EthioXpress

EthioXpress "Your go-to source for Ethiopian news and entertainment. Stay updated, informed, and entertained with
(1)

03/04/2024
04/02/2024
09/01/2024
09/01/2024

የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ በአሥመራ በነበራቸው የኹለት ቀናት ጉብኝት ከፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር በኹለትዮሽ፣ በቀጠናዊና ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊና ጥልቅ ውይይት ማድረጋቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር አስታውቋል።

ኹለቱ መሪዎች በኹለትዮሽና በጋራ የትብብር መስኮች ላይ ሰፋ ባለ ቀጠናዊ የትብብር ማዕቀፍ ለመስራት መስማማታቸውን የገለጠው ሚንስቴሩ፣ በትግዕስትና በቀና መንፈስ በመጓዝና "ከተንኳሽ አጀንዳዎች በመራቅ" ቀጠናዊ ትብብራቸውን ለማሳደግ መስማማታቸውን ጠቅሷል።

ኤርትራ ከሱማሊያ ጋር ባላት የኹለትዮሽ ግንኙነትና በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ በቅርቡ ዝርዝር መግለጫ እንደምታወጣም ሚንስቴሩ ገልጧል።(ዋዜማ)

 #አስደማሚ
08/12/2023

#አስደማሚ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሶማሊያ የነበረውን ሚና  መልሶ ለመቃኘት እያሰበ ነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሶማሊያ የነበረውን ሚና  መልሶ ለመቃኘት እያሰበ መሆኑን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ...
11/11/2023

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሶማሊያ የነበረውን ሚና መልሶ ለመቃኘት እያሰበ
ነው

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሶማሊያ የነበረውን ሚና መልሶ ለመቃኘት እያሰበ መሆኑን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለፁ።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ በተለይም በቀጠናው ለበርካታ ዓመታት በሰላም ማስከበርና ሽብርተኝነትን በመዋጋት ጉልህ አስታዋፅኦ ስታበረክት መቆየቷ ይታወቃል። የመከላከያ ሰራዊቱም በብቃትና ዲሲፕሊን አለም አቀፍ እውቅና ያተረፈና ምስጉን ነው።

ሆኖም በሶማሊያ ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስርና ከዚያ ባለተናነሰ ቁጥር ደሞ በተናጠል ሽብርተኝነትን በመዋጋት ጎረቤት ሶማሊያን በመርዳት እንዲሁም ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረውን አደጋ በመመከት ላይ ተጠምዶ ቆይቷል ።

በዚህም ከፍተኛ የቁስና የሰው ሃይል ዋጋ ተከፍሏል። በተለይም በተናጠል የምታካሄደውን የፀረሽብር ዘመቻ ያለምንም ድጋፍ በራሷ አቅም ሸፍና ቆይታለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህንን ፖሊሲ እንደገና በመፈተሽ የሠራዊት ሃይሏን በመሰብሰብ በአጎራባች አካባቢዎች ላይ ብቻ ያተኮረ የፀረሽብር ስራ ለመስራት እየታሰበ መሆኑን ለመከላከያ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ያገኘናቸው መረጃዎች ያመለክታሉ።

በሞቃድሾ መንግስት አከባቢ በቂ ለውጥ መምጣት አለመቻሉ መቋጫው በማይታወቅ ሁኔታ መስዋዕትነት እየከፈሉ ከመቀጠል ሌሎች አማራጮችን ማሰብ እንደሚገባ አንዳንድ አካላት በማሳሰብ ላይ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል።



በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን መካከል በታንዛኒያ የሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር መጀመሩን " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ዘግቧል።እንደ ዘገባው ከሆነ ባለፉት  ሳምንታ...
08/11/2023

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን መካከል በታንዛኒያ የሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር መጀመሩን " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ዘግቧል።

እንደ ዘገባው ከሆነ ባለፉት ሳምንታት የፌደራል መንግሥት እና የኦሮሚያ ክልል መንግስሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች እንዲሁም ሁለት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች ተሳታፊ የሆኑበት ውጤታማ የተባለ የፖለቲካ ውይይቱ ተካሂዷል።

ውይይቱ ውጤታማ ስለነበር እና በዚህም ምክንያት የፌደራል መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች የተሳተፉበት ውይይት ትላንት ጥቅምት 27/2016 ዓ/ም በታንዛኒያ ዳሬሰላም መጀመሩን ተነግሯል።

