Wollo herald

Wollo herald We speak what we see, we testify what we hear!

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በ32 አባል አገሮች ሲመሰረት የድርጅቱ የቃል-ኪዳን ሰነድ (ቻርተር) በአማርኛም ጭምር ተዘጋጅቶ መሪዎቹ የፈረሙበት መሆኑን ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን?
14/02/2025

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በ32 አባል አገሮች ሲመሰረት የድርጅቱ የቃል-ኪዳን ሰነድ (ቻርተር) በአማርኛም ጭምር ተዘጋጅቶ መሪዎቹ የፈረሙበት መሆኑን ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን?

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( ህ.ወ.ሓ.ት) በምንም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ አንዳይሣተፍ  ታገደ፡፡ህወሓት ን ለሦስት ወራት በምንም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ አንዳይሣተ...
13/02/2025

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( ህ.ወ.ሓ.ት) በምንም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ አንዳይሣተፍ ታገደ፡፡

ህወሓት ን ለሦስት ወራት በምንም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ አንዳይሣተፍ ያገደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው፡፡

የቫይረሱ የስርጭት መጠን ቢቀንስም በዓመት ከሰባት ሺህ በላይ ሰዎች በኤች አይቪ ይያዛሉ ***********************ወሎ ሔራልድ(ደሴ)የቫይረሱ የስርጭት መጠን እየቀነሰ ቢመጣም በዓመ...
13/02/2025

የቫይረሱ የስርጭት መጠን ቢቀንስም በዓመት ከሰባት ሺህ በላይ ሰዎች በኤች አይቪ ይያዛሉ
***********************
ወሎ ሔራልድ(ደሴ)

የቫይረሱ የስርጭት መጠን እየቀነሰ ቢመጣም በዓመት ከሰባት ሺህ በላይ ሰዎች በኤች አይቪ እንደሚያዙ ተገለፀ።

አለም አቀፍ የኮንዶም ቀን "ኮንዶምን ይጠቀሙ" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።

በጤና ሚኒስቴር የኤች አይቪ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈጻሚ ፍቃዱ ያደታ እንደገለጹት፤ አዲስ ከመያዝ ምጣኔ 13 በመቶ የሚሆኑት ለተለያዩ ማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ሴቶች መሆናቸዉን ገልጸዋል።

የአለም አቀፍ የኮንዶም ቀን ሲከበርም ለኤች አይቪ ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰብ ክፍሎች ስለኮንዶም አጠቃቀም ግንዛቤ በመፍጠር ይሆናልም ብለዋል።

ኤኤችኤፍ ኢትዮጵያ ማናጀር ቶሎሳ ወላና በበኩላቸዉ በአለማችን በየቀኑ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በአባላዘር በሽታ እንደሚያዙና ኮንዶምን በመጠቀም መከላከል እንደሚቻል ገልጸዋል። የኮንዶም ስርጭት ጉዳይም ትኩረት ሊሰጠዉ የሚገባዉ መሆኑ ገልጸዋል።

አንዲት በግ በአንዴ አምስት ግልገሎች ወለደች በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ወርቅ ከተማ አንዲት በግ 5 ግልገሎችን በአንዴ መውለዷን የእናርጅ እናውጋ ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ...
24/01/2025

አንዲት በግ በአንዴ አምስት ግልገሎች ወለደች

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ወርቅ ከተማ አንዲት በግ 5 ግልገሎችን በአንዴ መውለዷን የእናርጅ እናውጋ ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ።በጓ ከዚህ በፊትም በአንድ ጊዜ ሶስት እና አራት ግልገሎችን ወልዳ እንደነበር ከባለንብረቱ መስማታቸውን የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ማናለ ዋልተንጉስ ተናግረዋል።
የእናርጅ እናውጋ ወረዳ የእንስሳት በሽታ አሰሳ ቅኝትና ቁጥጥር ሐኪም ዶ/ር አዕምሮ አወቀ እንደተናገሩት ከሆነ ደርጊቱ የሚከሠተው በአንድ ጊዜ ማህፀን ዉስጥ ያሉ 5 እንቁላሎች ከ5 ወንድ የዘር ፍሬዎች ጋር ሲገናኙ ነው ብለዋል!!

