ወንድ-Male

ወንድ-Male “ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 2

13/01/2023
05/11/2022
01/11/2022

ወንድ ልጅ ከተወለደ ዓመታት የተቆጠሩባት በደቡብ ፖላንድ የምትገኝ አንዲት ትንሽ ከተማ ከንቲባ፤ ወንድ ልጅ ለሚወልዱ ጥንዶች ሽልማት እንደሚሰጡ አሳወቁ።

በከተማዋ ወንድ ልጅ ከተወለደ አስር ዓመት ሊሆን የተቃረበ ሲሆን ይህም የከተማዋን አስተዳዳሪ ሳያሳስባቸው አልቀረም።

• ለዓመታት የተጠፋፉት የወላይታ ሶዶዋ እናትና የኖርዝ ኬሮላይናዋ ልጃቸው

እምብዛም የዜና ርዕስ ሆና የማታውቀው ሚየሲች ኦድርዛንሰኪ የተባለችው ከተማ የወንድ ልጆች መወለድን ለማበረታታት በወሰደችው እርምጃ መነጋገሪያ ሆናለች።

አንድ መቶ ያህል ቤቶች ብቻ ያሏት ይህች ከተማ ሰፋፊ የእርሻ መሬት የሚገኝባት ሲሆን፤ ህጻናትን ለማሳደግ አመቺ ቦታ ናት ተብሎ ይታሰባል። ነገር ግን ባለፉት ዓመታት የአካባቢውን ነዋሪ ያሳሰበው ነገር የተወለዱት ህጻናት ሴቶች ብቻ መሆናቸው ነው።

በከተማዋ ያለው የወሊድ መጠን እጅግ በጣም አነስተኛ የሚባል ሲሆን፤ የመጨረሻው ወንድ ልጅ ከተወለደ በኋላ ባሉት ዓመታት ውስጥ 12 ህጻናት የተወለዱ ሲሆን ሁሉም ሴቶች ናቸው ተብሏል።

• የሕንድ 21 ሚሊዮን 'ያለተፈለጉ' ሴት ልጆች

• ወንዶች በአደባባይ ላይ ልጆች ቢያዝሉስ?

የወንዶች ቁጥር መቀነስ ጉዳይ በስፋት ትኩረት ያገኘው በከተማዋ የሚገኙ ሴቶች አንድ የበጎ ፈቃድ የእሳት አደጋ ሠራተኛን አሰልጣኛቸው እንዲሆን ከጠየቁት በኋላ ነው። ሴቶች ብቻ የሆኑበት የከተማው ቡድን አካባቢያዊ ውድድሮችን ካሸነፉ በኋላ ጋዜጠኞችና ተመራማሪዎች ጥያቄ በማንሳታቸው ጉዳዩ ትኩረት ማግኘቱም ተጠቅሷል።

የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ከንቲባ ራጅሙንድ ፍሪችኮ እንደተናገሩት፤ በጉጉት የሚጠበቀው ወንድ ልጅ ድንቅ ሽልማት የሚበረከትለት ሲሆን አንድ ዛፍ በስሙ ይሰየምለታል።

26/08/2022
08/07/2022

ሰበር ዜና፡ የጃፓኑ የቀድሞ ጠ/ሚ ሺንዞ አቤ በናራ በተተኮሰ ጥይት መሞታቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ቦሪስ ጆንሰን የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ በርካታ ቅሌቶች በመንግስት ሚኒስትሮች በጅምላ እንዲወጡ አድርጓል። 40ዎቹ ሚኒስቴሮች ለእንግሊዝ የማይ...
07/07/2022

ቦሪስ ጆንሰን የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ በርካታ ቅሌቶች በመንግስት ሚኒስትሮች በጅምላ እንዲወጡ አድርጓል። 40ዎቹ ሚኒስቴሮች ለእንግሊዝ የማይመጥን መሪ ነው ከሱ ጋር አንሰራም ብለው የስልጣን መልቀቂያ ካስገቡ በኋላ ነው ቦሪስ ጀንሰን ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁት።

