Central communication

Central communication & Broadcasting Production!!!

የሀዲያ ምድር ዳግማዊ በዛብህ ጴጥሮስን ለኢትዮጵያ እነሆ ብላለች! ሀዲያ ሌላኛውን የጦር ጀት አብራሪ መቶ አለቃ ነጋልኝ ኤርሚያስን ለሀገር አበርክታለች:: ባዳዋቾ ኮለኔል በዛብህን ሲወልድ ሚ...
11/01/2024

የሀዲያ ምድር ዳግማዊ በዛብህ ጴጥሮስን ለኢትዮጵያ እነሆ ብላለች!

ሀዲያ ሌላኛውን የጦር ጀት አብራሪ መቶ አለቃ ነጋልኝ ኤርሚያስን ለሀገር አበርክታለች::

ባዳዋቾ ኮለኔል በዛብህን ሲወልድ
ሚሻ ደግሞ ነጋልኝን ፈጥሯል

ሀዲያ ጀግና የማይጠፋው ምድር!
ሀዲያ ጀግና የሚወልድ ምድር!
ሀዲያ የምሁራን መፍለቂያ!
Via ➱ሀብን ሚዲያ

11/01/2024
10/01/2024
የሰላሙ አምላክ ሰላምን ያምጣልን       🙏 አሜን 🙏
10/01/2024

የሰላሙ አምላክ ሰላምን ያምጣልን
🙏 አሜን 🙏

ከ800 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ኮሚሽኑ ከታህሳስ 18 እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 404 ነጥብ 1...
09/01/2024

ከ800 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ከታህሳስ 18 እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 404 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 398 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፎች መያዙን አስታውቋል፡፡
ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሐኒት፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገራ ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡
የገቢ እና የወጪ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ አዋሽ እና ድሬደዋ ጉምሩክ ቅርንጫፎች ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዙ የኮሚሽኑ መረጃ ያስረዳል፡፡
ኮሚሽኑ በሕግ ማስከበር ሥራው የተሳተፉ ሰራተኞች፣ የክልሎችና የፌዴራል ፖሊስ አባላትን እንዲሁም ሕብረተሰቡን አመስግኗል፡፡
ድርጊቱን ለመከላከል ኮሚሽኑ ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ባላድርሻ አካላትና ሕብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ቴሌግራም :- https://t.me/centrcommunicatio

በአርባምንጭ ዙሪያ “የልዩ ወረዳ ጥያቄ” በሚያቀርቡ ነዋሪዎች እና የጸጥታ አካላት መካከል በተፈጠረ ግጭት ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ፡፡በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ በአካባ...
09/01/2024

በአርባምንጭ ዙሪያ “የልዩ ወረዳ ጥያቄ” በሚያቀርቡ ነዋሪዎች እና የጸጥታ አካላት መካከል በተፈጠረ ግጭት ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ በአካባቢው የጸጥታ ኃይሎችና የልዩ ወረዳ ጥያቄ በሚያቀርቡ ነዋሪዎች መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተሰምቷል፡፡
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን የአከባቢውን ነዋሪዎች ጠቅሶ የአሜሪካ ድምፅ ዘግቧል።
የአርባ ምንጭ ዙሪያ የፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክበበው አዳል “የመንግስት የጸጥታ ኅይሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የወሰዱት እርምጃ የለም” ብለዋል።
በአካባቢው ህግ ለማስከበር በሚንቀሳቀሱ የፀጥታ ሃይሎች ላይ “ተቃጣ” ያሉትን ጥቃት ለመከላከል ግን “አፀፋዊ እርምጃ ተወስዷል” በማለት ተናግረዋል ።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓም ባወጣው ሪፖርት በአከባቢው ውጥረት መኖሩን መግለፁን ናሁ ቴሌቭዥን ከዚህ ቀደም መዘገቡ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ የጋሞ ዞንን በሚመለከት ኢሰመኮ ያወጣው መግለጫ መሰረተ ቢስ መሆኑን የዞኑ ባለስልጣናት ገለፀው ነበር፡፡
የኢሰመኮን መግለጫ በተመለከ ቃላቸውን የሰጡት የጋሞ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ "ኢሰመኮ ያወጣው ሪፖርት መሰረት የሌለውና በመረጃ ያልተደገፈ" ሲሉ ማጣጣላቸውን ባሳለፍነው ሳምንት መዘገባችን አይዘነጋም።
ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇👇

ቴሌግራም :- https://t.me/centrcommunication

🇸🇳 ❤️ 💍 ላደገበት ለገጠራማ ከተማ ለማህበረሰቡ * ሆስፒታል በመገንባት* ስታዲዮም በመገንባት * ብዙ መሰረተ ልማታ በማድረግ በብዙ ሴናጋላውያን እንዲሁም በአፍሪካውያን የሚወደደው ሳዲዮ ማ...
09/01/2024

🇸🇳 ❤️ 💍

ላደገበት ለገጠራማ ከተማ ለማህበረሰቡ

* ሆስፒታል በመገንባት
* ስታዲዮም በመገንባት
* ብዙ መሰረተ ልማታ

በማድረግ በብዙ ሴናጋላውያን እንዲሁም በአፍሪካውያን የሚወደደው

ሳዲዮ ማኔ ከብዙ ዓመት እጮኛው አይሻ ጋር ተሞሽሯል 👰🤵💍 ♥
መልካም የትዳር ዘመን
አልፍ አልፍ መብሩክ !
🇸🇳 ❤️💍

ዜና ድንቃድንቅ‼️➖➖➖➖በ47,000 ብር ከተገዛው በሬ የ235,000 ብር ወርቅ ተገኘ።ይህ የሆነው በወላይታ ዞን ጠበላ ከተማ አስተዳደር ለገና በዓል ለቅርጫ ከታረደው በሬ 40 ግራም ወርቅ ...
09/01/2024

