉላት መካከልም አዋጭ የገንዘብ ቁጠባ 100,000 ብር ፣ ብርሀን ባንክ 150,000 ብር ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ 150,000 ብር እንዲሁም ሂል ቬንቸር የውስጥ ደዌ እና የቀዶ ህክምና ማዕከል ቀሪውን ብር በመሸፈን እስከምትድን ድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል በመግባት እና በመስጠት የሚያሥፈልጋትን በሙሉ አሟልተውላታል።

ም/ሳ ቤተልሄም ገዛኸኝም እገዛ ያደረጉላትን በሙሉ አመስግና በቀጣይም ስትድን የሀገሯን ስም እንደምታስጠራ ቃል ገብታለች።

"የዉጪ ባለሃብቶች በባንክ ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ ያስችላል የተባለዉ ረቂቅ አዋጅ ሀገሪቷን በድጋሚ በኢኮኖሚ በበለፀጉ ሀገራት ተፅዕኖ ስር እንዳያደርጋት ስጋት አለኝ " አምባሳደር ዲና ሙፍቲስ...
25/06/2024

"የዉጪ ባለሃብቶች በባንክ ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ ያስችላል የተባለዉ ረቂቅ አዋጅ ሀገሪቷን በድጋሚ በኢኮኖሚ በበለፀጉ ሀገራት ተፅዕኖ ስር እንዳያደርጋት ስጋት አለኝ " አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ስለ ባንክ የስራ ፍቃድ እና የዉጪ ዜጎች በባንክ ዘርፍ ላይ ስለሚሳተፉበት ሁኔታ በዝርዝር ያስቀመጠው እና በአዲስ መልክ መዘጋጀቱ የተነገረለት "የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅ" ሀገሪቷን ነፃ ወጥተው ነገር ግን ከቅኝ ገዢዎች በኢኮኖሚ የበላይነት ያልተላቀቁና በእዛ ተፅዕኖ ስር እንዳሉ የአፍሪካ ሀገራት እንዳያደርጋት ስጋት እንዳላቸው አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል ።

አምባሳደሩ ይህን ያሉት የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ በመራበት ወቅት ነዉ።
በሀገሪቷ እንዳንድ ዘርፎች ( ባንክን ) ጨምሮ ከዉጪ ኢንቨስተሮች ለተወሰነ ጊዜ ተገሎ የቆየበት የራሱ ምክንያቶች እንዳሉ ያስታወሱት ዲና ሙፍቲ አሁን ከዉጪ የሚገብት ባለሀብቶች በዘርፉ ከፍተኛ ልምድና ቴክኖሎጂ ያካበቱ እንደመሆናቸው ሀገሪቷ አሁን ላይ ያላት አቅም በዚህ ልክ መታየቱን እና ያላትን የአቅም ደረጃ ምን ያህል እንደሆነ እንዲፈተሽ ጠይቀዋል ።
የባንክ ዘርፎቹ በዚህ ፉክክር ዉስጥ ገብተውና ተወዳድረው የማሸነፍ አቅማቸውና ብቃታቸዉ በአዋጁ እንዲታይ የጠየቁት አምባሳደሩ ይህ ካልሆነ ግን ወደ "ኒዮኮሎኒያልዚም" ወይም በመሰረቱ ነፃ ወጥተዉ ነገር ግን ከቅኝ ግዢዎች በኢኮኖሚ የበላይነት ያልተላቀቁና በዛ ተፅዕኖ ስር እንዳሉት የአፍሪካ ሀገራቱ ኢትዮጵያ ወደዚህ እንዳትመለስ ስጋት አለኝ ብለዋል።
አሁን በስራ ላይ ያለዉ የባንክ ስራ አዋጅ ላለፉት 16 ዓመታት ሲሰራበት የቆየ መሆኑ ይታወቃል ። በቅርቡ በተደረገው የፖሊሲ ሪፎርም ደግሞ የዉጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው ትዉልደ ኢትዮጵያውያን በዘርፉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያስችል ማሻሻያ የተደረገ ሲሆን የባንክ ዘርፉ ለዉጪ ኢንቨስተሮች ክፍት እንዲሆን የሚኒስትሮች ምክርቤት ነሐሴ 8፤2014 ዓ.ም. ነበር።

(Capital)

በተራራማ ስፍራ ለቀናት ጠፍቶ የነበረው ሰው በቀን 4 ሊትር ውኃ እየጠጣ ሕይወቱን ማቆየቱ ተሰማ   | በአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ግዛት ለእግር ጉዞ ወጥቶ ለ10 ቀናት በተራራማ ስፍራ ጠፍቶ የነበ...
25/06/2024

በተራራማ ስፍራ ለቀናት ጠፍቶ የነበረው ሰው በቀን 4 ሊትር ውኃ እየጠጣ ሕይወቱን ማቆየቱ ተሰማ
| በአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ግዛት ለእግር ጉዞ ወጥቶ ለ10 ቀናት በተራራማ ስፍራ ጠፍቶ የነበረው ግለሰብ በቀን እስከ 4 ሊትር ውኃ እየጠጣ ሕይወቱን ማቆየቱ ተሰምቷል።
ሉካስ ማክሊሽ የተባለው ይህ ግለሰብ በካሊፎርኒያ ሳንታ ክሩዝ ተራራማ ቦታ ለሦስት ሰዓታት የእግር ጉዞ ለማድረግ ከወጣ በኋላ ነበር ጠፍቶ የቆየው።
ማክሊሽ ተራራ በመውጣት ልምድ ያለው ቢሆንም በቅርቡ በተራራማ አካባቢው የተነሳው እሳት አቅጣጫ ጠቋሚዎችን በማውደሙ መመለሻው ጠፍቶበት 10 ቀናትን በጫካ ውስጥ ለመቆየት መገደዱ ተጠቅሷል።
በተራራው ስፍራ የእግር ጉዞ ለማድረግ ወጥቶ ሳይመለስ ሲቀር የቤተሰብ አባላት ለፖሊስ ጥቆማ ሰጥተው ለቀናት የቆየ ፍለጋ ሲደረግ መቆየቱም ነው የተገለፀው።
ፖሊስ ማክሊሽን ለማግኘት ሲያደርግ የነበረው ጥረት ተሳክቶ በአሳሽ ድሮን (ሰው አልባ አውሮፕን) እግዛ ግለሰቡ በህይወት ሊገኝ መቻሉ ተጠቁሟል።
ፖሊስ በርካታ ሰዎች የማክሊሽን የድረሱልኝ ጩኸት ቢሰሙም ማክሊሽ ያለበትን ቦታ መለየት አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል ብሏል።
ሉካስ ማክሊሽ በአሳሽ ድሮን እገዛ ከ10 ቀናት በኋላ በህይወት እንደተገኘ ለጋዜጠኖች በሰጠው ቃል፤ በጫማው አማካይነት ውሃ እየሰበሰበ ሲጠጣ እንደነበረ ገልጿል።
“በየቀኑ እስከ 4 ሊትር ውሃ መጠጣቴን እርግጠኛ መሆን ነበረብኝ” ያለው ማክሊሽ፤ የዱር ፍሬዎችን እየለቀመ መብላቱንም ጨምሮ ተናግሯል።
ፖሊስ በርካታ አባላቱን በማሰማራት ለፍለጋ ወጥተው በሕይወት ስለደረሱለት ማክሊሽ ምስጋናውን ማቅረቡን ኤቢሲ ኒውስ ዘግቧል።

የግል ድርጅት የኮንስትራክሽን ብረታ ብረት ሲሰርቁ የነበሩ ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ የተያዙ።ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3:30 ከጥበቃ ሰራተኞች ጋ...
24/06/2024

