Eva +

Eva + Family reality YouTube Channel
Digital content creation, fun & more

የአመት ሰው ይበለን 🙏
26/07/2022

የአመት ሰው ይበለን 🙏

ቅዱስ ገብርኤል የንግሥ በዓል ቆይታችንን በትንሹ እናካፍላችሁ፤ ⛪❤️🤲ዉድ ተመልካቾቻችን፣ የዚህ ቻናል ቤተሰብ ስለሆናችሁ በጣም እናመሰግናለን፤ ለዚ...

🔥🔥🔥   video 🔥🔥🔥
06/07/2022

🔥🔥🔥 video 🔥🔥🔥

ስለ ራሳችን ድንገት በአዕምሮአችን የመጡ አምስት አምስት ጥያቄዎችን ስንጠያየቅ፣ ያልተጠበቁ መልስ!!!ከዚህ የተሻሉ ነገሮችን በቀጣይ ስንሰራ እንዲደርስዎ SUBSCRIBE ማድረግዎን አይርሱ!ስ.....

ከሥራ ወደ ቤት ስገባ፣ ያልተጠበቀ ነገር አየሁ! እስቲ እዩት፣   ማድረግ አይርሱ ! 👇🙏 እናመሰግናለን!
17/06/2022

ከሥራ ወደ ቤት ስገባ፣ ያልተጠበቀ ነገር አየሁ! እስቲ እዩት፣ ማድረግ አይርሱ ! 👇
🙏 እናመሰግናለን!

ድንገት ከስራ ስመጣ፣ እነሱ ምን እያደረጉ እንደነበረ አታውቁም! ኢቫ+ Reality Showአዲስ ለመጣችሁ ሰላያችሁ እናመሰግናለን፣ SUBSCRIBE አድርጉን፣ Comment ስጡን፣ ስለምትደግፉን እጅጉን እናመሰግ.....

ስለ   ከሰማነው 👇
10/06/2022

ስለ ከሰማነው 👇

09/06/2022

የሌላ ሀገር ዜጋ ጎብኝቶ እንዲህ ያደነቀውን እስቲ ስንቶቻችን አይተነው እናውቃለን? Comment

Good Night from beautiful Hawasa 🇪🇹
06/06/2022

Good Night from beautiful Hawasa 🇪🇹

Adama 😍
03/06/2022

Adama 😍

03/06/2022

Nooraa ❤ ሰላም ❤ Hello

13/05/2022


ከኮምፒዉተር ቫይረሶች መካከለ አንዱ የሆነዉ ትሮጃን ቫይረስ ምንድን ነዉ?

ትሮጃኖች (trojan) በኤ-ሚይል ወይም በሌሎች ዘዴዎች ማለትም በማህበራዊ የትስስር ገጾች ወይም ታማኝ ካልሆኑ የመተግበሪያ ክምችቶች በተጠቃሚዎች የጥንቃቄ ጉድለትና የእውቀት ክፍተት ምክንያት የሚወርዱና የሚጫኑ አጥፊ ሶፍትዌሮች ናቸው።

ትሮጃኖች ትክክለኛ ወይም ህጋዊ ሶፍትዌር የሚመስሉ ማለትም ጉዳት የሌላቸው፣ መደበኛ ወይም ችግር ፈቺ ስራዎችን የሚከውኑ መተግበሪያዎችን በመምሰል በውስጣችው ግን ሌላ ተንኮል አዘል ስራዎችን ወይም ሌላ መተግበሪያዎችን መጫን የሚያስችል አሰራር ያላቸው ማልዌሮች ናቸው።

አጥቂዎች ተጠቃሚውን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን ተፈጻሚ እንዲያደርግ በማታለል ሶፍትዌሮቹን እንዲጭን የሚያደርጉ አሰራሮችንም በውስጣቸው ያካተቱ ሲሆን፤ አንድ ጊዜ ከተጫኑ እና ስራ ላይ ከዋሉ በኋላ በውስጣቸው ያለው ተንኮል አዘል ኮድ ራሳቸውን እንዲያነቁ እና ሌሎች ተንኮል አዘል መተግበሪያዎችን በማውረድ መጠነ ሰፊ ጥቃቶችን ወይም ጉዳቶችን ማድረስ እንዲችሉ ያደርጋል።

ይህም ገደብ የለሽ የተጠቃሚነት ፈቃድን ማግኘት የሚያስችላቸውን ዘዴዎች በመጠቀም ዳታን መቀየር፣ ማጥፋት፣ መስረቅ እንዲሁም በርቀት ሆነዉ ኢላማ የተደረገን አካል የመቆጣጠ አሰራርን (ሪሞት ኮንትሮሊንግን) በመፍጠር አጥቂዎች ለስለላና ለመሳሰሉ አይነት የመቆጣጠሪያና የጥቃት ዘዴዎች እንዲጠቀሙባቸው የሚያስችሉ ናቸው።

Via INSA- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

13/05/2022

Atleet Daraartuun maal taate?
አትሌት ደራርቱን እንዲህ ያበሳጯት? 😭

5G ምን ያህል ፈጣን ነው?
09/05/2022

5G ምን ያህል ፈጣን ነው?

⛔️❌📢🆘⛔️❌ #ለጥንቃቄ እነዚህ በስፋት ሀገር ውስጥ ገበያ ላይ ያሉ "አንዳንድ" የቸኮላት ምርቶች ላይ ኮሜሳ የጤና ማሳሰቢያ ቢያወጣም ጠንካራ የሸማቾች ማህበር በሌላት ሀገራችን ዝም ተብሏል...
07/05/2022

⛔️❌📢🆘⛔️❌

#ለጥንቃቄ እነዚህ በስፋት ሀገር ውስጥ ገበያ ላይ ያሉ "አንዳንድ" የቸኮላት ምርቶች ላይ ኮሜሳ የጤና ማሳሰቢያ ቢያወጣም ጠንካራ የሸማቾች ማህበር በሌላት ሀገራችን ዝም ተብሏል!

ከኮሜሳ የውድድር ኮሚሽን የደረሰኝ መረጃ እንደሚጠቁመው በምስሉ ላይ በተቀመጠው ግዜ የተመረቱ የ KitKat እና Kinder ባች ምርቶች ችግር አለባቸው። በግዜ ገደቡ የተመረቱት የ KitKat ምርቶች የጠርሙስ ስብርባሪ፣ እንዲሁም የ Kinder ምርቶች ሳልሞኔላ ባክቴርያ ተገኝቶባቸዋል። በዚህ ምክንያት ጎረቤት ሀገራት ጭምር ምርቶቹን ከገበያ እያስወጡ ይገኛል።

እባክዎ Share አድርጉ፣ 🆕ℹ️🆓🆓🆓🆓🆓🆓🆓በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ኮሌጅ የዓይን ህክምና ትምህርት ክፍል HCP በተባለ ግብረሰናይ ድርጅት እገዛ 500 የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክ...
05/05/2022

እባክዎ Share አድርጉ፣
🆕ℹ️🆓🆓🆓🆓🆓🆓🆓
በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ኮሌጅ የዓይን ህክምና ትምህርት ክፍል HCP በተባለ ግብረሰናይ ድርጅት እገዛ 500 የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና /CATARACT SURGERY/ ከ ሰኔ 6-12/2014 ዓ.ም ለማድረግ አስቧል፡፡ ስለሆነም ይህን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ቅድመ ምርመራ፣ልየታና ምዝገባ በግንቦት ወር ባሉት ቅዳሜና እሁድ ቀናቶች ማለትም (ግንቦት 6፣7፣13፣14፣20፣21፣27፣28 ) ስለምናደርግ በኮሌጁ የስልክ አገልግሎት 967 በመደወል ለቅድመ ምርመራ፣ ልየታና ምዝገባ ቀጠሮ እንድትይዙ ስንል በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- በስልክ ቀጠሮ ያልተሰጠዉ ታካሚ ቅድመ ምርመራም፣ ልየታም ይሁን ምዝገባ ማድረግ አይችልም፡፡

Hiriyyoolee |   | የመጀመርያው የአፋን ኦሮሞ የሠርግ አልበም ሊመረቅ ነው!ሂሪዮሌ  ~ ጓደኝነት ነው [  ኑ በ ፍቅር  እናምሽ ] ሽብረቅ ድምቅ ፍክት ያለ ዝግጅት በጊዮን ሆቴልየመ...
04/05/2022

Hiriyyoolee |

| የመጀመርያው የአፋን ኦሮሞ የሠርግ አልበም ሊመረቅ ነው!

