Daily News Ethiopian

Daily News Ethiopian news page

Subscribe አድርጉ ቤተሰብየአቡነ አብረሀምና የአብይ ፍጥጫ ገብታችሁ እዩት !ይሄን ቻናል ሰብስክራይብ አድርጉ ሁላችሁም❗️
16/03/2024

Subscribe አድርጉ ቤተሰብ
የአቡነ አብረሀምና የአብይ ፍጥጫ ገብታችሁ እዩት !
ይሄን ቻናል ሰብስክራይብ አድርጉ ሁላችሁም❗️

የአቡነ አብረሀም እና የአብይ ፍጥጫ

ትላንት ለመምህራን ከወጡ 435 ቤቶች ውስጥ እንዲህም አይነት ነገር ታይቷል፣ አንድ ሰው ሁለት ግዜ! በርካታ ቅሬታ አቅራቢዎች ባደረሱኝ አስተያየት የመምህራን የቤት እጣ መውጣቱ ጥሩ ሁኖ ሳለ...
16/03/2024

ትላንት ለመምህራን ከወጡ 435 ቤቶች ውስጥ እንዲህም አይነት ነገር ታይቷል፣ አንድ ሰው ሁለት ግዜ!

በርካታ ቅሬታ አቅራቢዎች ባደረሱኝ አስተያየት የመምህራን የቤት እጣ መውጣቱ ጥሩ ሁኖ ሳለ አንድ ሰው ሁለት ግዜ መቅረቡ ግርምታን ፈጥሯል፣ ይህም የገባው ዳታ የተደጋገሙ ስሞች ያሉበት ነው ብለው እንዲጠረጥሩ እንዳደረጋቸው ገልፀዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ "ይህ እንደ ኮንዶሚኒየም እጣ አወጣጥ እንኳን በሺዎች ያሉበት ዝርዝር አይደለም፣ 435 ብቻ ነው፣ እንዴት በዚች ትንሽ ቁጥር እንዲህ አይነት ድግግሞሽ ሊኖር ይችላል" ብለው ጠይቀዋል።

የሚመለከተው አካል መልስ ከሰጠበት እመለስበታለሁ።

 #መልካምአንድነት ቦታው የሃዋሳዋ ወሰንተኛ ቢሻን ጉራቻ ከተማ ነው። በዛሬው ዕለተ ቅዳሜ የጥቁር ውሃ ማሪያም ህንፃ ቤተክርስቲያን አርማታ ሙሌት የሚከናወንበት ነው። እናም ምዕመኑ ከሃዋሳ፣ ...
16/03/2024

#መልካምአንድነት ቦታው የሃዋሳዋ ወሰንተኛ ቢሻን ጉራቻ ከተማ ነው።

በዛሬው ዕለተ ቅዳሜ የጥቁር ውሃ ማሪያም ህንፃ ቤተክርስቲያን አርማታ ሙሌት የሚከናወንበት ነው። እናም ምዕመኑ ከሃዋሳ፣ ከጥቁር ውሃ እና አካባቢው ተሰባስቦ ስራውን ከልቡ እያከናወነ ነው።

እናም በስራው ላይ ይህንን ተመለከትኩ። ሰው የስራ ልብስ የለበሰ በመሆኑ ሃይማኖቱ ይሄ ነው ብሎ መለየት አይቻልምና ሁሉም አንድ ሆኖ በአንድነት እየሰራ ነው። ትንሽ እረፍት ፈለኩና ከዛፍ ስር እንዳለሁ፣ ይሄው እነዚህ ስራ ላይ የነበሩ የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድሞቻችን የሶላት ሰዓት ደርሶባቸው ከህንፃ ቤተክርስቲያኑ አናት ላይ ወርደው ሲሰግዱ አገኘኋቸውና ፈቃዳቸውን ጠይቄ ፎቶ አነሳኋቸው።

የመልካም አንድነት፣ የመቻቻል ማሳያ ነው።

አየ ሰው ከስፍራው ያደረሰኝ መረጃ ነው።

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ አለአግባብ የወሰዱት ገንዘብ ካለ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድና ተማሪዎቹ በሕግ እንደሚጠየቁ አሳስቧልትናንት መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ...
16/03/2024

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ አለአግባብ የወሰዱት ገንዘብ ካለ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድና ተማሪዎቹ በሕግ እንደሚጠየቁ አሳስቧል

ትናንት መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከኢትዮጰያ ንግድ ባንከ ኤ.ቲ.ኤም ማሽን የሌላቸውን ገንዘብ ወጪ ያደረጉ የተቋሙ ተማሪዎች በፍጥነት በቅሊንጦ ቅርንጫፍ በመቅረብ እንዲመልሱ አሳስቧል።