የግል ድርጅት የኮንስትራክሽን ብረታ ብረት ሲሰርቁ የነበሩ ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ የተያዙ።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3:30 ከጥበቃ ሰራተኞች ጋር በመተባበር በድርጅቱ ኮድ 3 B ሰሌዳ ቁጥሩ AA 55608 በሆነ አይሱዙ መኪና የተለያዩ የኮንስትራክሽን ብረታ ብረት ጭነው ሊሰወሩ ሲሉ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ኢንተለጀንስ ባለሙያዎች እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ታውቋል።

የድርጅቱን ንብረት ለግል ጥቅማቸው ለማዋል ሲሉ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ተጠርጣሪዎች፦
1, ዋ/ሳጅን ገ/እንግዚአብሄር አባይ አባዬ፣
2 , ደረጄ ደባስ አዲና የእናት ባንክ ሳይት የጥበቃ ተቆጣጣሪ፣
3, ታደሰ ወንድም መሰለ የድርጅቱ ጥበቃ፣
4, ጀማል አላላ አሊ የድርጅቱ አይሱዙ መኪና ሹፌር ፣
5, ምሩጽ ኃይሉ በቀለ፣ ሰለሞን ግርማ ዘውዴ፣ ሳሙኤል ቢሳ ጽጌ እና ቢንያም መጋኝ መስቀሌ የተባሉት ተጠርጣሪዎች የድርጅቱን የኮንስትራክሽን ብረታ ብረት መኪና ላይ ሲጭኑ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሲሆን ዋና ሳጅን ገ/እንግዚአብሄር አባይ አባዬ የተባለ ፖሊስ ደግሞ ሕገ-ወጥ ተግባሩ ሲያስተባብር በቁጥጥር ሥር ውሎ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ታውቋል።

(የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ )

ተፈተዋልተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙን እና ታላቁ የቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ ፈይሳን ጨምሮ ሌሎችም ታሳሪዎች ዛሬ ተፈተው ቤተሰቦቻቸው ተቀላቅለዋል።አማኑኤል ፍልፍልቅ ድምጹን በስልክ ሰማሁት...
24/06/2024

ተፈተዋል

ተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙን እና ታላቁ የቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ ፈይሳን ጨምሮ ሌሎችም ታሳሪዎች ዛሬ ተፈተው ቤተሰቦቻቸው ተቀላቅለዋል።

አማኑኤል ፍልፍልቅ ድምጹን በስልክ ሰማሁት። ከጉብኝት የተመለሰ ሰው ይመስል ሳቅ በሳቅ ሆኗል።

"እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!" ያለኝን ቃል ብቻ ይዣለሁ።

*በድጋሚ ይህንን መልዕክት ልኮኛል

"ለተጨነቃችሁልኝ በጸሎት ለረዳችሁኝ ሁሉ ቸር አምላክ ዋስ ጠበቃ ይሁናችሁ!!"
Yared Shumete - ያሬድ ሹመቴ

በሕግ አምላክ‼️   | ህገወጡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምርጫ ከተካሄደ ሁለት ሳምንት ሆኖታል፤ ይህንን ድብቅ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ገፅ ይፋ ካደረኩት በኋላ በብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ...
24/06/2024