ዜና ድንቃድንቅ‼️
➖➖➖➖
በ47,000 ብር ከተገዛው በሬ የ235,000 ብር ወርቅ ተገኘ።

ይህ የሆነው በወላይታ ዞን ጠበላ ከተማ አስተዳደር ለገና በዓል ለቅርጫ ከታረደው በሬ 40 ግራም ወርቅ ተገኝቷል።

በከተማው ገና በዓልን ለማክበር ለቅርጫ ተብለው 47,000 ብር የተገዛውን በሬን ከታረደው በኋላ 40 ግራም ወርቅ ተገኝተዋል፣ በገንዘብ ሲተመን 235,000 ብር መገኘቱ ተሰምቷል።

መልካም የገና በዓል!!

ለአባይ ቴሌቪዥን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው********* አባይ ቴሌቪዥን እሁድ ታህሳስ 28/2016ዓ.ም 'ዋሸው እንዴ?' በተሰኘ ፕሮግራሙ ላይ የሴቶችን ስብዕና፤ መብት እና ክብር የሚያ...
09/01/2024

ለአባይ ቴሌቪዥን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው
*********
አባይ ቴሌቪዥን እሁድ ታህሳስ 28/2016ዓ.ም 'ዋሸው እንዴ?' በተሰኘ ፕሮግራሙ ላይ የሴቶችን ስብዕና፤ መብት እና ክብር የሚያጎድፉ እንዲሁም የህብረተሰቡን መልካም ባህልና ዕሴት የሚጥሱ በተለይም በሴት ልጆች ላይ የሚፈጸም ወንጀልን የሚያበረታቱ እና ታዳጊዎችን ላልተገባ ድርጊት የሚዳርጉ ሃሳብና አስተያየቶች በፕሮግራሙ ላይ መተላለፉን ባለስልጣኑ ያደረገው የሚዲያ ይዘት ክትትል ግኝት የሚያመለክት ሲሆን ከህብረተሰቡም ጥቆማዎች ቀርበዋል፡፡

አባይ ቴሌቪዥን በተደጋጋሚ የህብረተሰቡን መልካም ዕሴት፣ ሰላምና ደህንነት የሚያናጉ ፕሮግራሞችና ዘገባዎችን በጣቢያው ሲያሰራጭ ከባለስልጣኑ በኩል በተለያዩ መንገዶች ግብረመልሶችን በመስጠት እንዲሁም ከጣቢያው ሃላፊዎች ጋር ውይይቶችን በማካሄድ ጭምር መሻሻሎች እንዲደረጉ ጥረት ቢደረግም ጣቢያው ይህን መሰል ድርጊቶችን ለማረም ያልቻለ ሲሆን በዕለቱ የተሰራጨው ፕሮግራም የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ 1238/2013 አንቀጽ 68/2 ለ/ሐ/መ/ እና ሠ ላይ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን የጣሰ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በመሆኑም ጣቢያው በቀጣይ መሰል ህግን የሚጥሱ፣ ሃላፊነት የጎደላቸው፤ የሰውን ልጅ ስብዕና እና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ፕሮግራሞችን ከማሰራጨት እንዲቆጠብ ይህ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰቶታል፡፡

ንብረት ማውደም ሾፌር ማገት መግደል የተለመደ ሆኗል ህግ አስከባሪው አካል ፈቃድ የሰጣቸው የሚመስሉ ዘና ብለው ሲፈልጉ በቀን ሲፈልጉ በሌት መንገድ ዘግተው ሾፌር ገለው አግተው መኪና አጋይተው...
08/01/2024

ንብረት ማውደም ሾፌር ማገት መግደል የተለመደ ሆኗል ህግ አስከባሪው አካል ፈቃድ የሰጣቸው የሚመስሉ ዘና ብለው ሲፈልጉ በቀን ሲፈልጉ በሌት መንገድ ዘግተው ሾፌር ገለው አግተው መኪና አጋይተው የሚኖሩ እያየን ነው::

 #ቻይና በራሷ የሰራችው የኤሌክትሪክ አውሮፕላን ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰራው አውሮፕላኑ የመጀመሪያ በረራ አድረጓል። በሰዓት 218 ኪሎ ሜትር የሚጓ,ዘው አውሮፕላኑ በአንድ በረራ 1,10...
08/01/2024

#ቻይና በራሷ የሰራችው የኤሌክትሪክ አውሮፕላን

ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰራው አውሮፕላኑ የመጀመሪያ በረራ አድረጓል። በሰዓት 218 ኪሎ ሜትር የሚጓ,ዘው አውሮፕላኑ በአንድ በረራ 1,100 ኪሎ ሜትር ርቀት ይጓዛል።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://t.me/centrcommunication

ይህን ያውቁ ኖረዋል..🇪🇹🇸🇴ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ግጭት ከገባች ምን ይፈጠርባታል!በሶማሊያ ያለው 20,000 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሶማሊያን ለቆ ከወጣ የአልሸባብ ሃይል ሶማሊያን...
07/01/2024

ይህን ያውቁ ኖረዋል..🇪🇹🇸🇴

ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ግጭት ከገባች ምን ይፈጠርባታል!