ወጪ ያደረገውን ገንዘብ የማደመልስ ተማሪ ላይ ዩኒቨርሲቲው አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድና ተማሪዎቹ በሕግ እንደሚጠየቁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በተመሳሳይ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከትክክለኛ ሒሳባቸው ውጪ ገንዘብ ወጪ ያደረጉ ተማሪዎች የራሳቸው ያለሆነውን ገንዘብ በአስቸኳይ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የትኛውም ቅርንጫፍ በመሔድ ተመላሽ እንዲያደርጉ በጥብቅ አሳስቧል።

ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ …የአዲስ አበባ-ደሴ መንገድ መዘጋት የከፋ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ማሳደሩ ተገለጸከአዲስ አበባ በደብረ ብርሃን መንገድ በኩል ወደ ደሴ የሚደረገው የየብስ ትራንስ...
16/03/2024

ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ …

የአዲስ አበባ-ደሴ መንገድ መዘጋት የከፋ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ማሳደሩ ተገለጸ

ከአዲስ አበባ በደብረ ብርሃን መንገድ በኩል ወደ ደሴ የሚደረገው የየብስ ትራንስፖርት መቋረጡ ለከፋ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ ዳርጎናል፤ ሲሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና የሰሜን ሸዋ ዞኖች ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡

አስተያየት ሰጭዎቹ፥ ሕክምና ለማግኘት ተቸግረናል፤ የሸቀጥ ዋጋ ከዕጥፍ በላይ ጨምሯል፤ አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት ወደ ገበያ ለማቅረብ አልቻለም፤ ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በሰንበቴ ከተማ አካባቢ፣ ሕክምና መውሰድ የነበረባቸው አምስት እናቶች መንገዱ ስለተዘጋ በወሊድ ምክንያት እንደሞቱ፣ የከተማው ጤና ጣቢያ አመልክቷል፡፡

በተመሳሳይ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ከአጣዬ ከተማ አካባቢ፣ ለተሻለ ሕክምና በሌላ መንገድ በመወሰድ ላይ የነበረ አንድ ሕፃን፣ ወደ ሕክምና ተቋም ሳይደርስ ሕይወቱ እንዳለፈ፣ አንድ የጤና ባለሞያ ጠቁመዋል፡፡

ሌላው የአጣዬ ከተማ ነዋሪም፣ ቀደም ሲል ከተማዋ ከ10 ለማያንስ ጊዜ ቃጠሎ እንደተፈጸመባት አውስተው፣ ከዚያ ጥፋት ሳታገግም ለሌላ ጉዳት ተዳርጋለች፤ ብለዋል፡፡

የሁለቱ ሃይማኖቶች አጽዋማት እየተፈጸሙ ባለበት ወቅት መንገዱ መዘጋቱ ደግሞ፣ የሸቀጥ አቅርቦት እጥረቱ እንዲባባስ ማድረጉን፣ አስተያየት ሰጭዎቹ አስረድተዋል፡፡
Via:VOA

አዲስ አበባ‼️             ነገ መጋቢት 8  በአዲስ አበባ ከተማ  በመስቀል አደባባይ ከሰዓት በሗላ ከቀኑ 7፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ  የኢትዮጲያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክር...
16/03/2024

አዲስ አበባ‼️

ነገ መጋቢት 8 በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ከሰዓት በሗላ ከቀኑ 7፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጲያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የፀሎት መርሐ-ግብር ስለሚያከናውኑ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት:—

✔ ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ኡራኤል አደባባይ ላይ

✔ ከቦሌ ጌቱ ኮሜርሻል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ በታች እና በላይ እንዲሁም ግራና ቀኝ

✔የቀድሞው አራተኛ ክፍለጦር (ጥላሁን አደባባይ ላይ )

✔ ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት ላይ

✔ ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ

✔ ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ

👉መንገዶቹ ከጠዋቱ 4፡ 00 ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

👉አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ፕሮግራሙ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ጨምሮ ገልጿል፡፡

ገብታችሁ እዩት 👀👀🤔 እየገባችሁ ሰብስክራይብም አድርጉ 1 ሺህ መሙላት አለበት !
15/03/2024

ገብታችሁ እዩት 👀👀🤔 እየገባችሁ ሰብስክራይብም አድርጉ 1 ሺህ መሙላት አለበት !

ፍቅርሲዝም ምንድነው የሚለው ትግራይ ?