"ሞት ካልቀደመኝ እና ፈጣሪ ከረዳኝ እስከ ዩኒቨርሲቲ በመቀጠል በማገኘዉ ዕዉቀት ህዝቤን አገለግላለሁ!"(የ53 ዓመቱ ዕድሜ ባለፀጋ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ተፈታኝ)
05/07/2022

"ሞት ካልቀደመኝ እና ፈጣሪ ከረዳኝ እስከ ዩኒቨርሲቲ በመቀጠል በማገኘዉ ዕዉቀት ህዝቤን አገለግላለሁ!"
(የ53 ዓመቱ ዕድሜ ባለፀጋ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ተፈታኝ)

(Africa)የአፍሪካ የጤና ባለስልጣናት በአህጉሪቱ ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ እየተስፋፋ መምጣቱን በመጠቆም እንደ  #ድንገተኛ ሁናቴ እያስተናገዱት መሆኑን ገልፀዋል።በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት...
04/07/2022

(Africa)

የአፍሪካ የጤና ባለስልጣናት በአህጉሪቱ ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ እየተስፋፋ መምጣቱን በመጠቆም እንደ #ድንገተኛ ሁናቴ እያስተናገዱት መሆኑን ገልፀዋል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የሚታዩትን የፍትሃዊነት ችግሮች ለማስወገድ የበለፀጉ ሀገራት ውስን የክትባት አቅርቦቶችን እንዲያካፍሉም ጠይቀዋል።

እስካሁን ባለው በአፍሪካ 1,800 የሚጠጉ የዝንጀሮ ፈንጣጣ የተጠረጠሩ ኬዞች ያሉ ሲሆን ከ70 በላይ ሰዎች እንደሞቱ ተነግሯል ፤ ነገር ግን በላብራቶሪ ምርመራ የተረጋገጠው 109 ኬዝ ብቻ ነው ተብሏል።

ለበሽታው ምርመራ የሚያስፈልጉ የላብራቶሪ ምርመራ ገብአቶች እጦት እና ደካማ የሆነ የክትትል ስርዓት ብዙ ኬዞች ሳይታወቁ እንዲቀሩ እያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።

“ግዛቴን አሳልፌ ሰጥቻለሁ ” ዩክሬንየዩክሬን ጦር ስልታዊቷን ሊሲቻንስክ ከተማን የፑቲን ኃይሎች ይዘዋታል ሲል አመነ፡፡ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ የሞስኮ ጦር ከተማዋን አልተቆጣጠረም ፤ምኞ...
04/07/2022

“ግዛቴን አሳልፌ ሰጥቻለሁ ” ዩክሬን
የዩክሬን ጦር ስልታዊቷን ሊሲቻንስክ ከተማን የፑቲን ኃይሎች ይዘዋታል ሲል አመነ፡፡
ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ የሞስኮ ጦር ከተማዋን አልተቆጣጠረም ፤ምኞቱን ነው የሚነዛው ካሉ ከሰዓታት በኋላ ነው የኪዬቭ ጦር የከተማዋን ለቀናል ማረጋገጫ ዜና የተሰማው፡፡
ደም አፋሳሽ ውጊያ በተደረገባት ከተማ ያለው የጦር ኃይል እስከመበተን ደርሷል ቢባልም በዕርግጥ በምዕራባውያን አይዟችሁ የሚባሉት ኪዬቮች አፈግፍገናል ፤ስልታዊ ቦታ የመለወጥ ዕርምጃ ነው በሚል አስተባብለዋል ፡፡
የክሪሚሊን ጦር የተዋጊ ጀቶች፣የሚሳዔል፣የወታደር አቅም እና የጦር መሳሪያ ብልጫ በማግኘቱ ለድል በቅቷል ፡፡
የኪዬቭ ጦርም ይሄኑ አረጋግጧል፡፡
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ የአገራቸው ጦር ወደ ሊሲቻንስክ ከተማ ዳግም ተመልሶ ድል ይቀዳጃል ሲሉ ቃል ገብተዋል ፡፡
በዕርግጥ ፕሬዚዳንቱ ማሪዮፖልን ፣ሴቬሮዶኔስክን እና ሌሎች ወሳኝ ከተሞችን በቅርቡ በእጃችን እናስገባለን ቢሉም ተጨማሪ ግዛቶችን ሲለቁ እንጂ ዳግም ድል ሲቀናቸው አልተዩም በሚል ይወነጀላሉ፡፡
ጦርነቱ የሞስኮው ክሪሚሊን ከዋሽንግተኑ ነጩ ቤተ መንግስት፣ከሎንዶኑ ዳውኒንግስትሪት ቁ.10 ቢሮ እንዲሁም ከፓሪሱ ኤልዚ ቤተመንግት ጋር የከፈተው ተደርጎም ይወሰዳል፡፡