በሕግ አምላክ‼️
| ህገወጡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምርጫ ከተካሄደ ሁለት ሳምንት ሆኖታል፤ ይህንን ድብቅ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ገፅ ይፋ ካደረኩት በኋላ በብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል፤ አብዛኞቹ የሚመለከታቸው አካላት ግን ምርጫው የጨረባ መሆኑን እያወቁ ዝምታን መርጠዋል፤ ጥቂቶች ብቻ አደባባይ ወጥተዋል፤ እነማን ምን አሉ? ዝምታን የመረጡትስ ለምን? ቀጣይስ ምን ታስቧል? በጥቂቱ እንቃኘው፦
🔷 ማን ምን አለ?
ምክትል ፕሬዝዳንት ተብሎ የተመረጠው የአትሌቲክሳችን ምልክት ሻለቃ ሀይሌ ገ/ስላሴ ስለ ምርጫው ምንም እንደማያውቅ በወቅቱም ሀገር ቤት እንዳልነበረ፣ ሹመቱን ከሰው መስማቱን ተናግሯል፤ ከሶስት አመት በፊት በሙያህ አገልግል ተብዬ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውስጥ ገብቼ ነበር የሚለው ሀይሌ ሆኖም የማየው ሁሉ ደስ ስላላኝ ውሳኔዎች በጋራ ሳይሆን በግል ሲወሰኑ ስመለከት ለመራቅ ተገደድኩ፥ ከሶስት ስብሰባ በላይ አልተሳተፍኩም ብሏል፤ ጉባኤም ሆነ ምርጫ ከኦሊምፒክ በኋላ መደረግ እንዳለበት የሚናገረው ሀይሌ የአሁኑ ምርጫም ህጋዊ አይደለም ይላል፤ የፓሪስ ውጤት ሳይታይ የኦሊምፒክ ኮሚቴው ስራ ሳይገመገም ተቻኩሎ ምርጫ መደረጉ እንዳስገረመውና ምናልባትም የፓሪስ ውጤታችን ጥሩ ካልሆነ ስለማንመረጥ ሳይቀድሙን እንቅደማቸው ብለው ሊሆን እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል፤ ይህ ምርጫ ተሽሮ በቀጣይ በህጋዊ መንገድ ከተካሄደ ለመወዳደር ማሰቡን ጠቁሟል፤ የእሱን ሹመት በተመለከተ ለኦሊምፒክ ኮሚቴውና ለባህልና ስፖርት ሚንስቴር ማሳወቁን ገልፆ ኸረ በህግ ብሎ መፍትሄ ጠይቋል፤ ሀይሌ ተቃውሞውን ካሰማ በኋላ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ሀይሌን እንዳልመረጠው ቢገልፅም በዕለቱ የተመረጡት የቦርድ አባላት ለተሳታፊዎቹ ይፋ ሲሆኑ ግን የሀይሌ ስም መኖሩን በግል አረጋግጫለሁ
በሌላ በኩል የባህልና ስፖርት ሚንስቴር በማህበራት ጉባኤና ምርጫ ወቅት በታዛቢነት መገኘት ቢኖርበትም በኦሊምፒክ ጉባኤው ላይ ግን እንዳልተጋበዘ ምርጫውንም በሰሚ ሰሚ እንዳወቀ ሚንስትር ዴኤታው አምባሳደር መስፍን ቸርነት ተናግረዋል፤ ምርጫው ህጉን አልተከተለም ብለዋል፤ አያይዘው መንግስት ለቶኪዮ ኦሊምፒክ የሰጠው 156 ሚሊየን ብር ኦዲት እንዲደረግ ለኦሊምፒክ ኮሚቴ ጥያቄ ቢያቀርብም እምቢ መባሉን ገልፀዋል፤ ባህልና ስፖርት ሚንስቴር ከኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር ያለው የስራ ግንኙነት እየተቋረጠ መምጣቱንም አምነዋል
በሌላ በኩል በህገ ወጡ ምርጫ ጀግናው አትሌት ቀነኒሳ በቀለና ወጣቷ ጉዳፍ ፀጋዬ የአትሌቶች ተወካዮች ተብለው ተመርጠዋል፤ ከአትሌቶች ማህበር ባገኘሁት መረጃ አትሌቶቹ በመመረጣቸው ደስተኞች ቢሆኑም ስለ ምርጫው ማህበሩ ምንም እንደማያውቅና አትሌቶቹንም እንዳልወከላቸው አረጋግጠውልኛል፤ ህጉን ያልጠበቀ አካሄድ ነው ብለውኛል
🔷 ምንድነው ዝምታው?
ከጠቀስኳቸው አካላት ውጪ ሌሎች የጉዳዩ ባለቤቶች ዝምታን የመረጡበት ምክንያት አጠያያቂ ሆኗል፤ ኦሊምፒክ ኮሚቴው አሻሻልኩት ባለው ደንብ የምክትል ፕሬዝዳንትነት ቦታን በቀጥታ ያገኘው አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዝምታን ከመረጡት አንዱ ነው፤ ከሶስት አመት በፊት በተካሄደው ምርጫ የተቃውሞ መሪና አሰላፊ የነበረው ፌዴሬሽኑ በዚህ ጉባኤ ተወካይ መላኩን አረጋግጫለሁ፤ ከባለፈው ከተቃወመው ምርጫ የማያንስ የህግ ጥሰት በዚህኛውም የጨረባ ምርጫ ቢከሰትም ፌዴሬሽኑና መሪዎቹ ዝም ጭጭ ብለዋል፤ ስለ ጉዳዩ ለመጠየቅ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ለማግኘት በተደጋጋሚ ጥረት ባደርግም አልተሳካልኝም
ሌላው ዝምተኛ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ነው፤ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ከወር በፊት የደንብ ማሻሻያ ሲያደርግ እንዲሁም ከሁለት ሳምንት በፊት አወዛጋቢውን ምርጫ ሲያከናውን ምንም ጥሪ እንዳልቀረበለት ከፌዴሬሽኑ መረጃ አግኝቻለሁ፤ በምርጫው ላይም ተወካይ አላክንም ብለውኛል፤ ሆኖም ይህንን ህገወጥ ምርጫ በተመለከተ ተቃውሞም ሆነ ድጋፍ እስካሁን በፌዴሬሽኑ በኩል በይፋ አልተሰማም፤ ዝም ብቻ
በምርጫው የተገኙና ያልተገኙ አባል ማህበራት፣ ስማቸው ምርጫው ውስጥ የገባ አመራሮችና ስፖርተኞች እንዲሁም መንግስት ጉዳዩን አይተው እንዳላዩ ማለፋቸው ጥያቄን ያጭራል፤ አንዳንዶቹ የፓሪስ ኦሊምፒክ ይለፍና እንናገራለን ቢሉኝም ይህንን ታላቅ ስህተት ለማረም የታሪክ ተወቃሽም ላለመሆን ትክክለኛው ጊዜ አሁን መሆኑን ግን ማስታወስ ይኖርባቸዋል፤ በርካታ የመንግስትና የግል መገናኛ ብዙሀን በተመሳሳይ ዝምታን መምረጣቸው ያስተዛዝባል፤ እውነትን ፈልጎ ሸፍጥን አጋልጦ ህዝቡ እንዲፈርድ የማድረግ ሙያዊ ሀላፊነት አለባቸው፤ ከሰሞኑ ሸገር ስፖርት ስለ ምርጫው ለሚሰራቸው መሰናዶዎች ግን ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ
🔷 ቀጣይ ምን እንጠብቅ?
ህገወጡን ምርጫ በይፋ የተቃወሙት ሻለቃ ሀይሌ እንዲሁም የባህልና ስፖርት ሚንስቴር በቀጣይ ለማድረግ ያሰቡትን ይፋ አድርገዋል፤ ሀይሌ ይህ ምርጫ ካልተሰረዘ እስከ አለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ድረስ እንደሚሄድ ተናግሯል፤ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱም ለመንግስት አሳውቄ መፍትሄ እፈልጋለሁ ብሏል፤ መቀመጫውን ስዊዘርላንድ ያደረገው አለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ስለ ምርጫው የሚወስነው አልያም የሚያነሳው ጥያቄም በቀጣይነት ይጠበቃል
በኦሊምፒክ ኮሚቴው በኩል ደግሞ ይህንን ምርጫ በይፋ የተቃወሙትን በተለይ ሀይሌና ባህልና ስፖርት ሚንስቴርን እንዲሁም ሌሎች የሚመጡ ካሉ በተከፋይ ተሳዳቢዎቹ አፍ የተቀናጀ የስም ማጥፋት ዘመቻ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ሰምቻለሁ፤ እውነትን በጥቅም የመሸፈን ዘመቻ
🔷 የህግ ያለ የሚያስብሉ ጥሰቶች
በመጨረሻ በሰኔ አራቱ ጉባኤ የተጣሱትን ህጎችና ምርጫው ህገወጥ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎችን በጥቂቱ በድጋሚ እነሆ፦
★ምርጫውን ከሚዲያና ከአንዳንድ አባል ማህበራት በመደበቅ ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ብቸኛ እጩ ሆነው በድብቅ ተመርጠዋል፤ ከአባል ፌዴሬሽኖች አንዳንዶቹ ስለ ጉባኤውና ምርጫው ስለ ተሻሻለው ደንብም ሆነ ስለ እጩዎች መላክ የምናውቀው ጉዳይ አልነበረም፤ ጥሪም አልደረሰንም ብለዋል፥ ለምሳሌ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
★ አሁን ያለው የኦሊምፒክ ኮሚቴ ገና የ10 ወራት የስልጣን እድሜ ቢቀረውም ከህግ ውጭ ራሱን መርጦ በድጋሚ ቆይታውን አራዝሟል፤ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ለዚህ የሚሰጠው ምላሽ ባለፈውም ከቶኪዮ ኦሊምፒክ በፊት ነው ያደረግነው የሚል ነው፤ ያኔም ምርጫው ከኦሊምፒኩ በኋላ መስከረም ላይ እንዲደረግ በጠቅላላ ጉባኤው ቢወሰንም የዶ/ር አሸብር አመራር ከባህርዳርና ከሀዋሳ ምርጫ ማድረግ አትችሉም ተብለው ተሰደው አዲስ አበባ ላይ በር ዘግተው ምርጫ ማከናወናቸው በወቅቱም ብዙ ጫጫታና ሰልፍ እስርና ወከባ ማስተናገዳቸው ይታወሳል
★ የሀገሪቱ የስፖርት ማህበራት ማደራጃ ደንብ በየትኛውም ፌዴሬሽንም ሆነ ማህበር ውስጥ የሚገኝ አመራር ከሁለት የስልጣን ጊዜ ወይም ከስምንት አመት በላይ መመረጥ እንደማይችል ይደነግጋል፤ ፕሬዝዳንቱ ለሶስተኛ ጊዜ ተመርጠው ለሶስተኛ ጊዜ በአወዛጋቢ ሁኔታ ስልጣናቸውን አስቀጥለው ሀትሪክ ሰርተዋል
★ የክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነሮችና የፌዴሬሽን የፅህፈት ቤት ሀላፊዎች በማህበራት ጉባኤዎች ላይ መመረጥና በድምፅ መሳተፍ እንደማይችሉ ገለልተኛ ሆነው ብቻ እንዲሳተፉ የስፖርት ማህበራት ህጉ ይደነግጋል፤ አሁን ግን የክልል ኦሊምፒክ ቅርንጫፎች በሚል በቦርድ አባልነት ገብተዋል፤ የአዲስ አበባ አስተዳደር እንዲሁም የሀረሪና የአማራ ስፖርት ኮሚሽኖች የኦሊምፒክ ኮሚቴ የቦርድ አባል ሆነው ተመርጠዋል፤ የኦሊምፒክ ቻርተሩ የማይፈቅደው መንግስታዊ ተቋማት በኮሚቴው ውስጥ ማካተት ተሽሯል
★ የኦሊምፒክ ስፖርት ያልሆኑ ማህበራት በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውስጥ ድምፅ ሰጪ ተመራጭ አባል ወይም መሪ ሆነው መስራት እንደማይችሉ ሀገራዊው ህግ ያዛል፤ አሁን ግን ከኦሊምፒክ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው የባህል ስፖርቶች የቦርድ አባል ሆኖ ተመርጧል፤ ሌሎችም ህጎች ተጥሰዋል
መልዕክቴ ይህ ነው፦ ስፖርቱ የሁላችንም ነውና ሕግ ይከበር፥ በሕግ አምላክ!!!
(ታምሩ ዓለሙ)

የኢትዮጵያ አይዶል የምዕራፍ ሦስት የፍፃሜ ውድድር አሸናፊዎች    | አሸናፊዎችን 1ሚሊዮን ብር በሚያሸልመው በዚህ ውድድር በድምፅ መብራት ንጉሴ በተውኔት ደግሞ መድሐኒት ዘገየ አንደኛ በመው...
23/06/2024

