WORD of GOD

WORD of GOD “የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና...
— ዕብራውያን 4፥12

01/12/2023
18/08/2023

ሄሴድ ዓለም አቀፍ ቤተ-ክርስቲያን ሁለንተናዊ ደህንነትን ለትውልድ ማካፈል! ክርስቶስ ኢየሱስን በትውልድ ልብ ላይ መሳል! ሶተሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅአድራሻ፦ ቦሌ ደምበል ፊት ለፊት ወ.....

ወደ አንድ ጎሣ ንጉስ ሄጄ "ኢየሱስ ለአንተ ማን ነው?" ብዬ ጠየኩ እሱም መለሰልኝ "ኢየሱስ የነገስታት ንጉስ ነው!"። ወደ ኤሌክትሪክ ሠሪ ጋር ሄጄ ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየቁት እሱም "ኢየሱስ ...
07/07/2023

ወደ አንድ ጎሣ ንጉስ ሄጄ "ኢየሱስ ለአንተ ማን ነው?" ብዬ ጠየኩ እሱም መለሰልኝ "ኢየሱስ የነገስታት ንጉስ ነው!"። ወደ ኤሌክትሪክ ሠሪ ጋር ሄጄ ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየቁት እሱም "ኢየሱስ የዓለም ብርሃን ነው!" ብሎ መለሰልኝ።ወደ ቧንቧ ሰሪ ጋርም ሄድኩ "ኢየሱስ ማን ነው" ብዬ ጠየቁት
"የዘላለም ህይወት የሚያፈልቅ የውሃ ምንጭ ነው!"ብሎ መለሰልኝ።
ወደ ዶክተር ጋር ሄጄ ተመሳሳይ ጥያቄ አቀረብኩ "ኢየሱስ ለአንተ ማን ነው?" እሱም መለሰልኝ "ህይወትን የሚሰጥ፣የሚያድን ፣የሚፈውስ ፣ህይወትን የሚወስድ እሱ ነው" አለኝ።
ወደ ጫካም ወጣሁ እዛም አንድ አዳኝ አገኘሁ "ኢየሱስ ማን ነው?" ብዬ ጠየቁት እሱም መለሰ "ኢየሱስ የይሁዳ አንበሳ ነው!" ወደ አንዲት ሳይኮሎጂስትም ሄድኩ ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየኳት እርሷም "የጥበብ ሁሉ ምንጭ እሱ ነው!" አለችኝ።
ወደ ግንበኛ ዘንድም ሄድኩ "ኢየሱስ ማን ነው?" ብዬ ጠየኩት እሱም መለሰ "ግንበኞች የናቁት ድንጋይ ግን የማዕዘን ራስ የሆነ እሱ ነው" አለኝ።
ወደ አንዲት እንጀራ የሚጋጋሩ ባልቴት ጋር ሄድኩ ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየኳቸው እሳቸውም መለሱልኝ "ኢየሱስ የህይወት እንጀራ ነው!"
ወደ አንድ አባት ጋር ጠጋ አልኩ "የኔታ፣ኢየሱስ ማን ነው?" አልኳቸው "ልጄ፣እርሱ አልፋ እና ኦሜጋ ያለ እና የነበረ ሁሉን የሚገዛ ዘላለማዊ አምላክ ነው!" ብለው መለሱልኝ!
አሁንም እጠይቃለው ኢየሱስ ለአንተ (ለአንቺ) ማን ነው?

