29/03/2024
አብያተ ክርስቲያናት ወደ ሙዚየምነት የመቀየር ዕጣ ይደርስባቸው ይሆን... ?
ሰሞኑን በተለያየ የከተማዋ ክፍል ያሉ ነዋሪዎች መልሶ ማልማት በሚሉ ፕሮጀክቶት ቀድመው ይኖሩባቸው ከየበሩ መኖሪያ ስፍራቸው በመነሳት ወደ ሌላ ስፍራ እየተዘዋወሩ ይገኛሉ። እርግጥ ይህ አይነቱ ስራ ከተጀመረ ቆይቷል።ይህ የመልሶ ማልማት ሙሉ ከተማንዋን እንደሚያጠቃልል መንግስት የተለያየ ጊዜ ላይ ሲገልጥ ይሰማል።
እነዚህ በመልሶ ማልማት የሚለሙት ስፍራቸው ሰዎች የሚኖሩባቸው ሳይሆኑ አብዛኛዎቹ ፓርክ እና መሰል ነገሮች ብቻ ናቸው የሚገነቡባቸው ።አደጋውንም የከፋ የሚያደርገው ይህ ነው ።ይህ አይነቱ መፈናቀል የማህበረሰቡን የቀደመ ማህበረሰባዊ እሴት የአኗኗር ዘዪ ከማሳጣቱ በተጨማሪ በአካባቢው ላሉ የእምነት ስፍራዎች ትልቅ ተግዳሮትን ከፊት ይዘው መጥተዋል።
በከተማዋ ላይ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የእምነት ስፍራዎች ወይም አብያተ ክርስቲያናት እንዳሉ ይታወቃል ።የእነዚህ አብያተክርስቲያናት መሰራት በስፍራው ላሉ ምዕመናን መሰባሰቢያ ነው። ይህም ማለት የዕለት ዕለት የወንጌል አገልግሎት የሚያገኙበት ምዕመናን ከአምላቸው ጋር በጸሎት የሚገናኙበት ስጋወ ደሙን የሚቀበሉበት ሲከፋቸውም የሚያለቅሱበት ሲደሰቱም ደስታቸውን በምስጋና የሚገልጡበት አንባ እና መጠጊያቸው ናቸው።
ታዲያ በአጥቢያው የነበሩ እልፍ ምዕመናንን ተነስተው ወደ ተለያየ የመኖሪያ ስፍራ ከተበተኑ የአብያተክርስቲያናቱ እጣ ምንድን ነው የሚሆነው?እርግጥ ልማት እና መሰል ነገር እየተባለ የሚነሳው በውስጡ አብያተክርስቲያናቱን ምዕመናንን በማሳጣት እንዲዘጉ የማድረግ አላማ ኖሮት ነው ?ሰው በሌለበት ስፍራ ቤተክርስቲያን ምን ያደርጋል የሚል ጥያቄ መምጣቱስ ይቀራል?
በተለያየ አጋጣሚ ቤተክርስቲያኒቱ ስለያዘችው ስፍራ መብዛት በተደጋጋሚ ሲናገር ይሰማል እንዲሁ ስፍራዎቿን ከመቀማት ምዕመኖቿን ከአጥቢያቸው በማፈናቀል በሰፍራው አማኝ የለም ስለዚህ የያዛችሁትን ቦታ ይቀነሳል የሚል ሀሳብ ይዞ ብቅ ላለማለቱ ምን ዋስትና አለን?
ወደ ቀድሞ ነገሬ ስመለስ የታላቁ ቅደስት ስላለሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን በአጥቢያው ያሉ ምዕመናን መነሳት ቤተክርስቲያኑን ምዕመን አልባ አድርጎታል ።ዕለት ዕለት ላሉ የጸሎት ክዋኔዎች ለኪዳን ለቅዳሴ ለሰርክ ጉባዔ ወደዛ የሚሔደው ምዕመን በጣት የሚቆጠር ነው። ሌላው ቀርቶ የሰንበት ተማሪዎች ቁጥር የለም በሚባል ደረጃ ነው።ደብሩ ላይ የንግስ በዓል ሲኖር እንኳን ከያሉበት ተሰባስበው ነው በዝማሬ የሚያገለግሎት።ያን ታላቅ ደብር በምዕመናን ድርቅ ተመቶ ማየት እንዴት ያሳዝናል መሰላችሁ 🤔🤔
ታዲያ መሀል ከተማ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ከምዕመናን ሲስተማቲካሊ እየተነጠሉ በሔዱ ቁጥር ከሀይማኖት ስፍራነታቸው ይልቅ ለመጎብኝት የሚሆኑ ሙዚየሞች ወይንም ጭራሽ እንዳይኖሩ ላለመደረጋቸው ዋስትናቸው ምንድንነው?አማኝ በሌለበት ቤተክርስቲያን ምን ያደርጋል ሚል ፈሊጥ መጥቶ እነሱም በሒደት ላለመነሳታቸው ማረጋገጫችን ምንድን ነው?
ይህ ጥያቄ ባይመጣ እንኳን የአብያተክርስቲያናቱ የገቢ መሰረት ምዕመናን ናቸው።የቤተክርስቲያን የዕለት ዕለት አገልግሎት የሚከወነው ከምዕመናን በሚመጣት መባዕ እና ገንዘብ ነው ።የካህናቱ ደሞዝ አጠቃላይ ቤተክርስቲያኒቱ የምትከውናቸው ስራዎች ምዕመኖቿ በሚሰጧት ስጦታዎች ነው ።ታዲያ የእነዚህ ምዕመናን ከስፍራው መነሳት አብያተክርስቲያናቱን እንዳይቆሙ እና አገልግሎታቸውን እንዳይቀጥሎ አያግዳቸውም?
በደንብ ያደርጋቸዋል ለአገልጋይ ካህናቶቾ ደሞዝ መክፈል ካልቻለች ምዕመኖቿን ብቻ ሳይሆን አገልጋዮቿንም እያጣች ትመጣለች።