የኢትዮጵያ አይዶል የምዕራፍ ሦስት የፍፃሜ ውድድር አሸናፊዎች
| አሸናፊዎችን 1ሚሊዮን ብር በሚያሸልመው በዚህ ውድድር በድምፅ መብራት ንጉሴ በተውኔት ደግሞ መድሐኒት ዘገየ አንደኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነዋል።
የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰ የዋንጫ እና የገንዘብ ሽልማቱን ለአሸናፊዎቹ አበርክተዋል።
በተውኔት
1ኛ መድሐኒት ዘገየ
2ኛ ማሪያ ዮሴፍ
3ኛ ፀደኒያ ታፈስ
4ኛ ቅድስት ማሙሽ
በድምፅ
1ኛ መብራት ንጉሴ
2ኛ ሐብታሙ ውበት
3ኛ ምሕረት ረታ
4ኛ በማኔጅመንት ውሳኔ ትደነቅ እንዳለ
ተወዳዳሪዎች ከገንዘብ ሽልማቱ በተጨማሪ የዋንጫ እና የምስክር ወረቀትም ተበርክቶላቸዋል።

የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ፣ ከትላንት በስቲያ  ከአገር ወጥተው አሜሪካ የገቡ ሲሆን፤ ከአገር ለመውጣት የተገደዱት ለደህንነታቸው በመስጋት መሆኑን...
22/06/2024

የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ፣ ከትላንት በስቲያ ከአገር ወጥተው አሜሪካ የገቡ ሲሆን፤ ከአገር ለመውጣት የተገደዱት ለደህንነታቸው በመስጋት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በዛሬው ዕለት ረፋዱ ላይ በስካይፒ ከአሜሪካ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ፤ “የዛሬዋ ቀን ለእኔ ከባድ ናት፤ በግፈኞች ከአገር እንደወጣ በመገደዴ የልጄ ክርስትና ላይ ለመገኘት አልቻልኩም፤” በማለት ነው የጀመሩት፡፡
ባለፈው ሳምንት በተመሳሳይ ሰዓት በፐርፐዝ ብላክ ዋና መሥሪያ ቤት ተገኝተው፣ የኩባንያቸውና የራሳቸው የግል የባንክ ሂሳብ ለ3 ሳምንት ያህል ምክንያቱ ሳይነገራቸው መታገዱን ለጋዜጠኞች ያሳወቁት ዶ/ር ፍስሃ፤ በዚህ ሳምንት ደግሞ ከአሜሪካ ሆነው በደረሰባቸው ማስፈራሪያና ጫና ከአገር ለመውጣት መገደዳቸውን ተናግረዋል፡፡
የኩባንያቸው የባንክ ሂሳብ በማያውቁት ምክንያት ተዘግቶ እንቅስቃሴው መስተጓጎሉን የተመለከተ መግለጫ ለጋዜጠኞች መስጠታቸውን ተከትሎም፣ ብዙ አሳዛኝና ከባድ ነገሮች መከሰታቸውን ጠቁመዋል፤ ዋና ሥራ አስፈጻሚው፡፡
“ክሱ ባይደርሰንም የተዘረዘሩብን ክሶች በጣም የሚያስገርሙ ናቸው” ያሉት ዶ/ር ፍስሃ፤ “በወንጀል የተሰበሰበ ገንዘብ፣ ህገወጥ የመሣሪያ ዝውውር፣ ፋኖዎችን በገንዘብ መርዳት፣ ወዘተ-- የሚሉ ፈጽሞ ከእኛ ጋር የማይገናኙ ወንጀሎች መሆናቸውን ተረድተናል” ብለዋል፤ በመግለጫቸው፡፡
የዘረዘሯቸው ወንጀሎች በሙሉ ዋስትና የማያሰጡ ናቸው ያሉት ዶ/ር ፍስሃ፤ ዛሬ የሚከበረውን የልጄን ክርስትና ትቼ አገሬን ለቅቄ ለመውጣት የተገደድኩት ለደህንነቴ በመስጋቴ ነው፤ ብለዋል፡፡
“ኩባንያችን ሁሉንም ነገር የሚሰራው መቶ ፐርሰንት ህጉን ተከትሎ ነው፤በዚህ በኩል የሚወነጅሉበት ነገር ሲያጡ ነው ጉዳዩን ፖለቲካዊ ያደረጉት፡፡” ይላሉ፤ ሥራ አስፈጻሚው፡፡
ሆኖም የተዘረዘሩት ክሶች በሙሉ እኛን አይመለከቱም የሚሉት ዶ/ር ፍስሃ፤ በተደጋጋሚ እንደገለጽነው እኛ ኢኮኖሚያዊ እንጂ ፖለቲካዊ ፍላጎትና ዓላማ የለንም - ብለዋል፡፡ “ፐርፐዝ ብላክ የተቋቋመው የድሃ ገበሬውንና በአጠቃላይ የጥቁር ህዝቦችን ኢኮኖሚያዊ አቅም በማሳደግ ክብሩን ለማስመለስ ነው፤ ዓላማውና ፍላጎቱም ይሄው ነው፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ሰውን ብቻ ሳይሆን ገንዘብንም ማገት ተጀምሯል ያሉት የብላክ ፐርፐዝ መሥራች፤ ከአራት ሳምንት በላይ የባንክ ሂሳባችን የታገደበትን ምክንያት ያወቅነው በዚህ ሳምንት ነው ይላሉ - የባንክ ሂሳብ እግዱ እንዲነሳ 200 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ መጠየቃቸውን በመግለጽ፡፡ ክፍያውን የጠየቀው ማን እንደሆነ ለይተው ባይገልጹም፣ የስልክ ልውውጥ ማስረጃ እንዳላቸው ግን ዶ/ር ፍስሃ ተናግረዋል፡፡
“የጠየቁት ገንዘብ ከተሰጣቸው የታገደው ሂሳብ እንደሚለቀቅ፣ ወደፊት አብረውን እንደሚሰሩ፣ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ሁሉ በቀላሉ እንደሚያቀርቡልን ሁሉ ቃል ገብተዋል፡፡” ሲሉም አክለዋል፡፡
የተጠየቀውን ክፍያ የማልፈጽም ከሆነ ግን እንደሚያስሩኝ ነግረውኛል ብለዋል፡፡ “ዶ/ር ፍስሃ፤ አንድ ህይወት እኮ ነው ያለህ፤ ያለበለዚያ እናስርሃለን፤ እንገድልሃለን” ሲሉም አስፈራርተውኛል ያሉት ዶ/ር ፍስሃ፤ ህይወቴን በማጣት ለፐርፐዝ ብላክም ሆነ ለባለአክሲዮኖች የማተርፈው ነገር ስለሌለ ከአገር ለመውጣት ተገድጄአለሁ፤ ብለዋል፡፡
ይኼ በአፍሪካ ትልቁ የሆነው ሙስና ሲፈጸም ጠ/ሚኒስትሩ ያውቃሉ ብዬ አላምንም ያሉት ሥራ አስፈጻሚው፤ 20 ሺ ባለአክሲዮን ላቡን ጠብ አድርጎ የገነባው ኩባንያ ሲፈርስ ዝም ብለው ማየት የለባቸውም ነው ያሉት፡፡ “ፍትህ ተጓድሏል ስንላቸው ፍትህ ሊያሰፍኑና ለደህንነታችን ዋስትና ሊሰጡን ይገባል” ሲሉም ጠ/ሚኒስትሩን ጠይቀዋል፡፡
“ሌት ቀን የምንሰራው የድሃው ገበሬያችን ህይወት እንዲለወጥ ነው፤ የኑሮ ውድነት ታሪክ እንዲሆን ነው፤ የሽንኩርት ዋጋ እንዲረክስ ነው” ያሉት የኩባንያው መሥራች፤ በምላሹ ያገኘነው ግን ከአገር ተገድዶ መውጣትን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ እኔን የሚያሳዝነኝ ታሪክ ራሱን መድገሙ ነው ሲሉም - ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት በኢህአዴግ ዘመን እንዲሁ ከአገር ለመውጣት መገደዳቸውን አስታውሰዋል፡፡
ይሄ ሁሉ ሆኖም እኛ ከማንም ጋር መካሰስና መዋቀስ አንፈልግም፤ ሥራችንን በሰላም መቀጠል ነው የምንሻው ሲሉ የተናገሩት የፐርፐዝ ብላክ ሥራ አስፈጻሚው፤ ይህን ለማድረግ ግን ጠ/ሚኒስትሩ ለደህንነታችን ዋስትና እንዲሰጡን እንፈልጋለን ብለዋል - ዶ/ር ፍስሃ፡፡ “ዋስትናችንን ሊያረጋግጡልን የሚችሉት ጠ/ሚኒስትሩ ብቻ ናቸው” ሲሉም አክለዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ፣ ከዛሬ ጀምሮ “ፍትህ ለብላክ ፐርፐዝ” የተሰኘ ዓለማቀፍ ዘመቻ መጀመሩን ያስታወቁት ዶ/ር ፍስሃ፤ የዘመቻው ዓላማም ህጋዊ ሌብነትን (የኢኮኖሚ ሽብርን) በጋራ መታገል ነው ብለዋል፡፡
የባንክ ሂሳባችን በመታገዱ ሳናጣ እንድናጣ ሆነናል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ለመላው ኢትዮጵያውያን ባቀረቡት የድጋፍ ጥሪ፣ የታገደው ገንዘባችን እስኪለቀቅ ለሰራተኞቻችን ደሞዝ መክፈል እንድንችልና ይህቺን ክፉ ቀን እንድናልፍ ከጎናችን ቁሙልን ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል፤ የፐርፐዝ ብላክ ቦርድ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የሃላፊነት ሽግሽግ ማድረጉ ተነግሯል፡፡ በዚህም መሠረት ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ የቦርዱ ሊቀመንበርና የዓለማቀፉ ፐርፐዝ ብላክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንዲሆኑ የተወሰነ ሲሆን፤ የቀድሞው የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ም/ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ኤርምያስ ብርሃኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንዲሆኑ መወሰኑ ታውቋል፡፡
addisadmassnews.com

