Melkamu Ayano

Melkamu Ayano የወላይታን ታሪክ፣ ባህልና ወግ ለዓለም እናስተዋውቃለን። ሰርቶ ማሳየት፣ በውጤት የሚለካ ሕዝብ ልጅ ነንና።

05/06/2024
05/06/2024
05/06/2024
05/06/2024
ከገሱባ ከተማ አፈ ጉባኤ ጽ/ቤት ከመጡ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር አሁናዊ ተግባራት ያሉበትን ደረጃ  በመገመም ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ውይይታችንን አጠናቅቀናል።
05/06/2024

ከገሱባ ከተማ አፈ ጉባኤ ጽ/ቤት ከመጡ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር አሁናዊ ተግባራት ያሉበትን ደረጃ በመገመም ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ውይይታችንን አጠናቅቀናል።

24/05/2024
18/05/2024
ክልላዊ የባህልና ቱሪዝም ፌስቲቫልና ኤግዚቢሽን በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛልየባህልና ቱሪዝም ፌስቲቫልና ኤግዚቢሽን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝቦች ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነትን በሚ...
18/05/2024

ክልላዊ የባህልና ቱሪዝም ፌስቲቫልና ኤግዚቢሽን በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል

የባህልና ቱሪዝም ፌስቲቫልና ኤግዚቢሽን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝቦች ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነትን በሚያያንፀባርቅ መልኩ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በዝግጅቱ በክልሉ የሚገኙ 32ቱም ብሔር፣ ብሔረሰቦች የባህልና የቱሪዝም ሀብቶቻቸዉን እያስተዋወቁ ይገኛል።

"የባህልና ቱሪዝም ሀብቶቻችን ለመቻቻል ለሰላማችንና ለሁለንተናዊ ብልፅግናችን" በሚል መሪ ቃል ነዉ ነው የሚከበረው።

10/05/2024
10/05/2024
በጽ/ቤታችን በሕዋስ ውይይት በመቶ ቀናት ለማከናወን ያቀድናቸውን ዕቅዶች የተተገበሩትን በመለየት ቀሪ ዕቅዶች ላይ ሀሳብ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።ግንቦት 02/2016መልካሙ አያኖ የገሱባ ከ...
10/05/2024

በጽ/ቤታችን በሕዋስ ውይይት በመቶ ቀናት ለማከናወን ያቀድናቸውን ዕቅዶች የተተገበሩትን በመለየት ቀሪ ዕቅዶች ላይ ሀሳብ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።

ግንቦት 02/2016
መልካሙ አያኖ
የገሱባ ከ/ባ/ቱ/ጽ/ቤት

ዛሬ በጽ/ቤታችን የባለሙያ ትምህርት ማስረጃ ማጣራት ጋር በተያያዘ ውይይት አድርገናል። በዚህም የትምህርት ማስረጃ ከሰራተኞች እስከ ቀን 03/09/2016 እንዲያልቅ በመስማማት ዛሬ ተግባሩ እ...
08/05/2024

ዛሬ በጽ/ቤታችን የባለሙያ ትምህርት ማስረጃ ማጣራት ጋር በተያያዘ ውይይት አድርገናል። በዚህም የትምህርት ማስረጃ ከሰራተኞች እስከ ቀን 03/09/2016 እንዲያልቅ በመስማማት ዛሬ ተግባሩ እንዲጀመር ተደርጓል።

ሚያዚያ 30/08/2016
ገሱባ
የገሱባ ከ/ባ/ቱ/ጽ/ቤት

30/04/2024
22/04/2024
22/04/2024
22/04/2024
15/09/2023
24/09/2022

Gasuubba Ambaa Gadawa mantaa Hantalo Tasfayee 2015 M.L Wolaytta kochchaa laytta laamiyaa Gifaataa baalawu hashshu saruwan gattees giya lo"o ammuwa qofa aattidosona.

Wolytta dere asay benippe ha doommiddi aginaa qoodaa maaraan xeeruwaanne xumaa ceggenna giidi gatti qoodidi layttaa laammiddi yiidoogee qoncce.

Gidikkonne ha wolqqaama wolytta kochchaa oonatetta erissiyaa gifaataa baalay dumma dumma gaasotuun 1950 M.L ha doommiddi de'iya wodetun kaseegappe baalawu de'iya bonchchoy leeppi leeppi yiidogaa dumma dumma haydatinne he wodiyappe doommidi de'iya dere cimmatti qonccissoosona.

Gidoppe attiin ha nu oonatettaa erissiyaa gifaataa baalaay ubbakka masqalanne hara ammano baaletuurakka gayttennagaa ubbaakka hara eeqiyobaa gidennagaakka xaafettida haydatinne dere cimati dumma dumma ammano aawati yootoosona. Ha nu aawati, nuussi aattido an"ura gifaata baala mata wodiyappe ha doommidi wolaytta kochchay wolqqaama hanotaan boonchchidi ubbaakka ha baalay wolaytta dere asaa xalaala baala gidennan Kumetta Tophphiyanne salo gufantto baala gididi bonchettanadan wolaytta dere asaa ubbaynne xeelliyoogeti kushshetti oottanaw koshshees.

Ha nu wodiya yeletay nu laytta laamiya gifaata baalaa hara aybirakka gattennan nu oonatetta qonccissiya dumma sohoy immettiyo baalaa gidiyooga ammanidi ubbay bonchchana ha doomettida qaatta minttidi sinttawu kessana mala nu aawatetta issoy issoy kiyana koshshees giidosona gasuubba ambba gadaawa manta Hantalo Tasfaye.

