Abebaw Ayana-Yehagerie Lij

Abebaw Ayana-Yehagerie Lij Artist at Music Singer

ቴዲ አፍሮ ሙዚቅ ህይወቴ የሚለውን ሙዚቃ ከህይወቱ ጋር የተያያዘ ሙዚቃ እንደሆነ ይናገራል ሙዚቃውንም እንደሚፈልገው ሆኖለት እንደወጣ እንዲ ሲል ተናግሯል ስለሙዚቃ በልጅነቱ ካለው ፍቅር የተነ...
21/10/2023

ቴዲ አፍሮ ሙዚቅ ህይወቴ የሚለውን ሙዚቃ ከህይወቱ ጋር የተያያዘ ሙዚቃ እንደሆነ ይናገራል ሙዚቃውንም እንደሚፈልገው ሆኖለት እንደወጣ እንዲ ሲል ተናግሯል
ስለሙዚቃ በልጅነቱ ካለው ፍቅር የተነሳ በልጅነቱ ያጋጠመውን እንዲህ ሲል ተናግሯል ያንን ሁሉ ያካተተ ነው ሙዚቃ ህይወቴ የሚለው ሙዚቃ::

ስለ አባቱም እንዲህ የሚል ንግ ግር ተናግሯል አባቴ ብሎኝ ብሎኝ ሲያቅተው ሙዚቃ ውስጥ መግባት የምትፈልግ ከሆነ ስለሙዚቃ መማር አለብህ ብሎ ያሬድ ት/ቤትም ይዞኝ ሄዶ ነበር..... የልቡ አልሞላለትም ፕሮፌሽናል ሙዚቀኛ እንድሆን ነው ፍላጎቱ ብሏል:: ቴዲ አፍሮ በልጅነቱ ይጫወታቸው ከነበሩት ሙዚቃዎች መሃል የሚያዘወትረው ሙዚቃ እባክሽ ፍቅሬሆይ ተመከሪ የሚለውን /የጥላሁን ገሰሰን/ በጣም በተደጋጋሚ እየጮኸ የሚዘፍነው ሙዚቃ መሆኑንም ይናገራል::

የተማረከው የጠላት ኃይል አሁንም የአማራን እናት ጉርሻና ቡና አልተነፈገም!ፋኖ/ አማራ ለጠላቶቹ የሚራራ ስብዕና ያለው ነው!የተቀረው በአማራ ክልል ተሰማርታችሁ የምትገኙ ሀይሎች  በፋኖ ቅንድ...
02/08/2023

የተማረከው የጠላት ኃይል አሁንም የአማራን እናት ጉርሻና ቡና አልተነፈገም!

ፋኖ/ አማራ ለጠላቶቹ የሚራራ ስብዕና ያለው ነው!

የተቀረው በአማራ ክልል ተሰማርታችሁ የምትገኙ ሀይሎች በፋኖ ቅንድብህን ከምትባል የያዝከውን መሳሪያ ለፋኖ እያስረከብህ ቤተሰቦችህን ብትቀላቀል ይሻላል ።

02/08/2023
14/05/2015 ዓ.ም ለእኔ ደስ የሚልና ልዩ የሆነ ቀን ሆኖ ውሏል።ምክንያቱም 30 አመት ሙሉ ለቄስና ለሽማግሌ አስቸጋሪ የሆነን ትልቅ የቤተሠብ ጠብና ጥላቻ በእኔ መሪነትና አሰባሳቢነት በ...
23/01/2023

14/05/2015 ዓ.ም ለእኔ ደስ የሚልና ልዩ የሆነ ቀን ሆኖ ውሏል።
ምክንያቱም 30 አመት ሙሉ ለቄስና ለሽማግሌ አስቸጋሪ የሆነን ትልቅ የቤተሠብ ጠብና ጥላቻ በእኔ መሪነትና አሰባሳቢነት በሀያሉ እግዚያብሄር ተራዲነት ዳግሞ ላይመለስ ከጥላቻና ከቂም በቀል ምን አገኘን ብለን በመነጋገር የሠይጣንን ስራስር ቆራርጠን ጥለናል።
ሁሌም የማታሳፍረኝ የድንግል ማርያም ልጅ እግዚያብሄር ሆይ ክብርና ምስጋና ለአንተ ይሁን!!