178 ሺ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እየወሰዱ ነውየከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) እየተሰጠ ሲሆን በጠቅላላ 178ሺ ተማሪዎች ለፈተናው የሚቀመጡ ይሆናል። ...
22/06/2024

178 ሺ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እየወሰዱ ነው
የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) እየተሰጠ ሲሆን በጠቅላላ 178ሺ ተማሪዎች ለፈተናው የሚቀመጡ ይሆናል።
በ2015 ዓ.ም በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ መሰጠት የተጀመረው የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና የዘንድሮውን ፈተና በዛሬው ዕለት በማኔጅመንት፣ ጂኦሎጂና ፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን እና ዲቨሎፕመንት ማኔጅመንት ተማሪዎች በመስጠት ተጀምሯል።
በበይነ መረብ የሚሰጠው ፈተና ከሰኔ 14 እስከ ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን ከመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ አዲስና ድጋሜ ለፈተና የሚቀመጡ 178,000 ተማሪዎች በጠቅላላ የሚፈተኑበት ይሆናል። ለመውጫ ፈተና የተቀመጡት ተማሪዎች በየዩኒቨርስቲዎቹ የሚሰጠውን የመጨረሻውን መንፈቅ ዓመት ፈተና የወሰዱና የሚሰጡ ትምህርቶችንም ያጠናቀቁ ናቸው።
ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከያዛቸው የሪፎርም ስራዎች አንዱ የሆነውን የመውጫ ፈተናን ለማካሄድ ከፍተኛ ዝግጅት አድርጎ ያጠናቀቀ ሲሆን ለውጤታማነቱም ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል።
ለሁሉም የቅድመ ምረቃ እጩ ተመራቂዎች የሚሰጠው ይህ የመውጫ ፈተና ከዚህ ቀደም ለህክምና እና ለህግ ተማሪዎች ብቻ ይሰጥ እንደነበር ይታወሳል።
( የትምህርት ሚኒስቴር)

በጥቂት የታመነ በብዙ ይሾማል❗አሜሪካን ካንሳስ ሲቲ ነዋሪ የሆነችው ሳራ ዳርሊንግ ከስራ ወጥታ ወደ መኖሪያ ቤቷ በማቅናት ላይ ሳለች አንድ በዕድሜ ጠና ያሉ አዛውንት ከመንገድ ዳር ቁጭ ብለው...
22/06/2024