INTTE LAYTTAA QOODITE LAYTTAY INTTENA QOODOPPO!
YOO! YOO! GIFAATAA HASHSHU GATTEES!

~~~~ ~~~~~ ~~~~ ~~~
Dumma dumma salo guffanto odota siyanawune kaalanawu hagappe xaaddera de"iyageeta go"ettite!

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063886034182

https://www.facebook.com/profile.php?id=100069228998852

https://t.me/wolaytazonegovntcommudailynews

https://twitter.com/gesuba_town?t=2KYow150s72fykqQNzFzeQ&s=09

19/09/2022

"ዓለም አቀፉ ሚዲያ በኢትዮጵያ ላይ አሻጥር እየሰራ ነው"
- አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)

ዓለም አቀፉ ሚዲያ ካለፉት 2 ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ ላይ እየሰራ ያለው አሻጥር ሰላም በማረጋገጥ ሂደቱ ላይ እንቅፋት ሆኖ መገኘቱን አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ገለጹ፡፡

በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን ተሿሚ የሆኑት አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ‘ዘ አፍሪካ ሪፖርት’ ከተሰኘው ተነባቢ መጽሄት ጋር በነበራቸው ቆይታ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

መንግስት ለሰብኣዊ እርዳታ አቅርቦት ብሎ አውጆት የነበረውን ለ5 ወራት የዘለቀውን የተናጠል የተኩስ አቁም በመጣስ አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል በቆቦ ግንባር ጦርነት መክፈቱ ወደ ዘላቂ ሰላም ለመግባት የነበረውን ተስፋ አጨልሞታል ብለዋል፡፡

ቡድኑ ባደረሰው ጥቃትም ለበርካታ ሰላማዊ ሰዎች ሞት፣ መፈናቀልና ቡድኑ በወረራቸው አካባቢዎች በርካታ መንደሮችን መዝረፉን እና ማውደሙንም አምባሳደር ሄኖክ ለመጽሄቱ ገልፀዋል፡፡

ይሁንእጂ ሰላምን ረግጦ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት እያደረሰ ያለውን ወራሪ ቡድን ያወገዘ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አካልም ሆነ ሽፋን የሰጠ ሚዲያ አለመኖሩ የሚያሳዝን ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ አሸባሪው ህወሓት የከፈተባትን 3ኛ ዙር ጥቃት ለመመከት ፣የህዝቡን እና የግዛት አንድነቷን ለማስጠበቅ እንዲሁም የቡድኑን መስፋፋት ለመከላከል ትኩረት እድርጋ እየሰራች መሆኗን አምባሳደሩ አስታውቀዋል፡፡

በግልጽ በርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ከሽብር ቡድኑ የወገኑ ሆነው እውነታ የሌላቸው እና አድሏዊ ዘገባዎችን ሲሰሩ በመቆየታቸው ለኢትዮጵያ ሰላም እንቅፋት ሆነው እንደቆዩባትም ገልጸዋል፡፡

"ወራሪና ተወራሪ እኩል ለምን እንደሚታይ ግራ ያጋባል" ያሉት አምባሳደሩ፣ዓለምአቀፉ ማበረሰብ እና ሚዲያዎች ከራሳቸው ጋር የታረቀ ስራ እንዲሰሩም ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላምና ውይይት ዝግጁ መሆኑን ቀደም ብሎ ገልጻ እያለ የሽብር ቡድኑ ከልቡ ያልሆነ ከድርጊቱ ጋር በሚቃረን መልኩ ወረራ ፈጽሞ እና ጦርነት አውጆ ስለሰላም ማውራቱም ሊወገዝ እደሚገባ አምበሳደር ሄኖክ ጠቁመዋል፡፡

እንደ ኢቢሲ ዘገባ፤ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ከሚፈልጉ ሀይሎች ሁሉ ሚዛናዊና ትብብር በተሞላበት መልኩ ለመስራት ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን የገለጹት አምባሳደሩ፣በተለይ አፍሪካ ህብረት በሚመራው መፍትሄ የማፈላለግ ሂደት ኢትዮጵያ ትኩረት ሰጥታ እንደምትሰራም አረጋግጠዋል ለ ዘ አፍሪካን ሪፖርት፡፡

11/09/2022

የገሱባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተስፋዬ ሀንጣሎ አዲሱን ዓመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጳጉሜ 05 ቀን 2014ዓ.ም
ገሱባ

የገሱባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተስፋዬ ሀንጣሎ አዲሱን ዓመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አዲሱን ዓመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ተስፋዬ ሀንጣሎ ኢትዮጵያ በዓለም ልብ ውስጥ ጽፋ ካስቀረቻቸውና ለትውልድም እንደማይሻር ቅርስ ካስተላለፈቻቸው አበይት መለያዎች መካከል ዋነኛው የዘመን መለወጫ በዓል ነው። አባቶቻችንም ከመላው ዓለም ጋር አቻ ሆነን እንድንሰለፍ አድርገው ሰርተውናል። በራስ መቆም፣ እራስን መምሰል፣ በራስ ማጌጥና የራስን ማሳየት።

ዓለም የሚፈራውንና ያማረውን በሚከተልበት በዚህ ዘመን የራሳችን የዘመን መለወጫ ከራሳችን የቀን አቆጣጠር እንዲኖረን መደረጉ፣ የራሳችን በዓላት እንዲኖሩን አድርገው ለሰሩን ቀደምት ክብር ይግባቸውና ከበዓሉ አከባበር ውጭ ለዓለም ገበያ እራሳችንና ታሪክ፣ ትውፊቶቻችንን ይዘን መቅረብ በሚገባን ዘመን ላይ ተገኝተናል።

2015 አዲስ ዓመት በዓል ከሌሎቹ ዓመታት ለየት የሚያደርገው ሀገራችንን ኢትዮጵያን ለማፈራረሱ ታሪካዊ ጠላቶቻችንና የውስጥ ባንዳዎች አብረው ሰላማችንን ለማደፍረስ፣ ከምንም በላይ 21ኛው ክፍለ ዘመን የማይፈልገውንና ጊዜ ያለፈበትን ጠብመንጃ በማንሳት ወንድም በሆነው ሕዝብ ላይ ለሶስተኛ ጊዜ ባነሳባት ማግስት ላይ የምናከብረው በመሆኑ በሁለት ስሜቶች ውስጥ ሆነን የምናከብረው በዓል ቢሆንም በፈተና ውስጥ ሆነንም ሀገራችን ከፈተናዎቿም በላይ እንደሆነች በማመን መልካም ምኞታችንን የምንቸርበት ነው።

አዲስ ዓመት ማክበር ትርጉም የሚኖረው በጊዜ ውስጥ ለማለፍ የምንችል ከሆነ ነው። ጊዜ ይዞን ለሚሄድ ሰዎች አዲስ ዓመት የሚባል ነገር የለም። የጊዜ ዑደት ከጥንት እስከዛሬ የታወቀ፣ የተለመደ ነገር በመሆኑ። በሌሎች ያልተደረገ ነገር በእኛ ላይ ስለማይደረግ፤ ከዚህ በፊት ያልሆነ ነገር ዛሬ አዲስ ነገር ስለማይሆን። ሁሉም ቀናት፣ ሁሉም ሳምንታት፣ ሁሉም ወራት አምናም ነበሩ።

በጊዜ ውስጥ የሚያልፉ ሰዎች አዲስ ዐሻራ በየዘመኑ ያሳርፋሉ። ትናንት ያልታሰበና ያልተደረገ አዲስ ዐሻራ። ታሪክን ይቀይሩታል፤ አስተሳሰብን ይቀይሩታል፤ የሰውን ልጅ የአኗኗር ዘይቤ ይቀይሩታል። አዲስ ዕይታ፣ አዲስ ዓለም፣ አዲስ ምዕራፍ፣ አዲስ መንገድ፣ አዲስ ሀብት፣ አዲስ ቴክኖሎጂ፣ አዲስ አሠራር፣ አዲስ ዘይቤ ይፈጥራሉ። በዚህም ምክንያት ትናንትን ከትናንት ወዲያ፣ ዛሬን ከትናንት፣ ነገን ከዛሬ ይለዩታል። አዲስ ነገር በማድረግ፣ ዘመኑ ብቻ ሳይሆን ቀኑም አዲስ እንዲሆን ያደርጋሉ። ዓለም ዘወትር ስታስታውሳቸው የምትኖረው እንዲህ ያሉትን ሕያው ሰዎች ነው። ጊዜ ብዙዎችን ሲሽር በማይሻር ሥራቸው ሕያውነትን ተጎናጽፈው ጊዜን ራሱን አሸንፈውታልና።

በመሆኑም በዘመናት ውስጥ ከማለፍ ባለፈ ዘመኑን ሊያመላክቱ የሚችሉ እውነቶችን መስርቶ ማለፍን ይሻልና። ስለሆነም በዓሉን ስናከብር ወገን ላጡት ወገን በመሆን፣ በማምሻ ዕድሜያቸው ጧሪ ቀባሪ ላጡት ከጎናቸው በመሆን፣ በአጠቃላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ በመቃኘት እጅ ለእጅ ተያይዘን የምንሻገርበት ዓመት እንዲሆን እየጠየቅሁ ዓመቱ የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ።

እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