📯 Anniversary Is Loading ...3 years, 3 miles ... and many great memories. We’re thankful for all of you! Stay strong!===...
30/12/2022

📯 Anniversary Is Loading ...

3 years, 3 miles ... and many great memories. We’re thankful for all of you! Stay strong!

=== Alpha our State for Significance!===

📍Addis Ababa, Bole Sub-City, Alemnesh Plaza 6th Floor.
🌐 www.alphagenuine.com
☎️ +251930020395 Bole Branch
+251988010611 Megenagna Branch
+251943120133 Adama Branch

zanziman ellie ይባላል። በደቡብ  ሩዋንዳ በምትገኝ አንዲት መንደር ለየት ባለ አፈጣጠሩ ምክንያት በሰፈሩ የተጠላ፣የተገፋና እንደዝንጆሮና ጉሬላ የሚቆጠር የ23  አመት ልጅ ነው፡፡ ዛ...
18/12/2022

zanziman ellie ይባላል። በደቡብ ሩዋንዳ በምትገኝ አንዲት መንደር ለየት ባለ አፈጣጠሩ ምክንያት በሰፈሩ የተጠላ፣የተገፋና እንደዝንጆሮና ጉሬላ የሚቆጠር የ23 አመት ልጅ ነው፡፡

ዛንዚማን ከቤቱ የወጣ እንደሆን መንደርተኛው ሁሉ “ዝንጀሮ! ዝንጀሮ! ጉሬላ! ጉሬላ!... “እያሉ ይጮሁበታል። ዛንዚማን ድምፅ የሚረብሽው አይነት ልጅ ስለነበር ጩኸቱን ሽሽት መንደሯን ለቆ ወደ ጫካ ይሮጣል። መከረኛ እናቱ ልታስቆመው እያለቀሰች ትከተለዋለች፡ ዛንዚማን ሲሮጥ ፈጣን በመሆኑ ለእናቱ እሱን ማስቆም በጣም ከባድ ነበር። እናቱ ልጇን ለማስቆም በሳምንት እስከ 200 ኪ.ሜ የሮጠችበት ግዜያት ነበሩ ።በዚህ ሁኔታ መቀጠል ቢከብዳት ከገመድ በተሰራ መጥለፊያ ተጠቅማ መሮጥ ሲጀምር ጠልፋ ትይዘዋለች፡፡

እናቱ አምስት ልጆችን ወልዳ የሞቱባት ሲሆን ዛንዚማን ለፈጣሪ ተስላ የተሰጣት ልጅ ነው። ምንም እንኳን ዛንዚማን በመንደሩ እንደ ዝንጀሮና ጉሬላ የሚታይ ልጅ ቢሆንም ለእናቱ የፀሎቷ ምላሽ፣ በረከቷና ብቸኛ የስለት ልጇ ነው። ስለዚህ ተከትላው ብትሮጥ፣ ስለእሱ ብትዘለፍ፣ ስለእሱ ብትሰደብ ታክቷትና ሰልችቷት አያውቅም።

ከዕለታት አንድ ቀን የዛንዚማንን ህይወት የቀየረ፣ የእናቱን እንባ ያበሰ ነገር ተፈጠረ። afrimax english የተባለ ማህበራው ድረገፅ በልጁ ታሪክ በመሳብ ታሪኩ ላይ የሚያጠነጥን ዘጋቢ ፊልም ለአለም እንካቹ አለ።