በጥቂት የታመነ በብዙ ይሾማል❗
አሜሪካን ካንሳስ ሲቲ ነዋሪ የሆነችው ሳራ ዳርሊንግ ከስራ ወጥታ ወደ መኖሪያ ቤቷ በማቅናት ላይ ሳለች አንድ በዕድሜ ጠና ያሉ አዛውንት ከመንገድ ዳር ቁጭ ብለው ሲለምኑ ተመለከተች።
ሳራ ወደ አዛውንቱ በመጠጋት ቦርሳዋን ከፍታ የተወሰኑ ዶላሮችን ሰውየው ከጎናቸው ባስቀመጡት የፕላስቲክ ኩባያ ውስጥ አኑራ ጉዞዋን ቀጠለች።
ሳራ ከምንግዜውም በላይ በህይወቷ ደስተኛ ነበረች ከምትወደውና ከምታፈቅረው ጓደኛዋ ጋር በትዳር ለመጣመር የቀናት ዕድሜ ቀርቷቸዋል።
ለእርሷ ከፍተኛ ክብርና ፍቅር ያለው ፍቅረኛዋ እጅግ ውድ የሆነ ዳይመንድ _ የቃል ኪዳን ቀለበት ገዝቶ በጉልበቱ ተንበርክኮ የታገቢኛለሽ ጥያቄ ካቀረበላት እና በደስታ እሺ ካለችው ጊዜ አንስቶ ህይወቷ በሀሴት ተሞልቷል።
ምሽት ላይ እንደተለመደው በስስት የምትወደውን የዳይመንድ ቀለበት አይታ ለመተኛት ቦርሳዋን ከፈተችው በድንጋጤ ደርቃ ቀረች ቀለበቱ በቦታው አልነበረም።
ቦርሳዋን የከፈተችው መንገድ ዳር ቁጭ ብለው ለሚለምኑት አዛውንት ገንዘብ ለመስጠት ብቻ እንደነበር ትዝ ሲላት የሰውየው ገንዘብ መሰብሰቢያ ኩባያ ውስጥ ቀለበቱን አብራ ማኖሯን አስታወሰች።
ለእጮኛዋ ስልክ በመደወል ሁኔታውን አጫወተችው እጮኛዋም እየበረረ መጥቶ ተያይዘው በልመና ወደ ሚተዳደሩት ሽማግሌ ጋ ሄዱ።
ሰውየው በቦታው አልነበሩም "በእርግጥ ውድ የሆነ ቀለበት አግኝተው እንዴት ተመልሰው በቦታው ሊቀመጡ ይችላሉ" የእጮኛዋ ግምት ነበር።
በቀጣዩ ቀንም በድጋሚ ከእጮኛዋ ጋር ሽማግሌው
ተቀምጠው ወደሚለምኑበት ቦታ ሄዱ አሁንም ሰውየው በዚያ ስፍራ አልነበሩም።
"በቃ ጦስሽን ይውሰድ ከእንግዲህ እርምሽን አውጪ" አላት እጮኛዋ ።
በሦስተኛው ቀንም ሳራ ለእጮኛዋ ደውላ ወደ ሽማግሌው ቦታ እንዲሄዱ ጠየቀችው እጮኛዋም በመገረም "ስድስት ሺህ ዶላር የሚያወጣ ቀለበት ችግረኛ እና በረንዳ የሚያድር ሰው እጅ ገብቶ አገኘዋለሁ ብለሽ እንዴት ታስቢያለሽ ?" ነበር ያላት ... ሳራም "በቃ የዛሬን ብቻ እንያቸው ሰውየው ከሌሉ እርሜን አወጣለሁ" አለችው።
እጮኛዋም የሳራን ፍላጎት ለማሟላት ብቻ ተስማምቶ ጉዞዋቸውን አቀኑ ሽማግሌው በቦታው ተቀምጠው ሲለምኑ አገኙአቸው
ሳራ በደስታ ተዋጠች አላውቅሽም ብለው እንዳይሸመጥጡ የሚል ስጋት እንደገባት ወደ ሽማግሌው ተጠጋች።
"አባት ያስታውሱኛል ?" በማለት ጠየቀች
ሽማግሌው ቢል ሬይ ቀና ብለው ተመልክተዋት "አላወቅኩሽም ልጄ" ሲሉ መለሱላት።
ሳራም "ከ3 ቀን በፊት ከቦርሳዬ ገንዘብ አውጥቼ
ኩባያዎ ዉስጥ ሳስቀምጥ ሌላ ዕቃ አብሬ አኑሬ ነበር" ስትላቸው
"የጣት ቀለበት ነው ?"አሏት
"አዎን አባት"
ሽማግሌው ቢል ቀለበቱን ጠቅልለው ካስቀመጡበት ኪስ በማውጣት "አንድ ቀን እንደምትመለሺ አውቅ ነበር" በማለት ቀለበቱን ከሰጧት በኋላ ... ቀለበቱን ያገኘሁት ዕለት ትክክለኛ ወይም አርቴፊሻል ቀለበት መሆኑን ለማወቅ ወደ ጌጣጌጥ ሱቅ ወስጄው ነበር እነሱም ትክክለኛ መሆኑን ነግረውኝ 4,000 ዶላር ሊገዙኝ ጠይቀውኝ ነበር።"
"በእርግጥ ኑሮውን በበረንዳ ለሚያሳልፍና በልመና ለሚተዳደር ሰው 4 ሺህ ዶላር ከፍተኛ ገንዘብ ነው ነገርግን እኔን ለመርዳት ብላ በስህተት ቀለበት የጣለችን ሴት ንብረት መንካት አልፈለኩም። በመሆኑም በጥንቃቄ አኑሬው የአንቺን መምጣት ስጠባበቅ ነበር።"
ሲሉ መለሱላት።
ሳራ ዳርሊንግ እና እጮኛዋ የመልካሙን ቢል ሬይ ታሪክ ከታች ቀለበቷን ሲሰጣት ከሚታየው ምስል ጋር በማያያዝ በሶሻል ሚዲያ (Facebook) ላይ ለቀቁት ከታሪኩም ጎን ለጎን የእርዳታ ማሰባሰቢያ ጎፈንድሚ አካውንት ከፈቱ በቢል ሬይ ቀናነት እጅጉን የተደሰቱ አያሌ ግለሶቦች የዕርዳታ እጃቸውን ይዘረጉ ጀመር በአጭር ጊዜ ውስጥም 260,000$ ዶላር ተሰበሰበላቸው።
በአሁን ሰዓት ቢል ከበረንዳ አዳሪነት ወጥተው የቤት ባለቤት ሆኑ ተጨማሪ የመጦሪያ ገንዘብም አገኙ።
ታማኝነት ለራስ ነው ነገ መልሶ ይከፍላልና
https://www.godvine.com/homeless-man-returns-wedding-ring-dropped-in-his-cup-10258.html

ስድስት ኢትዮጵያውያን ሴቶች የስናይፐር ተኳሽ ሆነው ተቀጥረው በሱዳን ጦርነት ሱዋጉ መያዛቸው ተገለጸ የጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ክንፍ የሆነው የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ስድስት ኢትዮጵያው...
21/06/2024

ስድስት ኢትዮጵያውያን ሴቶች የስናይፐር ተኳሽ ሆነው ተቀጥረው በሱዳን ጦርነት ሱዋጉ መያዛቸው ተገለጸ

የጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ክንፍ የሆነው የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ስድስት ኢትዮጵያውያን ሴቶች ለተቀናቃኛቸው የጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ ቡድን የሆነው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ተቀጥረው ሲዋጉ እንደያዙ ገለጹ።

ኢትዮጵያ እና ሱዳን የሚዋሰኑበት እንዲሁም ከዚህ ቀደም ግጭት ያስተናገደው 'ገዳሪፍ' ግዛት አስተዳዳሪዎች ስድስቱን ኢትዮጵያውያን ለሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ሲያገለግሉ መያዛቸውን የአገሪቱ የዜና ምንጭ ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል።

የዜና ምንጩ በተመለከተው እና ባሰራጨው መረጃ መሰረት ሴቶቹ ከአንድ ዓመት በላይ ለጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ ቡድን ሲሰሩ እንደነበረ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ተምረውታል በተባለው የስናይፐር መሳሪያ ተኳሽ ሆነው መስራታቸው በምስል ማስረጃዎች ተረጋግጧል።

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ከዚህ ቀደም በሚያዝያ መጨረሻ ላይ እንደገለጸው የጀነራል አል ቡርሃን የሱዳን ታጣቂ ኃይል የውጭ ቅጥረኞችን ይቀጥራል በማለት ወንጅሎ "የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር (ህወሓት) ኃይሎች አሁን ከአል ቡርሃን እና አጋር ታጣቂዎቹ ወግነው እያጠቁን መሆኑን በማስረጃ አረጋግጠናል" ሲል ወቅሶ ነበር።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ግን ከአንድ ቀን በኋላ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ወቀሳ “መሰረት ቢስ” ነው ሲሉ አስተባብለውታል።

አሁን በገዳሪፍ ግዛት ተይዘዋል የተባሉ ስድስት ኢትዮጵያውያን ሴቶች በሱዳን ያለው ጦርነት እየተስፋፋ በመሆኑ ወደ ኢትዮጵያ "ለማምለጥ" በሙከራ ላይ እያሉ መያዛቸው ተዘግቧል።
Addis Maleda

እንግሊዝ ከዴንማርክ ነጥብ ተጋርተዋል !      | በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከዴንማርክ አቻቸው ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አ...
21/06/2024

እንግሊዝ ከዴንማርክ ነጥብ ተጋርተዋል !
| በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከዴንማርክ አቻቸው ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።
ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ግቧን ሀሪ ኬን ከመረብ ሲያሳርፍ ሞርተን ሁልማንድ ዴንማርክን አቻ ማድረግ ችሏል።
ሀሪ ኬን ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ስልሳ አራተኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
1️⃣ እንግሊዝ :- 4 ነጥብ
2️⃣ ስሎቬኒያ :- 2 ነጥብ
3️⃣ ዴንማርክ :- 2 ነጥብ
4️⃣ ሰርቢያ :- 1 ነጥብ
በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ እሁድ እንግሊዝ ከስሎቬኒያ እንዲሁም ዴንማርክ ከሰርቢያ ጋር ይገናኛሉ።

የጠፋችው ሩት አገኘሁ አመሻሽ ላይ ተገኝታለች🙏እግዚአብሔር ይመስገን🙏 ***በፀሎት ፣ በማፈላለግ ፣ ጥቆማ በመስጠት ከጎናችን በመቆም በFacebook, Telegram , Instagram , Ti...
20/06/2024