ሂሪዮሌ ~ ጓደኝነት ነው [ ኑ በ ፍቅር እናምሽ ]

ሽብረቅ ድምቅ ፍክት ያለ ዝግጅት በጊዮን ሆቴል

የመጀመርያው የአፋን ኦሮሞ የሠርግ አልበም እሁድ፣ ሚያዝያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም.
ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ይመረቃል፡፡

ሂሪዮሌ ~ ጓደኝነት ነው [ ኑ በ ፍቅር እናምሽ ]

በእለቱ በታሪክ የመጀመሪያ የሆነው የአፋን ኦሮሞ የሠርግ እና የባሕል አልበም ከመመረቁ ባለፈ
* ደረጃውን የጠበቀ የሠርግ ብፌና መጠጥ፤
* ምርጥ የሙዚቃ ኮንሰርት
* እንዲሁም 20 ውብ ጥንድ ሙሽሮች ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ ይሞሸራሉ

ሰርፕራይዝ አለ፡፡

የመግቢያ ዋጋ፣
ምግብና መጠጥን ጨምሮ 500 ብር ብቻ

የመግቢያ ካርዱን ለማግኘት ቦሌ መድኃኒያለም ኦሮሚያ ህንፃ በአካል ይምጡ

አልያም በእለቱ መግቢያ በር ላይም ያገኙታል ፡፡

ለበለጠ መረጃ
በ+251-975-099995 ላይ ይደውሉ

አዘጋጅ ቢቲኤም

Hiriyyoolee
BTM wallistoota qindeessuun sirboota yeroo Cidhaa, Guyyaa dhalootaa fi Ayyaanaa Albama guutuu hojjisiiseeru gaafa Ebla 30 bara 2014 waaree booda sa'aatii 10:00 eegalee Finfinnee Hoteela Gihonitti ni Eebbisiisa.
Isinis Sirna kanarratti akka argamtaniif Kabajaan yoo isin Afeerru Gammachuu Guddaadhaani.

03/05/2022

Starting with 2 Stories:
1. Yahoo refused Google
2. Nokia refused Android

Moral:
1. Update yourself with time, else you will become obsolete
2. Taking no risk is the biggest risk. Take risks and adopt new technologies.

2 more stories:
1. Google acquired YouTube and Android
2. Facebook acquired Instagram and WhatsApp

Moral:
1. Become so powerful that your enemies become your allies
2. Grow fast, become big, and then eliminate competition

2 more stories:
1. Barack Obama was a ice cream seller
2. Elon Musk was a worker in a lumber mill

Moral:
1. Don’t judge people based on their past jobs
2. Your present doesn’t decide your future, your courage and hard work does

2 more stories:
1. Colonel Sanders created KFC at the age of 65
2. Jack Ma who was rejected by KFC founded Alibaba

Moral:
1. Age is just a number - you can be successful at any age
2. Never ever give up in life - only those who never give up win

2 final stories:
1. Owner of Ferrari insulted a tractor maker
2. The tractor maker created Lamborghini

Moral:
1. Never underestimate or disrespect anyone
2. Success is the best revenge

You can be successful at any age and from any background.

Dream big. Set goals. Work hard.

Never ever give up in life. Go ahead.

Don't forget to follow us on BonTube
Like and Share 🙏🙏🙏

በቀጣይ ሁለት ወራት ስለ ነዳጅ ድጎማ መነሳት፣🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔹 የራይድ ታክሲ አገልግሎት ታሪፍ በመንግሥት የማይተመን ከሆነ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ አይሆኑም። 🔹 ድጎማው ሲነሳ ነዳጅ በ...
29/04/2022

በቀጣይ ሁለት ወራት ስለ ነዳጅ ድጎማ መነሳት፣
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘

🔹 የራይድ ታክሲ አገልግሎት ታሪፍ በመንግሥት የማይተመን ከሆነ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ አይሆኑም። 🔹 ድጎማው ሲነሳ ነዳጅ በሊትር ከ60 ብር ሊያልፍ ይችላል ተብሏል፣

በተለምዶ ራይድ ወይም የሳሎን ታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች የሚያስከፍሉት ታሪፍ በመንግሥት የማይወሰን ከሆነ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ እንደማይሆኑ ተጠቆመ።

ለሕዝብ ፋይዳ ካላቸው የትራንስፖርት ሰጪዎች በስተቀር፣ ለሁሉም ተሽከርካሪዎች የሚነሳው የነዳጅ ድጎማ ከሁለት ወራት ተኩል በኋላ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ ከዚያም የነዳጅ ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያው የሚተመን ይሆናል።

የታለመ የነዳጅ ዋጋ ድጎማ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ በተመረጡ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የሚውል፣ በጊዜ የተገደበ ድጋፍ እንደሆነ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው የውሳኔ ሐሳብ ያሳያል።
የአዲሱን አሠራር ሒደት የሚተነትነው የውሳኔ ሐሳብ የማዘጋጀት ሒደቱ ላይ የተሳተፉና ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሥራ ኃላፊ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የነዳጅ ድጎማው በተመረጡ ተሽከርካሪዎች ላይ መተግበር ያስፈለገው የመንግሥት ወጪ ለመቀነስና አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ለመርዳት እንደሆነ ተናግረዋል።
የሥራ ኃላፊው ለሪፖርተር እንደተናገሩት ከመንግሥት ሥምሪት ውጭ የሆኑ ታሪፋቸውም በገበያ የሚመራ ተሽከርካሪዎች የድጎማው አካል የማይሆኑ ሲሆን፣ ይህም ምንም እንኳን መካከለኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ላይ መጠነኛ ጫና ያሳድራል የሚል ፍራቻ ቢጭርም አስፈላጊ ውሳኔ መሆኑን አክለዋል።

ሪፖርተር ከውሳኔ ሐሳብ መረዳት እንደቻለው ድጎማው ሲነሳ የዓለም ነዳጅ ውጤቶች ገበያ ሁኔታን ያገናዘበ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ የሚደረግ ሲሆን፣ ይህም ከአምስት ዓመታት ላልበለጠ ጊዜ ተግባራዊ ይደረጋል።

በውሳኔው መሠረት በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በሚሆን ታሪፍና ሥምሪት ለመሥራት ከተስማሙ የትራንስፖርት ሰጪዎች በተጨማሪ፣ በማኅበር ታቅፈው የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ።
የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች፣ ኮድ 1 እና 3 ሚኒባሶች፣ የከተማ አውቶብሶች፣ አገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችና የመጫን አቅማቸው እስከ 47 የሆኑ የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪዎች የድጎማው ተጠቃሚ ይሆናሉ።

የሳሎን ታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች መካከል የሆነው የዛይ ራይድ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ታደሰ፣ ድጎማው መሰል አገልግሎት ሰጪዎችን ባለማካተቱ ቅር እንደተሰኙ የተናገሩ ሲሆን፣ የትራንስፖርት እጥረትን ሊያባብስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

አቶ ሀብታሙ እንደተናገሩት የትራንስፖርት እጥረት ሳይቀረፍ የራይድ ታክሲ አገልግሎት ከድጎማው ተጠቃሚ እንዳይሆን ማድረግ ያለውን ችግር ከማባባስ ባሻገር በዚህ አገልግሎት ሰጪዎች የሚሰበሰበውን የታክስ መጠን ሊቀንሰው እንደሚችልና የዘርፉን ዕድገት ሊያቀጭጨው እንደሚችል ሥጋታቸውን ለሪፖርተር አጋርተዋል።
ባለፉት አምስት ዓመታት ከ40 በላይ የሳሎን ታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች ገበያውን የተቀላቀሉ ሲሆን፣ ከ30 ሺሕ በላይ ተሽከርካሪዎች በሥራቸው አቅፈዋል ተብሎ ይገመታል። በአሁን ወቅት በአማካይ አሥር ብር በኪሎ ሜትር ያስከፍላሉ።

ድጎማው ሲነሳ አንድ ሊትር ነዳጅ አሁን ባለው ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መሠረት ከ60 ብር በላይ የሚደርስበት ዕድል ሰፊ በመሆኑ የታሪፍ ማስተካከያ ማድረጋቸው የማይቀር መሆኑን የሚያነሱት አቶ ሀብታሙ ይህም ወደ ሌሎች ዘርፍ ሊዛመት ስለሚችል ዋጋ ግሽበትን ሊያባብስ ይችላል ብለዋል።

በተመሳሳይ የራይድ ታክሲ ባለቤት የሆኑት አቶ ተመስገን አራጌ የተባሉ ግለሰብ በበኩላቸው መንግሥት ድጎማውን ካነሳ በዘርፉ የተሰማሩ አሽከርካሪዎች ከገበያ ሊወጡ የሚችሉበት ዕድል ሰፊ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን፣ መንግሥት ውሳኔውን በድጋሚ ሊያጤነው እንደሚገባ ተናግረዋል።

ምንጭ፡- ሪፖርተር

ሌሎች ተመሳሳይ ወሬዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርስዎ Like, Share, Follow BonTube ያድርጉ 🙏

  ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን መሰረታዊ ነጥቦች ፦ 1. ሲፒዩ(CPU)2. ራም(RAM) 3. የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)4. የስክሪን መጠን (Screen S...
28/04/2022



ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን መሰረታዊ ነጥቦች ፦
1. ሲፒዩ(CPU)
2. ራም(RAM)
3. የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)
4. የስክሪን መጠን (Screen Size)
5. የባትሪ ቆይታ (Battery Life)
6. የምስል ጥራት (Image Quality)

1. ሲፒዩ(CPU)
የኮምፒዉተር አይምሮ በመባል የሚታወቀው ሲፒዩ
(CPU), ላፕቶፕ ለመግዛት ሁላችንም ማየት ያለብን ዝርዝር ነው፡፡
• AMD A series or Intel Core i3 / i5: በየቀኑ
ለምንጠቀማቸው ስራዎች የሚሆኑ የሲፒዩ አይነቶች
ሲሆኑ Core i5 ለሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት እና አነስተኛ የዲዛይን ስራዎችን ለምሳሌ እንደ Photoshop, ArchiCad, AutoCadን የመሳሰሉ በጥሩ ሁኔታ እንድንሰራ ይጠቅሙናል፡፡ በተጨማሪም ግራፊክስ ካርድ ያለውና የሌለው በማለትም ይለያያሉ፡፡ግራፊክስ ካርድ ያለቸው የተሻለ የዲዛይን እና አኒሜሽን ስራዎችን ያከናውኑልናል፡፡ በዋጋውም ተመጣጣኝ ነው፡፡
• Intel Core i7፡ በጣም አስደማሚ የጌም እና
የዲዛይን እንዲሁም ልዩ የሆኑ የኮምፒውተር ስራችን ለምሳሌ አንደ ሜትሮሎጂ፤ውስብስብ ስሌቶችን እንድንሰራ የሚረዳን የላፐቶፕ አይነት ነው፡፡
2. ራም(RAM)
ለፍጥነት 4ጂቢ እና ከዛ በላይ የሆነ
RAM እንዲጠቀሙ እንመክሮታለን፡፡ ዋጋቸው አነስ ያሉ
ላፕቶፖች በ2ጂቢ ይመጣሉ፡፡ የዲዛይን ስራዎችን እና የሶፈትዌር ዴቨሎፕመንት ስራዎችን ለመስራት 6ጂቢ ራም እና ከዚያ በላይ ያለው ላፕቶፕ ቢገዙ ይመረጣል፡፡
3. የሃርድ ድራይቭ አይነት፡
ሁለት አይነት የሃርድ ድራይቭ አይነቶች ያሉ( HDDrive እና SSDrive) ሲሆን
በሃገራችን የተለመደው HDDrive ነው፡፡ SSDrive የተሻለ የፍጥነት አቅም እና ድራይቩ ላይ ያለውን ዳታ በፍጥነት መድረስ እና መገልበጥ (copy)ያስችለናል፡፡
4. የስክሪን መጠን
ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ ወደ ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ ናቸው፡፡
• 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም
ቀጭን እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ ይመዝናል፡፡
• 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ
የስክርን ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
• 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን
ሳይዝ ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ እንመክራለን ፡፡
• 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡
ላፕቶፖን ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ትልቅ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን ይግዙ፡፡ ለጌመሮች እና ትልልቅ የሶፈተዌር ዲዛይን ለሚያደርጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ የላፕቶፕ አይነት ነው፡፡

5. የባትሪ ቆይታ
አብዛኛው ሃገር ውስጥ የሚገቡት የላፕቶፕ አይነቶች 4 ሰዓታት የሚቆዩ ሲሆን ከ6-8 ሰዓታትም የሚቆዩ ኦርጅናል ላፕቶፖች አሉ፡፡

6. የምስል ጥራት
የተሻለ ጥራት የተሻለ ምስል እንድናገኝ ይረዳናል፡፡ 1366 x 768 ጥሩ የሚባል የምስል ጥራት ያለው ሲሆን ከዚህ የተሻለ ወጪ በማውጣት 1920 x 1080 የተሻለ ምስል ማግኘት እንችላለን፡፡ Full HD 1080P በመባልም ይታወቃል፡፡

Share እና Like ለእናንተ ቀላል፣ ለእኛ ሞራል 🤗

Share♨️Like🔅Follow🔘 BonTube

So ስለ University ከተወራ አይቀር የራሴን ታሪክ ላካፍላችሁ። (ማሳሰቢያ: this might be too personal and emotional to share here on Facebook!)...
28/04/2022

So ስለ University ከተወራ አይቀር የራሴን ታሪክ ላካፍላችሁ።

(ማሳሰቢያ: this might be too personal and emotional to share here on Facebook!)
***

So 2007 ዓ.ም.ላይ ነበር የህክምና ትምህርት (Medicine) ለማጥናት ተመድቤ፤ ከኖርኩባትና ካደኩባት ባህርዳር ወጥቼ ወደ ጎንደር ዩኒቨርስቲ የሄድኩት።

አዲስ ህይወት፣ አዲስ ነገር፣ አዲስ ልምድ፣ አዲስ አገር፣ አዲስ ማህበረሰብ፣ ከቤተሰብ መውጣት፣ ነፃነቱ፣ ጓደኞቼ... ሁሉም ነገር አጓጊ ነበር።
ይሄ ሁሉ ቢያጓጓኝም፣ እኔ በሰዓቱ የነበርኩበት ስሜት ግን ከዚህ በጣም የተለየ ነበር።

ከልጅነቴ ጀምሮ "ዶክተር እሆንልሻለሁ!" እያልኳት ያደኩ፣ "ዶክተር ትሆንልኛለህ!" እያለች ያሳደገችኝ እናቴ የ12ኛ ክፍል ውጤቴን ሆስፒታል አልጋ ላይ እያለች ነበር የሰማችው። እኔ የምኖረው ለእናቴ፣ እናቴ የምትኖረው ለእኔ ነበር። የእኔ የህይወት ግብ ተምሬ፣ ተመርቄ እሷን ማስደሰት ሲሆን ፤ የእርሷ የመኖር ምክንያት ደግሞ እኔን ማስተማር ነበር። ሁሌም የምትለኝ አንድ ነገር ነበራት፦ "አንተ ተመርቀህ አይቼህ ቀጣይ ቀን ብሞት አይቆጨኝም!"

ነገር ግን እርሷን ለማስደሰት ብዬ የደከምኩበትን ውጤት እንኳን በቅጡ አልሰማችኝም። እኔ ተናገርኩ እንጅ እርሷ መልስ አልሰጠችኝም። ህመሟ በርትቶ ራሷን አታውቅም ነበር፣ በግድ ቀስቅሼ ነግሪያት ሰምታኝ መልስ ሳትሰጠኝ ተመልሳ አሸለበች።

መዳኗን በተስፋ እየጠበቅኩ ከወር በላይ ባስታምማትም ወደ ዩኒቨርስቲ እንኳን ሳትሸኘኝ፣ እንደ ሌላው እናት በሶ ሳትቋጥርልኝ ተለየችኝ።
እንዳለችው ምኞቷ ሳይሳካላት፤ ካሰበችው ጊዜ በጣም ቀድማ ሄደች። በምታስፈልገኝ ሰዓት ራቀቸኝ። እሷ አረፈች! እኔ እረፍቴን አጣሁ።

በዚህ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ነበር ወደ ግቢ የገባሁት። ያኔ ወደ ግቢ የሄድኩት መሄድ ስላለብኝ እንጅ የመማር ሞራል፣ አቅምና እቅድ ኖሮኝ አልነበረም። ከዛ ይልቅ ሙሉ ጊዜና ሃሳቤን የሰጠሁት እቅዴ በቻልኩት አቅም ሁሉ ራሴን ማስደሰት፣ ከሃዘን መሸሽ፣ ብቸኝነቴን መርሳት፣ ራሴን ከእውነታው መደበቅ ነበር።

ለዚህ ደግሞ ጥሩ መንገድ ብዬ ያሰብኩት ማንኛውም ወጣት የሚያስበውን አማራጭ ነው፦ መጠጥ፣ ሱስ፣ እና ሴት! እነዚህ ነገሮች እንደ ምኞቴ ሃዘኔን አጥፍተው በደስታ ባይተኩልኝም፣ ለትንሽ ጊዜም ቢሆን እንዳላስበው አርገውኛል።
ከዛ ይልቅ ግን ራሴን ለመጉዳት እና በተጎጅነት ስሜት(Victim mentality) ውስጥ ለመኖር ተጠቅሜባቸዋለሁ።

በትምህርት ውስጥ ተደብቄ የኖርኩ፣ ጨዋ ወይም የቤት ልጅ በሚባል ማንነት ያደኩ ልጅ ስለነበርኩ፣ እነዚህን ልቅ ነገሮች ማድረግ ለእኔ አዲስ ነበር። ግን ሆነ ብዬ፣ አስቤበት ስለማደርገው ኩነኔ አልነበረብኝም።

"ማን ይቃወመኛል? ለየትኛው ህይወቴ ልጨነቅ?!