ባይ በረሃ ስንገባ የምናገኘዉ ቀለበታማ መንገድ!!
04/07/2022

ባይ በረሃ ስንገባ የምናገኘዉ ቀለበታማ መንገድ!!

"Education develops the intellect, and the intellect distinguishes man from other creatures"  Qedamawi Haile Selassie I ...
04/07/2022

"Education develops the intellect, and the intellect distinguishes man from other creatures" Qedamawi Haile Selassie I 🇪🇹"ትምህርት አእምሮን ያዳብራል፣ አእምሮ ደግሞ ሰውን ከሌሎች ፍጥረታት ይለያል"
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ 🇪🇹

አራት ሚስቶች ያሉትአንድ ሰው ነበር።አራተኛዋን ሚስቱንከሁሉም አስበልጦይወድዳት፥ ይንከባከባትምነበር።ሶስተኛዋን ሚስቱንምይወድዳት፥ ለጓደኞቹምያሳያት ነበር። ነገር ግን“እኔን ጥላኝ፡ ከሌላ ወን...
02/07/2022

አራት ሚስቶች ያሉት
አንድ ሰው ነበር።
አራተኛዋን ሚስቱን
ከሁሉም አስበልጦ
ይወድዳት፥ ይንከባከባትም
ነበር።
ሶስተኛዋን ሚስቱንም
ይወድዳት፥ ለጓደኞቹም
ያሳያት ነበር። ነገር ግን
“እኔን ጥላኝ፡ ከሌላ ወንድ
ጋር ትኮበልላለች” ብሎ
ሁሌም ይሰጋ ነበር።、
ሁለተኛዋን ሚስቱንም
ይወድዳት፡ ችግር
በገጠመውም ግዜ ሁሉ
ያዋያት ነበር፤ እሷም
ሰለቸኝ፡ ደከመኝ ሳትል
ዘወትር ትረዳው ነበር።
የመጀመሪያዋን ሚስቱን
ግን ጭራሽ አይወድዳትም
፤ እርሷ ግን በተቃራኒው
ከልብ ታፈቅረዋለች።
ከእለታት አንድ ቀን፡
ሰውዬአችን በጠና
ታመመ፤ በህይወት ብዙም
እንደማይቆይ ተረዳ።
“አራት ሚስቶች አሉኝ፤
ከሞትኩ በኋላ ብቸኝነት
እንዳያጠቃኝ አንዷን ይዤ
እሄዳለሁ።” ብሎም
ወሰነ።
በዚህም መሰረት
አራተኛውን ሚስቱን
አብራው እንድትሞትና
ከብቸኝነቱ
እንድታስጥለው ጠየቃት።
“በጭራሽ አይሆንም!”
ብቻ ብላ ሌላ ቃል
ሳትተነፍስ ጥላው ሄደች።
ሶስተኛ ሚስቱን ተመሳሳይ
ጥያቄ ሲጠይቃት
“እዚህ ህይወት
ተመችቶኛል፤ ከሞትክ
በኋላ ሌላ ባል አግብቼ
እኖራለሁ” ብላ
ተቃወመች።
ፊቱን ወደ ሁለተኛዋ
ሚስቱ ቢያዞር
“አዝናለሁ! አሁን ልረዳህ
አልችልም፤ ቢበዛ እስከ