08/11/2023

መከላከያ ማረን

አንጋጦ መትፋት መልሶ ከአፍ እዲሉ መከላከያን ወግቼ በህዝብ የተመረጠን መንግስት እገለብጣለሁ የሚለው ጃውሳው ቡድን አሁን መዋቅሩ ሁሉ ፈራርሶ የሚበላው እስኪያጣ ድረስ ከማህበረሰቡ እየተገለለ ይገኛል።

ኢትዮጵያን ለማፍረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎችን አደራጅቶ መከላከያን ለመውጋት የሞከረው ጃውሳው ቡድን አሁን ላይ ብትንትኑ መውጣቱ ተረጋግጧል ግማሹ ከድቷል ግማሹ እጅ ሰጥቷል የቀረው ተደምስሷል።

እንኳን አንድ የመንደር ሽፍታ ይቅር እና ማንኛውም የተደራጀ ሓይል መከላከያን ሊያሸንፍ አይችልም።



02/11/2023
የዘንዶ ቆዳ በመያዝና ሀሰተኛ የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን በማተም ወንጀል የተጠረጠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ክስ ተመሰረተየዘንዶ ቆዳ እና የተፈጥሮ ማዕድን በመያዝ እንዲሁም ሀሰተኛ የውጭ ሀገራ...
02/11/2023

የዘንዶ ቆዳ በመያዝና ሀሰተኛ የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን በማተም ወንጀል የተጠረጠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ክስ ተመሰረተ

የዘንዶ ቆዳ እና የተፈጥሮ ማዕድን በመያዝ እንዲሁም ሀሰተኛ የውጭ ሀገራት ገንዘቦችን በማተም ወንጀል የተጠረጠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ክስ ተመሰረተ።

ክሱ የተመሰረተው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ልደታ ምድብ 14ኛ ልዩ ልዩ ወንጀል ችሎት ሲሆን÷የፍትሕ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ ተደራራቢ ክሶችን አቅርቦባቸዋል።

ክስ የቀረበባቸው ተከሳሾችም 1ኛ አቦየም መኮምቢሊ ጂ፣ 2ኛ ርሆቦት ሮሄ ፣ 3ኛ ዳውድ ሲዲኪእና ኪምቢ ኪምቢ ጆን ይባላሉ።

በተከሳሾቹ ላይ የቀረበው አንደኛው ክስ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና አንቀጽ 356 ላይ የተደነገገውን ድንጋጌ ተላልፈዋል በሚል ነው።

ተከሳሾቹ ተከራይተው በሚኖሩበት በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ልዩ ቦታው ቦሌ አዲስ ት/ቤት አካባቢ ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓ.ም በፀጥታ አካላት በተደረገ ክትትል በጋራ በመሆን ሀሰተኛ ገንዘብ ለመስራት የሚያገለግሉ መሳሪያዎች፣ የተለያዩ ኬሚካሎች እና ሀሰተኛ ገንዘብ መስሪያ ወረቀቶችን በመጠቀም ሀሰተኛ የውጭ ሀገራት ገንዘቦች አመሳስለው በመስራት ላይ እያሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸው በክሱ ተመላክቷል፡፡

በዚህም ዐቃቤ ሕግ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተሳታፊ በመሆን ሀሰተኛ ገንዘብ የመስራት ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።

በ2ኛው ክስ ላይ ደግሞ ተከሳሾቹ አንድ የብር ማተሚያ ማሽን ፣ ሀሰተኛ ገንዘብ ለመስራት የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ ኬሚካሎች ፣ በዶላር ቅርፅ የተቆረጠ 55 ወረቀት፣ ጥቁር በዶላር ቅርፅ የተቆረጠ 27 ወረቀት፣ የሀሰት ገንዘብ ማዘጋጃ ኦሬንጅ ወረቀት እና ሌሎች 109 ወረቀት እንዲሁም22 የዶላር ማሸጊያ ፕላስቲክና ዶላር ለማተም የሚያገለግሉ መሳሪያዎች ተከሳሾቹ በጋራ ሲጠቀሙባቸው መገኘታቸው ተጠቅሷል፡፡

