Ethio_sweden

Ethio_sweden what is new

16/12/2023
21/09/2023

አራቱ የጃውሳ አዳሪዎች

የጃውሳ ግርግር ሌላ ምንም ባያደርግ እንኳን ለአምስት አካላት የሥራ ዕድል ይፈጥራል።
1.ሞጭልፎ አደሮች፦ ለትግሉ የድጋፍ ቻፕተር አቋቁመናል ይሉና በአዳራሽና በጎ ፈንድ ሚ ብር ይሰበስባሉ። ኩርማኗን ይልኩና በቀረው ሰቨን ኢለቨን፣ ነዳጅ ማደያ፣ የሐበሻ ሱቅ፣ ጋራጅ፣ ይከፍታሉ። ሀገር ቤት ቤት ይገዛሉ። የቅንጅት ጊዜ እንዲህ ነው የሆነው።
2.አውርቶ አደሮች፦ መረጃ እንሰጣለን፣ እንተነትናለን፣ እናጋልጣለን ይሉና ሌላ ጊዜ ሞክረው የከሸፈባቸውን ሚዲያ ይከፍታሉ። ዓላማቸው ግን የዪቱዩብ ገንዘብ መሰብሰብ ነው። ጃውሳ በአንድ ጥይት አራት ብርጌድ ድል አደረገ፤ በወንጭፍ አውሮፕላን ጣለ፤ በቀስት ሄሊኮፕተር ማረከ፤ በዱላ ድሮን አወረደ - እያሉ የቡና ቤት ሥዕል ይፈጥራሉ።
3.መሥርቶ አደሮች፦ ትግሉ የፖለቲካ አመራር ያስፈልገዋል ይሉና ፋአፓ፣ አሕፓ፣ ማሕፓ፣ የሚባሉ ፓርቲዎች ያቋቁማሉ። ከብዛታቸው የተነሣ ተጣመርን፤ ተቧደንን፤ ተጫፈርን የሚሉ መግለጫዎች ይበዛሉ። ከዚያ በየቦታው ሕዝብ እየሰበሰቡ ይደሰኩራሉ። ከተገኘም ፍራንካ ይሞጨልፋሉ። ካልተገኘም ለአሳይለም የሚሆን ኬዝ ይሸጣሉ።
4.መርቶ አደሮች፦ የጃውሳ ትግል በእኔ ነው የሚመራው የሚሉ ከትከሻ ሰፋ፣ ከሆድ ገፋ፣ ከጭንቅላት ሾጠጥ፤ ከአፍ ሞጥሞጥ ያሉ ሊቀ መንበሮች እንደ አሸን ይፈላሉ። ቀን ቀን ታክሲ ይሠራሉ፤ ሌሊት በሕልማቸው አራት ኪሎ ያድራሉ። የሥልጣን ንቃቃት እንዳይገላቸው በሕልማቸው የሥልጣን ቅቤ ይጠጣሉ።



04/09/2023
14/08/2023

ለህዝብ ጥቅም ሲባል

በአማራ ክልል የአቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ከሁሉ በላይ ክልሉ እንዲረጋጋ እና ወደ አስተማማኝ ሰላም እንዲመለስ ያደርጋል።

#ጃውሳውንም ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የህብረተሰቡን ሰላም የማያውክበት ደረጃ ላይ ለማድረስ እና የህግ ተጠያቂነትን ለማስፈን ያለው አማራጭ የአስቸኳይ ጊዜ አውጁ ነው።

ጊዜው ክረምት እንደመሆኑ እና ገበሬ የእርሻ ስራውን የሚሰራበት እንደመሆኑ ካለው ሀገራዊ እና አለማቀፋዊ ሁኔታም አንጻር የክልሉን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ወደ ተረጋጋ ሁኔታ ለመመለስ ያአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።

#ጃውሳው የአማራን ክልል ከሌሎች ክልሎች ጋር በማጋጨት ክልሉ እንዳይረጋጋ በማድረግ የዘረፋ ስራውን ለመስራት የሚሄድበትን ርቀት ባሳለፍናቸው ጥቂት ቀናት ማየት ችለናል።