መቃብርህ ብከተልህ
ነው።” ብላ አሳፈረችው።
ይህንን ተደጋጋሚ እንቢታ
ሲሰማ፡ ልቡ በሀዘን
ቀዘቀዘች።
ነገር ግን፡ ከጸጥታውና
ከሀዘኑ መሀል፡ አንድ
ድምጽ እንዲህ አለው፦
“እኔ አብሬህ እሄዳለሁ፤
የትም ብትሄድ
እከተልሀለሁ።”
ሰውየው ቀና ቢል፡ ታማኝ
ወዳጁን፡ የመጀመሪያ
ሚስቱን ተመለከተ።በቂ
ምግብ ያላገኘች ሰው
ትመስል በጣም ከስታናና
ገርጥታ ነበር።ድምጹ
በከባድ ሀዘን እየተሰባበረ
“በጤና እያለሁ፡ የበለጠ
ልንከባከብሽ ይገባኝ
ነበር!” አላት።
እንደ እውነቱ ከሆነ፡
ሁላችንም አራት
ሚስቶች/ባሎች አሉን።
1. አራተኛ ሚስት/ባል
ሰውነታችን ነው። ምንም
ያህል ብንንከባከበው፡
ስንሞት አይከተለንም።
2. ሶስተኛ ሚስት/ባል
ሀብትና ንብረታችን ነው።
ስንሞት ለሌሎች
ይተላለፋል።
3. ሁለተኛ ሚስት/ባል
ዘመድ ወዳጆቻችን
ናቸው። በህይወት እያለን
ምንም ያህል ቅርቦቻችን
ቢሆኑም፡ ከመቃብር
ባሻገር አይከተሉንም።
4. የመጀመሪያ ሚስት/
ባል ነፍሳችን ናት።
በምድር ላይ ቆይታችን
ሀብትን እና ዝናን
ስናሳድድ ችላ እንላታለን።
በሄድንበት ቦታ ሁሉ
አብራን የምትሄደው ግን
እርሷው ብቻ ናት።👌

02/07/2022

« ለካስ እንዲህ ይከብዳል።»
አልጋ ላይ ሞከረ ምንም አልተመቸው ፤
°
ሶፋ ላይ ሞከረ ምንም አልተመቸው ፤
°
መሬት ሁኚ አለኝ ምንም አልተመቸው ፤
°
ወጪ እንውጣ አለኝ ወጣሁ ተቻኩዬ ፤
°
ከአበቦች መሃል ዛፍን ደገፍ ብዬ ፤
°
ዳግም በጀርባዬ ሳር ላይ ተንጋልዬ ፤
°
አንዴ ተንበርክኮ አንድ ጊዜ ቆሞ ፤
°
ወደታች ወደላይ ወደጎንም ዘሞ ፤
°
እርሱም አላረካው ወደ ቤት መለሰኝ ፤
°
አኳኋኑን አላወቀው እኔንም ገረመኝ ፤
°
አልጋላይ ውጪ አለኝ እኔም ወጣሁለት ፤
°
ከፍ በይ ዝቅ በይ ሁሉንም ሆንኩለት ፤
°
መስኮት ስር በር ስር አንዴ ከግድግዳ ፤
°
ምግብ ቤት ሳሎን ቤት መኝታ ቤት ጓዳ ፤
°
አንዴ በመቀመጥ አንዴ በቁጭ ሲለኝ ፤
°
ዝም ብሎ አይደለም ተንቀሳቀሽ ሲለኝ ፤
°
እንዲያ ሲቅበዘበዝ አበደ መሰለኝ ፤
°
እቤት ውስጥ በመብራት ፤
°
ውጪ ደግሞ በፀሐይ ፤
°
ከግራ ወደ ቀኝ ፤
°
ወደታች አንዴ ወደ ላይ ፤
°
አኳኋኑ ሁሉ በሳቅ ያፈነዳል ፤
°
ፎቶግራፍ ማንሳት ለካ እንዲህ ይከብዳል።
አዳሜ ምን አስበሽ ነበር? 😂