ደግሞ ሌላ በረከት ❤🙏🙏      ውሳኔዬዘማሪት ቤቲ ወልዴ ቁጥር 4 የመዝሙር አልበም!በጣም የምንወዳትና የምናከብራት በመዝሙዎቿ የተባረክንባት በህይወቷ በዙ የተማርንባት ሰርዓት ባለው አምልኮ...
06/07/2023

ደግሞ ሌላ በረከት ❤🙏🙏
ውሳኔዬ
ዘማሪት ቤቲ ወልዴ ቁጥር 4 የመዝሙር አልበም!
በጣም የምንወዳትና የምናከብራት በመዝሙዎቿ የተባረክንባት በህይወቷ በዙ የተማርንባት ሰርዓት ባለው አምልኮ የምናውቃት ለብዙዎች ተምሳሌት የሆነች ድንቅ እህታችን አሁን ደግሞ ከአስራ አምስት አመት በኃላ በአዲስ ቅኔ ብቅ ብላለች ክብር ለእርሱ ይሁን ❤🙏I can't wait ቤቲሻ።

05/07/2023


**************
ከ 3:30 - ጀምሮ!
ቦታ:-አድራሻ ቦሌ ደምበል ኦሎምፒያ ወደ ባምቢስ በሚወስደው መንገድ ግሪክ ስኩል ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ:- 𝟎𝟗𝟎𝟗𝟎𝟎𝟕𝟕𝟎𝟎 ወይም 𝟎𝟗𝟎𝟗𝟒𝟗𝟎𝟗𝟎𝟗 ይደውሉ!!
አልያም ከታች ያለውን ሊንኩን ተጭነው በጎግል ማፕ ይምጡ
Dropped pin
https://maps.app.goo.gl/1XF6boRa3M6FvLox7

✍  የዩቲዩብ ጉዳይ*******************✍ እገሌን በሳቅ የገደለው የነብይ እገሌ ሽጉጥ ሽጉጥ የሚል ቀልድ ~ 370ሺህ ተመልካች✍ እገሌ እንባውን ጨርሶ ከጓደኛው እንባ በብድር ወስዶ...
02/07/2023

✍ የዩቲዩብ ጉዳይ
*******************
✍ እገሌን በሳቅ የገደለው የነብይ እገሌ ሽጉጥ ሽጉጥ የሚል ቀልድ ~ 370ሺህ ተመልካች
✍ እገሌ እንባውን ጨርሶ ከጓደኛው እንባ በብድር ወስዶ ያለቀሰበት የእገሌ ንግግር ~ 527ሺህ ተመልካች
✍ የእገሌ ለዘመናት ተደብቆ የቆየ አነጋጋሪ ሚስጥር በአጥር ሾልኮ ወጣ ~ 861ሺህ ተመልካች
✍ እገሊት የምትባለው ዘማሪት እጮኛዋ ሰርፕራይዝ ሊያደርጋት እንደሆነ ቀልቧ ነግሯት ከቤቷ ጀምራ ፌንት እየበላች የደረሰችበት ፕሮግራም ~ 666ሺህ ተመልካች
✍ እገሌ እና እገሌ ማይክ እየተቀባበሉ ነብይ እገሌን ያስደሰቱበት ቀውጢ አምልኮ ~ 396ሺህ ተመልካች
ወዲህ ደሞ.......
📌 ክርስቶስ ኢየሱስን በማወቅ ስር መስደድ ~ 119 ተመልካች
📌 የእግዚአብሔር ሚስጥር ክርስቶስ ~ 2853 ተመልካች
📌 የአዲሱ ኪዳን መካከለኛ ~ 194 ተመልካች
📌 የደሙ ኃይል ~ 1357 ተመልካች
📌 የእግዚአብሔር እረኝነት ~ 2149 ተመልካች
👉 ወዳጆቼ የቴክኖሎጂ ዋነኛው ጥቅም ለወንጌል ሩጫ መጥቀሙ ነው!!.....የክርስቶስን ወንጌል በያለንበት ሆነን መስማት እና መማር መቻላችን ነው!!
✍️ በዩቲዩብ ንግድ አትጠለፉ!!.....የእግዚአብሔርን ሚስጥር እንጂ የአገልጋዮችን ሚስጥር ለማወቅ አትሽቀዳደሙ!!.....የዳናችሁት በእግዚአብሔር ሚስጥር እንጂ በአገልጋይ ሚስጥር አይደለም!!.....ነፍሳችሁን በረብ አልባ ወሬ አትሙሏት!!....የአብ ዜና የሆነውን ክርስቶስን ዜና ያላደረጉ ፣ ለገንዘብ ሲሉ አገልጋዮችን ዜና ያደረጉ ዩቲዩበሮችን በመስማት ነፍሳችሁን አታጠውልጉ!!....ክርስቶስን ብቻ የሚያስተምሯችሁን አዳምጡ!!
📌 በከንቱ ለመዝናናት ሳይሆን በእግዚአብሔር ለመማር ታገሱ!!

