Yeju fortune

Yeju fortune We speak what we see, we testify what we hear!

16/04/2024

ኢራን ወደ እስራኤል ያስወነጨፈችው የሚሳኤልና የድሮን ጥቃት እና እስራኤል ለመከላከል ያወጡት በጀት።

📌30 የክሩዝ ሚሳኤሎች ከኢራን ወደ እስራኤል ቢተኮሱም አንዳቸውም የእስራኤልን ድንበር አላለፉም።

📌120 የባለስቲክ ሚሳኤሎች ኢራን ወደ እስራኤል ከተኮሰችው 120 ሚሳኤሎች 10 ብቻ የእስራኤልን ድንበር አቋርጠው አንዳንድ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ያደረሱ ሲሆን 110ቹ እስራኤል ከመድረሳቸው በፊት በእስራኤል ፀረ ሚሳኤሎች ተመትተዋል።

📌 ከኢራን 170 ሰው አልባ አውሮፕላኖች በእስራኤል ድንበር ላይ ከመድረሳቸው በፊት 100 የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወደ አመድነት ተለውጠዋል።

📌በአጠቃላይ ኢራን ከ85,000 ቶን በላይ የጥቃት ቅንቡላ በእስራኤል ላይ አድርጋለች።

📌በዚህ ቀን ለእስራኤል እራስን ለመከላከል የመከላከያ ሚኒስቴር ጥይት በጀት ብቻ
4.5 ቢሊዮን ዶላር ነው።

📌 የኢራን የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት 3 ዮርዳኖሳውያን (ዮርዳናውያን) ሲገደሉ በእስራኤል በኩል ከአንዲት ሕፃን ላይ ከደረሰው ቀላል ጉዳት ውጪ አንድም ሰው አልሞተም።

📌 እስራኤል 99% የሚሆነውን ከኢራን የተሰነዘረውን ጥቃት ያከሸፈችበት እና አስደናቂ ተአምራትን ያደረገችበት እና ወታደራዊ የበላይነት ያረጋገጠችበት ምሽት ነበር።

📌 ኢራንን በአንድ ጀምበር ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖችን፣ኩርዝ ሚሳኤሎችን እና ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን የላከችው 6.3 ቢሊዮን ዶላር አውጥታ ነው።

 #ወልድያ - 1930 ዓ.ም   back in September 1937Key search term 'Uoldia'Deutsche Fotothek/German Photo Library/Schottenloher, ...
11/02/2024

#ወልድያ - 1930 ዓ.ም

back in September 1937

Key search term 'Uoldia'

Deutsche Fotothek/German Photo Library/Schottenloher, Rudolf Photographs:
https://www.deutschefotothek.de

02/12/2023

ኢትዮጵያ እስከ መጋቢት መጨረሻ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ጋር አዲስ የብድር ስምምነት ላይ ካልደረሰች ባለፈው ሳምንት ከአበዳሪዎቿ ጋር የብድር መክፈያዋ ጊዜ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘምላት የደረሰችበት ስምምነት ውድቅ እንደሚኾን ሮይተርስ ዘግቧል።

የወልድያ ከተማ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክት ስራ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነዉ።ከአስፓልት ማንጠፍ በተጨማሪ ያሉ   የድልድይ፣የእግረኛ መንገድ፣የመንገድ ላይ መብራት ስራዎች በቀጣይ ተጠናክረዉ እን...
30/11/2023

የወልድያ ከተማ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክት ስራ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነዉ።

ከአስፓልት ማንጠፍ በተጨማሪ ያሉ የድልድይ፣የእግረኛ መንገድ፣የመንገድ ላይ መብራት ስራዎች በቀጣይ ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

በጋምቤላ ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ተገኘ*****************አኮቦ ሚኒራልስ በጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ ሰግሌ በተባለ አከባቢ ላለፉት  13 ዓመታት ሲያካሂድ የቆየው የወርቅ ፍለ...
28/11/2023

በጋምቤላ ከፍተኛ የወርቅ ክምችት ተገኘ
*****************
አኮቦ ሚኒራልስ በጋምቤላ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ ሰግሌ በተባለ አከባቢ ላለፉት 13 ዓመታት ሲያካሂድ የቆየው የወርቅ ፍለጋ ውጤታማ እንደሆነ እና ከፍተኛ የወርቅ ክምችት እንዳገኝ ኦል አፍሪካ ዘግቧል።
መቀመጫውን ስካንዲኒቪያ ሀገሮች ውስጥ ያደረገው አኮቦ ሚኒራልስ በሰገሌ አከባቢ ያገኘውን ከፍተኛ ምርት አምርቶ የሙከራ ሽያጭ መጀመሩም ተሰምቷል።
አኮቦ ሚኒራልስ ባወጣው መግለጫ ላይ "በሰግሌ አከባቢ ያገኘው የወርቅ ክምችት በኩባንያው ታሪክ ትልቅ ምዕራፍ ነው" ብሏል። አኮቦ ሚኒራልስ በጋምቤላ ከወርቅ ፍለጋ ወደ ማምረት በተሳካ መንገድ ከተጓዙ ጥቂት ኩባንያዎች መካከል አንዱ እንደሚያደርገውም የኦል አፍሪካ ዘገባ አመልክቷል።
የአኮቦ ሚኒራልስ መግለጫ በጋምቤላ ክልል አኝዋክ ዞን ዲማ ወረዳ የሚገኘው የሰገሌ ማዕድን በአለማችን ከፍተኛ የወርቅ ሃብት ካላቸው ቦታዎች አንዱ እንደሆነ እና በአማካይ በቶን 22 ነጥብ 7 ግራም ወርቅ እንደሚገኘበትም አብራርቷል፡፡
ኩባንያው የሙከራ ወርቅ የማውጣት ስራ የጀመረ ሲሆን የዋናው ፋብሪካ በሙሉ አቅም ወደ ስራሲገባ የኢትዮጵያ አመታዊ የወርቅ ማምረት አቅም ላይ ከፍተኛ ጭማሪን ይፈጥራል ተብሏል።

ፍርድቤቱ ለድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ከወር በፊት የሰጠዉን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ተጠየቀበትየፌዴራሉ ፍርድ ቤት ጥቅምት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በዋለዉ ችሎት ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍ...
26/11/2023

ፍርድቤቱ ለድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ከወር በፊት የሰጠዉን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ተጠየቀበት

የፌዴራሉ ፍርድ ቤት ጥቅምት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በዋለዉ ችሎት ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የሰጠዉን የፍርድ ዉሳኔ በመቃወም ላየን ፕሮሞሽን በጠበቃዉ በኩል ይግባኝ ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱ በመቃወሚያ ላይ በሰጠው ብይን እና በህጋዊ ማስረጃ ከተረጋገጡ ፍሬነገሮች ይልቅ ለግምት ክብደት በመስጠት የሰጠው ፍርድ ክርክር የሚመራበትን ሥርዓትና የማስረጃ ህግ መርህዎችን በግልፅ በመቃረን የሰጠው ፍርድ ጉድለት ያለበት በመሆኑ ይግባኝ እንደተጠየቀበት ካፒታል ሰምቷል።