የዛንዚማን እናት አምስት ልጆችን ወልዳ የሞቱባት ቢሆንም ከባለቤቷ ጋር በርከክ ብለው ነብስ ያለው ልጅ እንዲሰጣቸው ፈጣሪን ለምነው ከፈጣሪ የተሰጣቸው ውድ ልጇ መሆኑን፤ አባቱ ልጁ በተወለደ በሁለተኛ አመቱ በመሞቱ ዛንዚማንን የማሳደጉ ሀላፊነት በእናቱ ጫንቃ ላይ የተጣለ መሆኑን በዘጋቢ ፊልሙ ተናግራለች።

ይህ ዘጋቢ ፊልም ከተለቀቀ በኋላ ዛንዚማን በብዙዋች ዘንድ መነጋገሪያ ሆነ። አለም አቀፍ የዜና አውታሮች ሁሉ የፊት ለፊት ገፅ ርዕስ አደረጉት። በታዳጊው ታሪክና በእናቱ ፅናት የብዙዎቹ ልብ ተነካ። እንዴት እንርዳቸው? በምን እናግዛቸው? የሚሉ የእርዳታ እጃቸውን የሚዘረጉ በዙ…የዘጋቢ ፊልሙን መለቀቅ ተከትሎ የGofundme አካውንት በስማቸው ተከፈተ።

የዛንዚማን እናት “የዚህ አይነት ፍቅር ከአለም ላይ አለ?” ብላ እስክትጠይቅ ድረስ ብዙ የእርዳታ እጆች ተዘረጉላት። በህልም አለም ያለች እስኪመስል በአካውንታቸው ሚሊዮን ዶላሮች ተለገሰ።

እናት፤ የፅናትዋን ዋጋ፡ የምስጋናዋን ክፍያ ተቀበለች።

ታሪክ ተቀይሮ ልጇን ዝንጀሮ ዝንጀሮ… እያሉ ያሳድዱት የነበሩ ሳይቀሩ አብረውት ፎቶ ለመነሳት ይማፀኑት ጀመር።

ወዳጄ፤ በፈጣሪ ተስፋ አትቁረጥ፤ ምክንያቱም ቀና ሊያደርግህ ቀን አለውና፡፡

ሰዎች ከሚሉህ በላይም ፈጣሪ ሲፈጥርህም ምክንያት አለውና የሌለህን ትተህ ያለህን ዋጋ ስጥ!

🔑የማረጋገጫ አለመኖር ያለመኖር ማረጋገጫ አይደለም! ⚜የምንፈልገውና የምንመኘው ነገር ዛሬ እውን አልሆነም ማለት ነገ እውን አይሆንም ማለት አይደለም። የጨለማው መድመቅ የመንጋቱን እውነታ አያ...
10/12/2022

🔑የማረጋገጫ አለመኖር ያለመኖር ማረጋገጫ አይደለም!

⚜የምንፈልገውና የምንመኘው ነገር ዛሬ እውን አልሆነም ማለት ነገ እውን አይሆንም ማለት አይደለም። የጨለማው መድመቅ የመንጋቱን እውነታ አያደበዝዘውም።

⚜ የምኞቶቻችን መዘግየት የመቅረታቸው ምልክት አይደለም። ሰው በሙሉ ልቡ ያሰበውንና በእውነት የሚገባውን ያገኝ ዘንድ ግድ ይላል። ሩሚ በአንድ ግጥሙ እንዲህ ብሎ ነበር

🔑“Longing is the Core of mystery. Longing itself brings the cure.
The only rule is, suffer the pain. Your desires must be disciplined and what you want to happen in time, sacrificed.”