አምላክ ነው?! ስንት ስተማመነው እናቴን ከእኔ የወሰዳት አምላክ ስለ እኔ ህይወት ምን አገባው?
የምሰራው ነገር ሃጥያት ከሆነም እሰዬው! ይቃጠል!"

"ወይስ ሰው ነው?! የእኔ ጉዳት ቅንጣት የማይገባው ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ጓደኛ እና ሌላው ሰው የፈለኩትን ባደርግ ምን አስጨነቀው?! ውስጤን ማን አየልኝ?! ስሜቴን ቀርቦ ማን ጠየቀኝ?! ማን ሊረዳኝ ሞከረ?!"

በቃ በዛ ሰዓት በዚህ ስሜት እና አሰተሳሰብ ውስጥ ስለነበርኩ የትኛውንም ልቅ ነገር ባደርግ ራሴን አልኮንንም ነበር። ስለዚህ የፈለኩትን በፈለኩት ሰዓት እና ቦታ አደርጋለሁ፣ ለእኔ የመሰለኝን እፈፅማለሁ።

"ላለው ይጨመርለታል፣ ለሌለው ያንኑ ይወሰድበታል!" እንደሚባለው፤ ማማረሬ በዝቶ፣ እግዚአብሔርም ተማረረብኝ መሰለኝ ይባስ ብሎ እናቴ በሞተች በ10ኛው ወር በጣም የምወደው ምስኪኑ አባቴ ተከተላት።
ከእርሷ ሃዘን ሳልወጣ ሌላ ተጨማሪ ሃዘን።
"እዚጋ ደግሞ ሌላ ትኩሳት!" ብዬ መኖር ማቆም ስላልቻልኩ፣ አማራጭ አጥቼ የተለመደውን ህይወቴን ቀጠልኩ።

በዚህ ሁሉ ግን "ደስታዬን" እንጅ ሃዘኔን ለሰው አላሳይም ነበር። ሰዎች የማይረዱኝ የሚረዳኝ ሰው ጠፍቶ ሳይሆን እኔ ጉዳቴን ለማንም ስለማላሳይ ነበር። ሳቄን እንጅ ለቅሶዬን ሰው አያዬውም። ስዝናና በጋራ፣ ሳዝን ብቻዬን ነበር።
የእኔን ችግር ለሰው ከማጋራት ይልቅ፣ የተቸገሩ ሰዎችን መስማት እና መርዳት ይቀለኝ ነበር።

ለቤተሰቤ የመጨረሻ ልጅ ስለነበርኩ እና ታላላቅ እህቶችና ወንድም ስላሉኝ፣ በእንክብካቤ፣ በፍቅር እና በስርዓት ስላደኩ፣ ደስተኛ እና ሰላማዊ የልጅነት ጊዜ ስላሳለፍኩ፣ እንዲሁም የችግር እና የጭንቀት ልምድ ስላልነበረኝ ይሄን ሁሉ መቋቋም እና ማለፍ ለእኔ በጣም ከባድ ነበር።
ምን ማድረግ እንዳለብኝም አላውቅም ነበር። የማደገውን የማደረገው ከችግሬ ለመውጣት ሳይሆን እንዲሁ በደመ ነፍስ ጊዜያዊ እረፍት ለማግኘት ነበር። ይህ ደግሞ ችግሩ የበለጠ ስር እንዲሰድ እና ለከፋ አደጋ እንድጋለጥ አድርጎኛል። ይህን የተረዳሁት ግን በጣም ዘግይቼ፣ አሁን ላይ ሆኜ ወደ ኋላ ሳስበው ነው።

በዚህ ሁኔታ ላይ ደግሞ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መሆን ሁኔታውን የተለየ ያደርገዋል። ምክንያቱም ከቤተሰብ መለያየቱ፣ የጓደኛ ግፊቶች እና ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ያለው ነፃነትና አመች ሁኔታዎች፤ ችግሬን ከመፍታት ይልቅ የበለጠ እንዲባባስ እንዲሁም በራሴ የልጅነት እና ያላዋቂነት አስተሳሰብ እና በጊዜያዊ ስሜት እንድነጉድ መንገዱን አመቻችቶልኛል። ምናልባት በሰዓቱ ቤተሰብ ጋር ብሆን የተለየ ነገር ይፈጠር ነበር?! አላውቅም!

በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነበር የመጀመሪያዎቹ ሶስት የትምህርት አመታት ያለፋት። ትምህርቱን እንደ ምንም ተማርኩት፤ "ያለ ምንም ችግር" 4ኛ አመት (Clinical Year ) ደረስኩ። እኔ ላይ ግን የተሻሻለ ነገር አልነበረም። ከዛ ይልቅ ድብርት፣ ጭንቀት፣ ብቸኝነት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ድካም የበለጠ እየተባባሱብኝ የየዕለት ኑሮዬ ሆነው ቀጠሉ።
ላይብረሪ የምውለው እንኳን ለማንበብ ሳይሆን ብቻዬን ለመሆን እና ከህይወት ለመደበቅ ነበር። እንዲያም ሆኖ ጊዜው አለፈ።

4ኛ አመት ትምህርቴን ስጀምር ግን የተፈጠረው ነገር ከዚህ ሁሉ የባሰ እና የህይወቴ ታላቁ ክስተት ነበር....
፨፨፨

(ከዚህ በላይ ማንበብ ስለሚደክማችሁ ቀጣዩን ታሪክ በሌላ ክፍል...)

ዶ/ር ሱራፌል አየለ
የሀኪም ቴሌግራም ገፅ: t.me/HakimEthio

27/04/2022

ለአንድ ግለሰብ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ የስነ-ልቦና እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው በራስ መተማመን (self confidence) ነው፡፡ ብዙዎቻችን በራስ መተማመናችን አነስተኛ ወይም ከነጭራሹ ባለመኖሩ ምክንያት ያጣናቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡

ለመሆኑ በራስ መተማመን ምንድን ነው ?? በራስ መተማመን ማለት ስለ ራሳችን ችሎታ በቂ የሆነ እውቀት እና እምነት ኖሮን ከዚህ በመነሳት ደግሞ በግፊት እና በጫና ውስጥ ስንሆን ጥሩ ውሳኔዎችን መስጠት ነው ይለናል፡፡

በራስ መተማመን የራስ እውቀት እና ክብር (self esteem) እና የራስን ችሎታን የማወቅና ውጤታማ በሆነ መልኩ ነገርን እፈጽማለሁ ብሎ በራስ ላይ እመነት መጣል (self efficacy) ድምር ውጤት ሲሆን፤ በራስ የሚተማመን ሰው መገለጫዎቹም……..

ስለ ነገ ሲያስብ መልካም መልካሙ ነው የሚታየው፣ በራሱ የሚተማመን ሰው ምክንያታዊ በመሆን ምን ይመጣልን ከግምት ውጥ በማስገባት እና አደጋን በመጋፈጥ (risk taker) ኢላማውን ለመምታት የሚታትር ነው ፣ በእራሱ የሚተማመን ሰው እራሱን በትክክለኛ ደረጃ የሚወድ ነው….. ወዘተ በአንጻሩ ደግሞ በራሱ የማይተማመን ሰው ደግሞ የሚሞክራቸው ነገሮች የሚሳኩለት የማይመስሉት፣ ነገን ሲያስብ መጥፎው ብቻ እና ውድቀቱ ፈጥኖ የሚታየው፣ አቅሙን አሟጦ ለመጠቀም የሚፈራ ወዘተ… መገለጫዎች ያሉት ነው፡፡

በራስ መተማመንን እንዴት መገንባት እንችላለን?