ከአራት ዓመት በፊት የካቲት 14 ቀን 2012 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በተደረገዉ "የኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ጉዞ" የሙዚቃ ኮንሰርት ከሚገኘው ገቢ አዘጋጁ ላየን ፕሮሞሽን ኃ/ የተወሰነ የግል ማህበር ለድምፃዊ ቴዲ አሥር ሚሊዮን ብር ለመክፈል በፅሑፍ እና በቃል ተደርጓል ያለዉን የዉል ግዴታ ተፈፃሚ ሊሆን አልቻለም በሚል ጉዳዩን ወደ ፍርድቤት በመዉሰድ ላለፉት አራት ዓመታት ክርክር ሲደረግበት ቆይቷል።

በዚህ ሂደት ፍርድቤቱ ጥቅምት ወር በተሰየመዉ ችሎት ላየን ፕሮሞሽን እና ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ከኮንሰርቱ የተገኘውን 10 ሚሊዮን እኩል እንዲካፈሉ በሚል ብይን መስጠቱ ይታወሳል ።

ከድምፃዊ ቴዲ አፍሮ የቀድሞ ጠበቃ እና አሁን በላየን ፕሮሞሽን በኩል በመሆን የፍርድቤቱ ዉሳኔዉን በመቃወም ይግባኝ የጠቀየዉ ጠበቃ ሚሊዮን አሰፋ መርሻ ነዉ።

ህዳር 12፤2016 ዓ.ም. ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት ለፍትሃብሔር ይግባኝ ሰሚ ችሎት በቀረበው አቤቱታ “በህጋዊ አካል በታተመው መግቢያ ትኬት አማካኝነት የታደሙ ሰዎች ቁጥር የተረጋገጠ ሆኖ ሳለ ፍርድቤቱ ከህጋዊ ማስረጃ ይልቅ በግምት የተመሰረተ የሰጠዉ ፍርድ ጉድለት አለበት ፣ የፅሑፍ ውል የለም ካለ በኋላ መልሶ የቃል ውል አለ በማለት መልስ ስጪው ( ቴዲ አፍሮ) በክሱ መሠረት ያላስረዳውንና በክሱ ያልተመለከተውን አምስት ሚሊዮን ብር ይግባኝ ባይ ለመልስ ሰጪ ከወለድና ካስከተለው ወጪና ኪሣራ ጭምር ሊከፍል ይገባል በማለት የሰጠው ፍርድ ጉድለት ያለበት ነው ተብሎ እንዲሻር” የሚሉት ይገኙበታል ።

"አንድ ሰው 100 ሚሊዮን ብር ከሌለው ምንም የለውም!" «ከአንድ ጓደኛዬ ጋር በወር አንድ ሚሊዮን መስራት ከቻልን በየሶስት ወሩ እንዞራለን እንዝናናለን ተባባልን። ለሆኑ ልጆች ስንነግራቸው ...
24/11/2023

"አንድ ሰው 100 ሚሊዮን ብር ከሌለው ምንም የለውም!"

«ከአንድ ጓደኛዬ ጋር በወር አንድ ሚሊዮን መስራት ከቻልን በየሶስት ወሩ እንዞራለን እንዝናናለን ተባባልን። ለሆኑ ልጆች ስንነግራቸው ዶላር ነው ብለው ሳቁብን፣ ኧረ ብር ነው ስንላቸው በአመት 12 ሚሊዮን? አሉን። ለካ ሁሉም ነገር እስክትደርስበት ነው። አሁን በአመት 12 ሚሊዮን ምንም እንዳልሆነ ገብቶናል። አሁን ባለሁበት ሁኔታ አንድ ሰው 100 ሚሊዮን ከሌለው ምንም የለውም እላለሁ»
ወ/ሮ ሄይሪያ አህመድ በማርኬቲንግ ስራ ተሰማርታ የምትገኝ ስትሆን ከእዮሃ ሚዲያ ጋር ካደረገችው ኢንተርቪው የተወሰደ።

"ሁሉም የሚፈልገውን ብቻ ሰማኝሁሉም አብጠለጠለኝ።ሁሉም ስቀለው ስቀለው አሉኝ።እግዚአብሔር ይርዳኝ፣ለመስቀልም ዝግጁ ነኝ።"(ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ )
23/11/2023

"ሁሉም የሚፈልገውን ብቻ ሰማኝ
ሁሉም አብጠለጠለኝ።
ሁሉም ስቀለው ስቀለው አሉኝ።
እግዚአብሔር ይርዳኝ፣
ለመስቀልም ዝግጁ ነኝ።"
(ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ )

ወልቃይት!!!ደግሞ እንደ ተዋቡ..ጎንደር  ሹርቤዋን ሸገናይ ተሰርታ ፤በመይሳው ጥለት...የሚያምረው ቀሚሷን አሳምራ ሰርታ፤ሸብ የምትልበት.....ወልቃይት ነው ለካ ጉንጉን  መቀነቷ።ጃኖ መንግ...
17/11/2023

ወልቃይት!!!

ደግሞ እንደ ተዋቡ..
ጎንደር ሹርቤዋን ሸገናይ ተሰርታ ፤
በመይሳው ጥለት...
የሚያምረው ቀሚሷን አሳምራ ሰርታ፤
ሸብ የምትልበት.....
ወልቃይት ነው ለካ ጉንጉን መቀነቷ።

ጃኖ መንግስቱ ዘገየ
Mengistu Zegeye

‹ የምጽዓት ቀን ደርሷል › በሚል ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ኡጋንዳውያን ‹‹ ወደመጣንበት አልተመለስንም፤ አንመለስምም ›› አሉ  ‹‹ ኛንጋቶም፣ ኢትዮጵያ የቅድመ አያቶቻችን መሬት ነው ›› - ኡ...
10/11/2023

‹ የምጽዓት ቀን ደርሷል › በሚል ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ኡጋንዳውያን ‹‹ ወደመጣንበት አልተመለስንም፤ አንመለስምም ›› አሉ

‹‹ ኛንጋቶም፣ ኢትዮጵያ የቅድመ አያቶቻችን መሬት ነው ›› - ኡጋንዳውያኑ
‹ የምጽዓት ቀን ደርሷል › በሚል ወደኢትዮጵያ የመጡ ኡጋንዳውያን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ደቡብ ኦሞ ዞን፣ ኛንገቶም ወረዳ እንደሚገኙ አሻም አረጋግጣለች፡፡ አሻም የኡጋንዳውያን ተወካይ ነኝ ያሉትን ፓስተር ቪንሰንት ኩቺየንን በስልክ አነጋግራለች፡፡