ምርጫችሁ የሆነውን ቁጥር ኮሜንት ላይ አስቀምጡ🙏
02/07/2022

ምርጫችሁ የሆነውን ቁጥር ኮሜንት ላይ አስቀምጡ🙏

ሰበር ዜናየኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ VAR ለመጠቀም አንድ ከውጪ ካለ ድርጅት ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነ የሊጉ አክሲዮን ሰብሳቢ አቶ ክፍሌ ገለፁ።VAR በፕርሚየር ሊጋች...
30/06/2022

ሰበር ዜና
የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ VAR ለመጠቀም አንድ ከውጪ ካለ ድርጅት ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነ የሊጉ አክሲዮን ሰብሳቢ አቶ ክፍሌ ገለፁ።
VAR በፕርሚየር ሊጋችን እንዴት ይመለከቱታል? 🤔
ምንጭ ድሬመፅሄት ስፖርት

የእለቱ አጭር ታሪክ፡-የአህያ እና የነብር ታሪክአህያው ለነብር እንዲህ አለችው።"ሣሩ ሰማያዊ ነው"ነብሩም መለሰ፡-"አይ, ሣሩ አረንጓዴ ነው."ውይይቱ ጦፈ እና ሁለቱ ጉዳዩን ለግልግል ለማቅረ...
24/06/2022

የእለቱ አጭር ታሪክ፡-
የአህያ እና የነብር ታሪክ
አህያው ለነብር እንዲህ አለችው።
"ሣሩ ሰማያዊ ነው"
ነብሩም መለሰ፡-
"አይ, ሣሩ አረንጓዴ ነው."
ውይይቱ ጦፈ እና ሁለቱ ጉዳዩን ለግልግል ለማቅረብ ወሰኑ እና ይህን ለማድረግ ወደ ጫካው ንጉስ አንበሳ ቀረቡ።
አንበሳው በዙፋኑ ላይ ተቀምጦበት ወደነበረበት ጫካ ውስጥ ከመድረሱ በፊት አህያው እንዲህ ይጮህ ጀመር።
"ክቡርነትዎ እውነት ሣሩ ሰማያዊ ነው?"
አንበሳውም እንዲህ ሲል መለሰ።
"እውነት, ሣሩ ሰማያዊ ነው."
አህያው ወደ ፊት ሮጠ እና ቀጠለ።
"ነብር ከእኔ ጋር አልተስማማም እና እኔን ይቃረናል እና ያናድደኛል እባክዎን ይቅጡት."
ከዚያም ንጉሱ እንዲህ ብለዋል: -
"ነብር 5 አመት በጸጥታ ይቀጣል"
አህያው በደስታ ብድግ ብሎ መንገዱን ቀጠለ፤ እየረካና እየደጋገመ፡-
"ሣሩ ሰማያዊ ነው"...
ነብር ቅጣቱን ተቀበለ፣ነገር ግን አንበሳውን እንዲህ ሲል ጠየቀው።
"ግርማዊነትህ ለምን ቀጣኸኝ፤ ለመሆኑ ሣሩ ለምለም ነው?"
አንበሳውም እንዲህ ሲል መለሰ።
"በእርግጥ ሣሩ አረንጓዴ ነው"
ነብር እንዲህ ሲል ጠየቀ።
"ታዲያ ለምን ትቀጣኛለህ?"
አንበሳውም እንዲህ ሲል መለሰ።
"ይህ ሳሩ ሰማያዊ ወይም አረንጓዴ ነው ከሚለው ጥያቄ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም። ቅጣቱም እንዳንተ ያለ ደፋርና አስተዋይ ፍጡር ከአህያ ጋር ሲከራከር ጊዜ ማጥፋት ስለማይቻል እና በዚያ ላይ መጥቶ ያንን ጥያቄ ሊያስጨንቀኝ ስለማይችል ነው።
በጣም የከፋው የጊዜ ብክነት የእምነታቸው እና የይስሙላ ድል ብቻ እንጂ ለእውነትም ሆነ ለእውነታ ደንታ ከሌለው ቂል እና አክራሪ ጋር መጨቃጨቅ ነው። ምንም ትርጉም በሌላቸው ውይይቶች ላይ ጊዜ አታባክን... ለቀረቡላቸው ማስረጃዎች ሁሉ የመረዳት አቅም የሌላቸው ሰዎች እና ሌሎችም በኢጎ፣ በጥላቻና በቁጭት የታወሩ አሉ፤ እነሱም ብቸኛው ነገር እነሱ ባይሆኑም እንኳ ትክክል መሆን ይፈልጋሉ። አለማወቅ ሲጮህ ብልህነት ይዘጋል። የእርስዎ ሰላም እና መረጋጋት የበለጠ ዋጋ ያለው ነው።