የጠፋችው ሩት አገኘሁ አመሻሽ ላይ ተገኝታለች
🙏እግዚአብሔር ይመስገን🙏
***በፀሎት ፣ በማፈላለግ ፣ ጥቆማ በመስጠት ከጎናችን በመቆም በFacebook, Telegram , Instagram , TikTok share በማድረግ ከጎናችን ለቆማችሁ በውጪም ሆነ በሀገር ውስጥ ያላችሁ ኢትዮጵያን በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን** ብለዋል ቤተሰብ🙏🙏🙏
በመጨረሻም ፍለጋው በስኬት እንዲፈፀም ላደረጉት አዲስ አበባ ፓፕለሪ ጨርቆስ ፓሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አጥሌ ዘለቀን እና የሥራ ባልደረቦቻቸውን በሙሉ እና አቶ ደረጀ ገ/ሚካኤል እንዲሁም ጥቆማ/ፍንጭ በመስጠት አቶ አማረ ከተማን ፣በድጋሚ ቤተሰብ አመስግነዋል 🙏🙏🙏
እኛም ሼር አድርጉ ብለን ስንጠይቅ ፣ ሁሌ የማታሳፍሩን ቅን ፣ታዛኝ ቤተሰቦቻችን ፣ ክበሩልን
የዚህችን ብላቴና እናት ልብ አሳርፋችኋልና🙏🙏🙏 መከራ በቤታችሁ አይድረስ🙏🙏🙏
ውቤ ማኛው #ቢሾፍቱ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት ሽልማቶችን አገኘ ።    | የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2024፣ የአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ (...
20/06/2024

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት ሽልማቶችን አገኘ ።
| የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2024፣ የአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ (Best Entertainment Award in Africa) እና የአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ ገመድ ዓልባ ኢንተርኔት አገልግሎት (Best Wi-Fi Award in Africa) ዘርፍ ሽልማት አገኘ።
ይህ በ “Airline Passenger Experience Association” (APEX) የመንገደኞችን ድምፅ መሰረት በማድረግ ለአየር መንገዶች ዕውቅና የሚሰጥበት መድረክ በአቪዬሽን ኢንደስትሪው ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሽልማቶች አንዱ ሲሆን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ አየር መንገዶች ለሚያቀርቡት የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ዕውቅና የሚሰጥበት ነው።

ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ***የአከራይ ተከራይ አዋጅ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በህግ ከተ...
20/06/2024

ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
***
የአከራይ ተከራይ አዋጅ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በህግ ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግና የነበረውን የኪራይ ውል ማቋረጥ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል፡፡
በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ፍትሀዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማህበረሰቡ ላይ የሚፈጥረው ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት የቤት ኪራይ ስርአቱ በህግ የሚመራ እና ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ለችግሩ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ተገቢ ሆኖ ሰለታመነበት የመኖሪያ ቤት ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 መጋቢት 24/2016 መውጣቱ ይታወቃል።
የከተማ አስተዳደሩም የአዋጁን ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 7/2016 በማውጣት ተግባራዊ አድርጓል።
በመሆኑም አዋጁ ወጥቶ ተግባራዊ ከሆነበት ቀን ማለትም ከመጋቢት 24/2016 ጀምሮ መንግስት ከሚያስቀምጠው የኪራይ ውሳኔ ውጪ በአከራዮች የሚደረግ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ፈፅሞ የተከለከለ በመሆኑ አዋጁ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከህግ ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግና የነበረውን የኪራይ ውል ማቋረጥ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ቢሮው ገልጿል።
ይህ እንዳይፈፀምም ቢሮው ተገቢውን ቁጥጥር እና ክትትል እንደሚያደርግም ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የህግ ክልከላውን ተላልፈው የተገኙ አከራዮች ላይ በመመሪያ ቁጥር 7/2016 አንቀፅ 22 መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድም ቢሮው አሳስቧል።

የአፋልጉኝ ተማጽኖ  | ሩት አገኘሁ የተባለች የ14 ዓመት የ7ተኛ ክፍል ተማሪ የሆነች ታዳጊ።ሰኞ 10/10/2016 ዓ.ም ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ ተልካ እንደወጣች አልተመለሰችም።ቋሚ የመኖሪ...
20/06/2024

የአፋልጉኝ ተማጽኖ
| ሩት አገኘሁ የተባለች የ14 ዓመት የ7ተኛ ክፍል ተማሪ የሆነች ታዳጊ።
ሰኞ 10/10/2016 ዓ.ም ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ ተልካ እንደወጣች አልተመለሰችም።
ቋሚ የመኖሪያ አድራሻዋ ቢሾፍቱ ዲባዩ ክፍለከተማ ቢፍቱ ወረዳ።ልዩ ስፍራው 60ቁጥር አውቶቢስ ማዞሪያ አካባቢ።
ስትወጣ የለበሰችው ከላይ ጥቁር ኮፍያ ያለው ጃኬት ፣ ከስር ኦሞ ከለር ጅንስ ሱሪ ፣ ነጭ አዲዳስ ጫማ ነው ያረገችው ።
አባካችሁ ያያችኋት ወይም ስለእሷ የሰማችሁ በዚህ ስልክ ላይ ደውለው ጥቆማ ይስጡኝ።
እናቷ ሙሉመቤት ተሬሣ
0911769360 / 0910276852
አጎቷ በረከት ተሬሳ 0910736180
በተጨማሪ አንጀቴ ስለልጄ እየተላወሰ ነው።
በብዙ ተጨንቂያለሁ፤ ሁላችሁ በፀሎት እኔንም ልጄንም አስቡን። እናቷ ሙሉመቤት ተሬሣ ነኝ።
ስለምታደርጉልኝ ትብብር አመሰግናለሁ።

በአድዋ ከተማ ለወራት ታግታ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታዳጊ መገደሏን ፖሊስ አስታወቀ   | በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ ባልታወቁ ግለሰቦች ታግታ ሦስት ሚሊዮን ብር ተጠይቆባት የነበራችው ...
19/06/2024