ዘመድኩን በቀለ  በቀጥታ
13/03/2024

ዘመድኩን በቀለ በቀጥታ

ዘመድኩን በቀለ በ TikTok live አሁን

17/02/2024

በዝግ የተደረገው የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ላይ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ስለ ወደብ ጉዳይ ያረገው የተቀነጨበች ንግግር ።

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/Daily_News_Ethiopian

ኮካኮላ የሸራተን የአዲስ አመት ዋዜማ ኮንሰርት ስፖንሰር መሰረዙን ገለፀስፓንሰርሺፕ አጋርነት መሰረዛችንን ስለማሳወቅበአዲሱ ዓመት ዋዜማ በሸራተን አዲስ ሊከናወን የተሰናዳውን የሙዚቃ ድግስ ድ...
05/09/2023

ኮካኮላ የሸራተን የአዲስ አመት ዋዜማ ኮንሰርት ስፖንሰር መሰረዙን ገለፀ

ስፓንሰርሺፕ አጋርነት መሰረዛችንን ስለማሳወቅ
በአዲሱ ዓመት ዋዜማ በሸራተን አዲስ ሊከናወን የተሰናዳውን የሙዚቃ ድግስ ድርጅታችን ኮካ-ኮላ ቤቭሬጅስ አፍሪካ~ኢትዮጵያ ስፖንሰር አጋር የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

ነገር ግን በልዩ ልዩ ምክንያቶች የስፓንሰርሺፕ አጋርነታችንን የሰረዝን መሆኑንና የፕሮግራሙ አጋር አለመሆናችንን እናሳውቃለን።
ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አማ (ኮካ-ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ~ኢትዮጵያ)

ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ በሸራተን አዲስ ለአዲስ አመት የምታቀርበውን የሙዚቃ ኮንሰርት የኃይማኖት አባቶችን ትዕዛዝ በማክበር እንደሰረዘች ገለፀች።እኔ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ጳጉሜ 6 በሸራተን አ...
05/09/2023

ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ በሸራተን አዲስ ለአዲስ አመት የምታቀርበውን የሙዚቃ ኮንሰርት የኃይማኖት አባቶችን ትዕዛዝ በማክበር እንደሰረዘች ገለፀች።

እኔ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ጳጉሜ 6 በሸራተን አዲስ ለአዲስ ዓመት ዋዜማ የሙዚቃ ስራዬን ለማቅረብ ተፈራርሜ የተዘጋጀሁ ቢሆንም ይህን ስራ በመሰረዜ የሚያስከፍለኝ ዋጋ ቢኖርም ከሁሉም በላይ በቃሏ የምመራላት ቤትክርስትያን ሀይማኖት አባቶቼን ትዕዛዝ በመቀበል የማቀርበውን የሙዚቃ ስራ ሰርዤአለሁ !

ለውድ አድናቂዎቼ እንዲሁም የፕሮግራሙ አዘጋጆች ይቅርታ እየጠየኩ በሌላ ዝግጅት እንደማስደስታችሁ እና እንደምንገናኝ ስገልፅላችሁ በታላቅ አክብሮት እና ምስጋና ነው!

ኩኩ ሰብስቤ

05/09/2023

ነገ በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ነፃ ነው ተባለ

ነገ ጷግሜን 1/2015 ዓ.ም የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ በከተማ አውቶብስና በቀላል ባቡር የነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ እንደሆነ ተገልፇል።

በስልጤ የኦርቶዳክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆኑ ቤቶች ተለይተው ተቃጠሉ።ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ አስተዳደር ትናንት ማታ የኦርቶዳክስ...
05/09/2023

በስልጤ የኦርቶዳክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆኑ ቤቶች ተለይተው ተቃጠሉ።

ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)

በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ አስተዳደር ትናንት ማታ የኦርቶዳክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆኑ ቤቶች ተለይተው መቃጠላቸውና አሁንም በምእመናን ላይ ማስፈራራት እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ተገልጿል።

የሙስሊም ተማሪዎች ላይ ድግምት ተደርጓል በሚል ምእመናን ለወራት ዛቻና ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው የቆየ ሲሆን በትላንትናው እለት ነሐሴ 29 ማታ ግን ቤታቸው ተለይቶ እንደተቃጠለ እና የንግድ ሱቆቻቸው ላይም ቃጠሎና ዝርፊያ መፈጸሙን ነው የተገለጸው።

የጸጥታ ኃይሎች በመድረስ ለጊዜው መቀነስ ቢችልም አሁንም ቤተ ክርስቲያን እናቃጥላለን ፤ ምእመናንንም እንጎዳለን በማለት የውስጥ ለውስጥ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው የሚል መረጃ እየደረሰን በመሆኑ ስጋት ላይ ነን ፤ በርካታ ምእመናንም ከቤታቸው እየሸሹ ነው ብለዋል ሲል ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት ዘግቧል።

በተለያዩ ጊዜያት ለከተማ አስተዳደሩና ለሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ቢቆዩም ይሄ ነው የሚባል ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል ፤ በስልጤ ዞን አስቀድሞም በተለያዩ ዓመታት አብያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸው፣ ምእመናን መገደላቸውና መሰደዳቸው ይታወቃል።

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

ቅዱስ ሲኖዶስ የጷጉሜን 6 ቀናት ጸሎተ ምህላ እንዲኖር አወጀ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የጷጉሜን 6 ቀናት ጸሎተ ምህላ እንዲኖር አወጀ። ዛሬ ነሐሴ 29 ቀን ...
04/09/2023