አንድ የካምቦዲያ ዓሣ አጥማጅ በሜኮንግ ወንዝ ውስጥ 300 ኪሎ ግራም የሚይዝ ግዙፍ የንጹህ ውሃ ዓሣ መያዙን ሳይንቲስቶች በሰኔ ወር ገለጹ።
22/06/2022

አንድ የካምቦዲያ ዓሣ አጥማጅ በሜኮንግ ወንዝ ውስጥ 300 ኪሎ ግራም የሚይዝ ግዙፍ የንጹህ ውሃ ዓሣ መያዙን ሳይንቲስቶች በሰኔ ወር ገለጹ።

♦ ናዕት       #እያመመው ቁ.፪ዶፍ ....... ዶፍ ግርም ያለ ጊዜ ሆነ ሰዓቱበዳንኪራው ደምቆ በምቱ ለደቂቃም አይቆይ በስልቱቦግ እልም እያለ መብራቱ       ኡ .. ኡ ሬጌ ናዕት......
22/06/2022

♦ ናዕት
#እያመመው ቁ.፪
ዶፍ ....... ዶፍ
ግርም ያለ ጊዜ ሆነ ሰዓቱ
በዳንኪራው ደምቆ በምቱ
ለደቂቃም አይቆይ በስልቱ
ቦግ እልም እያለ መብራቱ
ኡ .. ኡ ሬጌ ናዕት... ሬጌ ናዕት
ብልጭልጭ ቢሆን ዳሱ ... ሬጌ ናዕት
ማን ሊታደም ከድግሱ ... >> >>
ብልጭልጭ ቢሆን ድንኳን ...>> >>
አይለወጥ ጎግ የእውነት መልኳን >> >>
ቢጋርድ ሐሳብ አርጎ ሜዳን ገደል
እም አእላፍ ስቃይ ጭንቀት ቢደረደር
የነፍስ ሕላዊ መሻት ዋዌ ሳይገባቸው
ስንቶች በዘር ተዘፍቀው ታዘብናቸው
ዘውግ ያወረው ድንበር ማላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል ዛሬም በእልፍ አዕላፍ ረሳ
እያረረ ሆዴ ብስቅ በማሽላ ዘዴ
ና ታደም ይለኛል ደግሞ በነ ኡኡ ሬጌ
ኡኡ ... ሬጌ ናዕት ሬጌ ናዕት
ብልጭልጭ ቢሆን ዳሱ ... ሬጌ ናዕት
ማን ሊታደም ከድግሱ ... >> >>
ተላላ ዝንጉ ሰብ የሙታን ሸማ ደዋሪ
ምን አለ አይል ከፊት ሆኖ ቅርብ አዳሪ
ተናገር አፌ ደፍረህ ሳትናወጥ ከቶ
ዝም አይሆንም ሜዳ ተራራ ሞት መጥቶ
ከበሮ ግም ሲል በእምቢ ነጎድጓድ ምቱ
ይናዳል የዘር ድንዛዜ ድውይ ቤቱ
ገለል በል ኤሳው ነፍሴን አንቀህ አታሳሳት
ብታገስ ባሰ ባንተ የልቤ እሳት
እያመመው.... እያመመው መጣ