~~~~ ~~~~~ ~~~~ ~~~
የተለያዩ ዓለም አቀፍ፣ አሁጉራዊ፣ ሀገራዊ፣ ዞናዊና ከተማዊ መረጃዎችን ለመከታተል የሚከተሉ የፌስ ቡክና ቴሌግራም ገፅዎችን ይጎብኙ፣

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063886034182

https://www.facebook.com/profile.php?id=100069228998852

https://t.me/wolaytazonegovntcommudailynews

https://twitter.com/gesuba_town?t=2KYow150s72fykqQNzFzeQ&s=09

16/07/2022
28/06/2022

በንግድና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን

የነዲጅ ውጤቶች የሥርጭት፣ የርክክብና የሽያጭ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 904/2014

ሰኔ 2014 ዓ.ም
አዱስ አበባ

የፌዳራል መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን ሥሌጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር
1263/2014 አንቀጽ 19(4) መሰረት የንግድና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ይህንን መመሪያ
አውጥቷሌ፡፡

አንቀጽ 1 አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ “የነዳጅ ውጤቶች የሥርጭት፣ የርክክብና የሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር
904/2014” ተብሎ ሉጠቀስ ይችሊሌ፡፡

አንቀጽ 2 ትርጓሜ

በዚህ መመሪያ ውስጥ የቃሉ አገባብ የተለየ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር፡-

1/ “የነዳጅ ውጤት” የሚሆኑት ከተፈጥሮ ድፍድፍ ነዳጅ እና ከፔትሮልየም ጋዝ፣ ባዮ-ፊውል
ወይም ሴንቴቲክ ነዳጅን ከማጣራት ወይም ከማቀናበር የተገኘ ንፁህ ወይም አግባብ በሆነው
መንገዴ የተደባለቀ የነዳጅ ውጤት ሆኖ ቤንዚንን፣ ኬሮሲንን፣ ናፍጣን፣ ቀላልና ከባድ ጥቁር ናፍጣንና የአውሮፕላን ነዳጅን ያካትታል፣

2/ “የግብይት ተሣታፊ” ማለት የነዳጅ ውጤቶችን የሚያስመጣ፣ የሚያጣራ፣ የሚያደበላልቅ፣ የሚያከማች፣ የሚያከፋፍል፣ የሚቸረችር፣ የሚያጓጉዝ፣ የሚልክ እና መሰል ተግባራትን እንዲያከናውን ፈቃድ የተሰጠው ሰው ነው፤

3/ “የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት” ማለት ነዳጅና የኤሌክትሪክ ሥራዎችን ሇማከናወን
የተቋምና የሙያ ብቃትን በማረጋገጥ በባለሥሌጣኑ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ነዉ፤

4/ “ባለሥልጣን” ማለት የነዲጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ነው፡፡

5/ “ኩባንያ’’ ማለት የነዳጅ ውጤቶችን ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በጅምላ በመግዛት
በማደያዎች እና በቀጥታ ተጠቃሚዎች በማሠራጨት ህጋዊ የሥራ ፈቃድ ያለው ነው፡፡

6/ “ድርጅት’’ ማለት የኢትዮጵያ ነዲጅ አቅራቢ ዴርጅት ነዉ፡፡

7/ “የነዳጅ አዳይ” ማለት ነዳጅን ከነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያ ገዝቶ ለተጠቃሚውና ነዳጅ ማደያ በለባቸው ከተማና አካባቢዎች በችርቻሮ ለሚቸረችር ሰው የሚሸጥ ነው፡፡

8/ “ርክክብ” ማለት ከወደብና ከዲፖ የተጫኑ የነዳጅ ውጤቶችን በማደያ ላይ በአጓጓዡና
በነዳጅ አዳዩ መካከል የሚደረግ የርክክብ ሥርዓት ነው፡፡

9/ “ማጓጓዣ” ማለት የነዳጅ ውጤቶችን ከወደብና ከዴፖዎች በመጫን ወደ ተለያዩ የክፍሎች የሚያጓጉዝ የነዳጅ ቦቴ ነው፡፡

አንቀጽ 3 የመመሪያው አስፈሊጊነት

በነዳጅ የግብይት ሰንሰለት ግልፅነት ያለው፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል፣ የነዳጅ
ትራንስፖርትና የርክክብ ሥርዓት በመዘርጋት፣ የምርቶቹን ተደራሽነትና የህብረተሰቡን
ተጠቃሚነት በማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

አንቀጽ 4 የተፈጻሚነት ወሰን

ይህ መመሪያ ከወደብ እስከ ነዳጅ ማደያዎች ድረስ ባለው የሥርጭት፤የርክክብና የሽያጭ ሂደት
ላይ ተሳታፊ በሆኑና የቁጥጥር ሚና ባላቸው አካላት ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

አንቀጽ 5 የባለሥልጣኑ ተግባራት

ባለሥልጣኑ የሚከተለትን ተግባራት ያከናውናል፡-
1/ የነዳጅ ሥርጭትና ርክክብ መመሪያን ተግባራዊነት በተመለከተ በክልሎች እና ከተማ
አስተዳደሮች የሚሠሩ ሥራዎችን ያስተባብራል፣ ይከታተላል፣