ቅዱስ ሲኖዶስ የጷጉሜን 6 ቀናት ጸሎተ ምህላ እንዲኖር አወጀ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የጷጉሜን 6 ቀናት ጸሎተ ምህላ እንዲኖር አወጀ።

ዛሬ ነሐሴ 29 ቀን 2015 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና በአቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በተሰጠው መግለጫ መሰረት የጷጉሜን ወር 6 ቀናት መላው ኦርቶዶክሳዊ በጸሎት እና በምህላ እንዲያሳልፍ መታወጁን ነው የገለጹት።

በመግለጫውም ዘመኑ ከደስታ እና የምስራች ይልቅ ሀዘንን የምንሰማበት ዘመን ስለሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የተቸገሩትን የተራቡትን ፣ የተፈናቀሉትን እና የተጎዱትን እያሰቡ በጾም እና በጸሎት እንዲያሳልፉ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ 13ተኛ ወር በሆነችው ወርሐ ጷጉሜ እለተ ምጽዓትን የምናስብበት ፤ ሠማይ የሚከፈትበት ፤ ጸሎት የሚሰማበት ሚስጥራዊ የሆነች ወር ነችና የበደሉንን ይቅር ብለን በንጹሕ ልቦና የቻልን ጾመን ያልቻልን በጸሎት እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት እና የምንለምንበት ወር ሊሆን ይገባል ሲሉ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው የቤተ ክርስቲያን በዓላት ሲደርሱ ከሥርዓቷ እና ከአስተምሮዋ ውጪ በ ሆነ መልኩ የተለያዩ አካላት የዳንኪራ ጥሪ በማዘጋጀት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አግባብነት የሌለው መሆኑን እና ምዕመናንም ከዚህ እንቅስቃሴ እራሳቸውን ሊያርቁ ይገባል ነው ያሉት።

የማትደፈረዋን እና የማትነካዋን ቤተክርስቲያን የሚነኩ ሰዎች በዝተዋል ፤ ቀጣዩ ዓመትም ኢትዮጵያውያን በሰላም በፍቅር የምንኖርበት የሚራቡ የሚፈናቀሉ የሚያዝኑ ሰዎች እንዳይኖሩ ሁሉም ምዕመን ጠዋት ኪዳን ከሰዓት በሠርክ ጸሎት በየአብያተ ክርስቲያን በመሄድ ያልቻለም በየቤቱ ሊጸልይ ይገባል ብለዋል።

© ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

«ልጅ ያሬድ በሚል የሚታወቀው ያሬድ ዘላለም ላይ የማድረገውን ምርመራ አጠናክሬ እቀጥላለሁ ›› ፌደራል ፖሊስየፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጄይላን አብዲ ‹‹ በመታወቂያ ስሙ ያሬድ ዘ...
04/09/2023

«ልጅ ያሬድ በሚል የሚታወቀው ያሬድ ዘላለም ላይ የማድረገውን ምርመራ አጠናክሬ እቀጥላለሁ ›› ፌደራል ፖሊስ

የፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጄይላን አብዲ ‹‹ በመታወቂያ ስሙ ያሬድ ዘላለም በቅፅል ስሙ ደግሞ ልጅ ያሬድ በሚል የሚታወቀው ግለሰብ ላይ የማድረገውን ምርመራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ›› ለአሻም ነግረዋታል፡፡

ከሰሞኑ ‹‹ ልጅ ያሬድ ›› በሚል ቅፅል ስም የሚጠራዉ የቀድሞ ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም በተረጋገጥ የፌስቡክ ገፁ ‹‹ የአንድ ትልቅ የእምነት ተቋምን ክብር በሚያጎድፍ መልኩ ባስተላለፈዉ ጸያፍና ማንንም ብሄር በማይወክል መልዕክት ምክንያት የፌደራል ፖሊስ ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም በቁጥጥር ስር እንዳዋለው ›› የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

‹‹ ግለሰቡ ተሰውሯራል፣ጠፍቷል እያሉ ያልተጣራና ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ የሚነዙና ኅብረተሰቡ ላይ ዉዥንብር የሚነዙ ›› ያሏቸው ‹‹ አካላት ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡም ›› አሳስበዋል፡፡

ጄይላን ሲቀጥሉ ‹‹ ይህን ከኢትጵያዊነት ያፈነገጠ ተግባር የፈጸመዉ ልጅ ያሬድ( ያሬድ ዘላለም) የተባለ ግለሰብ ከ3ቀናት በፊት የፌደራል ፖሊስ በቁጥጥሩ ስር አውሎት እንደሚገኝ ›› ጠቅሰው ‹‹ ህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲኖረው እንወዳለን ›› ሲሉ አክለዋል፡፡

