New art and event

New art and event Its smart page follow it for ethio beter life

10/09/2024

ውድ ኢትየጵያዊያን ።ይህ የዘመን አቆጣጠር የእኛና የእኛ ብቻ ነው ። እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ ።
2016 ለኔ ፈታኝ ዘመን ነበር ።ሆኖም አልፏል ይህ አመት እንደተቋጨ 2016 የፈተናችን የችግራችን የሀዘናችን የአመማችን መቋጫ ሆኖ 2017 አዲሱ አመት የሰላም የፍቅር የደስታ የስኬት ይሁንላችሁ ።
እንቁለጣጣሽ
ዮሐንስ ነኝ ከዲቲ

በአንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጓድ ውስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ በራሷ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች በጣምም መጮህ ጀመረች ባለቤቱም አህያዋን ለማውጣት ብርቱ...
01/08/2023

በአንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጓድ ውስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ በራሷ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች በጣምም መጮህ ጀመረች ባለቤቱም አህያዋን ለማውጣት ብርቱ ሙከራ ቢያደርግም ሊሳካለተ አልቻለም፡፡
አህያዋም ብዙ ያገለገለችና ያረጀች ስለሆነች እንዲሁም ሌሎች እንስሳትም ወደ ጉድጓዱ እንዳይገብበት በማሰብ ጉድጓዱ ውስጥ ሊቀብራት ወሰነ፡፡

ጎረቤቶቹንም አስተባብሮ ጉድጓዱን በአፈር መሙላት ጀመረ አህያዋ ይህን ስትመለከት እየቀበራት መሆኑነ ተረዳችና በሰቀቀን አለቀሰች፡፡ይሁን እንጂ አህያዋ አፈር ሲደፋባት አንድ ነገር ታደርግ ጀመር፡፡ አፈሩ በተደፋባት ቁጥር አፈሩን እያራገፈች ከአፈሩ ውስጥ ብቅ ትል ጀመር፡፡በተደጋጋሚ ከሚደፋባት አፈር ላይ መቆምም ትጀምራለች፡፡

በሂደት ውስጥ በአፈሩ ላይ በቆመች ቁጥር ከነበረችበት ጉድጓድ ከፍ እያለች ከፍ እያለች በመጨረሻም ጉድጓዱ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ መውጣት ቻለች፡፡

በሚገርም ሁኔታ አህያዋን ሊቀብሯት የሞከሩት ሰዎች በአህያዋ አወጣጥ በእጅጉ ተደነቁ፡፡
ሰው ያስባል እግዚአብሔር ይፈፅማል!

ከእግዚአብሔር አይምጣ እንጂ ከሰው የመጣ እሱ ይመልሰዋል::

ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ🙏

አማራ የባህል የእመነት የፍቅር የቱፊት የታሪክ አጠቃላይ የኢትዮጵያዊነት መሰረት ነው ለበለጠ መረጃ follow me
24/07/2023

አማራ
የባህል
የእመነት
የፍቅር
የቱፊት
የታሪክ
አጠቃላይ የኢትዮጵያዊነት መሰረት ነው
ለበለጠ መረጃ follow me

በአርማጭሆ  የሳንጃ ቴ/ሙ/ማስ/ተቋም በልዩልዩ የሙያ መስኮች  ያሠለጠናቸውን በርካታ ሰልጣኞች አስመረቀ። በምረቃ ሰነስርዓቱ  ተጋባዥ  እንግዳዎች ወላጆች  የተገኙ ሲሆን መድረኩን በልዩ ብቃ...
22/07/2023

በአርማጭሆ የሳንጃ ቴ/ሙ/ማስ/ተቋም በልዩልዩ የሙያ መስኮች ያሠለጠናቸውን በርካታ ሰልጣኞች አስመረቀ።
በምረቃ ሰነስርዓቱ ተጋባዥ እንግዳዎች ወላጆች የተገኙ ሲሆን መድረኩን በልዩ ብቃት የሀገርጫታ አድምቆት ውሏል ። በድጋሜ ሰልጣኞቻችን እና ወላጆች እንኳን ደስ አላችሁ ።
ሐምሌ15/2015 ዓ.ም
ሳንጃ

20/07/2023

አማራ ሆይ እሚሞትልህን እና ገዳይህን ለይ አማራን ለማዳከም የመጀመሪያው እራስ በእራሱ ማዎጋት ነው ። እናም ወገን አንድ እንሁን አንድ አማራ

29/04/2023

በዚህ ወቅት ያልታዘብኩት የለም ። በጣም በተረጋጋ እይታ ትዝብት ላይ ነኝ
ከሚዲያው, ከፖለቲከኛው :ከአመራሩ : ከፀሀፊው አረ ሰንቱን ???