በሶማሊያ ያለው 20,000 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሶማሊያን ለቆ ከወጣ የአልሸባብ ሃይል ሶማሊያን ከ72 ሰአት በነሰ ጊዜ ይቆጣጠራታል።ምክንያቱም ሶማሊያ ሶማሊያ በጣም ደካማ ከአልሸባብ ራሷን መከላከል የማትችል ደካማ ሀገር ናት። በዚህም ከአለም ደካማ የሚሊተሪ ሃይል ካላቸው ሀገራት ተርታ ተሰልፋለች። የሶማሊያ በ2023 የሚሊተሪ ሃይል መረጃዋ ከዚህ በታች አስቀምጣለሁ።

➠የሰራዊት ብዛት.... 17,000
➠ተጠባባቂ ሃይል.... 00
➠ ጀነራል መድፍ ..... 40
➠ሮኬት ፕሮጀክት......00
➠ ተዋጊ ጀት .......... 00
➠ተዋጊ ሄሊኮፕተር .....00
➠ባህር ሃይል .............00
➠ የውጊያ ታንክ...........15 ብቻ ያላት ሀገር ናት።
ለዚህም ነው በጀግና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የምትጠበቀው።

አይበለውና አልሸባብ ድጋሚ ሞቃዲሾን ከተቆጣጠረ
በአሜሪካ መሪነት ሃያላኑ ሶማሊያ ላይ ቁጥር ስፍር የሌለው የሰብዓዊ እርዳታን ጨምሮ ከፍተኛ ማዕቀቦች ይጣላሉ።ብዙ ሀገራት ከሶማሊያ ጋር ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ግንኙነት ያቋርጣሉ። አሸባሪው የአልሸባብ ሃይል የሶማሊያ ህዝብ ላይ የበቀል ሰይፋቸውን መዘው የሶማሊያን ህዝብ ቁምስቅል ያሳያቸዋል ወ.ዘ.ተ ክፉኛ ችግር ይገጥማታል።

ስለዚህ ሶማሊያ ይሄ ሁሉ ኪሳራ ከሚመጣባት ኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ድንፋታና ፉከራ ብትቀንስ ይሻላታል። ምክንያቱም ኢትዮጵያ የሶማሊያ የመኖር ያለመኖር ዋስትና ናት። መረጃው ከተለያዩ ዌብሳይቶች ያሰባሰብኳቸው ናቸው።

 #ሆሳዕና 🥩😎የገና ስጦታዛሬ በሆሳዕና ከተማ ሴች ዱና ቀበሌ ለገና በዓል ቅርጫ ባረድነው በሬ ውስጥ  * 11.9 ግራም ወርቅ የተገኘ ሲሆን ። * በሬው የተገዛው በ53 ሺህ ብር ሲሆን ወርቁ...
07/01/2024

#ሆሳዕና 🥩😎
የገና ስጦታ

ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ሴች ዱና ቀበሌ ለገና በዓል ቅርጫ ባረድነው በሬ ውስጥ

* 11.9 ግራም ወርቅ የተገኘ ሲሆን ።
* በሬው የተገዛው በ53 ሺህ ብር ሲሆን
ወርቁ ደሞ እልል ተብሎ በ125 ሺህ ብር ተሽጧል
በዚህ መስረት ለገና ብለን ባረድነው በሬ ምክንያት ይህው 72ሺህ የኢትዮጵያ ብር አትርፈናል::
Via Tame Samuel

🌴🌴🌴

ትላንት ምሽት በጥይት የተገደሉት የበድር መስጂድ ኢማም ሸይኽ አብዱ ያሲን ስርአት ቀብር ተፈፀመ!ትናንት ምሽት ከዒሻ ሶላት በኋላ አስኮ አዲስ ሠፈር ከሚገኘው በድር መስጂድ ወደ ቤታቸው እያመ...
07/01/2024

ትላንት ምሽት በጥይት የተገደሉት የበድር መስጂድ ኢማም ሸይኽ አብዱ ያሲን ስርአት ቀብር ተፈፀመ!

ትናንት ምሽት ከዒሻ ሶላት በኋላ አስኮ አዲስ ሠፈር ከሚገኘው በድር መስጂድ ወደ ቤታቸው እያመሩ ማንነቱ ባልታወቀ አካል ከጀርባ ጭንቅላታቸውን ተመተው የተገደሉት የመስጂዱ ኢማምና ኸጢብ እንዲሁም የተለያዩ ኪታቦችን በማቅራት የሚታወቁት አቅሪ ሸይኽ አብዱ ያሲን ስርዓተ ቀብራቸው በኮልፌ የሙስሊም መቃብር ተፈፅሟል።

ለእሳቸው አላህ ጀነትን እንዲወፍቃቸው እንዲሁም ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ መፅናናትን እንመኛለን።

ሀሩን ሚድያ

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላምአደረሳችሁ አደረሰን!🙏❤🙏
06/01/2024

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን
ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም
አደረሳችሁ አደረሰን!🙏❤🙏

የቱ ነው ትክክል?
06/01/2024

የቱ ነው ትክክል?

