አዱክ ሚዲያ/aduk media

አዱክ ሚዲያ/aduk media ይህ ፔጅ አዳዲስ መርጃዎች የምንልከው ፔጅ ነዉ ። ምርጥ አገልግሎት እዲሁም ዩቲዩብ እና አዳዲስ ግሩፕ /ቻናል ማስተዋወቅ ይችላሉ

12/01/2024
21/10/2023

19/10/2023

ለኔ ምን ግዜም ምርቱ ፊልም
#ማንዴ #1
💪💪💪😍😍😍

06/08/2023

MORE
ግብረሰዶማዊነትን
እንቃወማለን
ከ🇪🇹 እናጠፋለን
❌❌❌❌❌❌

05/08/2023

ግብረሰዶማዊነትን
እቃወማለሁ
❌❌❌

የአዊ ብሔረሰብ ህዝብን ወክለው ለሸዳይ በዓል ወደ ዋግ የተጓዙት አቶ እንግዳ ደኛው የዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ አቶ ላይኩን ሲሳይ ባቱ መምሪያ ኃላፊ፣የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ንፁህ...
22/08/2022

የአዊ ብሔረሰብ ህዝብን ወክለው ለሸዳይ በዓል ወደ ዋግ የተጓዙት አቶ እንግዳ ደኛው የዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ አቶ ላይኩን ሲሳይ ባቱ መምሪያ ኃላፊ፣የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ንፁህ ሽፈራው፣ ያራጋል ያያህ የፋግታ ለኮማ ወረዳ አስተዳደሪ ፣የአዊ ባህል አምባሳደር ወ/ሪት ቅድስት ብርሀኑ እና ሌሎችም ጋዝጋብላ ወረዳ አስ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።
መልካም በዓል

ወዝ ዳህነ ተትርኑ
አዲናስ

01/08/2022

💪💯 የብስለት ልህቀት!

💪💯 እድገትና ብስለት በህይወት መንገድ የምናመጣው ለዉጥ ነው ።
! የብስለት ልህቀት በሂደት የሚመጣ ነው ሆን ብለህ ባትኖረውም በምታልፋቸው የህይወት መንገዶች እያዳበርከው የምትመጣው ነው ። ለእልህ ቦታ አይኖርህም ፤ ጭፍን ጥላቻ አይኖርህም ፤ በቀል አይታይህም ፤ በምትኩ የእራስህ እድገት ላይ ፣ የእራስህ ጥንካሬ ላይ ታተኩራለህ ። የተዉህን መተው ፣ የረሱህን መርሳት ላንተ ቀላል ነው ። የፍቅርን ጥግ ከእራስህ ጋር ታሳልፋለህ ፣ ቀዳሚው መልካምነት ሌላውን በማይጎዳ መልኩ ለእራስህ ይሆናል ።
የማያነብ ሰው፤ አልተማረም ከምንለው፤ እንዴት ለይቼ አየዋለሁ፤ ይለናል ።
ራስን የማስተዳደር ጥበብ✍️
አዎ! የእውቀት ብዛት ብስለት አይሆንም፤ አዋቂም አያደርግም ፤ የእድሜ መግፋት ብስለትን አያመጣም ። ከእድሜው በላይ የበሰለ ፣ ከእድሜው በታች የወረደም ሰው አለና ። ብስለት ጥበብ ነው ፤ ብስለት የህይወት ሚስጥር ነው ፤ ብስለት ለጋሽና ቅንነት ነው፤ሰው ሁኖ ለሌሎች የመኖር ዘይቤ ነው ። ብስለት ጥሩ ተማሪ ያድጋል ፤ አስተዋይ ሰው ይቀየራል ፤ ብለሃትን ይወርሳል ፤ ብስለትን ይላበሳል ፤ እራሱን ይመራል ፤ የአቋም ሰው ይሆናል ።
በማስተዋል❤
ደግነትና ፍቅርን
ለሌሎች እንካፈል
መልካም ምሽት 🌆

31/07/2022

Why 🤔

"ሻደይ ኢትዮጵያ በግንባር፤ ለድል፣ ለአንድነትና ለክብር"ለሁለት ዓመታት በተለያዬምክኒያት ተቋርጦ ለነበረው የ2014 ዓ.ም ሻደይ የልጃገረዶች ጨዋታ አከባበር ከዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር...
31/07/2022

"ሻደይ ኢትዮጵያ በግንባር፤ ለድል፣ ለአንድነትና ለክብር"
ለሁለት ዓመታት በተለያዬ
ምክኒያት ተቋርጦ ለነበረው የ2014 ዓ.ም ሻደይ የልጃገረዶች ጨዋታ አከባበር ከዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ም/ቤት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

የሻደይ በዓል ከነሀሴ 16-21 በየአመቱ ይከበራል። በአሉ ለዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ልጃገረዶችም ሆነ ለመላው የዋግ ኽምራ ህዝብ ልዩ ትርጉም ያለው ባህል ነው።