🔱ሰው የሚፈልገውን ማግኘቱ ሳይሆን በስተመጨረሻ ዋጋ የሚኖረው፤ የሚፈልገውን ነገር ለማገኘት የሚገነባው ማንነቱ ነው። ደረስንበት ስንል የሚርቀን ነገር፤ በመንገዳችን ልንማረውና ልናውቀው የሚገባን ነገር ስላለ ነው። ጥበቃ ትልቅ መምህር ነው። ለተኛ ሰው የሌሊቱ መጨለም አያሰጋውም ሳያውቀው ይነጋልና። ነቅቶ ለሚጠብቅ ሰው ግን ሌሊቱ ያስፈራል፤ የሚነጋና ጎህ የሚቀድ አይመስልም። ሌሊቱ ሲነጋና ብርሃን ሲፈነጥቅ፤ ተኝቶ ካደረው ይልቅ ነቅቶ የጠበቀው የበለጠ አማኝ ይሆናል።

⚜ ነገሮች አልጨበት ካሉህ/ሽ፤ መጠበቁ ካደከመህ/ሽ ነቅተህ/ሽ የሌሊቱን መንጋት እየጠበቅህ/ሽ ነውና በፍጹም ተስፋ እንዳትቆርጥ/ጪ.

🔑ስለመንጋቱ ማረጋገጫ የለም ማለት ላለመንጋቱ ማረጋገጫ ነው ማለት አይደለም። መጠበቅ ከባድ ነው፤ የሚጠብቅ ሰው ሁሌም ማረጋገጫ ይፈልጋል፤ ሆኖም ግን ብዙ ነገሮች ለመሳካታቸው ማረጋገጫ አስቀድመው አይሰጡም። ስለዚህ በእምነት መጠበቁን እንለማመድ፤ ብዙ የጠበቀ ብዙ ይማራልና! ምኞት ለጊዜ እጅ ሲሰጥ፤ ነፍስ በትዕግስት ስትታሽ ተዓምር ይፈጠራል!!!

 !....ሰዎች.. ምን ይሉኛል የሚል ይሉኝታ ማቆም አለብህ፤  መቼም በዚህ ምድር ላይ ራስን እንደመሆን የሚያስደስት ነገር የለም። እናም   ሰዎች ምን ይሉኝ ይሆን? ሰዎች ስለኔ ምን ያስባሉ...
10/12/2022

!....ሰዎች.. ምን ይሉኛል የሚል ይሉኝታ ማቆም አለብህ፤ መቼም በዚህ ምድር ላይ ራስን እንደመሆን የሚያስደስት ነገር የለም። እናም ሰዎች ምን ይሉኝ ይሆን? ሰዎች ስለኔ ምን ያስባሉ? የሚለውን ማቆም ያለብህ አሁን ነው።

የእርስዎን መኪና የሚነዳው ማን ነው? ቤተሰብ ነው? ጓደኛ ነው? በዙሪያህ ያለ ሰው ነው? ወዳጄ ልቤ፣ መኪና በሁለት ሰው አይነዳም። መኪና ደግሞ ህይወትህ ነው። እንደ መኪና ሁሉ ህይወት በተለያዩ ሰዎች አይመራም፤ በሌሎች አስተሳሰብ የምትመራ ከሆነ ግን ወደ ገደል ነው የምትገባው!

ስለዚህ በአንተ ህይወት ማንም ማዘዝ የለበትም።
በገንዘብህ፣ በጉልበትህ፣ በአእምሮህ ማንም ሥልጣን ሊኖረው አይገባም። አንተና ፈጣሪ ካላዘዛችሁበት ሰዎች እንደ ጥላ ናቸው። አጥተህ ፀሐይ ስትጠልቅብህ ይበተናሉ፤ ኖሮህ ስትደመቅ ደግሞ ይከተሉሃል፤ ያከብሩሃል!

ስለዚህ በራስህ ላይ ሥልጣን ይኑርህ፤ እራስህን ሁን!