1.በራስ መተማመንህን የሚሸረሽሩ ሃሳቦችን ነቅሰህ አውጣ፡-

በአዕምሮህ ውስጥ ያሉትን አልችልም፣ አይሳካልኝም፣ እወድቃለሁ እና አይሆንልኝም የሚሉ አሉታዊ ሃሳቦችን ለያቸው፡፡ እነዚህ ሃሳቦች የጨለምተኛነትን ዘር በውስጥህ በመዝራት የራስ ዕውቀትህን በማሳነስ በእራስ መተማመንህን ይሸረሽሩታል፡፡

2.አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ አዎንታዊ ቀይራቸው፡-

ከላይ የተጠቀሱትን አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ ምክንያታዊ ወደ ሆኑ አዎንታዊ ሀሳቦች ቀይራቸው ለምሳሌ እችላለሁ፣ እሞክረዋለሁ ፣ አሳካዋለሁ ወደ ሚሉ ሃሳቦች ቀይራቸው እነዚህን እራስን የማበረታቻ እና ለራስ ዕውቅና መስጫ ሃሰቦች ቀስ በቀስ አዳብራቸው፡፡

3.አዎንታዊ ሃሳቦችህን ትኩረት ስጣቸው፡-

አዕምሮህ አሉታዊውን ሃሳቦች ብዙ ትኩረት እንዳይሰጠቸው ለአዎንታዊው ሃሳቦች ሰፊ ቦታና ጊዜ ስጣቸው፡፡ ለማሳካት የምታልመው ን ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ይህን ጉዳይ ወደ ትናኝሽ ሃሳቦች በመቀየር ወደ ተግባር ግባ፡፡

4.ዙሪያህን በጥንቃቄ ቃኘው፡-

በዙሪያህ ላሉ አዎንታዊ ሀሳቦችን እንድታስብና መልካም ድርጊቶችን እንድታከናውን ለሚያደርጉህ እና ለሚያግዙህ ወዳጆችህ ሰፊ ጊዜ ስጥ፣ በአንጻሩ ስለ ራስህ መጥፎ እንድታስብና ምቾት የማጣት ስሜት እንዲሰማህ ከሚያደርጉ ሰዎች እና ድርጊቶች በተቻለህ መጠን እራቅ፡፡

5.ችሎታህን ለይተህ አውጣ፡-

እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ በአንድ ነገር ላይ ጎበዝ ነው፡፡ ስለዚሀም አንተም ጎበዝ የሆንክበትን ወይም ብሰራው አሳካዋለሁ የምትለውን ነገር ነቅሰህ በማውጣት ትኩረትህን ወደእዚህ አድርገው፡፡

6.በራስህ ኩራ፡-

ባሉህ አዎንታዊ እና በጎ ጎኖች ምክንያት ተገቢ እና መጠነኛ የሆነ ኩራትን ኩራ፡፡

7.ሁሌም ራስህን ሁን፡-

አዳዲስ ሰዎችን ስትተዋወቅ ስለ እራስህ ውሸት በመናገር ዕውቅናን ለማግኘት አትሞክር፡፡

በራስ መተማመን ሁሌም ሚዛናዊ ሊሆን የሚገባው እሴት ነው፡፡ ዝቅተኛ በራስ መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን አስቀድሞ በመፍራት ነገሮችን ከመስራት ወይም ከመሞከር ይቆጠባል አልያም ደግሞ ከመጠን ያለፈ እና ጥግ የያዘ በራስ መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን ነገር ሁሉ እየሞከረ ራሱን አደጋ ውስጥ ይከታል፡፡ ስለዚህ በራስ መተማመን ሁለቱን በአመክንዮአዊ ልኬት ሚዛናዊ አድርጎ መጓዝን አብዝቶ ይጠይቃል፡፡

BonTube Share and Like 👍 ማድረግ አትርሱ!

አሜሪካዊው ቢሊየነር መስክ ትዊተርን በ44 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት ተስማማአሜሪካዊው ቢሊየነር ኢሎን መስክ የትዊተር ኩባንያን ለመግዛት መስማማቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ቢሊየነሩ ኤሎን መስክ ት...
26/04/2022

አሜሪካዊው ቢሊየነር መስክ ትዊተርን በ44 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት ተስማማ

አሜሪካዊው ቢሊየነር ኢሎን መስክ የትዊተር ኩባንያን ለመግዛት መስማማቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ቢሊየነሩ ኤሎን መስክ ትዊተር የተሰኘውን የማህበራዊ ሚዲያ በ44 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት ውል የፈጸመ ሲሆን ይህም በሚሊዮን በሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች እና በአለም የፖለቲካ መሪዎች የተሞላው ትዊተር በአለም ቁጥር አንዱ ባለጸጋ እንዲያዝ አድርጎታል፡፡

ፎርብስ መጽሄት መረጃ መሰረት 273.6 ቢሊዮን የሚገመት የተጣራ ሃብት ያለው ኤለን መስክ የአለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ ነው። ይህም በዋነኝነት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራች በሆነው ቴስላ ባለው ድርሻ እንዲሁም ስፔስ ኤክስ የተባለውን የኤሮስፔስ ድርጅትም ይመራል።

"ነፃ ንግግር የዲሞክራሲ መሰረት ነው፤ ትዊተር ደግሞ ለሰው ልጅ የወደፊት ህይወት ወሳኝ ጉዳዮች የሚከራከሩበት የዲጂታል ከተማ አደባባይ ነው። "ሲል ኤለን መስክ ስምምነቱን ይፋ ባደረገበት መግለጫ አስታውቋል።

"በተጨማሪም ትዊተርን አዳዲስ ይዘቶች በመጨመር ማሻሻል እንዲሁም የትዊተርን አልጎሪዝም ክፍት በማድረግ መተማመንን ለመጨመር፣ አይፈለጌ ሃሰተኛ አካውንቶችን በማስወገድ እና ሁሉንም ሰው በማረጋገጥ ትዊተርን ከምንጊዜውም በላይ ማድረግ እፈልጋለሁ" ሲል አክሏል።

"ትዊተር ትልቅ አቅም አለው። ይህንንም አቅም ለማሳየት ከኩባንያው እና ከተጠቃሚው ማህበረሰብ ጋር ለመስራት እጠብቃለሁ።" በማለት አስረድቷል።

ትዊተር በይዘቱ ላይ ከፖለቲከኞችና ተቆጣጣሪዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እየጨመረ ባለበትም ወቅት ነው ኤለን መስክ ይህንን ያሳወቀው።

Via ,

የትንሳኤ ሎተሪ ወጣ ~ ለዕድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ!!የትንሳኤ ሎተሪ   ቅዳሜ ሚያዝያ 15/ ቀን 2014 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝ...
25/04/2022

የትንሳኤ ሎተሪ ወጣ ~ ለዕድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ!!

የትንሳኤ ሎተሪ ቅዳሜ ሚያዝያ 15/ ቀን 2014 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል፡፡

1ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 0337949
2ኛ. 2,500,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር1202412
3ኛ. 1,250,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 0674207
4ኛ. 600,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 0765249
5ኛ. 300,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 0554605
6ኛ 150,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር1127709
7ኛ.100,000 ብር የሚያስገኘው የ7ኛ ዕጣ ቁጥር 1750931
8ኛ. 18 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው 3,000 ብር የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 24699
9ኛ. 18 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 74363
10ኛ.180 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 600 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 1684
11ኛ. 180 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 300 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 0538
12ኛ. 180 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 150 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 3850
13ኛ. 1,800 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 120 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 534
14ኛ. 1,800 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 90 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 687
15ኛ 18,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር45 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 50
(የማስተዛዘኛ ዕጣ) ደግሞ 1 ቁጥር በመሆን ወጥቷል፡፡
አስተዳደሩ ለእድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ ይላል።
ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር

Hello❤
25/04/2022

Hello

"... #ፈተና እኮ በፖሊስና በወታደር ታጅቦ በልዩ ሁኔታ ነው የሚሠራጨው፡፡ ባለፈው ፈተና አጅበው ከሚሄዱ የፌዴራል ፖሊሶች መካከል ሦስት በታጣቂዎች ተገድለውብናል፡፡ ፈተና ማሠራጨትና ሳይሰ...
25/04/2022

"... #ፈተና እኮ በፖሊስና በወታደር ታጅቦ በልዩ ሁኔታ ነው የሚሠራጨው፡፡ ባለፈው ፈተና አጅበው ከሚሄዱ የፌዴራል ፖሊሶች መካከል ሦስት በታጣቂዎች ተገድለውብናል፡፡ ፈተና ማሠራጨትና ሳይሰረቅ ማስፈተን የሞት የሽረት ጉዳይ እየሆነ ነው፡፡በዚህ የፈተና ስርቆት አካባቢያቸውን ለመጥቀም የሚያስቡ ነገሩ ትውልድን መግደል መሆኑን መረዳት አለባቸው፡፡ ለፖለቲካ ትርፍ የሚያደርገው ካለም ለጊዜው ፖለቲካዊ ትርፍ ቢያገኝበትም መልሶ ግን አገር መግደሉን መረዳት አለበት፡፡

#ተቃዋሚም ሆነ ማንም በትምህርት ሥርዓት ላይ መቀለድ በትውልድ ላይ መቀለድ ነው የሚል ስምምነትን ያሰፈነ መፍትሔ ያስፈልገናል፡፡ በመንግሥት በኩል ፈተናው የማይሰረቅበትን መንገዶች መፈለግ አለበት፡፡

#ተማሪዎች ተጣጥረው በሚያገኙት ዕውቀት ማለፍን እንዲያስቀድሙ ካላደረግን ስርቆቱን ማቆም አንችልም..."

ኘሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ Via Ethiopian Reporter

Vacancy Announcement:============Awash Bank invites competent and qualified candidates for the following positions. 1. S...
24/04/2022

Vacancy Announcement:
============
Awash Bank invites competent and qualified candidates for the following positions.
1. Senior Information Systems Auditor
2. Information Systems Auditor
3. Research and Development Officer
4. Legal Officer
5. Customer Service Officer I/ Direct Sales Representative/ Digital Channel Officer I
How to Apply 👇👇
For more information on qualifications and more, please join our Telegram channel https://t.me/awash_bank_official
Or Please visit the below link to our website:
https://www.awashbank.com/vacancy

Happy Easter 🤲

በኢትዮጵያ ዝቅተኛውን የደመወዝ ክፍያ ለመወሰን በኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌደሬሽን የላቀ ጥረት እየተደረገ ነው።◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦በዓለማችን ለሠራተኞቻቸው ዝቅተኛ የደመወዝ ...
23/04/2022

በኢትዮጵያ ዝቅተኛውን የደመወዝ ክፍያ ለመወሰን በኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌደሬሽን የላቀ ጥረት እየተደረገ ነው።
◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦
በዓለማችን ለሠራተኞቻቸው ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ ካላቸው አምስት አገራት መካከል ሶስቱ በአፍሪካ ይገኛሉ።
ውሳኔው በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚጸድቅ ከሆነ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወስን የደመወዝ ቦርድ ይቋቋማል ተብሏል።

የዓለም የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን የአፍሪካ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ፎረም በጥር ወር 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ባካሄደው የሁለት ቀናት ጉባኤ ላይ የአፍሪካ አገራት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወስኑ፣ የፌዴሬሽኑ ዋና ጸሐፊ ሻረን ባሮው አሳስበው ነበር፡፡

ዋና ጸሃፊው በወቅቱ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወስኑ ካሳሰቧቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ስትሆን ቀሪዎቹ ሀገራት ደግሞ ጋና፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ናይጄሪያ፣ ኒጀር፣ ሴኔጋልና ዛምቢያ ነበሩ፡፡

በዚህ ማሳሰቢያ መሠረትም ኢትዮጵያ በ2021 ዓ.ም ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ ወለልን ለመወሰን ረቂቅ ህግ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ገልጾም ነበር፡፡

በመሆኑም አል ዐይን አማርኛ ጉዳዩ የት ደረሰ ሲል የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌደሬሽን ጠይቋል፡፡
የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለአል ዐይን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ለመወሰን ስለተጀመረው ስራ አብራርተዋል፡፡

ኮንፌዴሬሽኑ በ2021 ዓ/ም በወቅቱ የሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሚባለው ተቋም ጋር ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ ወለል ለመወሰን የሚረዳ ረቂቅ ህግ ማዘጋጀቱን ያብራሩት አቶ ካሳሁን ህጉ በሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲቀርብ በተስማማነው መሠረት ረቂቅ ህጉ ለሚኒስትሮች ምክር ቤትም ቀርቧል ብለዋል፡፡

ይሁንና ወቅቱ አገር አቀፍ ምርጫ የነበረበት ጊዜ በመሆኑ ረቂቅ ህጉ በወቅቱ በነበረው መንግሥት ሳይታይ ቀርቷል። በምርጫ ወደ ስልጣን የመጣው አዲሱ መንግሥትም በቶሎ ረቂቅ ህጉ ላይ ተወያይቶ ደንቦቹን ለማጽደቅ ረቂቅ ህጉ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እየታየ ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም ምክር ቤቱ በረቂቅ ህጉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጥበት ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመሆን ግፊት በማድረግ ላይ እንደሆኑ አቶ ካሳሁን ተናግረዋል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በረቂቅ ህጉ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ካሳለፈ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጁ ላይ በተቀመጠው መሠረት ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ ወለል የሚወስን የደመወዝ ቦርድ ይቋቋማልም ነው ያሉት፡፡

ቦርዱ ከአሠሪ፣ ከሠራተኛ እና ከመንግሥት የተውጣጣ አባላት የሚኖሩት ሲሆን በጥናት ላይ የተመሠረተ ድርድር እንደሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው እንደገለጹት፣ አሁን ባለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ዝቅተኛው የተቀጣሪ ደመወዝ ለጊዜው 6,800 ብር መሆን አለበት ብለዋለል።

በቦርዱ የድርድር ውጤት መሠረት፣ አንድ ሰው በቀን ስንት ብር ቢከፈለው ምግብ በልቶ ማደር ይችላል? በወርስ ስንት ሊከፈለው ይገባል? በሚል ጥናት ላይ ተመስርቶ ውይይት እና ድርድር ከተደረገ በኋላ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚወሰን እና ወደ ተግባር እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

በዓለማችን ለሠራተኞቻቸው ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ ካላቸው አምስት አገራት መካከል ሶስቱ በአፍሪካ የሚገኙ ሲሆን እነሱም፣ ሞሪታኒያ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ኢትዮጵያ አነስተኛ የሰራተኞች ክፍያ የሚፈጸምባቸው አገራት መሆናቸውን የዓlም ሥራ ድርጅት መረጃ ያስረዳል፡፡

በሌላም በኩል ደግሞ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ጃፓን ለሰሠራተኞቻቸው በአንጻራዊነት የተሻለ ክፍያ የሚፈጽሙ አገራት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

Via -ain

ውሳኔው በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚጸድቅ ከሆነ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወስን የደመወዝ ቦርድ ይቋቋማል ተብሏል

በኑሮ ውድነት ምክንያት ልንፋታ ነው‼"ካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘው ኢሊሊ ሆቴል ለስራ ጉዳይ ቀጥሬው የነበረነን ሰው አናግሬ ስወጣ እንዲህ ገጠመኝ.....ሁለት ወጣት ሴትና ወንዶች መኪና ውስጥ ...
20/04/2022

በኑሮ ውድነት ምክንያት ልንፋታ ነው‼

"ካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘው ኢሊሊ ሆቴል ለስራ ጉዳይ ቀጥሬው የነበረነን ሰው አናግሬ ስወጣ እንዲህ ገጠመኝ.....

ሁለት ወጣት ሴትና ወንዶች መኪና ውስጥ ተቀምጠው በባነር ደግሞ 4 ወጣቶች ምስላቸውን ይዘው "በኑሮ ውድነት ምክንያት ሊፋቱ ነው" ብለው ሲለምኑ አገኘኋቸው። እየቀለዳችሁ እንዳይሆን ብዬ ከልጆቹ በተጨማሪ ጥንዶቹንም ፎቶ አንስቼ በፌስቡክ ልለጥፈው ወይ ስላቸው እባክህ ባንተ ገፅ ለጥፍልን ስላሉኝ ይኸው እኔም አጋርቼያችኋለሁ።"

Via - ሚስባህ

20/04/2022

አንድ ሰው በመጋዘን ውስጥ ስራ ላይ እያለ በጣም የሚወደው የእጅ ሰዓቱ ይጠፋበታል፡፡ በመጋዝኑ ውሰጥ እየተመላለሰም በፍለጋ ቢወድቅ ቢነሳ ሊያገኘው ባለመቻሉ ጨዋታ ላይ የነበሩ ልጆች በፍለጋ እንዲያግዙት፤ ሰዓቱን ላገኘለት ልጅም ሽልማት እንደሚሰጣቸው በመናገር ወደ ፍለጋ አሰማራቸው፡፡

ልጆቹም ሽልማት እንዳለው ባወቁ ጊዜ በፍጥነት ወደ መጋዝኑ በመግባት ሁሉን ቦታ በፍለጋ አዳረሱት፡፡ ነገር ግን ሰዓቱን ሊያገኙት አልቻሉም፡፡ መጋዘኑ ውስጥ ያለውን እቃ ቢያነሱ ቢጥሉ ማግኘት አልቻሉም፡፡ ሰውዬው ልጆቹ እንዳላገኙት ባወቀ ጊዜ ተስፋ በመቁረጥ የሰዓቱን ፍለጋ ሊያቆም ሲል አንድ ትንሽ ልጅ ጠጋ ብሎ አንድ እድል እንዲሰጡት ጠያቃቸው፡፡ ሰውዬውም እስኪ ይሞክር በሚል ስሜት ፍቃደኛ ሆኑለት፡፡ ከቆይታ በኋላ ትንሹ ልጅ ሰዓቱን እጁ ላይ አንጠልጥሎ ተመለሰ፡፡

ሰውዬውም በሰዓቱ መገኘት እጅግ ደስ እያለው ሌሎቹ ልጆች ማግኘት ያልቻሉትን እንዴት ሊያገኘው እንደቻለ ተደንቆ ጠየቀው።

ትንሹ ልጅም “እኔ ምንም አላደረኩም፡፡ ያደረኩት ነገር ከመጋዘኑ መሀከል ላይ በጸጥታ በመቆም ማዳመጥ ነበር፡፡ በፀጥታው ውስጥም የሰዓቱ መቁጠሪያ የሆኑት ዘንጎች ሲዞሩ የሚፈጥሩት ጠቅ…ጠቅ የሚለው ድምጽ ተሰማኝ ይህን አቅጣጫ ተከትዬ ስመለከት ሰዓቱን አገኘሁት” አላቸው፡፡

በጽሞና ውስጥ የሆነ አዕምሮ ነገሮችን ለይቶ መረዳት ይችላል፡፡ አርቆ ለማሰብም ፋታ ያገኛል፡፡

ስለሆነም ጫጫታ በበዛበት ዓለም ካለን ሰዓት ውሰጥ የተወሰኑትን ደቂቃዎች ለጽሞና ማዋል ከእራስ ጋር ለመነጋገርና መድረስ ወደምንፈልግበት የሕይወት ዓላማ አቅጣጫችንን ለማስተካከል ይረዳናል፡፡

ሠላም ለምድራችን!