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁየክርስቶስ የልደት በዓል ሁለት አስደናቂ ነገሮች የተፈጸሙበት ነው፡፡ የተጠበቀው ባልተጠበቀው መንገድ የመጣበት እና ያልተጠበቁት ባልተጠበቀ ...
06/01/2024

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ

የክርስቶስ የልደት በዓል ሁለት አስደናቂ ነገሮች የተፈጸሙበት ነው፡፡ የተጠበቀው ባልተጠበቀው መንገድ የመጣበት እና ያልተጠበቁት ባልተጠበቀ ቦታ የተገኙበት ነው፡፡ በኦሪትና በነቢያት ክርስቶስ ይመጣል የሚለውን ቃል የሰሙና ያነበቡ ብዙዎች ነበሩ፡፡ የጠበቁት ግን በነገሥታት ቤተ መንግሥትና በባዕለጸጎች እልፍኝ ውስጥ ነበር፡፡ የዓለምንና የሰው ልጅን ታሪክ የቀየረው ክርስቶስ በበረት ውስጥ ይወለዳል ብሎ የጠበቀ አልነበረም፡፡ በዚህም የተነሣ የዓለም ታሪክ በአስደናቂ ሁኔታ ሲቀየር ዓለም ራሷ ግን ተኝታ ነበር፡፡

የዓለምንና የሀገርን ታሪክ የሚቀይሩ ነገሮች በተለመዱና በሚጠበቁ መንገዶች ላይመጡ ይችላሉ፡፡ ብዙዎች በሚያውቁትና በሚተነትኑት አካሄድም ላይከሠቱ ይችላሉ፡፡ እንዲህ ባለ ሁኔታ መረዳት የሚገኘው እኛ የማናውቀው፣ ያልደረስንበትና የማንገምተው ሌላም መንገድ ሊኖር እንደሚችል ለመቀበል ከተዘጋጀን ብቻ ነው፡፡ ነገሮች ሁሉ እኛ በምናውቀው፣ በምንገምተውና በለመድነው መንገድ ብቻ እንዲመጡ ከጠበቅን ሊያልፉን ይችላሉ፡፡ የቤተ ልሔም ከተማና የይሁዳ አውራጃ ሰዎች የዓለምን ታሪክ ከቀየረው ከክርስቶስ ልደት ሳይሳተፉ የቀሩት ከለመዱትና ከሚያውቁት ውጭ ለሚመጣ ነገር ዝግጁዎች ስላልነበሩ ነው፡፡

የቤተልሔም ከተማና የይሁዳ አውራጃ ሰዎች በለመዱትና በሚያውቁት መንገድ የሚመጣን ነገር ሲጠብቁ፣ ባልለመዱትና በማያውቁት መንገድ የሚመጣን መፍትሔ ለመቀበል ዝግጁ የሆኑ ሌሎች አካላት ቤተልሔም ደርሰው ነበር፡፡ እረኞችና ሰብአ ሰገል፡፡ ሌሊቱን ሙሉ መንጋቸውን ሲጠብቁ ያደሩት የቤተልሔም እረኞች በአካባቢያቸው የነበሩትን መላእክት ለመመልከት ዕድል አግኝተዋል፡፡ ጊዜው ምሽት ነው፡፡ ምሽት ደግሞ የዕንቅልፍ ጊዜ ነው፡፡ ለሕዝብ ቆጠራ ወደ ቤተልሔም የመጡ ሰዎች ከተማዋን አጨናንቀዋታል፡፡ ከዚህ ያለፈ እንግዳ ነገር የጠበቀ የቤተልሔም ሰው የለም፡፡ ሁሉም የተለመደን ነገር በተለመደ መንገድ በማከናወን ተኝቷል፡፡

እረኞቹ ግን ከተኛው ማኅበረሰብ ተለይተው በሜዳ ላይ በንቃት ነበሩ፡፡ ይሄ ብቻ አይደለም፡፡ የዓለምን ታሪክ የቀየረው ክርስቶስ በእንግዶች ማደሪያ ሥፍራ ስላላገኘ የመጣው ወደ በረት ነው፡፡ የከተማው ሰዎች ሊያደርጉ ያልደፈሩትን እረኞቹ በረታቸውን ለዮሴፍና ለድንግል ማርያም ለቅቀው ወደ ሜዳ ወጡ፡፡ እረኞቹ ከሕዝቡ የተለየ መንገድና የተለየ ዝግጁነት ነበራቸው፡፡ በዚህ የተነሣ ከሊቃውንቱ፣ ከፈሪሳውያኑና ከሰዱቃውያኑ ተለይተው ያልታሰበውን ታሪክ ያልታሰቡት እረኞች ለማየት በቁ፡፡

የቤተልሔምን ሰዎች ብቻ ሳይሆን ንጉሥ ሄሮድስንም ባስደነገጠ መንገድ ሰብአ ሰገል ከምሥራቅ ‹የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው› እያሉ ከእረኞቹ ቀጥለው መጡ። ማንም አልጠበቀም፡፡ ያልተጠበቁት ሰብአ ሰገል ባልተጠበቀ ቦታ በበረት ተገኙ፡፡ ካልተለመደ ሥፍራ፣ ባልተለመደ መንገድ ተጉዘው፣ ያልተጠበቀ ቦታ ተገኙና ያልጠበቁትን ተአምር አዩ፡፡

