16/04/2024
ሰው ስትሆን በህይወትህ ብዙ ነገሮችን ታገኛለህ ፣ታጣለህ ፤ብዙ መንገድ ትሄዳለህ ፣ትመጣለህ ፤ሀዘን እና ደስታ ይፈራረቁብሀል ፤ ብዙ ስቃይና መከራ ፣ብዙ ስኬት እና እረፍት በህይወትክ ከሚያጋጥሙህ ነገሮች መሀከል ናቸው፡፡ በነዚህ ውስጥ በሁሉም ቦታ ፍቅር አለ፡ ሲነጋም ፍቅር አለ ሲመሽም ፍቅር አለ፡፡
ፍቅር ማለት ፍቅረኛ አይደለም፣ፍቅር ሰው አይደለም ፤ፍቅር አንድ ትልቅ ሀይልን የተላበሰ የፈጣሪ ፀጋ ነው፡፡ ቀመር የለውም ፣አቅጣጫ አይቀመጥለትም፡፡ ፍቅር መከላከያም ሆነ መቆጣጠሪያ ወይም ደሞ ሀይል መጨመሪያ የለውም፡፡
እደግመዋለው ፍቅር ማለት ፍቅረኛ ማለት አይደለም፡፡ ፍቅር ትምህርት ነው ፣ፍቅረኛ መምህር፡፡ ትምህርት ከመምህሩ በላይ የሆነ ተሰፍሮ ፣ተቆጥሮ ማያልቅ ከተመገቡት የሁሉንም ጭንቅላት እንደሚሞላው ሁሉ ፍቅርም ከአፍቃሪው በላይ የሆነ ለተመገቡት ሁሉ ህይወትን በሀሴት የሚሞላ ተሰፎሮ ማያልቅ እጅጉን ፍፁም አስደሳች እና ሰላም ያለው የህይወት ምግብ ነው፡፡
ሁላችንም እኩል ፍቅር ተሰጥቶናል ተቀብለን ምናስቀምጥበት ቦታ ይለያያል እንጂ . . .
መልካም ቀን