በአድዋ ከተማ ለወራት ታግታ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታዳጊ መገደሏን ፖሊስ አስታወቀ
| በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ ባልታወቁ ግለሰቦች ታግታ ሦስት ሚሊዮን ብር ተጠይቆባት የነበራችው የ16 ዓመቷ ታዳጊ መገደሏን ፖሊስ ተገለጸ።
የአድዋ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ተስፋዬ አማረ ረቡዕ ሰኔ 12/2016 ዓ.ም. ረፋድ ላይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ማኅሌት ተኽላይ ተቀብራበታለች በተባለበት ቦታ በተካሄደ ቁፋሮ አስክሬኗን ማውጣቱን ገልጸዋል።
ፖሊስ ታዳጊዋ ተቀብራበታለች የተባለው ቦታ ጥቆማ የደረሰው ማኅሌት ተኽላይን በማገት የተጠረጠሩ ግለሰቦች ታዳጊዋን ገድለው መቅበራቸውን አምነው የቀብር ቦታውን መርተው ካሳዩ በኋላ መሆኑን የፖሊስ ኃላፊው ተናግረዋል።
የ16 ዓመት ታዳጊዋ ማኅሌት ተኽላይ በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን አድዋ ከተማ መጋቢት 10/2016 ዓ.ም. ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከታገተች በኋላ ሦስት ሚሊዮን የማስለቀቂያ ብር ተጠይቆባት ነበር።
ኃላፊው ፖሊስ የታዳጊዋ አስክሬን ተቀብሮበታል በተባለው ቦታ ላይ ቁፋሮ በማድረግ አስከሬን ያወጣ ሲሆን፣ ከስፍራው የታጋቿ ልብስ እና ጫማን ማግኘቱንም ገልጸዋል።
የአድዋ ከተማ ፖሊስ ኃላፊ ተስፋዬ አማረ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አስክሬኑ በቁፋሮ ከወጣ በኋላ የታዳጊዋ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ በባለሙያ ምርመራ እየተደረገበ መሆኑንም ተናግረዋል።
በአድዋ ከተማዋ የሚገኙ የቢቢሲ ምንጮች እንደተናገሩት የማኅሌት ተኽላይ ቤተሰቦች መርዶው በፖሊስ ተነግሯቸው ሐዘን ተቀምጠዋል።
ማኅሌት ከሦስት ወራት በፊትን ነበር ወደ ትምህርት ቤት ብላ ከቤቷ ከወጣች በኋላ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታፍና መወሰዷን ታላቅ እህቷ ሚሊዮን ተኽላይ ከዚህ ቀደም ለቢቢሲ ተናግራ ነበር።
ማኅሌት ታግታ በነበረችበት ወቅት ለቢቢሲ ቃለ መጠይቅ ያደረችው እህቷ ሚሊዮን፣ አጋቾቹ ታዳጊዋን ለመልቀቅ ሁለት ጊዜ ወደ አባቷ ስልክ ደውለው ነበር።
“ድምጿን አልሰማንም . . . አባታችንም ምን እንደሚፈልጉ እና እንዴት እንደሚሰጣቸው ጠይቋቸው ነበር። እነሱም ‘የምንልህን ለመስጠት ታዘጋጃለህ’ ካሉ በኋላ ስልካቸውን እየጠበቅን ነው” ብላ ነበር።
ማኅሌት በዚህ ዓመት ወደ ሁለተኛ ደረጃ የሚያሸጋግራትን የ8ኛ ክፍል ፈተና ለመውሰድ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተማረች ሳለ ነበር የታገተችው።
ቤተሰብ ወደ ቋንቋ ትምህርት ቤት በባጃጅ ስትጓዝ ታግታ የተወሰደችባቸውን ልጃቸውን “ሥነ ምግባር ያላት የቤት ልጅ” ሲሉ ይገልጿታል።
ከእገታው በኋላ አጋቾቹ በማኅሌት ስልክ ወደ ወላጅ አባቷ ስልክ በመደወል “ልጅህን በሕይወት ማየት የምትፈልግ ከሆነ ሦስት ሚሊዮን ብር አዘጋጅ” የሚል ትዕዛዝ ሰጥተው እንደነበረ ሚሊዮን ለቢቢሲ ገልጻ ነበር
ማኅሌት ከታገተች በኋላ ቤተሰብ ልጃቸው ያለችበትን ቦታ እና አጋቾቿን ለማወቅ ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች በታዳጊዎች ላይ የሚፈጸም እገታ እየተበራከተ ይገኛል።
ድርጊቱን የሚፈጽሙ ግለሰቦች አብዛኛውን ጊዜ እገታውን ለመፈጸም ባለ ሦስት ጎማ ተሽከርካሪዎችን እንደሚጠቀሙ ይገለጻል።
ቀደም ብሎ በመቀለ ከተማ በሚገኙ የተለዩ ክፍለ ከተሞች ከትምህርት ቤት ልጆች አግተው ሲወስዱ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች እንዳሉ የከተማዋ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ለቢቢሲ ገልጾ ነበር።
ባለፈው ወር መጋቢት አቶ መሃሪ ከበደ የተባሉ ግለሰብ ልጅ የሆነ ህጻን ታግቶ ተወስዶ ቤተሰቦች አራት ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ተጠይቀው ነበር።
ህጻኑ ከአንድ ሳምንት በላይ በእገታ ስር የቆየ ሲሆን፣ ቤተሰቦች ከከተማዋ ፖሊስ ጋር በመተባበር ባደረጉት ጥረት ህጻኑ መጋቢት 17/2016 ዓ.ም. ተለቆ ከቤተሰቡ ጋር መቀላለቁን ቢቢሲ በወቅቱ ዘግቦ ነበር።
BBC

ወንዲ ማክ ከ15 ነጠላ ዜማዎች በኋላ የመጀመሪያ አልበሙን ሊያወጣ ነው።አዲስ አበባ ኮልፌ ነው ተወልዶ ያደገው፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በኮልፌ ሰላም በር፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በ...
19/06/2024

ወንዲ ማክ ከ15 ነጠላ ዜማዎች በኋላ የመጀመሪያ አልበሙን ሊያወጣ ነው።
አዲስ አበባ ኮልፌ ነው ተወልዶ ያደገው፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በኮልፌ ሰላም በር፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በቦሌ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል። የኮሌጅ ትምህርቱን በንፋስ ስልክ ቴክኒክ ተከታትሎ ተመርቋል።
ድምፃዊ ወንዲ ማክ መጀመሪያ ከህዝብ ያስተዋወቀው የሙዚቃ ስራ የቀድሞው አንጋፋ ድምጻዊ የጋሻው አዳል የሆነውን ግጥም ከራሱ በመጨመር "ምን ይጥራሽ" ወይም "ኮለል በይ" የተሰኘ ስራ ነው።
ወንደወሰን መኮንን (ወንዲ ማክ) 15 ነጠላ ዜማዎችን በመስራት ለህዝብ አድርሷል። በዚህም በተለያዩ የአለማችን ሀገራት በመሄድ የሙዚቃ ስራውን አቅርበዋል።
አሁን ከዘጠኝ አመት በኋላ "ይንጋልሽ" የተሰኘ የራሱን የመጀመሪያ አልበም አጠናቆ አርብ ሰኔ 14/2016 ዓም በራሱ ዩቲዩብ ቻናል እንደሚለቅ ተሰምቷል።
14 ሙዚቃዎችን የያዘው ይንጋልሽ አልበም ግጥም እና ዜማ ራሱ ወንዲ ማክ የሰራው ሲሆን በፍቅር፣ በማህበራዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥን እንደሆነ ተነግሯል።

" የሞባይል ስልክ እና ላፕቶፕ ጠፍቶብኛል የሚል ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መረከብ ይችላል " - ፖሊስየአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ባደረገው ክትትል ግምቱ 150 ሺህ ብር የሚ...
19/06/2024

" የሞባይል ስልክ እና ላፕቶፕ ጠፍቶብኛል የሚል ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መረከብ ይችላል " - ፖሊስ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ባደረገው ክትትል ግምቱ 150 ሺህ ብር የሚያወጣን ሞባይል ስልክን ከሌባ ላይ የገዛችን ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውሎ ንብረቱን ማስመለሱን አስታወቀ፡፡ ግለሰቧ ከወንጀለኞች በተለያየ ጊዜ የገዛቻቸው ልዩ ልዩ ሞባይል ስልኮችን ፣ ላፕቶፖችንና ታብሌት ይዞ ምርመራው መቀጠሉን አዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆል፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው ...
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው " አለምነሽ ፕላዛ " አካባቢ አንድ ግለሰብ ግምቱ 150 ሺህ ብር የሚያወጣ አይነቱ አይፎን ፕሮ ማክስ ሞባይል ስልክ ይቀማሉ። ይህን ተከትሎ አደይ አበባ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ያመለክታሉ።

የግለሰቡን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ፖሊስ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በቴክኖሎጂ በመደገፍ ባደረገው ክትትል የተሰረቀው ስልክ አራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ ከሚገኝ አንድ የሞባይል መሸጫ ሱቅ መኖሩ ይረጋገጣል፡፡

ፖሊስ የህግ አግባብን በመከተል ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትእዛዝ በማውጣት ባደረገው ብርበራ ከግለሰቡ ላይ የተቀማውን ስልክ ጨምሮ በልዩ ልዩ ጊዜያት ከተለያዩ ቦታዎች የተሰረቁ ፦

➡️ 85 ስማርት ሞባይል ስልኮችን ፣

➡️ 4 ለፕቶፖችን ፣

➡️ 1 ታብሌትና የላፕቶፕ ቦርሳዎችን በኤግዚቢትነት ይዟል።

የቅሚያ ወንጀል የፈፀመውን ተጠርጣሪ ለመያዝ ክትትሉ መቀጠሉን ፖሊስ አመልክቷል።

የሞባይል ስልክ እና ላፕቶፕ ጠፍቶብኛል የሚል ማንኛውም ግለሰብ አደይ አበባ ስቴዲዮም አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመቅረብ ሞባይል ስልኩን በመለየትና ትክክለኛ ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መረከብ እንደሚችል አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

Address

Africa Avenue/Bole Road
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EyohaMedia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to EyohaMedia:

Videos

Share


Other Media/News Companies in Addis Ababa

Show All