Gulu Updates

Gulu Updates በአካባቢያዊ ንግድ፣ፖለቲካ፣ስፖርት እና ወዘተ ላይ ሰበር ዜናዎችን፣የገፅታ ታሪኮችን እና ዝመናዎችን ለማግኘት ይከተሉን።

ባህርዳር ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ በመመለሷ መደበኛ አገልግሎቶች መሰጠት ጀምረዋል።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በባህርዳር ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት ሠላም የ...
14/08/2023

ባህርዳር ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ በመመለሷ መደበኛ አገልግሎቶች መሰጠት ጀምረዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በባህርዳር ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት ሠላም የማስከበር ስራ እያከናወነ ሲሆን ከተማዋ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ ተመልሳለች።

በዚህም ምክንያት መደበኛ አገልግሎቶች መሰጠት ጀምረዋል።

ሰራዊቱ ህዝቡን በማረጋጋትና ሰላምና ጸጥታን በመጠበቅ አለኝታነቱንና የህዝብ ወገንተኝነቱን በማሳየት የዜጎችን ደህንነት እየጠበቀ ይገኛል።

በከተማዋ የትራንስፖርትና የንግድ እንቅስቃሴ በመደበኛነት እየተከናወነ መሆኑንና በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ መኖሩን ማስተዋል ተችሏል።

የከተማዋ ነዋሪዎችም በየቤተ ዕምነታቸው የአምልኮ ስርአታቸውን ፈጽመው በሰላም ወደየመጡበት ሲመለሱ መመልከት ተችሏል።

ከተማዋ ወደ ሰላማዊ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ በመግባቷ ጸጥታዋም እየተጠናከረ መጥቷል።

የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ያስቀመጣቸው ትዕዛዞችና ክልከላዎች እየተተገበሩ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ህግን፣ ስርዓትንና ሞራልን መሰረት በማድረግ በዘራፊው ቡድን ላይ በወሰደው ርምጃ በአማራ ክልል ዋና ዋና ከተሞችና አካባቢዎች ወደ ሰላማዊ ሁኔታ መመለሳቸውን የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ መግለጹም ይታወሳል።

በዚህም በባሕር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን፣ ላሊበላ፣ ጎንደርና ሸዋሮቢት አካባቢ የህዝቡን ሠላም በማወክ የተሰባሰበው ዘራፊ ቡድን ላይ አስፈላጊውን ርምጃ በመውሰድ ከተሞቹን ማረጋጋት መቻሉን ገልጿል።

የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምርያ ዕዝ የክልሉን ሰላም በአጭር ጊዜ ወደነበረበት ለመመለስ የመጀመሪያ ምዕራፍ ስራውን በስኬት ማጠናቀቁንና የሁለተኛ ምዕራፍ ስራዎቹን እየተገበረ መሆኑንም እንዲሁ።

የሚያከናውናቸውን ተግባራትና የሚገኙ ውጤቶችን በቀጣይ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግና ህብረተሰቡ የህግ አስካባሪ አካላት ተልዕኳቸውን በስኬት እንዲወጡ ተገቢውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝም ገልጿል።

በሲዳማ ክልል 2016 በጀት ዓመት ውጤታማ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉበት ይሆናል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ አስታወቁ። በክልሉ የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም የሚ...
14/08/2023

በሲዳማ ክልል 2016 በጀት ዓመት ውጤታማ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉበት ይሆናል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ አስታወቁ።

በክልሉ የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም የሚገመግምና የ2016 በጀት ዓመት እቅድ ላይ የሚመክር መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት በክልሉ በ2015 በጀት ዓመት በተለያዩ መስኮች አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።

በተለይም በግብርና፣ በእንስሳት ልማት፣ በጤና፣ በትምህርትና ሌሎች ማህበራዊ ዘርፎች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰዋል።

በ2016 በጀት አመት በዘርፎቹ የተመዘገቡ ውጤቶች ተጠናክረው የሚቀጥሉበት እንደሚሆን አመላክተዋል።

በሌላ በኩል በክልሉ የዝናቡ ወቅት ቀደም ብሎ በመጀመሩ በመሠረተ ልማት ሥራዎች ላይ በሚፈለገው ልክ ሥራዎች እንዳልተከናወኑ ጠቁመው በ2016 በጀት ዓመት ያልተጠናቀቁ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ አክለውም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአገልግሎት አሰጣጥ የተገልጋዩን እርካታ በማረጋገጥ ረገድ ክፍተቶች መኖራቸውን አመልክተዋል።

በተያዘው 2016 በጀት ዓመት በዘርፉ ጉድለቶችን በመለየት ለማስተካከል እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

መድረኩ ለአምስት ቀናት እንደሚካሄድ ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሰበር ዜና
12/08/2023

ሰበር ዜና

10/08/2023

ኢትዮጵያ ከተለያዩ አገራት ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ትሰራለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር |

10/08/2023

ኢትዮጵያ በባለብዙ ወገንና በሁለትዮሽ ግንኙነት ውጤታማ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ አከናውናለች-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር |


10/08/2023

Ethiopia Live News |

09/08/2023

አዲስ ነገር – የቻይናው የመከላከያ ሚኒስትር የቻይና እና የአሜሪካ ጦርነት ዓለም አይታው የማታውቀው የከፋ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ሲሉ አስጠነቀቁ.

Address

Kebele 14-Nov, 200/1
Addis Ababa
1165

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gulu Updates posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gulu Updates:

Videos

Share