📢በዚህ የህይወት ቃል ከተፃፈዉ በስተቀር የመዳን መንገድ የለም❗️
30/06/2023

📢በዚህ የህይወት ቃል ከተፃፈዉ በስተቀር የመዳን መንገድ የለም❗️


29/06/2023

ፓስተሩ ፀጉሩን ሊስተካከል ገና ከመግባቱ....❓❌❓❌❓

ፀጉር አስተካካዩ ወንበሩ ላይ አስቀምጦ ሽርጡን እያስተካከለ በጥያቄ ያጣድፈው ጀመር....???

አስተካካዩ:- ፓስተር ነህ መሰለኝ?

ፓስተሩ:- እ....አዎ!

አስተካካዩ:- አይ እንደው እግዚአብሔር የሚባል ቢኖር ኖሮ ለምንድን ነው ይሔ ሁሉ ክፋት አለማችን ላይ የበዛው? እላለሁ ሁልጊዜ

እና ደግሞ.....ምናምን ምናምን እያለ ብዙም ለፓስተሩ የምላሽ ጊዜ እንኳን ሳይሰጠው ንግግሩን ቀጠለ

ፓስተሩ .....ምንም ሳይመልስለት ተቆርጦ ሲጨርስ ሒሳቡን ከፍሎ አመስግኖ ወጣ::

ከፀጉር ቤቱ አለፍ ብሎ ወደ ተቀመጠ ጎዳና ተዳዳሪ ፓስተሩ ጠጋ አለና "ወንድሜ ይሔንን ረጅም ፀጉርህን መስተካከል ትፈልጋለህ"? አለው::

ሰውዬውም ፈቃደኛ መሆኑን በደስታ ገለፀለት...

ወደ ፀጉር ቤቱ ይዞት እንደገባ ፓስተሩ ወደ አስተካካዩ እየተመለከተ "ፀጉር አስተካካይ የሚባል ቢኖር ኖሮ የዚህ ሰውዬ ፀጉር እንዲህ ባላደገ ነበር" አለው🧐

አስተካካዩም:- ፀጉር ቆራጭ እማ አለ ብዙዎች ወደ እኔ አልመጡም እንጂ…..

❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌❌

አዎ እግዚአብሔር ስለሌለ ሳይሆን ወደ እርሱ ለመፍትሔ የሚቀርብ ጠፍቶ ነው🥲

የለም አትበለኝ አንተ እሱ ጋር ሳትኖር😔

“ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥ ፊታችሁም አያፍርም" መዝ 34:5
#እግዚአብሔር

ከመጽሐፍ ቅዱስአንድ ጥቅስ ጋብዙኝ
28/06/2023

ከመጽሐፍ ቅዱስ
አንድ ጥቅስ ጋብዙኝ

     🔵 በሶሪያ ጦርነት ጊዜ ነዉ፥ በምድረ በዳ የተገኘዉ እዉነተኛ ወዳጅ።🔵 በሃገረ ሶሪያ አንድ ሙስሊም ሴት ከባሏ እና ከ አራት ልጇቿ ጋር የቤታቸዉ በረንዳ ላይ ቁርስ ይበላሉ፤ በድንገት...
24/06/2023