🔔ስለ ለምጽ (ለምጥ) በሽታ እና መፍትሔው🔔የለምጽ በሽታ የሚከሰትበት ምክንያት በቆዳ ውስጥ ያሉት ቀለም የሚያመነጩ ሕዋሳት ሲሞቱ ነው በማለት የሳይንስ ዓለም ይተነትነዋል።በሽታው በቆዳ ላይ ...
27/03/2022

🔔ስለ ለምጽ (ለምጥ) በሽታ እና መፍትሔው🔔

የለምጽ በሽታ የሚከሰትበት ምክንያት በቆዳ ውስጥ ያሉት ቀለም የሚያመነጩ ሕዋሳት ሲሞቱ ነው በማለት የሳይንስ ዓለም ይተነትነዋል።

በሽታው በቆዳ ላይ ነጣ ያሉ ነጠብጣቦች እንዲወጡ ወይም የተወሰነ የቆዳ ክፍል እንዲነጣ ያደርጋል።
ይህ በሽታ በአንዳንድ ተጠቂዎች ላይ በመጀመሪያ ከነጣው የቆዳ ክፍል አልፎ የማይስፋፋ ሲሆን በሌሎች ላይ ደግሞ ወደ መላው ሰውነታቸው በፍጥነት ይሰራጫል።

ለበርካታ ዓመታት ቀስ በቀስ እየተስፋፋባቸው የሚሄድ የበሽታው ተጠቂዎችም አሉ። ለምጽ የሚያስከትለው የሕመም ስሜት ካለመኖሩም በላይ በንክኪ አይተላለፍም።

በሽታው ዘርና ቀለም የማይለይ ከመሆኑም በላይ ሴቶችንና ወንዶችን እኩል ያጠቃል።
ሆኖም የበሽታው መነሻ እስከ አሁን በውል አልታወቀም።

የበባህላዊ ህክምና ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር እውን የሆነ እና የማያዳግም መፍትሔ በአበው ጠበብት አባቶች እና የጥበብ ሊሂቃን ዘንድ ያለ ምንም ቴክኖለጂ ያለ ምንም ናሙና ከ ፈጣሪ በተሰጣቸው ጸጋ መፈወሳቸው ሲሆን።

የዘመናዊ ህክምና አሰጣጥ ለየት የሚያደርገው ነገር ደግሞ የበሽታ አምራች ኃይል እራሱ የዘመኑ ስልጣኔ ይሆን እና! ፊቱን ዞር በማድረግ ደግሞ ላመረተው በሽታ የሚሆን ማስታገሻ መድኃኒት በማምረት ህብረተሰቡን የእድሜ ልክ ጥገኛ ይሆን ዘንድ ይገደዳል።

ይህ ማለት ሁሉም የባህል ህክምና አሰጣጥ እያደነቅኩ ወይም ሁሉም የዘመናዊ ህክምና አሰጣጥ እየነቀፍኩ ሳይሆን የኢትዮጵያ ቅርስ እና ተሰጥኦ የሆነው የጥንት ጥበብን በማንኳሰስ የተለያየ አጸያፊ ስም በመስጠት የምዕራባውያን ስልጣኔ አጉልቶ በማየት የሚሸረብ ሴራ ሳይ ጊዜ ቅሬታ ፈጥሮብኝ የሰጠኃት አስተያየት ናት።

እንጂ ዘመናዊ ህክምናም ብዙ መልካም እና ወደር የሌላቸው ህክምና የሚሰጥበት የተለያዩ ንቅለ ተከላዎች፤ የወሊድ ክንዉኖች፤ የተለያዩ ትሪትመንቶች፤በተለያየ አደጋ የሚደርሱ ጉዳቶች የሚሰጥ ህክምናዎች የተለያዩ በሽታ ፈጣሪ ዶክቶሮች የተመረቱ ወረርሽኞች እና የመሳሰሉት በማስታገስ ወደር አይገኝለትም።

ቢሆንም ግን ቅሉ ተወደደም ተጠላም ቀዳሚው የአበው ጥበብ እና የባህል ህክምና መሆኑን ልበ በሉልኝ።

ወደጉዳዬ ስመለስ የለምጽ (ለምጥ) በሽታ መፍትሔ
።።።።።።።።የለምጽ መድኃኒት።።።።።።።።።።
በምስሉ የምትመለከቷት ዕጽ ወርቅ በሜዳ ትባላለች።
የወርቅ በሜዳ ሥር እና ቅጠል አንድ ላይ በማድረቅ በመደቆስ ከገብስ ጠላ ጋር አብሮ በመጥመቅ አልያም ከ ጽራይ የገብስ ጠላ ጋር !

#የወርቅ በሜዳ ዶቄት አንድ የሻይ ማንኪያ
#ከገብስ የጠለለ ጠላ ግማሽ ሌትር ጋር ጨምሮ አሳድሮ ጧት በባዶ ሆድ ቀስ እያሉ መጠጣት።

ይህ ድርጊት ከ 7 ቀን እስከ 21 ቀን በተደጋጋሚ ይጠቀሙ ሙሉ ለሙሉ ይወገዳል።

በተጨማሪም የወርቅ በሜዳ ቅጠል እና ሥሩ ጨቅጭቆ ለሁለት 7 ይጠመቁ።
ለ 20 ደቂቃ ያክል ከጥምቀት በኃላ በሽታው ያለበት ቦታ ጸሐይ ላይ ሁኖ ማስመታት።

ይህ ጥበብ እንደቀልድ ባታዩት ምክሬ ነው ምክንያቱም ሙሉ መፍትሔ በዓይኔ ያየሁበት ጥበብ ነው።
ወርቅ በሜዳ የለምጽ መፍትሔ ማት የተለያዩ አሰጣጥም አላት።

የሚከለክለው፦
#የፍየል እና የላም ስጋ መብላት ለአንድ አመት ያክል አይመከርም።
#የሰው ጥላ እና ሰው ከሚዞርበ ቦታ ርቀን እንጠቀመው

ሼር ሼር
Via ዶክተር ሶፎኒያስ 📢 ያማክሩ! ይጠይቁ! ይወቁ! ልታማክሩ ወይም ልጠይቁ የምትፈልጉ ቴሌግራም ላይ 👇
https://t.me/DrSofonias

Of-Eeggannoof!=====/////=========Qoricha cephalexin(brand name KELEXIN) jedhamu kan bifa dhangala'aa(syrup) 250mg/5ml, d...
27/03/2022

Of-Eeggannoof!
=====/////=========
Qoricha cephalexin(brand name KELEXIN) jedhamu kan bifa dhangala'aa(syrup) 250mg/5ml, dhabbataa "Kilitch Estro Biotech, Ethiopia "n oomishamu rakkoo qulqullinaan walqabate qaba waan jedhameef taajajila hawaasaf akka hin oollee yeroof dhorkamee jira.
Ogessiis ta'ee hawaasni keenya kana beekee eeggannoo barbachisuu gochun dirqama!