09/03/2023
Follow @,fbhttps://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1725413521188350&id=100011591569133&mibextid=Nif5oz
29/01/2023

Follow @,fb
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1725413521188350&id=100011591569133&mibextid=Nif5oz

ተገናኝተዋል!

ይፈለጋል
ሚክያስ አዳነ በ2014 ዓ.ም. የአስራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በ666 ነጥብ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ወጣት ነው። ሚኪያስ ከሀገሪቱ ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ ከፍተኛውን ውጤት ማስመዝገቡ ብቻ ሳይሆን ከወሰዳቸው የትምህርት አይነቶች መሀከል የፊዚክስ ውጤቱ (100) በአሜሪካ የአንድ ኢትዮጵያዊ የናሳ ሳይንቲስትን ትኩረት ስቧል።
ተመራማሪው በቴክሳስ የናሳ ስፔስ ሳይንስ ባልደረባ የሆኑት ዶክተር ጥላዬ ታደሰ በለዛና ቁምነገር የራዲዩ ፕሮግራም በኩል ለተሻለ የትምህርት እድል "አፋልጉኝ" ብለዋል። የሚኪያስን አድራሻ የምታውቁ ለቅርብ ወዳጃቸው ዶክተር ሳምሶን ሚደቅሳ በስልክ ቁጥር 0948 110222 በመደወል ማሳወቅ ትችላላችሁ።

08/01/2023

የጥበብን የሚወድ ብቻ follow it arts page

የድምጻዊት አስቴር አወቀ “ሶባ” አዲስ አልበም የጥምቀት ዋዜማ ይወጣል !  | በዘመን አይሽሬ ድምጿ እና ከመድረክ አያያዟ በተጨማሪ በራሷ ተወዳጅ ግጥምና ዜማዎቿ የምትታወቀው ተወዳጇ ድምጻዊ...
04/01/2023

የድምጻዊት አስቴር አወቀ “ሶባ” አዲስ አልበም የጥምቀት ዋዜማ ይወጣል !

| በዘመን አይሽሬ ድምጿ እና ከመድረክ አያያዟ በተጨማሪ በራሷ ተወዳጅ ግጥምና ዜማዎቿ የምትታወቀው ተወዳጇ ድምጻዊት አስቴር አወቀ “ሶባ” የተሰኘ አዲስ አልበም የጥምቀት ዋዜማ እንደሚወጣ ሰዋሰው መልቲሚድያ አስታውቋል፡፡

በያዝነው አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ ለሕዝብ የተዋወቀው እና ከመቶ በላይ አንጋፋና ወጣት ተወዳጅ ድምጻዊያንን በጋራ ለመስራት ያስፈረመው ሰዋሰው መልቲ ሚድያ ፤ አስር የሙዚቃ ስራዎችን ያካተተው የድምጻዊቷ “ሶባ” የተሰኘ አዲስ አልበምን የጥምቀት ዋዜማ በሰዋሰው መተግበሪያ በኩል ለአድማጮች ያደርሳል ተብሏል፡፡

ድምጻዊ አስቴር አወቀ ከሰዋሰው መልቲ ሚድያ ጋር ስተፈራረም የሰዋሰው የማኔጅመንት አባላት ድምጻዊ አስቴር አወቀ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ድምጻዊት አስቴር አወቀ ከዚህ በፊት ሃያ አራት የሚደርሱ ዘመን አይሽሬ ተወዳጅ የሙዚቃ አልበሞችን እና ሁለት ነጠላ ዘፈኖችን ለሙዚቃ አፍቃሪያን ያደረሰች ሲሆን “ሶባ” ሃያ አምስተኛ አልበሟ ነው፡፡