ፓስተር ቪንሰንት ከአሻም ጋር ባደረጉት የስልክ ቆይታ ወደኢትዮጵያ የመጡት እ.አ.አ. የካቲት 21 ቀን 2023 እንደነበረ ያስታውሳሉ፡፡ አሁን 10 ወራትን እንዳስቆጠሩም ይናገራሉ፡፡

‹‹ ስንመጣ የተቀበሉንና ያገዙን የህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ከኛንጋቶም ወረዳ አስተዳዳር ጋር በመሆን ነው ›› ሲሉ የሚያስታወሱት ፓስተሩ ‹‹ በቦታው እንደደረስን እንኖር የነበረው በህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ነበር ›› ሲሉም ገልፀዋል፡፡

‹‹ ከዚህ ቀደም በሚዲያ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት በኩል እንደተገለጸው እኛ ወደ ዩጋንዳ እንደተመለስን ነው። ነገር ግን እኛ አልተመለስንምም አንመለስምም ›› ሲሉ አሰረግጠው ተናግረዋል፡፡

ለዚህ ምክንያታቸውን ሲያስረዱ ‹‹ ምክንያቱም ይህ አካባቢ የቀደምቶቹ እህቶቻችን እትብታቸው የተቀበረበትና መነሻቸው ነው፤ ከአመታት በፊት ከዚህ ነው ወደ ዩጋንዳ የሄዱት ›› ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

አክለውም ‹‹ ስለዚህ አሁን እየኖርንበት ያለው የናሮጎይ ቀበሌ በኛንጋቶሞ ወረዳ እየኖርን እንገኛለን ›› ብለዋል፡፡

ፓስተር ቪንሰንት አሁን ስለሚገኙበት ሁኔታም ለአሻም አስረድተዋታል፡፡ ‹‹ አሁን እየኖርንበት ያለንበት ሁኔታ መጥፎ አይደለም፤ የኛንጋቶም ወረዳ አስተዳደር ከቀበሌው ጋር በጋራ ሆነው መሬት ሰጥተውናል በዚያም ላይ ለሙከራና ማሳያ ያህል የእርሻ ስራ ጀምረናል። የተሰጠንም አንድ ሺህ ሄክታር መሬት ነው ›› ይላሉ፡፡

‹‹ ስራችን የሆነውን የእየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መስበክ ሲሆን ይህንንም በኛንጋቶም ወረዳና በአካባቢው ለሌሎች ማህበረሰቦች ነው። በሰላም ግንባታ ላይም በዚህ በኢትዮጵያ በተለይም በኛንጋቶም፣ በኬንያ፣ በደቡብ ሱዳን እያስተማርንና የራሳችንን ጥረት እያደረግን እንገኛለን ›› ብለዋል፡፡

‹‹ እኛ ወደ ኡጋንዳ በፍፁም አልተመለስንም፤ አሁንም እዚህ ኢትዮጵያ ነው ያለነው ›› የሚሉት ፓስተሩ ‹‹ በሚዲያ ከዚህ ቀደም እንደሰማነውና የኢትዮጵያ መንግስት እንደገለፀው ወደ ዩጋንዳ እንደተመለስን/እንደተባረርን ነበር፤ ይህ በፍፁም አልሆነም፤ ይህ ሀሰተኛ መረጃ ነው ›› ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

‹‹ ስለዚህ ተመልሰን ወደ ኡጋንዳ አንሄድም ይህ አሁን ያለንበት ቦታ ከአመታት በፊት እህቶቻችን ተሰደው የሄዱበት ነው። እኛ ንያንጋቶሞች ነን፥ ሀገራችንም ነው ›› ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

ኡጋንዳዊያኑ ‹ የክርስቶስ ሐዋሪያዎች› የተሰኘ እምነት ተከታዮች የዓለም ፍጻሜ በቅርቡ የሚጀምረው ከአካባቢያቸው መሆኑን በማመን ንብረታቸውን በመሸጥ ወደ ኢትዮጵያ በሕገወጥ መንገድ እየገቡ ያሉት ከየካቲት ጀምሮ እንደሆነ የኡጋንዳ ፖሊስ ከወራት በፊት መናገሩ ይታወሳል፡፡

ባለፈው ዓመት በወርሃ መጋቢት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ አምባሳደር መለስ አለም በሳምንታዊ መግለጫቸው ከ100 በላይ ኡጋንዳዊያን የዓለም ፍጻሜ ደርሷል ፣መድህን የሚገኘውም በኢትዮጵያ ነው በሚል ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል ስለተባሉት የሀይማኖት ሰዎች ምላሽ ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል።

በትግራይ ክልል 80 በመቶ የኢንዲስትሪዎችና የአገልግሎት ሠራተኞች ከሥራ ውጪ መሆናቸው ተገለጸ======= #=======አርብ ጥቅምት 30 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት...
10/11/2023

በትግራይ ክልል 80 በመቶ የኢንዲስትሪዎችና የአገልግሎት ሠራተኞች ከሥራ ውጪ መሆናቸው ተገለጸ
======= #=======

አርብ ጥቅምት 30 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል በኢንዱስትሪዎች 80 በመቶና ከአገልግሎት ዘርፉ ደግሞ 70 በመቶ ያህል ሠራተኞች በተለያዩ አጋጣሚዎች ከሥራ ውጪ መሆናቸው ተገልጿል።

መረጃው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያቋቋመው “በትግራይ የተፈጸመ ዘር ማፅዳት አጣሪ ኮሚሽን” በ11 ሺሕ 312 የግል የኢንዱስትሪዎችና የአገልግሎት ተቋማት ላይ አደረግኩት ባለው ጥናት መሰረት መሆኑም ተመላክቷል።

በኹለቱ ዘርፎች ላይ የተደረገው ጥናት በጦርነቱ ምክንያት የደረሰ ቀጥተኛ ውድመት፣ በውድመቱ ምክንያት የመጣ ኪሳራንና መንገዶች በመዘጋታቸውና የግንኙነት መስመሮች በመቋረጣቸው የደረሰ ጉዳትን የሚያካትት መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ኮሚሽኑ ከሰው ኃይል ጋር በተያያዘ የደረሰበት ውጤት ከጦርነቱ በፊት በ4 ሺሕ 180 የንግድ ተቋማት ውስጥ 99 ሺሕ 604 ሠራተኞች በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተቀጥረው ይሠሩ የነበረ ቢሆንም፤ በአሁኑ ጊዜ ይህ ቁጥር ወደ 17 ሺሕ 604 ወርዶ መገኘቱን ጠቁሟል።

በአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ በ7 ሺሕ 132 ተቋማት ላይ ጥናት መደረጉንና ከጦርነቱ በፊት ከነበረው 35 ሺሕ 692 የሥራ ኃይል ውስጥ 70 በመቶ ያህል በተለያየ ምክንያት ከሥራ ውጭ መሆኑን እንዳረጋገጠ ተነግሯል፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የማነ ዘርዓይ፤ “ተቋማቱ ሥራ ስለማይሠሩ ያሰናበቱዋቸውን ሠራተኞች ብቻ ሳይሆን የሞቱ፣ የቆሰሉና፣ የጠፉ ሠራተኞችንም ይጨምራል” ሲሉ መግለጻቸውም ተጠቁሟል።

“በግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ወደ ኹለት ሺሕ የሚሆኑ ተቋማት ላይ ጥናት አካሂደናል” ያሉት ኃላፊው፤ “ከእነዚህ ውስጥ የሞቱ፣ የቆሰሉ፣ አካላቸው የጎደለ ወይም የጠፉ ሠራተኞች በሚል ዝርዝር ውስጥ ተካተው በሥራ ገበታቸው ላይ እንደሌሉ ያረጋገጥናቸው 1 ሺሕ 653 ሠራተኞች ናቸው” ብለዋል።

የግብርናው ኢንቨስትመንት ዘርፍ በአጠቃላይ 49 ሺሕ ሠራተኞች የነበሩ ቢሆንም፤ ከጦርነቱ በኋላ ግን 1 ሺሕ 343 ሠራተኞች ብቻ በሥራ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል በኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎትና በግብርና ዘርፎች ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ በነበሩት ዓመታት በደረሰው ውድመት ምክንያት፤ ኢትዮጵያ ከግብርና ምርቶች የወጪ ንግድ ማግኘት ከነበረባት የውጭ ምንዛሪ ያጣችው ምን ያህል እንደሆነ ጥናቱ ሲጠናቀቅ እንደሚታወቅም ተመላክቷል።

ኮሚሽኑ በጥቅሉ በጦርነቱ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በትግራይ ክልል ላይ የደረሱ ጉዳቶችን ለማጣራት፤ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መቋቋሙ ይታወሳል።

የአቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም እንዳይሸጥ በፖሊስ ተከለከለ!የአቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም እንዳይሸጥ በፖሊስ መከልከሉን ድምፃዊው ገለፀ። አርቲስቱ ባስተላለፈው መልዕክት «በትናትናው እለት እንደ ...
29/08/2023

የአቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም እንዳይሸጥ በፖሊስ ተከለከለ!
የአቡሽ ዘለቀ አዲስ አልበም እንዳይሸጥ በፖሊስ መከልከሉን ድምፃዊው ገለፀ። አርቲስቱ ባስተላለፈው መልዕክት «በትናትናው እለት እንደ አባቴ እወድሻለሁ የተሰኜው አዲሱ አልበሜ በአዲስ አበባ እንዳይሸጥ በፖሊስ ተከልክሏል እንዲህ ስለሆነ ለሀገሬ እና ለህዝቦቿ ያለኝ ፍቅር አይቀንስም እንደ አባቴ እወድሻለሁ» ብሏል።

ሳቂታው  !💙ምስጋና ለአቶ ሀብተስላሤ ታፈሰ ይመራ ለነበረው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኮሚሽን ይግባና የዚህ ግለሠብ ፎቶ እንደ አልማዝ አመንሲሳ የቤታችን ግድግዳ ማድመቂያ ፤ የመስሪያ ቤቶች ግድግዳ...
24/08/2023

ሳቂታው !💙

ምስጋና ለአቶ ሀብተስላሤ ታፈሰ ይመራ ለነበረው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኮሚሽን ይግባና የዚህ ግለሠብ ፎቶ እንደ አልማዝ አመንሲሳ የቤታችን ግድግዳ ማድመቂያ ፤ የመስሪያ ቤቶች ግድግዳ ማስዋቢያ ፤ የፖስትካርዶች ቀለም ፤ ...በጠቅላላው የቤተሰባችን አካል እስኪመስለን ድረስ ውስጣችን ታትሞ የቀረ ምስል ነው ።

Afendi Muteki ባሰፈረው መረጃ መሠረት ፎቶውን ያነሳው የናሽናል ጂኦግራፊው ጋዜጠኛ የነበረው P. Blair በ1966 ነው ። ቦታው ደግሞ በቀድሞ ኤርትራ ክ/ሀገር ምእራባዊ ቆላማ ክፍል ተሰነይ ከተማ አከባቢ ነው ። ይህን ዝነኛ ፎቶ የናሽናል ጂኦግራፊው ጋዜጠኛ ብለየር ሲያነሳው ኢትዮጵያዊው የዶቼ ቬለ ጋዜጠኛ የነበረው ጌታቸው ደስታ (ነፍስ ይማር ) አብሮት ነበረ ።

በተለምዶ ቢኒ አመር እያልን የምንጠራው ይህ ግለሰብ የትግራይ ብሔር አካል የሆነው የቢኒ አመር ጎሳ አባል ነው ። ስሙ ኦማር መሐመድ ሐሚድ ሓምዳ ይባላል ። 1989 ላይም አርፋል ።

አስገባኝ በረኛ-አሆሆአስገባኝ በረኛ!በግዜ እንድንተኛአሆሆ አስገባኝ በረኛ!!ደግሞም በምትወዱትአሆሆ አስገባኝ በረኛበእገሌዋ ሞትአሆሆ አስገባኝ በረኛመጣሁ ባመቴ-ባመቴበተቀጠርኩት-ባመቴበዛችው ...
19/08/2023