አሳዛኝ ዜና!በሰሜን ወሎ ዞን በዳውንት ወረዳ ኩርባ ከተማ መነሻውን ያደረገ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ የ25 ስዎች ህይወት ማለፋን ተገለፀ። በዳውንት ወረዳ ኩርባ ...
23/01/2025

አሳዛኝ ዜና!

በሰሜን ወሎ ዞን በዳውንት ወረዳ ኩርባ ከተማ መነሻውን ያደረገ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ የ25 ስዎች ህይወት ማለፋን ተገለፀ።

በዳውንት ወረዳ ኩርባ ከተማ መነሻውን ያደረገ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ የ25 ስዎች ህይወት ማለፋን ከአከባቢው ፖሊስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በ80 ዓመት አዛውንት ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በእስራት እንድቀጣ ተወሰነ በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ በ 80 ዓመት አዛውንት ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመ...
22/01/2025

በ80 ዓመት አዛውንት ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በእስራት እንድቀጣ ተወሰነ

በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ በ 80 ዓመት አዛውንት ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በ 10 ዓመት ፅኑ እስራት እንድቀጣ ፍርድቤቱ ወስኗል ።

ወንጀሉ የተፈፀመው ህዳር 5/2017 ዓ.ም በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ ሚችሌ ሆለና አከባቢ ስሆን ተከሳሽ ወጣት ቶሎሳ ዘውዴ የተባለው ግለሰብ ከምሽቱ 6 ሰዓት ላይ የ 80 ዓመት አዛውንት ብቻቸውን ሚኖሩበትን መኖሪያ ቤት ሰብሮ በመግባት ድርግቱን መፈፀሙን በክሱ መዝገብ ላይ ተጠቅሷል ።

የወረዳ ፖሊስ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አዉሎ ወንጀሉ መፈፀሙን የሚያስረዱ የሰውና የሠነድ ማስረጃዎችን አደራጅቶ ለዐቃቤ ህግ አቅርቧል ።

ዐቃቤ ህግ ፣ ተከሳሹ አዛውንቷ በቤቷ ለብቻ እንደምትኖር አውቀው ቤት ሰብሮ በመግባት መከላከል በማትችልበት ሁኔታ ድርጊቱን እንደፈፀመ የሚያስረዱ ማስረጃዎች አስደግፎ ለዲላ ዙሪያ ወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክሱን አቅርቧል።

ዐቃቤ ህግ ያቀረበውን ማስረጃ የተመለከተው የዲላ ዙሪያ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት ተከሳሽ ወጣት ቶሎሳ ዘውዴ የተባለው ግለሰብ የፈፀመውን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ድርጊት በምስክር እና በህክምና ማስረጃ በማረጋገጥ ጥር 14 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሹ በ 10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድቤቱ ወስኗል።

በ  #የመን ባህር ላይ ጀልባ ተገልብጦ የ20  #ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ህይወት ማለፉን የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ገለጸባለፈው ሳምንት መገባደጃ በየመን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ ላይ በደ...
22/01/2025

በ #የመን ባህር ላይ ጀልባ ተገልብጦ የ20 #ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ህይወት ማለፉን የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ገለጸ

ባለፈው ሳምንት መገባደጃ በየመን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ ላይ በደረሰ የጀልባ በመገልበጥ አደጋ 9 ሴቶች እና 11 ወንዶች ጨምሮ 20 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መሞታቸውን ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት አስታወቀ።

አደጋው የተከሰተው ቅዳሜ ምሽት በጣይዝ አስተዳደር አል-ሀጃጃህ አቅራቢያ ሲሆን በሕይወት የተረፉ ሰዎች ወደ ባህር ዳርቻ ለመድረስ እንደቻሉ ድርጅቱ ትናንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ጀልባው 35 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከየመን ካፒቴን እና ረዳት ጋር አሳፍሮ ከ #ጅቡቲ ሀማርታ አካባቢ በመነሳት "በጠንካራ ወቅታዊ ነፋስ መካከል" ሲጓዝ እንደነበርም ድርጅቱ ገልጿል። የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በመን ተልዕኮ ኃላፊ የሆኑት አብዱስታቶር ኤሶቭ ክስተቱን "ስደተኞች የሚገጥሟቸውን አሳዛኝ ሁኔታዎች የሚያስታውስ" በማለት የገለጹ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ "የኢ-መደበኛን ፍልሰት ዋና መንስኤዎች" እንዲፈታ እና የስደተኞችን ክብር እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