2/ ነዳጅ በመጫን ወደ ሥምሪት የሚገቡትን የማጓጓዣዎችና የማደያዎችን መረጃ ከኩባንያዎች በመቀበሌ በድርጅቱ ያስተላልፋል ፣ አፈጸጸሙን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣

3/ ማጓጓዣዎቹ በተሰጣቸው የሥምሪት መዳረሻ በሆነው የነዳጅ ማደያ ደርሰው ማራገፋቸውንና
ህጋዊ ርክክብ መፈጸሙን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ በጉዞ ላይ እያሉ በማስቆም መረጃ የማጣራትና ከመስመር/መዳረሻ ዉጭ ሲጓዝ የተገኘውን የነዳጅ ተሽከርካሪን በህግ ቁጥጥር
ሥር እንዲውል ያደርጋል፣

4/ ከጅቡቲ ወደብና ከማሰራጫ ዴፖዎች የተጫነው የነዳጅ ውጤት በመረካከቢያ ሰነድ
እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ የነዳጅ ኩባንያዎችና ማደያዎች ሥራ ላይ እንዲያውሉት
ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፣

5/ በዘርፉ ያለ የግብይት ተዋናዮች የተሰጣቸውን ተግባራት በተገቢው ሁኔታ መፈጸማቸውን
ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
6/ ዕለታዊ የነዳጅ ውጤቶች የጭነት መረጃ በሲስተም በማደራጀት በክልሎች፣በከተሞችና
በማደያዎች መካከል ተደራሽነትና ፍትሐዊነት መኖሩን ይከታተላል፣ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፣

7/ በአሳማኝ ምክንያቶች ላይ ተመስርተው የሚቀርቡ የመድረሻ ለውጥ ጥያቄዎችን መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል፣ተገቢው ፈቃድ ሳይሰጣቸው ስምሪት ለውጥ በሚያደርጉ ኩባንያዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዳል፣ህጋዊ እርምጃ እንዱወሰድ ያደርጋል፡፡

8/ የነዲጅ መስፈሪያ ዱስፔንሰርና መሇኪያዎች በየዓመቱ ካሉብሬት/በትክክሌ መስራታቸውን
በማረጋግጥ/ ተዯርገው ስለትክክለኛነቱ የሚገልጽ እስቲከር መለጠፋቸውን ይከታተላል
ይቆጣጠራል፣

አንቀጽ 6 የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የንግድ ቢሮዎች ኃሊፊነት

1/ በክልል እና በከተማ መስተዳድር ውስጥ ለሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች በየቀኑ የሚላኩትን
የነዲጅ ውጤቶች መረጃ ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በመቀበል በተዋረድ ላሉት
የንግድ ቢሮ አካላትና የነዳጅ ማደያዎች ያስተላልፋል፣

2/ ነዳጅ ከተላከለት የነዳጅ ማደያ መድረሱንና መራገፉን ያረጋግጣል፣ ከዚህ መመሪያ ጋር
በተያያዘው ህጋዊ መረካከቢያ ሰነድ አማካይነት ርክክብ እንዲፈጸም ያስተባብራል፣
ይከታተላል፣

3/ የዞን ንግድ መምሪያዎች እና የወረዳ ንግድ ጽ/ቤቶች ክትትልና ቁጥጥር እንዲያደርጉ
ያስተባብራሌ፤ በትክክል መፈጸሙን ያረጋግጣል፣

4/ ከዞን፣ ከወረዳዎችና ከከተማ መስተዳድሮች የነዳጅ አቅርቦትና ሥርጭትን የተመለከቱ
ሪፖርቶችን አደራጅቶ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ና ለባለሥጣኑ ያስተላልፋል።

አንቀጽ 7 የዞን ንግድ መምሪያ የሥራ ኃሊፊነት

1/ ከክልል ንግድ ቢሮ የሚከተሉትንን ዕለታዊ የነዳጅ ስርጭት መረጃ በሥሩ ለሚገኙ
ወረዳዎችና ከተሞች ያሰራጫል፤ በመረጃው መሠረት ነዳጁ በተመዯደበላቸው ማደያዎች
ስለመድረሱና ተገቢው ርክክብ ስለመፈጸሙ በሚልኩለት ዕለታዊ የርክክብ ሪፖርት
መሠረት ክትትል ያደርጋል፤ ወረዳዎችንና ከተሞችን ያስተባብራል፣

2/ በተመደበለት ከተማና ነዳጅ ማደያ በወቅቱ ያልደረሰ ወይም ሳይደርስ የቀረ የነዳጅ ቦቴን
በተመለከተ ተገቢው ክትትል እንዲደረግ ለክልል የንግድ ቢሮ ከዝርዝር መረጃ ጋር ያሳውቃል፤

3/ ነዳጅ ማደያዎች የተራገፈውን ነዳጅ ለተጠቃሚው በትክክል እየተሸጠ መሆኑንና
እንዲስፈሊጊነቱ ማደያ በለባቸው ከተማዎችና አካባቢዎች በተዘረጋው ሥርዓት መሠረት

እየተከፋፈለ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ በወረዳዎችና በከተሞች የሚደረገውን የክትትልና
የቁጥጥር ሥራዎችን ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፣ በየወሩ ልብክልል ንግድ ቢሮ ሪፖርት ያደርጋሌ፡፡

አንቀጽ 8 የከተማ ወይም የወረዳ ንግድ ጽ/ቤት የሥራ ኃሊፊነት

1/ ነዳጅ አዳዩ የነዳጅ መረካከቢያ እና የሽያጭ ሰነድችን አደራጅቶ መያዙን ይቆጣጠራል፣

2/ በከተማው ወይም በወረዳው የነዳጅ ሥርጭት፣ ርክክብና የሽያጭ አፈፃፀሙን የሚከታተል ባለሙያ በቋሚነት ይመደባል፤ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፤

3/ የተመደበው ባሇሙያ አስቀድሞ በሚደርሰው ዕለታዊ የጭነት መረጃ መሰረት ተገቢውን
ክትትል በማድረግና በቦታው ላይ በመገኘት የተሣለጠ ርክክብ እንዲፈፀም ማድረግ
አለበት፤

4/ ለማደያው የተላከው የነዳጅ ቦቴ በቦታው ደርሶ ከማራገፉ በፊት እሽጉ ያልተከፈተ
መሆኑንና የተላከው የነዳጅ መጠን በትክክል መራገፉን በማረጋገጥ ከዚህ መመሪያ ጋር
ተያይዞ ባለው የመረካከቢያ መዝገብ ላይ እንዲመዘገብ በማድረግ በአሽከርካሪውና በነዳጅ
አዳዩ መካከል ርክክብ መፈጸሙን ባለሙያው ማረጋገጥ አለበት፤ በባለሙያው
የተፈረመበትና የወረዳው ንግድ ጽ/ቤት ማህተም የተደረገበት የርክክብ ማስረጃ ለሾፌሩና
ለነዳጅ አዳዩ ይሰጣል፤