15/03/2022

ፕሬዝዳንት ፑቲን
ጦርነቱን ስንጀምር እናሸንፋለን ብለን ብቻ አይደለም። አለምን እናስተምርበታለን ብለን ነው። አንዳዶች የሩሲን ወራሪነት አብዝተው ይዘምራሉ። ምዕራባውያን እኮ ሙሉ አፍሪካን ወረው እያለቡ ቁቤውን ለነሱ አሬራውን ለአፍሪካውን መልሰው የሚሸጡ አገር ናቸው። ከአለም የነዳጅ ቀጅ አገሮች ውስጥ አረብ አገሮችና አፍሪካውያን ናቸው። በነዳጅ ሀብት ግን የናጠጠ ጡንቻ ያላቸው ምዕራባውያን ናቸው። የአለም ማዕድን 75 በመቶው ከአፍሪካ የሚመጣ ነው። ይሄንን ሀብት ያላቸው አፍሪካዊያን ለምግብ የሚለምትኑ ምዕራባውያንን ነው።
እናም ይላል የኦን ዘደይ ጋዜጣ
ከምዕራባውያን የተረፈውን የሚጠብቅ አለም እኛን ለምን ደህንነታችንን አስጠበቁ ብሎ የሚወቅሰን ካለ ክሱ የድመትና የስጋ ፍርድ አይነት ይዘት እንዳለው ይወቁ። ስጋው የሚበላ አይጥ በዩን ድመትን ካመሰገነ ምንስ ክስ ቤት አስኬዳቸው ይላል።
እኛ ስለ ዩክሬን አንጨነቅም። ትርኢት በለመደ ጦጣ የምትመራ አገር ሩሲያን መግታት አትችልም። የዩክሬን ህዝብ የኛ ህዝብ ነው። ንብረቱ እንዳይጎዳ አድርገን ቀዝቀዝ ያለ ኦፕሬሽን ሰርተን በቅርቡ እናጠናቅቃለን። የኛ መውረር የሚገርመው
አለም አይጨነቅ። ነገ እኔ ከፕሬዝዳንትነት ልነሳ እችላለሁ። ነገ የሚመጣው መሪ የኔን ህልም አያሳከውም። ይህ አካባቢ ከሩሲ ጥላቶች መፅዳት አለበት። በጥላት የተከበበች ሩሲያን ልመራ አይደለም ቤተ መንግስት የገባሁት። ከጥላቶቿ በላይ ከፍ ያለች ጠንካራ ሩሲያን ለመፍጠር ነው ወደ ስልጣን የመጣሁት።
አሜሪካ ሩሲያ ቻይናን መሳሪያ ጠየቀች የሚል ፕሮፓጋንዳ መስራቷ ብዙም አያስገርምም። በአፋቸው አለምን አታለው ገሀነም አድርገው መኖር ይችላሉ። ሩሲያን ግን ማማት እንጅ መንካት አይችሉም።

ዘገባው የኦን ዘደይ እና የጆርዳን ጋዜጣ ነው።

Via

ብዙ ስለሚነገርላቸው የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጠባቂዎች ምን ያክል ያውቃሉ…?ሰሞኑን የምዕራባውያን የእግር እሳት እንደሆኑ የሚነግረላቸው የሞስኮው ሰው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ...
12/03/2022

ብዙ ስለሚነገርላቸው የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጠባቂዎች ምን ያክል ያውቃሉ…?

ሰሞኑን የምዕራባውያን የእግር እሳት እንደሆኑ የሚነግረላቸው የሞስኮው ሰው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን በጀመሩት ወታዳራዊ ዘመቻ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ቀዳሚው አጀንዳ ከሆኑ ሰነባብተዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን የጀመሩት ጦርነት አጀንዳ የሆኑትን ያክል፤ በርካታ የዓለም አቀፍ የሚድያ አውታሮች ስለ ስብዕናቸው እና የህይወት ዘይቤያቸው ሲናገሩም ይስተዋላል።

የቀድሞ የሩሲያ የስለላ ተቋም (ኬጂቢ) አባል የነበሩት ቭላድሚር ፑቲን፤ ለብዞዎች ግልጽ ካልሆነው የቤተሰብ ሁኔታ አንስቶ ስለሚደረግላቸው እጅግ የተራቀቀና ከሌሎች የዓለም መሪዎች የተለየ የደህንነት ጥበቃም በርካቶች ሲናገሩ ይደመጣል።
በተለይም “ፍጹም የመድከም ስሜት አይታይባቸውም” ስለሚባሉት የፑቲን ጠባቂዎች በርካታ ነገሮች ይባላሉ።
ቭላድሚር ፑቲን በማንኛውም ሁኔታ ላይም ቢሆኑ ላብ የማያጠምቃቸው እና ቅዝቃዜ የማይበግራቸው እንዲሁም የፕሬዚዳንቱን እያንዳንዷን የእግር ኮቴ እንቅስቃሴና እስትንፋስ በትኩረትና ቅርበት የሚከታተሉ “ባላባቶች” የተሰኙ ጠባቂዎች አላቸው።
ፑቲን ሊሄዱበት ካሰቡ እንደሁም ባሉበት ስፍራ ሁሉ እነዚህ ጠባቂዎች (የደህንነት ቡድን አባላት) አሉ።
ሩሲያ ቢዮንድ የተሰኘ ድረ ገጽ እንዳስነበበው፤ የፑቲን ጠባቂዎች፤ ፕሬዝዳንቱ ላይ ሊቃጡ ይችላሉ የሚሏቸውን አደጋዎች እንዲሁም በጉብኝት ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ እንደ መሬት መንቀጥቀጥና ጎርፍ ዓይነት የተፈጥሮ አደጋዎች የመተንተን ብቃት ያላቸው ሁለገብ ጠባቂዎች ናቸው።

ሌላው አስገራሚው ነገር በሩሲያ የደህንነት አገልግሎት አማካኝነት በፑቲን ለጠባቂነት የሚመረጡት ጠባቂዎች በሌላው ዓለም እንደተለመደው ከወታደር ቤት የተመለመሉ አለመሆናቸው ነው።
ሩሲያ ቢዮንድ አንድ የቀድሞ የፑቲን ጠባቂ ነግሮኛል ብሎ እንደጻፈው ከሆነ "የፕሬዝዳንቱ ጠባቂዎች በየተራራው የመዝለልና አድፍጦ የመወጋት ልምድ ሊኖራቸው ይገባል የሚለው ለፑቲን አይሰራም" ይላል።
የቀድሞ የፑቲን ጠባቂ " የትግል ልምድ ጠቃሚ ነው ነግር ግን ለእኛ ስራ እምብዛም አይደለም፣ የጠባቂዎች ስራ ታዋቂውን ሰው ከማይታይ ሰው መጠበቅ እንዲሁም ጥቃት የሚያድረስ አካል ካለም ጥቃት መሰንዘር ብቻ ነው" ሲልም አክሏል።
የፕሬዝዳንቱን ደህንነት መጠበቅ ቀዳሚው የጠባቂዎቹ ኃላፊነት መሆኑን ያስረዳው የቀድሞ ጠባቂ፤ ጠባቂዎች በፕሬዝዳንቱ ላይ ሊቃጡ የሚችሉ አደጋዎችን ቀድሞ ለመተንበይ የሚያስችል "ኦፕሬሽናል ሳይኮሎጂ" ሊኖራቸው እንደሚገባም አንስቷል።
የፑቲን ጠባቂ ለመሆን ከ35 ዓመት በታች፣ ከ175 እስከ 190 ሴንት ሜትር ቁመት እንዲሁም ከ75 እስከ 90 ኪ.ግ ክብደት መሆን እንደሚያስፈልግም ተናግሯል።
ይህ ብቻ አይደለም የፑቲን ጠባቂዎች የውጭ ቋንቋዎች የመረዳት አቅም ያላቸውንና ፖለቲካን በደምብ የሚገነዘቡ ሊሆኑ እንደሚገባና ይህም በተለያዩ አጋጣሚዎች ከፑቲን ጋር ቀርበው የሚያወጉ ሰዎች ማንነት ለማወቅ እንደሚያስችላቸውም አስረድቷል።

ሩሲያ ቤዮንድ የፕሬዚዳንቱ ጠባቂዎች የመቋቋም አቅምና በስፖርት የዳበረ ሰውነት ያላቸው፣ ወፍራም ልብሶች እንቅስቃሴያቸውን ሊያደናቅፉ የችላሉ በሚል ከፍተኛ ቅዝቃዜን ለመቋቋም እና ቀላል ካፖርት እንዲለብሱ የሰለጠኑ መሆናቸውም ይነገራል።
ከፍተኛ ሙቀት ውስጥ ሆነው ላብ አይታይባቸውም ነው የሚባልው፡፡
የፊዚዮሎጂ ሂደቶችን የሚነኩ መድኃኒቶችን እንደሚጠቀሙ የሚነገርላቸው የፑቲን ጠባቂዎች አልፎ አልፎ ጭንቀታቸውን ለማስታገስ ሲጋራ እንዲያጨሱ ይፈቀድላቸዋል ይፈቀድላቸዋልም ነው የተባለው።
አንድ የፕሬዝዳንቱ ጠባቂ እድሜው 35 ዓመተት ከሞላው ከሞላው ከስራው በጡረታ እንደሚሰናበትም ሩሲያ ቤዮንድ በደርረ ገጹ አስነብቧል።

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 19:00
Tuesday 08:00 - 19:00
Wednesday 08:00 - 19:00
Thursday 08:00 - 19:00
Friday 08:00 - 19:00
Saturday 08:00 - 17:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eva + posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share



You may also like