#ጃውሳ

27/06/2023
13/05/2023
25/02/2023

በጋራ ለማደግ በሀሳብ የበላይነትና በሚዛናዊ እይታ መዳኘት ያሻል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ብዝሃነቶች የገነቧት ሀገር ናት። የበርካታ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሀገር የሆነችዉ ኢትዮጵያ ባህሪዋን የሚመስል የፖለቲካ እይታና ሚዛናዊነትን የተላበሰ ቅኝት ትሻለች።

ዘርፈ ብዙ ብዝሃነቶች በገነቧት ኢትዮጵያ ልዩነቶቹን የተቀበለና ያከበረ አማካይ የፖለቲካ ሀሳብና አስተሳሰብን ማስፈን ሀገር ግንባታዉን በፅኑ መሠረት ላይ ለመትከል ጠቃሚ ነዉ።
በኃይልና በሴራ ፖለቲካ ጫና ለመፍጠር ከመሞከር ይልቅ በሀሳብ ገበያና በሚዛናዊነት መዳኘት ዘመናዊነት ነዉ።

ከቀኝና ከግራ ዘመም የጠርዝ የፖለቲካ አስተሳሰብ ችኮነትና ከፅንፈኝነት ይልቅ ለኢትዮጵያና ለህዝቦቿ ነባራዊ ሁኔታ ቅርብ የሆነ ፣ ከብዝሃነት ጋር የተስማማ ፣ ተፈፃሚ ሊሆን የሚችልና ዉጤት የሚያስገኝ አማራጭ መከተል ተገቢ ነዉ።

ብዝሃነትን ለማስተናገድም ይሁን ፍትሃዊ መቻቻልን ለማስፈን ፉክክር እና ትብብር ሚዛናቸውን ጠብቀው በሀሳብ የበላይነት እና በሚዛናዊነት እንዲዳኙ ማድረግ ይጠበቃል ።
የአገር ግንባታዉን ሂደት የተሳካ ማድረግ የሚቻለዉ ከጠርዝ ወደ መሃል በሀሳብ መንሸራሸር ሲቻል ነዉ ። የፖለቲካ ሜዳዉ ተዋናዮች በተለይም የፖለቲካ እና የሙያ ሊሂቃን ለሀሳብ የበላይነት እና ለሚዛናዊ እይታ መጠናከር የበኩላቸውን ማበርከት ይጠበቅባቸዋል ።
Oromia Prosperity Party / OPP /

01/02/2023
01/02/2023
22/12/2022

ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እና ለአገራዊ አንድነት ተጠናክሮ መውጣት የእያንዳንዳችን ዜጋ ድርሻ ከፍ ያለ መሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ ሁላችንም ለአገር በምናበረክተው አስተዋጾኦ ልክ ነው አገር ሰላሟ ሊረጋገጥ የሚችለው፣የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መንገዷ ቀናኢ ሊሆን የሚችለው፣ልማቷ በሚፈለገው ልክ ፈጣንና ዘላቂ መሆን የሚችለው፡፡ለዚህ ደግሞ በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ መድረስ ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡

አገራዊ መግባባት ማምጣት የሚያስችል አካታች ብሄራዊ ምክክር በማድረግ በብዙ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ ልዩነቶችን ማጥበብ የሚያስችል ፈጣንና መላውን ህዝብ ያሳተፈ ምክክር በማድረግ በህዝባችን መሰረታዊ ጥያቄዎች ላይ ዘላቂ እና የማያዳግም እምርታዊ ለውጥ እንዲመጣ ያላሰለሰ ጥረት መደረግ እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሶ ወደ ስራ መግባት የተቻለው፡፡

የልዩነቶች ምንጭ በሆኑ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንዲደረግና ብሔራዊ መግባባት እንዲመጣ በተለያዩ አካላት ሲጠየቅ የነበረውን ጥያቄ በመንግስት በኩል ምላሽ አግኝቶ በጥያቄዎቹ መሰረት ሃገራዊ ምክክሮችን ለማካሄድ ሰፊ ርብርብ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ከዚህ አኳያ በመንግስት በኩል የተሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ነው፡፡