5/ በነዳጅ ማደያው የተራገፈው ነዳጅ በሚኒስቴር መ/ቤቱ በተወሰነው የችርቻሮ ዋጋ መሠረት
ለተጠቃሚው እየተሸጠ መሆኑን ይከታተላል፣ይቆጣጠራል፣

6/ በነዳጅ ማደያ የተራገፈውና የተሸጠው የነዳጅ ዓይነትና መጠን በየወሩ ለዞኑ ንግድ መምርያ
ሪፖርት ያደርጋል፣

7/ የነዳጅ መስፈሪያ ዲስፔንሰርና መለኪያዎች በየዓመቱ ካሊብሬት/በትክክል መስራታቸውን
በማረጋግጥ/ ስለትክክለኛነቱ የሚገልጽ እስቲከር መለጠፍ አለባቸው፣

8/ በመመሪያው መሠረት በማይፈጽሙ አካላት ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፣
እንዲወሰድ ያደርጋል።

አንቀጽ 9 የኢትዮጵያ ነዲጅ አቅራቢ ዴርጅት ኃሊፊነት

1/ ከባለሥልጣኑ በሚላክለት የነዳጅ ማደያዎችና የማጓጓዣ ቦቴዎች መረጃ መሠረት የነዳጅ
ሽያጭና የጭነት አገልግሎት ከተሟላ የጉዞ ሰነድች ጋር ይሰጣል፣

2/ የነዳጅ ቦቴዎች ከወደብ ወይም ከአገር ውስጥ ዴፖዎች ነዳጅ ጭነው ከመውጣታቸው በፊት የነዳጅ ተረካቢ መዳረሻ የሚያመለክት ክልል፣ከተማ፣የነዳጅ ማደያውና የባለቤቱ ስም፣
የተሸከርካሪው ታርጋ ቁጥር፣ የጫነው የነዳጅ ዓይነትና መጠን፣የሾፌሩ ሥምና ስልክ ቁጥር
እንዱሁም የነዳጅ የጭነት ሰነድ (FDC) ቁጥር የያዘ ጽሑፍ ከረዳት ሾፌሩ መቀመጫ ፊት
ለፊት ባለው ሥፍራ መለጠፍ አለበት፣

3/ የየዕለቱን የነዳጅ ውጤቶች የሥርጭት መረጃ ለባለስልጣኑና ለሚመለከታቸው አካላት
በየቀኑ ያስተላልፋል፣

4/ በሚኒስቴሩ በሚወሰነው የጊዜ ገደብ መሠረት ለጭነት የሚቀርቡ የነዳጅ ቦቴዎች የጂ.ፒ.ኤስ
ቴክኖልጂ የተገጠመላቸው መሆኑን በማረጋገጥ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል።

5/ ከወደብ ወይም ከሀገር ውስጥ ዴፖዎች ነዳጅ የጫነ ማጓጓዣ በተመደበለት መድረሻ
በማድረስ ነድልጁን ስለማራገፉና ተገቢውን ርክክብ ስለመፈፀሙ ከወረዳው ወይም ከከተማ
አስተዳደሩ ንግድ ጽ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሲያቀርብ ብቻ ለአሽከርካሪው ቀጣይ የጭነት
አገልግሎት ይሰጠዋል፣

6/ ይህ መመሪያ በሚኒስቴር መ/ቤቱ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ከስድስት ወራት የዕፎይታ ጊዜ
በኋሊ የየኩባንያቸውን ዓርማ ወይም ምልክት ለጥፈው ለሚቀርቡ የነዳጅ ቦቴዎች ብቻ
አገልግሎት ይሰጣል፣

7/ ከባለሥልጣኑ በሚሰጠው የፅሁፍ ውሳኔ መሠረት የታገዱ ኩባንያዎች፣ ማደያዎችና
ተሽከርካሪዎች እንዳይስተናገደ ያደርጋል፣

አንቀጽ 10 የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ኃሊፊነት

1/ ይህን መመሪያ ለማደያዎች፣ ለትራንስፖርት ማህበራትና ባለንብረቶችና ለአሽከርካሪዎች
በማድረስ እንዲያዉቁትና እንዲተገብሩት የማድረግ ኃሊፊነት አለበት፣

2/ የመንገድን ሁኔታ እና ርቀት በማገናዘብ አሽከርካሪው ከጭነት መነሻ እስከ መድረሻው ድረስ የሚወስድበትን የጊዜ ገደብ ይወስናል። ለባለሥልጣኑና ለሚመለከታቸው ያሣውቃል፤
አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በላይ ዘግየተው በሚደርሱ አሽከርካሪዎች ላይ ተገቢውን የእርምት እርምጃ ይወስዳል፣

3/ ነዳጅ የጫነ አሽከርካሪ ማሽከርከር የሚችለው ከንጋቱ 10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት
ባለው ጊዜ ብቻ መሆኑን ለአጓጓዡ በማሣወቅ ይከታተላል፣ይቆጣጠራል፣

4/ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 3 የተገላለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ ኩባንያዎች በተገለፀው ገደብ
ውሰጥ የየራሣቸውን የማሸከርከር የጊዜ ገደብ መወሰን ይችላል፤

5/ ኩባንየው የጭነት ስምሪት ለድርጅቱ ሲሰጥ ለባለሥልጣኑ በኢሜይል ወይም በኢንተርኔት
ወዲያውኑ ማሳወቅ አለበት፣

6/ ነዳጅ ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ተደራሽ እንዲሆን የእያንዲንደን የነዳጅ ማደያ ፍላጏትና
ወቅታዊ አቅርቦቱን ያገናዘበ ፍትሃዊ ስርጭት ማድረግ አለበት፣

7/ የነዳጅ አጓጓዥ ተሸከርካሪዎች ሥምሪት ሲሰጣቸውና ነዳጅ ጭነው ሲንቀሳቀሱ የተሟላ
የጭነት ሰነድ መያዛቸውን ማረጋገጥ አለበት፣

8/ ከወደብና ከሀገር ውስጥ ዴፖ የተጫነው ነዳጅ ለታዘዘለት ማደያ ወይም ሌላ መድረሻ
በትክክል መድረሱንና መራገፉን የመከታተልና የማረጋገጥ ሃሊፊነት አለበት፤ ይህንኑ
ለባለስልጣኑ በየቀኑ የማሳወቅ አለበት፣ ይህን ካሌፈጸመ በህግ ተጠያቂ ይሆናል፤