በዚህም ዐቃቤ ሕግ ሀሰተኛ ነገሮችን ለመስራት የሚያገለግሉ መስሪያ እና መሳሪያዎች መያዝ ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል፡፡

በተጨማሪም ተከሳሾቹ በጋራ በመሆን ምንም አይነት ፈቃድ ሳይኖራቸው 71 ነጥብ 15 ግራም የሚመዝን ካኦሊናይት የተፈጥሮ ማዕድን በመኖሪያ ቤት ውስጥ ይዘው የተገኙ መሆኑን የጠቀሰው ዐቃቤ ሕግ÷ ፈቃድ ሳይኖረው የተፈጥሮ ማዕድን መያዝ እና የአዋጁን ድንጋጌዎች መተላለፍ ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል፡፡

በሌላ በኩል በሁሉም ተከሳሾች ላይ በተደረገው ማጣራት የፀና የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሀገር ውስጥ ሲኖሩ የተያዙ መሆናቸው በክሱ ተገልጾ÷ የፀና የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖር በሀገር ውስጥ የመኖር ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል።

በተጨማሪም ፈቃድ ሳይኖራቸው የዱር እንስሳት ቆዳ ማለትም የዘንዶ ቆዳ ይዘው የተገኙ በመሆኑ በፈፀሙት ምንም አይነት ፈቃድ ሳይኖር የዱር እንስሳት ውጤቶች ይዞ መገኘት ወንጀል ክስ ተከሰዋል።

በተጨማሪም ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች በተጠቀሰው ተከራይተው ይኖሩበት በነበረው መኖሪያቸው ውስጥ አጠቃላይ 2 ሺህ 705 ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር የተገኘ በመሆኑ÷ ሀሰተኛ ገንዘብ ይዞ የመገኘት ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል።

አራተኛ ተከሳሽ በአራተኛ ክስ ላይ ብቻ የተጠቀሰ ሲሆን÷ ቀሪዎቹ ግን በሁሉም ክሶች ላይ መካተታቸው ተመላክቷል፡፡

በዚህ መልኩ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበባቸው ተደራራቢ ክሶች በችሎት እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን÷ ተከሳሾቹ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል።

ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ ላይ የቀረበው ተደራራቢ ክስ መሆኑን እና የተፈጸመው ወንጀል የሀገር ኢኮኖሚን የሚጓዳ ተግባር መሆኑን ጠቅሶ÷ የዋስትና ጥያቄያቸውን በመቃወም ተከራክሯል።

በተጨማሪም ተከሳሾቹ ቋሚ አድራሻና የፀና የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው በመሆኑ በዋስ ቢወጡ የዋስትና ግዴታቸውን አክብረው ላይቀርቡ ይችላሉ በማለት የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ እንዲደረግ ጠይቋል።

የግራ ቀኙን ክርክር የተከታተለው ችሎቱ መርምሮ ዋስትናው ላይ ብይን ለመስጠት ለፊታችን ጥቅምት 26 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ግብጽ ለሲናይ በረሀ ስትል ሚሊዮኖችን እንደምታሰልፍ ገለጸችየእስራኤ-ሀማስ ወይም ፍልስጤም ጦርነት ከተጀመረ 25ኛ ቀኑ ላይ የሚገኝ ሲሆን አሁንም እልባት አልተገኘለትም።የዓለምን ትኩረት የሳበ...
02/11/2023

ግብጽ ለሲናይ በረሀ ስትል ሚሊዮኖችን እንደምታሰልፍ ገለጸች

የእስራኤ-ሀማስ ወይም ፍልስጤም ጦርነት ከተጀመረ 25ኛ ቀኑ ላይ የሚገኝ ሲሆን አሁንም እልባት አልተገኘለትም።

የዓለምን ትኩረት የሳበው ይህ ጦርነት በየዕለቱ አዳዲስ ክስተቶችን እያስተናገደ ሲሆን እስራኤል በፍልስጤማዊያን ላይ እያደረሰች ያለውን ጥቃት እንድታቆም ግፊቱ ቀጥሏል።

የእስራኤል ደህንነት 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ፍልስጤማዊያንን ወደ ሲናይ በረሀ የማዛወር እቅድ እንዳለው ግብጽ አስታውቃለች።

