፩ News Amharic

፩ News Amharic Voice of voice less ፡Free to write the trueth
(3)

ይህ ስለ እውነት የተከፈለ መስዋዕትነት ነው።አድርባይ ሆኖ ከውሸት ጋር ሥጋን እያደለቡ ከመኖር-ከእውነት ጋር በነጻ ህሊና ስቃይን ተሸክሞና ተጎሳቁሎ መኖር ክቡር ነው።በሆዳቸው ወድቀው ቪ 8ና...
04/12/2023

ይህ ስለ እውነት የተከፈለ መስዋዕትነት ነው።አድርባይ ሆኖ ከውሸት ጋር ሥጋን እያደለቡ ከመኖር-ከእውነት ጋር በነጻ ህሊና ስቃይን ተሸክሞና ተጎሳቁሎ መኖር ክቡር ነው።
በሆዳቸው ወድቀው ቪ 8ና የደሀ መሬት የተሰጣቸው አሳማዎች በዚህ ምስል ሢሳለቁ እያዬሁ ነው።
አንድ ሊታወስ የሚገባው ሀቅ ግን-እነ አቶ ዮሀንስ ቧያለው እና ክርስቲያን ታደለ ይህን መንገድ የመረጡት፤አሳማዎቹ በሆዳቸው ወድቀው ያገኙትን “እንሥሳዊ ዕድል”ተጠይፈው መሆኑ ነው።

አይታዟችሁ ወንድሞቻችን! ይህም ያልፋል!!

03/12/2023
ለመሰቀልም ዝግጁ ነኝ። 🙏🙏🙏❤️❤️❤️ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ :-ሁሉም  የሚፈልገውን ብቻ ሰማኝ። ሁሉም አብጠለጠለኝ። ሁሉም ስቀለው ስቀለው አሉኝ። እግዚአብሔር ይርዳኝ፣ ለመሰቀልም ዝግጁ ነኝ...
26/11/2023

ለመሰቀልም ዝግጁ ነኝ።

🙏🙏🙏❤️❤️❤️

ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ :-

ሁሉም የሚፈልገውን ብቻ ሰማኝ።

ሁሉም አብጠለጠለኝ።

ሁሉም ስቀለው ስቀለው አሉኝ።

እግዚአብሔር ይርዳኝ፣

ለመሰቀልም ዝግጁ ነኝ።

🙏🙏🙏

26/11/2023

ቬሮኒካ አዳነ በህመም ምክንያት ዝግጅቶቿን ማቅረብ እንዳልቻለች አስታወቀች።===========ቬሮኒካ አዳነ ዝግጅቶቿን በአሜሪካ በተለያዩ ከተማዎች ለማቅረብ አሜሪካ በቅርቡ መግባቷ የሚታወቅ ነ...
26/11/2023

ቬሮኒካ አዳነ በህመም ምክንያት ዝግጅቶቿን ማቅረብ እንዳልቻለች አስታወቀች።
===========
ቬሮኒካ አዳነ ዝግጅቶቿን በአሜሪካ በተለያዩ ከተማዎች ለማቅረብ አሜሪካ በቅርቡ መግባቷ የሚታወቅ ነው። ነገር ግን ባጋጠማት ህመም ምክንያት ዝግጅቷን በበቂ ሁኔታም ማቅረብ እንዳልቻለች በማህበራዊ ገጿ ላይ እንዲህ ስትል አስታውቃለች።

"NOVEMBER 25 ዳላስ ላይ ሾ እንዳለኝ አሳዉቄ ነበር; ፎቶ ላይ እንደምታዩት ከባድ ነገር ቢያጋጥመኝም ዳላስ ላይ የምትገኙ ቤተሰቦቼን ላለማስከፋት ቦታዉ ላይ ተገኝቼ ነበር; ለመዝፈን ብሞክርም ለመዝፈን አልቻልኩም ; ዳላስ የሚገኙ ኢትዮዽያዉያን እና ኤርትራዉያንም ቦታዉ ላይ መገኘቴን ብቻ ተረድተዉ መናገር ከምችለዉ በላይ ፍቅር እና ክብር ሰተዉኝ ቆንጆ ጊዜ አብረን አሳልፈናል; መጨረሻ ላይም የአቅሜን 6; 7 ዘፈን ተጫዉቼ ወርጃለዉ።

ዳላስ የምትገኙ ቤተሰቦቼ በድጋሚ ይቅርታ 🙏🏽

ስትል መልክቷን አስተላልፋለች።

ክብር!respect!
26/11/2023

ክብር!
respect!