አስገባኝ በረኛ-አሆሆ
አስገባኝ በረኛ!
በግዜ እንድንተኛ
አሆሆ አስገባኝ በረኛ!!
ደግሞም በምትወዱት
አሆሆ አስገባኝ በረኛ
በእገሌዋ ሞት
አሆሆ አስገባኝ በረኛ
መጣሁ ባመቴ-ባመቴ
በተቀጠርኩት-ባመቴ
በዛችው ቀኔ-ባመቴ
አጥፍቼ እንደሆን-ባመቴ
እቀጣለሁ እኔ-ባመቴ!!!
አሆ አሰለለኝ-አሆ ሆየ በል(2)
አሆ አሰለለኝ-ከፈረስ አፍንጫ
አሆ አሰለለኝ-አሆ ሆየ በል
አሆ አሰለለኝ-ይውላል ትንኝ
አሆ አሰለለኝ-አሆ ሆየ በል
አሆ አሰለለኝ-ኧረ የኔ ጌታ
አሆ አሰለለኝ-አሆ ሆየበል
አሆ አሰለለኝ-ጤና ይስጥልኝ!......................................
ቡሔን ናቡሔ በሉት(2)
ቡሔ እየው ከዛ ማዶ
ቡሔን ና ቡሔ በሉት
ቡሔ ነብር ይጓጉራል
ቡሔን ና ቡሔ በሉት
ቡሔ ኧረ የኔ ጌታ
ቡሔን ና ቡሔ በሉት
ቡሔ ገሎ ይፎክራል
ቡሔን ናቡሔ በሉት
ቡሔ ፎክሮ ፎክሮ
ቡሔን ና ቡሔ በሉት
ቡሔ ውሀ ቢጠማው
ቡሔን ና ቡሔ በሉት
ቡሔ በጎራዴ ጭሮ
ቡሔ ና ቡሔ በሉት
ቡሔ በጋሻ አጠጣው.............................
የቡሔ ሶለላ የቡሔ(2)..........................
ሆያ ሆየ እርም-ይታያል ኮረም
ሆያ ሆየ ናናና-ተው ስጠኝ ብሩንን ምዘዝና
ሆያ ሆየ ጉዴ-ሸብረብ አለ ሆዴ
ኧረ ነቃ ነቃ ጉሮሯችን ነቃ
አሆ አሆይ በል
አሆ ናናና አሆ ና ቸርየ
የዋንዛው ካሚሳ-ካሚሳ
ሊሠጠኝ ነው ሃምሳ
የዋንዛው ነብር-ነብር
ሊሠጠኝ ነው ብር.......................
ከዚህ ቤት ወርቅ ይፍሰስበት!
ክበር በስንዴ
ክበር በጤፍ
ምቀኛህ ሁላ ይርገፍ-እንደቆላ ዛፍ!!

በኢትዮጵያ ህግ መንገድ ላይ መሳሳም እስከ 1 ወር ና የገንዘብ ቅጣት ያስቀጣል ተባለ።መንገድ ላይ መሳሳም እንደ ፋሽን የሆነው የዚህ ዘመን ትውልድ ይሄን ማወቅ አለበትም በሚል ይፋ ተደርጓል።...
02/08/2023

በኢትዮጵያ ህግ መንገድ ላይ መሳሳም እስከ 1 ወር ና የገንዘብ ቅጣት ያስቀጣል ተባለ።

መንገድ ላይ መሳሳም እንደ ፋሽን የሆነው የዚህ ዘመን ትውልድ ይሄን ማወቅ አለበትም በሚል ይፋ ተደርጓል።

ህግ አስከባሪዎችም መንገድ ላይ የሚሳሳሙትን በቁጥጥር በማዋል እስር ቤትም የማስገባት ሙሉ መብት አላቸው ተብሏል።

በዚህም ህግ መሰረት መንገድ ላይ ባለማወቅ የምትሳሳሙ ወደፊትም ለመሳሳም ያሰባችሁ ካላችሁ በኢትዮጵያ ህግ መስረት
👇👇
🙏👉 1 ወር ወይንም የገንዘብ መቀጫ ስለምትቀጡ ተጠንቀቁ ተብሏል።

ልጅ እናቱን አስመርቋል"እናታችን በብዙ ልፋት እኛን ለወግ ለማረግ አብቅታናለች፤ እሷ ዛሬ ለዚህ በመብቃቷ በጣም ደስተኛ ነኝ"- ወጣት ሚኪያስ የማነ "እናታችን ለፍታ እኛን አሰተምራ ለወግ ለ...
31/07/2023

ልጅ እናቱን አስመርቋል
"እናታችን በብዙ ልፋት እኛን ለወግ ለማረግ አብቅታናለች፤ እሷ ዛሬ ለዚህ በመብቃቷ በጣም ደስተኛ ነኝ"
- ወጣት ሚኪያስ የማነ

"እናታችን ለፍታ እኛን አሰተምራ ለወግ ለማዕረግ አብቅታናለች፤ ዛሬ እሷ በተራዋ ለዚህ በመብቃቷ በጣም ደስተኛ ነኝ፤ እኔም በተራዬ ላስመርቃት ነው የመጣሁት" ሲል እናቱን ለማሰመረቅ የመጣው ወጣት ሚኪያስ ይማነ ተናግሯል።

የወጣት ሚኪያስ ይማነ ወላጅ እናት ወይዘሮ ምህረት ወልደማርያም በሂሳብ መዝገብ አያያዝ ተመርቀዋል።

የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 6ሺህ 244 ሰልጣኞችን በሚሊኒየም አዳራሽ በዛሬው እለት አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ አንዷ የሆኑትን ወላጂ እናቱን ሊያስመርቅ የተገኘው ወጣት ሚኪያስ ይማነ፣ እናታችን በብዙ ልፋትና መከራ አልፋ እኛን አስተምራ አድርሳናለች፤ እሷ በተራዋ ለዚህ በመብቃቷና በዚህ ደስታ ላይ ተሳትፌ የእናቴን ደስታ በማየቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ ሲል ለኢፕድ ተናግሯል።

ወጣት ሚኪያሰ ለኢፕድ እንደገለጸው፣ እናታችን ሳትማር ለፈታ እኛን ለወግ ለማዕረግ አብቅታናለች እኔ ደግሞ በተራዬ ላስመርቃት ነው የመጣሁት ይላል።

ከእናቴ የተረዳሁት ትምህርትን እድሜ እንደማይገድብ ነው ያለው ወጣት ሚኪያስ የእናቴ ጥንካሬ፣ አልበገር ባይነትና ለዚህ ደረጃ መድረስ ለቀጣይ ሕይወቱን ትልቅ ስንቅ እንደሚሆንለትና ብዙ ነገር እንደተማረበት ነግሮናል።

ሌሎች እናቶች ከእኔ እናት በመማር ወልደን ከብደን ልጆቻችንን ብቻ ካስተማርን በቂ ነው የሚለውን ሀሳብ መቅረፍ አለባቸው፤ ምክንያቱም ሁሉም ነገር ካለፈ በኋላ እንዳዲስ የመጀመር እድሉ ስላላቸው ነው ይላል ወጣት ሚኪያሰ።

ለመማር እድሜ አይወስንም የሚለው ወጣት ሚኪያሰ እናቶቻችን ትልቅ ለውጥ ልያመጡ እንደሚችሉ በመረዳት ተምረው ዕራሳቸውንም ሀገራቸውንም ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡

የዛሬ ተመራቅና የወጣት ሚኪያስ ይማነ ወላጅ እናት ወይዘሮ ምህረት ወልደማርያም፣ ከአዲስ አበባ ፖሊ ቴክንክ ኮሌጅ በሂሳብ መዝገብ አያያዝ ተመርቅያለሁ፡፡ ነገር ግን ሶስት ልጆችን ወልጄ ያለአባት አስቴምሬ ለወግ ለማረግ አብቅቼ የልጅ ልጆቼን ማየቴ ለዛሬዋ ቀን ለመድረስ እንዳላገዳቸው ይናገራሉ ።