የግብጽ ጠቅላይ ሚንስትር ሞስጠፋ ማድቡሊ እንዳሉት "ግብጽ ለሲናይ በረሀ ስትል ሚሊዮኖችን ታሰልፋለች" ብለዋል።

እንደ አልአረቢያ ዘገባ ግብጽ የእስራኤል ደህንነትን እቅድ ፈጽሞ አትቀበልም ያሉ ሲሆን ለሲናይ በረሀ ስትልም ሚሊዮን ዜጎቿን ለማሰለፍ እና ለመገበር ዝግጁ ማለታቸው ተገልጿል።

👉👉👉👉የተማሪዎች ምደባትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥቷል።ማብራሪያ ፦- ...
01/11/2023

👉👉👉👉የተማሪዎች ምደባ

ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ማብራሪያ ፦

- የምደባ ስርዓቱ በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በመጀመሪያ የዩኒቨርስቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል።

- የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ ተማሪ ያስመዘገበውን አጠቃላይ ውጤት በምደባ ስርዓት ሂደት ውስጥ መለያ አድርጎ ይጠቀማል፡፡ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሌሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህግና ደንቦችን ባልጣሰ መልኩ ምርጫቸውን በመጠበቅ ረገድ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

- የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የቅበላ አቅም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ተማሪዎች 46 ዩኒቨርሲቲዎች ለምርጫ ቀርበውላቸዋል፡፡

- የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ የትምህርት ፕሮግራሞች እና የተመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራም መሰረት ያደረገ ነው።

- በተቋማት የጾታ ተዋጽኦን ለመጠበቅ በሚኖረው የምደባ ስርዓት የጾታ ተዋጽኦና ሚዛን እንዲጠበቅ ተደርጓል።

- የምደባ ስርዓቱ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚመደቡ ተማሪዎችን ተዋጽኦ በጠበቀ መልኩ እንዲሆን ያግዛል፡፡ ይህም ከአንድ ት/ቤት የወጡ ተማሪዎች በአንድ ዩኒቨርሲቲ ወይም ፕሮግራም ውስጥ እንዳይታጨቁ ይደርጋል፡፡

- የምደባ ስርዓቱ ተማሪዎች ያስመዘገቡትን ውጤት ታሳቢ ያረገ ሲሆን ይህም ተመሳሳይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች አንድ ላይ እንዳይመደቡ በማድረግ የተለያየ ችሎታና ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎችን ቀላቅሎ ለማስተማር ያግዛል፡፡

- የምደባ ስርዓቱ እንደ ወሊድ ያሉ ልዩ ሁኔታዎችን ያማከለ ነው፡፡ በመሰል ሁኔታ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመቀጠል የሚቸገሩ ከሆነ ትክክለኛ ለውጥና ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡

- በምደባ ወቅት የጤና ችግር ኖሮባቸው ትክክለኛ የሕክምና ማስረጃ ላላቸው ተማሪዎች ምደባው በተለየ መልኩ ሊታይ ይችላል፡፡

• አስፈላጊ ማስረጃዎች፡ ከትምህርት ቤታቸው የድጋፍ ደብዳቤ እና ከህዝብ ጤና ተቋማት የህክምና ምስክር ወረቀት በሶስት ዶክተሮች እና በህክምና ዳይሬክተሩ የጸደቀ።

- በተማሪዎቹ መካከል ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትዮች ካሉ የምደባ ስርዓቱ ከፍተኛ ነጥብ ያገኘው/ችው ተማሪ ከተመደበበት/ችበት የትምህርት ተቋም ቀሪው መንትያ ደግሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በቀጥታ ይመድባል።

- የምደባ ሲስተሙ የአካል ችግር ላለባቸው ተማሪዎች እኩል እድሎችን የሚሰጥ ሲሆን ልዩ ፍላጎቶቻቸውን እና ለምደባ መስፈርቶቻቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰራ ይሆናል።

ትምህርት ሚኒስቴር ሀሰተኛ የህክምና ማስረጃ የሚያቀርብ ተማሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከምደባ ውጭ የሚሆን መሆኑን አሳስቧል።

31/10/2023
በቅርቡ የተከበሩ ሀይማኖታዊና ባህላዊ በዓላት እንዲሁም ብሄራዊ ሁነቶችን ተገን በማድረግ ጸረ ሰላም ሀይሎች ለመፈፀም ያሴሩትን የሽብር ዕቅድ ማክሸፍ መቻሉ ተገለፀ በቅርቡ የተከበሩ ሀይማኖታዊ...
31/10/2023