🔵 በሶሪያ ጦርነት ጊዜ ነዉ፥ በምድረ በዳ የተገኘዉ እዉነተኛ ወዳጅ።
🔵 በሃገረ ሶሪያ አንድ ሙስሊም ሴት ከባሏ እና ከ አራት ልጇቿ ጋር የቤታቸዉ በረንዳ ላይ ቁርስ ይበላሉ፤ በድንገትም እየተጫወቱ ምግባቸዉን እየተመገቡ ሳሉ:- ወደ አይር መንገዱ የተወረወረ ሚሳኤል የእነሱ ቤት ላይ ያርፋል ሚሳኤሉም በወደቀ ቅጽበት የዛች ሴት [ስሟን ካልተሳሳትኩ አሊማ] ሁለት ወንድ ልጇቿ እና ባለቤቷ ይሞታሉ፣ አሊማ ላይ ከባድ ጉዳት በእግሯ ላይ ሲደርስ ሁለት ሴቶች ልጆቿ መጠነኛ ጉዳት ያገኛቸዋል።
🔵 ለተወሰነ ቀን ሕክምና ካደረገች በሗላ አሊማ ያላትን ንብረት ሁሉ ትሸጥና እጇ ላይ ያለዉን ሁሉ ብር ድንበር ለሚያሻግር ደላላ ሰጥታ ወደ ሌላ ሃገር ከባህር ማዶ ለመሰደድ ትሄዳለች፤ ጉዞዉ ለሊት ስልነበር በጣም የሚያሳዝነዉ አሊማ ከደረሰባት ጉዳት የተነሳ በክራንች ስለምትሄድ ያዉም ሁለት ሕጻናት ሴቶች ልጆች ይዛ እርመጃዉ በጣም የተገታ ነበር። በዚህ ጊዜ ከፊት ከፊት የሚመራቸዉ ደላላ ወደ አሊማ ይመጣና በጣም ተቆጥቶ:- [ስሚ አንቺ ሴትዮ ለሊቱ ከነጋ ሰዎቹ ደርሰዉ ይገድሉናል አንቺ በደንብ አልራመድ ብለሽ እኛን ልታሲዥን ነዉ የራስሽ ጉዳይ] ብሎ ክራንቹን በእግሩ መጥቶ ይጥልባታል አንዴ ብሩን ሰልተቀበለ የአልሚና ጉዳይ ትቶ በሩጫ ያመልጣል። አሊማ ከሁለት ሕጻናት ልጆቿ ጋር በለሊት በጫካ ዉስጥ ወድቃ ታለቅሳለች። እያለቀሰችም እያለ በድንገት ሰዉነቱ የፈረጠመ ረጅም ጎልማሳ ሰዉ ይመጣና:- [አይዞሽ በሶሪየሎ እንባዋን በእጁ ያብሳል፣ በእጁም ደግፎ ያስነሳትና በአንድ እጁ እሷን በሌላኛዉ እጁ ሁለት ሴት ልጆቿን ይዞ በጣም በፍጥነት እየተራመደ ከነበሩበት አገር ያወጣቸዋል]፤ የሚፈለግቡት ሃገር ካደረሳቸዉ በሗላ [ሰለም ሁኑ] ብሎ ሊሄድ ሲል አሊማ [አንተ መልካም ሰዉ አላህ ዉለታህን ይክፈልህ ስምህንና አድራሽን ንገረኝ ደዉዬ ላገኝህ እፈልጋለሁ ትለዋለች]
እሱም:- ስምሽን አዉቀዋለሁ አሊማ ነዉ የሁለት ልጆቿንም ስም ይጠራና አድራሻዬን በቅርቡ ታዉቂዋለሽ ባለሽበት ቦታ እመጠላሁ እስከዛዉ ግን ስሜ አልመሲ ኢሳ ነዉ ብሏት ተሰወረ።
🔵 ከቀናት በሗላ አሊማ የሄደችበት ሃገር ያሉ ባልና ሚስት የወንጌል አገልጋዮች ጌታ ስለ አሊማ ይነግራቸዋል፤ ከዛም ሄደዉ ወንጌል እንዲሰብኩላት አዘዛቸዉ። እነሱም ጌታን ታዘዉ ወደ አሊማ ቤት ሄዱ በሯን ሲንኳኩም አሊማም በሯን ከፍታ ተቀበለቻቸዉ፣ መልዕክቱንም ይነግሯት ጀመር:- [99 በጉቹን ትቶ አንዷን የጠፋችዉን በግ ሊፈልግ ስለሄደዉ ሲያገኛትም ተሸክሟት በደስታ ስለተመለሰዉ እረኛ ገና እያወሩላት እያሉ አሊማ በመሃል አቋረገጠቻቸዉ እና ጮህች ይሄ የእኔ ታሪክ ነዉ ከቀናት በፊት ጠፍቼ ወድቄ በሞት አፋፍ ላይ ተሸክሞ አተረፈኝ በፈርጣማ እጆቹ የታደገኝ አልመሲ ኢሳ ነዉ] አለች በጉልበቷ ተንበረከከች፥ አድራሻዉ የጠፋባትን ደጉን እረኛ አልመሲ ኢሳ እዉነተኛዉን አዳኙን በቃሉ በኩል አገኘችዉ!
🔵 የኢየሱስ አድራሻዉ ቃሉ ዉስጥ ነዉ፤ አልመሲ ኢሳ ያድናል!
#ምንጭ:- ከአንድ ሚሽነሪ የተገኘ እዉነተኛ ታሪክ
🔵 መልካም ቀን፤ ሐምሌ 26/11/2013ዓ.ም። “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።”
— 2ኛ ቆሮንቶስ 13፥14

