05/11/2024
#ደብረማርቆስ
ይህች የምትመለከቷት ወጣት ለስራ ወደ መናሃሪያው አካባቢ ትሄዳለች፡፡
በሄደችበት አጋጣሚ አንድ ማየት የተሳነው ሰው ማዳበሪያ ተሸክሞ ታየዋለች፡፡
ይህች ንጽህ የለበሰች ከተሜ ወጣት ልብሴ ይቆሽሻል ብላ ለአለባበሷ አልተጨነቀችም፡፡ ይልቁንም ግለሰቡ የሚሄድበትን ከጠየቀች በኋላ ማዳበሪያውን ተሸክማ ለሚፈልግበት አድርሳው ተመለሰች፡፡
አለባበስን አይቶ መፍረድ ደግነትን ከልብስ ጋር ማዛመድ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ እድሜና ጤና ይስጥሽ በሉልኝ ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው፡፡
🙏🙏🙏