‹‹ ግለሰቡ በማህበራዊ ሚዲያ ወጥቶ የአንድ ብሄር ተወካይ በሚመስል መልኩ ያስተላለፈው ግብረገብነት የጎደለው፣ የተወደደና የተከበረ የእምነት ተቋም ላይ ያስተላለፈው ጸያፍ ቃላቶች ታላቁን የኦሮሞ ህዝብም ሆነ የአማራን ህዝብ የሚወክል አይደልም ›› ሲሉም ነቅፈዋል፡፡

‹‹ ማንም ደግሞ ለዚህ ግለሰብ የሠጠዉ የእምነትም ሆነ የብሔር ውክልና የለም ›› በማለት ፌደራል ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቁዋል፡፡

‹‹ ሌሎችም ከእንዲህ ዓይነት ከኢትጵያዊነት ከወረደና የእምነት ተቋማትን በመሳደብ ህዝብን ለቁጣ የምታነሳሱና፣ አንድን ብሄረሰብ ከሌላዉ ለማጋጨት በተለያየ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች የምትቀሳቀሱ ከድርጊታቸዉ እንዲታቀቡ ›› አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ‹‹ ልጅ ያሬድ የተባለውን ግለሰብ እና ተባባሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሠረት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮን ›› ጠይቃለች፡፡

‹‹ በግለሰቡ እና ተባባሪዎቹ ድፍረት የተሞላበት ድርጊት በርካታ ኦርቶዶክሳዊያንም ኢትዮጵያውያንም ላይ ከፍተኛ ቁጣን በመቀስቀሱን እና ከፍትህ አደባባይ ፍርድን ስለሚጠብቁ ፖሊስን ለማገዝ ይሔን አቤቱታ አቅርቤያለሁ ›› ብላለች።

ቤተ ክርስቲያኗ አክላም ‹‹ የተከሳሹ ድርጊት በዋናነት የቤተ ክርስቲያኗን መልካም ስም የሚያጎድፍ ድርጊት፤ ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ጥላቻ በመግለጽ ሰዎችን ለአመጽ እና ብጥብጥ የሚያነሳሳ፤ የቤተክርስቲያንን የአምልኮ ቦታ ያራከሰ ፤ የምዕመናኑን ስሜት የሚነካ በመሆኑ ፣ በሚያዋርድ እና ቤተክርስቲያንን በሚያናንቅ መልኩ የተፈጸመ በመሆኑ በግለሰቡ እና በተባባሪዎቹም ላይ ጭምር ፖሊስ ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ክስ እንዲመሠርት ለአቃቤ ሕግም እንዲልክ ›› ጠይቃለች።

ዘገባው የአሻም ቴሌቪዥን ነው!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጅ ያሬድ የተባለውን ግለሰብ እና ተባባሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሠረት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮን ጠየቀች።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተ...
04/09/2023

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጅ ያሬድ የተባለውን ግለሰብ እና ተባባሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሠረት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮን ጠየቀች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልጅ ያሬድ በተባለውን ግለሰብ እና በተባባሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሠረት ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ በላከችው ደብዳቤ ጠይቃለች።

በላከችው ደብዳቤም ከዚህ ቀደም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሮ ፣ በሃይማኖት አባቶቿ ፣ በምዕመናኗ እና የአምልኮ ቦታዎቿን ባንቋሸሹ እንዲሁም የሐሰተኛ ንግግር ባስተላለፉት በነፓስተር ዮናታን አክሊሉ ፣ በነቢይ ኢዩ ጩፋ ፣ በአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተ ክርስቲያን እና በክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቤተ ክርስቲያን ላይ አቤቱታ አቅርባ ውጤት በመጠባበቅ ላይ ሳለች ይህ እንደገጠማት ነው የገለጸችው።

በግለሰቡ እና ተባባሪዎቹ ድፍረት የተሞላበት ድርጊት በርካታ ኦርቶዶክሳዊያንም ኢትዮጵያውያንም ላይ ከፍተኛ ቁጣን በመቀስቀሱን እና ከፍትህ አደባባይ ፍርድን ስለሚጠብቁ ፖሊስን ለማገዝ ይሔን አቤቱታ አቅርቤያለው ብላለች።

የተከሳሹ ድርጊት በዋናነት የቤተ ክርስቲያኗን መልካም ስም የሚያጎድፍ ድርጊት በመሆኑ ፤ ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ጥላቻ በመግለጽ ሰዎችን ለአመጽ እና ብጥብጥ የሚያነሳሳ በመሆኑ ፤ የቤተክርስቲያንን የአምልኮ ቦታ ያራከሰ በመሆኑ ፤ የምዕመናኑን ስሜት የሚነካ ፣ በሚያዋርድ እና ቤተክርስቲያንን በሚያናንቅ መልኩ የተፈጸመ በመሆኑ በግለሰቡ እና በተባባሪዎቹም ላይ ጭምር ፖሊስ ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ክስ እንዲመሠርት ለአቃቤ ሕግም እንዲልክ ጠይቃለች።