ያዳፈነው እሳት ከሆዱ ሳይወጣ
ልቤ እንደ ካቻምናው እያመመው መጣ
የሚያዜም ይመስላል ሲያጣጥር ተጨንቆ
ውስጡን ሲሰብቅለት ኡ..እያለ ማሲንቆ
ኡ .... ኡ....
ኡ....ኡ....
እያመመው መጣ ... እያመመው መጣ
የተረገጠ ዕለት በጊዜው ውስጥ እግር ...
ታፍኖ የቆየ በሆታ ግርግር....
ትንሽ ጋብ እያለ የጭብጨባው ጩኸት...
እረጭ ሲል ውሸት ይናገራል እውነት...
እያመመው መጣ...እያመመው መጣ
ቂምን ሻረውና ወይ ፍቅርን አንግሰው
ሁለት ሆኖ አያውቅም አንድ ነው አንድ ሰው
ከሀገርም ይሰፋል ያ የፍቅር ገዳም
መጠሪያው ሰው እንጂ ዘር አይደለም አዳም
ዶፍ .... ዶፍ
ዶፍ ቢዘንብ እሳት ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አልኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት
ዳር አለው እንዴ ድንበር... ዳር አለው እንዴ
ዳር አለው እንዴ ፍቅር ... >> >>
የዘር ሃይማኖት ድንበር >> >>
ዳር አለው እንዴ ፍቅር >> >>
በዚህ ለፀና እውነት >> >>
የፍቅር ሀገር ከጥንት >> >>
ዘብ ያጥራል ሁሉም እስከሞት >> >>
ዶፍ ቢዘንብ እቶን እሳት >> >>
ዶፍ .... ዶፍ
ዶፍ ቢዘንብ እሳት ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አልኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት።

22/06/2022

ናዕት? ምን ማለት ነው ተርጉሙልን የሚያውቅ ካል🙏

(ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን እንዳለው) ሰባት ሰዓት ወስዶባቸዋል። በቪዲዮ እየቀረጹ የህጻናትን አንገት ቀንጥሰዋል። እየጨፈሩ የአዛውንቶችን ሰውነት በሜንጫ ተልትለው ገድለዋል። እየፎከሩና እየሸለሉ...
22/06/2022

(ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን እንዳለው) ሰባት ሰዓት ወስዶባቸዋል። በቪዲዮ እየቀረጹ የህጻናትን አንገት ቀንጥሰዋል። እየጨፈሩ የአዛውንቶችን ሰውነት በሜንጫ ተልትለው ገድለዋል። እየፎከሩና እየሸለሉ የእናቶችን ደረት በጥይት ደብድበው ጨፍጭፈዋል። አራት መቶ ነፍሶችን ለሞት ለመማገድ የከለከላቸው አልነበረም። ለእነዚያ ምስኪን ወገኖች ማንም ሳይደርስላቸው ይህቺን ምድር በግፍ ተሰናበቷት። ያማል...ያማል!
አሁንም የድረሱልን ጩኸት ከዚያ የስቃይ፣ አኬልዳማ ምድር ይሰማል። ስልኬ እረፍት አጥቷል። በውስጥ መስመር በሚደርሰኝ የጽሁፍና የፎቶግራፍ መልዕክቶች ፍጹም ተረብሼአለሁ። የእንባ ከረጢቴ ደርቋል። ውስጤ ድምጽ አልባ ሆኖ ይነፈርቃል። ዛሬም ከወለጋ ምድር ነፍሶች የሚታደጋቸው አላገኙም። ተጨማሪ ዕልቂት እንዳይኖር ምን እናድርግ? ቁጥሮች እየጨመሩ ነው። ምናልባትም በሚቀጥሉት ቀናት የተገደሉት ቁጥር በእጥፍ ሊጨምር ይችላል። የሰይጣን ጆሮ ይስማው። መንግስት አረ በህግ አምላክ?! ችግኙን ሌላ ጊዜ እንተክላለን።
እውነት ለመናገር ቀና ማለት አቅቶኛል። እነዚህ ነፍሶች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በመረጡት ምክር ቤት ተነፍጓቸው እንደመስማት ቅስም ሰባሪ ሀዘን የለም። አራት መቶ ነፍሶችን በግማሽ ቀን ውስጥ ያጣች ሀገር ድንኳን ጥላ፣ ሰንደቋን ዝቅ አድርጋ ሀዘን እንደመቀመጥ በቸበርቻቻና የፓርቲ ድግስ ስትምነሸነሽ እንደማየት ልብ የሚያቆስል በደል የለም። ምነው ፈጣሪስ ጨከነ? እንዴት መንግስት ከህዝብ ጋር እልህ ይገጥማል? ብሽሽቅ በሰው እልቂት?! አቤቱ! ወይ ፍረድ ወይ ውረድ!? ግድየለም፣ አሁንም ሞት አድፍጦ የሚጠብቃቸው ወገኖቻችን የድረሱልን ድምጽ ይሰማልና ተጨማሪ ዕልቂት እንዳይከሰት እልሃችንን እንዋጠው።

ሼር እምታደርጉ ሰዎች ግን እኔን ለማሳፈን ነው 😥
22/06/2022

ሼር እምታደርጉ ሰዎች ግን እኔን ለማሳፈን ነው 😥

እያረረ ሆዴ ብስቅ በማሽላ ዘዴ  ና ታደም ይለኛል ደግሞ በነ ኡኡ ሬጌ
22/06/2022

እያረረ ሆዴ ብስቅ በማሽላ ዘዴ
ና ታደም ይለኛል ደግሞ በነ ኡኡ ሬጌ

የሩስያ ሩብል በካፒታል ቁጥጥር እና በመጪው ወር መጨረሻ የታክስ ክፍያዎች ቃል በገባው የሞስኮ ልውውጥ ላይ ከዶላር ጋር ሲነፃፀር በሰባት ዓመት ገደማ ከፍ ብሏል, መንግሥት አዲሱን በጀት ሲያ...
20/06/2022

የሩስያ ሩብል በካፒታል ቁጥጥር እና በመጪው ወር መጨረሻ የታክስ ክፍያዎች ቃል በገባው የሞስኮ ልውውጥ ላይ ከዶላር ጋር ሲነፃፀር በሰባት ዓመት ገደማ ከፍ ብሏል, መንግሥት አዲሱን በጀት ሲያቀርብ.

እናናዬ
17/06/2022

እናናዬ

From Lagos, Nigeria
16/06/2022

From Lagos, Nigeria

16/06/2022

1. በፋና ቴሌቪዥን ሳያት እውነት እኔ የወለድኳት ያለምወርቅ ናት ብያለሁ- እናቷ ወ/ሮ ሆድዬ
2. አርቲስት ሔለን በድሉ ስሜን ሲያጠፉ ነበር ያለቻቸውን ዩቲዩበሮች ከሰሰች
3.መነጋገሪያ የሆነችው አፍቃሪ “ቺት አደርጋብኝ ነው ብሎ ሲያስወራ ሰፈር ጥዬ ጠፋሁ || ሶስት አመት ያፈቀርኩት ሰው በሳምንት ውስጥ ሌሏ ሰው አገባ
4.ስታሊን ገ/ስላሴ ተገነጠለ
5.ከአትሌት ኃይሌ ጋር የDNA ምርመራ ብናደርግ ደስ ይለኛል. አትሌት ኃይሌን በመምሰሌ ብዙ ፈተና አሳልፊያለሁ

Address

Addis Ababa
262700

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወንድ-Male posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share