ከወራት በፊት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ከ #የመን የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ ተገልብጣ ቢያንስ 38 ሰዎች መሞታቸው እና ሌሎች 100 ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁ ይታወሳል።

በተጨማሪም ባሳለፍነው አመት ሚያዚያ ወር 77 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሳፍራ ከየመን ወደ ጅቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ በደረሰባት የመገልበጥ አደጋ 21 ሰዎች ሞተዋል።

ዘጠኝ ህፃናትን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ።በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ የቆቦ ከተማ ኗሪ የሆነው ወጣት ፈንታው አድሴ የተባለ ግለሰብ እድሜያቸው ከ5 እስከ 9 አመት...
11/01/2025

ዘጠኝ ህፃናትን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ።

በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ የቆቦ ከተማ ኗሪ የሆነው ወጣት ፈንታው አድሴ የተባለ ግለሰብ እድሜያቸው ከ5 እስከ 9 አመት የሚሆኑ ዘጠኝ ህፃናትን በመድፈር ወንጀል ተከሶ በ25 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን ራያ ቆቦ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሎ የቆቦ ከተማ አስ/ር ፖሊስ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ክፍል ምርመራውን በሰዉና በህክምና ማስረጃ በማጠናከር መዝገቡን ለራያ ቆቦ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት ልኳል።

መዝገቡ የደረሰው የወረዳው ፍርድ ቤትም ጥር 1 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን ያርማል እሱንም ሌሎቹንም ያስተምራል ያለዉን የ25 ዓመት ፅኑ እስራት እና የ10,000 ብር የገንዘብ መቀጮ ወስኖበታል።

በፍርድ ሂደቱ አስተያየታቸዉን የሰጡት የተጎጅ ቤተሰቦችም ዉሳኔዉ ማንኛውም ሰዉ ወንጀል ፈፅሞ በመሰወር ከጥፋት ማምለጥ እንደማይችል የተረጋገጠበትና ከወንጀል ድርጊት መታቀብ እንደሚገባዉ የሚያስተምር ፍርድ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።

በሰሜን ወሎ ዞን በ11 ቀበሌዎች ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሰብል ክምር በከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ወደመበ  #አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ 11 ቀበሌዎች ጥር 1/2017 ...
10/01/2025

በሰሜን ወሎ ዞን በ11 ቀበሌዎች ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሰብል ክምር በከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ወደመ

በ #አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በዋድላ ወረዳ 11 ቀበሌዎች ጥር 1/2017 ዓ.ም በደረሰው “ምክንያቱ ባልታወቀ” የእሳት ቃጠሎ የ154 አርሶ አደሮች የሰብል ክምር መቃጠሉ ተገልጿል፡፡

የዋድላ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሙሉየ ረታ 4 ሺህ 560 ኩንታል የሚኾን 152 ክምር ላይ የደረሰው ቃጠሎ ጉዳት ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት ጠቁመዋል፡፡

የዋድላ ወረዳ የአደጋ መከላከል እና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ጽሕፈት ቤት ቡድን መሪ ምትኩ ሞላ በበኩላቸው እስካሁን ባለው መረጃ 770 የሚኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የጉዳቱ ሰለባ መኾናቸው ተዘግቧል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር  ቴዎድሮስ አድሓኖም ገብረ እየሱስ እስራኤል ጥቃት እየፈጸመች በነበረችበት በየመኑ ፣ ሰንዓ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እንደነበሩ ገለጹ❗ በጥቃቱ አንድ የአ...
26/12/2024

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሓኖም ገብረ እየሱስ እስራኤል ጥቃት እየፈጸመች በነበረችበት በየመኑ ፣ ሰንዓ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እንደነበሩ ገለጹ❗

በጥቃቱ አንድ የአውሮፕላኑ ሰራተኛ ተጎድቷል።

"ከሁለት ሰዓታት በፊት፣ ከሰንዓ ለመብረር ወደ አውሮፕላኑ ልንሳፈር ስንል አየር ማረፊያው የአየር ጥቃት ተፈጸመበት" ብለዋል።

"መላኩ ተፈራ የእግዜር ታናሽ ወንድምየዛሬን ማርልኝ ሁለተኛ አልወልድም" የተባለው ተረት መላኩ ተፈራ እጅ ለገቡት ለእኚህ ሰው ሊቀ ትጉሐን በፍርዱ ወጨፎ ነበር። በወቅቱ የፀጥታ ሰዎች እጅ የ...
25/12/2024