ሀገርን ምንጊዜም የሰው ልጅ ሲጓዝባቸው በኖሩ መንገዶች ብቻ መታደግ አይቻልም፡፡ ሰው ሁሉ በሚያውቃቸው፣ በለመዳቸውና በተረዳባቸው መፍትሔዎች ብቻ ሀገርን መመንጠቅ አይቻልም፡፡ መኪኖችና አውሮፕላኖች በሚጓዙበት መንገድ መንኮራኩሮችን ወደ ሕዋ መውሰድ እንደማይቻለው ሁሉ፡፡ ወደ ሕዋ ለመሄድ የምድር ስበትን ሰብሮ፣ በፍጥነትና በኃይል ባልተለመደ የጉዞ ስልት መመንጠቅን ይጠይቃል፡፡

እንዲህ ያለ ጉዞ ከተለመደውና ከሚታሰበው መንገድ ወጥቶ መሄድን የግድ ይላል፡፡ ስለዚህም ይሄንን መንገድ የሚረዳ ከሚጠበቀውና ከሚታሰበው ውጭ ለመጓዝ ፈቃደኛ የሆነ ወገንን ይፈልጋል፡፡ አሁን ሀገራችን ያለችው

የአክሱም ኢምፓየር በጥንታዊው ዓለም ከነበሩት አስደናቂ ኃይሎች አንዱ ነበር። በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰሜናዊ ክፍል የምትገኝ ሲሆን በአንድ ወቅት የምስራቅ አፍሪካን እና የአረቢያን ...
06/01/2024

የአክሱም ኢምፓየር በጥንታዊው ዓለም ከነበሩት አስደናቂ ኃይሎች አንዱ ነበር። በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰሜናዊ ክፍል የምትገኝ ሲሆን በአንድ ወቅት የምስራቅ አፍሪካን እና የአረቢያን ክፍል ትቆጣጠር ነበር። በአፍሪካ ውስጥ ስላሉት ማንኛቸውም ሀይለኛ ጥንታዊ ስልጣኔዎች ስናስብ የግብፅ ስልጣኔ ብቻ ወደ አእምሯችን ይመጣል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአክሱም ሥልጣኔ ከጥንታዊ አውሮፓና እስያ ጋር ግንኙነት ከነበራቸው የአፍሪካ ቀደምት ማኅበረሰቦች አንዱ ነበር፣ ነገር ግን ስለ እሱ ብዙም የሚታወቅ ነገር የለም።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር  ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው ለ2016 ዓመተ ምህረት  ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና)የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ የማዕከላዊ ...
06/01/2024

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው ለ2016 ዓመተ ምህረት ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና)የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው ለ2016 ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል(ገና) ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ ታላላቅ በዓላት አንዱ የሆነዉን የገና በዓልን ስናከብር በፈርሃ ፈጣሪ የታነፀ የመንፈስና የሞራል ስብዕናን በመጎናፀፍ ሠላምን፣ አብሮነትንና ወንድም/ እህትማማችነትን የማጠናከር ተነሳሽነታችንን ከፍ በማድረግ መሆን ይኖርበታል ብለዋል።

የተራራቁ ወዳጅ ዘመዳሞች ተሰባስበው በዓልን የማክበር መልካም እሴት አለን ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) በመላው አለም የሚኖሩ ለሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ያስተላለፉትን ጥሪ ርዕሰ መስተዳድሩ አድንቀዋል።

ይህንኑ በማስመልከት በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ የሁለተኛው ትዉልድ የክልሉ ተወላጆች ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የዘንድሮዉ የገና በዓል ሀገራችን ኢትዮጵያ ከሶማሌ ላንድ ጋር የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ሥምምነት ሰነድ በፈረመችበትና የBRICKS አባል ሀገር ሆና በይፋ በተቀላቀቀለችበት ማግስት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ

የገናዉ በዓል በአዲስ የታሪክ እጥፋት መክፈቻ ምዕራፍ ላይ እየተከበረ ነዉ ብለዋል።

የመግባቢያ የስምምነት ሰነዱ መፈረም ለሀገራችን ዘርፈ ብዙ ስትራቴጂካዊ ጥቅሞችን የሚያስገኝ በመሆኑ ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ በማዉጣቱ ሂደት ጉልህ ሚና ይጫወታል።

በአዲስ ምዕራፍ አዲስ ተስፋ ለአዲስ ክልል በሚል መሪ ሀሳብ ክልሉ በይፋ ተመስርቶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በጀመረበት ወቅት ላይ መሆኑ የዘንድሮውን የገና በዓል የተለየ ያደርገዋል ብለዋል።
የክልሉን ህዝብ የልማት ፍላጎት ለማሳካት በሁሉም ዘርፍ የላቀ ጥረት እየተደረገ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም የመላውን ህብረተሰብ ተሳትፎ ይጠይቃል ሲሉም ተናግረዋል።

ክልሉ በአዲስ መልክ መመስረቱን ተከትሎ ኢንቬስትመንትን ማበረታታት፣የቱሪዝም ሀብቶቻችንን ማልማት እና ማስተዋወቅ፣ምርታማነትን ማሳደግ፣የአካባቢውን ሰላም በጽኑ መሰረት ላይ መገንባት፣የህዝብ ለህዘዝብ ትስስርን ማጠናከር እና ሌሎች የህዝብን ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት መደረጉን ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው አስረድተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ህብረተሰቡ ከዚህ ቀደም ያለውን የመረዳዳት እና የመደጋገፍ ባህል በማጠናከር በዓልን በማይመች ሁኔታ ላይ እያከበሩ ያሉ ወገኖቻችንን በመደገፍ ማክበር እንዳለበትም ጠቁመዋል።

