09/09/2023
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሞሮኮ በደረሰው ርዕደ መሬት የበርካታ ሰዎች ሕይወት በመጥፋቱ የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ
*************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሞሮኮ በደረሰው ርዕደ መሬት የበርካታ ሰዎች ሕይወት በመጥፋቱ የተሰማቸውን ኀዘን በመግለጽ ለሞሮኮ ሕዝብ እና መንግሥት መፅናናትን ተመኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት የኀዘን መግለጫ፣ ኢትዮጵያ በዚህ ከባድ ወቅት ከሞሮኮ ሕዝብ እና መንግሥት ጎን መሆኗን ገልጸዋል።
በሞሮኮ በደረሰ ርዕደ መሬት የሟቾች ቁጥር እስካሁን 1 ሺህ 305 መድረሱን እና 1 ሺህ 832 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።