EthioInfo

EthioInfo You will get any updates, news, events and information about Ethiopia

The future of Ethiopia!
23/11/2023

The future of Ethiopia!

27/10/2023

ነገሮችን ክመታገል በብልሃት እናድርገው!

ዓለም እየተንቀጠቀጠች ነው። እስራኤል ኡ! ኡ! እያለች ነው። አሜሪካ እስራኤልን የነካ አይኔን ነካ ስትል ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥታለች። የአውሮፓ ህብረት ዋ! ዋ! ብለዋል። ኢራን ሐማስን ...
08/10/2023

ዓለም እየተንቀጠቀጠች ነው። እስራኤል ኡ! ኡ! እያለች ነው። አሜሪካ እስራኤልን የነካ አይኔን ነካ ስትል ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥታለች። የአውሮፓ ህብረት ዋ! ዋ! ብለዋል። ኢራን ሐማስን አንቆለጳጵሳ አበጀህ የኛ ልጅ ከሚል ሰውንድ ትራክ ጋር የአድናቆት መግለጫ አውጥታለች። ካታር የቀውሱ መነሻ 'ሰፋሪዎች' ናቸው ስትል ጣቷን ወደ ቴል አቪቭ ቀስራለች። ሰውዲ በልቧ ሐማስን ይዛ አንተም ተው አንተም ተው ብላለች።

ጠቅላይ ሚነስትር ቤንጃሚን ኔታናሁ ከሀገሪቱ ፀጥታ ምክር ቤት ጋር አስቸኳይ ስብሰባ ካደረጉ በኃላ ክተት አውጀዋል። እስራኤል ጦርነት ላይ ናት...ያውም ቀይ ጦርነት አሉ። እናም በምድርም በሰማይም ጠላቶቻችንን ድብቅ መትተን ወደ መቃብር እንሸኛቸዋለን ሲሉ ዝተዋል።

ዓለምን በሙሉ አስጨንቆ በአንድ እግር ያቆመው የሐማስ ድንገቴና ያልተጠበቀ ጥቃት ነው። ሐማስ ዛሬ ከሰዓታት በፊት በአምስት ደቂቃዎች ውስጥ ሁለት ሺህ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል አስወንጭፏዋል። እየሩሳሌም እየራደች ነው። ቴል አቪቭ ደንግጣለች። ሐይፋ ተመታለች። አሽኬሎን በባሩድ ጭስ ተሸፈንላች። እስከአሁን 50 የሚሆኑ እስራኤላውያን ተገድለዋል። በጋዛ ሰርጥ አቅራቢያ ከሚትገኘው Ashkelon ከተማ ሲቪሎች እና የእስራኤል ወታደሮች በሐማስ ታግተዋል። ይህ በታሪክ ውስጥ ሐማስ እስራኤል ላይ ከፈፀማቸው ጥቃቶች የከፋው ነው ተብለዋል። ቡዱኑ ይሄን ሁሉ ዝግጅት አድርጎ ከጋዛ 70 ኪሎ ሜትር ተጉዞ ቴላአቪቭ ደርሶ ኤርፖርት ላይ ሲተኩስ፣ ወታደራዊ አመራሮችን እስከማገት ሲደርስ... የዓለም ኮሽታ መረጃ አታመልጠውም የሚባለው ሞሳድ የት ነበር እየተባለ ነው።

ጥቃቶቹን ተከትሎ ጠቅላይ ሚነስትር ቤንጃሚን ኔታናሁ ጦርነት አውጀናል ካሉ በኃላ የእስራኤል አየር ሀይል ጋዛን ክፉኛ እየደበደበ ነው። እስከአሁን ወደ 200 የሚጠጉ ሰዎችን ገድለዋል። ጋዛ በእሳት እየነደደች ነው። የሴቶች ዋይታ፣ የህፃናት ለቅሶ አይለዋል። ሆስፒታሎች በቁስለኞች ተሞልተዋል። ነገሩ በዚህ በዛም አስፈሪ ሆኖዋል። ጦርነቱ ወደ ቀጠናው እንዳይስፋፋም ያሰጋል።

ሐማስ ሰሞኑን የአይሁድ አክራሪዎች የአልአቅሳ መስጂድን በመውረር አስነዋሪ ድርጊት በመፈፀማቸው ጥቃቱ የበቀል መሆኑን ገልፀዋል። ጥቃቱ የሚቀጥል እንጂ የሚቆም አይደለም ብለዋል። ጥቃቱ ልክ ከዓመታት በፊት የሀሰን ነስረላ ሒዝቦላ ድንገቴ ጥቃት ፈፅም እስራኤልን አስገድዶ ለድርድር እንዳስቀመጣት አይነት ተደርጎ እየተወሰደ ነው።
አሁን እስራኤልም ክፉኛ ተቆጥታለች። ብረቷ መሪ ጎልዳ ሜር በሙኒክ ኦሊምፒክ ላይ በፍሊስጤም ታጣቂዎች የተገደሉትን የእስራኤላውያን አትሎቶችን ደም እንደተበቀሉ ሁሉ ጠ/ሚ/ር ኔታናሁም የእስራኤላውያን ደም ደመከልብ እንደማይሆን ዝቶ ተገዝቶ ተናግረዋል። የሀገሪቱን ተጠባባቂ ጦርም ለክተት ጠርተዋል።

ብቻ መካከለኛው ምስራቅ በነበልባል እሳት እያተቃጠለች ነው። ሰላሙን ያውርድ እንዳልል ሰላሙ በቀላሉ የሚወርድ አይመስልም። ምድሪቱ ደም አትጠግብም። አሁንም ገና የብዙዎችን ደም ትጠጣለች።
ዘገባው ተፃፈ በጥላዬ ያሚ

29/01/2023

ሩሲያ እና ኤርትራ በምን ነጥቦች ላይ ተወያዩ?

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EthioInfo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share