ሰው ሲማርነው ትልቅ ደረጃ የሚደርሰው ያሉት ወይዘሮ ምህረት ሌሎች እናቶች ችሎታው እያላቸው ቤት ከሚቀመጡ እኔን በማየት እንዲማሩና ትልቅ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ፈልጋለው ብለዋል፡፡

በመቀሌ ከተማ ሰልፍ የወጡ ከስድስት ሺሕ በላይ አካል ጉዳተኛ የሕወሓት ታጣቂዎች በፖሊስ ኃይል መበተናቸው ተገለጸ======= #=======በትናንትናው ዕለት በመቀሌ ከተማ ድጋፍ እንዲደረግላች...
29/07/2023

በመቀሌ ከተማ ሰልፍ የወጡ ከስድስት ሺሕ በላይ አካል ጉዳተኛ የሕወሓት ታጣቂዎች በፖሊስ ኃይል መበተናቸው ተገለጸ
======= #=======

በትናንትናው ዕለት በመቀሌ ከተማ ድጋፍ እንዲደረግላችው እና ጥቅማ ጥቅም እንዲከበርላቸው ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተሰባሰቡ ከስድስት ሺሕ በላይ አካል ጉዳተኛ የሕወሓት ታጣቂዎች፤ በፖሊስ ኃይል እንዲበተኑ መደረጋቸውን ትንሳኤ ሰባ እንደርታ ፓርቲ ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።

ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ወደ ተለያዩ የክልሉ ቦታዎች ተመልሰው ከቤተሰቦቻቸው በሚደረግላቸው ድጋፍ የሚኖሩ ከስድስት ሺሕ በላይ በጦርነቱ ወቅት ቆስለው የአካል መጉደል ያጋጠማችው ወጣቶች፤ በመቀሌ ከተማ ሃያ ኹለት ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን እና ፖሊስ ሠልፈኞቹን በኃይል እንዲበተኑ ማድረጉን የትንሳኤ ሰባ እንደርታ ፓርቲ አደራጅ ጊደሰና መድኅን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የፓርቲው አደራጅ አክለውም፣ ከዚህ ቀደም በሕወሓት ሥር ተመዝግበው ከሚገኙ 274 ሺሕ ታጣቂዎች መካከል 50 ሺሕ የአካል መጉደል ያጋጠማቸው ታጣቂዎች፤ በሕወሓት የሰው ኃይል አሥተዳደር ኃላፊ ኮለኔል ነጋሽ ዳኘው አማካኝነት ሰርተፍኬት እና ገንዘብ ተሰጥቷቸው በቅርቡ መሰናበታቸውን ገልጸዋል።

ተማሪዎች ፈተና ጨርሰው ሲመለሱ አደጋ ደረሰባቸው👉እስካሁን በአደጋው የሞተ ተማሪ የለምየቁጭ አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ከእንጅባራ ዩኒቨርስቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲያጓ...
29/07/2023

ተማሪዎች ፈተና ጨርሰው ሲመለሱ አደጋ ደረሰባቸው

👉እስካሁን በአደጋው የሞተ ተማሪ የለም

የቁጭ አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ከእንጅባራ ዩኒቨርስቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲያጓጉዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ተገልብጦ ጉዳት ደርሷል።

በቀን 21/11/2015 አ/ም ከምሽቱ ተማሪዎችን ከእንጅባራ ዩኒቨርስቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ይዞ ሲጓጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተገልብጦ ቀላል እና ከባድ ጉዳት ማድረሱ የተሰማ ሲሆን፣ እስካሁን ምንም አይነት ሞት እንደሌለ እና የተጎዱ ተማሪዎች በአስቸኳይ ወደ ህክምና እንደተላኩ ታውቋል።

የፌደራል እንባ ጠባቂ ተቋም አዲሱን የሸገር ከተማ አስተዳደርን ሊከስ መሆኑን አስታወቀ‼️ የሸገር ከተማ አስተዳደር የመኖሪያና ንግድ ቤቶቻቸውን ያፈረሰባቸው ዜጎች ላቀረቧቸው አቤቱታዎች ምላሽ...
28/07/2023

የፌደራል እንባ ጠባቂ ተቋም አዲሱን የሸገር ከተማ አስተዳደርን ሊከስ መሆኑን አስታወቀ‼️

የሸገር ከተማ አስተዳደር የመኖሪያና ንግድ ቤቶቻቸውን ያፈረሰባቸው ዜጎች ላቀረቧቸው አቤቱታዎች ምላሽ እንዲሰጥ የፌደራል እንባ ጠባቂ ተቋም የጊዜ ገደብ ሰጥቻለሁ ማለቱን ቪኦኤ ዘግቧል።

እንባ ጠባቂ ተቋም የሸገር ከተማ አስተዳደር ቤታቸውን ካፈረሰባቸው ነዋሪዎች 100 ሺህ አቤቱታዎች መቀበሉን ቀደም ሲል አስታውቆ ነበር። የከተማዋ አስተዳደር በተሰጠው ቀነ ገደብ ምላሽ ካልሰጠ፣ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስደው ተቋሙ መናገሩን
ዘገባው አመልክቷል።

የETV የአገልግሎት ክፍያን ከመብራት ክፍያ ላይ ተደምሮ ሊሰበሰብ ነው!ይህ የሚሆነው ከ50 ኪሎ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ሃይል የምትጠቀሙ ደንበኞች ላይ መሆኑ ተገልፇል። ከሰኔ ወር ጀምሮ የቴ...
26/07/2023

የETV የአገልግሎት ክፍያን ከመብራት ክፍያ ላይ ተደምሮ ሊሰበሰብ ነው!
ይህ የሚሆነው ከ50 ኪሎ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ሃይል የምትጠቀሙ ደንበኞች ላይ መሆኑ ተገልፇል። ከሰኔ ወር ጀምሮ የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ በየወሩ 10 ብር ከወርሃዊ ኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ቢል ጋር ተዳምሮ እንዲዘጋጅ መደረጉ ተገልፇል።

በናዝሬት የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያን ባንዲራ መስቀል ተከልክሎ በነጭና በሰማያዊ ለማክበር ተገደዋል።
25/07/2023

በናዝሬት የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያን ባንዲራ መስቀል ተከልክሎ በነጭና በሰማያዊ ለማክበር ተገደዋል።

የጁ የባህል ማዕከል 🙇የወልድያ ከተማ አስተዳደር የወልድያ ባህል አዳራሽን  ሙሉ ግቢዉ  የየጁ የባህል ማዕከል ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩ ታዉቋል።በዚህም መሰረት በዉስጡ 👉አዳራሹን ለተለያዩ...
25/07/2023