ለመላው ለክልሉ እና ለሀገራችን የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሰላም፣የጤና የፍቅር እና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆን ርዕሰ መስተዳድሩ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

 #በጃፖን በአዲስ አመት እለት በተከሰተ ርዕደ መሬት የሞቱ ሰዎች 100 ደረሰበጃፖን በአዲስ አመት እለት በደረሰ የርዕደ መሬት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 100 ከፍ ያለ ሲሆን 200,ሰዎ...
06/01/2024

#በጃፖን በአዲስ አመት እለት በተከሰተ ርዕደ መሬት የሞቱ ሰዎች 100 ደረሰ

በጃፖን በአዲስ አመት እለት በደረሰ የርዕደ መሬት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 100 ከፍ ያለ ሲሆን 200,ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም።

የርዕደ መሬቱ አደጋ በሀገሪቱ በስምንት አመት ውስጥ እጅግ አስከፊው ነው ተብሏል።

በጃፖን ምዕራብ ጠረፍ የተከሰተው በርዕደመሬት 7.6 መጠን ያለው ሲሆን መሰረተልማቶችን አውድሟል፣ 23ሺ ሰዎች ቤት አልባ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

የነፍስ አድን ሰራተኞች በፈራረሱ ህንጻዎች ውስጥ የጠፉ ሰዎችን እየፈለጉ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።

የሴንትራል ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፡ 👇👇👇👇
https://t.me/centrcommunication
https://t.me/centrcommunication
https://t.me/centrcommunication
https://t.me/centrcommunication

✅December 25 ላይ ምዕራባውያን የሚያከብሩት በዓል እውነት የክርስቶስ የልደት ቀን ነውን?የገና ዛፍ ምንድነው?የገና አባትስ ማነው?✅ በአብዛኛው አውሮፓ፡አሜሪካና ቅኝ በተገዙ አንዳነድ ...
06/01/2024

✅December 25 ላይ ምዕራባውያን የሚያከብሩት በዓል እውነት የክርስቶስ የልደት ቀን ነውን?የገና ዛፍ ምንድነው?የገና አባትስ ማነው?
✅ በአብዛኛው አውሮፓ፡አሜሪካና ቅኝ በተገዙ አንዳነድ አገሮችእንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ዲሴምበር 25 የሚከበረው የ እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ሳይሆን ታላቁ የጥፋትና የአመጽ ሰው
ንጉስ ናምሩድ የ ፀሐዩ አምላክ/ሳተርናሊያ ወይም ሚትራ የተወለዱበት ቀን ነው፡፡
✅እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ዲሴምበር 25 የሚከበረውን የ“ገና”
“Christmas” በአል ምክንያት በማድረግ በተደረገው የታሪክ ጥናት እንደ
ፈረንጆቹ አቆጣጠር A.D. 324 ላይ ለመጀመሪያ ግዜ Christmas
በዓል እንደተከበረ መረጃዎች ተገኝተዋል::በሮማውያን አገዛዝ በዘመነ በባዛንታይን ስርወ መንግስት በግዜው
አብዛኛውን የአለም ክፍሎች በመግዛት የሚያስተዳድረው ንጉስ “ጁስቲኒያን”
Justinian [A.D. 527-565] በይፋ የገና “Christmas” በአል እንዲከበር
አወጀ::
✅በበረዶው
የክረምት ወራት ጸሐይ በምትጠፋበት ግዜና አብዛኛው የአውሮፓና ከፊል
የሰሜን አሜርካ እንዲሁም ከፊል የኤሽያ አገሮች ቀኑ በጨለማ በሚዋጥበት
ግዜ የሮማውያን ወታደሮች ለ “ፀሐይ አምላክ” ዲሴምበር 25 ላይ አምልኮና
በአል ያደርጉ ነበር፡፡ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ(ኦሪት ዘጸአት 20:3)
✅የገና ዛፍ(Christmas tree) የሚሰራው ከ ጥድ ነው፡፡ምክንያቱም በአብዛኛው በአውሮፓና አሜሪካ የክረምት ወቅት ላይ ሌሎች ዛፎች ቅጠላቸውን ያረግፋሉ፡ጥድ ግን በዚህ ወቅት ቅጠሉን የማያረግፍ አምላክ ቢሆን ነው በማለት የገና ዛፍን ያመልኩታል፡፡ከአምልኮ ጋር በማያያዝ እንጅ የገና ዛፍ ከክርስቶስ ልደት ጋር ምንም አይገናኝም፡፡
ትንቢተ ኤርሚያስ 10:1-6
እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፡እግዛብሄር በእናንተ ላይ የተናገረው ቃል ስሙ፡፡እግዛብሄር እንዲህ ይላል፡፡የ አህዛብን መንገድ አትማሩ፡፡ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፡ምክንያቱም አህዛብ ይፈሩታልና፡፡
የ አህዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፡ዛፍ ከዱር ይቆረጣል፡በሰራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሰራል፡፡
በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፡እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል፡፡እንደተቀረፀ አምድ ናቸው እነርሱም አይናገሩም፡መራመድም አይቻላቸውም ይሸከሟቸዋል፡ክፉ መስራት አይቻላቸውምና፡ደግሞም መልካም ይሰሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሯቸው፡፡
አቤቱ እንዳንተ ያለ የለም፡አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በሀይል ታላቅ ነው፡፡
✅የገና አባት የሚባለው “ሳንታ ክላውስ” ማን
ነው?
እንደ World book Encyclopedia መረጃ መሰረት ወፍራሙና ዘናጩ ሰው
ሳንታ ክላውስ ወይም በተለምዶ የገና አባት የሚባለው
የጥንት የስካንዲኒቪያን አገሮች ኖርዌጂያን ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦች ዘንድ
የባእድ ( pagan) አምልኮ ታሪክ ያለው ሲሆን ለምሳሌ በጥንት ኖርዌጂያኖች
እምነት መሰረት ሳንታ ክላውስ በቤት ውስጥ ባለ የእሳት ጭስ መውጫ
(ቼሚኒ) በኩል ይገባል የሚል እምነት ስላላቸው የጥንቶቹ ኖርዌጂያኖች
የቤታቸውን ጭስ ማውጫ ቼሚኒ በጣም ትልቅ አድርገው ይሰሩ ነበር::
በተጨማሪም “ሐርታ” የሚባል አማልክት ያላቸው ሲሆን ይህ አማልክት
በቤታቸው ባለ እሳት ማንደጃ አካባቢ በላይ ቢመጣ ለቤታችን ጥሩ እድል
ይሆናል ብለው ያምናሉ::
✅✅ስለዚህ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች የፈረንጆች የገና በዓል ሙሉ በሙሉ የሰይጣን አምልኮ የሚካሄድበት፡የክርስቶስ ስም የማይነሳበት ሴጣናዊ በዓል ነው፡፡
✅ይህ አምልኮ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእኛም ሀገር እየተዘወተረ እየመጣ ነው፣ማወቁ አይከፋም። ለገና ዛፍ መግዣ ወጪ ባታወጡ ተገቢ ነው።
👇👇👇👇👇👇👇👇
http://t.me/centrcommunication
http://t.me/centrcommunication
http://t.me/centrcommunication