ሰዎች የሚወዱህ ጥንካሬህን መዝነው ነው። ምን ይሉሃል መሰለህ.. "እሱ'ኮ የማነበትን ነው የሚያደርገው" ይሉሃል፤ "ምን አይነት ጎበዝና ደፋር ነው" እያሉ ያከብሩሃል። በጥንካሬህና ራስህን ስትሆን ትከበራለህ፤ ሰዎች ባይወዱህ እንኳን በልባቸው እንዳተ መሆን ይፈልጋሉ።

ስለዚህ ለራስህ ቅድሚያ ስጥ። አግኝተህ ብታጣ፣ ታመህ ብትተኛ፣ ነግደህ ብትከስር፣ ሰዎች "አይዞህ" ሊሉህ ይችሉ ይሆናል ህመምህን ግን ማንም አብሮ ሊታመምልህ አይችልም፤ በገባህበት ገደል ማንም መግባት አይፈልግም።
..አንድ ሰው ወደ ከርሰ መቃብር ሲገባ አብሮ የተቀበረ የለም። እንዲህ ያለ ታሪክ አልሰማንም። የምናውቀው እስከ መቃብር ቦታ ሸኝተው "ወይኔ፥ ወይኔ" ብለው አልቅሰው ቀብረው ሲመለሱ ነው።

ስለዚህ በዚች ዓለም ማንም አብሮህ ስለማይቀበር
ቅድሚያ ለራስህ ቦታ ስጥ፤ የምታደርገውን ነገር እምንበት። አንተ ካላመንክበት፤ ዓላማህን ካላወቅህው ግን ሰዎች እንደ እንዝርት ወደፈለጉበት ያሽከረክሩሃል!

እናም ወዳጄ ልቤ፣ ለራስህ የምትሰጠው ቦታ መቀየር ያለብህ አሁን ነው። በራስህ ላይ ራስህን ሹም!

መልካም ቀን ይሁንላችሁ 💚💛

የተሻለ ሕይወት ለመኖር እና ሕልምህን ለማሳካት፣ ማንም አንዳች ነገር እስኪያደርግልህ መጠበቅ የለብህም። ሕልሙ ያንተ ነው፤ የታየህም ለአንተ ነው። ስለዚህ መከፈል ያለበትን ዋጋ መክፈል ያለብ...
10/12/2022

የተሻለ ሕይወት ለመኖር እና ሕልምህን ለማሳካት፣ ማንም አንዳች ነገር እስኪያደርግልህ መጠበቅ የለብህም። ሕልሙ ያንተ ነው፤ የታየህም ለአንተ ነው። ስለዚህ መከፈል ያለበትን ዋጋ መክፈል ያለብህ አንተ ራስህ ነህ።

አንተ ለሕልምህ ምንም ዐይነት ዋጋ ሳትከፍል፣ ሌሎች ሰዎች ለአንተ ሕልም ዋጋ እንዲከፍሉ መጠበቅ የለብህም። አንተ ለሕልምህ የመጨረሻውን ዋጋ እና አስፈላጊውን መሥዋዕትነት ሁሉ ስትከፍል፣ ሌሎች ሰዎች ሊረዱህ ይችላሉ።

ራስህን ስትቀይር፣ ሌሎች ሰዎችም ሊቀየሩ ይችላሉ። ራስህን ሕልሙን ማሳካት ወደሚችል ሰውነት ስትቀይር፣ በአካባቢህ ያሉ ሰዎችም ሕልምህን እንድታሳካ ሊረዱህ ይችላሉ። ራስህን ስትቀይር፣ ሁሉም ነገር መቀየር ይጀምራል።

ሕይወትህ፣ ቤተሰብህ፣ ሥራህ፣ ገቢህ፣ ጤንነትህ እንዲሁም የምትፈልገው ነገር ሁሉ እንዲቀየር፣ በመጀመሪያ አንተ መቀየር አለብህ።

መሸነፍ ውስጥ ማሸነፍ አለ፣መውደቅ ውስጥ መነሳት አለ፣በመታመም ውስጥ ጤንነት አለ፣ዋናው መውደቅህ ወይም መሸነፍህ ሰይሆን ወድቆ መነሳትህ ነው።
03/12/2022

መሸነፍ ውስጥ ማሸነፍ አለ፣
መውደቅ ውስጥ መነሳት አለ፣
በመታመም ውስጥ ጤንነት አለ፣
ዋናው መውደቅህ ወይም መሸነፍህ ሰይሆን ወድቆ መነሳትህ ነው።

አራቱ ለስኬት በጣም አስፋላጊ የሆኑ ነገሮች...1ኛ አመለካካት፡- ሁሉም ነገር በትክክለኛ አመለካከት ይጀመራል፡፡ ትክክለኛ አመለካካት ለብቻው በቂ ባይሆንም የመጀመሪያው ደረጃ ነው… ምክንያቱ...
03/12/2022

አራቱ ለስኬት በጣም አስፋላጊ የሆኑ ነገሮች...

