Ethiopia Daily

Ethiopia Daily This is helpful

https://aaaonline.info/syAAXE arif ena ya online birr maseraia app bezehe link gebu ena mokera...ya ewant Ethiopia wust ...
23/11/2024

https://aaaonline.info/syAAXE arif ena ya online birr maseraia app bezehe link gebu ena mokera...ya ewant Ethiopia wust yekafelal mokerut

ጥበብ እንቁ ልጇን ተነጠቀች። ትውልዱ እዚሁ አዲስ አበባ ተክለ ሀይማኖት ሰፈር የነበረው ታሪኩ ብርሀኑ (ባባ) ብዙዎች የሚወዱትና የሚያደንቁት የጥበብ ልጅ ነበረ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራ...
11/12/2022

ጥበብ እንቁ ልጇን ተነጠቀች።

ትውልዱ እዚሁ አዲስ አበባ ተክለ ሀይማኖት ሰፈር የነበረው ታሪኩ ብርሀኑ (ባባ) ብዙዎች የሚወዱትና የሚያደንቁት የጥበብ ልጅ ነበረ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይም በቅንነትና በታዛዥነት ተሳትፏል።

ከሰራቸው ፊልሞች መካከል፦
👉3+1
👉300 ሺ
👉አስነኪኝ
👉ባላ ገሩ
👉የፍቅር ABCD
👉ብላቴና
👉ቦሌ ማነቂያ
👉እንደ ባል እና ሚስት
👉ኢንጂነሮቹ
👉እርቅ ይሁን
👉ኢዮሪካ
👉ጉዳዬ
👉ሀገርሽ ሀገሬ
👉ሕይወቴ
👉ህይወት እና ሳቅ
✔ከባድ ሚዛን
✔ፍቅር እና ፌስቡክ
✔ከቃል በላይ
✔ላውንድሪ ቦይ
✔ኮከባችን
✔ማርትሬዛ
✔ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2
✔ሞኙ የአራዳ ልጅ 4
✔ትዳርን ፍለጋ
✔አንድ ሁለት
✔ብር ርርር
✔ወደው አይሰርቁ
✔ወፌ ቆመች
✔ወንድሜ ያዕቆብ
✔እንደ ቀልድ
✔ወቶ አደር
✔አባት ሀገር
✔የሞግዚቷ ልጆች
✔ይዋጣልን
✔ዋሻው
✔ወሬ ነጋሪ
✔ወጣት በ97

ሞትህን መስማት ያማል፡ ነፍስህን ይማር።
ልቅሶ መድረስ የምትፈልጉ የታሬ ቤት ተክለሀይማኖት ፔፕሲ አጠገብ ነው

🇳🇱 Netherlands vs. Argentina 🇦🇷🇭🇷 Croatia vs. Brazil 🇧🇷🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 England vs. France 🇫🇷🇲🇦 Morocco vs. Portugal 🇵🇹The World ...
08/12/2022

🇳🇱 Netherlands vs. Argentina 🇦🇷
🇭🇷 Croatia vs. Brazil 🇧🇷
🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 England vs. France 🇫🇷
🇲🇦 Morocco vs. Portugal 🇵🇹

The World Cup quarter-final ties are confirmed. 🤩

08/12/2022

ፍርድ ቤቱ አቶ ስብሐት ነጋ ወደ ውጭ ሀገር እንዳይወጡ መከልከሉ ተገቢ አደለም ሲል ውሳኔ ሰጠ።

የችሎቱ ዳኞች የሰጡት ውሳኔ አቶ ስብሐት ወደ ውጪ ሀገር እንዳይወጡ መከልከሉ ተገቢ አደለም የሚል ውሳኔ እንጂ እንዲወጡ ይፈቀድ የሚል ውሳኔ አለመሆኑንም አስረግጠው ገልጸዋል።

አቶ ስብሐት ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር ልሄድ ስል በፌደራል ፖሊስ ከኤርፖርት ታግጃለው ሲሉ ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ የፍታብሔር ምድብ የመሰረታዊ መብቶች ጉዳዮች ችሎት አቅርበው ነው።

አቶ ስብሐት ነጋ በከፍተኛ ህመም ላይ መሆናቸውን እና ህክምና አድርገው ለመመለስ ወደውጭ ሀገር ሊሄዱ ሲሉ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከኤርፖርት እንዲመለሱ መደረጋቸውን ለችሎቱ በቀረበው ክስ ላይ ተጠቅሷል።

ኢትዮጲያ በአለም አቀፍ ደረጃ የፈረመቻቸውን ህጎችን እና በህገመንግስቱ የተቀመጡ የዜጎችን የመቀሳቀስ መብት በሚጣረዝ መልኩ ፍርድ ቤት ባላዘዘበት ሁኔታ ፖሊስ ከስልጣኑ ውጪ የጉዞ እግድ መጣሉ እና አቶ ስብሐት ነጋ በከፍተኛ ህመም ላይ ሆነው ውጭ ወተው ታክመው ሊመለሱ ሲሄዱ ከኤርፖርት እንዲመለሱ መደረጉ የህግ አግባብነት የለውም የህግ ሲሉ ጠበቃቸው ታደለ ገ/መድህን ለችሎቱ አቅርበው ነበር።

የአቶ ስብሐት ነጋ ክስ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ዙሪያ ፖሊስ መልስ ባለማቅረቡ ምክንያት መልስ የመስጠት መብቱ እንዲታለፍ በህዳር 23 ቀን ብይን መስጠቱ ይታወሳል።

በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ በሰጠው ተለዋጭ ቀጠሮ መሰረት ፍርድ ቤቱ አቶ ስብሐት ነጋ ወደ ውጭ ሀገር እንዳይወጡ መከልከሉ ተገቢ አደለም ሲል ውሳኔ ተሰጥቷል።

የችሎቱ ዳኞች የሰጡት ውሳኔ አቶ ስብሐት ወደ ውጪ እንዳይወጡ መከልከሉ ተገቢ አደለም የሚል ውሳኔ እንጂ እንዲወጡ ይፈቀድ የሚል አለመሆኑን አስረግጠው ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል ከነበረው ጦርነት ጋር ተያይዞ በፌደራል መንግሥቱ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ የነበሩት የህወሓት አመራሮች ማለትም የድርጅቱ መስራች የነበሩት አቶ ስብሐት ነጋ እና እህታቸው ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ፣ አቶ ዓባይ ወልዱ፣ አቶ አባዲ ዘሙ፣ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር እና አቶ ኪሮስ ሐጎስ በምህረት እንዲፈቱ መወሰኑን ተከትሎ ከስር መፈታታቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ሀዋሳ ከተማ ገቡጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ፣ ክብርት ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸዉ፣ ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ክቡር አቶ አደ...
07/12/2022

ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ሀዋሳ ከተማ ገቡ

ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ፣ ክብርት ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸዉ፣ ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ክቡር አቶ አደም ፋራህ እና ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የቱሪዝምና የኢንቬስት መንት መዲና መዲና ወደሆነችው ሀዋሳ ከተማ 17ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ለማክበር ዛሬ ገብተዋል።

07/12/2022

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርስቲ ረብሻ ለመቀስቀስ የሞከሩ ተማሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።ቀሪው በአስለቃሽ ጭስ ተበትኗል።አሁን ላይ ረብሻው መቆሙ ተሰምቷል።

የሳውዲአረቢያ ተጫዋቾች ውዱን መኪና ለእያንዳንዳቸው  በትናንትናዉ እለት ሳይጠበቅ አርጀንቲናን ሁለት ለአንድ ለረቱት የሳዉዲአረቢያ ብሔራዊ ቡድን ለእያንዳንዳቸዉ ከአለማችን ዉድ መኪናዎች በቀ...
07/12/2022

የሳውዲአረቢያ ተጫዋቾች ውዱን መኪና ለእያንዳንዳቸው

በትናንትናዉ እለት ሳይጠበቅ አርጀንቲናን ሁለት ለአንድ ለረቱት የሳዉዲአረቢያ ብሔራዊ ቡድን ለእያንዳንዳቸዉ ከአለማችን ዉድ መኪናዎች በቀዳሚነት የሚጠቀሰዉን Rolls-Royce መኪና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

ከዛ በተጨማሪ ደግሞ የትናንትናዉን እለት እንደታሪካዊ ቀን በመዘከር በየአመቱ የእረፍት ቀን እንደሚያደርጉት መናገራቸዉም ይታወሳል።

ቄስ በሊና ሳርካ አረፉ።የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል " ለቤተክርስቲያንና ለሀገራችን ኢትዮጵያ በረከት የነበሩት ቄስ በሊና ሳርካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ። ...
07/12/2022

ቄስ በሊና ሳርካ አረፉ።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል " ለቤተክርስቲያንና ለሀገራችን ኢትዮጵያ በረከት የነበሩት ቄስ በሊና ሳርካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ። " ያለ ሲሆን ለቤተሰቦቻቸው፤ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም በአጠቃላይ ለወንጌል አማኙ ማህበረሰብ መፅናናት ተመኝቷል።

ቄስ በሊና ሳርካ ከ60 ዓመታት በላይ በወንጌል አማኞች ዘንድ በማገልገል " የወንጌል አርበኛ " የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል።

ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተገነግሯል።

07/12/2022



መቐለን ጨምሮ የተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች ከ18 ወራት በኋላ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የኃይል ቋት ማግኘት እንደጀመሩ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በመቐለ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሰሜን ሪጅን ሠራተኞችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ሰራተኞቹ ከትናንት ማክሰኞ ምሽት ጀምሮ መቐለን ጨምሮ ፦
- መኾኒ ፣
- ውቅሮ፣
- ዓዲግራት፣
- ዓብይዓዲ እና ሌሎች በአካባቢው ያሉ ከተሞች ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የኃይል ቋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት ጀምረዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ክልሉ ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የኃይል ቋት ያገኝ የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት በጦርነቱ ምክንያት ከሰኔ ወር 2013 ዓ/ም ወዲህ ተቋርጦ ቆይቶ ነበር።

ነገር ግን በዚህ መሃል በትግራይ ክልል ከሚገኝ የኃይል ምንጭ፣ በክልሉ አስተዳደር አስተባባሪነት በውስን መጠን እና መቆራረጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ለሕዝቡ ይቀርብ እንደነበር ተጠቁሟል።

ከ18 ወራት በኋላ የኤሌክትሪክ ኃይል የተመለሰው ትናንት ማክሰኞ አመሻሽ ከ11 ሰዓት ጀምሮ ሲሆን የኤልክትሪክ አገልግሎት በመቐለ እና በተለያዩ የክልሉ ከተሞች መቅረብ መጀመሩ ለነበረው የኃይል ፍላጎት መልስ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል ሲል ዶቼ ቨለ ዘግቧል። Ethiopian Broadcasting Corporation

Address

Adis Ababa
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia Daily posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Nearby media companies