"መላኩ ተፈራ የእግዜር ታናሽ ወንድም
የዛሬን ማርልኝ ሁለተኛ አልወልድም"

የተባለው ተረት መላኩ ተፈራ እጅ ለገቡት ለእኚህ ሰው ሊቀ ትጉሐን በፍርዱ ወጨፎ ነበር።
በወቅቱ የፀጥታ ሰዎች እጅ የገቡት የደብረ ታቦሩ ሰው ሊቀ ትጉሐን በፍርዱ በእናታቸው የተገጠመው የ"ልቀቅልኝ" ምኞት ሥነ ቃል ኾኖ ቀረ።

መቀሌ ከተማ በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች የተመደቡ ከንቲባዎች በስራ ገበታ ላይ የሉም ተባለታኅሳስ 09 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች የተመደቡ ...
18/12/2024

መቀሌ ከተማ በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች የተመደቡ ከንቲባዎች በስራ ገበታ ላይ የሉም ተባለ

ታኅሳስ 09 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች የተመደቡ ከንቲባዎች በስራ ገበታ ላይ የሌሉ ሲሆን የከንቲባ ፅህፈት ቤት ታሽጎ በፀጥታ ሃይሎች ጥበቃ ስር እንደሚገኝ ተገልጋዮች መናገራቸው ተገልጿል።

በአስተዳደሩ ዋና በር በቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ተገለግጋዮች ሲገቡ ሲወጡ ይታያሉ ፤ ፍትሻ በሚካሄድበት ቦታ ከተለመደው በተለየ ብዛት ያላቸው የፀጥታ አካላት እንደሚስተዋሉ ተመላክቷል።

ግብፅ የህዳሴውን ግድብ ጉዳይ በተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ለሚመራው አዲሱ የአሜሪካ መንግስት ለማቅረብ እየሰራች መሆኑን አል አረቢያ አል ጃዲድ የተሰኘው ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ ጋዜጣው የግ...
18/12/2024

ግብፅ የህዳሴውን ግድብ ጉዳይ በተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ለሚመራው አዲሱ የአሜሪካ መንግስት ለማቅረብ እየሰራች መሆኑን አል አረቢያ አል ጃዲድ የተሰኘው ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

ጋዜጣው የግብፅ መንግስታዊ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር የቴክኒክ ሰራተኞች ግድቡ በሚያስከትለው ባደረሰው ጉዳት ላይ አዳዲስ መረጃዎችን እንዲያዘጋጁ ታዘዋል፡፡

ከእነዚህ መካከልም ባለፉት አራት አመታት ውስጥ የግብፅ መንግስት ውሀ ለማጣራት በሚል ያወጣውን ወጪ የሚገልፅ እንደሚገኝበት አስረድቷል፡፡ በአጠቃላይ በግድቡ ውሀ ሙሌት የተነሳ በግብፅ ላይ የደረሰውን ጉዳት በዝርዝር የሚተነትን አዲስ መረጃና ሰነድ በማዘጋጀት ለአዲሱ የትራምፕ አስተዳደር ለማቅረብ ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡

በቀጣይነትም ግድቡ በሙሉ አቅሙ ስራ በሚጀመርበት ወቅት በግብፅ ላይ የሚያስከትለውን አደጋ የሚገልፀው ይህ ሰነድ ወደፊት በግድቡ ስራ ላይ ስምምነት ላይ እንዲደረስ የሚል ምክረ ሀሳብ የሚይዝ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ግብፃዊያን ይህንን ሰነድ እያዘጋጁ ባሉበት ወቅት ሱዳንም ተመሳሳይ ሰነድ በማዘጋጀት አብረው ለትራምፕ ለማቅረብ ማቀዳቸውን ጋዜጣው ጨምሮ አስረድቷል፡፡