06/01/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Efrem Legesse, የቆሴ ነዋሪዎች ድምጽ

ከታህሳስ 15 እስከ ጥር 14፣ 2016 ዓ.ም በተመረጡ የግብይት ማዕከላት በዳሸን ካርድ እና በአሞሌ ግብይት ሲፈጽሙ ከግብይትዎ 5 % ተመላሽ ገንዘብ ያገኛሉ።ተመላሽ ገንዘብን የሚያገኙባቸውን...
05/01/2024

ከታህሳስ 15 እስከ ጥር 14፣ 2016 ዓ.ም በተመረጡ የግብይት ማዕከላት በዳሸን ካርድ እና በአሞሌ ግብይት ሲፈጽሙ ከግብይትዎ 5 % ተመላሽ ገንዘብ ያገኛሉ።
ተመላሽ ገንዘብን የሚያገኙባቸውን የንግድ ማዕከላትን ማስፈንጠሪያውን ተጭነው ይመልከቱ:

#ኢትዮጵያ

ህንድ ተጠልፋ የነበረችውን መርከብ ማስለቀቅ መቻሏን አስታወቀችየህንድ ባህር ኃይል እንደገለጸው የባህር ኃይሉ ኮማንዶዎች በአረቢያን ባህር  ተጠልፋ በነበረችው እና የላይቤሪያን ሰንደቅ አላማ ...
05/01/2024

ህንድ ተጠልፋ የነበረችውን መርከብ ማስለቀቅ መቻሏን አስታወቀች

የህንድ ባህር ኃይል እንደገለጸው የባህር ኃይሉ ኮማንዶዎች በአረቢያን ባህር ተጠልፋ በነበረችው እና የላይቤሪያን ሰንደቅ አላማ በምታውለበልበው መርከብ ላይ ማረፍ ችለዋል።

ስለጉዳዩ ማብራሪያ ያልሰጠው ባህር ኃይሉ አሁን ላይ የማጽዳት ዘመቻ እያካሄደ እንደሚገኝ ገልጿል።

የህንድ የጦር መርከብ ኤምቪ ሊላ ኖርፎልክ የተሰኘችው መርከብ በሶማሊያ ጠረፍ በሚገኘው የአረቢያን መጠለፏን ከሰማ ከአንድ ቀን ባልበለጠ ጊዜ ዛሬ ከሰአት በኋላ መያዝ ችሏል።
በመርከቧ ላይ 15 የሚሆኑ ህንዳውያን ሰራተኞች ነበሩ።

https://t.me/centrcommunication

የውጭ ዜና ፑቲን ለሩሲያ ለሚዋጉ የውጭ ዜጎች ዜግነት እንዲሰጣቸው ትዕዛዝ ሰጡ፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡  የሩሲያው ፕሬዝደንት ቬላድሚር ፑቲን በዩክሬን ለሩሲያ የሚዋጉ የውጭ ዜጎች እና ቤተሰቦቻቸው ...
05/01/2024

የውጭ ዜና
ፑቲን ለሩሲያ ለሚዋጉ የውጭ ዜጎች ዜግነት እንዲሰጣቸው ትዕዛዝ ሰጡ
፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቬላድሚር ፑቲን በዩክሬን ለሩሲያ የሚዋጉ የውጭ ዜጎች እና ቤተሰቦቻቸው ዜግነት እንዲያገኙ የሚያስችል አዋጅ ላይ መፈረማቸው ተገለጸ፡፡