1ኛ አመለካካት፡- ሁሉም ነገር በትክክለኛ አመለካከት ይጀመራል፡፡ ትክክለኛ አመለካካት ለብቻው በቂ ባይሆንም የመጀመሪያው ደረጃ ነው… ምክንያቱም በጎ የሆነ ትክክለኛ አመለካከት ካለ ውስጣችን ትክክለኛ መነቃቃትና በመያዝ ወደ ስኬት መንገድ ያስገባችዋል፡፡

2ኛ እውቀት፡- ወዴት እንደምትሄዱና በየት በኩል እንደምትሄዱ ማወቁ ነው፡፡ ይሄ ማለት ዕቅድን በግልፅ መያዝ ነው፡፡ ስለምታደርጉት ነገር በቂ የሆነ እውቀት መያዝ… ግቦችን ጥርት ባለ መልኩ ደርድሮ በቅደም ተከተል ማስቀመጥ… ፕላን 1 ወይም 2(ኤ እና ቢ) ብሎ መለየት፡፡ አሳማኝ የሆነ ዕቅድ ማውጣት፡፡

3ኛ ችሎታ፡- እነዚህ ዕቅዶች በተግባር መቀየር የሚችል በቂ ችሎታ መያዝ… እንዴት እንድምታመርቱ… ምን ዓይነት ነገር እንደምታመርቱ… እንዴት የሚመረተው እንደሚሸጥ… የመሸጥ ችሎታ…

4ኛ ተግባራዊ የውድድር መንፈስ፡- ሁሉም ነገር ያለውድድር አይሆንም… ሁልጊዜም የተግባር ሰው የሚያስብል ይሄ ውድድርን ለዕድገትና ለብልፅግና ሲጠቀሙ ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች ችሎታ ኖራቸው የተግባር ልምድ ኖራቸው ይወድቃሉ… ይሸነፋሉ እና በዚህ አጋጣሚ ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡
ሶስቱ አመለካከት… እውቀት… ችሎታ በማንበብ እና በቀላሉ ሊገኙ የሚችሉ ናቸው ግን ተግባራዊ የውድድር መንፈስ አይኖራቸውም፡፡

ብዙዎችን ከጨዋታ ውጪ የሚያደርገው ተግባራዊ የውድድር መንፈስ አለመጨበጥ ነው፡፡ ይሄን ስኬትን ለመጎናፀፍ ይሄን የውድድር መንፈስ ተግባራዊ ማድረግ አለብን፡፡
በጎ አመለካከት የያዙ ሰዎች አሉ… ግን ስኬታማ የቢዝነስ ሰዎች አይደሉም
ከፍተኛ እውቀት ያላቸው ሰዎች አሉ… ግን የራሳቸው ቢዝነስ የላቸው
ከፍተኛ ችሎታ ያላቸው … ባለፀጋ መሆን አልቻሉም፡፡

ተግባረዊ የውድድር መንፈስ ሞክረነው አሸናፊ ያደርገናል… ይሄ ደግሞ በተግባር የሚሰራ እንጂ በወሬ አይደለም፡፡
አንዳንድ ሰዎች እውቀቱን አመለካከትን ችሎትን ዘለው ወደ ወደ ውድድሩ ይገባሉ፡፡ ይሄን ይሸነፋሉ፡፡ አወዳደቃቸው አስቀያሚ ይሆናል፡፡

28/07/2022

Address

Addis Abeba
Addis Ababa

Telephone

+251948768781

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abebaw Ayana-Yehagerie Lij posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share