በቅርቡ የተከበሩ ሀይማኖታዊና ባህላዊ በዓላት እንዲሁም ብሄራዊ ሁነቶችን ተገን በማድረግ ጸረ ሰላም ሀይሎች ለመፈፀም ያሴሩትን የሽብር ዕቅድ ማክሸፍ መቻሉ ተገለፀ

በቅርቡ የተከበሩ ሀይማኖታዊና ባህላዊ በዓላት እንዲሁም ብሄራዊ ሁነቶችን ተገን በማድረግ ጸረ ሰላም ሀይሎች ለመፈፀም ያሴሩትን የሽብር ዕቅድ ማክሸፍ መቻሉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ዋና ሰብሳቢ እና የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት በ2016 ዓ.ም በተከታታይ የተከበሩ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ክብረ በዓላት እንዲሁም ብሄራዊ ሁነቶች በሰላም እንዲጠናቀቁ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱት የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተለያዩ ክፍሎች የምስጋናና ዕውቅና ፕሮግራም አካሄዷል።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ዋና ሰብሳቢ እና የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ እንደገለጹት የአዲስ ዓመት መባትን ተከትሎ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በአደባባይ በተለያዩ አካባቢዎች የታደሙባቸው ኃይማኖታዊ እና ባህላዊ ክብረ በዓላት እንዲሁም ብሄራዊ ሁነቶች ተስተናግደዋል። እነዚህን ሁነቶች ለማደናቀፍ ፀረ-ሰላም ቡድኖች የተቀናጀ ርብርብ አድርገዋል ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪም የብልፅግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት ስልጠና ከተጠናቀቀ በየደረጃው ያለ ኃላፊ ሀገር ማጽናት የሚያስችለውን አቅም ያጎለብታል በሚል ስሌት ስልጠናውን ፀረ-ሰላም ቡድኖች ለማደናቀፍ በሀሰት ፕሮፖጋንዳ የተደገፈ ከፍተኛ ርብርብ አድርገው እንደነበር አመልክተዋል። ይሁንና የእነዚህን ቡድኖች ሴራ ለማክሸፍም የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አግልግሎት አመራሮችና አባላት ከመንግስት ጸጥታ ሀይሎች ጋር በየጊዜው የሚመጡ መረጃዎችን በማቀናጀት እና በመተንተን መረጃዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ የማድረግ ስራ ማከናወናቸውን አቶ ተመስገን ተናግረዋል። በዚህም የጠላት ዕቅድ እንዲከሽፍና ሀይማኖታዊ፣ ባህላዊና የተለያዩ ሁነቶች በሰላም እንዲከበሩ ተደርጓል ብለዋል።

በአማራ ክልል በፋኖ ስም የሚነግደውን ዘራፊና ጽንፈኛ ቡድን እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ደግሞ የሸኔ ሽብር ቡድን በተደጋጋሚ ኃይማኖታዊ እና ባህላዊ ክብረ በዓላት እንዲሁም ብሄራዊ ሁነቶችን ለመበጥበጥና ሁከት ለመፍጠር ጥረቶች ቢያደርጉም እንዳልተሳካለቸው የገለፁት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ዋና ሰብሳቢ እና የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ፤ የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተለያዩ ክፍሎች አመራሮችና አባላት ላደረጉት ያልተቋረጠ ድጋፍና ጥረት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው ዘራፊና ጽንፈኛ ኃይል በቅድሚያ ክልሉን ከዛም የፌዴራል ስርዓቱን ለማፍረስ ያቀደና ያለመ ኃይል መሆኑን የተናገሩት ተመስገን፤ ለዚህም ሰነድ አዘጋጅቶ እና የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ስልት ነድፎ ከተሞችን የመቆጣጠርና ሰላም የማደፍረስ እልፍ ሲልም የኢትዮጵያን ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል የተንቀሳቀሰ ቡድን መሆኑን አመልክተዋል። ሆኖም ግን ከሌሎች የፌዴራልና የክልል የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም ሰላም ወዳዱ ህዝብ ጋር በተሰሩ ስራዎች በአጠረ ጊዜ በክልሉ የነበረው የሰላም መደፍረስ ከፍተኛ መሻሻል እየታየበት መሆኑን ተናግረዋል።