የውጭ ዜጎች ፖስፖርቱን ለማግኘት ቢያንስ ለአንድ ዓመት የፈረሙበትን ኮንትራት ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።

በመደበኛው የሩሲያ ጦር እና መደበኛ ባልሆነ ጦር የተሳተፉ ሁሉ የዚህ መብት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ የፕሬዝደንት ፑቲን እርምጃ የውጊያ ልምድ ያላቸው የውጭ ዜጎች እንዲቀላቀሉ ለማበረታት ያለመ መሆኑ እየተገለጸ ሲሆን ሩሲያ ምን ያህል የውጭ ዜጎች በዩክሬን ውጊያ እንዳሰለፈች ይፋ አልተደረገም።

ኪም ጆንግ ኡን ደቡብ ኮሪያና አሜሪካ ጦርነት ከጀመሩ ጦራቸው ሀገራቱን “ከምድር እንዲያጠፋ” አዘዙየሰሜን ኮሪያው መሪ የ2024 የመጀመሪያውን ወታደራዊ ትእዛዝ አስተላልፈዋል። አሜሪካና ደቡብ...
05/01/2024

ኪም ጆንግ ኡን ደቡብ ኮሪያና አሜሪካ ጦርነት ከጀመሩ ጦራቸው ሀገራቱን “ከምድር እንዲያጠፋ” አዘዙ

የሰሜን ኮሪያው መሪ የ2024 የመጀመሪያውን ወታደራዊ ትእዛዝ አስተላልፈዋል። አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ በተጠናቀቀው 2023 የመከላከያ ትብብራቸውን አጠናክረዋል።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤👇
https://t.me/centrcommunication
https://t.me/centrcommunication

05/01/2024
አርብ የፍቅር ቀን❤ጌታ ሆይ ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ስትል በዕለተ አርብ በቆረስከው ስጋህ ባፈሰሰከው ደምህ ብለህ አቤቱ  ማረን ይቅርም በለን፡፡🙏🌷ሼር ሼር ሼር🤍💫
05/01/2024

አርብ የፍቅር ቀን❤

ጌታ ሆይ ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ስትል በዕለተ አርብ በቆረስከው ስጋህ ባፈሰሰከው ደምህ ብለህ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን፡፡🙏

🌷ሼር ሼር ሼር🤍💫

 #ሀርጌሳ " ሀገራችንን አልሸጥንም " - ሙሴ ባሂ አብዲባለፉት ቀናት ኢትዮጵያ የነበሩት የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ዛሬ ሐሙስ ዕለት ወደ ሀርጌሳ ተመልሰዋል።ፕሬዚዳንቱ ሀርጌሳ ሲገቡ ...
04/01/2024

#ሀርጌሳ

" ሀገራችንን አልሸጥንም " - ሙሴ ባሂ አብዲ

ባለፉት ቀናት ኢትዮጵያ የነበሩት የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ዛሬ ሐሙስ ዕለት ወደ ሀርጌሳ ተመልሰዋል።

ፕሬዚዳንቱ ሀርጌሳ ሲገቡ ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

አደባባይ ወጥቶ ለተቀበላቸው ህዝብ ባሰሙት ንግግር ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑ ገልጸዋል።

ፕሬዜዳንቱ " ሀገራችንን አልሸጥንም " ያሉ ሲሆን " ኢትዮጵያ የባህር ሃይል ጦር ሰፈር #በሊዝ ነው የምትከራየው " ብለዋል።

" ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ እውቅና ለመስጠትም ተስማምታለች " ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ መቼ እንደሆነ ቀኑን በግልፅ ባይናገሩም የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት #በቅርቡ ለሶማሌላንድ እውቅና እንደሚሰጥ በድጋሚ ለህዝባቸው ገልጸዋል።

" ይህ የሶማሌላንድ ህዝብ ላለፉት ሶስት አስርት አመታት የደረሰበት ትልቅ ስኬት ነው " ሲሉም ገልጸዋል።

ስምምነቱ በሁለቱም ወገን በኩል ፍላጎትና ጥቅማቸውን መሰረት ያደረገ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል ፤ ሶማሌላንድን እንደ ራሷ አንድ ግዛት የምትቆጥራትና የተፈረመው ስምምነት ሉዓላዊነቴን ጥሷል በሚል የተቃወመችው ሶማሊያ ውስጥ ዛሬ የተቃውሞ የአደባባይ ሰልፎች ሲደረጉ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል።

ፎቶ / ቪድዮ ፦ ሶማሌላንድ፣ ሀርጌሳ (ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 206 ዓ/ም)
#ምንጭ 👇👇👇

04/01/2024

ሚዲያ በሁሉም ለሁሉም አስፈላጊ ነው ፥ ምክንያቱም ሚዲያ የአንድ ሀገር መንግስት ላይ ሚና ይጫወታል።
ዛሬ ከታዘብኩት አንዱን ላጋራችሁ ከስር ፎቶው የምትመለከቱት የሚዲያ ባላበት ለልማት የሰጠበት ትኩረት ይገርማል። ስለዝህ ሁላችንም በያለንበት መስክ ለልማት እና ለስራ ቅድሚያ መስጠት ስንችል ለጦርነት ለዘረኝነት ለአድመኝነት እና ለሌሎች ተንኮል ተጠምደን እንውላለን። please የተፈጠርንበትን አላማ አንዘጋ ባለንበት ጠንክረን እንስራ።


Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Central communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category