Via: ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

04/09/2023

ትላንቱ የአርሰናል እና ማንቸስተር ዩናይትድ ጨዋታ መሀል በኢትዮጵያ በሁለቱ ደጋፊዎች መካከል በአንድ ስፖርት ባር ውስጥ የተፈጠረው ክስክስ ።

03/09/2023

ቀነኒሳ ሆቴል የተፈጠረውን እውነታ አንዷለም አፈረጠው
የአማርኛ ትርጉም ቪዲዮ

ይሄ የምትመለከቱት ዛሬ ተመርቆ የተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ነው ።ይህን ቅርንጫጀፍ (አብይ ቅርንጫፍ) በማለት ተሰይሟል በእንግሊዝኛም (Abiy Branch) በማለት ሰይመውታል...
02/09/2023

ይሄ የምትመለከቱት ዛሬ ተመርቆ የተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ነው ።

ይህን ቅርንጫጀፍ (አብይ ቅርንጫፍ) በማለት ተሰይሟል በእንግሊዝኛም (Abiy Branch) በማለት ሰይመውታል ስያሜው በጠ/ሚኒስትሩ ስም መሰየም ለምን አስፈለገ አብይ ቅርንጫፍ ከተባለ በእንግሊዝኛ main branch ነበር መባል የነበረበት ነገር ግን ስየሜው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው የተሰየመው (አብይ ቅርንጫፍ ወይም Abiy Branch) በማለት።

02/09/2023

በዛሬው ዕለት በቴል አቪቭ በሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ደጃፍ በተነሳ ብጥብጥ ቢያንስ 140 ሰዎች ቆሰሉ። ሶስቱ ኤርትራዊያን ለህይወታቸው በሚያሰጋ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። ዝርዝሩን በስፋት እናቀርባለን።

30/08/2023

ሰበር
በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የሚኖሩበት የፀሐይ ሪልስቴት አፓርትመንት ባለቤት (ቻይናዊ) እና ግብረአበሮቹ በ"ዶላር ወንጀል" ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ። በአሁኑ ሰዓት ሲኤምሲ የሚገኘው ፀሐይ ሪልስቴት በመከላከያ፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ተከቦ ከፍተኛ ፍተሻ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። ቁጥሩ ያልታወቀ የዶላር ክምችት በቁጥጥር ስር መዋሉንም ከፖሊስ ምንጮች ሰምተናል። ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን ይዘን እንቀርባለን።

30/08/2023

ምን አይነት ዝቅጠት ነው ይሄ የሚያሳየው ሀገር ሚመሩ ሰዎች ኢትዮጵያን ለማጥፋት እየሰሩ እንደሆነ ነው።

የአቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም እንዳይሸጥ በፖሊስ ተከለከለ!የአቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም እንዳይሸጥ በፖሊስ መከልከሉን ድምፃዊው ገለፀ። አርቲስቱ ባስተላለፈው መልዕክት «በትናትናው እለት እንደ ...
29/08/2023

የአቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም እንዳይሸጥ በፖሊስ ተከለከለ!

የአቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም እንዳይሸጥ በፖሊስ መከልከሉን ድምፃዊው ገለፀ። አርቲስቱ ባስተላለፈው መልዕክት «በትናትናው እለት እንደ አባቴ እወድሻለሁ የተሰኜው አዲሱ አልበሜ በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ በፖሊስ ተከልክሏል እንዲህ ስለሆነ ለሀገሬ እና ለህዝቦቿ ያለኝ ፍቅር አይቀንስም እንደ አባቴ እወድሻለሁ» ብሏል።

"ለአቡነ ተክለሃይማኖት የእረፍት ቀን ንግሥ በዓል ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም የሚያቀኑ ምዕመናን በምሽት ጉዞ እንዳያደርጉ ተጠየቀ"በየዓመቱ ነሐሴ 24 ቀን ለሚከበረው የአቡነ ተክለሃይማኖት የእረ...
29/08/2023

"ለአቡነ ተክለሃይማኖት የእረፍት ቀን ንግሥ በዓል ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም የሚያቀኑ ምዕመናን በምሽት ጉዞ እንዳያደርጉ ተጠየቀ"

በየዓመቱ ነሐሴ 24 ቀን ለሚከበረው የአቡነ ተክለሃይማኖት የእረፍት ቀን ንግሥ በዓል ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም የሚያቀኑ ምዕመናን በምሽት ጉዞ እንዳያደርጉ የአቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም አስተዳዳሪ አባ ፍቅረማርያም ተከስተ አሳሰቡ።