9/ ሚኒስቴሩ በሚወስነው የጊዜ ገደብ ውስጥ የኩባንያውና ከኩባንያው ጋር ውል ገብተው
የሚሠሩ የነዳጅ ቦቴዎች ጂ.ፒ.ኤስ እንዲገጥሙ ማድረግና መደገፍ አለበት፣

10/ በወደብ፣ በመንገድ ላይ እና በመድረሻ ቦታዎች የነዳጅ ቦቴዎች ላይ አደጋ ሲከሰት
መንስኤዉን በመለየት በ24 ሰዓት ዉስጥ ለባለሥልጣኑ ሪፖርት ማድረግ አለበት፣

11/ በኩባንያዉ ወይም በግለሰብ የሚገነባው ማደያ የኩባንያዉን የደረጃና የድህንነት
መስፈርቶችን አሟሌቶ የተጠናቀቀ መሆኑን በማረጋገጥ ነዳጅ የማቅረብ ዉል መግባት
አለባት፣

12/ የአሽከርካሪዎችን የሥራ አፈጻጸም የመከታተል፣የማብቃትና ጉድለት ባለባቸው ላይ እርምጃ የመውሰድ ሃሊፊነት አለበት፣

13/ የቦቴ አሸከርካሪው አስቀድሞ የጫነው ነዳጅ እንዲያደርስ የታዘዘበት ማደያ ማድረሱንና
ማራገፉን ሳያረጋገጥ ዳግም ስምሪት መስጠት የለበትም፣

14/ የእያንዳንዱን ማደያ፣ ተሸከርካሪና አሽከርካሪ ትክክለኛ መረጃ አድራጅቶ መያዝ አለበት፤

15/ የመድረሻ ስምሪት ለውጥ ማድረግ ሲያስፈልገው በቂ ምክንያት መኖሩን በማረጋገጥና ማስረጃ በማያያዝ ባለሥልጣኑን ማስፈቀድ አለበት፣

16/ በተለያየ ምክንያት ከስምሪት የወጡ ተሸከርካሪዎችና ሥራ ያቆሙ ማደያዎች ሥራ
ካቆሙበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ለባለሥጣኑ ማሳወቅ አለበት፣

17/ በነዳጅ ማደያዎች የተተከለ የነዳጅ የመቅጃ ማሽኖችን የመጠገን እና ለማደያው
ኦፕሬተርና ሠራተኞች ስለነዳጅ አያያዝና ደህንነት በተመለከተ ስልጠና መስጠት አለበት፣

18/በነዳጅ ግብይት ለመሣተፍ የተዘጋጁ አዳዲስ ተሸከርካሪዎችና ማደያዎች ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ለባለሥልጣኑ ማሳወቅና ማስመዝገብ አለበት፣

19/ይህ መመሪያ በሚኒስቴሩ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ባለት የስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ
የሚያስተዳድራቸው ቦቴዎች በሙሉ የኩባንያውን ዓርማ ወይም ምልክት ለጥፋው እንዲሰማሩ ያደርጋል፤

20/ ሥራ ባቆመና በጥገና ላይ ባለ የነዳጅ ማደያ ስም ነዳጅ መሸጥም ሆነ መጫን የለበትም፣

21/ በአንድ ማደያ ስም የተጫነን ነዳጅ ለሁለት ማደያዎች ማካፈል ካስፈለገ ከመነሻው
በሁለቱም ማደያዎች ስም የጉዞ ሰነዴ መዘጋጀት አለበት፤ ይህን ማድረግ ያልተቻለ እንደሆነ
ቦቴው ከመድረሱ በፊት የሁለተኛውን ማደያ ሥም ለሚመለከታቸው አካላት ማሣወቅ አለበት፤

22/ ከወደብና ከዴፖ የተጫነው ነዳጅ በእያንዳንደ ነዳጅ ማደያ ደርሶ በመረካከቢያ ሰነድ
ርክክብ እንዲደረግ ማድረግ አለበት፣

23/ የነዳጅ ኩባንያዎች የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን በመጠቀም ግዥና ሽያጭ ማከናወን
አለባቸው፡፡

አንቀጽ 11 የነዲጅ አዳይ ኃላፊነት

1/ ከብለሥልጣኑ በሚሰጠው የርክክብ ቅፅ መሠረት የነዳጅ ርክክብ መዝገብ ያደረጃል፣ ላለች
የነዲጅ ርክክብና የሸያጭ ሰነድችን አሟሌቶና አደራጅቶ መያዝ አለበት፣

2/ ነዳጅ የጫነ ተሽከርካሪ ከማደያው ሲደርስ የቦቴው እሽግ አለመከፈቱን በማረጋገጥ የወረዳው ወይም የከተማው አስተዳደር የንግድ ጽ/ቤት ሠራተኛ በተገኘበት ከአሽከርካሪው ጋር ርክክብ ይፈፅማሌ፤ ስለመረከቡ በንግድ ጽ/ቤቱ ተወካይ የተረጋገጠ ማስረጃ ለአሽከርካሪው መስጠት አለበት፣

3/ በርክክብ ወቅት አሽከርካሪው በተቀመጠለት የመድረሻ ጊዜ ውስጥ መድረሱን በማረጋገጥና
በመዝገቡ ላይ የተቀመጡትን መጠይቆች በሙለ በትክክል በመሙላት አሽከርካሪውን ማስፈረም አለበት፣
4/ የነዳጅ አዳዩ በሚመለከታቸው ተቆጣጣሪ አካላት ሲጠየቅ መዝገቡን የማቅረብና የማሣየት
ግዴታ አለበት፣

5/ በነዳጅ መጠን መለኪያ ፍልው ሜትር የተለካውና የቦቴው ካሉብሬሽን ከሚያሰየው መጠን ጋር በማመሳከር ትክክለኛነቱን አረጋግጦና መዝግቦ ለአሽከርካሪው መስጠት አለበት፣

6/ በቦቴው ካሉብሬሽን እና በፍልው ሜትሩ መካከል የመጠን ልዩነት ካጋጠመ ልዩነቱ
በኩባንያው፣ በትራንስፖርተሩ መካከል ባለው ውል መሰረት እልባት እንዲያገኝ ይደረጋል፣