የጥፋት ኃይሉ በክልሉ ውስን ቀበሌዎችና ወረዳዎች ላይ እየተሹለከለከ ወደተራ የሽፍትነትና የደፈጣ ጥቃጦች የመሰንዘር ተራ ውንብድና ውስጥ የገባ መሆኑን ጠቅሰው ለክልሉ አንጻራዊ ሰላም ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የፌደራልና የክልሉ መንግስት ፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ሌት ተቀን ለሰራችሁ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ምስጋና ይገባችዋል ብለዋል።

በአማራ ክልል አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲታወጅና የጸጥታ ችግር ሲገጥም በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰው ሽብርተኛው የሸኔ ቡድን በንፁሃን ላይ ግፍ ለመፈፀም ቢሞክርም በሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ በፌደራልና የክልሉ መንግስት ፀጥታ አካላት የማያዳግም እርምጃ እንደተወሰደበት አቶ ተመሰገን ጥሩነህ ገልፀዋል። ይህም ውጤት የተገኘው የደኅንነት እና የጸጥታ ተቋማት በጋራ ተናበው መስራት በመቻላቸው መሆኑን አብራርተዋል።

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መረጃ እንዳመለክትው ህዝቡ የራሱንና የአካባቢውን ሰላም በማስከበር ረገድ ከሀገር መከላከያን ሰራዊትና ከሁሉም ፀጥታ ኃይሎች ጎን በመቆም እያሳየ ያለውን ድጋፍ እንደተለመደው አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።

  አሸዋና ግመል ብቻ ትዝ የሚላቹ ነዎች ...አፋር...🇪🇹👌ይህ ውብ ቦታ በአፋር ክልል በዞን 3 አዋሽ ፈንታአሌ ወረዳ ዶሆ ቀበሌ የሚገኝ በዘንባባ ተክሎች የተከበበ ውብና ማራኪ የተፈጥሮ ፉ...
31/10/2023

አሸዋና ግመል ብቻ ትዝ የሚላቹ ነዎች ...

አፋር...🇪🇹👌

ይህ ውብ ቦታ በአፋር ክልል በዞን 3 አዋሽ ፈንታአሌ ወረዳ ዶሆ ቀበሌ የሚገኝ በዘንባባ ተክሎች የተከበበ ውብና ማራኪ የተፈጥሮ ፉልውሃ ሲሆን የተፈጥሮ ፉልውሃ ከመዝናኛ ባለፈ ለተለያዩ በሽታዎች ፈውስ እንዳለውም ይነገራል።

አፋርን ይጎብኙ
VISIT AFAR

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከደቡብ ኮሪያ ቹንቾን ከተማ ከንቲባ ጋር ተወያዩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከደቡብ ኮሪያ ቹንቾን ከተማ ከንቲባ ዮክ ቶንግ ሃን ጋር ውይይት ...
31/10/2023

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከደቡብ ኮሪያ ቹንቾን ከተማ ከንቲባ ጋር ተወያዩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከደቡብ ኮሪያ ቹንቾን ከተማ ከንቲባ ዮክ ቶንግ ሃን ጋር ውይይት አደረጉ፡፡

ከንቲባዋ የደቡብ ኮሪያ ቹንቾን ከተማ ከንቲባ ዮክ ቶንግ ሃን እና ከወጣቶች ዲፕሎማሲ ልዑካን ቡድናቸው ጋር የሁለቱ ከተሞች እህትማማችነት 20ኛ ዓመት አክብረናል ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

በቀጣይ በትብብር በምንሰራቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል ነው ያሉት፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ካሏት 24 እህት ከተሞች አንዷ የሆነችው ከቹንቾን ከተማ ጋር ለ20 ዓመታት የዘለቀው የእህትማማችነት ግንኙነታችንን ይበልጥ በማጠናከር የቹንቾን ከተማ ከንቲባ ዮክ ቶንግ ሃን እና የወጣቶች ዲፕሎማሲ ልዑካን ቡድንን ተቀብለን ስናስተናግድ የአዲስ አበባ ከተማን ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን የሚያልቁ ታላላቅ ስራዎችን ለመስራት የገባነውን ቃል በማደስ ለላቀ ስራ ራሳችንን በማዘጋጀት ጭምር ነው ብለዋል ከንቲባዋ፡፡