ዘማሪት Meskerem Getu ከተናገረችዉ፦ከልጅነቴ ጀምሮ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው ያደኩት። ሌላም አምላክ አላውቅም ኢየሱስን ብቻ። ተስፋ ኳየር የሚባል የሕፃናት መዝሙር አገልግሎት ውስጥ...
23/06/2023

ዘማሪት Meskerem Getu ከተናገረችዉ፦
ከልጅነቴ ጀምሮ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው ያደኩት። ሌላም አምላክ አላውቅም ኢየሱስን ብቻ። ተስፋ ኳየር የሚባል የሕፃናት መዝሙር አገልግሎት ውስጥ አገለግል ነበር። ሁል ጊዜ ለበአል ለበአል እንዘምር ነበር። ነብሴ እስክትወጣ ነው የምወዳቸው። ከትምህርት ቤት ወጥቼ ዩኒፎርሜን ወርውሬ ከነሱ ጋር ለመሆን ለመፀለይ፤ ለመዘመር እየሮጥኩ እሄድ ነበር። ትላንትናዬን ዞር ብዬ ሳስበው አስታውሼ የማልጠገበው የሚያረካኝ የሕይወት ምዕራፍ ነው። ክርስትናዬ የተቀረፀው የዚያኔ ነው። ከቅዱሳን ጋር መዋደድና ቤተሰብነት፤ የተንገዳገዱትን መደገፍ፤ የደከመው ሲገኝ በመንፈስ ማነቃቃት፤ እርስ በእርስ እየተፀላለይን የአንዳችንን ሸክም ሌላችን እየተሸከምን ከድካማችን እየተማርን... ለኔ ወንድምና እህቶቼ እነሱም ናቸው። ያስተሳሰረን ፍቅር የላይኛው ስለነበረ ሀይለኛ ነው። ልቤ የሚረዳው ይህን እውነታ ነው። የሚገርማችሁ ይኸው ካደኩኝም በኋላ ክፍለ ሃገር ያሉ የሚናፍቁኝ ዘመዶቼን ሄጄ ለመጠየቅ ጊዜ አላገኝም ነበር። ምክንያቱም ሌላኛው ክፍለ ሃገር ያሉትን በክርስቶስ ቤተሰቦቼን በመዝሙር ወንጌልን ለማገልገል እሄድ ስለነበር ማለት ነው። ለኔ ከዚህኛው ፍቅር በኢየሱስ ቤተሰብ ከሆንበት መሰባሰብ የሚለያየን የሚበልጥብን ምንም ነገር አለ ብዬ አላምንም።
ትላንት በታሪክ ውስጥ ቤተሰቦቻችን ተበዳድለው፤ ተቆሳስለው ከነበረ በክርስቶስ ፍቅር የማይፈወስ ቁስል የማይረሳ ትላንት ስለሌለ አልድን ያለንን ስብራት ሁሉ ወደሚጠግኑ ሩህሩህ የጌታ እጆቹ እናምጣቸው እሱ ይፈውስልናል እንባችንን ያብሳል። እኛ ግን በእኛና በሞተልን ጌታ መሐል ጣልቃ ሊገባ ከሚወድ የትኛውም ዋና ነገር ከአምላካችን ሳይለየን በፊት ልንለየው ይገባናል። ከዚህ በኋላ እኛ የኛ አይደለንም የምንኖረው ለሞተልን ነው። እርሱ ኢየሱስ ነብሱን እስከመስጠት ውድድ ካደረገን በላይ የሚወደን ማንም የለም። የኛ እርስ በርስ መዋደድ እርሱን መልሰን እንደምንወደው ማሳያ ነው። በልባችን የተሸሸገ ጥል ካለ ጌታን አንወደውም ማለት ነው .
#እንዋደድ # 🙏