በአልባኒያ ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የነበረው ጋናዊው አጥቂ በጨዋታ መሐል ሕይወቱ አለፈ  | በአልባኒያ ሊግ ዘጠኝ ግቦችን በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የነበረው ጋናዊው አጥቂ ራፋኤል ...
12/11/2023

በአልባኒያ ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የነበረው ጋናዊው አጥቂ በጨዋታ መሐል ሕይወቱ አለፈ

| በአልባኒያ ሊግ ዘጠኝ ግቦችን በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የነበረው ጋናዊው አጥቂ ራፋኤል ድዋሜና በጨዋታ መሐል ሕይወቱ ማለፉ ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡

ተጫዋቹ የተሰለፈበት ኢግናቲያ ክለብ ከፓርቲዛኒ ጋር እየተጫወተ ባለበት ወቀት በ23ኛው ደቂቃ አካባቢ ተዝለፍልፎ የወደቀ ሲሆን፤ አፋጣኝ የሕክምና ክትትል ቢደረግለትም በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡

ዳዋሜና ራሱን ስቶ ከወደቀ በኋላ በህክምና ባለሙያዎች እርዳታ ከሜዳ እንዲወጣ ከተደረጓ በኋላ ሕይወቱ ማለፉን ነው የአልባኒያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የገለጸው፡፡

የ28 ዓመቱ ራፋኤል ድዋሜና በስፔን፣ ስዊዘርላንድ፣ ኦስትሪያ እና ዴንማርክ ባሉ ክለቦች በመጫወት የተሳካ ጊዜ አሳልፏል።

በዚህ የውድድር ዘመን በአልባኒያ ሊግ ዘጠኝ ግቦችን በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነበር ሲሆን፤ በፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ህይወቱም ዘጠኝ ጊዜ ለሀገሩ ጋና ተጫውቷል።

ተጫዋቹ ከልብ ሕመም ጋር በተያያዘ በ2021 ከእግር ኳስ ራሱን እንዲያገል ከህክምና ባለሙያዎች ምክር ቀርቦላት እንደነበር ዶቼ ቬለ ዘግቧል፡፡

ይሔ አበበ ህዝብሚበላው በሶ አጥቶ ፣ መከራ ሲበላስናይፐር ይዟል ፣ ጩቤ ጥሎ ጫላ።ጣሳ ማጠብ ትቶ ፣ ጨቡዴ ኪስ ያጥባልሀገር ስትበለፅግይባስ ይጨልማል ፣ ሊነጋ ነው ሲባል😏😂
12/11/2023

ይሔ አበበ ህዝብ
ሚበላው በሶ አጥቶ ፣ መከራ ሲበላ
ስናይፐር ይዟል ፣ ጩቤ ጥሎ ጫላ።
ጣሳ ማጠብ ትቶ ፣ ጨቡዴ ኪስ ያጥባል
ሀገር ስትበለፅግ
ይባስ ይጨልማል ፣ ሊነጋ ነው ሲባል😏😂

ላሊበላ 💔💔💔ድምፅ ሁኑ የቅዱስ ላሊበላ ፍልፍል ውቅር  አብያተ ክርስቲያናት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ስፍራና መገለጫ ብቻ አይደለም። * የሙስሊሙም * የጴንጤውም * የካቶሊኩም  አጠቃላይ የሁሉም...
12/11/2023

ላሊበላ 💔💔💔

ድምፅ ሁኑ

የቅዱስ ላሊበላ ፍልፍል ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ስፍራና መገለጫ ብቻ አይደለም።

* የሙስሊሙም
* የጴንጤውም
* የካቶሊኩም

አጠቃላይ የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ የሆነ ከሃገር አልፎ የአለም ቅርስ ነው።

በየትም አለም ያለን የሃገራችሁ ታሪክና ቅርስ ጥቀሱ ቢባል ያለ ማቅማማት በአንደኛ ደረጃ የምንጠራው ቅዱስ ላሊበላን ነው።

እንዲሁም የምንኮራበት ማንነት ቅርሳችንና ታሪካችን ነው::

ይሄ ውቅር እንደ ቤተክርስቲያን ፈርሶ ዳግም የሚሰራ አይደለም ::

መንግስት በምንም ይሁን በምን ሁኔታ ላይ ይሄ በዓለም UNESCO የተመዘገበውን ቅርሳችን መጠበቅ ግድ ይለዋል::