ይህን ማሳካት ስንችል ይዞት የሚመጣው ውጤት ከፍተኛ መሆኑ ጥያቄ የለውም፡፡ ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን በመገንባት፣በህብረ ብሄራዊ ፌዴራሊዝም መሰረት ላይ የታነጸ አገራዊ አንድነትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡

20/12/2022

ፅንፈኞችን #መቃወምና #መታገል ለኢትዮጵያ ያለንን ጥልቅ #ፍቅር መገለጫ አንዱና #ዋነኛው መንገድ ነው። ፅንፈኞች ለሚያገኟት #ፍርፋሪ ህዝባችንን እርስ በእርስ አጣልተውና አጋድሎ ኢትዮጵያን ስበታትኑ #ዝም ብዬ ልመለከት አልችልም። እኔም ትግሉን ተቀላቅያለሁ!!
መንግስት ፅንፈኞችን ለመዋጋት በሚያደርገው ኦፕሬሽን መረጃ በመስጠት፣ሎጂስቲክ በማቅረብና የፅንፈኞችን ሀሳብ ባለመግዛት እተባበራለሁ‼️
የፅንፈኝነት መርዝ ሀገሬን ስበክላት ዝም አልልም‼️


19/12/2022

ከረከሰ አዕምሮ መንደር

ሞት ፤ ጭካኔ ፤ ጥላቻ ፤ ዘረኝነት ፤ ክፈት እና ከሌሎች ርካሽ ነገሮች ብቻ ናቸዉ የሚገኙት ፡፡ ለዛ እኮ ነዊ ፖለቲከኞቻችን ረክሰዉ ፖለቲካ የሚያረክሱት ፤ ዘረኞች ረክሰዉ ዘር ያሰድባሉ ፤ ፅንፈኞች ከመርከስ አልፈዉ #አዉሬ ከሆኑ ሰነብተዋል፡፡ ፅንፈኝነት የረከሰ አዕምሮ አስተሳሰብ ፍሬ ነዉ ፡፡


አንደ ጲላጦስ እጁን ታጥቦ  የሚሰጥ ለሞት አሳልፎ የሞት አጋፋሪዉ የፅንፈኞች ሁሉ አዉራበህፁሃን ሞት ሆዱን የሚሞላ በሴራ በተንኮል  አብዘዝቶ ጋለ ይሃዉ ተመልከቱት ክር *** ታደለክርስቲያን...
05/12/2022

አንደ ጲላጦስ እጁን ታጥቦ የሚሰጥ ለሞት አሳልፎ
የሞት አጋፋሪዉ የፅንፈኞች ሁሉ አዉራ
በህፁሃን ሞት ሆዱን የሚሞላ

በሴራ በተንኮል አብዘዝቶ ጋለ
ይሃዉ ተመልከቱት ክር *** ታደለ
ክርስቲያን ታደለ

26/08/2022


መንግሥት እስከ አሁን ድረስ ለሰላም በሩን ክፍት አድርጎ ቢጠባበቅም ጁንታው ጥቃቱን ቀጥሎበታል።

በመሆኑም የፌዴራል መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር የገለጸው ዝግጁነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለጁንታው ፀረ ሰላም ዕብሪት ምንጭ የሆኑ ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ ርምጃ ይወስዳል። የተመረጡ የጁንታውን ወታደራዊ ዐቅሞችም ይመታል።

ስለሆነም በትግራይ የምትኖሩ ወገኖቻችን በተለይም የጁንታው ወታደራዊ መሣሪያዎች እና ማሠልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች ራሳችሁን እንድታርቁ ይመከራል።

25/08/2022

" " - WFP

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢዝሊ ድርጅታቸው ለእርዳታ ሥራው የሚያውለውን 570,000 ሊትር ነዳጅ " የትግራይ ባለሥልጣናት ሰርቀዋል " ብለዋል።