ድምጻዊቷ ከሃገር ውስጥም በተጨማሪ በታላላቅ ዓለማቀፍ መድረኮች ስራዎቿን በማቅረብ ከፍተኛ አድናቆትን በማግኘት ኢትዮጵያዊቷ የሶል ሙዚቃ ንግስት በመባልም ትታወቃለች፡፡

ሰዋሰው መልቲ ሚድያ ጥበበኞች የሚገባቸውን የፈጠራ ዋጋ እንዲያገኙ በማድረግ የሃገራችን ጥበብ ባህር ማዶ ተሸጋሪ እንዲሆን ለማስቻል በከፍተኛ ኢንቨስትመንት የተቋቋመ ሀገር በቀል ድርጅት ነው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም

New ivents  2 ሜትር ከ89 ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ጋናዊው ወጣት የዓለም ረጅሙ ሰው እየተባለ  ነው ❗️
03/01/2023

New ivents


2 ሜትር ከ89 ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ጋናዊው ወጣት የዓለም ረጅሙ ሰው እየተባለ ነው ❗️

የእመቤታችን ፻፳ ስሞችብቸኛዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፻፳ ስሞችን እንዲህ ብላ ትጠራታለች ።፩ የኖኅ መርከብ ፪ የሴም ዕድል ፈንታው...
29/12/2022

የእመቤታችን ፻፳ ስሞች

ብቸኛዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፻፳ ስሞችን እንዲህ ብላ ትጠራታለች ።