የጁ የባህል ማዕከል 🙇

የወልድያ ከተማ አስተዳደር የወልድያ ባህል አዳራሽን ሙሉ ግቢዉ የየጁ የባህል ማዕከል ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩ ታዉቋል።

በዚህም መሰረት በዉስጡ
👉አዳራሹን ለተለያዩ የባህል እሴቶች ማሳያ ምቹና ዉብ ማድረግ
👉የባህል እሴቶች ማሳያ ሙዝየም
👉የወጣቶች ማንበቢያና መዝናኛ
👉የቱሪስት መረጃ ማዕከል
👉የእደ ጥበብ ዉጤቶች መሸጫ
👉የመፀዳጃ ቤት እና የመኪና ማቆሚያ እንደሚያካት ታዉቋል።

24/07/2023

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ 17 ቢሊዮን ብር ዓመታዊ በጀት አጸደቀ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ለ2016 በጀት ዓመት የሚሆን 17 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ። የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካጸደቀው በጀት ውስጥ 74 በመቶው የሚሸፈነው የፌደራል መንግስት ለትግራይ ክልል ከሚያስተላልፈው የድጋፍ በጀት ነው።

የትግራይ ክልል የሰሜኑ ጦርነት ከተነሳ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በመደበኛ ሁኔታ በጀት ያጸደቀው፤ ባለፈው ሳምንት አርብ ሐምሌ 14፤ 2015 እንደሆነ የክልሉ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ሀንሳ ተክላይ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ለክልሉ መንግስት የሚመደበው በጀት ከዚህ ቀደም ይጸድቅ የነበረው በትግራይ ክልል ምክር ቤት ነበር።

የ2016 በጀት በጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ የጸደቀው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ህግ የማውጣት ስልጣኑን ለክልሉ ስራ አስፈጻሚ አካል በመስጠቱ መሆኑን ኮሚሽነሯ አስረድተዋል። የክልሉ ካቢኔ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባደረገው ስብሰባ፤ ለ2016 በጀት ዓመት 17 ቢሊዮን ብር በጀት ማጽደቁን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አባል የሆኑት ወ/ሮ ሀንሳ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ይህ በጀት የሰሜኑ ጦርነት ከመቀስቀሱ አስቀድሞ ለ2013 በጀት ዓመት ጸድቆ ከነበረው “ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ” ጋር ሲነጻጸር ቅናሽ ማሳየቱን ጠቁመዋል። የአሁኑ በጀት በ2012 በክልሉ ምክር ቤት ከጸደቀው በጀት ጋር ሲነጻጸር ያለው ልዩነት የ300 ሺህ ብር ገደማ ብቻ ነው።

ትዊተርን በዚህ ዓመት የገዛው ከበርቴ ኢለን መስክ የቲዊተርን ታዋቂ 'ሰማያዊ ወፍ' አርማ በ"X" ቀይሯል።
24/07/2023

ትዊተርን በዚህ ዓመት የገዛው ከበርቴ ኢለን መስክ የቲዊተርን ታዋቂ 'ሰማያዊ ወፍ' አርማ በ"X" ቀይሯል።

24/07/2023

(“አቡነ እስጢፋኖስ)
"…አደይ የሚሉት በግርድፉ ሲተረጎም አስገድዶ የደፈረኝ፣ ደፍሮም ያስረገዘኝ፣ አስረግዞም ያስወለደኝ የልጄ አባት መነኩሴ ነው። ያም መነኩሴ አሁን በመንበረ ሰላማ "ጳጳስ" ሆኖ ተመረጠ ነው የሚሉት።
ሙሉ የአማርኛ ትርጉም
ጥያቄ፤- “ስሞት ማን ይባላል?”
“ስሜ መልኮም አብርሃም ነው፡ ባለትዳር ነበርኩኝ፤ የሶስት ልጆች እናት ነኝ። ከባለቤቴ ተፋትቻለሁ። ሁለቱ ልጆቼ ከአንድ አባት የተወለዱ ሲሆን ሶስተኛዋና “ተዓምር” የምትባለው ልጄ ግን ከሌላ የቤተክርስቲያን አባት ነው የወለድኳት።”
ጥያቄ፦ “ማን ከሚባል አባት ?
“ከአባታችን አባ ፀጋይ ነው የተወለደችው።”
ጥያቄ፤- “እንዴት ከቤተክርስቲያን አባት ተወለደች ? እስኪ እንዴት እንደተፈፀመ ንገሩኝ እስኪ ?”
“ነይ ሻይ አፍይልኝ? ብለው ሻሂ እያፈላሁ ነው ድንገት መጥተው የደፈሩኝ። ከዚያ በኋላ ሲተውኝ ወደ አገሬ ሄድኩኝ፡፡ ከዚያ በኋላ መጥተው “ልጄን አሳድጊልኝ አደራ አሉኝ። አራት ዓመት ሲሞላትም ወደምኖርበት መንደር ኩሃ መጥተው፣ ልጃቸውን ተዓምርን ወደ መቀሌ ወስደው ልብስ ገዝተውና ገንዘብ ሰጥተው ላኳት። “
ጥያቄ፦ ለመሆኑ ተዓምርን ከአባ ፀጋይ ለመውለዶት ሚስጢሩን የሚያውቅ ሌላ ሰው አለን?”
“በርግጥ ብዙ ሰው የሚመስለው ከቀደመው በሕግ አግብቼው ከነበረው ከሁለት ልጆቼ አባት የወለድኳት አድርጎ ነው።”
ጥያቄ ፤ “ ለመሆኑ አባ ፀጋዬ የሚኖሩበትን ገዳም ያውቃሉ?”
“ገዳሙ …ፋት ነው የሚባለው” (የገዳሙ ስም የመጀመሪያዎቹ ሁለት ቃላት በጥራት አይሰሙም፣ አካባቢውን የምታውቁ ሰዎች ሰምታችሁ ብታስታውቁን እናስተካክለዋለን)
“ገዳሙ ፀበል ለመጠመቅ ሔጄ የነበር ሲሆን፣ አንድ አባት ግን ተዓምርን ከአባ ፀጋዬ እንደወለድኳት ሚስጢሩን ያውቃሉ።”
ጥያቄ፤- “አሁን ስማቸው ማን ይባላል?”
“አቡነ እስጢፋኖስ ነው የሚባሉት።”
ጥያቄ ፤ “ለመሆኑ አባቷ መሆኗን ይመሰክራሉ?”
“አዎን እመሰክራለሁ፣ ልጅቷ 18 ዓመት ሞልቷታል። እስከዛሬ አሳድጌያታለሁ። አሁን ግን እርሳቸው ይውሰዷት”

"በበጀት መነፈግ የሚቀየር ማንነት በወልቃይት ጠገዴ የለም!" ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 17/ 2015 ዓ.ም. በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ወፍአርግፍ ከተማ የወረዳው አስተዳደ...
24/07/2023