ሉሲዎች የመልስ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉበ2024 ኦሎምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከናይጀሪያ አቻው ጋር ይካሄዳል።ጨዋታው ምሽት ...
31/10/2023

ሉሲዎች የመልስ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ

በ2024 ኦሎምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከናይጀሪያ አቻው ጋር ይካሄዳል።

ጨዋታው ምሽት 12፡10 ላይ በአቡጃ አቢዮላ ስታዲየም የሚደርግ መሆኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሉሲዎቹ የመልስ ጨዋታቸውን ለማድረግ ከቀናት በፊት አቡጃ የገቡ ሲሆን በሞሽድ አቢዮላ አለም ዓቀፍ ስታዲየም ልምምድ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

በአዲስ አበባ በተደረገው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች አንድ አቻ በሆነ ውጤት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።

በከተማዋ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን በማስተዋወቅ ዘርፉን ይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀበከተማዋ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን በማስተዋወቅ ዘ...
31/10/2023

በከተማዋ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን በማስተዋወቅ ዘርፉን ይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ

በከተማዋ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን በማስተዋወቅ ዘርፉን ይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የ“አለም የቱሪዝም ቀን”ን ምክንያት በማድረግ በዘርፉ ለቱሪስት አገልግሎት ከሚሰጡ ቢጫ ቱሪስት ታክሲ ማህበራትን በማስተባበር ከመስቀል አደባባይ እስከ ሜክሲኮ ጉዞ አድርገዋል፡፡
በመርሃግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገ/እግዚአብሔር: በከተማዋ የሚገኙ ተፈጥሮአዊ ባህላዊና ታሪካዊ መስህቦች የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆኑና ቱሪስቶች በከተማዋ የቆይታ ጊዜያቸውን ለማራዘም የማስተዋወቁን ስራ ሁሉም ሊያከናውን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ከውጭ ሀገራትም ይሁን ከሀገር ውስጥ ለጉብኝት የሚገቡ እንግዶችን የሚያጓጉዙ የታክሲ ማህበራት በኢትዮጵያዊ እንግዳ አቀባበል እሴት እንግዶችን በመቀበል በዘርፉ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
ከመስቀል አደባባይ እስከ ሜክሲኮ በተደረገው ጉዞ የተሳተፉ የቱሪስት ታክሲ ማህበራት አባላትም ማህበሩ ከውጪ የሚገቡ ቱሪስቶችን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጀምሮ በመቀበል የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ምቹ በሆነ ሁኔታ እንዲጎበኙ እያደረጉ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
የቢጫ ቱሪስት ታክሲ ማህበራት ዘርፉን ለማዘመንና ለበርካቶች የስራ እድል በመፍጠር ረገድ አበርክቶዋቸው ላቅ ያለ ስለመሆኑም ተመላክቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቬንዙዌላ ቦሊቫሪያን ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ኢቫን ጊል ፒንቶን ዛሬ ማለዳ አነጋግረዋል።Prime Minister Abiy Ahmed receive...
31/10/2023

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቬንዙዌላ ቦሊቫሪያን ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ኢቫን ጊል ፒንቶን ዛሬ ማለዳ አነጋግረዋል።
Prime Minister Abiy Ahmed received Yvan Gil Pinto, the Foreign Minister of the Bolivarian Republic of Venezuela earlier this morning.

በበቆሎ ሽፋን ካናቢስበጉምሩክ ኮሚሽን ሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አማካኝነት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 ኦሮ 60116 የጭነት ማመላለሻ አይሱዙ ተሸከርካሪ በቆሎን ሽፋን አድርጎ በውስጡ ካናቢስ /ሃሺሽ...
31/10/2023