፩ የኖኅ መርከብ
፪ የሴም ዕድል ፈንታው
፫ የአብርሃም ዘመድ
፬ የዮሴፍ አረጋጊ
፭ ምሥራቀ ምሥራቃት
፮ የሴም ምርቃቱ
፯ ሶልያና
፰ መንፈሳዊት ሀገር
፱ በትረ አሮንን
፲ የገነት ኮል
፲፩ ወለተ ዳዊት
፲፪ ሐመልማላዊት
፲፫ የይስሐቅ ሽቱ
፲፬ ጽጌ ሃይማኖት
፲፭ ቤዛዊተ ዓለም
፲፮ የጌዲዮን ጸምር
፲፯ ዕፀ ሕይወት
፲፰ የሙሴ ጽላት
፲፱ እሙ ለፀሐዬ ጽድቅ
፳ የሳሙኤል ሽቱ
፳፩ በአታ
፳፪ የኢያሱ የምስክር ሐውልት
፳፫ የአሮን ካህን ጸናጽል
፳፬ የአሚናዳብ ሰረገላ
፳፭ የዳዊት መሰንቆ
፳፮ የሰሎሞን ቀለበት
፳፯ የኤልሳዕ ልሑኩት
፳፰ የኢሳይያስ ትንቢት
፳፱ የሚኪያስ ኤፍራታ
፴ መዝገበ ብርሃን
፴፩ የያዕቆብ መሰላል
፴፪ ደብተራ ዘትዕይንት
፴፫ የዘካርያስ ደስታ
፴፬ የናሆም ፈዋሽ
፴፭ መሠረተ ሕይወት
፴፮ ሀገረ ክርስቶስ
፴፯ ኪዳነ ምሕረት
፴፰ ንጽሕት ጸምር
፴፱ እኅትነ ነይ
፵ አንቀጸ አድኅኖ
፵፩ መዓዛ እረፍት
፵፪ ርግብዬ ሠናይት
፵፫ አንቀጸ ብርሃን
፵፬ ናዛዚተ ኅዙናን
፵፭ ወለተ ጽዮን
፵፮ ብርሃነ ሕይወት
፵፯ ኆኅተ ምሥራቅ
፵፰ ሐመልማለ ወርቅ
፵፱ ፍኖተ ሕይወት
፶ ተቅዋም ዘወርቅ
፶፩ ጽላተ ኪዳን
፶፪ ጽላተ ሕግ
፶፫ ዳግሚት ሰማይ
፶፬ ምሥጢረ ስብሐት
፶፭ የእሴይ ሥር
፶፮ ምልእተ ጸጋ
፶፯ ምልእተ ክብር
፶፰ ምልእተ ፍስሐ
፶፱ የሕዝቅኤል አዳራሽ
፷ መቅደስ
፷፩ የኤልያስ መሶበ ወርቅ
፷፪ ሐረገ ወይን
፷፫ ሰአሊተ ምሕረት
፷፬ ሀገረ እግዚአብሔር
፷፭ የገብርኤል ብሥራት
፷፮ አቁራሪተ መዐት
፷፯ ቅድስተ ቅዱሳን
፷፱ ሕሪተ ክብር
፸ ንጽሕተ ንጹሐን
፸፩ እመ ብዙኃን
፸፪ ድንግል
፸፫ ውድስት
፸፬ ልዕልት
፸፭ ብጽዕት
፸፮ ማኅደረ ሰላም
፸፯ ማዓርገ ሕይወት
፸፰ ቤተ ሃይማኖት
፸፱ ማኅደረ ስብሐት
፹ ማኅደረ ትፍሥሕት
፹፩ የሰማዕታት እናት
፹፪ የመላእክት እህት
፹፫ የነብያት ትንቢት
፹፬ የአዳም ተስፋ
፹፭ እመ አምላክ
፹፮ እመ ብርሃን
፹፯ የሐዋርያት ሞገስ
፹፰ ርኅርተ ልብ
፹፱ የሲና ዕፀ ጳጦስ
፺ የአቤል የውሐት
፺፩ ሙጻአ ፀሐይ
፺፪ ታቦት ዘዶር
፺፫ ምልእተ ውዳሴ
፺፬ የደስታ መገኛ
፺፭ አዳም ቆማ
፺፮ ምዕራግ
፺፯ የሴት ቸርነት
፺፰ የሄኖክ ደግነት
፺፱ እግዝትእነ ማርያም
፻ ቡርክት
፻፩ የቅዱስ ኤፍሬም ባራኪ
፻፪ ጽርሐ ንጽሕት
፻፫ ማኅደረ መለኮት
፻፬ እምነ ጽዮን
፻፭ እሙ ለአማኑኤል
፻፮ መዝገበ ብርሃን
፻፯ ሙዳዬ መና
፻፰ ጽጌ ሃይማኖት
፻፱ እህቱ ለሙሴ
፻፲ ርግበ ጸዐዳ
፻፲፩ ነዬ ሠናይት
፻፲፪ ገራሕቱ ለአብርሃም
፻፲፫ ደብተራ ፍጽምት
፻፲፬ ብርሃነ ቅዱሳን
፻፲፭ መድኃኒተ ይእቲ
፻፲፮ ወለቱ ለዳዊት
፻፲፯ ማርያም ቅድስት
፻፲፰ ወለተ ሀና ወእያቄም
፻፲፱ ሐመልማለ ገነት
፻፳ አክሊለ ንጹሐን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

28/12/2022
🇺🇬 ዩጋንዳ በዩጋንዳ 102 ልጆችና 568 የልጅ ልጆች አባት የሆነዉ ግለሰብ በስተመጨረሻ የወሊድ መከላከያ ለመጠቀም ወሰነ የ67 አመቱ ኡጋንዳዊ ገበሬ መዚ ሙሳ ሃሳህያ ከ12  ሚስቶች 102...
28/12/2022

🇺🇬 ዩጋንዳ

በዩጋንዳ 102 ልጆችና 568 የልጅ ልጆች አባት የሆነዉ ግለሰብ በስተመጨረሻ የወሊድ መከላከያ ለመጠቀም ወሰነ

የ67 አመቱ ኡጋንዳዊ ገበሬ መዚ ሙሳ ሃሳህያ ከ12 ሚስቶች 102 ልጆች እና በስሙ 568 የልጅ ልጆች በማስመዝገብ ግዙፍ ቤተሰብ መስርቷል።