"በበጀት መነፈግ የሚቀየር ማንነት በወልቃይት ጠገዴ የለም!" ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ

ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 17/ 2015 ዓ.ም. በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ወፍአርግፍ ከተማ የወረዳው አስተዳደር ያሰራው ህንፃ የዞኑ ምክትል አሰትዳዳሪ እና የዞኑ የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሐላፊ ጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በተገኙበት ተመርቋል።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ክብረአብ ስማቸው በዕለቱ እንደተናገሩት ፤ ይህ ህንፃ ምንም በጀት ባልተመደበለት ዞን አመራሩ የውሎ አበሉን በመሰረዝ ነዋሪው ደግሞ ያለውን ሁሉ እየሰጠ በወኔና በእልህ የተሰራ ቤት ነው ያሉ ሲሆን ፤ እንዲሁም በውጭ የሚገኙ የወልቃይት ጠገዴ የዲያስፖራ ማህበረሰብ ለህንፃው መጠናቀቅ ያበረከቱት አስተዋፅኦ የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።

አቶ ገ/እግዚአብሔር ደሴ የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሐላፊ በበኩላቸው ፣ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ሌሎች አርአያ የሚሆን ፅናትን ነታደለ የማይበገር አማራ ነው በዚህም እንኮራለን ብለዋል።

በመጨረሻም የዕለቱ የክብር ዕንግዳ ጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ሌሎች በኢትዮጵያ የሚገኙ ዞኖች ሰኔ ሲመጣ ወር ላይ የተሰጠን በጀት ጨርሰናል ድጎማ ይሰጠን ብለው ያገኛሉ ፤ እኛ ለዚህ አልታደልንም ያሉ ሲሆን ምንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ብናልፍም በክብራችን እና በማንነታችን ለገንዘብ ስንል አንደራደርም ብለዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በበጀት መከልከል ምክንያት ማንነቱን ይቀይራል ማለት የማይታሰብ ነው !

አሳዛኝ ክስተት 😭የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪና ወላጅ አባቷ ከምርቃት ሲመለሱ በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አለፈ!በዛሬው እለት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከሱልልታ ከተማ አቅራቢ በምት...
22/07/2023

አሳዛኝ ክስተት 😭

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪና ወላጅ አባቷ ከምርቃት ሲመለሱ በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አለፈ!

በዛሬው እለት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከሱልልታ ከተማ አቅራቢ በምትገኘው ኮሰ በር አካባቢ ከቀኑ 11:30 በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት አልፏል። ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ፅጌ 16 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሀይሩፍ ተሽከርካሪ 65 መንገደኞችን ካሳፈረ ከህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ጋር ተጋጭቶ አደጋው ደርሷል።

በአደጋው የሀይሩፉ አሽከርካሪን ጨምሮ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን በሱልልታ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት የትራፊክ ደህንነት ቁጥጥር ዋና ሳጅን ደፋሩ ምትኩ ተናግረዋል። ከሟቾቹ መካከል የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪና ወላጅ አባቷ ከምርቃት ሲመለሱ በትራፊክ አደጋው ህይወታቸው ሲያልፍ የተመራቂዋ ታናሽ ወንድም የሆነ የ 16 ዓመት ታዳጊ በአደጋው ክፉኛ ቆስሏል።

በአደጋው ህይወታቸውን ካጡ አምስት ሰዎች በተጨማሪ ሶስት ሰዎች ላይ ከባድ ስድስት ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ቁጥጥር ዋና ሳጅን ደፋሩ ምትኩ ተናግረዋል።

የ20 የክብር ዶክትሬቶች ንጉስ           ******1- ግንቦት 20 ቀን 1946 ዓ.ም ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ2- ግንቦት 25 ቀን 1946 ዓ.ም ከኮሎምቢያ ...
22/07/2023

የ20 የክብር ዶክትሬቶች ንጉስ
******
1- ግንቦት 20 ቀን 1946 ዓ.ም ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
2- ግንቦት 25 ቀን 1946 ዓ.ም ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ
3- ግንቦት 28 ቀን 1946 ዓ.ም ከሞንትሪያል ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክተሬት
4- ግንቦት 30 ቀን 1946 ዓ.ም ከሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
5- ግንቦት 1946 ዓ.ም ከመክጊል ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
6- ሐምሌ 16 ቀን 1946 ዓ.ም ከኬምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
7- ሐምሌ 29 ቀን 1946 ዓ.ም ከአቴና ብሔራዊና ካፓዲስትሪን ዩኒቨርሲቲ በፍልስፍና የክብር ዶክተሬት ድግሪ
8- 1946 ዓ.ም አትላንታ ጆርጂያ ከሚገኘው ሞርሐውስ ኮሌጅ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
9- ጥቅምት 10 ቀን 1947 ዓ.ም ከኢክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
10- ከቦን ዩኒቨርሲቲ በእርሻ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
11- ሕዳር 4 ቀን 19 49 ዓ.ም ከባናራስ ሂንዱ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ጽሑፍ ዶክተሬት ድግሪ
12- ሐምሌ 5 ቀን 1951 ዓ.ም ከሞስኮ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
13- ሐምሌ 8 ቀን 1951 ዓ.ም ከፕራግ ከቻርልስ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የዶክተሬት ድግሪ
14- ህዳር 27 ቀን 1952 ዓም ከላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
15- መስከረም 22 ቀን 1956 ዓ.ም ከጆርጅ ታውን ዩኒቨርሲቲ በሥነ-ጽሑፍ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
16- መስከረም 18 ቀን 1957 ዓ.ም ከሩማኒያ ከቡካሬስት ዩኒቨርሲቲ የሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
17- መስከረም 30 ቀን 1959 ዓ.ም ከሊባኖስ ዩኒቨርሲቲ የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ቻርልስ ሄሉ ባሉበት ክብር ዶክትሬት
18- ሚያዚያ 24 ቀን 1960 ዓ.ም ከታይላንድ ከተማስት ዩኒቨርሲቲ የህግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
19- ግንቦት 9 ቀን 1960 ዓም ከምዕራብ አውስትራሊያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የክብር ዶክተሬት ድግሪ
20- ግንቦት 13 ቀን 1960 ዓም ከደቡብ ኮሪያ ዩኒቨርሲቲ የህግ ዶክሬት ድግሪ
***********

በአፍሪካ ብቸኛው ተወዳዳሪያቸው፣ ኔልሰን ማንዴላ ናቸው። አልበርት ኤነስታይን በአጠቃላይ 17 የክብር ዶክትሬቶች ያገኘ ሲሆን፣ ከፍተኛው ቁጥር 32 በዴቪድ አቴንበርግ የተያዘ ነው።

Address

Woldia

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yeju fortune posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share