13/06/2024
እግዚአብሔር አንድ ነው
እስራኤል ሆይ ስማ እግዚአብሔር አንድ ነው
አንተም አምላክህን ከልብህ እመነው
በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ሀይልህ
በፍጹም ሀሳብህ ኢየሱስን ውደድ
በመንገድም ስትሄድ ስትቀመጥም
ስትነሳም ሁሌ ተጨዋወተው
ለልጆችህም እያስተማርከው
ትውልድህ በሙሉ እርሱን ይወቀው
እውነቱ ይሄ ነው ለዘላለም
እግዚአብሔር አንድ ነው አይለወጥም /2×
ፍጥረትን ሲፈጥር ምድርን ሲያጸና
ማን ነበረ አብሮት ከእርሱ ጋር
ኢየሱስ ብቸኛ ነው አልፋ እና ኦሜጋ
ዘላለም የሚኖር ፊተኛ ኋለኛ
እውነቱ ይሄ ነው ለዘላለም
እግዚአብሔር አንድ ነው አይለወጥም /2×
የማይታፈርበት እውነትን ይዘናል
ብቻውን ያለውን ኢየሱስን አምነናል
እንናገራለን በሕይወት ዘመናችን
ኢየሱስ ብቻ ነው ንጉስ አምላካችን
ሽማ ኢስራኤል/2×
አዶናይ ኤሎሄኑ
አዶናይ ዔካድ
አዶናይ ሲድ ኬኑ
አዶናይ የሽዋቴኑ
ኢየሱስ በምድር ይነግሳል
ፍጥረት በሙሉ ይሰግዳል
ስሙም አንድ ይሆናል
ብቻውንም ይመለካል
አንድ ነው/4