ከአንድ በላይ ማግባት ህጋዊ በሆነበት የትውልድ መንደር ሉሳካ በአስከፊ ድህነት ውስጥ ሃሳህያ ቢያድግም በቂ ሀብትና ክብር በማካበት ለብዙ አስርት አመታት የመንደር ሊቀ መንበር ሆኖ ለመሾም እና ለማግባት ሲተጋ ቆይቷል።

ሃሳህያ የመጀመሪያ ሚስቱን በ1971 በ16 ዓመቷ ያገባ ሲሆን 12 እስኪሞሉ ድረስ አዳዲስ ሚስቶችን ማግባቱን ቀጥሏል።

አባቴ ሁለት ልጆችን ብቻ ስለወለደ፣ ዘራችን ሊጠፋ ይችላል የሚል ስጋት ነበረብኝ ሲል ገልጿል፡፡

ሟቹ አባቴ ምዋማዲ ሙዱምባ ሁለት ሚስቶች ነበሩት ግን ሁለት ልጆችን ብቻ ነው የወለደው። ይህም የቤተሰባችን የመጥፋት አደጋ ላይ ጥሏል ሲሉ መዚ ሙሳ ሃሳህያ ለኡጋንዳው ሞኒተር ጋዜጣ ተናግረዋል።

ከሃሳህያ ልጆች መካከል አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት ከእሱ እና ከሚስቶቹ ጋር አብረው የሚኖሩ ሲሆኑ የተቀሩት ደግሞ ወጥተው የራሳቸው ቤተሰብ መስርተዋል።

የ67 ዓመቱ አርሶ አደር በቤት ውስጥ ያሉትን ልጆች በስም እንደማያውቃቸው ተናግሯል።ከዚህ በኃላ ባለው ህይወቱ የወሊድ መከላከያ ለመጠቀም መወሰኑን ገልጿል።

Via ዳጉ ጆርናል

🥺🥺🥺

🌴🌴🌴

27/12/2022

Yohannes Ambachew -እንዳላይ

27/12/2022

Yohannes Ambachew - እንድላይ

ጥርን በአማራ ክልል‼️ ~~~~~ ❶ ታህሳስ 26-30 የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ከአስዳማሚው የቤዛ ኩሉ ሥነ-ሥርዓት ጋር - በላሊበላ፣❷ ጥር 6 የዳግማዊ ቴዎድሮስ የልደት በዓል - በ...
26/12/2022