23/06/2023





ባንተ ደስ ይለኛል ይስሃቅ ሰዲቅ

18/06/2023

እግሮች የረገጡትን በጥንቃቄ እረግጣለሁ
ከፊት ከፊት ስትሄድ ከኋላ ከኋላ እከተልሃለሁ
ባሪህን አጠናለሁ እንድመስል እቸኩላለሁ
ግራ ቀኝ አላማትርም ታላቄ ነህ እሰማሃለሁ
አንተን ነው የማየው
እኔ አንተን ነው ምከተለው
አንተ ነህ ምሳሌዬ
አንተ ነህ ዋናዬ

የማለዋውጠው እውነት ነውበሁኔታዎች የማላጥፈውየሚመሰክረው ህይወቴመልካምነትህን ነው አባቴ የሚዘምረው አንደበቴመልካምነትህን ነው አባቴ
16/06/2023

የማለዋውጠው እውነት ነው
በሁኔታዎች የማላጥፈው
የሚመሰክረው ህይወቴ
መልካምነትህን ነው አባቴ
የሚዘምረው አንደበቴ
መልካምነትህን ነው አባቴ

This song is about the goodness of God, that is demonstrated to us through His actions and intentions toward us, no matter what the circumstances we go throu...

ሩቅ አልሄድም ለማየት የአንተን ምህረትከቦኝ የለም ወይ  በየማለዳዉከቦኝ የለም ወይ በየምሽቱከቦኝ የለም ወይ እለት እለት ከቦኝ የለም ወይ ያንተን ምህረት      Ayda Abraham - ID
16/06/2023

ሩቅ አልሄድም ለማየት የአንተን ምህረት
ከቦኝ የለም ወይ በየማለዳዉ
ከቦኝ የለም ወይ በየምሽቱ
ከቦኝ የለም ወይ እለት እለት
ከቦኝ የለም ወይ ያንተን ምህረት
Ayda Abraham - ID

አልቻልኩም አቅቶኛል ብላችሁ ተስፋ በቆረጣችሁበት ነገር ላይ አቅም የሚሰጣችሁና የሚያበረታችሁ የጌታ እጅ ይዘርጋላችሁ!!
16/06/2023

አልቻልኩም አቅቶኛል ብላችሁ ተስፋ በቆረጣችሁበት ነገር ላይ አቅም የሚሰጣችሁና የሚያበረታችሁ የጌታ እጅ ይዘርጋላችሁ!!

