ተጠያቂነት ማረጋገጥ ከተቋም ግንባታ ተግባሮቻችን ጋር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ።
በርካታ ዜጎቻችን ልብ የሚሰብር የቪዲዮ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ሲቀባበሉ ተመልክተናል። የጀመርነው ተቋማዊ ለውጥ ሀላፊነትን ከነተጠያቂነቱ አጣምሮ የያዘ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ከፌዴራል ፓሊስ አመራሮች ጋር መረጃ ተለዋዉጠናል።
በድርጊቱ የተሳተፉ ሁለት የፓሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል ። ህጉን ተከትሎ የማጣራትና ተገቢው የእርምት እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል።
በዚህ አጋጣሚ ዜጎች ለሰብዓዊ መብት መከበር እንዲህ አይነት ህገወጥ ተግባራትን በመከታተልና በማጋለጥ ረገድ ማህበራዊ ሚዲያን አዎንታዊ ለሆነ ተግባር ማዋል መቻላቸው ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
የፖሊስን ተቋም በአስተሳሰብ፣ በአሰራር፣ በአደረጃጀት፣ በሰው ሀይል አቅም ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ለማዘመን በጥቅሉ ተቋማዊ አቅሙን ለመገንባት ላለፉት ሶስት አመታት ገደማ በሰላም ሚኒስቴር መሪነት ሰፊ ርብርብ ተደርጎ ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝቷል።
ለዘመናት የተከማቸን ችግር ለመቅረፍ የተጀመረው ተቋማዊ ለውጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና መሰል ችግሮችን ለመፍታት አይነተኛ መሳሪያ እንደሚሆን ይታመናል።
የሰላም ባለቤት እርስዎ ነዎት!
ሙፈሪያት ካሚል
ተቃውሞ
#ተቃውሞ
በአዲስ አበባው የኢሬቻ በዓል አከባበር የተቃውሞ ድምጾች ተሰምተዋል። በእስር ላይ የሚገኘው ጃዋር መሐመድ እንዲፈቱ የሚጠይቁ እና በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስተዳደር ላይ ተቃውሞዎች ተደምጠዋል። (ኢትዮጵያን ዴይሊ )
Bbc
ዕውነቱን ዓለም እየተረዳው ነው!
እነ ቢቢሲ እያጭበረበሩ መቀጠል አይችሉም!
ይህች የቢቢሲ ጋዜጠኛ በአትላንቲክ ካውንስል የአፍሪቃ ማዕከል ምክትል ዳይሬክተርን ወደ ትግራይ ዕርዳታ ለማስገባት ስላጋጠማቸው ችግር ስትጠይቃት ዳይሬክተሯ ችግሩ የተፈጠረው መንግሥት የተናጠል ተኩስ አቁም ቢያውጅም የህወሃት ጁንታ ጦርነት ባለማቆሙና ይልቁንም ወደ አጎራባች ክልሎች ጦርነቱን በማስፋፋቱ መሆኑን ገልፃ በተለይም ዕርዳታ የሚያልፍበትን የአፋር ክልል የጦር ቀጠና ስላደረገው ችግሩ መፈጠሩን ገልፃ መንግሥትም ችግሩን ማባበሱን አክላበታለች።
ከዚህ በተጨማሪ የህወሃት ጁንታ ኢትዮጵያውያንን ለ30 ዓመታት አሰቃይቶ የገዛ ቡድን መሆኑን ገልፃ ከሥልጣን ሲባረርም ወደ ትግራይ በመሄድ እና በዛ የነበረውን የሰሜን ዕዝ በማጥቃት ጦርነት መቀስቀሱን አስረድታለች።