ጥርን በአማራ ክልል‼️
~~~~~
❶ ታህሳስ 26-30 የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ከአስዳማሚው የቤዛ ኩሉ ሥነ-ሥርዓት ጋር - በላሊበላ፣

❷ ጥር 6 የዳግማዊ ቴዎድሮስ የልደት በዓል - በጎንደር፣

❸ ጥር 10 የከተራ በዓል - በጎንደር፣ በላሊበላ፣ በምንጃር ሸንኮራ፣ በባህር ዳር እና በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች፣

➍ ጥር 11 የጥምቀት በዓል - በጎንደር፣ በላሊበላ፣ በምንጃር ሸንኮራ፣ በባህር ዳር እና በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች፣

➎ ጥር 12 የዘገሊላ በዓል - በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች፣

❻ ጥር 13 የግዮን በዓል - በሰከላ ወረዳ - ግሽ ዓባይ፣

❼ ጥር 14-15 የጀልባ ቀዘፋ ትርኢት - በባህር ዳር፣

❽ ጥር 18 የሰባር ጊዮርጊስ የንግሥ በዓል - በባህር ዳር፣ ደብረ ብርሃን፣ ደሴ እና በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች፣

❾ ጥር 21 የአስተርዮ ማርያም በዓል - በግሸን፣ በመርጡለ ማርያም፣ በደረስጌ እና በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች፣

❿ ጥር 23 የ83ኛው የአገው ፈረሰኞች ማህበር ክብረ በዓል - በእንጅባራ፣

⓫ ጥር 25 የመርቆርዮስ በዓል - በደብረ ታቦር፣
----
ይምጡ! በልዩ ልዩ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ስነስርዓቶች ደምቀውና ተውበው በሚከበሩ በዓላት ላይ ይታደሙ!

አህያ ለነብር እንዲህ አለው።  "ሣር ሰማያዊ ነው" ነብሩም መለሰ፡- "አይ፣ ሣር አረንጓዴ ነው."ክርክሩ ጦፈ።  እናም ሁለቱ ጉዳዩን ለግልግል ለማቅረብ ወሰኑ። ይህን ለማድረግ ወደ ጫካው ን...
14/12/2022

አህያ ለነብር እንዲህ አለው።
"ሣር ሰማያዊ ነው"

ነብሩም መለሰ፡-
"አይ፣ ሣር አረንጓዴ ነው."

ክርክሩ ጦፈ። እናም ሁለቱ ጉዳዩን ለግልግል ለማቅረብ ወሰኑ። ይህን ለማድረግ ወደ ጫካው ንጉስ አንበሳ ቀረቡ።

አንበሳው በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ወደነበረበት ጫካ ከመድረሳቸው፣ አህያው እንዲህ በማለት ይጮህ ጀመር።

"ክቡርነትዎ ሣር ሰማያዊ ነው አይደል?’’

አንበሳውም

"እውነት ነው። ሣር ሰማያዊ ነው። ‘’ ሲል መለሰ።

አህያው በአሸናፊነት ስሜት እየዘለለ ንግግሩን ቀጠለ።

"ነብር ከእኔ ጋር መስማማት አልቻለም። እኔን ይቃረናል፤ እባክዎን ይቅጡት። ''

ከዚያም ንጉሱ

"ነብር 5 አመት በፅሞና/በዝምታ ይቆይ ዘንድ ቅጣት ተጥሎበታል።" በማለት ፍርድ ሰጡ።

አህያው በደስታ እየፈነደቀ ብድግ ብሎ መንገዱን ቀጠለ፤ እየደጋገመም:-

"እየሰማችሁ! ሣር ሰማያዊ ነው"...በማለት ጩኸቱን ቀጠለ።

ነብር ቅጣቱን ተቀበለ፣ ነገር ግን

"ግርማዊነትዎ ግን ለምን ቀጡኝ? ለመሆኑ ሣር ለምለምና አረንጓዴ አይደል እንዴ?’’ በማለት አቤቱታውን አቀረበ።

አንበሳውም

"በእርግጥ ሣር አረንጓዴ ነው" ሲል አረጋገጠለት።

"ታዲያ ለምን ይቀጡኛል?"

አንበሳውም፤

"ይህ ሳሩ ሰማያዊ ወይም አረንጓዴ ነው ከሚለው ጥያቄ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ቅጣቱም እንዳንተ ያለ ደፋርና አስተዋይ ፍጡር ከአህያ ጋር ሲከራከር ጊዜ ማጥፋት ስለሌበትና በዚያ ላይ ይህን አይነት የወረደ ጥያቄ ይዞ መጥቶ እኔን ሊያስጨንቀኝ ስለማይገባ ነው።’’ ሲል መለሰለት ይባላል።
---------+++++ ----------

በጣም የከፋው የጊዜ ብክነት ፍላጎቱ የይስሙላ ድል ማግኘት ብቻ እንጂ ለእውነት ደንታ ከሌለው ቂል እና አክራሪ ጋር መጨቃጨቅ ነው።

ምንም ትርጉም በሌላቸው ውይይቶች ላይ ጊዜህን አታባክን...