12/06/2023

❝በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤❞
ሮሜ 12: 12

"ከክርስቶስ ውጪ በሆነ ማንነት ማንም ምንም ቢያከማች ትርፉ ኪሳራ ነዉ! የኢየሱስ እጅ የሌለበት ነገር በሙሉ ኪሣራ እንጂ ትርፍ የለዉም!!
11/06/2023

"ከክርስቶስ ውጪ በሆነ ማንነት ማንም ምንም ቢያከማች ትርፉ ኪሳራ ነዉ! የኢየሱስ እጅ የሌለበት ነገር በሙሉ ኪሣራ እንጂ ትርፍ የለዉም!!

አንዳንድ ጴንጤዎች እኮ ከልብ ናቸዉ!! የጌታን ወንጌል አዉቀዉ በጫካ ተደብቀዉ ለነበሩ /ከገዳም/ ወጥተዉ ባገኙበት አጋጣሚ ሁሉ ወንጌል እንዲደርስ ያደርጋሉ!!
11/06/2023

አንዳንድ ጴንጤዎች እኮ ከልብ ናቸዉ!! የጌታን ወንጌል አዉቀዉ በጫካ ተደብቀዉ ለነበሩ /ከገዳም/ ወጥተዉ ባገኙበት አጋጣሚ ሁሉ ወንጌል እንዲደርስ ያደርጋሉ!!

ወንጌላዊ ቶም ሮጀር ኤድቫርድሰን በኖርወይ የሚኖር ፍቅርን እና ርህራሄን የተሞላ በፈውስ አገልግሎት የሚታወቅ የወንጌል መልዕክተኛ ነው። ይህን ማለት ለምን አስፈለገ? የሚለኝ ይኖር ይሆናል። ...
11/06/2023

ወንጌላዊ ቶም ሮጀር ኤድቫርድሰን በኖርወይ የሚኖር ፍቅርን እና ርህራሄን የተሞላ በፈውስ አገልግሎት የሚታወቅ የወንጌል መልዕክተኛ ነው። ይህን ማለት ለምን አስፈለገ? የሚለኝ ይኖር ይሆናል። መልሱ አጭርና ግልጽ ነው። እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር 2005 ዓ.ም በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት መለኮታዊ ፈውስ የሚል ኮርስ ያስተማረኝና በሕመም ለሚሰቃዩ ሰዎች ፍቅርና ርህራሄ እንዲኖረኝ በተግባር ያስተማረኝ ድንቅ አስተማሪዬ ነበር። ትምህርቱ እውቀት ብቻ ሳይሆን ተግባራዊም ነው።
ክርስቶስን በተመለከተ እና ክርስቶስ በፈውስ አገልግሎት ሊጠቀምበት ሲፈልግ እንዴት እንደተገለጠለት ሲናገር የሚገልጠው ከእንባ ጋር ነው። እውነት ለመናገር በእርሱ ከተማርኩ በኋላ እግዚአብሔር እኔን ተጠቅሞ ብዙዎችን ሲፈውስ አይቻለሁ።
Evangelist Tom Roger Edvardsen is a Norwegian evangelist known for his loving and compassionate healing ministry. Why is it necessary to say this? Maybe someone will tell me. The answer is short and clear. He was my wonderful teacher who taught me a course called Divine Healing at the Bible school in 2005 according to the Ethiopian calendar and taught me to have love and compassion for people who are suffering. The lesson is not only knowledge but also practical.
It is with tears that he tells about Christ and how it was revealed to him when Christ wanted to use him in healing ministry. To be honest, I have seen God use me to heal many people after learning from him.