በበቆሎ ሽፋን ካናቢስ
በጉምሩክ ኮሚሽን ሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አማካኝነት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 ኦሮ 60116 የጭነት ማመላለሻ አይሱዙ ተሸከርካሪ በቆሎን ሽፋን አድርጎ በውስጡ ካናቢስ /ሃሺሽ/ የተባለውን አደንዛዥ እጽ ግምታዊ ዋጋው ብር 6.6 ሚሊየን የሚሆን በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን ሁለት ተጠርጣሪዎችም በህግ ቁጥጥር ሥር ውለዋል ፡፡
በተመሳሳይ 18/02/2016 ዓ/ም መነሻውን ጅንካ መስመር ያደረገ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ.አ A16682 ኤፍ.ኤስ.አር የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪ ግምታዊ ዋጋቸው ብር 13 ሚሊየን 980ሺ የሚያወጡ የተለያዩ ብዛት ያላቸውን በተን የስልክ ቀፎዎች በሕገወጥ መንገድ ሲያንቀሳቅሱ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል ።
በወር ውስጥ በኬላ ፍተሻ ብቻ ግምታዊ ዋጋቸው 6ሚሊየን 325ሺ 340 ብር የሆኑ የተለያዩ አዳዲስ አልባሳት ፣ የሞተር ሳይክል መለዋወጫዎች ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ሌሎች እቃዎች፤ በአርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ ፖሊስ ግምታዊ ዋጋቸው 9ሚሊየን 521ሺ 530 የሚገመት አዳዲስ አልባሳት፤ የተልተሌ ወረዳ ፖሊስ ግምታዊ ዋጋቸው 1ሚሊየን 087ሺ 900 ብር ብዛት ያላቸው የሞተር ሳይክል መለዋወጫዎች እና የእንስሳት መድሀኒት እንዲሁም የሰው መድሀኒቶች፤ በበረራ የፌዴራል ፖሊስና የጉምሩክ ሰራተኞችና አመራሮች በጋራ በመሆን ደግሞ ግምታዊ ዋጋቸው ብር 8ሚሊየን 390ሺ 700 ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን እንዲሁም የኮንሶ ዞን ፓሊስ በተሰጣቸው ጥቆማ መሰረት ግምታዊ ዋጋቸው 521ሺ 180ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ክትትል በማድረግ እና በመያዝ ገቢ አድርገዋል ።
(የገቢዎች ሚኒስቴር)

በእንጦጦ ፓርክ ዙሪያ የውንብድና ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንጦጦ ፓርክ ዙሪያ የቅሚያ እና የውንብድና ወንጀል ሲፈፅሙ በነበሩ ሁለት ግለሰቦች ላይ...
31/10/2023

በእንጦጦ ፓርክ ዙሪያ የውንብድና ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንጦጦ ፓርክ ዙሪያ የቅሚያ እና የውንብድና ወንጀል ሲፈፅሙ በነበሩ ሁለት ግለሰቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ መተላለፉን የሽሮሜዳ አካባቢ ጣቢያ ፖሊስ ገለፀ፡፡
የጣቢያው የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ፍቅሩ ማሞ እንደገለጹት÷ ዮናስ ዳኜና ለጊዜው ያልተያዘው ግብረአበሩ በ2015 ዓ.ም በተለያዩ ቀናት በፓርኩ ዙሪያ በሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ላይ የኃይል ተግባር በመጠቀም የቅሚያ እና የውንብድና ወንጀል በመፈፀም ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ የተለያዩ ንብረቶችን ሲዘርፉ ቆይተዋል፡፡
ወንጀል ፈፃሚዎቹ ፍርድ ቤት ከቀረቡ እና የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸው ከእስር ከተለቀቁ በኋላ በቀጠሮ ቀን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ መቅረታቸውንም አመላክተዋል፡፡
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉለሌ ምድብ ችሎት ሁለቱም ተከሳሾች በተደጋጋሚ ቀጠሮ ሊቀርቡ ባለመቻላቸው በሌሉበት እያንዳንዳቸው በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አሳልፏል ብለዋል፡፡
ፖሊስም ፍርደኞቹን አፈላልጎ ለማረሚያ ቤት ለማስረከብ ባደረገው ጥረት ዮናስ ዳኜ የተባለው ግለሰብ ጥቅምት 18 ቀን 2016 ዓ.ም በቁጥጥር ስር መዋሉ እና ግብረአበሩን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በእንጦጦ ፓርክ ለመዝናናት የሚመጡ ግለሰቦችም የደኅንነት ስጋት እንዳይሰማቸው ፖሊስ የመከላከል አቅሙን በማሣደግ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ እና ቀደም ሲል አልፎ አልፎ ይፈፀሙ የነበሩ ወንጀሎችን ማስቆም መቻሉንም አረጋግጠዋል።

Address

Adds Ababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EthioXpress posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share