ትራምፕ በስልጣን ላይ በነበሩት ወቅት በግድቡ ዙሪያ ሶስቱን አገራት ለመሸምገል ጥረት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡ በወቅቱ ውዝግቡን ለመፍታት በሚል አንድ የስምምነት ሰነድ አዘጋጅተው የነበረ ቢሆንም በዚያ ሰነድ ላይ ኢትዮጵያ አልፈርምም ማለቷ ይታወሳል፡፡

የአንድ ሳምንት ልጇን አንቃ የገደለችው እናት በቁጥጥር ስር ዋለች ‼️በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በባስኬቶ ዞን ተጠርጣሪዋ የ14 ዓመት ታዳጊ ስትሆን  በላስካ ከተማ 02 ቀበሌ ልዩ ስሙ ባዳይስ ...
18/12/2024

የአንድ ሳምንት ልጇን አንቃ የገደለችው እናት በቁጥጥር ስር ዋለች ‼️

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በባስኬቶ ዞን ተጠርጣሪዋ የ14 ዓመት ታዳጊ ስትሆን በላስካ ከተማ 02 ቀበሌ ልዩ ስሙ ባዳይስ መንደር ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ የወንጀል ድርጊቱ ተፈፅሟል።

የክስ ዝርዝሩ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ ሰናይት እንዳለ የተባለችዉ ታዳጊ የባስኬቶ ዞን ኗሪ ስትሆን በቁጥጥር ስር ልትዉል የቻለችዉ ልጇን በመግደልና በመጣል ወንጀል ተጠርጥራ መሆኑን የባስኬቶ ዞን ፖሊስ መምርያ አስታውቋል።

ግለሰቧ የመዉለጃ ጊዜዋ ሲቃረብ ከባስኬቶ ወደ ጅንካ በመሄድ ከቀናት በኋላ በጅንካ ሆስፒታል የወለደች ሲሆን የሆስፒታሉ ሰራተኞች ብቻዋን መሆኗን አይተዉ ቤተሰብ የለሽም ወይ በማለት ሲጠይቋት ዘመድ የለኝም የሚል ምላሽ በመስጠቷ ሰራተኞቹ ልዩ ድጋፍና ክትትል ቢያደርጉላትም በሶስተኛዉ ቀን ከሆስፒታሉ በማምለጥ ወደ ባስኬቶ መመለሷ ተገልጿል።

በመቀጠልም ተከሳሽዋ የማሽላ እርሻ ዉስጥ ልጇን አንቃ በመግደልና በመጣል ወደ ትዉልድ ስፍራዋ መመለሷን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

የእርሻዉ ባለቤቶች ለስራ ወደስፍራዉ ሲመጡ የህፃን ልጅ አስክሬን ማግኘታቸዉን ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ፖሊስ አስክሬኑን በማንሳት አስፈላጊዉን ምርመራ በማድረግ ከላስካ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ጋር በመተባበር ስረአተ ቀብር መፈፀሙን ገልጿል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዋን ለመያዝ ባደረገዉ ክትትል በባስኬቶ ዞን ቦክቡጫ ቀበሌ በቁጥጥር ስር አዉሎ በምርመራ እያጣራ መሆኑን ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ ተናግረዋል።

ሚስት ባሏን ደሀ ነህ ብላ በፈታች በማግስቱ ባል  የሚሊዮን ዶላሮች ሎተሪ አሸነፈ❗ሰውዬው ለተወሰነ ጊዜ ሥራ አጥ ነበር እና ሚስቱ በሂደቱ ላይ እምነት መጣል ትዕግስት ስለሌላት ወደ ፊት ለመ...
15/12/2024

ሚስት ባሏን ደሀ ነህ ብላ በፈታች በማግስቱ ባል የሚሊዮን ዶላሮች ሎተሪ አሸነፈ❗
ሰውዬው ለተወሰነ ጊዜ ሥራ አጥ ነበር እና ሚስቱ በሂደቱ ላይ እምነት መጣል ትዕግስት ስለሌላት ወደ ፊት ለመቀጠል ወሰነች። ሆኖም የፍቺ ሰነዶችን ከፈረመ ከአንድ ቀን በኋላ ህይወቱን ሙሉ በሙሉ የሚለዉጠውን ሎተሪ አሸንፏል።

በመንገዳችን ላይገርጂ!
13/12/2024

በመንገዳችን ላይ
ገርጂ!

Address

Woldia
26

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wollo herald posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share