ዉርደታቹን የምጠባበቁ እጃቸዉን በአፍችው ላይ የምጨኑበትን  የእግዚአብሔር ጉበኘት በቤታቸው ይግባል::
11/06/2023

ዉርደታቹን የምጠባበቁ እጃቸዉን በአፍችው ላይ የምጨኑበትን የእግዚአብሔር ጉበኘት በቤታቸው ይግባል::

በዚህ አለም ላይ ስንኖር  በህይወታችን ውስጥ ብዙ አሳሳቢ እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች  ይገጥሙናል ....እንዴት ይሆናል የተባለውን እንዲሆን ፣እንዴት ይቻላል የሚባለውን  እንዲቻል ፣እንዴት ሊታ...
09/06/2023

በዚህ አለም ላይ ስንኖር በህይወታችን ውስጥ
ብዙ አሳሳቢ እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ይገጥሙናል ....
እንዴት ይሆናል የተባለውን እንዲሆን ፣
እንዴት ይቻላል የሚባለውን እንዲቻል ፣
እንዴት ሊታለፍ ነው የተባለውን እንዲታለፍ የሚያደርግ ብቸኛው የመፍትሄ መንገድ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

09/06/2023

For God so loved the world that he gave his one and only Son, that whoever believes in him shall not perish but have eternal life.
John 3:16
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤” ዮሐንስ 3፥16
#ኢየሱስያድናል #ኢየሱስ

09/06/2023

በእግዚአብሔር የተመረጥኩ ሰው ነኝ....የሚል

08/06/2023

#ታኦኔ
ቆየት ያለ #የወላይትኛ ዝማሬ ተጋበዙልኝ
ሰምተው ሼር ያድርጉ!!

08/06/2023

#በሰርጉ #ቀን
#ወንጌልን #የሰባከው #ጀግና #ሙሽራ

ወደ ሮሜ ሰዎች 10
15 መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ?

ያድናል
08/06/2023

ያድናል

07/06/2023

=====>
ፍቅር የሆነውን ለመስበክና ለመዘመር ያለ ፍቅር ወደ መድረክ ማውጣት በጽሐፍ ቅዱስ እውነት አይፈቀድም። ትሁቱን ኢየሱስ ለማሳየት በትቢት መፎከር እህል የሌለውን ገለባ አውዱማ ላይ አውጥቶ መውቀጥ ነው። ወንድምህን በምላስ ጦር እየቀጠቀጥን እኔ ልክ ነኝ ማለት ትልቅ ፍኛ ውስጥ ነፋስ ሞልቶ መጨወት ነው። የፍቅር ጌታ ሳይቀድም እንደት አገልግሎት ይቀድማል? ለፍቅር ከሰማይ የወረደውን ኢየሱስን ሳያውቅ እንደት አገልግሎቱን አወቀው?
" እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።"
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:16)
====>
አንድ ሰው በአገልግሎቱ በጣም አደገ የሚባለው በፍቅር ስያድግና ሁሉን አቃፊ ልብና አዕምሮ ስኖር ብቻ ነው!!! ዘማሪ ገዛኸኝ 👍❤️

07/06/2023

🔥🥰🙏
ዛሬ ደግሞ የእነዚህን ወጣቶች ቪዲዮ አንድ ሰው በውስጥ ላከልኝና ሰማሁት...እጅግም ወደድኩት...ጥሩ መልዕክት ደስ በሚል አዘማመር ስልት አቅርበውታልና ስሙላቸው...ሼርም አድርጉላቸው...ወጣቶች ሲነሱ በርቱ እንድንል እፈልጋለሁ...🙏
https://fb.watch/k-QCTXEgIm/

06/06/2023

𝖒𝖆𝖒𝖚𝖘𝖍𝖆's short video with ♬ original sound

የምንጠብቀው ተስፋችን ኢየሱስ ይመጣል !
06/06/2023

የምንጠብቀው ተስፋችን ኢየሱስ ይመጣል !

05/06/2023

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when WORD of GOD posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share