በየዓመቱ ነሃሴ 24 ቀን በሚከበረዉ በዚህ ንግሥ በዓል በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ወደ ገዳሙ እንደሚያቀኑ የጠቀሱት የገዳሙ አስተዳዳሪ አባ ፍቅረማርያም ፤ በአካባቢው ያለዉን የጸጥታ ሁኔታ በመስጋት ዘንድሮ ለክብረ በዓሉ የሚገኙ ምመናን ቁጥር ሊቀንስ እንደሚችል ገምተዋል።

እንደ አስተዳዳሪዉ ገለጻ ፤ ምዕመናን ከምሽት 1 ሰዓት በኋላ ጉዞ እንዳያደርጉ መክረዋል። በዘንድሮው የንግሥ ክብረበዓልም እስከ 10 ሺህ የሚደርሱ ምዕመናን ይገኛሉ ብለዉ እንደሚጠብቁ አክለዋል።

የደብረሊባኖስ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ብርሃኑ ሌንጮም ይህንኑ በመግለጽ ምዕመናን በሌሊት ከሚደረጉ ጉዞዎች እንዲጠበቁ አሳስበዋል።

የወረዳዉ ፖሊስ ከሱሉልታ ጀምሮ ከሚገኙ የጸጥታ አካላት ጋር በትስስር የመንገዱን ደህንነት እንደሚያስጠብቁ የገለጹ ሲሆን ሆኖም የሌሊት ጉዞዎች ከደህንነት አኳያ እንደማይመከሩ ጠቅሰዋል።

በተጨማሪነትም ሀገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች መጨናነቅ እንዳይፈጠር ቦታ መዘጋጀቱን ፣ የክረምት ወቅት እንደመሆኑ አሽከርካሪዎች ጠምዝማዛ እና ገደላማ በሆኑ አካባቢዎች በጥንቃቄ እንዲያሽከረክሩ እና በክብረ በዓሉ ለሚከሰቱ ማንኛቸዉም የማጭበርበር እና የስርቆት ድርጊት አፋጣኝ ችሎት ለመስጠት መዘጋጀታቸዉንም ገልጸዋል።

ምንጭ: ብስራት ሬዲዮ

አትሌት ሰለሞን ባረጋ ከመኪና አደጋ ተረፈ''ሰለሞን ባረጋ እንደ ሁል ግዜው ትላንት የጫካ ልምምዱን አጠናቆ ወደ ከተማ ሲመለስ አዲስ አበባ ውስጥ  የካ ክፍለ ከተማ  ሾላ ገቢያ ውስጥ ሰለሞን...
27/08/2023

አትሌት ሰለሞን ባረጋ ከመኪና አደጋ ተረፈ''

ሰለሞን ባረጋ እንደ ሁል ግዜው ትላንት የጫካ ልምምዱን አጠናቆ ወደ ከተማ ሲመለስ አዲስ አበባ ውስጥ የካ ክፍለ ከተማ ሾላ ገቢያ ውስጥ ሰለሞን የሚያሽከረክራት መኪና ከሌላ መኪና ጋር የተጋጨ ሲሆን የአደጋው መንስኤ ቅድሚያ ባለመሰጣጠት የመጣ መሆኑ ተገልጿል።

በወቅቱ ስለሞን በሚያሽከረክረው መኪና ውስጥ የነበሩት ሁለት አትልቶች መጠነኛ ጉዳት ሲያጋቸው በአትሌት ሰለሞንም ሆነ በሌሎች ሰዎች ላይ ምንም አይንት ጉዳት አልደረሰም።

27/08/2023

ደብረ ማርቆስ

 የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን ከአሁን በኋላ በካድሬነት ሳይሆን በብቃታቸው ብቻ እንደሚመረጡ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን ያለው ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ....
27/08/2023



የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን ከአሁን በኋላ በካድሬነት ሳይሆን በብቃታቸው ብቻ እንደሚመረጡ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን ያለው ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 30ኛውን ዓለም አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ምን አሉ ?

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" የትምህርት ቤቶች አስተዳዳሪዎች ከአሁን በኋላ የሚመረጡት በካድሬነት ሳይሆን፣ ባላቸው ብቃትና ችሎታቸው ላይ መሠረት ተደርጎ ይሆናል።

በዚህ መሠረት በአገር አቀፍ ደረጃ በብቃታቸውና በችሎታቸው የተመዘኑ 1,600 የትምህርት አስተዳዳሪዎች ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል። ይህ ዓይነቱ አሠራር ቀጣይነት ይኖረዋል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሳደግ ሥራ በተጨማሪ የመምህራንና ርዕሳነ መምህራን ብቃትና ችሎታ ማጎልበት ትኩረት ተሰጥቶበታል፡፡