ጉርሻዎች ከድሮው ጀምረን ጦርነትን የማንደግፍ እንዲሁም ወንድም ወንድሙን መግደል የለበት ብለን በአቆማችን የፀናን ነን::

እባካችሁ ታሪክ አናበላሽ
እባካችሁ 🙏

ትኩረት ላሊበላ 💔💔💔

🙏🙏🙏

''እንደ ሀገር የምንለይበትእንደ ሀይማኖት የምንባረክበትእንደ ታሪክ የምንኮራበት እንደ ህንፃ ጥበብ የምንገረምበትየላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትየትላንት አባቶቻችን ፣የዛሬ የእኛ፣የነገ ል...
12/11/2023

''እንደ ሀገር የምንለይበት
እንደ ሀይማኖት የምንባረክበት
እንደ ታሪክ የምንኮራበት
እንደ ህንፃ ጥበብ የምንገረምበት

የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት
የትላንት አባቶቻችን ፣የዛሬ የእኛ፣የነገ ልጆቻችን ታሪክ''

12/11/2023

ከእዳ ወደ ዱብ እዳ

የሆነ ጊዜ 😪😪😪😪

12/11/2023

አንዲት ባለትዳር በሎተሪ ያገኘችው ብር የግል ወይስ የጋራ ሀብት ነው❓
🤔

♥ምኑ ነው ስህተቴ ?♥ በድጋሚ የቀረበተሳሳትሽ አትበለኝ ፥ የቱ ነው ስህተቴጥበብ ነው ማርከሻ ፥ የብዕር ጥይቴ።አዎ!  መንጋማ አለ ፥ ከጥንት መሠረቱኢየሱስን አስረው ፥ በርባንን ሲያስፈቱ።...
08/11/2023

♥ምኑ ነው ስህተቴ ?♥ በድጋሚ የቀረበ

ተሳሳትሽ አትበለኝ ፥ የቱ ነው ስህተቴ
ጥበብ ነው ማርከሻ ፥ የብዕር ጥይቴ።
አዎ! መንጋማ አለ ፥ ከጥንት መሠረቱ
ኢየሱስን አስረው ፥ በርባንን ሲያስፈቱ።

ዛሬም በኔ ዘመን…..!

የመንጋ ፍርድ ነው ፥ ሀገሬን የፈታት
አዋቂ ዝም ብሎ ፥ መንጋ እየፈታታት።
በድንጋይ በርሚል ውስጥ ፥ ሺ ድንጋይ ቢቀቀል
ሺ ዘመን ተጥዶ ፥ እልፍ ዓመት አይበስል።

አገር ተረክቦ ፥ በሰፈር የኮራ
የመንጋ ፍርድ አይደል ፥ ያበቃን ለተራ?
የቱ ጋ ነው የሳትኩ ፥ አርመኝ መምህሩ
ምላስክን አጥፈኽው ፥ ሞክር በብዕሩ።
ዘመን የሰጠው ቅል ፥ ድንጋይ ቢሰብር ጣሪያ፤
ማዕዘን ተደርጎ አይሆን ቤት መሥሪያ።
ሰውነት ነው ልኩ ፥ የሰው ሚዛን ፍርዱ፣
አዋቂ እንዲበይን መንጋዎች ይውረዱ።

አሁንም እላለሁ….!

በመንጋ ተፈጭቶ ፤ በመንጋ ተጋግሮ
እልፍ ጾም አዳሪ ፥ ወና ነው ጉረሮ።
ቤት መምታት ቤት መድፋት ፥ ስንኝ መቋጠሩ
ጥበቡ ቢያቅተው፤
ቤት እያፈረሰ ፥ ሕዝብ እያስደደ
አገሩን አመሰው።
እኔ ይህንን ሰው፣
ሌላ ምን ልበለው፣
መንጋነትም ሲያንሰው።

በባዶነት ሙሌት ፥ በዘር እብሪት ታስሮ፣
ከጥበብ ጓዳ ውስጥ ፥ ከሰውነት አጥሮ።
አበውን ሲያሰደድ ፥ ሲያርድ ሲያጎሳቁል፣
አንተም መንጋ ካልሆንክ ፥ መቼም ሰው ነው አትል።

እና ምኑ ላይ ነው ፥ ብዕሬ የሳተች፣
ብሔር የነቀፈች ፥ ሕዝብን ያዋረደች?
ንገረኝ በሞቴ ፥ የመንጋው ጠበቃ
አንተም ሰው ሁንና ፥ መንጋነትህ ይብቃ!
ባለፈ ዓመት ክረምት ፣ ዛሬ አይታረስም
ጀግኖች አይጠሩም ፣ በፈሪዎቹ ስም!