7/ ነዳጅ አዳዩ በማደያው የነዳጅ መጠን መለኪያ ፍልው ሜትር ማስገጠም አለበት፣

8/ የነዳጅ መጠን መለኪያ ፍልው ሜትር በሁለም የነዳጅ ማደያዎች ተገጥመው የሚጠናቀቅበት የጊዜ ገደብ በሚኒስቴሩ ይወሰናል፣

9/ የነዳጅ ማደያ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ መጠቀም አለበት፣ በቀጣይ አገልግሎት
አሰጣጥን የሚያቀላጥፍ አውቶማቲክ የሽያጭ እና የደረሰኝ ማሽን ማስገጠምና መጠቀም
አለበት፣

10/በነድልጅ ማደያው የተራገፈው የነዳጅ ዓይነትና መጠን አስመልክቶ በተረከበበት ዕለት
በአካባቢው ለሚገኘው የንግድ ጽ/ቤት እና ለኩባንያው በጽሑፍ ሪፖርት ማድረግ አለበት፣

11/ማንኛውም ነዳጅ አዳይ የነዳጅ ውጤቶችን ሚኒስቴሩ በየጊዜው በሚወስነው የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እና በሚወጣው የሕዝብ ማስታወቂያ መሠረት መሸጥ አለበት፣ በሚኒስቴሩ ከተወሰነው ዋጋ በላይ በሚሸጥ የነዳጅ አዳይ ላይ የአካባቢው ንግድ ፅ/ቤት አስተዲደራዊና ህጋዊ እርምጃ መውሰድ አለበት፤

አንቀጽ 12 የነዳጅ ቦቴ ባለንብረት ወይም የትራንስፖርት ማህበራት ኃላፊነት፣

1/ ይህንን መመሪያ ለአሽከርካሪዎች የማድረስ፣እንዲያውቁትና እንዲተገብሩት የማድረግ ኃላፊነት አለበት፣

2/ ተሸከርካሪው ነዲጅን ሇማጓጓዝ የሚያስችሇው የካሉብሬሽንና የብቃት ማረጋገጫ
ሰርትፊኬት እንዱኖረው ማዴረግ አሇበት፣

3/ ሚኒስቴሩ በሚወስነው የጊዜ ገዯብ ውስጥ በነዳጅ ቦቴዎች ላይ በኩባንያዉ መስፈርት
መሠረት ጂ.ፒ.ኤስ ማስገጠም አለበት፣

4/ በዚህ መመሪያ አንቀፅ 12 ንዑስ አንቀፅ 5 እና 6 መሠረት ከነዳጅ አዳዩ ጋር የነዳጅ
ርክክብ እንዲፈፀም ያደርጋል፤

5/ አሽከርካሪው ሊኖረው የሚገባውን የሥራ ብቃትና ዲሲፒሊን ያሟሉ መሆኑን እና
ተጠያቂነትን ለያረጋግጥ በሚያስችል አኳኋን ቅጥር መፈጸም አለበት፣

6/ የተሸከርካሪውን ስምሪት የመከታተልና ችግሮች ሲኖሩ በፍጥነት ማስተካከል አለባቸው፣

7/ የነዳጅ ውጤቶችን የማጓጓዝ ሂደቱ አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት እንዳይስተጓጎል መከታተል
አለበት፣

8/ የእያንዲንደን ተሸከርካሪ እና አሽከርካሪ ሙለ መረጃ አዯራጅቶ መያዝ አሇበት፣
ሲጠየቅም ጉዲዩ ሇሚመሇከታቸው ተቆጣጣሪ አካሊት ማቅረብ አሇበት፣
9/ በነዲጅ ቦቴዎች ሊይ ኩባንያዎች አርማቸውን ወይም ምሌክታቸውን እንዱሇጥፉ መተባበር
አሇበት፣
10/ በነዲጅ ቦቴዎች ሊይ ከረዲት ውጭ ላሊ ሰው እና ህገወጥ ዕቃ እንዲይጭን ሇአሽከርካሪው
ማሳወቅ አሇበት፣
11/ ነዲጅ የጫነ ቦቴ ከንጋቱ 10 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ብቻ እንዱጓዙ ማዯረግ
አሇባቸው፡፡
12/ አሽከርካሪዎች የተሰጣቸውን ሥምሪት ተቀብሇው እንዱፈፅሙ መከታተሌና መቆጣጠር
አሇበት፤
13/ አሽከርካሪዎች ያሇበቂ ምክንያት ነዲጅ ጭነው እንዲይቆሙ መከታተሌ አሇበት፤
አንቀጽ 13 የነዲጅ ቦቴ አሽከርካሪዎች ኃሊፊነት
1/ ከወዯብ ወይም ከሀገር ውሰጥ ዳፖ የተረከበውን ነዲጅ ሇተጫነሇት ማዯያ ወይም
መዲረሻ በተቀመጠሇት የጊዜ ገዯብ ውሰጥ በማዴረስና የወረዲው ወይም የከተማው ንግዴ
ፅ/ቤት ሠራተኛ በተገኘበት በመረካከቢያ መዝገብ በማስመዝገብ ርክክብ መፈፀም
አሇበት፤ የርክክብ ሰነድችን በጥንቃቄ በመያዝ ሇሚመሇከታቸው ይሰጣሌ፤
2/ በዚህ መመሪያ አንቀፅ 12 ንዑስ አንቀፅ 5 እና 6 ሊይ በተገሇፀው አግባብ ከነዲጅ አዲዩ
ጋር የነዲጅ ርክክብ ማዴረግ አሇበት፤
3/ በኩባንያው በኩሌ የስምሪት ሇውጥ ሲያጋጥም ጥያቄው ሇባሇሥሌጣኑ ቀርቦ ስሇመፈቀደ
የጽሑፍ ማስረጃ ሳይዯርሰው ነዲጁን ወዯላሊ መዲረሻ መውሰዴ የሇበትም፣
4/ የነዲጅ ቦቴውን እሽግ ሇተጫነሇት የነዲጅ ማዯያ ዯርሶ በነዲጅ አዲዩና በንግዴ ጽ/በት
ሠራተኛው ታይቶና ትክክሇኛነቱ ተረጋግጦ እስኪፈታ ዴረስ የመጠበቅ ግዳታ አሇበት፣
5/ የተሸከርካሪውን ስምሪት ሇመቆጣጠር የሚገጠሙትን ጂፒኤስ እና ላልች መሣሪያዎችን
በጥንቃቄ የመያዝ ግዳታ አሇበት፣

6/ ነዳጅ ጭኖ በሚንቀሳቀስበት ወቅት የተሟላ የጉዞ ሠነዶችን መያዝ አለበት፣

7/ በነዳጅ ቦቴዎች ላይ ከረዳት ውጭ ያለ ሰው እና በህግ የተከለከሉ ዕቃዎችን መጫን
የለበትም፣

8/ ኩባንያ በቦቴ ላይ የሾፌር ረዳትን የመጠቀም ሁኔታን በራሱ አሠራር ሊወስን ይችላል፣

9/ ነዳጅ የጫነ አሽከርካሪ የሥራ ሠዓት ከንጋቱ 10 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ሲሆን
ኩባንያው ይህንኑ ያገናዘበ የሥራ ሰዓት መወሰን ይችላል፣