" ምግብ ለማድረስ ነዳጅ ከሌለን በሚሊዮኖች ይራባሉ " ያሉት ቢዝሊ ድርጊቱን " የሚያስቆጣ እና አሳፋሪ " ብለውታል።

አሁኑን የተሰረቀው ነዳጅ እንዲመለስ ጠይቀዋል።

በኬንያ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ዊሊያም ሩቶ ራይላ ኦዲንጋን አሸነፉዊሊያም ሩቶ የኬንያን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ በ50.49 በመቶ ድምጽ አሸነፉ
15/08/2022

በኬንያ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ዊሊያም ሩቶ ራይላ ኦዲንጋን አሸነፉ

ዊሊያም ሩቶ የኬንያን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ በ50.49 በመቶ ድምጽ አሸነፉ

12/08/2022

Biyya qormaata keessatti injifannoon gara Badhaadhinaatti imalaa jirtu Itoophiyaa!.

Guutiinsi Bishaanii Hidha Haaroomsaa Guddichaa Itoophiyaa marsaa sadaffaan milkaa'inaan xummuramee jira. Kun aaga Badhaadhinaati. Qormaanni kamiyyuu Badhaadhina itti imalaa jiru irraa akka nu hin ittisne agarsiisa. Eyyeen! Duulli baandoota keessaa fi dhiibbaan humnoota alaa daandii keenyarraa nun maqsine. Akka sibilaa nu cimsaa jira. Imala keenyarratti akka cichinu daran nu cimsaa jira. Baga gammaddan!Baga gammanne!
Itoophiyaan dhiibbaa hunda dandamattee dhamaatii lammiilee isheetiin gara badhaadhinaatti ni ceeti!

Hooggansa si'ataafi qulqullina qabu kennuun raawwii pirojektootaa ariifachiisuun dheebuu ummanni misoomuuf qabu guuta.

Kallattii sirrii, si'ataafi qulqullina qabuufi hirmaannaa lammileen taasisan guddina biyyaa ariifachiisa.

Jijjiiramaa as hojiiwwan pirojektii gurguddaa mootummaafi ummanni waliin ta'uun hojjechaa jiraniin milkaa'inniifi injifannoon hedduun galmaa'aa jiru.

Mootummaan jijjiiramaa, Hidha Haaromsaa Guddicha Itoophiyaa duraan maqaan qofa faarfamaa ture, qorachuun adda baasee daandii ittiin pirojektichi milkaa'u qiyaasuun hojiitti seene.

Xiyyeeffannaa kennameefi fedhiin ummanni misoomuuf qabu walitti ida'amuun hojichi milkiin itti fufe.

Haati iyyeessaa sabbata ishee irraa hiikuun waan qabdu gumaachite. Bishaan Abbayya barootaaf dhaabachuu dide kan dhaabe tokkummaan sabaafi sablammootaafi ummattoota Itoophiyaati.

Waggoota 4n darbaniif xiyyeeffannaa kennameen hojiin pirojektichaa har'a 83% irra ga'ee jira. Tarbaayinoonni hidha haaromsaa annisaa burqisiisuu eegalan agarsiiftuu daandii badhaadhinaati. Har'a ammoo guutiinsi bishaanii marsaa 3ffaan milkaa'inaan xummuramuun ifatti ibsamee jira.
Irra deebiin baga gammanne!

 የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ።                                                                  ...
11/08/2022



የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ።

ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉባ ወረዳ በታደሙበት ዝግጅት ነው በዛሬው ዕለት 2ኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት የጀመረው።

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ካሉት 13 ተርባይኖች መካከል ዩኒት 9 የሚባለው ሁለተኛው ተርባይን የተሳካ ተከላ እና ሙከራ ከተደረገ በኋላ ኃይል የማመንጨት ስራው እውን መሆኑን ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

ዛሬ በይፋ ሥራ የጀመረው ሁለተኛው ዩኒት 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio_sweden posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share