ትኩረት ካገኙ መሠረታዊ ጉዳዮች ትምህርት ቤቶችን በግብዓትና በጥራት ከማሻሻል ባሻገር ክህሎት፣ ብቃትና ችሎታ ባላቸው ርዕሳነ መምህራን እንዲተዳደሩ ማድረግ ትልቁን ድርሻ ይይዛል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል በተጨማሪ በዕውቀት ተማሪዎቻቸውን ተወዳዳሪ ማድረግ የሚችሉ መምህራንን ማብቃት ከተያዙ ግቦች መካከል አንዱ ነው።

ባለፉት 30 ዓመታት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ጥራት ወርዷል ፤ በኑሮ ለተሻሉ ደግሞ የግል ትምህርት ቤቶች የሚማሩበት ሥርዓት ተዘርግቷል።

ይህ ዓይነት አካሄድ በዜጎች መካከል በኑሮ ደረጃ ከተፈጠሩ ልዩነቶች አልፎ በትምህርት ዘርፍ ላይ መታየቱ ትልቅ ክስረት ነው። ይህ አካሄድ በአገር አቀፍ ደረጃ አደገኛ ሁኔታዎች የሚፈጥር ነው ፤ በየትኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በገንዘብ ዕጦት ሳቢያ የትምህርት ጥራት ሊጓደልባቸው አይገባም።

ትምህርት የአገር የሉዓላዊነት እሴት መለኪያ ነው ፤ በዚህ ጉዳይ ለዓመታት የተቀለደበት ዘርፍ ነው አሁን እርስ በርስ መነጋገር የማይቻልበት ሁኔታ ላይ መደረሱ የችግሩ ማሳያ ነው።

የትምህርት ዘርፍ መሠረታዊ መርሆዎች ሁለት ናቸው ፤ ዜጎች በብሔራቸውና በሃይማኖታቸው ሳይታዩ እኩል ጥራት ያለው ትምህርት የማግኘት መብታቸውን ማረጋገጥ አንደኛው ነው።

የትኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች ከሁሉም እኩል ተወዳዳሪና ተፎካካሪ የሚሆኑበትን የትምህርት ሥርዓት በመዘርጋት፣ አሁን ያለውን የኢፍትሐዊነት ችግር በዘላቂነት መፍታት ይቻላል።

በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉ ከአሥር ዓመታት በኋላ ትምህርት ቤቶች እንደ አሁኑ የፀብ (የረብሻ) መፍለቂያ ሳይሆኑ የመወዳደሪያና የብቃት ማጎልበቻ ይሆናሉ፡፡

ከዚህ በኋላ እንደ ከዚህ ቀደሙ ዲግሪ እንደ ከረሜላ የሚታደልበትን አሠራር አስቀርቶ፣ በብቃት እና በችሎታ ብቻ ዜጎች ማዕረግ የሚያገኙበት ሥርዓት በዘላቂነት ይዘረጋል። "

Via Reporter Newspaper

ተቋርጦ የነበረው የሶስትዮሽ የሕዳሴ ግድብ ድርድር በግብፅ ካይሮ ተጀመረ - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት*********************************ተቋርጦ የነበረው የሶስትዮሽ የ...
27/08/2023

ተቋርጦ የነበረው የሶስትዮሽ የሕዳሴ ግድብ ድርድር በግብፅ ካይሮ ተጀመረ - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
*********************************

ተቋርጦ የነበረው የሶስትዮሽ የህዳሴ ግድብ ድርድር በዛሬው እለት በግብፅ ካይሮ መጀመሩን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የሶስትዮሽ ድርድሩ ከዚህ በፊት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አቡዳቢ ሲደረግ ቆይቶ ረቂቅ ስምምነት ማዘጋጀት ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም ከዛ ወዲህ ድርድሩ ሳይካሄድ ቆይቷል።

ይሁንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በግብፅ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ከግብፁ ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ጋር በደረሱት ስምምነት መሰረት የሶስትዮሽ ድርድሩ ዳግም ተጀምሯል።

በዚህም ረቂቅ ስምምነቱ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይትና ድርድር እንደሚደረግ ተጠቁሟል።

ድርድሩ የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት እና የወደፊት የመልማት መብት ባስከበረ መልኩ ለማካሄድም አስፈላጊው ዝግጅት ተከናውኗል።

19/08/2023

አረንጓዴው ጎርፍ 💚💛❤️

1.ጉዳፍ
2. ለተሰንበት
3. እጅጋየሁ

እንኳን ደስ አላችሁ፣ አለን💚💛❤️

በቡዳፔስት የአለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች የፍፃሜ ውድድር የወርቅ፣ የብር እና የነሃስ ሜዳሊያዎች አገኘች።ሲፋን ሀሰን ውድድሩን በአንደኝነት ለመጨረስ በተቃረበችበት ወቅት ወድቃ አሳዛኝ ተሸናፊ ሆናለች።

07/08/2023

ፋኖ በጨበጣ ሲዋጋ
ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Daily News Ethiopian posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share


Other Media/News Companies in Addis Ababa

Show All