10/ የነዳጅ ቦቴ አሽከርካሪ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 8 ላይ በተመለከተው የሥራ ሰዓት
ወቅት ለመመገብና ለዕረፍት በአንድ ቦታ ከ2 ሰዓት በላይ መቆም የለበትም፡፡
ከተጠቀሰው ጊዜ በሊይ ያለበቂ ምክንያት ቆሞ በተገኘ የቦቴ አሽከርካሪ ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል፤

11/ አሽከርካሪው የጫነውን ነዳጅ በህገወጥ ተግባር ላይ ካዋለ በህግ ተጠያቂ ይሆናል፣

12/ የጫነውን ነዳጅ ከተጫነለት መድረሻ ውጭ በሌላ ማደያ ካራገፈ ከባለማደያው ጋር
በጋራ፣ በህግ ተጠያቂ ይሆናል፣አስተዳደራዊ እርምጃም ይወስዳል፣

13/ ነዳጅ ጭኖ በጉዞ ላይ እያለ በተቆጣጣሪ አካላት የሚጠየቀውን መረጃ የመስጠት ወይም
የማሳየት ግዴታ አለበት፡፡

አንቀጽ 14 የነዲጅ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ኃላፊነት

1/ ባሇሙያው ቁጥጥር በሚያደርግበት ወቅት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ከሚመለከተው
የአከባቢ ፖሊስ እና የፍትህ አካላት ድጋፍ መጠየቅ ይችላል፣

2/ ባለሙያው ተቆጣጣሪ ስለመሆኑ የሚገልፅ የመስሪያ ቤት መታወቂያ ወረቀት እና
የሥራ ትእዛዝ ደብዳቤ መያዝና ቁጥጥር ለሚደረግበት አካል ወይም ባለቤት ማሳየት
አለበት፤

3/ በቁጥጥር ሥራ ወቅት የታየውን ጉድለት ለድርጅቱ ባለቤት ወይም ህጋዊ ተወካይ
የማሳወቅ እና በቁጥጥር ወቅት በታዩ ግኝቶች ላይ መፈራረም አለባቸው፤

4/ ተቆጣጣሪው አካል ለቁጥጥር ሲወጣ የቁጥጥር ተግባራትን ከሚያስተባብረው ኃላፊ ጋር ስለሚቆጣጠረው ማደያ ወይም የነዳጅ ቦቴ ወይም ሌላ ተግባር እና በሚደረገው የቁጥጥር አካሄድ ላይ ስምምነት ያደርጋል፤

5/ ተቆጣጣሪው አካል ባደረገው ቁጥጥር ያገኘውን ውጤት በቼክ ሊስት ላይ በመሙላት
ቁጥጥር ከተደረገበት ድርጅት ጋር በመፈራረም ለሃላፊው ሪፖረት ያቀርባል።

6/ ተቆጣጣሪው አካል የቁጥጥር ተግባሩ አስገዳጅ በሆነ ምክንያት ከመንግሥት የሥራ
ስዓት ውጪ የሚያከናውን ከሆነ አግባብ ካለው ባለሥልጣን የትእዛዝ ደብዳቤ መያዝና
ቁጥጥር ለሚደረግበት ድርጅት ማሳየት አለበት፡፡

አንቀጽ 15 አስተዳደራዊ ቅጣት

1/ ማንኛውም የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያ እና አዳይ በዚህ መመሪያ የተዘረዘሩትን ተግባራት
በአግባቡ ያልፈጸመ እና መመሪያውን የጣሰ ሆኖ ሲገኝ እንደየጥፋቱ ክብደት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ከመስጠት ጀምሮ ከአከፋፋይነት ከማገድ እስከ ፈቃድ መሠረዝ የሚያደርስ እርምጃ ይወሰድበታል፡፡

2/ ማንኛውም የነዳጅ ቦቴ ባለንብረት እና አሽከርካሪ በዚህ መመሪያ የተዘረዘሩትን
ተግባራት በአግባቡ ያልፈጸመ እና መመሪያውን የጣሰ ሆኖ ሲገኝ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ
ከመስጠት ጀምሮ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒቴር ጋር በመነጋገር የነዳጅ ጭነት
ሥምሪት እና የአሽርካሪነት ፈቃድን ከማገድ እስከ መሠረዝ የሚያደርስ እርምጃ ይወሰድበታል፡፡

3/ በየእርከኑ የቁጥጥር ሥራ እንዲሠራ ሥልጣን የተሰጠው ማንኛውም አካሌ በአዋጅ
ከተሰጠው ሥሌጣንና በዚህ መመሪያ ሊይ ከተዘረዘረው አሠራር ውጭ የቁጥጥር ሥራ
ሲያከናውን የተገኘ አካሌ እንዯየጥፋቱ ክብዯት በዱሲፒሉን ሥርዓት ከመጠየቅ እስከ ከሥራ መባረር የሚያደርስ እርምጃ እንዲወሰድበት ይደረጋል፡፡

4/ በዚህ መመሪያ መሠረት የሚሰጠው አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተጠበቀ ሆኖ በወንጀል
እና በፍትሐ ብሔር ህግ ተጠያቂ ይሆናለ፡፡

አንቀጽ 16 የመተባበር ግዳታ

ተቆጣጣሪው አካል ይህን መመሪያ በማስፈፀም ሂደት ሲጠየቁ የአከባቢው ፖሊስ እና የፍትህ
አካላት የመተባባር ግዳታ አለባቸው፡፡

አንቀጽ 17 ተፈፃሚነት የሚኖራቸዉ ህጎች
በዚህ መመሪያ የተቀመጡ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ የወንጀል እና የፍትሐ-ብሔር ህጎች ተፈፃሚ ይሆናል።

አንቀጽ 18 አስፈፃሚ አካላት

ይህ መመሪያ በባሇሥሌጣን መ/ቤቱ በክልል እና በከተማ አስተዳደር፣ በዞን እና በወረዳ ንግድን
በሚመሩ አካላት አማካይነት ተፈጻሚነት ይኖረዋል።

አንቀጽ 19 መመሪያው የሚጸናበት ጊዜ
ይህ መመሪያ ከፀዯቀበት ከሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡
አቶ ገብረ መስቀሌ ጫላ
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
አዱስ አበባ

Address

Addis Ababa
19636

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Melkamu Ayano posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Melkamu Ayano:

Share