@ገጣሚ - ህሊና ደሳለኝ ♥ ♥

08/11/2023

▶ በዐማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን ልዩ ልዩ ወረዳዎች ግጭቶች እንደቀጠሉ ነው

በዐማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን በተለያዩ ወረዳዎች፣ በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች እና በፋኖ ቡድን ታጣቂዎች መካከል፣ ለሳምንታት ጋብ ብሎ የቆየው ግጭት፣ ካለፈው ሳምንት ቅዳሜ ጀምሮ ዳግም ተባብሶ እንደቀጠለ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ዛሬ ቆይታ ያደረጉት፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን የጃቢ ጠህናን፣ የደጋ ዳሞት፣ ቡሬ ደምበጫ ፈረስ ቤት እና ቋሪት ወረዳ ነዋሪዎች፣ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተጀመረው ግጭት፣ እስከ ዛሬ ድረስ እንደቀጠለ ተናግረዋል፡፡

ለግጭቱ መቀስቀስ እንደ ምክንያት የጠቀሱትም፣ የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች፣ በየአካባቢው ከጀመሩት የቤት ለቤት ፍተሻ ጋራ ተያይዞ የመብቶች ጥሰት በመፈጸሙ ነው፤ ብለዋል፡፡

ዛሬ፣ ለአራተኛ ቀን የቀጠለውን ግጭት ተከትሎ፣ በየአካባቢው የንግድ እና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እንደተዘጉ መኾናቸውን፣ ነዋሪዎቹ አክለው ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ በዐማራ ክልል ሰሜናዊ ዞኖች፣ በመከላከያ ኀይሉ እና በፋኖ ታጣቂ ቡድን መካከል የተቀሰቀሰው ዐዲስ ጦርነት፣ በላሊበላ ከተማ የሚገኘውን የላሊበላ ውቅር አብያተ መቅደሶች፣ አደጋ ላይ ጥሏል፤ የሚል ስጋት በነዋሪዎች ዘንድ ፈጥሯል፤ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ አገልግሎት ሚኒስትሩ፣ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ፣ የዐማራ ክልል የሰላም ኹኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደተሻሻለ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

VOA Amharic

08/11/2023

"የአሰላው የአህያ ቄራ ሥጋውን ለአገር ውስጥ ገበያ እያቀረበ ነው" የሚለውን የሸገርን ዘገባ ካነበብኩ በኋላ በየሬስቶራንቱ የበላሁት ሥጋ ያቅለሸልሸኝ ይዟል።😁
Asaye

የተለያዩ ቴክኖሎጅዎችን መተዋወቅማወቅ /ለምትፈልጉ በዩቲዩብ ይከታተሉን!♥♥♥https://youtube.com/-dm6wf please ♥subscribe,♥Like ♥Share
01/08/2023

የተለያዩ ቴክኖሎጅዎችን መተዋወቅማወቅ /ለምትፈልጉ በዩቲዩብ ይከታተሉን!♥♥♥
https://youtube.com/-dm6wf
please
♥subscribe,
♥Like
♥Share

የተለያዩ ቴክኖሎጅዎችን መተዋወቅማወቅ /ለምትፈልጉ በዩቲዩብ ይከታተሉን!♥♥♥https://youtube.com/-dm6wf please ♥subscribe,♥Like ♥Share
01/08/2023

የተለያዩ ቴክኖሎጅዎችን መተዋወቅማወቅ /ለምትፈልጉ በዩቲዩብ ይከታተሉን!♥♥♥
https://youtube.com/-dm6wf
please
♥subscribe,
♥Like
♥Share

Share your videos with friends, family, and the world

https://youtu.be/LykjBFd3MQwSubscribe,Like &Share
01/08/2023

https://youtu.be/LykjBFd3MQw
Subscribe,Like &Share

-dm6wf This video usted to give our phone with a smart profile pictureSubscribe and Like our video &Turn on notifications for new videosFacebook : ...

Address

Addis Ababa

Telephone

+251928583575

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ፩ News Amharic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ፩ News Amharic:

Videos

Share