የዋግ ኽምራ ህዝብ ከጥንት ማለትም ከኖህ ጀምሮ እያከበረ የመጣው ታላቅና ውብ ባህሉ ነው። ይህ ጨዋታ ዛሬ ልጃገረዶች በድምቀት የሚጫወቱትና የሚያከብሩት ይሁን እንጂ ሰረ-መሰረቱ ሲታይ ሀይማኖታዊ ውክልና ያለው እንደሆነ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ አባቶች ያስቀምጣሉ።

ከጊዜ በኋላ ግን በሙሉ በሙሉ ወደ ትልቅ ባህልነት የተለወጠ ድንቅ የዋግ ኽምራ ባህል ሆኗል። የዋግ ኽምራ ልጃገረዶች ወርሀ ነሀሴ እንደገባ ሻደይን እንዴትና በምን ሁኔታ እንደሚያከብሩ ዝግጅ ያደርጋሉ። ያኔ የት ሄድሽ ወዴት ጠፋሽ ብሎ የሚቆጣ አባት የለም፤ ምክኒያቱም የነጻነት ጊዚያቸው ነው።

ምዕራባውያን የሚመጻደቅበት "የሴቶች ነጻነት ከኛ በላይ ላሳር የሚሉበት"፣ አለም ሳይነቃ ሴቶች ከማጀት ወጥተው አደባባይ የወጡበት፣ የክብራቸውና የነጻት ቀናቸው የሆነው "ሻደይ" በዋግ ኽምራ የሚከበረው ነው።
በዓሉ የነጻነታቸው ቀን ብቻ ሳይሆን የነጻነታቸው መሰረትም ነው፤ አንድ ቀን ወይም በአንድ ወቅት ብቻ አክብረውት የተወሰነ ነጻነት የሚያገኙት ሳይሆን መሰረት የጣሉበት የልዕልናቸው ቀንዲል ነው።

እናም ይህ ውብ ባህል፣ ሲከበር በግንባር "ከባላንጣ" ጋር ተፋጠን ያለንበት በመሆኑ የዘንድሮ ሻደይ ከዚህ ቀደም ሲከበር ከነበረው ልዩ ትርጉም ተሰጥቶት "በፌድራል ደረጃ ይከበራል"። ለዚህም የብሄረሰብ አስተዳደሩ በሁለንተናዊ ተግባራት ቅድመዝግጅት እያደረገ ነው።

የዋግ ኽምራን ህዝብ አሁን ያለበትን ሁነት የሚያክም፣ ብርሀን ከፊት እንዳለ አመላካችና ወደ ብርሀኑ የሚወስድ ምህዋር እንደሆነ ታስቦ የሚከበር ነው።

ሻደይ በዋናነት የዋግ ልጃገረዶች ባህል ይሁን እንጂ፣ መላው ኢትዮጵያውያን የሚጫወቱበት የጋራ ኩራታችን ነው፤ በተለይ የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት በዋግ ግንባር ሆኖ ሻደይ ሲከበር ልዩ ስሜት አለው።

"ሻደይ ኢትዮጵያ በግንባር፤ ለድል፣ አንድነትና ለክብር" በሚል መሪ ሀሳብ የሻደይ በዓል ይከበራል። ይህ የሆነበት ምክኒያት ሀገራዊና አሁናዊ አንድምታውን ያገናዘበ እንዲሆን ታስቦ ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ድል ትሻለች፣ በአንድነትና በአብሮነት እንዲሁም በክብር የምትኖር ሀገር እንድትሆን የዋግ ኽምራ ኽዝብ ምኞት ነው። አንድነት ከሌለ ሀገር የለም፤ ፍቅር ከሌለ አብሮነት አይታሰብም።

ለዚህ አብነት የሚሆነው የሻደይ ጨዋታ ነው። የሻደይ ጨዋታ በተናጠል የሚጫወቱት አይደለም፤ በጸብ መሀከል የሚከወን ክዋኔም፣ ከበራም አይደለም። ልጃገረዶቹ በአንድነት ተሰባስበው በአንድነት ወጥተው በጋራ ሜዳ ላይ ይጫወታሉ። በአንድ ገበታ ላይ ማዕድ ይጋራሉ። ይህ ሳይሆን ቢቀር አንዲት ሴት ብቻዋን የምትጫወትበት ወኔም ሞራልም የላትም።

እኛ ኢትዮጵያንም የመጨዋቻ ሜዳችን በፍቅር፣ በአብሮነት ካልተጫወትን ለአንድ ሰው የምትሆን ሀገር ስለሌለች ሁላችንም በጋራ ሜዳችን ተቻችለን ሳይሆን ተከባብረንና ተዋደን የምንኖርባት ሀገራችን የምንጠብቅበት ተምሳሌት ነው።

እንደ ሀገር የገጠመንን ፈተና በድል ተወጥተን፣ በሻደይ ባህላችን ደምቀን እንውላለን፤ እንደ ሀገርም ሆነ እንደዋግ በግምባር ላይ ብንሆንም ባህላችንና እሴታችን መጠበቅ የግድ በመሆኑ ሻደይን እናከብራለን።
በዘንድሮ ዓመት ከሻደ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አዱክ ሚዲያ/aduk media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share