የቀረቡላቸውን ማስረጃዎች ሁሉ የመረዳት አቅም የሌላቸው፣ በትዕቢት፣ በጥላቻና በበታችነት ስሜት የታወሩ ብዙ ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች የሚፈልጉት ብቸኛው ነገር እነሱ ትክክል ባይሆኑም እንኳ ትክክል መሆን ነው።

አስተውል!

አላዋቂ ሲጮህ ብልህ ዝም ይላል!!!

ካላስፈላጊ ክርክር የአንተ ሰላም እና መረጋጋት የበለጠ ዋጋ አለው!

ነብስህ በሰላም ትረፍ
13/12/2022

ነብስህ በሰላም ትረፍ

24/10/2021

ቆንጆ ግጥምና ዜማ ከፈለጉ በውስጥ መስመር ያናግሩኝ

ፍትህ ለኢትዮጵያ ፍትህ ለእስክንድ ነጋሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይክ ሽር ያድረገው
22/10/2021

ፍትህ ለኢትዮጵያ
ፍትህ ለእስክንድ ነጋ
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይክ ሽር ያድረገው

በቅርብ ቀን አዲስ ነገር ለኢትዮጵያን እስከዛው ላይክ ሸር and follow it
20/10/2021

በቅርብ ቀን አዲስ ነገር ለኢትዮጵያን እስከዛው ላይክ ሸር and follow it

አንድ ተወዳጅ አርቲስት ።ታላቅጥበብን የተቸረው ነገር ግን ሰሞኑን ሰለሱ ከፈኝ ግን እንዲህ ብሎ አዚሞ ሰለነበር ተስፍ አልቆርጥም ተወዳጁ #ቴዎድሮስ ታደሰ (ያሰብከው ባይሞላም) ያሰብከው ባይ...
13/10/2021

አንድ ተወዳጅ አርቲስት ።ታላቅጥበብን የተቸረው ነገር ግን ሰሞኑን ሰለሱ ከፈኝ ግን እንዲህ ብሎ አዚሞ ሰለነበር ተስፍ አልቆርጥም ተወዳጁ #ቴዎድሮስ ታደሰ (ያሰብከው ባይሞላም) ያሰብከው ባይሞላምያልከው ባይሳካም
ያለምከው ቢጠፋ
ወዳጅ ፊቱን ቢያዞር በውሎህ ባትረካ
አትዘን እንግዲህ ከቶ አትቁረጥ ተስፋ
ጊዜ ሰው ሲፈትን እምነትን ሲከዳ
እውነትም በተራው እውነትነት ሲያጣ
ህሊናህ ካልከዳህ ወዝህን ብታጣም
ከማገገም በቀር ድካም አይበጅህም
ወዳጅ ፊቱን ቢያዞር በውሎህ ባትረካየዕለት ውል የቀን ቁርስ በዝምታ አይመጣም
የዘመን ኩርንችት በለስ አያወጣም
ድርሻህን ተወጣ ተስፋን ላበደረህ
ንፉግ አይባልም ያለውን የቸረ
ኧረ እንዲያው ዝምታስ ምን ሊሆን
ልብ እየተረታ ሆድ እያመነታ
አንደበትህ ታስሮ በጊዜ አትረታ
ጉም ጉሙን ትተህ ተናገር ለአንድ አፍታ
ልብም እንደ ባዳ ከክህደት ተማክሮ
እውነት በሆድ ይዞ እውነት ተቸግሮ
የነገን ሳይቋጨው በተስፋ ውሎ አድሮ

ድካም ይጫነዋል እድሜ ብዙ ቆጥሮ
አዬ ጉድ አዬ ጉድ ይላል የሃገሬ ሰው
ትዝብቱ ታምቆ ሆዱን ሲያላውሰው
ቀኑም ቢጨላልም ለሊቱም ቢነጋ
ላያልፍ አያለፋም ከሀሰት አትጠጋ
ያሰብከው ባይሞላም ያልከው ባይሳካ
ያለምከው ቢጠፋ
ወዳጅ ፊቱን ቢያዞር በውሎህ ባትረካ
አትዘን እንግዲህ ከቶ አትቁረጥ ተስፋ
ጌታም አይጣላህ ሳይደግስ ሳይዘክር
እውነት ከቤት ይዘህ በብድር አትመስክር
ሆድ ከሃገር አይበልጥም ግን ከሃገር ይሰፋል
የወለዱት እንጂ ቃል እንዴት ይጠፋል
ቅጥፈትን ጸጋ አድርጎ ለምኖ ያደረ
አትሁን እንግዲህ ነገ ነው ያማረ
ጎዳናህ ሐቅ ይሁን ውልህን አትርሳ
ዳግም አይጎዳም ወድቆ የተነሳ
ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው
ምንድነው ዝምታዬ
ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው
ገላዬን ሳይከዳው
ምን ይሆን ሚስጥሩ
የዛሬው ዝምታዬ
ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው
ምንድነው ዝምታዬ
ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው
ገላዬን ሳይከዳው
ሃሳብ ያደረው
ምንድነው ቅሬታዬ
ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው
ምንድነው ዝምታዬ
ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው
ገላዬን ሳይከዳው
ምን ይሆን ሚስጥሩ
የዛሬው ዝምታዬ
ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው
ምንድነው ዝምታዬ
ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው
ገላዬን ሳይከዳው
ሃሳብ ያደረው
ምንድነው ቅሬታዬ
ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው
ምንድነው ዝምታዬ
ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው

09/10/2021

መዚቃ መስራት ፈልገው ግጥም ተቸግረዋል ።ለዝነኛው ገጣሚ ዮሐንስ አምባቸው ያማክሩት
+251940659695

ቃለ መሃላ ፈጽመዋል  | ተሹመዋል1. አቶ ደመቀ መኮንን:  ም/ጠ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር2. ዶ/ር  አብርሃም በላይ: የአገር መከላከያ ሚኒስትር3. አቶ አህመድ ሽዴ: የገንዘብ ...
06/10/2021

ቃለ መሃላ ፈጽመዋል

| ተሹመዋል

1. አቶ ደመቀ መኮንን: ም/ጠ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
2. ዶ/ር አብርሃም በላይ: የአገር መከላከያ ሚኒስትር
3. አቶ አህመድ ሽዴ: የገንዘብ ሚኒስትር
4. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል: የሥራና ክህሎት ሚነስትር
5. አቶ ኡመር ሁሴን: የግብርና ሚኒስትር
6. ኢንጂ. አይሻ መሐመድ: የመስኖና ቆላማ አከባቢዎች ሚኒስትር
7. ዶ/ር ኢነጂ ሀብታሙ ኢተፋ: የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር
8. ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ: የትምህርት ሚኒስትር
9. ወ/ሮ Dagmawit Moges : የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር
10. አቶ ገብረመስቀል ጫላ: የንግድና ቀጠናዊ ትስስር
11. አቶ መላኩ አለበል: የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
12. አቶ ብናልፍ አንዷለም: የሰላም ሚኒስትር
13. ዶ/ር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ: የፍትህ ሚኒስትር
14. ዶ/ር Lia Tadesse, Minister of Health (የጤና ሚኒስትር)
15. አቶ በለጠ ሞላ ጌታሁን: የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
16. አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ: የቱሪዝም ሚኒስቴር
17. አቶ ላቀ አያሌው: የገቢዎች ሚኒስትር
18. ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ: የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር
19. ኢንጂ. ታከለ ኡማ: የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር
20. ዶ/ር ፍጹም አሰፋ: የፕላን ልማት ሚኒስትር
21. ዶ/ር Ergogie Tesfaye : የሴቶችና ማህበራዊ ሚኒስትር እና
22: አቶ ቀጄላ ቱሉ: የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ናቸው።

02/10/2021

አዳም ሂዋን ተመልከቱት

30/09/2021

#ኢትዮጵያ ሀገሬ በልጆችሽ ኩሪ
ሞልቷል ብዙ ጄግና ድንበር አስከባሪ።

Nice
30/09/2021

Nice

#ኢትዮጵያ ሀገሬ በልጆችሽ ኩሪ
ሞልቷል ብዙ ጄግና ድንበር አስከባሪ።

ሃይለ እየሱስ ፈይሰረ በቅርብ ቀን ሌሎችም ከሙዚቃው ጋ የተያያዙ መረጃዎች እንዲደርሰዎት follow dishta gina
29/09/2021

ሃይለ እየሱስ ፈይሰረ በቅርብ ቀን ሌሎችም ከሙዚቃው ጋ የተያያዙ መረጃዎች እንዲደርሰዎት follow dishta gina

እኔም ለወገኔ አለሁ ለአዳም ለሂዋን ፔጁን ላይክ 300ኮሜንት 400ሽር 500
18/09/2021

እኔም ለወገኔ አለሁ
ለአዳም ለሂዋን
ፔጁን ላይክ 300
ኮሜንት 400
ሽር 500

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when New art and event posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share